Audio
በዩቲዩ መከታተል ላልቻሉ ወገኖች በአነስተኛ መጠን የተዘጋጀ፡፡ በተሻለ ጥራት ለማድመጥ የዩቲዩብ ገጻችንን ይጎብኙ፡፡
ለምን አልሰለምኩም? via @like
ኢየሱስ “አለመሰቀሉን” የሚያመለክቱ ጥንታውያን መዛግብት ይገኙ ይኾንን?
አንዳንድ ሙስሊሞች የክርስቶስን ስቅለት የሚያስተባብል ማስረጃ ያገኙ መስሏቸው የኖስቲሲዝምን ጽሑፎች ሲጠቅሱ እየተመለከትን ነው፡፡ በኢየሱስ ምትክ ሌላ ሰው ተሰቅሏል የሚለው ግምት በእስልምና የተጀመረ አይደለም፡፡ ኖስቲሳውያን የተሰኙ የእምነት ቡድኖች ይህንን ያምኑ ነበር፡፡ ኖስቲሲዝም (Gnosticism) በሁለተኛውና በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ተከታዮችን አፍርቶ የነበረ የኑፋቄ ቡድን ሲሆን አጀማመሩንና የተጀመረበትን ዘመን በተመለከተ በሊቃውንት መካከል ስምምነት የለም፡፡ አንዳንዶቹ ከአይሁድ ኑፋቄያዊ ቡድኖች የተገኘ እንደሆነ ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ ክርስቲያናዊ አውድ ይሰጡታል፡፡ ሙሉ በሙሉ አረማዊ ስረ መሠረት እንዳለው የሚናገሩ ሊቃውንትም አሉ (Geisler, Encyclopedia of Christian Apologetics; p. 504)፡፡ ኖስቲክ (Gnostic) የሚለውን ቃል ለመጀመርያ ጊዜ የተጠቀመው ሄንሪ ሞር የተሰኘ በ17ኛው ክ.ዘ. የኖረ ሰው ሲሆን “ዕውቀት” የሚል ትርጉም ካለው ኖሲስ (Gnosis) ከሚለው የግሪክ ቃል የተዋቀረ ነው (Britannica, Encyclopedia of World Religions; p. 380)፡፡ ኖስቲሲዝም በተሰኘው እምነት ስር የሚመደቡ ብዙ ቡድኖች የሚገኙ ሲሆን ከክርስትና የሚለዩዋቸው ዋና ዋና ትምህርቶቻቸው የሚከተሉት ናቸው፡-
• የብሉይ ኪዳን አምላክ ከአዲስ ኪዳን አምላክ የተለየ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን አምላክ ክፉና ውሱን ሲሆን የአዲስ ኪዳን አምላክ ሁሉን ቻይ ነው፡፡
• ፍጥረት የተፈጠረው በሶፍያ (ጥበብ) ውድቀት ምክንያት ነው፡፡
• ቁስ የተባለ ሁሉ ክፉ ነው፡፡
• ኢየሱስ በሥጋ አልመጣም፣ በመስቀል ላይ አልሞተም፣ ትክክለኛው ኢየሱስ መንፈስ ነው፡፡
• የመንፈስ ትንሣኤ እንጂ የሥጋ ትንሣኤ የለም፡፡ (Geisler, p. 504)
ስለ ኖስቲሳውያን ከጥንት ቤተ ክርስቲያን አበው ጽሑፎች ብዙ መረጃዎችን የምናገኝ ሲሆን በ1945 ዓ.ም. ነጅ ሐማዲ በተባለ ቦታ የኖስቲሳውያን እምነቶች የተንጸባረቁባቸው ብዙ መጻሕፍት በመገኘታቸው ምክንያት ስለ እነርሱ ያለን መረጃ ከፍ ብሏል፡፡ ከነዚህ መጻሕፍት መካከል “የቶማስ ወንጌል” የተሰኘው መጽሐፍ ይገኝበታል (Britannica, Encyclopedia of World Religions; p. 380)፡፡ በቁርአን ውስጥ የሚገኘው ኢየሱስ በህፃንነቱ ከጭቃ ወፍ ሠርቶ ስለማብረሩ የሚናገረው ታሪክ ከዚህ ወንጌል ላይ የተወሰደ ነው (The New Testament Apocrypha, vol. 1, rev. ed. by W. Schneemelcher, trans. R. McL. Wilson, Westminster / John Knox, 1991, p. 444)፡፡
እነዚህ የእምነት ቡድኖች ከክርስትና ያፈነገጡ ሲሆኑ ኢየሱስ ትክክለኛ የሰው አካል እንዳልነበረው የሚያምኑ ናቸው፡፡ ትክክለኛ የሰው አካል ካልነበረው ደግሞ ሊሰቀል አይችልም፡፡ ባሲለደስ የተሰኘ የሁለተኛው ክፍለ ዘመን ኖስቲሳዊ የቀሬናው ስምዖን በኢየሱስ ምትክ መሰቀሉን ጽፏል፡፡ በዚህም መሠረት ስምዖን ሲሰቀል ኢየሱስ አጠገባቸው ቆሞ ሲስቅ ነበር፡፡ ንፁህ ሰው ሲሰቀል ሳለ ኢየሱስ ደግሞ መንፈስ ስለሆነ ስለማያዩት ቆሞ ሲስቅ አስቡት፡፡ እንዲህ ያለውን ተረት ከማስረጃ በመቁጠር የሚያናፍሱ ሙስሊሞች ሕሊናቸውን ከወዴት ጥለውት ይሆን? በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ማኒ የተሰኘ ሦርያዊ ሰው ኢየሱስ ከሞት ያስነሳው የናይን ከተማ መበለት ልጅ በምትኩ መሰቀሉን ጽፏል (Geisler, p. 147)፡፡ እነዚህ ግምቶች እንደ እስላማዊው ግምት ኹሉ በሥነ መለኮታዊ ፍላጎት ላይ የተመሠረቱ ሲሆኑ ምንም ዓይነት ታሪካዊ መሠረት የሌላቸው ከንቱ ተረቶች ናቸው፡፡ በወንጌላት ውስጥ ከተጻፉት የዐይን ምስክሮች ዘገባዎች ጋር ይጣረሳሉ (ማቴዎስ 27፣ ማርቆስ 14፣ ሉቃስ 23፣ ዮሐንስ 19)፤ እንደዚሁም ከቀዳሚያን የሮም፣ የአይሁድና የግሪክ ዘገባዎች ጋር ይጣረሳሉ፡፡ በአንደኛው ክፍለ ዘመን በክርስትና ወዳጆችም ሆነ ባላንጣዎች የተጻፈ ክርስቶስ መሰቀሉን የሚክድ ቅንጣት ታክል ዘገባ የለም፡፡ በኢየሱስ ቦታ ሌላ ሰው መተካቱን የሚናገሩ በኖስቲዝም ተፅዕኖ ያደረባቸው ግለሰቦች የጻፏቸው ጽሑፎች ከ150 ዓመታት በኋላ ነበር መታየት የጀመሩት (Geislere, p. 147)፡፡
ኖስቲሳውያን ኢየሱስ የሚዳሰስ አካል እንደሌለው ስለሚያምኑ ሊሰቀል አይችልም ይላሉ፤ ነገር ግን ደግሞ የስቅለቱ ትዕይንት መፈፀሙን መካድ ስለማይችሉ በምትኩ ሌላ ሰው መሰቀሉን በመናገር ደካማ እምነታቸውን ከታሪካዊ ዘገባ ጋር ለማስታረቅ ሞክረዋል፡፡ ኖስቲሳውያን የዚህ ዓለም ፈጣሪ ክፉ አምላክ (ዲያብሎስ) እንደሆነ ያስተምራሉ፡፡ ሙስሊሞች ኢየሱስ የሚዳሰስ አካል እንዳልነበረው የሚያምኑትንና ፈጣሪያቸው ሸይጧን መኾኑን የሚያስተምሩትን የእምነት ቡድኖች ግምት የክርስቶስን ስቅለት ከሚያሳዩት የተትረፈረፉ ዘገባዎች ይልቅ እንደ ተዓማኒ ማስረጃ መቁጠራቸው በእጅጉ አስገራሚ ነው፡፡ “የጨነቀው ዱቄት ከንፋስ ጋር ይወዳጃል” አሉ!

ዛሬ እግር ጥሎኝ በሙስሊሞች ግሩፕ ውስጥ ገብቼ አንድ ኦዲዮ ሰማሁ፡፡ በኦድዮው ውስጥ ሲናገር የሚደመጠው ሰው ክርስቲያን እንደነበረና እስልምናን እንደተቀበለ ይናገራል፡፡ ከክርስትና ለምን እንደወጣ ሲናገር መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ እንደሚጋጭ ማረጋገጡን፣ እንደ ዳዊት ያሉ ነቢያት ኃጢአትን ስለሠሩ ምሳሌ ሊሆነው የሚችል ገፀ ባሕርይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለማግኘቱን፣ በነ ጳውሎስ የተሰበከው ክርስትና ከሮማውያን የተቀዳ መሆኑን፣ የኢየሱስን አምላክነት መጠራጠሩን፣ ወዘተ. ይዘረዝራል፡፡ ከዚያስ? ከዚያማ ያልገባውን እንደመጠየቅና ማስረጃዎች እንደማጤን በግጭ የተሞላ በመሆኑ ምክንያት የሙስሊሙ ዓለም እንዳይፈርስ በመስጋት ኡሥማን ኤዲት ያስደረገውንና ሌሎች ቅጂዎችን ሰብስቦ በማቃጠል ለማስተካከል የሞከረውን፣ በአል ሐጃጅ ዘመን እንደገና የታረመውን፣ በ 1923 ዓ.ም. በግብፅ ሊቃውን እንደገና ኤዲት የተደረገውን፣ ከዚህ ሁሉ ጥረት በኋላ 26 የሚሆኑ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ቅጂዎች ያሉትን “የማይጋጭ” መጽሐፍ ቁርአንን አገኘ፡፡ ነቢያት ሰብዓዊ ድካም ያለባቸው መሆናቸውን በማወቅ ኃጢአት የሌለበትን ቅዱሱን ኢየሱስን እንደመከተል ከ 9 ዓመት ህፃን ጋር የተኛውን፣ የማደጎ ልጁን ሚስት ቀምቶ ያገባውን፣ የጦር ምርኮኛ ሴቶችን እንዲደፍሩ ለወታደሮቹ ፈቃድ የሰጠውን፣ ንፁሃንን ሲገድልና ሲያስገድል የኖረውን፣ በዝርፍያና በቅሚያ ራሱን ሲያበለፅግ የኖረውን፣ ድግምት ተሠርቶበት ሰይጣን ሲጫወትበት የኖረውን፣ “ቅዱሱን ነቢይ” ሙሐመድን አገኘ፡፡ የሮማውያንን አምልኮና ርክሰት ባለመቀበላቸው ምክንያት ሲሰደዱ ከኖሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ትምሕርት ይልቅ እንደ ሐጅ፣ ረመዳን፣ ጠዋፍ፣ ካዕባ፣ ቂብላና የመሳሰሉትን ከአረብ ፓጋኖች የኮረጀው እስልምና በለጠበት፡፡ ለኛ ካለው ታላቅ ፍቅር የተነሳ ከሰማይ ወርዶ፣ ሥጋ ለብሶ በመካከላችን በመኖር ፍቅሩን ከገለጠልን አምላክ ይልቅ ራሱን መግለጥ የማይችል፣ የማይታወቅ፣ ሰዎችን ሆነ ብሎ ለገሃነም የፈጠረ፣ አታላይ የሆነ አላህ የተሰኘ የአረብ ፓጋኖች የምናብ አምላክ በለጠበት፡፡ ወገኖቼ እንዲህ ካለው መታወር ይሰውረን!
ስለ ኢየሱስ መሞት
ሰሞኑን ደግሞ የሕያ የተባለው አብዱል ከዚህ በፊት ጓደኛው ወሒድ ሞክሮት የነበረውን ሙግት አምጥቶ ስለ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ግራ መጋባቱን እና አለማወቁን አሳይቶናል። የ Basiledes እና ሌሎች Gnostic የተባሉትን አስተምህሮት እንደ ሙግት ማቅረቡ አስቂኝ ሆኖ ሳለ በዚህ ጉዳይ ላይ ለጓደኛው የጻፍነውን አለማንበቡ ደግሞ ignorant ያደርገዋል። ባሲለደስ የጻፈው መጽሐፍ አንድም አሁን የለም። ያለው በearly church fathers መጻሕፍት ውስጥ ስለ እሱ የተጻፉ ጥቂት ስንኞች ብቻ ናቸው። እነኚህ ኖስቲኮች ደቀ መዛሙርትም አልነበሩም። ለማንኛውም ለሙግቶቹ ከዚህ በፊት መልስ ሰጥተናል። አሁን ግን፣ እሱ ታማኝ ካልሆኑ የኖስቲኮች ሙግት ይሆኑኛል በሚል ሐሳብ ኢየሱስ አልሞተም ብሎ ከተጠቀማቸው፣ እኛ ደግሞ #ከእስልምና ታማኝ ምንጮች #ኢየሱስ_ሞቶ_ከሞትም_ተነስቷል የሚል ቃል እናስነብበዋለን።
የ አልጠበሪ ታሪክ ቅጽ 4 ገጽ 123
According to Ibn Humayd- Ibn Ishaq- an impeccable authority- Wahb b. Munabbih al-Yamani: GOD ALLOWED JESUS, THE SON OF MARY, TO DIE AT THREE O'CLOCK IN THE DAY; then He took him unto himself.
"ኢብን ሁመይድ ከ ኢብኑ ኢሻቅ እንደዘገበው (ዘገባውም በጣም ታማኝ ወይም ከማያከራክር ስልጣን impeccable) አላህ የ መሪያም ልጅ ዒሳን (ኢየሱስ) ከ ቀኑ በ 3 ሰአት ላይ #እንዲሞት አደረገ። ከዛም ወደላይ አነሳው።"
(ተፍሲር አል ጦበሪ ሱራ 3:55 ላይም ይመልከቱ)
ስለዚህ በ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ዙሪያ ግራ የተጋባው ከ 600 አመታት በኋላ የመጣው እስልምና ነው እንጂ ክርስትና አይደለም።
@Jesuscrucified

የቁርአን መበረዝ
በጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት
“በክፍለ ዘመናት መካከል ከ114 ሱራዎች መካከል አንድም ቃል አልተለወጠም፡፡ ስለዚህ ቁርአን ከአሥራ አራት ክፍለ ዘመናት በፊት ለሙሐመድ የተገለጠ በሁሉም ረገድ ልዩና ተዓምራዊ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡”
እንዲህ ያሉ ቃላት ለዘመናት ከሙስሊሞች ዘንድ ሲደመጡ ኖረዋል፡፡ ሙስሊሞች ቁርአን እንከን በሌለው መንገድ ተጠብቆ ለዘመናችን እንደበቃ በፍፁም መተማመን ይናገራሉ፡፡ ቁርአን ከሰማይ የወረደ ዘላለማዊ የአላህ ቃል መሆኑን ከማመናቸው አንፃር በቁርአን ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች መካከል የአንድ ፊደል ልዩነት እንኳ ሊኖር መቻሉን አለማመናቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ታድያ ይህ እምነት ማስረጃ ይኖረው ይሆን?
ዶ/ር ዳንኤል ብሩቤከር የተሰኙ የቁርአን ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ሊቅ በቅርቡ ባሳተሙት “Corrections in Early Qurʾān Manuscripts: Twenty Examples” በተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ እውነቱ ሙስሊሞች ከሚናገሩት በተጻራሪ እንደሆነ በማስረጃ አረጋግጠዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሜይ 21/ 2019 የተለቀቀ ሲሆን እስከ ዛሬ ድረስ ሙስሊም ሊቃውንት ከሕዝባቸው የሰወሯቸውን አስደንጋጭ ግኝቶች በውስጡ ይዟል፡፡
እኚህ የቁርአን ሊቅ ምርምሩን ያደረጉት ከ7ኛው እስከ 10ኛው ክፍለ ዘመን በተገለበጡት የቁርአን ጽሑፎች ላይ ነው፡፡ ግኝታቸውን በተመለከተ እንዲህ በማለት ጽፈዋል፡-
“በጥናት ወረቀቴ ውስጥ 800 የሚሆኑ ተጨባጭ እርማቶችን የመዘገብኩ ብሆንም በአሁኑ ወቅት ግን በሺህዎች የሚቆጠሩትን አግኝቻለሁ፤ ይህ ጉዳይ ማለቂያ ያለውም አይመስልም፡፡”
በማስከተል በፒ ዲ ኤፍ ባዘጋጀነው ጽሑፍ ውስጥ የሚገኘው ከብዙ በጥቂቱ የቀረበ ነው፡፡ ጽሑፉን በማውረድ ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ 👉👇 http://www.ewnetlehulu.org/am/q-mss-corruption-brubaker/

ለምን አልሰለምኩም? pinned «የቁርአን መበረዝ በጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት “በክፍለ ዘመናት መካከል ከ114 ሱራዎች መካከል አንድም ቃል አልተለወጠም፡፡ ስለዚህ ቁርአን ከአሥራ አራት ክፍለ ዘመናት በፊት ለሙሐመድ የተገለጠ በሁሉም ረገድ ልዩና ተዓምራዊ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡” እንዲህ ያሉ ቃላት ለዘመናት ከሙስሊሞች ዘንድ ሲደመጡ ኖረዋል፡፡ ሙስሊሞች ቁርአን እንከን በሌለው መንገድ ተጠብቆ ለዘመናችን እንደበቃ…»
Audio
በዩቲዩብ መከታተል ላልቻላችሁ በአነስተኛ መጠን የተዘጋጀ፡፡ ለተሻለ ጥራት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይጎብኙ፡፡
አድሃ በኢንጂል
🐏
🐏
በመላው ዓለም የሚገኙት ሙስሊሞች በየዓመቱ የአል-አድሃን በኣል ያከብራሉ፡፡ ይህ በኣል በሙስሊሞች የጨረቃ አቆጣጠር መሠረት ዙል ሒጃ በመባል በሚታወቀው ወር 10ኛ ቀን ላይ ይውላል፡፡ አድሃ የሚለው ቃል ዳሂያ ወይንም መሥዋዕት ከሚለው የአረብኛ ሥረወ ቃል የተገኘ ነው፡፡ የአል-አድሃ በኣል የመሥዋት በኣል ወይንም ታላቁ በኣል፣ ዒድ አል ከቢር በመባል ይታወቃል፡፡ በአል-አድሃ በኣል ዕለት ሙስሊሞች ፈጣሪ የአብርሃምን ልጅ የዋጀበትን ክስተት ለማስታወስ በግ ይሠዋሉ፡፡ ይህ ክስተት የክርስቶስን ቤዛዊ መሥዋዕትነት ከሚያመለክቱ የተውራት ተምሳሌታዊ ትንቢቶች መካከል አንዱ ነው። የቀድሞ ሙስሊም በነበረው በወንድም ፉአድ መስሪ የተጻፈውን ይህንን ግሩም ቡክሌት ያንብቡ…
http://www.ewnetlehulu.org/am/way-of-salvation/adha/