ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ወሒድ የተሰኘ አንድ ሰለምቴ ነኝ ባይ አብዱል “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” የሚለውን ንግግር በተመለከተ በኛ ጽሑፍ ውስጥ የሚገኝ ነጥብ በመጥቀስ በስድብ የታጀበ አጭር ጽሑፍ ለቋል፡፡ የጽሑፉ ሙሉ ቃል ሲቀነስ የአረብኛው ኮተት እንዲህ የሚል ነው፡-
-----
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 4417
አነሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ በሑድ ጦርነት የፊት ጥርሳቸው ተሰበረ፣ እራሳቸው ቆሰለ፤ ደም ከፊታቸው ይጠርጉ ነበር፤ እንዲህ አሉ፦ “ያ ህዝብ እንዴት ሊድን ይችላል ነብዩን እያቆሰለ እና ጥርሱን እየሰበረ ወደ አላህ ይፀልይለታል? በዚያን ጊዜ የላቀው እና ክቡሩ አላህ፦ 3፥128 “አላህ በእነርሱ ላይ ይቅርታ እስኪያደርግ ወይም እነርሱ በዳዮች ናቸውና እስኪቀጣቸው ድረስ ለአንተ ከነገሩ ምንም የለህም” የሚለውን አንቀጽ አወረደ።
ነብያችንየጸለዩት ጸሎት ደግሞ ምን እንደሆነ ዐብደላህ ከእርሳቸው የሰማውን በሦስተኛ መደብ በሚቀጥለው ቁጥር እንዲህ ይነግረናል፦
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 4418
ለእኔ የአላህን መልእክተኛ ስመለከት ታዩኝ የተናገሩትን ሰማዋቸው፦ ነብይ በህዝቡ ሲደበድቡት፣ ደም ከፊቱ ሲጠርግ፦ “ጌታዬ ሆይ ህዝቦቼን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርታ አድርግላቸው” አለ።
አንዳንድ ቂል መሃይማን “ጌታዬ ሆይ ህዝቦቼን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርታ አድርግላቸው” የሚለውን ከዚህ ጥቅስ ጋር ለማዛመድ ሞክረዋል፦
ሉቃስ 23፥34 ኢየሱስም፦ *አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው* አለ።
የሚያጅበው ግን ይህንን ንግግር እንኳን ኢየሱስ ሊናገረው ይቅርና የሉቃስ ወንጌል ላይ ባሉት የግሪክ እደ-ክታባት ላይ ሽታው የለም። ይህንን የአዲስ ኪዳን ለዘብተኛ ምሁር ዶክተር ሄርማን እና ጽንፈኛ ምሁር ጀምስ ኃይት ተናግረዋል። NIV የግርጌ ማስታወሻ ላይም፦ “Luke 23፥34 some early manuscripts do not have this sentence” በማለት እርማችሁን እንድታወጡ አርድቷችኃል፡፡
---
እኛ የጠቀስነው ሐዲስ ሳሒህ አል-ቡኻሪ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እንዲህ ይላል፡-
Bukhari, Volume 9, Book 84, Number 63:
Narrated 'Abdullah: As if I am looking at the Prophet while he was speaking about one of the prophets whose people have beaten and wounded him, and he was wiping the blood off his face and saying, "O Lord! Forgive my people as they do not know."
አብዱላህ እንዳስተላለፈው፡- ወደ ነቢዩ (ሙሐመድ) እያየሁ ሳለሁ ከነቢያ መካከል አንዱ ሕዝቦቹ ደብድበውት ባቆሰሉት ጊዜ ደሙን ከፊቱ ላይ እየጠረገ እንዲህ ሲል የተናገረውን ተናገሩ፡- “ጌታ ሆይ! ሕዝቤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው፡፡”
ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው አብዱላህ የተባለው የሙሐመድ ተከታይ ባስተላለፈው ዘገባ መሠረት ሙሐመድ ከቆሰለ በኋላ ይህንን ንግግር ተናግሯል፡፡ ነገር ግን ሐዲሱ ግልፅ አድርጎ እንዳስቀመጠው ሙሐመድ ንግግሩን ለመናገር የመጀመርያው ሰው አልነበረም፡፡ ከእርሱ በፊት አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ ነቢይ ተናግሮታል፡፡ የኛ ጥያቄ እንዲህ ያለ ንግግር የተናገረ ሙስሊሞች የሚቀበሉት “ነቢይ” ከኢየሱስ ውጪ ማን ነው? የሚል ነው፡፡ ንፁሃን ሰዎችን በእንቶ ፈንቶ ጉዳዮች ሲያርድና ሲያሳርድ የኖረው ሙሐመድ ሰዎችን ለመግደል በወጣበት አውደ ውጊያ ውስጥ ሆኖ ለዚያውም ቆስሎና ጥርሱ ረግፎ ሳለ እንዲህ ያለ ንግግር መናገሩ የማይመስል ቢሆንም ንግግሩ በሐዲሱ ውስጥ ተጠቅሷል፤ ስለዚህ ሙስሊሞች እንዲህ ያለ ንግግር የተናገረ ከኢየሱስ ሌላ እነርሱ የሚቀበሉት “ነቢይ” ማን እንደሆነ እንዲነግሩን ጠይቀናቸዋል፡፡ ሆኖም ወሒድ ለስድብ የተፈጠረ የሚመስለውን ምላሱን በከንቱ ከማስረዘም በዘለለ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ይልቁኑ ሐዲሱ በሙሐመድ የተጠቀሰው አባባል ከእርሱ በፊት በኖረ ሌላ ነቢይ ተነግሮ የነበረ መሆኑን በግልፅ ተናግሮ ሳለ ቡኻሪ ውስጥ የሚገኘውን ሐዲስ ሳይሆን ሌላ ሐዲስ በመጥቀስ አልፎ ተርፎም ትርጉሙን በማዛባት ለማድበስበስ ሞክሯል፤ ሐሳዊው ወሒድ፡፡
ይህ ሰው በገዛ ሃይማኖቱ ላይ ከዋሸ በኋላ በክርስትና ላይም እንዲህ ሲል ዋሽቷል፡- “የሚያጅበው ግን ይህንን ንግግር እንኳን ኢየሱስ ሊናገረው ይቅርና የሉቃስ ወንጌል ላይ ባሉት የግሪክ እደ-ክታባት ላይ ሽታው የለም፡፡” ከዚያም አንዳንድ ጥንታውያን የግሪክ ቅጂዎች ይህንን ንግግር ይዘው አለመገኘታቸውን በተመለከተ NIV የእንግሊዘኛ ትርጉም በግርጌ ማስታወሻው ላይ ያስቀመጠውን ይጠቅሳል፡፡ ማስታወሻው እንዲህ የሚል ነው፡- “some early manuscripts do not have this sentence.” ስለዚህ በ NIV መሠረት ይህ አባባል በአንዳንድ ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ውስጥ አልተጠቀሰም፡፡ “በአንዳንድ አልተጠቀሰም” ማለት በሁሉም አልተጠቀሰም ማለት አይደለም፡፡ ወሒድ ግን “የሉቃስ ወንጌል ላይ ባሉት የግሪክ እደ-ክታባት ላይ ሽታው የለም” በማለት አረፈው፡፡ ወሒድ አላዋቂ፣ ሲከፋም ቀጣፊ ነው፡፡ ይህ ጥቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ውስጥ የንባብ ልዩነቶች (Textual Variants) ሆነው ከተመዘገቡት መካከል አንዱ ቢሆንም በብዙ ጥንታውያን የግሪክ የእጅ ጽሑፎች ውስጥ ይገኛል፡፡ ቁርአንን ጨምሮ የትኛውም ጥንታዊ መጽሐፍ ከእንዲህ ያሉ ችግሮች የጸዳ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሊቃውንት ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎችን በማመሳከር ትክክለኛው ንባብ የትኛው እንደሆነ ያሳውቃሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ረገድ ቁርአንን ጨምሮ ከየትኛውም ጽሑፍ ጋር ለውድድር ሊቀርብ በማይችልበት ሁኔታ ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ስለሚገኝ ጥበቃውና አስተላላፉ እጅግ አስተማማኝ ነው፡፡
ለማንኛውም ይህ አብዱል በእስላማዊ ምንጮችም ሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሲዋሽ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፤ ሐሳዊነቱንም በአደባባይ አሳይቷል፡፡ ጌታ ቢፈቅድ የያሕያን ኩረጃዎች እንዳጋለጥነው ሁሉ ይህ ሰው ከዊኪ ፒድያ በቀጥታ በተረጎማቸው ጽሑፎቹ ውስጥ የተሰገሰጉትን ቅጥፈቶቹን በቅርቡ ማጋለጥ እንደምንጀምር ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
----
ዳንኤል
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)


ሙስሊሞች ይህንን መላ ምት መቀበላቸው ምን ችግር ያስከትላል?

1. ከቁርአንና ከሐዲስ መጻሕፍት ጋር ይጋጫል፡፡ የሙሴ ተውራት በመሐመድ ዘመን በአይሁድና በክርስቲያኖች እንጅ እንደነበረ ቁርአንና እስላማዊ ሐዲሳት ይመሰክራሉ (ሱራ 2፡40-41፣ 2፡89፣ 2፡91፣ 2፡101፣ 10፡94፣ 7፡169፣ 2፡44፣ 2፡113፣ 2፡121፣ 3፡93፣ 3፡113፣ 5፡66፣ 5፡68፣ 5፡43-44፣ 5፡65፣ 2፡4፣ Sunan Abu Dawud, Book 38, Number 4434)፡፡ በታሪክ የታወቀው ተውራት (ቶራህ) የዶክሜንተሪ ሃይፖቴሲስ አቀንቃኞች እየተቿቸው የሚገኙት የአምስቱ መጻሕፍት ስብስብ በመሆኑ ሙስሊሞች ይህንን መላምት ከተቀበሉ የገዛ እምነታቸውን ውድቅ አደረጉ ማለት ነው፡፡
2. የመላምቱ ዋልታና ማገር “የእስራኤላውያን አሓዳዊነት በዝግመተ ለውጥ ከመድብለ አማልክታዊነት የተገኘ በመሆኑ የሙሴን ያህል ዕድሜ የለውም” የሚል ነው (Geisler, pp. 1390-91)፡፡ ነገር ግን ከአብርሃም ጀምሮ፣ ልጁ ይስሓቅና የይስሐቅ ልጅ ያዕቆብ እንዲሁም ከእርሱ የተገኙት አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱን አምላክ ያመልኩ እንደበር ሙስሊሞች ስለሚያምኑ ሊያስኬዳቸው አይችልም፡፡ መላምቱን መቀበል አብረሃምና ነገዶቹ አንዱን አምላክ አያውቁትም ማለት ይሆናልና፡፡
3. የመላምቱ ዋና ዓላማ እግዚአብሔር አምላክ በሙሴ በኩል የሠራቸውን ተዓምራትና እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ያደረጉትን ጉዞ ማጣጣል በመሆኑ ሙስሊሞች ይህንን መላምት ከተቀበሉ እነዚህን እውነታዎች ሊክዱ ነው፡፡ እነዚህን እውነታዎች መካድ ደግሞ ቁርአንን መካድ ነው (ሱራ 28፡30-32፣ 26፡61-68)፡፡
4. አንድ ሰው የቁርአንንም ክፍሎች በዚህ መንገድ ከፋፍሎ ተመሳሳይ መላምት መፍጠር ይችላል፡፡ ለምሳሌ ያህል ረብ የሚለው የፈጣሪ ስም በ 11 የቁርአን ሱራዎች ውስጥ አይገኝም (24፣ 48፣ 49፣ 58፣ 61፣ 62፣ 77፣ 88፣ 95፣ 104፣ 112)፡፡ እንዲሁም አላህ የሚለው ስም በ 18 ሱራዎች ውስጥ አይገኝም (54፣ 55፣ 56፣ 68፣ 75፣ 78፣ 83፣ 89፣ 92፣ 93፣ 94፣ 99፣ 100፣ 105፣ 106፣ 108፣ 113፣ 114)፡፡ ስለዚህ ረብ ያልተጠቀሰባቸውን፣ አላህ ያልተጠቀሰባቸውን እንዲሁም ረብና አላህ ተቀላቅለው የተጠቀሱባቸውን ሱራዎች ይዘን ከሦስት የተለያዩ ምንጮች የተቀዱ ናቸው ልንል እንችላለን፡፡ ዶክሜንተሪ ሃይፖቴሲስ ማለት በአጭሩ ይህ ነው፡፡ ሙስሊም ወገኖች ቁርአንን በተመለከተ እንዲህ ያለውን ግምታዊ አመለካከት የማይቀበሉ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን ፈጥነው ተቀብለው የሚያስተጋቡበት ምክንያት ምን ይሆን?
አብዛኞቹ የሙስሊም ሰባኪያን ሙግቶች ከለዘብተኛ የሥነ መለኮት ሊቃውንት ምንጮች የተቃረሙ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህ ሰባኪያን ሙግቶቹ ለክርስትናም ሆነ ለእስልምና የጋራ የሆኑ አመለካከቶችን በመካድ ላይ የተመሠረቱ መሆናቸውን ባለማስተዋል ኮርጀው የሚያቀርቡ ሲሆን በሒደቱም የገዛ ሃይማኖታቸውን አፈር ድሜ ሲያበሉ ማየት አዝናኝ ትዕንት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ በብዙ ጽሑፎቻቸው ውስጥ ከሚደጋግሟቸው ሙግቶች መካከል አንዱ “ዶክሜንተሪ ሃይፖቴሲስ” የተሰኘው ነው፡፡

ዶክሜንተሪ ሃይፖቴሲስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይዘትና የአጻጻፍ ስልቶች በመነሳት የደራሲያኑን ማንነት እንዲሁም የተጻፉበትን ዘመን ለመገመት የሚሞክር የጥናት ዘዴ ሲሆን ለዚህ የጥናት ስልት ፈር ቀዳጅ በመባል የሚታወቀው ጀርመናዊው ሊቅ ጁሊየስ ወልሃውሰን ነው (1844-1918 ዓ.ም.)፡፡ የዚህ መላ ምት ዋና ትኩረት የኦሪትን ተዓምራዊ ይዘትና የሙሴን ጸሐፊነት ማጣጣል ሲሆን መሠረቱም የእስራኤላውያን የአሓዳዊነት እምነት በዝግመተ ለውጥ ከመድብለ አማልክታዊነት ወደ አሓዳዊነት ያደገ ነው የሚል ነው፡፡ በወልሃውሰን ግምት መሠረት አምስቱ ብሔረ ኦሪት አራት ምንጮች ያሏቸው ሲሆን ያሕዌያዊ፣ ኤሎሂማዊ፣ ዘዳግማዊና ካህናዊ (Jehovist, Elohist, Deuteronomist, Priestly) በማለት ሰይሟቸዋል፡፡ በአጭሩ J-E-D-P በመባል የሚታወቁ ሲሆን እንደየ ቅደም ተከተላቸው የዘጠነኛው፣ የስምንተኛው፣ የስድስተኛውና የአምስተኛው ዓ.ዓ. ምንጮች ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምቱን አስቀምጧል፡፡ (Norman Geislere: Encyclopedia of Christian Apologetics, p. 1391)

ክርስቲያኖች ይህንን መላምት ለምንድነው የማይቀበሉት?

1. መላምቱ በታሪክና በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ውድቅ ነው፡፡ የጥንት አይሁድ፣ ለምሳሌ ያህል የአንደኛው ክፍለ ዘመን ሊቃውንት የነበሩት ፋይሎና ጆሲፈስ (ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን) የአምስቱ ብሔረ ኦሪት ጸሐፊ ሙሴ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም መጻሕፍቱ በሙሴ የተጻፉ መሆናቸውን ይመሰክራል፡፡ ከአምስቱ መጻሕፍት አራቱ፣ ማለትም ዘጸአት፣ ዘሌዋውያን፣ ዘኁልቁና ዘዳግም በሙሴ የተጻፉ መሆናቸውን መጻሕፍቱ ራሳቸው ይመሰክራሉ (ዘጸ. 24፡4፣ ሌዋ. 1፡1፣ 4፡1፣ 5፡14፣ ዘኁ. 1፡1፣ 33፣2፣ ዘዳ. 1፡1፣ 4፡44፣ 29፡1)፡፡ መጽሐፈ ኢያሱን ጨምሮ ሌሎች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትም ይህንኑ ምስክርነት ያረጋግጣሉ ( ኢያ. 1፡7፣ መሳ. 3፡4፣ 1ነገ. 2፡3፣ 2ነገ 14፡6፣ ዕዝ. 3፡2፣ ነህ. 1፡7፣ መዝ. 103፡7፣ ዳን. 9፡11፣ ሚል. 4፡4)፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ሐዋርያቱ ከእነዚህ መጻሕፍት ከመጥቀሳቸውም ባለፈ በሙሴ የተጻፉ ስለመሆናቸው ተናግረዋል (ማቴ. 4፡7-10፣ 8፡4፣ ማር. 7፡10፣ 12፡26፣ ሉቃ. 20፡28፣ 24፡44፣ ዮሐ. 7፡19፣ ሐ.ሥ. 3፡22፣ 28፡23፣ ሮሜ 10፡19፣ 1ቆሮ 9፡9፣ ዕብ. 9፡19-20)፡፡ ስለዚህ የታሪክና የቅዱት መጻሕፍት ምስክርነቶች መላ ምቱን ውድቅ ያደርጉታል፤ ተዓማኒነታቸውንም ለመጠራጠር የሚያበቃ ምክንያት የለም፡፡
2. J-E-D-P የጽሑፍም ሆነ የአርኪዎሎጂ ድጋፍ የሌለው መላ ምት ነው፡፡ አምስቱ የሙሴ መጻሕፍት በተለያዩ ዘመናትና በተለያዩ ቦታዎች የተጻፉ መሆናቸውን የሚያሳይ ምንም ዓይነት የጽሑፍም ሆነ የአርኪዎሎጂ ማስረጃ የለም፡፡
3. ጁሊየስ ወልሃውሰን የእስራኤላውያን የአሓዳዊነት እምነት በዝግመተ ለውጥ ከመድብለ አማልክታዊነት ወደ አሓዳዊነት ያደገ ነው ብሎ ያስቀመጠውን የመላምቱን መነሻ ውድቅ የሚያደርጉ የአርኪዎሎጂ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ስለዚህ የአሓዳዊነት ይዘት ያላቸው መጻሕፍት በሙሴ ዘመን ሊኖሩ እንደማይችሉ መናገር ከአርኪዎሎጂ ማስረጃ ጋር መላተም ነው፡፡ (Ibid., 1392)
4. የመላምቱ “ማስረጃ” እንደሆነ የተነገረው በመጻሕፍቱ ውስጥ የሚገኘው የአጻጻፍ ልዩነት በቀላሉ ሊብራራ የሚችልና ውኀ የማይቋጥር ነው፡፡ የመላምቱ ፈር ቀዳጅ የነበረው ወልሃውሰን “ከያሕዌያዊ ምንጭ የተገኙ” ብሎ የፈረጃቸው ክፍሎች “ኤሎሂም” ከሚለው ይልቅ “ያሕዌ” የሚለውን የእግዚአብሔርን የተፀውዖ ስም የሚጠቀሙ ሲሆን “ከኤሎሂማዊ ምንጭ የተገኙ” ያላቸው ደግሞ “ኤሎሂም” የሚለውን የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል ዘፍጥረት 1 ኤሎሂምን የሚጠቀም ሲሆን 2 ደግሞ ያሕዌን ይጠቀማል፡፡ እንዲህ እያለ የመጽሐፉን የተለያዩ ክፍሎች “ከያሕዌያዊና ከኤሎሂማዊ ምንጮች የተገኙ” በማለት ከፋፍሏቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁለቱ ስሞች ያላቸውን አገባብ ስንመለከት ኤሎሂም የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት፣ ያሕዌ ደግሞ እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር ሕብረት ማድረጉንና የሰዎች አምላክ መሆኑን በሚያሳዩ ክፍሎች ውስጥ ጥቅም ላይ ውለው እንመለከታለን፡፡ ስለዚህ ሙሴ ሁለቱን ስሞች በተለያየ አገባብ መጠቀሙ የተለያዩ መልእክቶችን ከማስተላለፍ አንፃር በዓላማ ያደረገው እንጂ ተቺዎች እንደሚሉት እነዚያ ክፍሎች ከተለያዩ ምንጮች ስለተቀዱ አይደለም፡፡ “ያሕዌ” በተጠቀሰባቸው የዘፍጥረት አብዛኞቹ ክፍሎች ውስጥ “ኤሎሂም” የሚለው ተደራቢ ሆኖ “ያሕዌ-ኤሎሂም” ተብሎ ተጠቅሶ መገኘቱም የትወራውን መሠረተ ቢስነት የሚያረጋግጥ ሌላ ማስረጃ ነው፡፡ ካህናዊ ሕግጋትና ሌሎች ሕግጋት ልዩነት ስላላቸው የአጻጻፍ ልዩነቶቹን መነሻ በማድረግ “ካህናዊና ዘዳግማዊ ምንጮች” ብሎ ያስቀመጠው ግምትም የሚያስኬድ አይደለም፡፡ እጅግ ደካማ ነው፡፡


ሙስሊሞች ይህንን መላ ምት መቀበላቸው ምን ችግር ያስከትላል?

1. ከቁርአንና ከሐዲስ መጻሕፍት ጋር ይጋጫል፡፡ የሙሴ ተውራት በመሐመድ ዘመን በአይሁድና በክርስቲያኖች እንጅ እንደነበረ ቁርአንና እስላማዊ ሐዲሳት ይመሰክራሉ (ሱራ 2፡40-41፣ 2፡89፣ 2፡91፣ 2፡101፣ 10፡94፣ 7፡169፣ 2፡44፣ 2፡113፣ 2፡121፣ 3፡93፣ 3፡113፣ 5፡66፣ 5፡68፣ 5፡43-44፣ 5፡65፣ 2፡4፣ Sunan Abu Dawud, Book 38, Number 4434)፡፡ በታሪክ የታወቀው ተውራት (ቶራህ) የዶክሜንተሪ ሃይፖቴሲስ አቀንቃኞች እየተቿቸው የሚገኙት የአምስቱ መጻሕፍት ስብስብ በመሆኑ ሙስሊሞች ይህንን መላምት ከተቀበሉ የገዛ እምነታቸውን ውድቅ አደረጉ ማለት ነው፡፡
2. የመላምቱ ዋልታና ማገር “የእስራኤላውያን አሓዳዊነት በዝግመተ ለውጥ ከመድብለ አማልክታዊነት የተገኘ በመሆኑ የሙሴን ያህል ዕድሜ የለውም” የሚል ነው (Geisler, pp. 1390-91)፡፡ ነገር ግን ከአብርሃም ጀምሮ፣ ልጁ ይስሓቅና የይስሐቅ ልጅ ያዕቆብ እንዲሁም ከእርሱ የተገኙት አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱን አምላክ ያመልኩ እንደበር ሙስሊሞች ስለሚያምኑ ሊያስኬዳቸው አይችልም፡፡ መላምቱን መቀበል አብረሃምና ነገዶቹ አንዱን አምላክ አያውቁትም ማለት ይሆናልና፡፡
3. የመላምቱ ዋና ዓላማ እግዚአብሔር አምላክ በሙሴ በኩል የሠራቸውን ተዓምራትና እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ያደረጉትን ጉዞ ማጣጣል በመሆኑ ሙስሊሞች ይህንን መላምት ከተቀበሉ እነዚህን እውነታዎች ሊክዱ ነው፡፡ እነዚህን እውነታዎች መካድ ደግሞ ቁርአንን መካድ ነው (ሱራ 28፡30-32፣ 26፡61-68)፡፡
4. አንድ ሰው የቁርአንንም ክፍሎች በዚህ መንገድ ከፋፍሎ ተመሳሳይ መላምት መፍጠር ይችላል፡፡ ለምሳሌ ያህል ረብ የሚለው የፈጣሪ ስም በ 11 የቁርአን ሱራዎች ውስጥ አይገኝም (24፣ 48፣ 49፣ 58፣ 61፣ 62፣ 77፣ 88፣ 95፣ 104፣ 112)፡፡ እንዲሁም አላህ የሚለው ስም በ 18 ሱራዎች ውስጥ አይገኝም (54፣ 55፣ 56፣ 68፣ 75፣ 78፣ 83፣ 89፣ 92፣ 93፣ 94፣ 99፣ 100፣ 105፣ 106፣ 108፣ 113፣ 114)፡፡ ስለዚህ ረብ ያልተጠቀሰባቸውን፣ አላህ ያልተጠቀሰባቸውን እንዲሁም ረብና አላህ ተቀላቅለው የተጠቀሱባቸውን ሱራዎች ይዘን ከሦስት የተለያዩ ምንጮች የተቀዱ ናቸው ልንል እንችላለን፡፡ ዶክሜንተሪ ሃይፖቴሲስ ማለት በአጭሩ ይህ ነው፡፡ ሙስሊም ወገኖች ቁርአንን በተመለከተ እንዲህ ያለውን ግምታዊ አመለካከት የማይቀበሉ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን ፈጥነው ተቀብለው የሚያስተጋቡበት ምክንያት ምን ይሆን?
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለሰልማን መጽሐፍ ምላሽ ክፍል 4 በዚህ ሊንክ ገብተው ያንብቡ http://www.ewnetlehulu.org/am/our-answers/sel-book-review-4/
ሰምታችኋል? ሙስሊሞች ቁርአን የፈጣሪ ቃል መሆኑን ለማረጋገጥ አዲስ መንገድ አገኘን እያሉ ነው። እርሱም ድመት ቁርአን አትረግጥም የሚል ነው። የምቀልድ መስሏችሁ ነው? እዩትማ https://m.youtube.com/watch?v=eSOWhIv5lq0
ለሰልማን መጽሐፍ ምላሽ ክፍል 4 በዚህ ሊንክ ገብተው ያንብቡ 👇👉 http://www.ewnetlehulu.org/am/our-answers/sel-book-review-4/
“አይሻ ስትናገር፡- የአላህ መልእክተኛ ላይ ድግምቱ ሰርቶባቸው፣ ከሚስቶቻቸው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈጽሙ እንደሚያደርጉት እንዲሁ ብቻቸውን ያደርጉ ጀመር፡፡ እርሳቸው ከሚስታቸው ጋር እየፈጸሙ ይመስላቸዋል፣ ግን አልነበረም፡፡ ሌላዋ ሚስታቸው ሶፍያም እንዲህ ዓይነት ተግባር የሚያስፈጽመው በጣም ዓደገኛው የድግምት አይነት ነው አለች፡፡” (ሳሂህ አል-ቡኻሪ 71 ፡ 660 ቅጽ 7)
መሐመድ እውነተኛ ነቢይ ከነበረ ሰይጣን እንዴት በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሊጫወትበት ቻለ?
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰባው ሱባዔና የሙስሊም ሰባኪያን የኩረጃ ሙግት
http://www.ewnetlehulu.org/am/seventy-weeks-of-daniel/

ወሒድ የተሰኘ አንድ አብዱል በዳንኤል ትንቢት የተነገረው “ሰባ ሱባዔ” የኢየሱስን መምጣት እንደማያመለክት ሙግት አቅርቧል፡፡ ይህ ሙግት ከረበናተ አይሁድ የተቀዳ ሲሆን ከክርስቲያናዊው ትርጓሜ አኳያ ውኀ የሚያነሳ አይደለም፡፡ አስደናቂው ትንቢት እንዲህ ይነበባል፡-

“ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል። ስለዚህ እወቅ አስተውልም ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፡፡ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች። ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል ጥፋትም ተቀጥሮአል።” ዳንኤል 9፡24-27

በዚህ ትንቢት መሠረት ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፡፡ ስለዚህ በጥቅሉ ስድሳ ዘጠኝ ሱባዔ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሱባዔ (ሸቡአ) በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ሰባት ዓመታት ናቸው፡፡ በአይሁድ አቆጣጠር መሠረት እነዚህ በአጠቃላይ 483 ዓመታት ናቸው፡፡ የኢየሩሳሌም ቅጥር እንዲጠገን በ444 ዓ.ዓ. ንጉሥ አርጤክስስ ትእዛዝ ካወጣበት ጊዜ ጀምሮ ሲቆጠር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ተሰቀለበት ዘመን ያመጣናል፡፡

ወሒድ ለዚህ ያቀረበው የማስተባበያ ሙግት ብዙ ስህተቶችን የሸከፈ ነው፡፡ የመጀመርያው ስህተት “ትእዛዙ የወጣበትን ዘመን” ወደ ኤርምያስ ዘመን መውሰዱ ነው፡፡ በዚህም መሠረት “ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ” የሚለውን በንጉሥ አርጤክስስ ዘመን የወጣውን ትእዛዝ ሳይሆን እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም እንደገና መሠራት ለነቢዩ ኤርምያስ የሰጠውን ቃል እንደሚያመለክት ይነግረናል፡፡ ወሒድ የጠቀሰው የኤርምያስ ትንቢት 29፡10-14 እንዲሁም 30፡18 ላይ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ኤርምያስ ስለ ኢየሩሳሌም እንደገና መሠራት የተናገረው ትንቢት ንጉሥ ሴዴቅያስ ገና ሳይማረክ በ593 ዓ.ዓ ገደማ የተነገረ ነው፡፡ ወሒድ ግን “ይመጣል” የተባለው መሢህ ቂሮስ መሆኑን ለማረጋገጥ እንዲመቸው አርባ ዘጠኝ ዓመታትን የያዙትን ሰባቱን ሱባዔዎች ለብቻቸው ከነጠለ በኋላ ቆጠራውን ሴዴቅያስ ከተማረከበትና የኤርምያስ አገልግሎት ከተገባደደበት ከ586 ዓ.ዓ ጀምሮታል፡፡ “ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ቃሉ የመጣው ከተማይቱ በፈረሰችበት በ 586 ቅድመ-ልደት ነው” በማለትም ከእውነት የራቀ ነገር ይናገራል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ኤርምያስ ትንቢቱን የተናገረው ሴዴቅያስ ገና ንጉሥ ሳለ ነበር፡፡ ይህ የወሒድን ስሌት የሚያዛባ ወሳኝ ነጥብ ነው፡፡

ዳንኤል በተናገረው ትንቢት መሠረት ቆጠራው የሚጀምረው “ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት” ጊዜ እንጂ ትንቢት ከተነገረበት ጊዜ አይደለም፡፡ ይሁን እንኳ ብንል ነቢዩ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎን ምርኮና ስለ ኢየሩሳሌም እንደገና መሠራት ከነቢዩ ኤርምያስ በማስቀደም ተናግሮ ሳለ ቆጠራውን ከእርሱ ከመጀመር ይልቅ ከኤርምያስ የምንጀምርበት ምክንያት ግልፅ አልተደረገም (ኢሳ. 14፡1-6፣ 48፡17-20፣ 54)፡፡ ምናልባት “ዳንኤል የኤርምያስን መጽሐፍ ሲያነብ ስለነበር” የሚል ምላሽ ይሰጠን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሙግቱ “ትእዛዙ መለኮታዊ ቃል ነው” በሚል እሳቤ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ እንዲህ ያለ ምላሽ አያስኬድም፡፡ ትእዛዙ “መለኮታዊ ቃል” ከሆነ ኢሳይያስ መለኮታዊውን ቃል አስቀድሞ ተናግሮታል፡፡ ስለዚህ ስሌቱ መጀመር ያለበት ከዚያ ነው፡፡ ሲጀመር ደግሞ መለኮታዊ ቃል በጊዜ ተገድቦ “ከዚህ ዓመት ይጀምራል” ስለማይባል የዳንኤል አነጋገር “የነገሥታትን ትእዛዝ ወይም አዋጅ” የተመለከተ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ ወደ ጎን አድርገን በወሒድ መረዳት መሠረት እንሒድ ብንል እንኳ ቆጠራውን መጀመር ያለብን ኤርምያስ ለመጀመርያ ጊዜ ስለ ጉዳዩ ከተናገረበት ጊዜ እንጂ ከኤርምያስ የአገልግሎት ፍጻሜ ዘመን አይደለም፤ ምክንያቱም “…ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ” ተብሎ በግልፅ ተጽፏልና፡፡ ትእዛዙ የኤርምያስ ትንቢት ነው ከተባለ ኤርምያስ ትንቢቱን የተናገረው ሴዴቅያስ ገና ንጉሥ ሳለና ኢየሩሳሌም ከመፍረሷ በፊት በመሆኑ ስሌቱ ከቂሮስ ጋር አይገጥምም፡፡ እውነቱ ይህ ከሆነ ደግሞ የወሒድን ሙግት ውኀ በላው ማለት ነው፡፡

የዳንኤልን ትንቢት በአስተውሎት ስናነበው የሰውየው ሙግት ትርጉም አልባ መሆኑ ይበልጥ ግልፅ ይሆንልናል፡፡ ትንቢቱን ደግመን እናንብበው፡- “…ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፡፡” በትንቢቱ መሠረት መሢህ የሚመጣው ከሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ በኋላ፣ ማለትም ከስድሳ ዘጠኝ ሱባዔ በኋላ ነው (7+62=69)፡፡ ስለዚህ መሲሁ የሚመጣው ከ 483 ዓመታት በኋላ ነው (69×7=483)፡፡ ነገር ግን ወሒድ እንደነገረን መሢሁ ቂሮስ ከሆነና ስሌቱ የሚጀምረው ከ605 ዓ.ዓ ከሆነ ውጤቱ ወደ 122 ዓ.ዓ ያመጣናል (605-843=122)፡፡ በዚህ ጊዜ እንግዲህ ቂሮስ ከሞተ ክፍለ ዘመናት አልፈዋል፡፡

ሁለተኛው ስህተቱ እብራይስጡን በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም ለገዛ ሙግቱ ችግር መፍጠሩ ነው፡፡ “…እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፡፡ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች” የሚለውን “ከዚያም በስድሳ ሁለት ሱባዔ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ጎዳና እና ከቅጥር ጋር ትሠራለች” በማለት በመተርጎም የኢየሩሳሌምን መሠራት ከአራት ክፍለ ዘመናት በላይ አራዝሟል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ኢየሩሳሌም በነህምያ ዘመን በአርጤክስስ ፈቃድ መሠራት ጀምራ በተወሰኑ ዓመታት ውስጥ የተሟላች ከተማ ሆናለች፡፡ የወሒድ ትርጓሜ የእብራይስጡን ሐሳብ የማያንጸባርቅ ከመሆኑም በተጨማሪ የኢየሩሳሌምን መሠራት ከአራት ክፍለ ዘመናት በላይ በማራዘም ከታሪክ ጋር ይጋጫል፡፡ ነገር ግን ዘግይቶ በለቀቀው ጽሑፍ የመጀመርያ ሐሳቡን ረስቶት እንዲህ በማለት ተጻራሪ ሐሳብ ያቀርባል፡-

“…የመቅደሱ ግንባታ የተጠናቀቀው በ 516 ቅድመ-ልደት ነው። ከመጀመሪያው ከቂሮስ አዋጅ ከ 539 እስከ የመቅደሱ ግንባታ መጠንናቀቅ 516 ድረስ 23 ዓመት እንጂ 49 ዓመት አይደለም፥ 539-516= 23 ዓመት ይሆናል።”

አቶ ወሒድ፤ ከራስ ጋር መጋጨት የነቢዩ ሱና በመሆኑ አንፈርድብህም፡፡
“እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች” የሚለውን ደግሞ ከምርኮ ዘመን ጀምሮ ያለውን የጭንቀት ዘመን እንደሚያመለክት ይናገራል፤ የምርኮው ዘመን የጭንቅ ዘመን እንደነበረ የሚናገሩ ጥቅሶችንም ጠቅሷል፡፡ ጥቅሱ “በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች” ስለሚል መሠራትን እንጂ መፍረስን አይጠቅስም፡፡ የምርኮው ዘመን የጭንቀት ዘመን መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ኢየሩሳሌም ዳግመኛ ስትሠራ የነበረው ተቃውሞና ጭንቀት ደግሞ በነህምያ መጽሐፍ ውስጥ በስፋት ተዘግቧል፡፡ “በጭንቀት ዘመን … ትሠራለች” የሚለውን ወደ ኋላ ወስዶ ከመፍረስ ዘመን ጋር ማጣበቅ የወሒድን አንብቦ የመረዳት አቅም ጥያቄ ላይ ይጥላል፡፡ የመፍረስ ዘመን የራሱ የሆነ ጭንቀት እንደነበረበት ሁሉ የመሠራት ዘመንም የራሱ የሆነ ጭንቀት ነበረው፡፡ ጥቅሱ በመሠራት ዘመን ስለነበረው ጭንቀት የሚናገር በመሆኑ “ጭንቀት” የሚል ቃል በሁለቱም ዘመናት ስለተጠቀሰ ብቻ ቆጠራውን ከምርኮ ዘመን መጀመር ትርጉም አይሰጥም፡፡

ሦስተኛው ስህተቱ የጥቅሱን ሰዋሰዋዊ ይዘት የሚያዛባ የዘመን ስሌት መጠቀሙ ነው፡፡ የመሲሁን መገደል በተመለከተ የተነገረውን እንዲህ በማለት ተርጉሞታል፡-

በ 605 ቅድመ-ልደት”BC” ከተማይቱ ተማረከች፥ የጭንቀቱ ዘመኗ ጀመረ። ከ 605 ጀምረን 62 ሱባዔ ስንቆጥር 171 ቅድመ-ልደት”BC” ይሆናል። ቅድሚያ 62 ሱባዔ 434 ዓመት ነው፥ 62×7=434 ይሆናል። እንግዲህ ከምርኮ 605 ጀምሮ 434 ዓመት ስንቆጥር 171 ቅድመ-ልደት”BC” ነው። 605-434=171 ይሆናል። በዚህ ጊዜ የተገደለ መሢሕ አለ፦ ዳንኤል 9፥26 “ከስድሳ ሁለት ጊዜ በኋላ መሢሕ ይገደላል” ፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም።

“ተገደለ” እያለን ያለው “መሢህ” ሊቀ ካህኑ አንያስ ወልደ ስምዖን ነው፡፡ አንጥያኮስ ኤጲፋኔስ በ 170 ዓ.ዓ. ሣልሳዊ አንያስን አስገድሎት ነበር፡፡ ወሒድ የመጀመርያዎቹን ሰባት ሱባዔዎች በተመለከተ ከ 586 ዓ.ዓ ጀምሮ እስከ ቂሮስ ዘመን ማስላቱን እናስታውስ፡፡ በማስከተል የሚመጡትን 62 ሱባዔዎችን በተመለከተ ከተቀራራቢ ዓመት በመነሳት አስልቷል፡፡ ጥቅሱ ግን በግልፅ “ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል” በማለት ይናገራል፡፡ ሰባቱና ስድሳ ሁለቱ ሱባዔዎች ተከታትለው የሚመጡ እንጂ ተደራራቢ አይደሉም፡፡ “እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል” ተብሎ የመሢህ መምጫ ከስድሳ ዘጠኝ ሱባዔዎች በኋላ እንደሆነ በግልፅ ተነግሮ ሳለ ስድሳ ሁለቱን ሱባዔዎች በሰባቱ ላይ እንደ መደመር አንዱን አንስቶ በሌላው ላይ መደረብ የጥቅሱን ሰዋሰዋዊ አወቃቀር መናድ ነው፡፡ የጥቅሱን ተፈጥሯዊ ንባብ ተከትለን ከኼድን ትንቢቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለት የሚያሳይ እንጂ የሣልሳዊ አንያስን መገደል የሚያመለክት እንዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ የእብራይስጡን ሰዋሰዋዊ አወቃቀር ለማየት ይህንን ገፅ ይጠቀሙ፡- https://biblehub.com/text/daniel/9-25.htm፡፡ የወሒድን ትርጓሜ የሚደግፍ ምንም ነገር የለም፡፡ የጥቅሱ ሰዋሰዋዊ አወቃቀር የማያፈናፍን መሆኑን የተረዱ ብዙ የአይሁድ ሊቃውንት “መሢህ” የአይሁድ ደጋፊ የነበረውን ንጉሥ አግሪጳን ወይንም በሮማውያን ሥልጣኑን የተቀማውን ሊቀ ካህን ሊያመለክት እንደሚችል ይናገራሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች ይህንን አመለካከት ለማፅደቅ “ይገደላል” ተብሎ የተተረጎመውን “ይከሬት” የሚለውን ቃል አሳስተው ይተረጉማሉ፡፡

በማስከተል ደግሞ ይህ አብዱል ከመሢህ መገደል በኋላ ከተማይቱንና መቅደሱን እንደሚያጠፋ የተነገረው አለቃ አንጥያኮስ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ነገር ግን ቀደም ሲል እንደተመለከትነው አንጥያኮስ በዚህ ትንቢት ውስጥ ቦታ ስለሌለው ከመሢህ መገደል በኋላ የመጣው አለቃ ሮማዊው ጀነራል ቲቶ (ታይተስ) ነው፡፡ በትንቢቱ ውስጥ ይፈጸማሉ የተባሉት ተግባራት በአንጥያኮስ አልተፈፀሙም፡፡ በትንቢቱ መሠረት “የሚመጣው አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ” ተብሎ የተነገረ ቢሆንም አንጥያኮስ መቅደሱን ከማርከስ በዘለለ ከተማይቱንም ሆነ መቅደሱን አላጠፋም፡፡ ሮማዊው ቲቶ ግን ከተማይቱንም መቅደሱንም ሙሉ በሙሉ አጥፍቷል፡፡ የአንጥያኮስ ስደት በጣት ለሚቆጠሩት ዓመታት ብቻ የቆየ በመሆኑ “ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል” ከተባለው ትንቢት ጋር አይጣጣምም፡፡ በሮማዊው የጦር መሪ በቲቶ አማካይነት ኢየሩሳሌምና መቅደሱ የፈረሱበት ሁኔታ በአይሁድ ታሪክ እጅግ የከፋው ውድመት ሲሆን በዚህም ምክንያት የኢየሩሳሌምና የመቅደሱ ባለቤትነት ጥያቄ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የጦርነት ሰበብ እንደሆነ መቀጠሉ ጥርጥር የለውም፡፡ ይህም ትንቢቱ አንጥያኮስን ሳይሆን ቲቶን እንደሚያመለክት በግልፅ ያስገነዝባል፡፡

እንደሚገደል የተነገረው መሢህ ሣልሳዊ አንያስ ነው የሚሉ ወገኖች ቁጥር 24 ላይ የተባለውን ልብ ማለት ያስፈልጋቸዋል፡-

“ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።” (ዳን. 9፡24)

ለግልጽነት ያህል በአዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንብበው፡-

“ዐመፃን ለማቆም፣ ኃጢአትን ለማስወገድ፣ በደልን ለማስተሰረይ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፣ ራዕይንና ትንቢትን ለማተምና እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለ ተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል፡፡”

ስለዚህ ሰባው ሱባዔ ከምርኮ ዘመን ጀምሮ እስከ አንጥያኮስ መምጣትና ሣልሳዊ አንያስ መገደል ያለውን ዘመን የሚመለከት ከሆነ እነዚህ ትንቢቶች እንዴትና መቼ እንደተፈጸሙ ሊያስረዳን የሚችል ሰው ይኖር ይሆን? እነዚህ ትንቢቶች በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሥራ የተፈጸሙና በዳግም ምፅዓቱ ወደ ምልዓት የሚመጡ መሆናቸው መጽሐፍ ቅዱስን አንብቦ ከሚያውቅ ሰው ኹሉ የተሰወረ አይደለም፡፡

የመጨረሻው ሱባዔ ጉዳይ በመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት መካከል አከራካሪ ርዕስ ነው፡፡ አንዳንዶች በቲቶ ወረራ ዘመን ፍፃሜን እንዳገኘ የሚናገሩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ወደፊት በመጨረሻው ዘመን ከክርስቶስ ተቃዋሚ መምጣት ጋር ተያይዞ ይፈፀማል ይላሉ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከዘመነ ፍጻሜ ጋር አያይዞ ትንቢቱን ተርጉሞታል (ማቴ. 24፡15)፡፡ የሆነው ሆኖ ሰባኛው ሱባዔ በስድሳ ዘጠኙ ትርጓሜ ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡ በስድሳ ዘጠነኛው ሱባኤ ላይ መሢህ እንደሚመጣና እንደሚገደል በግልፅ ተጽፏል፤ እርሱ ደግሞ ከጌታ ኢየሱስ ውጪ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም፡፡
👍1
የአዋጁን ጅማሬ በተመለከተ ይህ አብዱል በክርስቲያኖች መካከል መግባባት አለመኖሩን ለመግለፅ ሞክሯል፡፡ ኢየሩሳሌምን የተመለከቱ አዋጆች በተለያዩ ዘመናት መውጣታቸው የሚታወቅ ቢሆንም በግልፅ የከተማይቱ ቅጥር እንዲሠራ የፈቀደው በ444 ዓ.ዓ የወጣውና በነህምያ አማካይነት ተፈፃሚ የሆነው የአርጤክስስ አዋጅ በመሆኑ ብዙ ክርስቲያን ሊቃውንት ስድሳ ዘጠኙን ሱባዔዎች ማስላት የሚጀምሩት ከዚያ ነው፡፡ አራቱ አዋጆች የሚከተሉት ናቸው፡-

የቂሮስ አዋጅ፡- ዕዝራ 1:1-3፣ (538 ዓ.ዓ)፡፡ አዋጁ መቅደሱ እንዲገነባና አይሁድ ወደ ምድራቸው እንዲመለሱ የሚናገር ነው፡፡
የዳርዮስ አዋጅ፡- ዕዝራ 6:1-12፣ (521 ዓ.ዓ)፡፡ የዳርዮስ አዋጅ የቤተ መቅደሱ ግንባታ እንዲቀጥል የቂሮስን አዋጅ የሚያድስ እንጂ አዲስ ግንባታን የሚመለከት አይደለም፡፡
የመጀመርያው የአርጤክስስ አዋጅ፡- ዕዝራ 7:12-26፣ (457 ዓ.ዓ)፡፡ ይህኛውም አዋጅ ከቤተ መቅደሱ ጋር የተያያዘ እንጂ ኢየሩሳሌምን የሚጠቅስ አይደለም፡፡
ሁለተኛው የአርጤክስስ አዋጅ፡- ነህምያ 2:1-8 (444 ዓ.ዓ)፡፡ ይህ አዋጅ የኢየሩሳሌምን ቅጥር መገንባትን የተመለከተ ነው፡፡
የዳንኤል ትንቢት የኢየሩሳሌምን መሠራት የሚመለከት በመሆኑ ከተማይቱ እንድትሠራ የፈቀደው ብቸኛ አዋጅ በነህምያ አማካይነት ተፈፃሚ የሆነው የአርጤክስስ አዋጅ በመሆኑ ቆጠራውን ከዚያ መጀመር ትክክልና አሳማኝ ነው፡፡ ስሌቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የትንቢት ዘመን አቆጣጠር በኛ ዘመን ወዳለው አቆጣጠር በመቀየር ላይ የተመሠረተ ሲሆን በትክክል 33 ዓ.ም ላይ ይመጣል፡፡ ወሒድ ይህንን አቆጣጠር ባለመረዳቱ ምክንያት በፀሐይ የዘመን አቆጣጠር በማስላት “ከ 62 እና 7 በኋላ መሢሕ ይገደላል” የሚለውን ይዘን ከሄድን ከ 38 በኋላ ይገደላል ተብሎ እንደ እነርሱ እምነት ኢየሱስ የተገደለው በ 33 ድኅረ-ልደት ነው፥ ያ ማለት ኢየሱስ ከተገደለ በኋላ ከ5 ዓመት በኃላ መሢሕ ይገደላል ማለት ትንቢቱ ፉርሽ ይሆናል” ሲል በተወናገረ አጻጻፉ ይሟገታል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢቶች ሊቅ የሆኑት ሐሮልድ ዎልተር ሆኤህነር (Harold Walter Hoehner) ትክክለኛውን አቆጣጠር እንዲህ አስቀምጠዋል፡-

“ስድሳ ዘጠኙን ሱባዔዎች እያንዳንዳቸውን በሰባት ዓመታት እና እያንዳንዱን ዓመት በ360 ቀናት ብናባዛ 173,880 ቀናትን እናገኛለን፡፡ በዚህ መሠረት በ444 ዓ.ዓ. እና በ33 ዓ.ም. መካከል ያለው ልዩነት 476 የፀሐይ ዓመታት ናቸው፡፡ 476ን በ365 ቀናት፣ 5 ሰዓታት፣ 48 ደቂቃዎች፣ 45.975 ሴኮንዶች ብናባዛ [በአንድ ዓመት ውስጥ 365 1/4 ቀናት ናቸው ያሉት] የምናገኘው ውጤት 173,855 ቀናት፣ 6 ሰዓታት፣ 52 ደቂቃዎች፣ 44ሴኮንዶች፣ ወይንም 173,855 ቀናት ይሆናሉ፡፡ ይህ በ444 ዓ.ዓ. እና በ33 ዓ.ም. መካከል መቆጠር የነበረባቸውን 25 ቀናት ብቻ የሚያስቀር ይሆናል፡፡ ሃያ አምስቱን ቀናት በመጋቢት 5 (444 ዓ.ዓ.) ላይ ብንደምር ኒሳን 10/ 33 ዓ.ም. ወደ ሆነው ወደ መጋቢት 30 (33 ዓ.ም.) እንመጣለን፡፡ ይህም ኢየሱስ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ነው፡፡”

የምሑሩን ጽሑፍ ዋቢ አድርገው የጻፉት ዕውቁ ክርስቲያን ዐቃቤ እምነት ጆሽ ማክዱዌል በዚህ ላይ አክለው እንዲህ ይላሉ፡-

በነቢዩ ዳንኤል ትንቢት መሠረት ኢየሩሳሌምን ለመጠገንና ለመሥራት አዋጅ ከወጣበት ጊዜ፤ ማለትም ከኒሳን 1/444 ዓ.ዓ. ጀምሮ መሲሁ ወደ ኢየሩሳሌም እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ 483 ዓመታት (69×7) ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ዓመት 360 ቀናት ካሉት የአይሁድ (ትንቢታዊ) ዓመት ጋር እኩል ነው፡፡ (ይህም በአጠቃላይ 173,880 ቀናት ይሆናል፡፡) … ስድሳ ዘጠኙ ሱባኤ ከመደምደሙ በፊትና ሰባኛው ሱባኤ ከመግባቱ በፊት ሁለት ክስተቶች መታየት አለባቸው፡- የመሲሁ ሞት (ዳንኤል 9፡26) እና የኢየሩሳሌምና የቤተመቅደሱ (በሮማዊው) ልዑል (ታይተስ ወይም ቲቶ) በ70 ዓ.ም. ላይ መደምሰስ ነው፡፡ ስሌቶቹ በሙሉና የአዋጁ በ444 ዓ.ዓ. መውጣት ትክክል ከሆነ ክርስቶስ የተሰቀለው ወደ ኢየሩሳሌም በክብር መግባቱን ተከትሎ ሚያዝያ 3/33 ዓ.ም. ነው የሚሆነው፡፡ (Josh McDowell, Evidence That Demands a Verdict, pp. 197-201)

ረበናተ አይሁድ ይህንን ሃቅ ቢቀበሉ የኢየሱስን መሢህነት መቀበል ግዴታ ስለሚሆንባቸው ይህ አብዱል የተጠቀመውን የመሳሰሉ የተለያዩ ደካማ ሙግቶችን በማቅረብ ትንቢቱ አዳኛችን ኢየሱስን የተመለከተ መሆኑን ለመካድ ይሞክራሉ፡፡ ሙስሊም ወገኖችም ትንቢቱ “ክርስቶስ አልተሰቀለም” የሚለውን ከታሪክ ጋር የተኳረፈ መሠረተ ቢስ እምነታቸውን ውድቅ የሚያደርግና የመጽሐፍ ቅዱስን መለኮታዊነት የሚያረጋግጥ ማስረጃ በመሆኑ ከእውነት ለመሸሽ የረበናተ አይሁድን ትርጓሜዎች ያቀነቅናሉ፡፡

ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞቶ ከሙታን ተነስቷል፡፡ ይህ በቅዱሳን ነቢያት አስቀድሞ የተተነበየና በሐዋርያት ምስክርነት የጸና የታሪክ እውነታ ነው፡፡ በስሙ ያመነ የዘላለምን ሕይወት ያገኛል፡፡ የጥፋትን መንገድ የመረጠ ግን ከላይ ያየነውን በመሳሰሉት ከንቱ ሙግቶች ውስጥ በመደበቅ ዘመኑን ይፈጃል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የሙስሊም ወገኖቻችንን የልብ ዓይኖች በመክፈት ወደ ክርስቶስ ብርሃን ይመራቸው ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው፡፡
ሰሞኑን አንዲት አብዱሊት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ተለያዩ አዘጋገቦችን በመጥቀስ “ግጭት ናቸው” ብላ ስትከራከር ተመለከትኩ፡፡ እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ወገኖች በዚያው ሒሳብ ተከታዮቹን የቁርአን ዘገባዎች ቢመለከቱ መልካም ነው፡-

የዘካርያስና የመልአኩ ንግግር – ሁለት ዘገባዎች፣ ብዙ ግጭቶች

መልአክ ወደ ዘካርያስ በመምጣት ስለ ያሕያ (ዮሐንስ) ልደት እንዳበሰረ በተነገረባቸው ሁለት የቁርአን ዘገባዎች መካከል ብዙ ግጭቶች ይገኛሉ፡፡ ካነበብናቸው በኋላ ግጭቶቹን እንዘረዝራለን፡-
ዘገባ አንድ፡- 3፡38-41 “እዚያ ዘንድ ዘከርያ ጌታዉን ለመነ- ጌታዬ ሆይ ከአንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለኔ ስጠኝ፤ አንተ ጸሎትን ሰሚ ነህና አለ። እርሱም በጸሎት ማድረሻዉ ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት ጠራችዉ። አላህ በየሕያ ከአላህ በሆነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም፣ ከደጋጐቹ ነቢይም ሲሆን ያበስርሃል፤ በማለት፥ (መላእክት ጠራችዉ) – ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና በእርግጥ የደረሰብኝ ስትሆን ባልተቤቴም መካን ስትሆን፥ ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለ (መልአኩም) እንደዚሁ አላህ የሚሻዉን ነገር ይሠራል አለዉ፤ ፡- ጌታዬ ሆይ! ለኔ ምልክትን አድርግልኝ አለ፤ ምልክትሕ ሦስት ቀን በጥቅሻ ቢሆን እንጅ ሰዎችን አለማናገርህ ነዉ፤ ጌታህንም በብዙ አዉሳ፤ በማታና በጧትም አወድሰዉ፥ አለዉ።”
ዘገባ ሁለት፡- 19፡2-11 “(ይህ) ጌታህ ባሪያውን ዘከሪያን በችሮታዉ ያወሳበት ነው። ጌታውን የምስጢር ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፦ አለ ጌታዬ ሆይ እኔ አጥንቴ ደከመ ፤ ራሴም በሺበት ተንቀለቀለ፤ አንተንም በመለመኔ ጌታዬ ሆይ! (ምንግዜም) ዕደለ ቢስ አልኾንኩም። እኔም ከበኃላዬ ዘመዶቼን በእርግጥ ፈራሁ፤ ሚስቴም መካን ነበረች፣ ስለዚህ ከአንተ ዘንድ ለኔ ልጅን ስጠኝ፤ ሃይማኖትህን ይበድላሉ ብዬ የሚወርሰኝ ከያዕቆብ ቤተሰቦችም የሚወርስ የኾነን፣ (ልጅ)፤ ጌታዬ ሆይ! ተወዳጅም አድርገው። ዘከሪያ ሆይ! እኛ በወንድ ልጅ፣ ስሙ የሕያ በኾነ፣ ከዚህ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት እናበስርሃለን፤ (አለው)። ፦ ጌታዬ ሆይ! ሚስቴ መካን የነበረች ስትኾን፣ እኔም ከእርጅና ድርቀትን በእርግጥ የደረስኩ ስኾን፣ እንዴት ልጅ ይኖርኛል! አለ። (ጅብሪል) አለ (ነገሩ) እንደዚሁ ነው ጌታህ ከአሁን በፊት ምንም ያልነበርከውን የፈጠርኩህ ስኾን፣ እርሱ በኔ ላይ ቀላል ነው፤ አለ። ጌታዬ ሆይ! (እንግዲያስ) ለኔ ምልክትን አድርግልኝ አለ፤ ምልክትህ ጤናማ ሆነህ ሳለህ ሦስት ሌሊትን (ከነቀናቸዉ) ሰዎችን ለማነጋገር አለመቻልህ ነዉ፤ አለው። ከምኲራቡም በሕዝቦቹ ላይ ወጣ፤ በጧትና በማታ (ጌታችሁን) አወድሱ በማለትም፣ ወደነሱ ጠቀሰ።”
በዚህ ትረካ ውስጥ ብዙ ግጭቶች ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ያህል፡-
• የመልአኩና የዘካርያስ ንግግር ትክክለኛው የቱ ነው? መልአኩ ለዘካርያስ “አላህ በየሕያ ከአላህ በሆነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም፣ ከደጋጐቹ ነቢይም ሲሆን ያበስርሃል” አለው ወይንስ “ዘከሪያ ሆይ! እኛ በወንድ ልጅ፣ ስሙ የሕያ በኾነ፣ ከዚህ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት እናበስርሃለን” አለው? መልአኩ የተናገረው በሦስተኛ ነጠላ መደብ “አላህ … ያበስርሃል” በማለት ተናገረ ወይንስ በአንደኛ ብዙ መደብ “እኛ … እናበስርሃለን” አለው?
• በመጀመርያው ጥቅስ ውስጥ ተናጋሪው መልአኩ ሲሆን “አላህ … ያበስርሃል” በማለት በሦስተኛ ነጠላ መደብ ይናገራል፡፡ በሁለተኛው ውስጥ ግን “እኛ … እናበስርሃለን” የሚለው ንግግር የአላህ ሲሆን ያለ መልአክ ጣልቃ ገብነት አላህና ዘካርያስ እየተነጋገሩ ነው፡፡ ስለዚህ መልአክ ተልኳል ወይንስ አልተላከም? በሁለቱም አጋጣሚዎች መልአክ ከተላከ በሁለተኛው ውስጥ ንግግሩ በመልአክና በዘካርያስ መካከል ከመሆን ይልቅ በዘካርያስና በአላህ መካከል ስለምን ሆነ?
• ዘካርያስ ምን ብሎ መለሰ? “ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና በእርግጥ የደረሰብኝ ስትሆን ባልተቤቴም መካን ስትሆን፥ ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?” በማለት ወይንስ “ጌታዬ ሆይ! ሚስቴ መካን የነበረች ስትኾን፣ እኔም ከእርጅና ድርቀትን በእርግጥ የደረስኩ ስኾን፣ እንዴት ልጅ ይኖርኛል!” በማለት? የቱ ነው ትክክለኛው ንግግር?
• የመልአኩ መልስ ምን የሚል ነበር? “እንደዚሁ አላህ የሚሻዉን ነገር ይሠራል” የሚል ወይንስ “(ነገሩ) እንደዚሁ ነው ጌታህ ከአሁን በፊት ምንም ያልነበርከውን የፈጠርኩህ ስኾን፣ እርሱ በኔ ላይ ቀላል ነው” የሚል?
• ዘካርያስ ምልክትን በጠየቀ ጊዜ የተሰጠው ምላሽ ምን የሚል ነበር? “ምልክትሕ ሦስት ቀን በጥቅሻ ቢሆን እንጅ ሰዎችን አለማናገርህ ነዉ” የሚል ወይንስ “ምልክትህ ጤናማ ሆነህ ሳለህ ሦስት ሌሊትን (ከነቀናቸዉ) ሰዎችን ለማነጋገር አለመቻልህ ነዉ” የሚል? በመጀመርያው ላይ “ቀን” እንደተባለና በሁለተኛው ላይ “ሌሊት” እንደተባለ ልብ በሉ፡፡ በሁለተኛው ላይ በቅንፍ (ከነቀናቸው) የሚለውን የጨመሩት ተርጓሚዎች እንጂ በአረብኛው ውስጥ አይገኝም፡፡
የቱ ነው ትክክል?
👍1
Audio
ቁርአን በትክክል ተጠብቋልን? በሚል ርዕስ በወንድም ዳንኤል የቀረበውን ትምሕርት በዩቲዩብ መከታተል ላልቻላችሁ ወገኖች በአነስተኛ መጠን በድምፅ አዘጋጅተናል፡፡ በተሻለ ጥራት ለማድመጥ የዩቲዩብ ቻናላችንን ይጎብኙ፡፡
የይሖዋ ምስክሮችና ዮሐንስ 1÷1
“ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” ጽሑፉን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ 👉👇 http://www.ewnetlehulu.org/am/jw-on-john1-1/