ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ስለ ኢየሱስ መሞት

ሰሞኑን ደግሞ የሕያ የተባለው አብዱል ከዚህ በፊት ጓደኛው ወሒድ ሞክሮት የነበረውን ሙግት አምጥቶ ስለ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ግራ መጋባቱን እና አለማወቁን አሳይቶናል። የ Basiledes እና ሌሎች Gnostic የተባሉትን አስተምህሮት እንደ ሙግት ማቅረቡ አስቂኝ ሆኖ ሳለ በዚህ ጉዳይ ላይ ለጓደኛው የጻፍነውን አለማንበቡ ደግሞ ignorant ያደርገዋል። ባሲለደስ የጻፈው መጽሐፍ አንድም አሁን የለም። ያለው በearly church fathers መጻሕፍት ውስጥ ስለ እሱ የተጻፉ ጥቂት ስንኞች ብቻ ናቸው። እነኚህ ኖስቲኮች ደቀ መዛሙርትም አልነበሩም። ለማንኛውም ለሙግቶቹ ከዚህ በፊት መልስ ሰጥተናል። አሁን ግን፣ እሱ ታማኝ ካልሆኑ የኖስቲኮች ሙግት ይሆኑኛል በሚል ሐሳብ ኢየሱስ አልሞተም ብሎ ከተጠቀማቸው፣ እኛ ደግሞ #ከእስልምና ታማኝ ምንጮች #ኢየሱስ_ሞቶ_ከሞትም_ተነስቷል የሚል ቃል እናስነብበዋለን።

የ አልጠበሪ ታሪክ ቅጽ 4 ገጽ 123

According to Ibn Humayd- Ibn Ishaq- an impeccable authority- Wahb b. Munabbih al-Yamani: GOD ALLOWED JESUS, THE SON OF MARY, TO DIE AT THREE O'CLOCK IN THE DAY; then He took him unto himself.

"ኢብን ሁመይድ ከ ኢብኑ ኢሻቅ እንደዘገበው (ዘገባውም በጣም ታማኝ ወይም ከማያከራክር ስልጣን impeccable) አላህ የ መሪያም ልጅ ዒሳን (ኢየሱስ) ከ ቀኑ በ 3 ሰአት ላይ #እንዲሞት አደረገ። ከዛም ወደላይ አነሳው።"
(ተፍሲር አል ጦበሪ ሱራ 3:55 ላይም ይመልከቱ)

ስለዚህ በ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ዙሪያ ግራ የተጋባው ከ 600 አመታት በኋላ የመጣው እስልምና ነው እንጂ ክርስትና አይደለም።
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified