Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
አጥፍቶ ጠፊው አሕመዲን ጀበል
*********************
አጥፍቶ ጠፊ የራሱን ሕይወት በመሠዋት ሌሎችን ለማጥፋት የቆረጠ ሰው ነው፡፡ በዓለም ዙርያ የሚታዩት አጥፍቶ ጠፊዎች ብዙ ጊዜ ፈንጂ በመታጠቅ ሕዝብ ወደ ተሰበሰበበት ቦታ በመሄድ ራሳቸውን የሚያፈነዱ ናቸው፡፡ አሕመዲን ጀበል የተሰኘው ፅንፈኛ ሙስሊም አጥፍቶ ጠፊ ነው፡፡ ነገር ግን እንደ እምነት ወንድሞቹ ፈንጂ በመታጠቅ ሳይሆን ክርስቲያኖችን የሚጎዱና ሰላማዊ ሙስሊሞች ሊነኳቸው የማይፈልጓቸውን አደገኛ እሳቤዎች በመታጠቅ የተሰማራ አጥፍቶ ጠፊ ነው፡፡ አጥፍቶ ጠፊዎች ብዙ ጊዜ ስለ ሃይማኖታቸው ያላቸው ዕቀውቀትና ንቃተ ኅሊናቸው ከበስተጀርባ ሆነው ለተልዕኮ ከሚያሰማሯቸው ወገኖች ያነሰ ሲሆን ከተልዕኮ አቀባዮቻቸው የሚሻሉት በድፍረታቸው ብቻ ነው፡፡ እኔ የዚህን ሰው መጻሕፍት በሙሉ እና በተለያዩ ማሕበራዊ መገናኛዎች ላይ የሚጽፋቸውን ብዙ ጽሑፎቹ በትኩረት አንብቤያለሁ፡፡ ለአንድ መጽሐፉም ምላሽ የሚሆን ጥራዝ አሳትሜያለሁ፡፡ ጽሑፎቹን በማነጻጸር የደረስኩበት ድምዳሜ ቢኖር የአንድ ሰው ሥራ ብቻ ሊሆኑ እንደማይችሉ ነው፡፡ የተወሰኑት መጻሕፍቱና በማሕበራዊ ሚድያ የሚያሰራጫቸው ጽሑፎቹ የረባ የሥነ ጽሑፍ ክህሎት እንደሌለው የሚያሳብቁ፣ ዕውቀትና ብስለት የሚያጥራቸው ሲሆኑ ሌሎች ሥራዎቹ ደግሞ ከፍ ባለ የሥነ ጽሑፍ ደረጃ የተጻፉና በተለይም ታሪክ ጠቀስ ይዘታቸው ልሒቃዊ ቃና ያለው ናቸው፡፡ ለአብነትም ከግብፆች ሙስሊም ብራዘርሑድ ሙዳየ ቃላት የተመዘዙ አገላለፆች የተሰገሰጉበት “ፈርዖን የአምባገነኖች ተምሳሌት” የሚለው መጽሐፉና “ሦስቱ አፄዎች” በሚል ርዕስ የታተመው ጥራዝ ከሌሎች መጻሕፍቱ በብዙ መንገድ የተለዩ ናቸው፡፡ አቶ አሕመዲን በሙስሊሞች ዘንድ የታሪክ ምሑር ተደርጎ የሚሞካሽ ቢሆንም ቋንቋ እንጂ ታሪክ ማጥናቱን የሚያሳይ መረጃ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ በመጻሕፍቱ ውስጥ የሚገኙት አንዳንድ ይዘቶች መረጃዎችን በተባራሪ ከሚያገኝ እርሱን ከመሰለ ሰው የማይጠበቁ በመሆናቸው ያለጥርጥር የዚህ ሰው መጻሕፍት ላልታተሙ መዛግብትም ጭምር ቅርበት ባላቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚገኙ ሙስሊም የታሪክ ሊቃውንት የተጻፉ ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህን መጻሕፍት በዚህ ሰው ስም እያሳተሙ የሚገኙ መረጃዎችን ባልተገባ ሁኔታ ለአክራሪዎች አጀንዳ እንዲውሉ እንዲሁም ተጣምመውና ተሳክረው እንዲቀርቡ እያደረጉ ያሉ ምሑራን ማንነት ሊጣራና እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል፡፡ እነዚህ ወገኖች ካሉበት የኃላፊነት ደረጃ አንፃር ጽሑፎቹን በራሳቸው ስም ማሳተም ተጠያቂ ስለሚያደርጋቸው ነው ለማንኛውም መሥዋዕትነት ራሱን ባዘጋጀው ዕውቀት አጠሩና ደፋሩ አጥፍቶ ጠፊ አማካይነት እያሳተሙ የሚገኙት፡፡ ትክክለኞቹ አገር አፍራሾች እነርሱ ናቸውና አንድ ሊባሉ ይገባል፡፡ አጥፍቶ ጠፊው አሕመዲን ጀበልም የነርሱ መጠቀሚያ ሆኖ አገር እየመረዘ የባሰ ጥፋት ከማስከተሉ በፊት እንደርሱ ላሉት ፅንፈኛና ኅሊና የለሾች ወደተገባው የጸባይ ማረምያ ሊወሰድ ይገባል፡፡

የእኔ ጥያቄ የዚህ ሰው መስለም አለመስለም ዛሬ ላይ ላለነው ለእኛ (ለሙስሊሙ ለክርስቲያኑ) የሚያስገኝልን ፋይዳ ምንድን ነው? በእርሱ መስለም አለመስለም ሰዎች ከገሃነም እሳት ለመዳናቸው ዋስትና ያስገኛሉን? ሰውየው የጀነት በር ነውን? የዚህን ሰው ታሪክ ዛሬ ላይ የሚያነሱ የሚጥሉትና አብዝተው የሚያጮሁት እነማን ናቸው? ለምን? እንደሚባለው ነጃሽ (ንጉስ አስሀማ ወይም አርማህ) ሰልሞ ነበርን? የእስልምና የታሪክ ድርሳናት ለዚህ መልስ የሚሆን ይኖራቸው ይሆን? በቅርብ ቀን ዝርዝሩን ይጠብቁኝ!!!!
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ሰላም ሰላም ውድ ጓደኞቼ ሁላችሁም! ሰሞኑን "የመስጂዶች ታሪክ በአዲስ አበባ" የተሰኘ መጽሐፍ አገኘሁና ማንበብ ጀመርኩ እላችኋለሁ፡፡ እናም እናንተዬ ገጽ 17 ላይ ስደርስ እንዲህ የሚል ርዕስ አነበብኩ "መስጅድና ሙስሊሞች"፡፡ እስከ ገጽ 19 ድረስ ሐሳቡ ይቀጥላል፡፡ እናም ያንን ያነበብኩትን ለግንዛቤ ያክል ስለሚጠቅማችሁ ላስነብባችሁ ወደድኩ፡፡ አንብባችሁ ስትጨርሱ እነዚህን ጥያቄዎች ተመልሳችሁ ብትመልሱልኝ ደስ ይለኛል፡-
1. መስጂድ ምንድን ነው ትላላችሁ? በራስህ/በራስሽ አገላለጽ ጻፍ
2. እስልምና ምንድን ነው ትላለህ?
3. በዚህ መረዳት ሙስሊሞችን ምን ትላቼዋለህ?
1. መስጂድ ምንድን ነው ትላላችሁ? በራስህ/በራስሽ አገላለጽ ጻፍ
2. እስልምና ምንድን ነው ትላለህ?
3. በዚህ መረዳት ሙስሊሞችን ምን ትላቼዋለህ?
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ያልሰማህ ስማ የሰማህ ላልሰማው አሰማ 'ነጃሽ' እንዳልሰለመ የእስልምና የታሪክ ምንጮችና ቁርአን ማረጋገጫ ሰጥተዋል!
ክፍል አንድ፡-
ከሰሞኑ ነጃሽ ሰለመ አልሰለመም የሚለው ሰጥ አገባ እንደገና አገርሽቷል፡፡ በቅርብ እንኳን ሙስሊሞች በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት "ሀገሬ" በሚለው ቲያትር 'ነጃሽ'ን (ንጉስ 'አስሀማን' ወይም 'አርማህ'ን) ዘክረዋል፡፡ መነባንቡ፣ ግጥሙ ብዙ ነው፡፡ ከዛ መለስ ብለን ትንሽ ዐረፍንና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት "አንዳንድ አክራሪ ሙስሊሞች እንደሚሉት ንጉሥ አርማህ አልሰለመም" በማለቱ የሃሩን ቲዩብ አዘጋጅ ሁሉም ሙስሊሞች አክራሪዎች ናቸው እንዳለ አድርጎ በመነዛቱ፣ አድማጮቹና ስመጥር የሆኑ የእስልምናው ፕሮፌሰርም ይህችኑ በማጮኻቸው በአገሪቱ አቧራ ተነስቶ ሰንብቷዋል፡፡ ጎራ ለይቶ አንተ እሱ መባባሉ ገና አልበረደም፡፡
የእኔ ጥያቄ የዚህ ሰው መስለም አለመስለም ዛሬ ላይ ላለነው ለእኛ (ለሙስሊሙና ለክርስቲያኑ ማለቴ ነው) የሚያስገኝልን ፋይዳ ምንድን ነው? በእርሱ መስለም አለመስለም ሰዎች ከገሃነም እሳት ለመዳናቸው ዋስትና ያገኛሉን? ሰውየው የጀነት በር ነውን? የዚህን ሰው ታሪክ ዛሬ ላይ የሚያነሱ የሚጥሉትና አብዝተው የሚያጮኹት እነማን ናቸው? ለምን? እንደሚባለው ነጃሽ (ንጉሥ አስሀማ ወይም አርማህ) ሰልሞ ነበርን? የእስልምና የታሪክ ድርሳናት ለዚህ መልስ የሚሆን ይኖራቸው ይሆን?
የክርክሩ አስኳል፡-
ሰጥ አገባው ሰውዬው የጀነት በር ስለሆነ አይደለም፡፡ ታዲያ ምክንያቱ ምንድን ነው ካላችሁ "የታሪክ ሽሚያ"፡፡ ከታሪኩ ጀርባ ብዙ የሚመዘዙ ወዳልተዘነጋው ሕልም አስወንጫፊ ጉዳዮች አሉበት፡፡ ያ ባይሆን ኖሮ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የኢስላምናንና የኢትዮጵያን ግንኙነት እንዲሁም ስለ ነጃሽ መስለም የተረከበትን መጽሐፍ በ"ጭቆና" አይገልጸውም ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ግን አሁንም ሩቅ ዘመን ላይ ያለ ያላደገ አስተሳሰብ እንዳለ አመላካች ነው፡፡ ላይመስል ይችላል፡፡
የአልሰለመም ተሟጋቾች፡-
የነጃሽን መስለም የማይቀበሉት ወገኖች የውስጥና የውጭ የታሪክ ሊቃውንትን ምስክርነት በማጣቀስ እንዲህ በማለት መከራከሪያቸውን ያቀርባሉ፡-
አገራችን የ3000 ዓመት ታሪክ ያላት አገር ናት፡፡ ከዛም በጥቂቱ ገለጥ ስናደርግ ከአራተኛው ምዕተ ዓመት እስከ አንድ ሽ ዓመተ ምሕረት ድረስ በኢትዮጵያ የነገሡ ክርስቲያን ነገሥታት ስም ዝርዝር አለን፡፡ ታዲያ በዝርዝሩ ውስጥ "አል-ነጋሽ" የሚባል ስም ያለው ንጉሥ አልተጠቀሰም የለም፡፡ የውጭ የታሪክ ሊቃውንትም ጭምር እንዲህ የሚባል ንጉሥ ነግሦ እንደነበር አልጻፉም፡፡
የሰለመ ንኑሥ ቢኖር ኖሮ፡-
• ታሪኩ በግልጽ ተመዝግቦ ይገኝ ነበር፡፡ በጣም አውዳሚ ታሪክ ያላቸው የአሕመድ ግራኝ እና የዩዲት ጉዲት ታሪክ ተመዝግቦ እንደሚገኘው የእርሱም ይጻፍ ነበር፡፡ ነገር ግን ያ አልሆነም፡፡
• ንጉሡ ሰልሞ ቢሆን ኖሮ፤ በአሕመድ ግራኝና በዩዲት ጊዜ ተነሥቶ እንደነበረው ዐይነት ብጥብጥ ይነሣ ነበር፡፡ ይህም የታሪክ ክስተት ስለሆነ ይመዘገብም ነበር፤ ነገር ግን የለም፡፡
• የክርስቲያኑ ነገሥታት ታሪክ ማብቂያው እዛ ላይ ይሆን ነበር፡፡ ምክንያቱም ቀዳሚው ከሰለመ ቀጣዩ ንጉሥም እንደዛው ሙስሊም ስለሚሆን፤
• እንደ "ነጋሽ" ተቆጥሮ ስሙ የሚጠራው ንጉሥ የነገሠበት ዘመን እና ሙስሊም ስደተኞች የመጡበት ዘመን የሚገናኝ አለመሆኑ ሌላው ጉዳይ ነው፡፡
• አንዳንድ የታሪክ ሊቃውንት በታሪክ ድርሳኖቻቸው የሙስሊም ስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ሲጠቅሱ ንጉሥ ስለመስለሙ ግን አልጠቀሱም፤ በማለት ሙግታቼውን ያጠናክራሉ፡፡
"ነጃሽ" ሰልሟል ለዚህ መረጃ አለን የሚሉት ሙስሊሞችም፡-
"ታሪክ አለን" ለሚለው ከ7ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ላለው ታሪክ "ኢትዮጵያዊ ምንጮች" (የቤተ መንግሥት ዜና መዋዕሎችና የቤተ ክህነት ጽሑፋት) በታሪክ መረጃ ምንጭነት እንደማይቀበሏቸው የተለያዩ የታሪክ ሊቃውንት ይመሰክራሉ፡፡ ለምሳሌ ፕ/ሮ በጅ፣ ክቡር አቶ ተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ ፕ/ሮ ስርግው ሐብለ ሥላሴ፣ ደ/ር ላጲሶ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ መጻፍ የተጀመረው ዘግይቶ 14ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ታሪካችሁ ተቀባይነት የለውም የሚል ሙግት ያቀርባሉ፤
ሂጅራን የተመለከተው የዛ ዘመን ትክክለኛው የኢትዮጵያ ታሪክ ተመዝግቦ የሚገኘው በአረብ የታሪክ ሊቃውንት ነው፡፡ ለምሳሌ ኢብን ሒሻምና አት-ጦበሪን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለእነዚህ የአረብ የታሪክ ጸሐፍት ተአማኒነት ምስክርነታቸውን እነዚሁ ዕውቅ የታሪክ ሊቃውንት ሰጥተዋል፡፡ ታዲያ እነዚህ የእስልምና የታሪክ ጸሐፍት ነጃሽ በሙስሊም ስደተኞቹ እጅ እስልምናን ስለመቀበሉ ጽፈዋል፡፡ አስረጅ ይሆኑ ዘንድ፡-
• ነጃሽና ሙስሊም ስደተኞች በተለያየ ጊዜ ያደረጓቸው ቃለምልልሶች ተዘግበዋል
• ነቢዩ ሙሐመድና ነጃሽ የተለዋወጧቸው ደብዳቤዎች ተዘግበዋል
• አላህ በቁርአን ይህንን ማረጋገጡ የሚሉትን እንደ አስረጅ ያቀርባሉ
እውን እንደተባለው የእስልምና የታሪክ ጸሐፍት ከ"ኢትዮጵያ ምንጮች" ይልቅ ለታሪካችን የተሻለ ታማኝነት አላቸውን? እነዚህ የታሪክ ሊቃውንት የተባሉት ምሁራን የእስልምና የታሪክ ምንጮችን በምን ሚዛን ገምግመው ይህንን ማዕረግ አሸከሟቸው? እስከ ምን ድረስና በምን መንገድ መረመሯቸውና ለተአማኒነታቸው የምስክር ቃላቸውን ሊሰጡ ቻሉ? ስለ እስልምናስ ምን ያክል ያውቃሉ? ምሁርነት በዚህ ዘመን ሚዛኑ እየቀለለ መጥቷል፤ እነዚህንም ወላፈኑ ሊነካቸው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምክንያቱም የማያውቋቸውን የታሪክ ድርሳናት ስላነበቧቸው ብቻ ያልተገባ ማዕረግ ሰጥተው ተገኝተዋልና፡፡ ይህን ማስረጃዎቼ የሚያስረዱልኝ ቢሆንም፤ የእስልምና የታሪክ ድርሳናት በሐሰተኛ ትርክቶች የተጨናነቁና ተአማኒነት የሌላቸው የታሪክ ምንጮች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡ በተለይም ከሙስሊም ስደተኞችና ከነጃሽ ጋር በተያያዘ የቀረቡት የታሪክ ክስተቶች ልብ የወለዳቸው ታሪኮች ናቸው፡፡ ስለዚህ እንዲህ እላለሁ "ያልሰማህ ስማ የሰማህ ላልሰማው አሰማ 'ነጃሽ' እንዳልሰለመ የእስልምና የታሪክ ምንጮችና ቁርአን አረጋግጠዋል"፡፡ ይህንን ለማሳየት የምከተለው አካሄድ የሙስሊም ታሪክ ጸሐፍቱንና የቁርአንን መንገድ ይሆናል ተከታተሉኝ፡-
ይቀጥላል…
ሳሂህ ኢማን ነኝ
ቸር ይግጠመን!

❤1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
የአቡበክር ቁርአንን የማሰባሰብ ሂደት ከጥርጣሬ የፀዳ ነበርን?
ሙስሊም ወገኖች ለቁርአን በትክክል ተጠብቆ መቆየት እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ሌላው ነጥብ በኸሊፋ አቡበክር ዘመን በአንድ ጥራዝ መሰብሰቡን ነው፡፡ ቁርአንን በቃላቸው ያጠኑ ብዙ ሰዎች በየማማ ጦርነት (ሐርበ ሪዳ) በማለቃቸው ምክያት በስጋትና በችኮላ የተፈፀመውን ይህንን የማሰባሰብ ሒደት ፍፁም ከጥርጣሬ የጸዳና ቁርአን ላይ ለውጥ አለመደረጉን ባረጋገጠ መንገድ የተሠራ በማስመሰል ይናገራሉ፡፡ እውነቱ ግን ከዚያ እጅግ የራቀ ነው፡፡ የአቡበክርን የማሰባሰብ ሒደት በከፍተኛ ጥርጣሬ እንድንመለከት የሚያደርጉ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ተከታዩ ጽሑፍ ለሐሰን ታጁ መጽሐፍ ከሰጠነው ምላሽ ላይ የተወሰደ ነው፡፡
ሐሰን ታጁ ቁርአን በነቢዩ ዘመን በአንድ ጥራዝ ለምን እንዳልተሰበሰበ ሲገልፁ “በየጊዜው በመውረድ ሂደት ላይ ስለነበርና ጽሑፉ ስላልተጠናቀቀ ነው” ይላሉ (ገፅ 19)፡፡
ቀደም ሲል እንደገለፅነው የቁርአን ሁለት ሦስተኛው በመሐመድ ዘመን በጽሑፍ መጠበቁን የሚያመለክት የረባ ማስረጃ የለም፡፡ ሆኖም ቁርአን በመሐመድ ዘመን በአንድ ጥራዝ ያለመሰብሰቡ ምክንያቱ ሐሰን ታጁ የጠቀሱት ብቻ አይደለም፡፡ አል-ሱዩጢ የተሰኙ ሙስሊም ሊቅ እንዲህ ይላሉ፡-
“ነቢዩ መሐመድ የተወሰኑ ሕግጋትንና ንባባትን የመሻር ሐሳብ ስለነበራቸው ቁርአንን በአንድ ጥራዝ አልሰበሰቡትም፡፡”[1]
ቁርአንን ለመጀመርያ ጊዜ በአንድ ጥራዝ እንዲሰበሰብ ያደረጉት ኸሊፋ አቡበክር ሲዲቅ ነበሩ፡፡ አቶ ሐሰን ቁርአን በአቡበክር ዘመን የተሰበሰበበትን ሂደት ሲገልፁ፡- “ሐርበ ሪዳ” በተሰኘ የአመፅ ጦርነት ምክንያት የማማ በተባለ ቦታ በርካታ የነቢዩ ባልንጀሮች የሞቱበት ሁኔታ መከሰቱን፤ ከነዚህ መካከል በቁርአን ሊቅነታቸው የታወቁ 70 ያህል ሶሐቦች መሞታቸውን፤ የቁርአን አዋቂዎች ሞተው ያለቁ እንደሆን ቁርአንን ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ሂደት ሊቋረጥ መቻሉ ዑመርን እንዳሰጋው፤ ስለዚህ ቁርአን የተጻፈባቸው ቁሳቁሶች ሁሉ በኸሊፋው ኃላፊነት ስር እንዲሰበሰቡ ሐሳብ እንዳቀረበ፤ በዚህም መሠረት የማሰባሰቡን ሂደት “ምግባረ ሰናይ” የነበረው ዘይድ በበላይነት እንዲመራው እንደተመረጠና ይህንኑ እንዳከናወነ አትተዋል (ገፅ 20-22)፡፡ ነገር ግን በማሰባሰቡ ሂደት ወቅት የነበረውን አጨቃጫቂ ሁኔታና ሸፍጥ ሳይገልፁ አልፈዋል፡፡ በአቡበክር ዘመን የተደረገው ቁርአንን የማሰባሰብ ሂደት አጠራጣሪ የሚሆንባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ፡-
1. የመጀመርያው መታወቅ ያለበት ጉዳይ ቢኖር ስለዚህ የማሰባሰብ ሂደት የሚናገሩት ድርሳናት በወቅቱ የተጻፉ ሳይሆኑ ነገሩ ከተከሰተ ከክፍለ ዘመናት በኋላ የተጻፉ መሆናቸው ነው፡፡ ዘጋቢዎቹ ምንም ያህል ቅኖችና ሐቀኞች ቢሆኑ ታሪኩ በጊዜ ርዝመት መበረዝ መቻሉ የሚያከራክር አይደለም፡፡ በዚህ ሂደት ወቅት አስደንጋጭ የሆኑ ጉዳዮች ሳይዘገቡ የመታለፋቸው ሁኔታ እጅግ ሰፊ ነው፡፡ ታሪኩ መቀየሩን ከሚያሳዩ ማስረጃዎች መካከል አንዱ በአቡበክር ዘመን ቁርአን በወረቀት ላይ እንደተጻፈ መነገሩ ነው፡፡ ነገር ግን ሐቀኛ በሆኑት የታሪክ መዛግብት መሠረት ሙስሊሞች ፐፓይረስ የተሰኘውን ከደንገል የሚዘጋጅ መጻፍያ መጠቀም የጀመሩት በዑመር ዘመን ግብፅን ከወረሩ በኋላ ነበር፡፡ ወረቀት በሙስሊሞች ጥቅም ላይ የዋለው ደግሞ አቡበክር ካለፉ ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በኋላ ሰመርቃንድ በተሰኘ ቦታ ነበር፡፡ በባግዳድ ወረቀትን ማምረት የተጀመረው በስምንተኛው ክፍለ ዘመን መገባደኛ በቻይናውያን እርዳታ ነበር፡፡[2]
2. ቁርአንን በአንድ ጥራዝ የማሰባሰብ ሂደት ለመጀመርያ ጊዜ በዘይድ አማካይነት እንደተከናወነ በእስላማዊ ድርሳናት ውስጥ ቢነገርም[3]ይህንን የሚጣረስ ሌላ ዘገባ አለ፡-
“ኢብን ቡራይዳህ እንዳስተላለፉት፤ ለመጀመርያ ጊዜ ቁርአንን በሙሳሂፍ (ጥራዝ) የሰበሰበው የአቡ ሁዛይፋህ ባርያ የነበረውና ነፃ የወጣው ሰሊም ነበር፡፡”[4]
(ሰሊም ቁርአንን እንዲያስተምሩ በነቢዩ መሐመድ ሥልጣን ከተሰጣቸው አራት ሰዎች መካከል አንዱ ነበር፡፡)[5]
እንግዲህ ሙስሊም ምሑራን ሁለት እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ዘገባዎችን ተጋፍጠዋል፡፡ ከሁለቱ አንዱ የግድ ውሸት መሆን አለበት፡፡ ቁርአንን በአንድ ጥራዝ የሰበሰበው የመጀመርያው ሰው ማነው? የሚለውን ቀላል ጥያቄ ከጥርጣሬ በጸዳ ሁኔታ መመለስ ያልቻሉ ድርሳናት ሌሎች ትርክቶቻቸው አስተማማኝ ሊሆኑ አይችሉም፡፡
3. በመሐመድ ዘመን በቁርአን ውስጥ የተካተቱ ነገር ግን ዘይድ ያስወገዳቸው ክፍሎች ነበሩ፡፡ እስላማዊ ድርሳናት እንዲህ ሲሉ ይናዘዛሉ፡-
“አብዱላህ ቢን አባስ እንዳስተላለፉት፤ ኡመር ቢን ኸጧብ በአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ምስባክ ላይ ተቀምጠው እንዲህ አሉ፡- ‹‹አላህ መሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) በእውነት ላካቸው፤ መጽሐፍንም አወረደላቸው፤ በእርሳቸው ላይ በተወረደው ውስጥ በድንጋይ የመውገር አንቀፅ ነበር፡፡ አነብንበነዋል፣ በትውስታችን ውስጥ መዝግበነዋል እንዲሁም ተረድተነዋል፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በድንጋይ ወግሮ የመግደልን ቅጣት ይተገብሩ ነበር፤ ከእርሳቸው በኋላ እኛም ተመሳሳይ ነገር እንፈፅም ነበር፡፡ በጊዜ ሂደት ሰዎች ‹በአላህ መጽሐፍ ውስጥ የውግረትን ሕግ አላገኘንም› በማለት በአላህ የተደነገገውን ይህንን ድንጋጌ ችላ እንዳይሉ እፈራለሁ፡፡ ዝሙትን የሚፈፅሙ ባለትዳር ወንዶችና ሴቶች በማስረጃ ከተረጋገጠ፣ እርግዝና ከተፈጠረ ወይም ከተናዘዙ እንዲወገሩ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ የተቀመጠ ግዴታ ነው፡፡››”[6]
በአንድ ዘገባ መሠረት ዑመር ይህንን አንቀፅ በዘይድ ወደሚመራው ኮሚቴ ባመጣ ጊዜ ዘይድ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም፤ የሰጠው ምክንያት ደግሞ ከዑመር ውጪ ሌላ ምስክር ስላላገኘ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡[7] ነገር ግን ይህ አንቀፅ የቁርአን አካል እንደነበር የመሐመድ ሚስት አይሻ መመስከሯ ተነግሯል፡፡[8] ዘይድ ቁርአንን ሲሰበስብ በጽሑፍ ሊገኝ ያልቻለው በፍየል ስለተበላ መሆኑም ተዘግቧል፡፡[9]
ይህ አንቀፅ በመሐመድ ዘመን የቁርአን አካል እንደነበር በመናገራቸው ዑመርና አይሻ ቅጥፈት ፈጽመው ይሆን? ከአራቱ ኸሊፋዎች መካከል አንዱና የመሐመድ የቅርብ ወዳጅ የነበረው ዑመር እንዲሁም የነቢዩ ሚስት አይሻ የሰጡት ምስክርነት ካልታመነ የማን ምስክርነት ሊታመን ነው? በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሌሎች ብዙ የቁርአን ክፍሎች አለመካተታቸውን እንዴት እርግጠኛ መሆን ይቻላል?
4. በየማማ በተደረገው ጦርነት ወቅት ከሞቱት ሰዎች ጋር የጠፉ የቁርአን አናቅፅ እንደነበሩ እስላማዊ ትውፊቶች ይመሰክራሉ፡፡ ይህ ማለት ሁሉም የቁርአን ክፍሎች በሁሉም አነብናቢዎች እኩል በሆነ ሁኔታ አልተሸመደዱም ነበር ማለት ነው፡፡ ይህንን የሚያረጋግጡ ድርሳናት እነሆ፡-
ኢብን አቢ ዳውድ የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡- “ብዙ የወረዱ የቁርኣን ጥቅሶች በየማማ ጦርነት ላይ በሞቱት ብዙ ሰዎች ይታወቁ ነበር … ከጦርነቱ በተረፉት ሰዎች ግን አይታወቁም ነበር እንዲሁም በጽሑፍ አልሠፈሩም ነበር፡፡ ቁርኣን ሲሰበሰብ አቡበክር፣ ዑመርም ሆነ ኡሥማን አያውቋቸውም ነበር፡፡ ከእነርሱ በኋላ በነበረ አንድም ሰው ጋ ማግኘት አልተቻለም፡፡”[10]
አል-ሱዩጢ፣ ኢትቃን በተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ ተከታዩን ማስጠንቀቅያ አስፍረዋል፡- “ከእናንተ መካከል ማንም ሰው ሙሉውን ቁርኣን አግኝቼዋለሁ ብሎ መናገር የለበትም፡፡ የቁርኣን አብዛኛው ክፍል የጠፋ ሆኖ ሳለ ሁሉን አውቃለሁ ብሎ መናገር እንዴት ይቻላል? ከዚህ ይልቅ የተረፈውን አግኝቼዋለሁ ብሎ ይናገር፡፡”[11]

በዚህ ሁሉ ችግሮችና ውዝግቦች የታጀበው የአቡበክር ቁርአንን የማሰባሰብ ሂደት ተዓማኒነት ሊኖረው የሚችለው በምን መስፈርት ነው?
[1] Al Suyuti. Al Itqan fi
[11] Al Suyuti. A- Itqan fi `ulum al Qur’an; part 2, p. 25; Cited in: Ibn Warraq. Which Koran?; p. 24
--------------
http://www.ewnetlehulu.org/am/abubakr-quran-compilation/
[1] Al Suyuti. Al Itqan fi
ulum al Qur’an; p. 378; Cited in: The Qur’an Dilemma; Former Muslims Analyze Islams Holiest Book. 2001, Vol. 1, p. 49
[2] The Qur’an Dilemma. Vol. 1, p. 51
[3] Ibn Abi Dawud, Kitab al-Masahif, p. 5
[4] Al Suyuti. Al-Itqan; p. 135
[5] Sahih al-Bukhari, Volume 6, Book 61, Number 521
[6] Sahih Muslim, 17:4194
[7] Al Suyuti. Al Itqan; p. 385;፤ Cited in: The Qur’an Dilemma; Vol. 1, p. 52
[8] Sahih Muslim, book 8, no. 3421
[9] Sunan Ibn Majah; 3፡9፡1944
[10] Al Suyuti. Al- Itqan fi
ulum al Qur’an; part 2, p. 25; Cited in Ibn Warraq. Which Koran?: Variants, Manuscripts, Linguistics; Prometheus Books, 2011, p. 24[11] Al Suyuti. A- Itqan fi `ulum al Qur’an; part 2, p. 25; Cited in: Ibn Warraq. Which Koran?; p. 24
--------------
http://www.ewnetlehulu.org/am/abubakr-quran-compilation/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
የኡሥማን ቁርአንን የማረም ሒደት ከጥርጣሬ የፀዳ ነበርን?
ተከታዩ ጽሑፍ ሐሰን ታጁ ቁርአን በኸሊፋ ኡሥማን ዘመን የተሰበሰበበትን በብዙ አጠራጣሪ ክንውኖች የተከበበውን ሒደት ከጥርጣሬ የጸዳ ለማስመሰል በመጽሐፋቸው ውስጥ ላሰፈሩት ሙግት የሰጠነው ምላሽ ነው፡፡
ሐሰን ታጁ በኡሥማን ዘመን ስለተደረገው ቁርአንን የማረምና የማስተካከል ሥራ ያቀረቡት ሐተታ በአሳሳች ምልከታዎች የተሞላ ነው፡፡ ኡሥማን ቁርአንን ለምን ማረም እንዳስፈለገው ሲገልፁ እዲህ ብለዋል፡-
የእስልምና ግዛት እያደር እየሰፋ፤ ለአረብኛ ቋንቋ እንግዳ የሆኑ ሕዝቦች የሙስሊሙን ኡምማህ እየተቀላቀሉ ሄዱ፡፡ በዚያ ወቅት ቁርአን በመጽሐፍ መልክ ተዘጋጅቶ ያልተበተነና በቃል የሚተላለፍ በመሆኑ የንባብ ስልት ለአዳዲስ ሰላሚዎች ማስቸገሩ እና ልዩነትም መፈጠሩ አልቀረም፡፡ በአርመንያና በአዘርቤጃን ዘመቻ ላይ የተሳተፈው ሁዘይፋህ ቢን አልየማን በቁርአን የንባብ ስልት ላይ የተከሰተውን ልዩነት ማስተዋሉ አልቀረም፡፡ በዚህ ሳቢያ የደረሰውን መወዛገብም አስተዋለ፡፡ እናም ኡሥማን ዘንድ በመቅረብ እንዲህ ሲል ተማፀናቸው፡- ‹‹ሕዝበ ሙስሊሙ ልክ እንደ አይሁዶችና ክርስቲያኖች በሃይማኖት መጽሐፉ ከመወዛገቡ በፊት አንዳች መላ ዘይዱ፡፡›› (ገፅ 22-23)
ሙስሊሙ ማሕበረሰብ በቁርአን ላይ መለያየት የጀመረው ለአረብኛ ቋንቋ እንግዳ የሆኑ ሕዝቦች በመስለማቸው ምክንያት ብቻ ሳይሆን በዋናነት የመሐመድ ባልደረቦች ይጠቀሟቸው የነበሩ የተለያዩ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ቁርአኖች በመሰራጨታቸው ነበር፡፡ የኢራቅና የሦርያ ሙስሊሞች ለጂሃድ በአርመንያና በአዘርባጃን ድንበር ላይ በተገናኙ ጊዜ ‹ትክክለኛው የቁርአን ቅጂ የቱ ነው?› በሚለው ጥያቄ ላይ ውዝግብ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ከሦርያ የመጡ የሁምስ ሙስሊሞች የአል ሚቅዳድ ኢብን አል-አስዋድን ቅጅ ይቀበሉ የነበረ ሲሆን የተቀሩት የሦርያ ሙስሊሞች ደግሞ የኢብን ከዕብን ቅጂ ይከተሉ ነበር፡፡ በኢራቅ የነበሩት የበስራ ሙስሊሞች የአቡ ሙሳን ንባብ ይከተሉ የነበረ ሲሆን የኩፋ ሙስሊሞች ደግሞ የኢብን መስዑድን ይከተሉ ነበር፡፡[1] ስለዚህ የመለያየቱ አብይ መንስኤ የተለያዩ የቁርአን ቅጂዎች መሰራጨት እንጂ የአረብኛ ቋንቋ ችግር አልነበረም፡፡ የኡሥማን ዓላማ የግጭት መንስኤ የሆኑትን እነዚያን የተለያዩ የቁርአን ቅጂዎች በማስወገድ ወጥ የሆነ የንባብ ሥልት ያለውን አንድ ቅጂ ማዘጋጀት ነበር፡፡
ከእስላማዊ ድርሳናት ከምናገኛቸው መረጃዎች በመነሳት የኡሥማን የእርማት ሥራ እጅግ አጠራጣሪ የሚሆንባቸውን ብዙ ምክንያቶች መጥቀስ እንችላለን፡-
1.የኡሥማን ቅጂ በአቡበክር ዘመን በዘይድ ተዘጋጅቶ በዑመር እጅ በነበረውና የዑመር ልጅ ሐፍሷ[2] በወረሰችው ጥራዝ ላይ የተመሠረተ ነበር፡፡[3] የዚያ ጥራዝ የአሰባሰብ ሂደት እጅግ አጠራጣሪ መሆኑን ቀደም ሲል ተመልክተናል፡፡
2.ዘይድ የመሐመድ ጸሐፊ የነበረ ቢሆንም ቁርአንን እንዲያስተምሩ በመሐመድ ዕውቅና ከተሰጣቸው አራቱ አነብናቢዎች መካከል አልነበረም፡፡ አራቱ አነብናቢዎች አብዱላህ ኢብን መስዑድ፣ ሰሊም፣ ሙዓዝና ኡበይ ቢን ከዕብ ነበሩ፡፡[4] ቁርአንን እንዲያስተምሩ በመሐመድ ዕውቅናና ሥልጣን የተሰጣቸው ግለሰቦች እያሉ ዘይድ ለዚህ ሥራ መመረጡ ጥያቄን ያጭራል፡፡
3. ቁርአንን የማነብነብ ብቃቱ በመሐመድ የተመሰከረለትና ቁርአንን እንዲያስተምር ተሹሞ የነበረው ኢብን መስዑድ[5] ከኮሚቴው ውስጥ እንዲገለል ተደርጎ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳም ቅሬታውን እንዲህ በማለት ገልፆ ነበር:-
“ሙስሊሞች ሆይ! ቁርአንን እንዳልጽፍ እኔን በማግለል እስልምናን ስቀበል [ገና ሳይወለድ] በአባቱ አካል ውስጥ በካፊርነት ለነበረው ሰው [ለዘይድ] ኃላፊነት ተሰጠ፡፡”[6]
ኢብን መስዑድ ያቀረበው ይህ ቅሬታ ተገቢ ነበር፡፡
4. ኢብን መስዑድ በኡሥማን ትዕዛዝ በዘይድ ተዘጋጅቶ የነበረውን ቁርአን ጨምሮ ሕዝበ ሙስሊሙ የተጭበረበረ ንባብ የሚከተል መሆኑን በማሳወቅ በግልፅ ተቃውሟል፡፡[7] የኩፋ ሕዝቦች በኡሥማን ውሳኔ የፀደቀውን አዲሱን ቁርአን እንዳይቀበል አድርጓል፡፡[8] በዚህም ምክንያት የኩፋ ሕዝብ አል-ሐጃጅ ኢብን ዩሱፍ አል-ሣቃፊ ሥልጣን እስከያዘበት ዘመን ድረስ የኢብን መስዑድን ቁርአን ተቀብሎ ኖሯል፡፡[9]
5. ኡሥማን በቁረይሽ ዘዬ ከተጻፈው አዲሱ ቁርአን ውጪ ሌሎች ቁርአኖችን በማቃጠል እንዲወድሙ በማድረጉ በዘመኑ በነበሩት ሙስሊሞች ዘንድ ተነቅፏል፡፡ “ቁርአንን የቀደደ ሰው” እስከመባልም ደርሷል፡፡[10]
6. ኡሥማን የቀደሙትን ቁርአኖች አቃጥሎ የእርሱን ብቻ ኦፊሴላዊ በማድረጉ ምክንያት የመረጃ ስወራ አለመኖሩን እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም፡፡
7. ኡሥማን አዲሱን ቁርአን ኦፊሴላዊ በማድረግ ሌሎችን ቢያቃጥልም የሐፍሷን ቁርአን ሳያቃጥል በመመለሱና በሌሎች አነብናቢዎች የተዘጋጁትን ቁርአኖች በሙሉ ሳያጠፋ በማለፉ ምክንያት ሌሎች የቁርአን ቅጂዎች በድጋሚ ችግር መፍጠራቸው አልቀረም፡፡ የእነዚህ ንባቦች የተወሰኑ ክፍሎች ኢብን አቢ ዳውድ አል ሲጂስታኒና አቡ አል-ፈሥ ዑሥማንን የመሳሰሉ ጥንታውያን ሙስሊም ሊቃውንት በጻፏቸው መጻሕፍት ውስጥ ተጠብቀዋል፡፡ እነዚህ ልዩነቶች ሲገመገሙ በቁርአን ውስጥ ከፍተኛ ለውጦች መደረጋቸውን ያመለክታሉ፡፡[11]
8. ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተገኙት ከኡሥማን ቁርአን ላይ እንደተገለበጡ የሚነገሩት ጥንታዊ የቁርአን ጽሑፎች እርስ በርሳቸው የማይመሳሰሉ ሲሆኑ ብዙ ግጭቶች በመካከላቸው ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ጽሑፎች ማየት የሚፈልግ በግርጌ ማስታወሻው ላይ የተሰጡትን ድረ-ገፆች በመጎብኘት ፎቶግራፎቹን ማግኘት ይችላል፡፡[12]
ከላይ ከጠቀስናቸው ነጥቦች አኳያ ሐሰን ታጁ የቁርአን አሰባሰብ ጥርጣሬን ሊያጭሩ ከሚችሉ ነገሮች የፀዳ መሆኑን ለማሳየት በመጽሐፋቸው ውስጥ ገፅ 18-27 ያሠፈሯቸው ሐሳቦች በሙሉ ውድቅ ናቸው፡፡ ቁርአን በመሐመድ ዘመንም ሆነ በኸሊፋዎች ዘመን በትክክል መጠበቁን እንድናምን የሚያስችል ማስረጃ የለም፡፡ በእስላማዊ ድርሳናት ውስጥ ሰፍረው የሚገኙት ማስረጃዎች ከዚያ በተፃራሪ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡
[1] The Qur’an Dilemma; Vol. 1, p. 52
[2] ሐፍሷ የሁለተኛው ኸሊፋ የዑመር ኢብን አል-ኸጧብ ልጅ ስትሆን ከነቢዩ መሐመድ ሚስቶች መካከል አንዷ ነበረች፡፡
[3] Sahih al-Bukhari, vol. 6, bk 61, no. 510
[4] Sahih al-Bukhari, Vol. 6, Bk 61, no. 521
[5] Ibid.
[6] Ibn Abi Dawud al-Sijistani. p. 24-25; Cited in: The Qur’an Dilemma; Vol. 1, p. 54
[7] Ibn Sa’d’s Kitab al-Tabaqat al-Kabir, Vol. 2, p. 444
[8] Nöldoke, Tarikh al-Qur’ān 280, 339; Cited in: The Qur’an Dilemma; Vol. 1, p. 54
[9] Encyclopedia of the Qur’ān Vol. 1, p. 348; Cited in: The Qur’an Dilemma; Vol. 1, p. 54
[10] Ibn Warraq. The Origins of the Koran: 1998, p. 102
[11] The Qur’an Dilemma; Vol. 1, p. 59
[12] http://www.qurantext.org
www.answering-islam.org/PQ/A1.htm#AppendA

ሮሜ 9:5
የእስልምና ሰባኪያን ደግመን ደጋግመን በማያውቁት ነገር ውስጥ እንዳይዘባርቁ ብንመክራቸውም፣ በተለይ የግሪክ ቋንቋን በተመለከተ፣ መስሚያቸውን ደፍነው አሳፋሪና ከእውቀት የራቀ ፅሁፋቸውን ከመለጠፍ እየተቆጠቡ አይደሉም። ይሄም ተራ የሆነ የማወናበጃ ስልት እንጂ ሌላ አይደለም።
ሮሜ 9:5ን አስመልክቶ ወሒድ የሚባል ግለሰብ (ባለፈው ተስፋዬ ሮበሌ ብሎ ስለ ግሪክ ሰዋ ሰው የዘባረቀውና ያጋለጥነው ሳያንስ) አሁንም ቅጥፈቱንና፣ ፋላሲውን(fallacy) እንዲውም ምንም እውቀቱ ሳይኖረው ቋንቋውን መዳፈሩን ቀጥሎበታል።
ልጁ ፅሁፉን የሚጀምረው ጳውሎስን እንዲህ ብሎ በማጣጣል ነው። “ለእኛ ለሙሥሊሞች ጳውሎስ የኢየሱስ ሐዋርያ ሳይሆን የግሪክንና የሮምን ዶክትሪን ከኢየሱስ ደክትሪን ጋር ለማስማማት የታገለ ጥሩ ፈላስፋ ነው።”
ለመሆኑ፣ የእስልምን ምሁራንና መፅሓፍቶች ልክ እንደ ወሒድ ጳውሎስ #ፈላስፋ ብቻ ነው ይላሉ ወይስ ወሒድ ከራሱ ሓይማኖት ጋር እየተጣላ ነው? ቁርአንና ተፍሲር ጳውሎስ ከአምላክ የተላከ መልዕክተኛ መሆኑን ይናገራሉ። ላስነባቹ:-
ወደነርሱ ሁለት ሰዎችን በላክንና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ፣ በሦስተኛው አበረታንና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ፣ (የሆነውን ምሳሌ ግለጽላቸው)።” (ሱረቱ ያሲን (የያሲን ምዕራፍ) 36:14)
አሁን እዚህ ጋር ጳዉሎስ የሚለዉ የታለ? ትሉ ይሆናል:: ደግሞም ብላችኋል ግን አልተሳሳታችሁም ልክ ናችሁ "ጳዉሎስ" የሚል ስም የለም። ነገር ግን፣ ቁርአንን ለመረዳት የቁርአን መተርጉማን (ሙፈሲሮች) የተናገሩትን ማየት ያስፈልጋ፤ እንጂ ቁርአንን (ቁርአን የቃላት ውርጂብኝ ብቻ ስለሆነ) በቁሙ በማንበብ ብቻ መረዳት በፍጹም አይቻልም፡፡ ይሄንን ሙስሊሞችም ጠንቅቃችሁ ታውቁታላችሁ።
የቁርአን ትርጉም ተፍሲር ይባላል። በጣም ታዋቂና ተቀባይነት ያላቸው ተፍሲሮች ደግሞ ኢብን ካቲር እና አል ጃለሊን ናቸው። ከነዚህ ውስጥም እንደ #ኢብን_ካቲር ያለ ተቀባይነት ያለው ተፍሲር የለም። በዚህ የቁርአን አንቀፅ ላይም የምናየው የኢብን ካቲርን ተፍሲር ይሆናል። እንዲህ ይላል:-
📚“(በሶስተኛዉ አበረታናቸዉ) ማለት፣ “እኛ በሶስተኛዉ መልዕክተኛ ደገፍናቸዉ ፣ አበረታናቸዉ” ማለት ነው። ኢብኑ ዩራይጅ ከ ዋህብ ኢብኑ ሱለይማን እና ከሹአይብ ያባይ እንዳስተላለፉት:-“ የመጀመሪያዎቹ የሁለቱ መልዕክተኞች ስም #ስምኦን(#ጴጥሮስ) እና #ዩሐንስ የሶስተኛዉ ስም ደግሞ #ጳዉሎስ ነበር። ከተማዋም አንፆኪያ ነበረች።
ስለዚህ ወሒድ ከእስልምና ጋር መጣላት ካልፈለገ በስተቀር መፅሓፍቶቹን ማመንና የጳውሎስን መልዕክተኛነት መቀበል ግድ ይለዋል።
ወደ ሮሜ 9:5 ስንመለስ፣ ልጁ እንዲህ ብሎ ፅፏል።
“ሮሜ 9፥5 አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ *"ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ እርሱ ለዘላለም የተባረከ ይሁን! አሜን*"። καὶ ἐξ ὁ Χριστὸς τὸ κατὰ σάρκα ὁ ὢν ἐπὶ πάντων Θεὸς εὐλογητὸς εἰς τοὺς αἰῶνας ἀμήν.
Whose are the fathers, and of whom as concerning the flesh Christ came. God, who is over all be blessed for ever. Amen.” Reivised standard version 1971 ,
ግሪኩ ላይ "ኤስቲን" ἐστιν ማለትም "ነው" የሚል ቃል የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ "ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ይሁን" የሚል ፍቺ እንዳለው እሩቅ ሳንሄድ የዐማርኛ ምሁራን ይነግሩናል። በ 1971 ዕትም Reivised standard version "ይሁን"be" ብሎ አስቀጦጣታል "be blessed for ever"። "አሜን" የሚለው ቃል ለምስጋና የመጣ እስከሆነ ድረስ "ለዘላም የተባረከ ይሁን" ማለት ምስጋና ነው። ማነው ለዘላም የተባረከ ይሁን የተባለው? ስንል ለዘላም የተባረከ ይሁን የተባለው "ከሁሉ በላይ" የሆነ አምላክ ነው። እርሱም ከኢየሱስ እና ከመላው ፍጥረት ሁሉ በላይ የሆነው አብ ነው”
በዚህች አንቀፅ ወሒድ ሁለት መሰረታዊ ስህተቶችና እውቀት ማጣትን አሳይቶናል።
1. ከግሪክ ሰዋሰው አንፃር
2. ከሎጂክ አንፃር
1. የግሪክ ሰዋሰው
ἐστιν (estin) የ eimi(I Am) ሶስተኛ መደብ ነጠላ verb ሲሆን ትርጉሙ “Is” ነው። ነገር ግን በግሪክ ቋንቋ ብዙ ግዜ ይህ verb to be መግባት እያለባትም ከአረፍተ ነገር ውስጥ ያወጣታል ወይም Drop ያደርጋታል። ለምሳሌ ሮሜ 7:12 Ο νομος αγιος και εντολη αγια… (The law is holy and the commandment is holy…) በዚህ ክፍል ውስጥ በግሪኩ ἐστιν (estin) የሚል የለም ነገር ግን ወደ ኢንግሊዘኛ ሲተረጎም የግድ Is ታስፈልጋለች። ይሄ የሆነበት ምክኒያት ግሪክ ይህቺን ግስ drop ስላረጋት ነው እንጂ እንዲህ ተብላ መፃፍ ትችላለች “Ο νομος αγιος(ἐστιν)…በተጨማሪም αγιος(ቅዱስ) የሚለው ቃል እንደ predicate adjective እየተጠቀመ ስለሆነ ትርጉሙ ግልፅ ነው። ስለዚህ፣ estin የምትለው ስላልገባች የመፅሃፍ ቅዱስ ትርጉም ስህተት ነው ብሎ መሞገት ተራ ሞኝነትና እውቀት አልባነት ነው።
ከላይ የፃፍኩት የልጁን አላዋቂነት ለማጋለጥ እንጂ ሲጀመር በሮሜ 9:5 ላይ verb to be ወይም የeimi, estin... በሌላ የግሪክ Mood ገብቷል። በግሪክ ቋንቋ ውስጥ ከTense በተጨማሪ mood የሚባሉ አሉ። አምስት mood አሉ፣ Indicative, imperative, infinitive, participle እና subjunctive. “Estin” አሁን indicative mood ነው።
በሮሜ 9:5 ላይ ግን የገባው የverb to be present paticiple mood ሲሆን እሱም ὢν የሚለው ነው። ትርጉሙም “being” ወይም “who is” ማለት ነው። ὁ Χριστὸς τὸ κατὰ σάρκα ὁ ὢν ἐπὶ πάντων Θεὸς (The Christ according to flesh WHO IS(being)OVERALL GOD ወይም ...በሁሉም ነገር ላይ አምላክ የሆነው ክርስቶስ)። ስለዚህ የቃል በቃል ትርጉሙ እንደዚህ ይሆናል። Who is የሚለው reflect የሚያደርገው ክርስቶስ ላይ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለዚህ ክርስቶስ ሁሉም ላይ አምላክ ነው እያለን ነው ክፍሉ።
2. የሎጂክ ግድፈት
ወሒድ አይናችን እያየ ቃሉ የሚናገረውን ሸምጥጦ፣ “ከሁሉ በላይ የሆነው” የተባለው እየሱስ አይደለም ካልን በኋላ ለዚህ ሙግቱ እንዲደግፈው የተጠቀማት ደግሞ ጳውሎስ አይሁድ ስለሆነ እየሱስ አምላክ ነው ብሎ አያምንም ብሎናል። ይሄ begging the question ይባላል። የተናገረውን prove ሳያረግ በፊት assume ማድረግ።
መፅሓፍ ቅዱስን ስናነብ ግን የክርስቶስን አምላክነት ከሰበኩት ውስጥ አንደኛው ጳውሎስ መሆኑን ነው።
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች ምዕ. 1)
----------
15-16፤ እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።
17፤ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።

👍1
18፤ እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው።
19-20፤ እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።
ወሒድ ቀጥሎ የፃፋቸው ከዚህ በፊት የተመለሱ ስለሆኑ አስፈላጊ ከሆነ ብቻ እንፅፍበታለን።
ወንድም ናኦል
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
19-20፤ እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።
ወሒድ ቀጥሎ የፃፋቸው ከዚህ በፊት የተመለሱ ስለሆኑ አስፈላጊ ከሆነ ብቻ እንፅፍበታለን።
ወንድም ናኦል
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ለቁርአን ግጭቶች መልስ ለመስጠት ለሞከረ ሙስሊም ሰባኪ የሰጠናቸውን ምላሾች በተከታዮቹ ሊንኮች ገብታችሁ ታነቡ ዘንድ እንጋብዛለን። እስከ ግጭት ቁጥር 28 ድረስ ከዚህ ቀደም ምላሽ የሰጠን ሲሆን በዚህ ዙር ከ 29-34 የሚገኙትን 5 "ምላሾች" ፈትሸናል። ሙሉ ዝርዝሩን ለማየት በዚህ ሊንክ ተጠቀሙ
http://www.ewnetlehulu.org/am/quran/book-of-contradictions/
------
29. መልእክተኞች ሆነው የተላኩት ሰዎች ብቻ ወይስ ሌሎች ፍጥረታትም ጭምር? http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-contra-29/
30. የሙሐመድ ገነት መግባት እርግጥ ነው ወይስ አይታወቅም? http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-contra-30/
31. ዮናስ በምድረ በዳ ተጥሏል ወይስ አልተጣለም? http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-contra-31/
32. ህፃናት ጡት እንዲጥሉ አላህ ያዘዘው ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ነው? http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-contra-32/
33. ለጦርነት ላለመዝመት መሐመድን ፈቃዱ የጠየቁት ሁሉ ተወቃሾች ናቸው ወይስ አይደሉም? http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-contra-33/
34. ሙሴ ሕዝቡን ነፃ ለማውጣት በተላከ ጊዜ ያመኑለት ጥቂት ወገኖቹ ብቻ ወይንስ የግብፅ ደጋሚዎችም ጭምር? http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-contra-34/
------
መልካም ንባብ!
እስልምና መልስ የለውም!

🔥1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
አላህን ፈለግሁት ኢየሱስን አገኘሁት – ዶ/ር ነቢል ቁሬሺ መጽሐፉን ለማውረድ ሊንኩን ይከተሉ:- http://www.ewnetlehulu.org/am/nabeel-book/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
የሰልማን ኮከብን ቅጥፈቶች የሚያጋልጥ አዲስ ጽሑፍ
ክርስትና መለኮታዊ ሃይማኖት ነው! እስልምናስ?
የመጽሐፍ ሒስ – ክፍል 6
http://www.ewnetlehulu.org/am/sel-book-review-6/
ክርስትና መለኮታዊ ሃይማኖት ነው! እስልምናስ?
የመጽሐፍ ሒስ – ክፍል 6
http://www.ewnetlehulu.org/am/sel-book-review-6/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ለጥያቄያችን በአንድ ሙስሊም ሰባኪ የተሰጠውን "መልስ" እንዲህ ፈትሸናል። ሊንኩን ይከተሉ:- http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-contra-35/