Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
በቁርአን ውስጥ ከአይሁድ የአዋልድ መጻሕፍት የተቀዱ በርካታ ታሪኮች ይገኛሉ። Rev. W. ST Clair Tisdall. The Sources of Islam; Translated and Abridge by Sir William Muir: pp. 21-38 ላይ ተከታዮቹ ኩረጃዎች ተዘርዝረዋል። የአዋልድ መጻሕፍቱ በሙሉ ቅድመ እስልምና የተጻፉ መሆናቸውን ልብ ይሏል:-
1. አብረሃም በእሳት ውስጥ ተጥሎ ነበር የሚለውን ጨምሮ ስለ አብርሃም በቁርአን ውስጥ የተወሱት ታሪኮች በሙሉ ሚድራሽ ራባ በተሰኘ የአይሁድ መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ (ሱራ 21፡51-71)
2. ቁርአን ስለ ንግሥተ ሳባ ያቀረባቸው ትረካዎች ሁለተኛ የመጽሐፈ አስቴር ተርጉም በተሰኘ የአይሁድ መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ (ሱራ 27፡17-44)
3. ሃሩትና ማሩት ስለተባሉት ደጋሚ “መላእክት” የተነገረው ሚድራሽ ያልኩት በተሰኘ የአይሁድ መጽሐፍ ውስጥ ይገኛል፡፡ (ሱራ 2፡102)
4. የሲና (ጡር) ተራራ በእስራኤላውያን አናት ላይ ስለመንሳፈፉ የተነገረው አቦዳ ሳራህ በተሰኘ የአይሁድ መጽሐፍ ውስጥ ይገኛል፡፡ (ሱራ 7፡171)
5. የወርቁ ጥጃ ድምፅ ስለማሰማቱ የተነገረው ፒርኬ ረቢ ኤልኤዘር በተሰኘ የአይሁድ መጽሐፍ ውስጥ ይገኛል፡፡ (20፡88)
እውን ቁርአን ከሰማይ የወረደ ።ገለጥ ነውን?

አዲስ ጽሑፍ
መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ!
ለአቡ ሀይደር የተሰጠ መልስ
http://www.ewnetlehulu.org/am/ask-those-who-read-the-book/

ከቁርአን ውስጥ የጠፉ 213 አንቀጾች!
————
ሙስሊም ኡስታዞች ቁርአን አልተጨመረበትም ከላዩ ላይም አልተቀነሰም በማለት ሲጓደዱ መስማት የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን የመጀመርያዎቹ ሙስሊሞች በርካታ የቁርአን ክፍሎች ጠፍተው መቅረታቸውን መስክረዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል በኡበይ ቢን ካዕብ ምስክርነት መሠረት ሱረት አል-አሕዛብ መጀመርያ “ሲወርድ” ርዝመቱ የሱረት አል-በቀራ ያህል እንደነበርና ገሚሱ ጠፍቆ አሁን ያለው ብቻ ሊተርፍ ችሏል፡-
عن عاصم بن بهدلة عن زر قال
قال لي أبي بن كعب : كأين تقرأ سورة الأحزاب أو كأين تعدها قال قلت له ثلاثا وسبعين آية فقال قط لقد رأيتها وإنها لتعادل سورة البقرة ولقد قرأنا فيها الشيخ والشيخة إذا زنيا فارجموهما البتة نكالا من الله والله عليم حكيم
Narrated ‘Aasim ibn Bahdalah, from Zirr, who said:
Ubayy ibn Ka‘b said to me: How long is Soorat al-Ahzaab when you read it? Or how many verses do you think it is? I said to him: Seventy-three verses. He said: Only? There was a time when it was as long as Soorat al-Baqarah, and we read in it: “The old man and the old woman, if they commit zina, then stone them both, a punishment from Allah, and Allah is Almighty, Most Wise.”
ዓሲም ኢብን ባህደላህ ከአዚር ሰምቶ እንደተናገረው፡-
ኡበይ ኢብን ካዕብ እንዲህ አለኝ፡- አንተ ስታነበው ሱረት አል-አሕዛብ ምን ያህል ይረዝማል? ወይም ምን ያህል አንቀጽ ነው ብለህ ታስባለህ? ሰባሦስት አንቀጽ ነው ብዬ መለስኩለት፡፡ እርሱም ይህ ብቻ ነው? በማለት መለሰልኝ፡፡ የሱረት አል-በቀራ ያህል የሚረዝምበት ጊዜ ነበር፡፡ በውስጡም እንዲህ የሚል ነበር፡- “ጎልማሳ ወንድና ሴት ዝሙት ከፈፀሙ ሁለቱንም ውገሯቸው፤ ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ቅጣት ነው፤ አላህ ሁሉን ቻይ ጥበበኛም ነው፡፡” (ሙስናድ አሕመድ ሐዲስ ቁጥር 21245)
ኢብን ሐዝም የተባለ ሊቅ ይህ ሐዲስ ሳሂህ መሆኑ የቀን ፀሐይ ያህል ግልፅ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ኢብን ከሢር ደግሞ ኢስናዱ የሐሰን ደረጃ እንዳለው ተናግሯል፡፡ ታላላቅ ሙስሊም ሊቃውንት ይህ ሐዲስ እውነት መሆኑን ይስማሙበታል፡፡ ሱረት አል-በቀራ (የላሚቷ ምዕራፍ) 286 አንቀፆች ያሉት ሲሆን ሱረት አል-አሕዛብ ደግሞ 73 አንቀፆች ብቻ ናቸው ያሉት ስለዚህ 213 ያህል አንቀፆች ከአላህ መጽሐፍ ውስጥ ጠፍተዋል ማለት ነው፡፡

👍2
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ይሄ ደግሞ ከክፍል 1 የባሰ ነው። እስከ መጨረሻው ስሙት። ሰው በማያውቀው ጉዳይ በድፍረት እንዲህ ሲተረተር ከሙሐመድ በኋላ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም! Shame! https://youtu.be/VM3-Dsw2vPE
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ደካማ አመክንዮ የተዛባ ምንጭ
የቁርአንን ኩረጃዎች ለማስተባበል የተደረገ ከንቱ ጥረት
ተለማማጁ ሙስሊም ዳዋጋንዲስት ከነበረበት ሀይበርኔሽን ነቅቶ የማይስተባበለውን ለማስተባበል በመሞከር እንደተለመደው ግንባሩን በማመቻቸት መስመራችን ላይ ገብቶልናል፡፡ በዚህ ምላሻችን በምንመለከተው ጽሑፉ ውስጥ የቁርአንን ኩረጃ ለማድበስበስ ሞክሯል፡፡ ነገር ግን እንደተለመደው ጽሑፉ በደካማ ሎጂክና መረጃዎችን በማዛባት ላይ የተመሠረተ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-plagiarism-response/

❤1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ቁርአን የተረት መጽሐፍ መሆኑን የሚያሳይ አጭር ጽሑፍ
አብርሃምና አምልኮተ ጣዖት
ትርጉም አልባ የቁርአን ትረካ
http://www.ewnetlehulu.org/am/abraham-and-worship-of-idols/
አብርሃምና አምልኮተ ጣዖት
ትርጉም አልባ የቁርአን ትረካ
http://www.ewnetlehulu.org/am/abraham-and-worship-of-idols/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
መድብለ ጋብቻና እስታስቲክስ
=========
ሙስሊም ሰባኪያን ብዙ ጊዜ መድብለ ጋብቻን በእስታቲስቲክስ አስታከው ለማጽደቅ ሲሞክሩ ይታያሉ፡፡ አላህ መድብለ ጋብቻን የፈቀደው በዓለም ላይ የሴቶች ቁጥር ከወንዶች ስለሚበልጥ ነው ይሉናል፡፡ ነገር ግን መረጃዎችን ስናገላብጥ ጉዳዩ እነርሱ ከሚሉት የተገላቢጦሽ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የአገራችን ሙስሊም ሰባኪያን በዓለም ላይ የሴቶች ቁጥር ከወንዶች ይበልጣል የሚለውን ዶ/ር ዛኪር ሲናገር ሰምተው በደመነፍስ ይደጋግሙታል እንጂ መረጃዎችን አገላብጠው ትክክለኛውን ቆጠራ አጣርተው አይደለም፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የወንዶች ቁጥር 50.4% ሲሆን የሴቶች ቁጥር ደግሞ 49.6% ነው፡፡ በ2019 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ በዓለም ላይ የወንዶች ቁጥር ከሴቶች በ 68,436,343 እንደሚበልጥ ነው ግምት የተቀመጠው (ወንዶች 3,915,735,823፣ ሴቶች ደግሞ 3,847,299,480 ናቸው)፡፡ በዕድሜ ከፋፍለን ስንመለከት ደግሞ ከ 15 ዓመት በታች ዕድሜ የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ይበልጣል፡፡ ከ 15-64 ዓመትም እንዲሁ የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ይበልጣል፡፡ የሴቶች ቁጥር ከወንዶች በመጠኑ በልጦ የሚታየው ከ 65 ዕድሜ በላይ ነው፡፡ ስለዚህ ጋብቻ በሚፈፀምበት ዕድሜ የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ይበልጣል፡፡ መረጃውን በዚህ ድረ ገፅ ታገኛላችሁ https://countrymeters.info/en/World
የሚገርመው ነገር በሁሉም ሙስሊም አገራት ሊባል በሚችልበት ሁኔታ የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ይበልጣል፡፡ ለምሳሌ ካታር ለአንድ ሴት 3.29 ወንዶች፣ ኤምሬቶች ለአንድ ሴት 2.19 ወንዶች፣ ኩዌት ለአንድ ሴት 1.43 ወንዶች፣ በሳዑዲ ለአንድ ሴት 1.21 ወንዶች፣ ወዘተ. ነው፡፡ የተቀረውን በዚህ አድራሻገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ፡- https://www.nationmaster.com/country-info/stats/People/Sex-ratio/Total-population
ስለዚህ ለሙስሊም ሰባኪያን ማስተላለፍ የምፈልገው ምክር አንድ ሰው ስለተናገረ ብቻ ዝም ብላችሁ ያለ ማስረጃ መናገር አላዋቂነት በመሆኑ አጣርታችሁ ተናገሩ የሚል ነው፡፡

ለየሕያ ኢብኑ ኑህ፡-
ሰሞኑን "የቁርአን ኩረጃዎች?" የተሰኘውን መጣጥፍህን ተመልክቸዋለሁ፡፡ እኔንም ከአብዱልሀቅ ጀሚል ጋር አጋምደህ ስሜን አንስተሀል፡፡ ወንድሜ ዳንኤል ከልክህ በላይ መልሶልሀል፡፡ ከወንድሜ የጎደለ የመሰለኝን ልሞላ ብዕሬን አንስቻለሁ፡፡ ባለፈው የአብዱልሐቅን መጽሐፍ ለመተቸት ማስታወቂያ ባስነገርክበት ወቅት ገርመኸኝ እርሱን ለመተቸት የሞራልና የእውቀት ብቃት እንደሌለህ ነግሬህ እንደነበር ማስረጃ በመጥቀስ ነግሬህ እንደነበር የምትዘነጋው አይመስለኝም፡፡ ጥቂትም ሐሳቦችን ተለዋውጠናል፡፡ አሁንም ያሳየኸን ያንኑ ዕውቀት አጠርነትህን እንደሆነ ምን ያክል ገብቶህ እንደሆነ አላውቅም፡፡ ለነገሩ ቢገባህ እንዲህ ለመጫጫር አትሞክርም ነበር፡፡ ለማንኛውም ይህች መናኛ የሙግት ጽሑፍህን በጥቂቱ እድፈቷን ላስመልክትህ፡-
1. የክርስቲያኖችን የሙግት ሐሳብ ማጣመም
"ቁርዓንን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት ከሚነሱ የክርስቲያኖች መከራከሪያ ሚዛኑ ከፍ ያለ ጥቀስ ብባል ይህኛውን የሚገዳደር ያለ አይመስለኝም። “ቁርአን ከመጽሀፍ ቅዱስ ኮርጇል”…"
ይህ የጸሐፊዎችን የሙግት እምብርት የመገንዘብ እጥረትን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡ እውነት ነው ሐሳቡ እንደ ሙግት ሐሳብ ይነሳል፤ ነገር ግን የትኛውም ክርስቲያናዊ ጸሐፊ የቁርአንን ኩረጃ እንደ ዋና መከራከሪያ ነጥብ አንስቶ አያውቅም፡፡ ዋነኛውና መሠረታዊው ጥያቄ ነቢዩ ሙሐመድ የእውነተኛው አምላክ መልእክተኛ ናቸውን? የሚለው ነው፡፡ ኩረጃ ደግሞ ነቢዩ ሙሐመድ የእውነተኛው አምላክ መልእክተኛ ላለመሆናቸው እንደ አስረጅ ነጥብ አንድ ተብሎ ይነሳል፡፡ በጠቀስካቸው ክርስቲያናዊ ጸሐፍትም እኔንና ወንድሜን ዳንኤልን ጨምሮ የሆነው ይኸው ነው፡፡
2. የአብዱልሀቅ "ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት ነውን?"
አማን ገረመውና አብዱልሀቅ አንድ ሰው ነው አይደለም ለሚለው ግምትህ ወንድሜ ዳንኤል በቂ ምላሽ ስለሰጠህ መድገሙ ስለማያስፈልገኝ እዘለውና ወደ ጠቀስከው የኩረጃ ትችትህ ልለፍ፡-
"አማን ገረመው የተሰኘ ፀሀፊ ስሞቹን የሙስሊም በማድረግ ከሚያሳትማቸው መጽሀፍት ውስጥ አንዱ የሆነው “ኢስላም መለኮታዊ ሀይማኖት ነውን?” በተሰኘው መጽሀፉ ገፅ 103 ላይ የቁርአን ምንጭ ብሎ ከዘረዘራቸው ውስጥ አንዱ “ነብዩ ሙሐመድ “ﷺ” መጽሀፉን ከክርስቲያኖች የተማረው” እንደሆነ ለማስረዳት ሲደክም እናየዋለን። የሚያስቀው ክፍል ግን ቀደም ብሎ ከገፅ 63 ጀምሮ ደግሞ “የቁርአን ምንጭ ሰይጣን ነው” በሚል ሊያስረዳ ሲደክም እንደነበር ስታሳስታውሱ ነው። አንድ ሰው የቁርአን ምንጭ መጽሀፍ ቅዱስ ነው ብሎ “ከተነተነ” በኃላ መልሶ “ቁርአን የሰይጣን ቃል ነው” ካለ በተዘዋዋሪ መጽሀፍ ቅዱስ የሰይጣን ቃል መሆኑን መስክሯል ማለት ነው።"
ለዚህ ነው ቀደም ብዬ እንዳልኩህ መጽሐፉ ከአንተ አቅምና ዕውቀት በላይ ነው፡፡ ምናልባት ጽሑፍህ ደርሶት ምላሽ ይሰጥህ ይሆናል፤ እስከዛው ግን መጽሐፉን በጥንቃቄ እንዳነበበ ሰው ልመልስልህ፡-
• መጽሐፉን ማንበብህ የሚያስመሰግንህ ቢሆንም እጅግ እንደሞገተህና ከአቅምህ በላይ ሆኖ እንዳስጨነቀህ ጽሑፍህ ያሳብቃል፡፡ በጠቀስካቸው ሁለቱ ገጾች ላይ ያሉት ሐሳቦች በተመለከተ ፍጹም የጸሐፊውን ሐሳብ ልታገኘው አልቻልክም፡፡ በገጾቹ ስለ ቁርአን ኩረጃ የሚናገር ምንም ነገር እንደሌለ ያነበቡ ሁሉ ምስክሮች ናቸው፡፡ ጸሐፊው ከገጽ 60-109 ባለው ገጾች እያስነበበን ያለው "የመለኮታዊ መጸሐፍ ቁርአናዊ መለኪያዎች" በሚል በአንድ ርዕስ ላይ ነው፡፡ አምስት ቁርአናዊ መለኪያዎችን አውጥቷል፤ በዛም ራሱን ቁርአንን ይለካል ቁርአን የራሱን መለኪያዎች እንኳን ማለፍ እንዴት እንደተሳነው ለአንባቢዎቹ ያሳያል፡፡ ልኬታው ቁርአንን በቁርአን ሚዛን እንጂ ቁርአንን በመጽሐፍ ቅዱስ አይደለም፡፡ በቁርአንና በመጽሐፍ ቅዱስ መካከል ስላለ መመሳሰል አለመመሳሰል አንድም ቦታ ላይ አላነሳም፡፡ ታዲያ ከየት አምጥተህ ነው "አንድ ሰው የቁርአን ምንጭ መጽሀፍ ቅዱስ ነው ብሎ “ከተነተነ”" ልትል የቻልከው? ስለዚህ ስተኸዋል አላገኘኸውን፡፡
• የጠቀስካቸው ገጾች የያዙትን ሐሳብ በተመለከተ፡- በእነዚያ ገጾች በጉልህ ሁለት መለኪያዎች ይታያሉ፤ አንዱ "ከአላህ ዘንድ የወረደ መሆን ይኖርበታል" በሚል መለኪያ ከገጽ 60-66 ድረስ ይዘልቃል፡፡ በዚህ መለኪያ "ቁርአን እውን ከአላህ ወርዷልን?" በማለት 23 ዓመታት ወደ ነቢዩ ይመላለስ ነበር የተባለውን አካል ማንነት ከኢስላም መዛግብት በማመሳከር ይፈትሻል፡፡ ሙስሊሞችን የሚነዝሩ ማስረጃዎችን ከኢስላም መዛግብት እየመዘዘ የነቢዩ የዋሻ እንግዳ ሰይጣን እንደ ነበርና ቁርአን ከአላህ እንዳልወረደ ያትምልናል፡፡ ይህንን ሲያደርግም መጽሐፍ ቅዱስና ቁርአንን በማነጻጸር አይደለም፡፡ በሁለተኛው መለኪያም "ከሰውና ከሰይጣን ጣልቃ ገብነት ነጻ የሆነ" በማለት ከገጽ 101-109 ማስረጃውን ያቀርባል፣ ይለካል፣ ምልከታውን ያቀርባል፡፡ በዚህም እንደ ምድር መንቀጥቀጥ የሚያርገፈግፉ ኢስላማዊ ማስረጃዎችን እያቀረበ ቁርአን በራሱ መለኪያ የገጠመውን ውድቀት ያሳያል፡፡ ይህንንም ሲያደርግ በመለኪያው ላይ እንደሚታየው ጣልቃ የገቡ የተባሉት "ሰውና ሰይጣን" እንደሆኑና እንዴት ባለ መንገድ ጣልቃ ገብ እንደሆኑ በማስረጃው ያሳያል፡፡ ታዲያ አንተ "የቁርአን ምንጭ ብሎ ከዘረዘራቸው ውስጥ አንዱ “ነብዩ ሙሐመድ “ﷺ” መጽሀፉን ከክርስቲያኖች የተማረው”" የሚለውን ከየት አመጣኸው? እርሱ ከክርስቲያኖች ተኮረጀ ብሏል? አሁንም ስተሃል አብዱልሀቅን አላገነኸውም፡፡ መጽሐፉን ያነበቡ ሊመሰክሩ እንደሚችሉት ስለ ክርስቲያኖቹ ያወራው፣ ስለ ማንንነታቸው ስማቸውን ሳይቀር የተናገሩት ቁርአንና የኢስላም ጽሑፋት ናቸው፡፡ አብዱልሃቅ የተቸው በዛ ላይ የአላህ የተናገረውን እንጂ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቁርአን ኮረጀ የሚል መደምደሚያ አላስቀመጠም፡፡ ይልቁንም ሰዎች የተባሉት ክርስቲያኖቹ፣ ሱሃባዎቹ፣ ሰይጣናት፣ ዛፍ ለቁርአን አንቀጾችን አዋጥተውለት የተጻፈ ነው፤ ስለዚህ በራሱ መለኪያ መለኮታዊ መጽሐፍ አለመሆኑን መስክሯል በማለት የትችቱን መደምደሚያ አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ ስተሀል፡፡
3. ቁርአንና ኩረጃውን በተመለከተ የሰጠኸው ምላሽ
የጀመርከው "መመሳሰል ሁሌም ኩረጃ አይደለም" በሚል ነበር፡፡ በዚህ ሲጀምር በቁርአንና በመጽሐፍ ቅዱስ መካከል መመሳሰል እንዳለ ማመኑን ያሳያል፡፡ መመሳሰሉ አለ ማለት ሁሌም ኩረጃ አለ ማለት እንዳልሆነ ለማስረዳት ሲታትር ወንድሜ ዳንኤል ለዛ ከበቂ በላይ ምላሽ ሰጥቶበታል፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት በእርሱ ባልተዳሰሱት ላይ ጥቂት ልበልና የአንባቢን ግንዛቤ ሙሉ እናድርግ፡-
• መመሳሰሉ አለ ካልክ ከኡስታዝ አቡ ሀይደር ጋር ማን ያስታርቅህ?
የሕያ መጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን መሳሰል እንዳላቸው ሲያምን ኡስታዝ አቡ ሀይደር ደግሞ ላለመደናገር ማመሳከር በሚለው መጽሐፉ ከገጽ 41-48 ባለው ቁርአንና መጽሐፍ ቅዱስ በሐሳብም ሆነ በመልእክት እርስ በእርሳቸው እንደሚቃረኑ ተናግሯል፡፡ ታዲያ ማን ያስታርቅህ? በአንድ ለአንድ እየሠሩና እየተባበሩ እንዲህ መለያየት? እያሰብክ መመለስ እንደሚሳንህ ሌላው ማሳያ ነው፡፡ ለማንኛውም መጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን በሐሳብም ሆነ በመልእክት እርስ በእርስ ይቃረናሉ በሚለው የአቡ ሀይደር ሐሳብ እኔም እስማማለሁ፡፡ አብዱልሀቅ ጀሚል የዚህ ሐሳብ ተጋሪ መሆኑ በመጽሐፉ በግልጽ ይታያል፡፡
• የመመሳሰሉን መንስኤ በተመለከተ፡-

👍3❤1
"በተመሳሳይ ምንጫቸው አንድ የሆኑ ነብያት ያመጡት መልዕክት በይዘት ቢመሳሰል አንደኛው ከአንደኛው ቀድቶ ሳይሆን መሠረቱ አንድና አንድ ስለሆነ ብቻ ነው።"
የሕያ የመመሳሰላቸው መንስኤ ከአንድ ምንጭ የተቀዱ መሆናቸው እንደሆነ ለማሳየት ሞክሯል፡፡ በዚህም በትልቁ ስተሀል፡፡ በትክክል አንብበኸው ቢሆን የጠቀስከው የአብዱልሀቅ "ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት ነውን?" መጽሐፍ በሁለት ርዕሶች ትንተናው ስለሰጠበት ከማንሳትህ በፊት ደጋግመህ ታስብበት ነበር፡፡ ለማንኛውም አብዱልሀቅ "የቁርአን የመለኮታዊ መጽሐፍ መለኪያዎች" በሚለው ትንተናው ቁርአን መለኮታዊ መጽሐፍ አለመሆኑን፣ ከተለያዩ ምንጮች ተሰባስቦ የተሰደረ፣ ሰይጣንም ያዋጣበት እንደሆነ፣ የዋሻው እንግዳቸውም ገብርኤል መልአኩ እንዳልነበር መረጃን ዋቢ በማድረግ አሳይቷል፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን የሚመሳሰሉበት ሊኖር አይችልም፡፡ አለ ብለህ ድርቅ ካልክም ደግሞ ኩረጃው ትክክል ነው ወደሚል መደምደሚያ ያደርሰናል፡፡ በሁለተኛው "በኢስላም የእውነተኛ ነቢይ መመዘኛ ነቢዩ ሲመዘኑ" በሚለው ርዕስ ነቢዩ አንዱንም የራሳቸውን መለኪያ ባለማሟላት ከእውነተኛ ነቢያት ጎራ ወጥተው ወድቀዋል፡፡ ይህም መጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ከአንድ ምንጭ ላለመቀዳታቸውና አንድ አምላክ እንዳላካቸው ማሳያ ይሆናል፡፡ እንዲህ ሆኖ ሳለ አሁንም መመሳሰሉ እንዳለ ካመንክ ኩረጃው እርግጥ በሆኑን አንተው እያረጋገጥክ ነው ማለት ነው፡፡
እነዚህ ሁለት ነጥቦች የአቡ ሀይደርንና የአብዱልሀቅን መጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን አይመሳሰሉም የሚለውን የሙግት ሐሳባቸውን እርግጥ ያደርገዋል፡፡ ይህ የምጋራውና የማምንበት ነጥብ ነው፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስንና ቁርአንን በተመለከተ "መመሳሰሎች ሁሌም ኩረጃ አይደሉም" የሚለው የሙግት ሐሳብህ ገለባ ነው፡፡ ይህንን ስል ግን ቁርአን ከመጽሐፍ ቅዱስ አልተመሳሰለም ማለቴ አልኮረጀም ማለቴ አይደለም፡፡ ከዚህ 66 መጽሐፍትን ካቀፈው ጥቁር መጽሐፍ ውስጥ ግን ምንም ተመሳሳይ ሐሳብ የለም ማለቴ መሆኑ ግንዛቤ ይያዝልኝ፡፡ እንዲያውም ያልተኮረጀ አንድም እንደሌለ ማስረጃዎቸን ማቅረብ እችላለሁ፡፡
• በኩረጃ የተፈረጁ ታሪኮች በማለት የተሰጠው ማሳያ/ምሳሌ
የሕያ ይህን ሐሳብ ለመሞገት እንዲህ የሚል ማስተባበያ አቅርቧል፡-
"ተኮርጀዋል በሚል በተደጋጋሚ የሚጠቀሱ ታሪኮች በዋነኛነት ጥንተ ነገር አጥኝዎች/Orentalists/ የገለጿቸው ናቸው። ለዚህ ስራ በብዙዎች ዘንድ እንደ መነሻ ተደርጎ የሚቀርበው በ19ኛው ክፍለ ዘመን አብርሐም ጊገር በተሰኘ አይሁድ የተፃፈው መጽሀፍ ነው። መጽሀፉ እንዲሁ መመሳሰሎችን ከመዘርዘር በዘለለ በነብዩ ሙሐመድ “ﷺ” ጊዜ የትኛው የአይሁድ መጽሀፍ በየትኛው ክፍል እንደነበር እራሱ አያትትም። ከዚያም በተጨማሪ ነብዩ ሙሐመድን “ﷺ” በምን መልኩ ይህን ሊያውቁ ቻሉ? የትኛው ራባይ አስተማራቸው? የሚለውን አሰመልክቶም ምንም የሚሰጠው ማብራሪያ የለም።"
እንዲህ የሚል ማስተባበያ ለመጻፍ ብዕርኑ የሚያነሳ ሰው በነጥቡ ላይ ዕውቀት አጠርና ለሙግቱ የማይመጥን ሰው መሆኑን ከጅምሩ ይገልጣል፡፡ የኒህን ሰው መጽሐፍ ያውቀዋል? ለእያንዳንዱ ሙግቱስ ማስረጃን ላለመስጠታቸው ምን ያክል እርግጠኛ ነው? የትኛውን መጽሐፋቸውን ነው የሚያውቀው? ለማንኛውም ራባይ አብርሃም ገኢገር ለጻፏቸው መጽሕፍት በሙሉ ደረጃውን የጠበቀ ይመጥናል ያሉትን ማጣቀሻ ከበቂ በላይ ሰጥተውናል፡፡ የሕያ ያ አይበቃም ካለና ሙሉ መረጃ እንዳልሰጡ ካሰበ አሁን እኛ አለን ይህንን ክፍተት እንሞላዋለን አይዞት፤ የትኛው ከይትኛው መጽሐፍ እንደተወሰደ በድንቅ ማስረጃ ማቅረብ የምንችልበት ደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡ ለዚህ ማሳያ በቅርቡ ወንድማችን ዳንኤል ለነቢዩ ሙሐመድ ሱራ 2 እና 3 ትን ስለጻፈላቸው ሰውና ስለ ነቢዩና ስለመገለጣቸው ምን ይል እንደነበር ከቡኻሪ ሐዲስ ጠቅሶ አስነብቦናል፡፡ አብዱልሀቅ ጀሚልም በመጽሐፉ ነቢዩ ከማን እንደተማሩ፣ ማን በእርሳቸው ዙሪያ እንደነበር፣ ምንን ከማን እንዳመጡትና እንዴት እንደተጠቀሙበት፣ የራሳቸው የሆነ አንድም እንደሌለ በማስረጃ አጥግቦ አስነብቦናል፡፡ ለማንኛውም የሕያ እንዳልከው ሳይሆን ነቢዩ ሙሐመድ የትኛውን የቁርአን ክፍል ከየትኛው መጽሐፍ እንዳመጡት፣ ለዚህም ማንን ሊጠቀሙ እንደቻሉ፣ ያንንም በምን መልኩ ሊያውቁ እንደቻሉ መናገር እጅግ ቀላል ነው አታስብ፡፡
የራባይ አብርሃም ግኢገርንና እርሳቸውን ተከተሉ የሚላቸው በቁርአን ኩረጃ ላይ የሚያነሱትን ሙግት ለማስተባበል ያመጣውን ምሳሌ እንመልከት፡፡ እንዲህ አለ፡-
"የኖህ አስተምህሮና የሙሴ አስተምህሮ መመሳሰል አንደኛው ኮራጅ ነው አያስብልም። ሁለቱም መሠረታቸው ተመሳሳይ ከመሆኑ አንፃር የአስተምህሯቸው መመሳሰል የሚጠበቅ ነው። ከዚያ በዘለለ ደግሞ እርምት የሚያስፈልጋቸው አንዳንድ ቅጥፈቶችም አሉ።ለአብነት አንዳንድ ፀሀፍት ነብዩ ሙሐመድ “ﷺ” ከብሉይና አዲስ ብቻ ሳይሆን ከአይሁድ ታልሙዶችም ጭምር ወስደዋል የሚሉ ክሶችን በማቅረብ ብዙ መመሳሎችን ይጠቅሳሉ። … ከነዚህ ውስጥ ግን ምናልባት መዳሰስ የሚኖርባቸው የተወሰኑ ቅጥፈቶች ይኖራሉ። ለአብነት በቁርአን የተጠቀሰው የሰበዕ ታሪክ (በሱራ 27) በአይሁድ መጽሀፍት ውስጥ ይገኛል የሚለው የተዛባ ክስ ነው። ይገኝበታል የተባለው የመጽሀፈ አስቴር “ታርጉም” መጽሀፍ የተፃፈበትን አመት ለተመለከተ ሰው ከነአካቴው ከቁርአን በኃላ እንደሆነ ይገነዘባል። የመጀመሪያው ታርጉም የተፃፈው በ700 ገደማ ሲሆን ሁለተኛው ታርጉም ደግሞ የተፃፈው በ800 አመት ገደማ ነው። ይህ ማለት ከነብዩ ሙሐመድ “ﷺ” መሞት ከብዙ አመታት በኃላ ማለት ነው (“Esther”, The Jewish Encyclopedia ገፅ 238)
እንደ ኢንሳይክሎፒዲያ ጁዳይካ ገለፃ ከሆነ ደግሞ የዚህ መጽሀፍ ፀሀፊ የተወሰኑ የአረብኛ ፁሁፎችን እንደምንጭነት ተጠቅሞ ነበር ይለናል (Targum Sheni”, Encyclopaedia Judaica) ይህ ማለት ፀሀፊው እራሱ የነበረው ከነብዩ ሙሐመድ “ﷺ” ህልፈት ከብዙ አመታት በኃላ ሲሆን ለዚህ ፁሁፉም የተለያዩ አረብኛ ምንጮችን ተጠቅሞ ነበር።…"
ይህንን እንዳነበብኩ ከጉግል ጎልጉሎ ተርጉሞ የራሱ በማስመሰል ያሳተመው "አልተሰቀለም" ትዝ አለኝ፡፡ ይህንንም እንደዛው ጎልጉሎ ያመጣበት አለ ብዬ ነው ያሰብኩት፡፡ ራሱ አንብቦ መረጃውን የሰደረ ሰው ሚሆንማ ኖሮ ሁለቱን አውደ ጥበቦች በዚህ መልኩ አይጠቅሳቸውም ነበር፡፡ ለምን አትሉኝም?
1. “Esther”, The Jewish Encyclopedia ገፅ 238 በማለት በጠቀሰው ገጽ ላይ የሚለው ሐሳብ የለም፡፡ በገጽ 238 ላይ የተመለከተው ገጽ 237 ላይ የጀመረ "Esther, Apocryphal book" ለሚለው ማብራሪያ ነው፡፡ ይህ የመጽሐፉን እድሜ ከክርስቶስ ልደት በፊት ወደ ነበረ የመቃቢያን ዘመን ሲወስደው ያይ ነበር፡፡ ስለ አስቴር መጽሐፍ ትርጉም የተጻፈበት ዓመት የሚዘረዝረው ሐሳብ ያለው ግን ገጽ 234 ላይ ነው፡፡ ታዲያ ካልጎለጎለ በስተቀር ይህንን ቀላል ስህተት እንዴት ሊሳሳት ይችላል?
2. Targum Sheni”, Encyclopaedia Judaica ን አንብቦ ቢሆን ኖሮ ትርጉሙ ስለተጻፈበት ዓመት 700 እና 800 ያለውን አይጽፍም ነበር፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ቁጥሮች አልተጠቀሱምና፡፡

Date፡-
The date of the work cannot be determined exactly. The view of S. Gelbhaus (see bibl.) that it belongs to the amoraic period, in the fourth century, is disproved by the fact that it contains later material. P. Cassel (see bibl.) dates it in the sixth century and explains its mention of Edom to be the rule of Justinian (527–565)… L. Munk (see bibl.) puts its date still later, in the 11th century, but he gives no proof. It seems that the most acceptable view is that which places its composition at the end of the seventh or the beginning of the eighth century, a view that is strengthened by its relationship to the Pirkei de-R. Eliezer. ("Targum Sheni”, Encyclopaedia Judaica, vol 19, page 513-514)
3. "ለዚህ ፁሁፉም የተለያዩ አረብኛ ምንጮችን ተጠቅሞ ነበር" የሚለው ነው፡፡ የአረብኛን የስነ ጽሑፍ ታሪክ ቢያውቅ ኖሮ ቁርአን ማለት አለመሆኑን መረዳት በቻለ ነበር፡፡
ለማንኛውም የሕያ ለማስተባበያ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ቁርአን እንዳልተኮረጀ ማሳያ ሊሆኑ ፈጽሞ አይችሉም፡፡ ለዚህ በርካታ ነጥቦችን ማንሳት ቢቻልም ከራሱ መረጃዎች በመነሳት ጥቂት ልበል፡-
• Targum Sheni የአራማይስጥ ትርጉም ሲሆን ቀደም ብላችሁ እንዳነበባችሁት ስለተተረጎመበት ጊዜ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ጸሐፍት የተለያዩ የጊዜ መላምቶችን ሰጥተዋል፡-
ይህ አውደ ጥበብ የትርጉም ሥራው ጊዜ በጣም ተቀባይነት ያለው ብሎ ያመነው 7ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ እኛ 8ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ መሆኑን ነው፡፡ መላምት መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ ይህ ጊዜ ምንም ነቢዩ ሙሐመድ በሕይወት ያልነበሩበት ጊዜ ቢሆንም ውል ያለው የቁርአን መጽሐፍ የተጻፈበት ወቅት እንዳልነበር የቁርአን ታሪክ ያስረዳል፡፡ ራሱ የሕያ "የቁርአን አሰባሰብ"ን በተመለከተ ለተማሪዎቹ ለማስተማር የቁርአን ታሪክና ሳይንስ መጽሐፍትን ሲያገላብጥ በዚህ ጊዜ ምን ደረጃ ላይ እንደነበር ያየ ይመስለኛል፡፡ ዛሬ ላይ በአብዛኛው ሙስሊም እጅ ያለው በ1926 ዓ.ም ግብጽ ላይ እንደገና ማሻሻያ የተደረገለት የሐፍስ ቅጅ እንኳን ተጻፈ የሚባለው ከ706–796 ወይም 90–180 AH በኖረው Hafs al-Asadi al Kufi በተባለ ሰው ነው፡፡ ከዚህ ሰው በፊት የተጻፈ አንድም የቁርአን መጽሐፍ ለምልክት እንኳን ምድር ላይ የለም፡፡ ይህ በቱርኩ ሙስሊም ፕሮፌሰሮች ተረጋግጧል፡፡ የአራማይስጥ ቋንቋም እስከ መዲና ድረስ ይነገር ስለነበር የተተረጎመበትና የትርጉም መጽሐፉ በአካባቢው በነበሩ አይሁዶች ዘንድ የታወቁና የተስፋፉ ነበሩ፡፡ ስለዚህ የቁርአን ጸሐፊዎች ከእነዛ መጽሐፍት አልኮረጁም ብሎ ማሰብ ሞኝነት ይሆናል፡፡
• Encyclopedia of Islam vol 1, page 1220
" BILKlS፡- is the name by which the Queen of Sheba is known in Arabic literature. The story of the 1 Queen's visit to King Solomon (based on I Kings X, i-io, 13) has undergone extensive Arabian, Ethiopian, and Jewish elaborations and has become the subject of one of the most wide-spread and fertile cycles of legends in the Orient. … Although the Kur'an and its commentators have preserved the earliest literary reflection of the complete Bilkis legend, there is little doubt that the narrative is derived from a Jewish Midrash. This judgement is based not only on intrinsic probability and our knowledge of the general influence of the Midrashic genre on early Islam, but is also supported by: …"
ስለዚህ የንግሥቷን ታሪክ የሚጋሩና የእኔ የእኔ የሚሉት ብዙ ሕዝቦች እንደመሆናቸው ከኢስላም በፊት አገር የናኘ አፈ ታሪክ እንደነበር ከዚህ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ታሪኩ እንደተባለው የ7ኛና 8ኛ ክፍለ ዘመን ታሪክ ሳይሆን ከዛ የቀደመ ነው፡፡ ለዚህ አንድ ምሳሌ ከታሪክ አት-ጠበሪ መጥቀስ ይቻላል፡፡ በዚህ መጽሐፍ የተጠቀሰ ጡባ የሚል (the Yemeni leader who ruled between A.D. 410 and 435 and occupied Mecca) የየመን ንጉሥ ነበር፡፡ እስከ መካ ድረስ ይገዛና ይቆጣጠር ነበር፡፡ ይህ ሰው ከመዲና በወሰዳቸው ሁለት ራባዮች አማካኝነት ይሁዲነትን ተቀብሎ ነበር፡፡ ስለ ንግሥት ሳባ በቅኔዎቹ እንዲህ ይል እንደነበር ታሪክ ዘግቦታል፡-
The History of al-Tabari, vol 5, page 174.
"…Bilgis was my paternal forebear (literally, "aunt") and ruled over them until the hoopoe came to her"
ስለሆነም አፈ ታሪኩ ነቢዩ ሙሐመድ ከመወለዳቸው ከ100 ዓመት ቀድሞ የነበርና አካባቢውን ያጥለቀለቀ ነበር እንጂ ተርጁም ሸኒ ላይ የጀመረ አይደለም፡፡ ስለዚህ ነቢዩ ይህንን አፈ ታሪክ ከአይሁዳውያን አልኮረጁም ብሎ ለመንፈራገጥ መሞከር ትርፉ መላላጥ ነው፡፡
ሳሂህ ኢማን!
ቸር ይግጠመን!!

🔥2
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
🔥2
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ስቅለት በዮሴፍ ዘመን?
ቁርአንን ከታሪካዊ ቅጥፈቱ ለመታደግ የተደረገ ያልተሳካ ጥረት
***********
በዮሴፍ ዘመን ሰዎች በስቅለት መቀጣታቸውን በተመለከተ ቁርአን የፈፀመውን የታሪክ ቅጥፈት ለማስተባበል አብዱሎች እየተራወጡ ይገኛሉ (ሱራ 12፡41)፡፡ ሰለምቴ ነኝ ባዩ ኡስታዝ እንደተለመደው እጅ እጅ በሚለው የአጻጻፍ ስልቱ ባዘጋጀው ጽሑፉ ቁርአንን ለመታደግ ረጅም ትግል አድርጓል፡፡ ነገር ግን የሙግቱን ነጥብ ፈፅሞ አልተረዳም፡፡ ስለ ምን እየተወራ እንዳለ እንኳ ያወቀ አይመስልም፡፡ ይህ ርዕስ ከኛ በፊት የነበሩት ክርስቲያንና ሙስሊም ሊቃውንት ሰፊ ክርክር አድርገውበት ሙስሊሞቹ ተስፋ ቆርጠው የተውት ርዕስ በመሆኑ የአገራችን ኡስታዞች “መልስ” ብለው ከመጻፋቸው በፊት ከዚህ ቀደም ምን ተባለ? ብለው የመጠየቅ ልምድ ቢኖራቸው መልካም ነበር፡፡
ኡስታዙ በቁርአን ላይ ለሰነዘርኩት ሒስ ምላሽ በሚል በጽሑፉ ውስጥ ሁለት ሙግቶችን ነው ያቀረበው፡-
በመጀመርያ ስቅለት በዮሴፍ ዘመን ተግባራዊ ይደረግ እንደነበር የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማስረጃ አለመኖሩንና ከዮሴፍ ዘመን በጣም ዘግይቶ የተጀመረ ልማድ መሆኑን ካመነ በኋላ ፈርዖናውያን ወንጀለኛን በስቅላት እንደሚቀጡ የሚያሳይ ታሪካዊም ሆነ ሥነ-ቁፋሮአዊ መረጃ አለመገኘቱ ክስተቱን ውሸት እንደማያደርገው ሊያስረዳን ሞክሯል፡፡ ያቀረበው ሰበብም የታሪክ ተማራማሪዎች ያልደረሱበት አላህ ብቻ የሚያውቀው ምስጢራዊ ክስተት ሊኖር ይችላል የሚል ነው፡፡ ይህ የግብፃውያንን ማንነት ካለማወቅ የመነጨ ስህተት ነው፡፡ ግብፃውያን ታሪካቸውንና አኗኗራቸውን በዝርዝር በጽሑፍና በምስል በማስቀረት ይታወቃሉ፡፡ በዚህ ምክንያት የተለያዩ የአገዳደል ዓይነቶችን መዝግበው ያቆዩ ሲሆን የመስቀል ስቅላት አልተጠቀሰም፡፡ በግብፃውያን አለመጠቀሱ ብቻ ሳይሆን እስከ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ቅድመ ክርስቶስ ድረስ ስቅለት መፈጸሙን የሚያሳይ ምንም ዓይነት የጽሑፍም ሆነ የአርኪዎሎጂ ማስረጃ የለም፡፡
በሁለተኛ ደረጃ የሰጠው “ማስረጃ” መጽሐፍ ቅዱስ በዮሴፍና በሙሴ ዘመን ስቅለት መኖሩን ይናገራል የሚል ነው፡፡ ለዚህ ነው የሙግቱን ነጥብ ፈፅሞ አልተረዳም ያልኩት፡፡ እኔ እያወራሁ ያለሁት በእንጨት ላይ አንጠልጥሎ ስለመግደል (hanging) ወይም የጥንት ግብፃውያን እንደሚያደርጉት ረጅም እንጨት በሰውነት ውስጥ አሳልፎ በመውጋት ስለማንጠልጠል (impalement) አይደለም፡፡ እኔ እያወራሁ ያለሁት የስቅለት ዓይነት በቁርአን ውስጥ አሻሚ ባልሆነ ሁኔታ በግልፅ ስለተቀመጠው የስቅለት ዓይነት ማለትም በመስቀል ላይ ሰዎችን ሰቅሎ ስለመግደል (Crucifixion) ነው፡፡ በሱራ 12፡41 ላይ ዮሴፍ ህልም ሲፈታ فَيُصْلَبُ “ፈዩስዕለቡ” (ይሰቀላል) በማለት ይናገራል፡፡ በተጨማሪም ሱራ 7፡124 ላይ ፈርዖን لَأُصَلِّبَنَّكُمْ “ለ-ኡሰሊበነኩም” (በእርግጥ እሰቅላችኋለሁ) በማለት ይናገራል፡፡ ይህም በግንድ ላይ መንጠልጠልን ሳይሆን በመስቀል (በአረብኛ “ሰሊብ”፣ በእንግሊዝኛ “Cross”) ላይ መሰቀልን የሚያሳይ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ ይህ ልማድ ደግሞ ከስድስተኛው ክፍለ ዘመን ቅድመ ክርስቶስ በፊት ስለመኖሩ ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም፡፡ ለዚህ ነው የቁርአን ደራሲ ተሳስቷል ያልኩት፡፡
ኡስታዙ ይህንን ነጥብ ባለመረዳቱ ምክንያት የመስቀል ስቅለትንና መንጠልጠልን ሊያምታታ ችሏል፡፡ ቁርአንን ከታሪካዊ ቅጥፈቱ ለመታደግ ጥረት ሲያደርግ ሳለ እግረ መንገዱን እንደ ልማዱ እሱ ራሱ ሌላ ታሪካዊ ቅጥፈት ሲፈፅም ማየት ደግሞ አስቂኝ ጉዳይ ነው፡፡ “[በ]ታሪክ[ም] ሆነ [በ]ሥነ-ቁፋሮ ወንጀለኛ[ን] በስቅላት [ስለመቅጣት] ያለው መረጃ በ 559 ቅድመ-ልደት በፋርሳዊያን ጊዜ ነው…” በማለት ከተናዘዘ በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ መንጠልጠል የተነገሩትን ጥቅሶች በመጥቀስ ሁሉንም ዓይነት ስቅለት አንድ አድርጓል፡፡ (ፊደላትን በዚህ [] ምልክት ውስጥ ያስገባሁት የተወናገረውን አጻጻፉን ለማስተካከል መሆኑን ልብ በሉ፡፡) ነገር ግን በታሪክ ተመራማሪዎች መሠረት እስከ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ቅ.ክ. የታሪክም ሆነ የስነ ቁፋሮ ማስረጃ የሌለው ሁሉም ዓይነት ስቅለት ሳይሆን ቁርአን በስህተት ወደ ዮሴፍና ሙሴ ዘመን የወሰደው የመስቀል ስቅለት (Crucifixion) ነው፡፡ ሌላው የስቅለት ዓይነት በግብፅ ውስጥም ጭምር ጥቅም ላይ ይውል እንደነበር ከበቂ በላይ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ነገር ግን መሳሳት የማይሰለቸው ኡስታዝ የቁርአንን ስህተት ለመሸፈን ሲሞክር ራሱ ስህተት ፈጽሟል፤ “የቆጡን አወርድ ብላ…” እንዲሉ (A.J. Van Loon. Law and Order in Ancient Egypt: The Development of Criminal Justice from the Pharaonic New Kingdom until the Roman Dominate; Leiden University, 2014, p. 19)፡፡
በነገራችን ላይ ስቅለት (Crucifixion) በዕብራይስጥ ቋንቋ “ትስሊባ” ሲሆን “ተስሊብ” ከሚለው የአረብኛ ቃል ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት 40፡22፣ 41፡13፣ ዘዳግም 21፡22-23 እና 2ሳሙኤል 21፡12 ላይ በዮሴፍ፣ በሙሴና በዳዊት ዘመን ስቅለትን ሲጠቅስ የተጠቀመው ቃል “ታላህ” የሚል መንጠልጠልን የሚያመለክት ቃል ነው፡፡
http://www.ewnetlehulu.org/am/tasleeb/
Telegram: t.me/ewnetlehulu

❤2
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ያሕዌ አምላካችን ሊያድነን መጥቷል!
የሚልክያስ ትንቢትና የሙስሊም ሰባኪያን ስሁት ሙግት
http://www.ewnetlehulu.org/am/the-voice-crying-in-the-desert/

ክፍል አራት፡- ነጃሽ አልሰለም
ፈጠራ ሁለት፡- በነጃሺ ላይ ዕምነትን መሠረት ያደረገው አመፅና የጉዞው ዝግጅት
"ሐበሾች ተነሱበት፤ ለነጃሺም አንተ ሃይማኖታችንን ትተሀል አሉት፤ አመፁበትም፡፡ እርሱም ወደ ጀዕፈር ጀልባን በማዘጋጀት ላከበት እንዲህም አለው፡- እርሷ ላይ ውጡ እና ዝግጁ ሁኑ፤ ከተሸነፍኩ የፈለጋችሁበት ቦታ እስክትደርሱ ሂዱ፤ ካሸነፍኩ ደግሞ እዚሁ ተረጋግታችሁ ቆዩ፡፡
ከዚያም መጽሐፍ አነሳና ከእርሱ ከአላህ ውጭ አምላክ እንደሌለ እና ሙሐመድም መልዕክተኛውና ባሪያው መሆናቸውን እንደሚመሰክር ኢሳም ባሪያው መልዕክተኛውና መንፈሱ፣ ወደ መርየም የጣላት ንግግሩ መሆናቸውን በመፃፍ በቦርሳው ውስጥ አድርጎ ከልብሱ ውስጥ በስተቀኝ ከትከሻው ሥር በማድረግ ደብቆ ወደ ሐበሻዎች ዘለቀ፡፡ እነርሱም በሠልፍ ሆነው ጠበቁት፡፡" (ነጃሺ እና የሀበሻ ምድር በእስልምና መነጽር ገጽ 66)
ታሪኩ ከኢብን ኢስሀቅ የተወሰደ መሆኑ በዚሁ መጽሐፍ ላይ በዋቢነት ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ ይህ ሐሳዊ የታሪክ ጸሐፊ ከዘመናት በኋላ የፈጠረው ታሪክ ለመሆኑ በውስጡ የተጠቀጠቁት በርካታ ታሪክና ጆግራፊያዊ ስህተቶች ያሳብቃሉ፡፡ ከነዛ ሁለቱን እንመልከት፡- የመጀመሪያው "ኢሳም ባሪያው መልዕክተኛውና መንፈሱ፣ ወደ መርየም የጣላት ንግግሩ መሆናቸውን በመፃፍ" የሚለው ነው፡፡ ይህንን በክፍል ሦስት ተንተን አድርገን ተመልክተነዋል፡፡ ለማስታወስ ያክልም ይህ የኢሳን ማንነት የሚገልጸው ሐሳብ ቁርአን ውስጥ ሱራ 4 ፡ 171ኛው አንቀጽ ላይ ይገኛል፡፡ የወረደውም 626 ዓ.ም አካባቢ እንደሆነና ይህም ጀዕፈርና ጓደኞቹ ከተሰደዱ ከአሥር ዓመት በኋላ ማለት ነው፡፡ ኢሳን በተመለከተ በእነርሱ ዘመን እንዲህ ዐይነት ዕውቀት አልነበረም፡፡ ታዲያ ከዓመታት በኋላ ገና ሊወርድ ያለውን ዕውቀት ከየት አምጥቶ ሊናገር ይችላል? ስለዚህ ታሪኩ የተፈጠረ ለመሆኑ እማኝ መጥራት አያስፈልግም፡፡
ሁለተኛው "ወደ ጀዕፈር ጀልባን በማዘጋጀት ላከበት እንዲህም አለው፡- እርሷ ላይ ውጡ እና ዝግጁ ሁኑ፤ ከተሸነፍኩ የፈለጋችሁበት ቦታ እስክትደርሱ ሂዱ፤ " የሚለው ነው፡፡ የኢስላም ጸሐፍት ነጃሽ የአክሱም ንጉሥ መሆኑን ነው የሚነግሩን፡፡ ይህ አባባል ግን ነጃሽ አክሱማዊ እንዳልሆነ በግልጽ ያሳያል፡፡ ምክንያቱም አክሱም ላይ ምንም ዓይነት ከቀይ ባሕር ጋር የሚገናኝ የወንዝ ዘር የለም፡፡ ጀልባ አንሳፋፊ ወንዝ በሌለበት ንጉሡ ይህንን የመሰለ መልእክት ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡ አክሱምና ጀልባ ፈጽሞ አይተዋወቁም፡፡ በእርግጥ ብሏል የሚባል ከሆነ ታሪኩ ከአክሱም ወደ ምጽዋ ይሸጋገራል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የነጃሽ መስጊድና የመቃብር ታሪክ በውሸት ላይ የተመሰረተ ኩሸታዊ ትርክት ይሆናል ማለት ነው፡፡ እናም ነጃሽ የአክሱም ንጉሥ ሳይሆን በቀይ ባሕር አካባቢ የሚገኝ የአንድ አካባቢ ነዋሪ ሰው ነበር ማለት ነው፡፡ ይህን የሚያረጋግጥልን ምጽዋ ውስጥ የሚገኘው የነጃሽ መስጊድ ነው፡፡ (የመስጊዱን ፎቶግራፍ አያይዠላችኋለሁ) እናም ይህንን ከአክሱም ጋር አገናኝቶ መዘባረቅ የአካባቢውን መልካምድር የማያውቁ ጀሯቸው የጠገበውን ብቻ የሚጽፉ የኢስላም ታሪክ ጸሐፍት የፈጠራ ሥራ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ነጃሽ የሚባል የአክሱማዊ ንጉሥ አልነበረም የሚለውን መከራከሪያ የእውነተኛነት ማማ ላይ ያነግሠዋል፡፡ ለዚህም ነው ነጃሽ አልሰለመም የምንለው፡፡
ፈጠራ ሦስት፡- በነጃሽ ላይ ነቢዩ ያደረጉት ሶላተል ጂናዛ
ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል “የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ615-1700” ገጽ 60 ላይ እንዲህ ሲል ማስፈሩ ይታወሳል፡፡ ለነገሩ በቅርብ ሰው ሊያገኘው ከሚችለው ልጥቀስ ብዬ ነው እንጂ በርካታ የኢስላም የታሪክ ድርሳናት የዘገቡት ታሪክ ነው፡-
ነቢዩ በሐበሻ የሞተውን የነጃሽን ቀብር አላህ እያሳያቸው ከአጠገባቸው እንዳለ አስከሬን በአደባባይ ሶላት ሰግደውለታል፡፡ በሶላቱ ተካፋይ ከነበሩ ሶሓቦች መካከል ጃቢር፣ አነስ ቢን ማሊክና ዐብዱላህ ኢብኑ አባስ ስለ ክስተቱ አስተላልፈውልናል፡፡ ተከታዮቻቸውን ለሶላት ነቢዩ ሲጣሩ አንዳንድ መናፍቃን እርስ በእርሳቸው “ሙስሊም ባልሆነ ሰው ላይ እንስገድን?” ሲሉ ተናገሩ፡፡ እንዲህም አሉ፡-
“ይህን ሰው ተመልከቱ፡፡ በጭራሽ አይቶት በማያውቀውና የሃይማኖቱ ተከታይ ባልሆነ ሐበሻዊ ክርስቲያን ላይ ይሰግዳል!” ሲሉ ተናገሩ፡፡ አላህም የሐበሻዊው ንጉሥ ነጃሽ ኢስላምን መቀበሉን በማረጋገጥ የሚከተለውን የቁርአን አንቀጽ አወረደ፡-
ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ ሲኾኑ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው በዚያም ወደእነርሱ በተወረደው የሚያምኑ ሰዎች አልሉ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ (ዐሊ-ኢምራን 3 ፡ 199)
ይህ የተጠቀሰ የቁርአን አንቀጽ ነጃሽ የሞተበትንና ነቢዩ በእርሱ ላይ ሶላተል ገኢብ የሰገዱበትን ጊዜ ማወቅ ስለሚያስችል ብዙ መድከምን ያስቀራል፡፡ በአብዛኛው የኢስላም ሊቃውንት ዘንድ ሱረቱል ዐሊ-ኢምራን 625 ዓ.ም አካባቢ እንደ ወረደ ይታመናል፡፡ እንዲሁም በሌላ ወቅት የወረደ አንቀጽ እንደተቀላቀለባቸው አንዳንድ ሱራዎች (ለምሳሌ እንደ ሱራ 96) ከዚህ ወቅት በኋላ የወረደና የዚህ ሱራ አካል የተደረገ አንድም አንቀጽ ዐሊ-ኢምራን ውስጥ የለም፡፡ በቁጥር ሁለት ላይ የሚጠራጠሩ አሉ፡፡ ስለዚህ የዚህ ሱራ አንቀጾች በሙሉ ማለት ይቻላል 625 ዓ.ም ላይ የወረዱ አንቀጾች በመሆናቸው የነጃሽም ሞት በዚሁ ዓመት ላይ እንደሆነ ከአንቀጹ ለመረዳት ብዙም ዕውቀት አይጠይቅም፡፡ እዚህ ላይ ግን ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የጠቀሰው የአንቀጹ አስባብ ሁሉም የቁርአን ሊቃውንት የሚቀበሉት አመለካከት ወይም የሚቀበሉት አስባብ አለመሆኑ ብርቱ ጥያቄን ያጭራል፡፡ ሊቃውንቱ ለምን ሊቀበሉት አልቻሉም? በዚህ ወቅት ላይ ነጃሽ ስላልሞተ በሕይወት ስለነበረ ይሆን? መልሱ ወረድ ብለው ሲያነቡ ያገኙታል፡፡
እንግዲህ እንደነ ኡስታዝ አህመዲን በዚህ ሱራ አንቀጽ እንደተገለጸው የነቢዩ ሙሐመድ ለነጃሽ ለሞተ ሰው የሚደረግ ሶላት ማድረጋቸው ለነጃሽ መስለም እንደ ማስረጃ ከቀረበ፣ አላህም በቃሉ በዚህ ዓመት ላይ ሞተ ብሎ ለነቢዩ ራዕዩን ካወረደና ማረጋገጫ ከሰጠ ለሁለት ጉዳይ አስተማማኝ መረጃ አገኘን ማለት ነው፡-
የመጀመሪያው የነጃሽ መስለም ትርክት ከታሪክ ጸሐፍቱ ልብ የተወለደ ሐሰተኛ ታሪክ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ለዚህ ራሱን ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን ምስክር ልጥራ፡፡ ከላይ በጠቀስኩት መጽሐፉ ስለ ሱራ 3 ፡ 199 ብቻ ሳይሆን የዚህን ተቃራኒ ነጃሽ የሞተበትን ዓመት በማያሻማ ሁኔታ አስቀጧል፡-
“በሐበሻ ነጃሽ መሞቱን በዕለቱ መልአኩ ጅብሪል (ገብርኤል) ለነቢዩ ሙሐመድ ነገራቸው፡፡ ነጃሽ አስሐማ የሞተው ኦክቶበር/ኖቬምበር 630 (ረጅብ ወር 9ኛ ዓ.ሂ) ነበር፡፡ እርሱ በሞተ ዕለት ነቢዩ ወደ ወቂእ የሶሐቦች ቀብር ስፍራ ሄደው ሶላተል ጋኢብሰግደውበታል፡፡” (የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ615-1700 ገጽ 55)

በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ምን የሚሉት ነው? ነጃሽ መች ነው የሞተው? 625 ዓ.ም ላይ ወይስ ከአምስት ዓመታት በኋላ 630 ዓ.ም ላይ? ይህ ተቃርኖ እንዴት መጣ? ነው ወይስ ነቢዩ የሰገዱት ከአምስት ዓመት በኋላ የሚሞተውን ሞት እያሰቡ ነበርን? ኡስታዙ ይህንን ሲከታትብ አላስተዋለውም ነበር? ውድ አንባቢ የቁርአን ሊቃውንቱ ኡስታዝ የጠቀሰውን የሱራ 3 ፡ 199 አስባብ ለምን ሊቀበሉት እንዳልፈለጉ አሁን ግልጽ ሆነለዎት ይሆን? አዎን ይህንን የመሰለ ተቃርኖ እንደሚፈጥር ስላወቁ ብቻ ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ነጃሽ ሰለመ ብለው ቢያወሩ እንዴት ሊታመኑ ይችላሉ? ለዚህ ነው ነጃሽ አልሰለመም የምለው፡፡
ሁለተኛው ከአምስት ዓመት በኋላ የሚሆንን ክስተት አሁን ላይ እንደሆነ አድርጎ የሚናገር ከሆነ ቁርአን የአላህ ቃል ላለመሆኑ እንካችሁ ማስረጃዬን ማለት መሆኑ የገባቸው አልመሰለኝም፡፡ ስለዚህ ነጃሽ ሰለመ የሚለውን ትርክት ከታሪክ ጸሐፍቱ ልብ የተወለደ ሐሰተኛ ታሪክ መሆኑ እሙን ነው፡፡ በእርግጥ የቁርአን መለኮታዊ ቃልነት ፈተና ውስጥ መውደቅ የሚጀምረው በዚህ ብቻ ሳይሆን ከሱራው ስያሜ ነው፡፡ ለጊዜው ይህ ይቆይና ወደ ነጃሽ ልመለስ፡፡ በሙስሊሞች ዘንድ ቁርአን መለከታዊ ቃል እንደሆነ ይታመናል፡፡ ታዲያ አላህ ከአምስት ዓመት በኋላ ሊሞት ያለውን ሰው አሁን እንደሞተ አድርጎ ለነቢዩ ይህንን አንቀጽ በማውረዱ የሐሰት ትርክት ተባባሪ ሆኗል፡፡ ይሁንና አላህ እውነተኛው አምላክ ከሆነ እንዲህ ዓይነት ቅጥፈት ሊፈጽም ከቶውን አይችልም፡፡ የነቢዩና የታሪክ ጸሐፍቱ ቅጥፈት ብቻ ነው፡፡ ይህም ቁርአን መለኮታዊ ቃል ላለመሆኑ ማሳያ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ነጃሽ ሰልሞ ነበር የሚለው ትርክትም ልብ ወለድ እንጂ ነጃሽስ አልሰለመም፡፡
ይቀጥላል!
ሳሂህ ኢማን ነኝ
እወዳችኋለሁ በመጨረሻው ክፍል በሰላም ያገናኘን፤ ሰላሙን ሁሉ ተመኘሁላችሁ!