ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar) via @like
ከጥቂት ዓመታት በፊት ወደ ሰባት ሺሕ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ባለአክሲዮኖች 350 ሚሊዮን ብር ገደማ በሆነ ካፒታል ለማቋቋም ያሰቡት ዘምዘም የተሰኘ እስላማዊ ባንክ በምሥረታ ላይ እያለ መፍረሱ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ግንቦት 14/2011 በሚሊንየም አዳራሽ በነበረው የኢፍጣር ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ እስላማዊ ባንክ በኢትዮጵያ እንዲከፈት የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ሲገቡ ታይተዋል፡፡ ባንኩ እውን ይሆን ዘንድ የተወሰኑ ሙስሊሞች ጥያቄ ሲያቀርቡና ግፊት ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን የመንግስትም ሆኑ የግል ባንኮች “ከወለድ ነፃ” የተሰኙ መስኮቶችን በመክፈት ለዚህ ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸው ይታወቃል፡፡ ዳሩ ግን አንዳንድ ሙስሊም ወገኖች በዚህ የረኩ አይመስልም፡፡ በእስላማዊ ሕግ የሚመራ፣ ሙስሊሞችን ነጥሎ የሚያስተናግድ፣ “እስላማዊ” የሚል ታፔላ የለጠፈ የተለየ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲዘረጋላቸው መጠየቃቸውን ቀጥለዋል፤ ከመንግሥት ዘንድም አዎንታዊ ምላሽ የተሰጣቸው ይመስላል፡፡ የእስላማዊ ባንክ ዓላማ ከወለድ ነፃ የሆነ ብድር መስጠት ከሆነና ለዚህም የሚሆኑ መስኮቶች በየባንኮቹ ውስጥ ተከፍተው ሳሉ ሌላ የተለየ ባንክ ማቋቋም ማስፈለጉ በብዙ ሰዎች ዘንድ ጥያቄን ፈጥሯል፡፡ ለዚህም ስንል በብሪቲሽ ክርስቲያን ኮንሰርን የተዘጋጀውን ስለ እስላማዊ ባንክ ምንነትና አሠራር እንዲሁም የፋይናንስ ሥርዓቱን በማወክ በማሕበረሰቡ ላይ የሚያስከትለውን ችግር የሚዳስሰውን ይህንን ጠቃሚ ጽሑፍ ለአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በሚስማማ መንገድ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል፡፡ ሊንኩን ተጭነው ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ http://www.ewnetlehulu.org/am/whats-wrong-with-islamic-bank/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar) via @like
ረመዳን ሊጠናቀቅ ጥቂት ከናት ቀሩ፡፡ ባለፉት 26 ቀናት ሙስሊም ሽብርተኞች በዓለም ዙርያ 140 የሽብር ጥቃቶችን ያደረሱ ሲሆን 686 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ በቀጣይ 4 ቀናት ስንት ንፁሃን ይሞቱ ይሆን? በዚህ ወር ከእስር ከተፈታው ደም አፍሳሽ ጋኔን እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቡን እንዲታደግ አጥብቀን ልንጸልይ ይገባል፡፡
አብዛኞቹ ሙስሊሞች፣ በተለይም የአገራችን ሙስሊሞች ሰላም ወዳዶች ናቸው፡፡ ነገር ግን “የሰላም ሃይማኖት” እንደሆነ የተነገረለት ሃይማኖታቸው እንዲህ የሰቆቃ ምንጭ የመሆኑን እውነታ መጋፈጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ችግሩ አንድና አንድ ነው፤ እርሱም እስላማዊ ቅዱሳት መጻሕፍት ሽብርን ማበረታታቸው ነው፡፡ ቁርአንና ሐዲሳት የሽብር ማኑዋሎች እንደሆኑ ብንናገር ከእውነት የራቅን አንሆንም፡፡ የበለጠ ለማወቅ ይህንን ገፅ ይጎብኙ http://www.ewnetlehulu.org/am/terrorism/
በቁርአን ሚስቶችን መምታት አልተፈቀደምን?
የኡስታዝ አቡ ሐይደር ክህደት ሲጋለጥ 👉👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/women-in-islam/idrib/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ሰሞኑን አነጋጋሪ ኾኖ ስለሰነበተው እስላማዊ ባንክ የተጻፈውን ጽሑፍ ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር በፒዲ ኤፍ አዘጋጅተናል፡፡ ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም በቀጥታ ማውረድ ይቻላል፡፡ http://www.ewnetlehulu.org/wp-content/uploads/2019/06/islamic_bank.pdf
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar) via @like
የነቢይነት ማሕተም ወይንስ የጤና ችግር?
ሙሐመድ የነቢይነት ማሕተም ጀርባው ላይ እንዳለው ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ? በእስላማዊ መጻሕፍት ውስጥ የተጻፈውን አስገራሚ ጉዳይ ሊንኩ ውስጥ ታገኛላችሁ http://www.ewnetlehulu.org/am/muhammad/seal/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar) via @like
ለያሕያ ሒስ የተሰጠ መልስ.pdf
330.5 KB
ያሕያ ኢብኑ ኑሕ “ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት ነውን?” በሚል ርዕስ በተጻፈው መጽሐፍ ላይ ላቀረበው ትችት የተሰጠ አጭር መልስ፡፡
ሙሴና ሙሐሙድ የማይመሳሰሉባቸው 50 ነጥቦች 👉👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/muhammad/mo-vs-moses/
የሰሞኑ የያሕያ ኢብኑ ኑህ መንፈራገጥ ግርም እያለኝ ነው፡፡ “አልተሰቀለም” የሚለው “መጽሐፉ” መቶ በመቶ ከአንድ ዌብሳይት ላይ የተኮረጀ መሆኑን ወንድማችን ዳንኤል በማስረጃ ካጋለጠበት በኋላ “ተዓማኒነት የሌለው ምንጭ ጠቅሷል” በሚል የአብዱል ሃቅ ጀሚልን መጽሐፍ እየተቸ ይገኛል፡፡ የመልስ ምት መሆኑ ነውi ሲጀመር አንድ ሰው ትችት ለመሰንዘር የሞራል ብቃት ያስፈልገዋል፡፡ ያህያ እስከ አሁን ሁለት “መጻሕፍትን” (ድንቄም መጻሕፍትi) ያሳተመ ሲሆን በሁለቱም ውስጥ አንድም እደግመዋለሁ አንድም ምንጭ አልጠቀሰም! የመጀመርያውን “መጽሐፉን” 101 Clear Contradictions in the Bible በሚል ርዕስ ሻቢር አሊ በተባለ ሰው ከተጻፈ የዌብሳይት ጽሑፍ የገለበጠ ሲሆን ሁለተኛውን ደግሞ 65 Reasons to Believe Jesus Did Not Die on the Cross በሚል ርዕስ አይ. ኤች. ከውሰር በተሰኘ አውስትራሊያዊ የአሕመዲያ ኢማም ከተጻፈ የዌብሳይት ጽሑፍ ላይ ነው የገለበጠው፡፡ የሚገርመው ነገር ያህያ ሙግቶቹን ራሱ ተመራምሮ የደረሰበት በማስመሰል በመግቢያው ላይ መግለፁ ነው፡፡ የልበ ወለድ መጻሕፍትና ፊልሞች እንኳ አልፎ አልፎ “የመነሻ ሐሳብ ከእገሌ” የሚል ማሳሰብያ ይኖራቸዋል፡፡ ሰው ኢ-ልቦለዳዊ መጻሕፍትን ጽፎ እንዴት አንድ ምንጭ እንኳ አይጠቅስም??? እንዲህ ያለ ፀያፍ ተግባር የመፈፀም አባዜ የተጠናወተው ሰው ነው እንግዲህ ስለ ምንጭ አጠቃቀስ ዓይኑን በጨው አጥቦ ትችት ሊሰነዝር የሚዳዳው፡፡ እንደ ተረቱ ከሆነ ጅብ ቁርበት አንጥፉልኝ ያለው የማያውቁት አገር ሄዶ ነው፡፡ ያህያ ግን ይህንን ሁሉ ጉዱን በሚያውቁት ሰዎች ፊት ሲመጻደቅ ትዝብት ላይ መውደቁ በህሊናው ውልብ አላለም፡፡ ወንድም ዳንኤል ባቀረበበት በማስረጃ የተደገፈ የማያወላዳ ሒስ ምክንያት ድንብርብሩ ስለወጣና የቲፎዞ ክምችቱ እየተበታተነ ስለሚገኝ ሁሉንም ነገር እያደረገ የሚገኘው “ካፈርኩ አይመልሰኝ” በሚል ስሜት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ስህተትን አምኖ በመቀበል አለመታረም ከስህተቶች ሁሉ የከፋው ስህተት ነው፡፡ ያህያ ደህና መካሪ በማጣቱ ምክንያት ገና ሳይጀምር የከሸፈ አሳዛኝ ፍጡር ነው፡፡ ነፍስ ይማር!
Selman Desperate.pdf
708.8 KB
ስህተትን በሐሰት ካባ መሸፈን አያዋጣም!
የሰልማን ቅጥፈት ሲጋለጥ
መጽሐፍ ቅዱስ መርዛማ እፅዋትን እንድንመገብ ያዛልን?
መጽሐፍ ቅዱስ መርዛማ እፅዋትን እንድንመገብ ያዛልን?

አንድ ሙስሊም እንዲህ ሲል ይጠይቃል፡-

"እግዚአብሔርም አለ። እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፡፡" (ኦሪት ዘፍጥረት 1:29)

በዚህ አንቀፅ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ሲመክር ምድር ላይ የፈጠራቸውን የእፅዋት ዘር በጠቅላላ ለምግብነት መጠቀም እንደምንችል ይገልጻል፡፡ እንደሚታወቀው ደግሞ በዚህ ምድር ላይ ያሉ እፅዋት በጠቅላላ ለምግብነት ምቹ አይደሉም፤ መርዛማ ፍሬዎችን ጨምሮ ለሰው ልጅ ተስማሚ ያልሆኑ ፍጥረታትም እንዳሉ አይዘነጋም፡፡

ታዲያ እግዚአብሔር እነዚህን ሳይቀር ያለምንም መለያየት ለመብልነት ፈጠርኩ ሲል ምን ማለቱ ነው? ሌላው ይቅርና እርስዎ ልጅዎትን ከግቢ ውጭ ካሉ እፅዋት ውስጥ የፈለገውን እንዲበላ ይመክሩታል?

------
ዶ/ር ዛኪር ናይክ ከዶ/ር ዊልያም ካምቤል ጋር በነበራቸው ክርክር ወቅት ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡ የጠያቂው ችግር ቃሉ የትና መቼ እንደተነገረ አለማስተዋሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ይህንን ቃል የተናገረው ለአዳምና ለሔዋን ሲሆን ከውድቀት በፊት በኤደን ገነት ውስጥ ነበር፡፡ ሰው በኃጢአት ከመውደቁና ምድር ከመረገሟ በፊት ሁሉም ነገር መልካም እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡-

“ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።” (ዘፍጥረት 1፡12)

ነገር ግን ከውድቀት በኋላ ምድር በመረገሟ ምክንያት እፅዋት ጎጂ ወደመሆን ተለወጡ፡-

“አዳምንም አለው፦ የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።” (ዘፍጥረት 3፡17-18)

በርግጥ እግዚአብሔር አምላክ ያለ ምንም ልዩነት ሁሉንም እፅዋት እንዲበሉ ለሰው ልጆች ፈቅዷል የሚለው የጠያቂው ምልከታ ስህተት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሰዎች ለትዕዛዙ ያላቸውን ታማኝነት ይፈትንበት ዘንድ የፈጠረውን መልካምና ክፉውን ከሚያሳውቀው ዛፍ እንዳይበሉ ከልክሏቸዋል፡-

“እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው። እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ … እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” (ዘፍጥረት 2፡8-9፣ 2፡16-17)

በዚህ ጥቅስ መሠረት እግዚአብሔር አምላክ ያበቀላቸው ዛፎች “ለመብላትም መልካም” የነበሩ ሲሆን መብላት የሌለባቸውንም አንዱን ለይቶ ነግሯቸዋል፡፡

ስናጠቃልል ይህ ፈቃድ የተሰጠው ከውድቀት በፊት በኤደን ገነት ውስጥ ለአዳምና ለሔዋን መሆኑ ከግንዛቤ ውስጥ ሲገባ ጥያቄው በተሳሳተ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ መሆኑ ግልፅ ይሆናል፡፡

------

አሁን ደግሞ ተራው የናንተ ነው፡፡ እስኪ የገዛ አመክንዮአችሁን ቁርአን ላይ ተግባራዊ እናድርግና የሚሆነውን እንይ፡፡ ሱራ 6፡145 ላይ በተጻፈው መሠረት የተከለከሉት ምግቦች 4 ዓይነት ብቻ ሲሆኑ ሌላው ሁሉ ተፈቅዷል፡-

“(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- «ወደእኔ በተወረደው ውስጥ በክት ወይም ፈሳሽ ደም ወይም የአሳማ ስጋ እርሱ ርኩስ ነውና ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም…” (ሱራ 6፡145)

ስለዚህ በዚህ ጥቅስ መሠረት በክት፣ ፈሳሽ ደምና የአሳማ ሥጋ ብቻ ነው የተከለከለው፡፡ ጎጂ እንስሳትም ለምግብነት ተፈቅደዋል ማለት ይሆን?

ለእስልምና ሙግቶች ምላሽ
ወሒድ በእየሱስ ተመላኪነት

ከዚህ በፊት የክርስቶስ መመለክ፣አለመመለክ ጉዳይ ላይ ወሒድ ከጅሆቫ ዊትነሶች ሰርቆ ያቀረበውን ሙግት ማፍረሳችን ይታወቃል። በተለይ ደግሞ λατρεύω (ላትሬይኦ፣ አምልኮ) በሚለው ቃለ ዙሪያ ሙግታችንን አቅርበናል። የኡስታዞቹ ሙግት ይህ ቃል አንዴም ለእየሱስ አለመግባቱን ሲሆን እኛ ደግሞ መግባቱን በደምብ አሳይተናል። ለምሳሌ:-
የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 22
3፤ ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል( λατρεύσουσιν ) ፊቱንም ያያሉ፥ 4፤ ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።
ከላይ በተጠቀሰው ጥቅስ ላይ ማብራሪያም ሰጥተናል (እዚው ቻናል ላይ ማግኘት ይችላሉ)።

ወሒድ ይሄ መልስ ሲሰጠው እንግዲህ ካፈርኩ አይመልሰኝ ይመስል ከስህተቱ ከመማር ይልቅ ሌላ ተደራራቢ ስህተት ያላቸው ፅሁፎችን ለጥፏል። እሱንም በማያውቀው ቋንቋ (ግሪክ) እየገባ። ለማንኛውም እስኪ እንመልከተው።

ሙግቱን እንዲህ ብሎ ይጀምራል፣
“….ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* αὐτῷ μόνῳ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
"አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። ይህ ጌታ አምላክ ለኢየሱስ የዳዊትን ዙፋን የሰጠው አብ ነው”

ምላሽ:
1. αὐτῷ የሚል ቃል በማቴዎስ ወንጌል የገባበት አወቃቀርና በዮሓኒስ ራእይ የገባበት አወቃቀር ፈፅሞ የተለያየ ነው። ማቴዎስ ላይ የአረፍተ ነገሩ object አንድ ስም ወይም noun ነው። እሱም “ጌታ አምላክ” ነው። ልብ በል፣ ጌታ እና አምላክ አይልም። ለዚህ ነው αὐτῷ ነጠላ የሆነቸው። ይሄ አንድ “essence” (ማንነትና ምንነት የሚሉ አማርኛ ቃላቶች essence የሚለውን ቃል በፊሎሶፊ ደረጃ ስለማያብራሩ አንጠቀምም) ብቻ እንደሚመለክ የሚያሳይ ነው። ልብ በል፣ አንድ “አካል” ወይም person መሆኑን ክፍሉ ምንም አይነግረንም። ምክኒያቱም “አምላክ” የሚለው ቃል “essence” ነው። ለምሳሌ “ሰው” የሚል ቃል የኛን essence የሚገልፅ ነው፣ ልክ እንደዛው “አምላክም” የፈጣሪ essence ነው። እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ የምናምነው አንድ essence ያለው አምላክ በሶስት አካል(person) መኖሩን ነው። ስለዚህ፣ እየሱስ ሰይጣንን “ጌታ አምላክህን ብቻ አምልክ” ሲለው፣ ስለ essence እንጂ ስለ አካል እያወራና እራሱን ከአምላክነት ክፍል(category) እያወጣ አይደለም። ስለዚህ፣ ከአንድ በላይ የሚመለክ essence ስለሌለ αὐτοῖς የሚለውን ቃል መጠቀም አያስፈልግም ማለት ነው። በነገራችን ላይ፣ ወሒድ እዚህ ክፍል ላይ ስለ እኛ እምነት የተጣመመ ሙግት ሰርቶ እራሱ የሰራውን ሙግት መልሶ ማፍረስ መሞከሩ በሎጂክ ውስጥ strawman fallacy እንለዋለን።

2. ልጁ የዮሓኒስን ራእይ አፃፃፍ በማቴዎስ ወንጌል አይን አይቶ ኤግዝጄስስ መስራት መሞከሩ አንድ ቃል (ምሳሌ፣ αὐτῷ) ሁሌም ተመሳሳይ አይነት ፊቺ በሁሉም ሁኔታ በመፅሓፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሚኖረው አድርጎ ማሰቡን ያሳያል። ይሄ ደግሞ በመፅሓፍ ቅዱስ አተረጓገም ውስጥ word study fallacy እንለዋለን። አንድ ክፍል ላይ ፍቺ ለመስጠት የፀሓፊውን አፃፃፍ ስልት፣ ኮንቴክስት እና የመሳሰሉትን ማየት ያስፈልጋል። ቀጥለን የልጁን ፅሁፍ እንመልከት።

ቀጥሎ እንዲህ ብሎ ፅፏል

“ይህ ጌታ አምላክ ከበጉ ማንነት በሰዋስው ተነጥሎ ተቀምጧል፦
ራእይ 21፥22 *"ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና"* መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።

ልብ አድርግ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት እንደሆኑ ለማሳየት "ናቸው" በሚል የብዜት አያያዥ ግስ ተቀምጧል፥ በተጨማሪም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። ስለዚህ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት ናቸው፥ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አብ ከሆነ "በጉ" ደግሞ ኢየሱስ ነው። በጉ የሚታረድ ማንነት ስለሆነ ፍጡር ነው”

ምላሽ
እዚህ ላይ ወይም ወሒድ ግሪክ ማንበብ አይችልም ወይ ደግሞ ውሸታም ነው። ግሪኩን እናንብብ
Καὶ ναὸν οὐκ εἶδον ἐν αὐτῇ· ὁ γὰρ Κύριος ὁ Θεὸς ὁ Παντοκράτωρ ναὸς αὐτῆς #ἐστιν, καὶ τὸ Ἀρνίον
በግሪኩ፣ “ናቸው” የሚል የብዜት አያያዝ #የለም። ἐστιν (estin) የሚለው ቃል የ “eimi, ‘is’,” ሶስተኛ መደብ ሆኖ ነጠላ ነው። ብዜትን ማሳየት ቢፈልግ ኖሮ ἐισιν (eisin) ይሆን ነበር። ስለዚህ፣ በአማርኛው የአማርኛን ግራመር እንጠብቃለን ብሎ ወደ “ናቸው” ተሮገሙት እንጂ ትክክለኛው ግሪክ “ነው” የሚል ነጠላ ትርጓሜ ይሰጣል። ልብ በል፣ እየሱስና አብን ጠርቶ በነጠላ እየገለፃቸው ነው ማለት ነው።
“በጉ የሚታረድ ስለሆነ ፍጡር ነው” ብሎ ወሒድ ተናግሯል። በዚህች አረፍተ ነገር ብቻ ሁለት ሓሰተኛ ሙግቶችን fallacies ሰርቷል። Begging the question እና straw man። ግዜውም ርዕሳችንም ስላልሆነ እነኚህ ሁለቱ fallacyዎችን እራሱ እንዲያጠናና ለሚቀጥለው እንዲያስተካክል ምክሬን እለግስለታለው።

ቀጥሎ ልጁ እንዲህ ይላል
“ራእይ 22፥3 *"የእግዚአብሔር እና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል"*፥ λατρεύσουσιν αὐτῷ ፊቱንም ያያሉ።

እግዚአብሔር እና በጉ ሁለት ማንነት መሆናቸው ለማሳየት አሁንም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። አሁንም "አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። "ያመልኩታል" እንጂ "ያመልኳቸዋል" አላለም፥ ይህ የሚመለክ እግዚአብሔር እንጂ በጉ አይደለም፦”

ምላሽ

1. በመጀመሪያ ደረጃ እግዚያብሔር እና በጉ ሁለት person እንጂ ሁለት essence አይደሉም። ስለዚህ “እና” ወይም kai ሁለት person መሆናቸውን ከማሳየት የዘለለ ምንም ለሙግትህ ጥቅም የለውም
2. “አውቶ” የሚለው ቃል፣ ነጠላ መሆኑ ይታወቃል። ቅድም እንዳየነውም estin የሚለውን ነጠላ verb to be ለአብና በጉ ዮሓኒስ ሲጠቀም አይተናል። እዚህም ክፍል ላይ ነጠላ pronoun ለሁለት አካል ሲጠቀም እናያለን። ብዙ ምሁራን የዮሓኒስን ራእይ ሲያጠኑ፣ የአብና ወልድን እና ሌሎች አንዳንድ ቴዎሎጂካል ነገሮችን አስመልክቶ ዮሓኒስ የግራመር ሕጎችን ለስን መሎኮት አላማ ሲያስተካክላቸው ተስተውሏል። ራዕይ ምዕ 1:4 ላይ ይሄንን ማስተዋል እንችላለን። ይሄ ግን ሌላ ትልቅ ርዕስ ስለሆነ ወደሱ አልገባም። ነገር ግን ራእይ 22:3 ላይ ምሁራን የፃፉትን ላስነብባቹ።

ቀጥለህ/ሽ አንብብ/ቢ....👇👇

Ναολ Τζιγι

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
...የቀጠለ

ሪቻርድ ቡክሓም

John, who is very sensitive to the theological implications of language and even prepared to defy grammar for the sake of theology (cf. 1:4), may well intend the latter. But in either case, he is evidently reluctant to speak of God and Christ together as a plurality. He never makes them the subjects of a plural verb or uses a plural pronoun to refer to them both. The reason is surely clear: he places Christ on the divine side of the distinction between God and creation, but he wishes to avoid ways of speaking which sound to him polytheistic. The consistency of usage shows that he has reflected carefully on the relation of Christology to monotheism. It is significant that one of the passages in question (22:3-4) concerns worship (The Theology of the Book of Revelation, pp. 60-61).
ሪቻርድም ሆነ ብዙ ምሁራን እንደሚናገሩት፣ ዮሓኒስ፣ አብና ወልድን በብዜት verbም ሆነ pronoun ሲወክላቸው አይታይም። ይህ ደግሞ የሚያሳየው “latreou”(አምልኮ) የሚል ቃል ለእየሱስም መጠቀሙን ነው።
That 'they will serve him' likely does not refer only to God or only to the Lamb. The two are conceived so much as a unit that the singular pronoun can refer to both... That both are sitting on only one throne and together form one temple (21:22) enhances their perceived unity. Also, this unity is highlighted by both having the titles 'Alpha and Omega' (1:8; 21:6; 22:13). Such statements as these in 21:22 and 22:3 were among those that gave rise to later Trinitarian formulas (Beale, The New International Greek Testament Commentary- The Book of Revelation [Wm. B. Eerdmans Publishing Co. & Paternoster Press, 1999], p. 1113).

“አውቶ” የሚለው pronoun ለ አብ ብቻ ነው መሆን ያለበት ብንል እራሱ ስህተት ውስጥ ነን። ምክኒያቱም በአጠቃላይ፣ የግራመር ሕጉ ውስጥ፣ አንድ pronoun በቅርበት ወደሱ የሚጠጋውን ስም (antecedent or immidiate noun) ነው የሚገልፀው። በራእይ 22:3 ላይ ደግሞ “λατρεύσουσιν αὐτῷ,(latreusousin auto) ለሚለው፣ በቅርበት ያለው ስም “በጉ” ስለሆነ “ያመልኩታል”የተባለው በጉን(እየሱስን) መሆኑ ነው።

ስለዚህ፣ ኡስታዞቹን የምመክረው ምክር ቢኖር “Don’t embarrass your self” የሚል ይሆናል!! 🙂

Ναολ Τζιγι

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
እስላማዊ ሐዲሳት እንደ ቁርአን ሁሉ ከእውነት የራቁ ብዙ አስገራሚ አፈ ታሪኮችን በውስጣቸው የያዙ መጻሕፍት ናቸው፡፡ እነዚህን አፈ ታሪኮች በአስተውሎት የተመለከተ ሰው መጻሕፍቱ ስለ ሙሐመድ የሚሰጡትን ምስክርነቶች በተመለከተ ለጥርጣሬ መዳረጉ የማይቀር ነው፡፡ ለዛሬ በዚህች አጭር ጽሑፍ የምንመለከተው ዓምር ቢን ማዕሙና የተሰኘ የሙሐመድ የቅርብ ተከታይ ከእስልምና ዘመን በፊት እንዳጋጠመው የተናገረውን ታሪክ የተመለከተ ነው፡፡ ልብ በሉ፤ ተናጋሪው ከሙሐመድ ሰሓባዎች መካከል አንዱ ሲሆን ከእስልምና ዘመን በፊት የገጠመውን ትክክለኛ ገጠመኝ ነው የሚያወጋው፡፡ እንዲህ ይላል፡-

Narrated 'Amr bin Maimun:
During the pre-Islamic period of ignorance I saw a she-monkey surrounded by a number of monkeys. They were all stoning it, because it had committed illegal sexual intercourse. I too, stoned it along with them. (Sahih al-Bukhari, Volume 5, Book 58, Number 188)

“ዓምር ቢን ማዕሙና እንደተናገረው፡-
‹‹ከእስልምና በፊት በነበረው ያለማወቅ ዘመን አንዲት ሴት ጦጣ በብዙ ጦጣዎች ተከባ አየኋት፡፡ ሕገ ወጥ የወሲብ ግንኙነት በመፈፀሟ ምክንያት በድንጋይ ሲወግሯት ነበር፡፡ እኔም አብሬያቸው ወገርኳት፡፡››” (ሳሂህ አል-ቡኻሪ፣ ቅፅ 5፣ መጽሐፍ 58፣ ቁጥር 188)

ይህንን የተናገረው ከሙሐመድ ተከታዮች መካከል አንዱ ሲሆን ተዓማኒ ሐዲስ ተደርጎ በአል-ቡኻሪ ስብስብ ውስጥ ተካቷል፡፡ ጥቂት ጥያቄዎች ስለዚህ ሐዲስ፡-
1. ይህ የሙሐመድ ተከታይ ጦጢት ስለፈፀመችው ኃጢአት ሊያውቅ የቻለው እንዴት ነው? ጦጣዎቹን ጠይቆ ወይንስ ወንጀሉን ስትፈፅም ተከታትሎ አይቷት? አይቷትስ ቢሆን ወንዱ ጦጣ ሕጋዊ ባሏ እንዳልሆነ በምን መንገድ አወቀ?
2. ወንዱ ጦጣ የት ገባ? ሮጦ አምልጦ ይሆን?
3. በእንስሳት ዓለም በተለይም በጦጣዎች ዘንድ እንዲህ ያለ ልማድ ስለመኖሩ ሙስሊሞች ማስረጃ ሊያቀርቡልን ይችላሉ?

አሁን ወደ ቁም ነገሩ፡፡ ይህ ሐዲስ አፈ ታሪክ መሆኑ ምንም ጥርጥ የለውም፡፡ ነገር ግን እንደ ተዓማኒ ታሪክ ተቆጥሮ ከቁርአን ቀጥሎ ትልቅ ጀረዳ በተሰጠው የሐዲስ ስብስብ ውስጥ ሰፍሯል፡፡ እንዲህ ያሉ ታሪኮችን እንደ እውነተኛ ታሪክ የሚቆጥሩ ሰዎች የአስተሳሰብ ደረጃቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ምናልባት በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በአረብ በረሃ ውስጥ ለኖረ ቤድዊን ትርጉም ይሰጥ ይሆናል፤ በሰለጠነው ዓለም ለሚኖር ሰው ግን ትርጉም አልባ ተረት ነው፡፡ ሙሐመድ እውነተኛ ነቢይ መሆኑን እንዳረጋገጡ የነገሩን ሰዎች መሰል ታሪኮችን ከእውነት የሚቆጥሩ ወገኖች መሆናቸው ደግሞ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ሙሐመድን በቅርበት የሚያውቁት እነዚያ የዓይን እማኞች መሰል ታሪኮችን እንደ እውነተኛ ታሪክ የሚቀበሉ ከሆነ ስለ ሙሐመድ የሰጧቸውን መስክርነቶች ለመጠራጠር በቂ ምክንያት አለን፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ወለድን እንደሚከለክልና እስላማዊውን “የወለድ አልባ” የባንክ ሥርዓት መቃወማችን ትክክል አለመሆኑን ለማሳየት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ሲጠቅሱ ተመልክተናል፡፡ በነገራችን ላይ በርዕሱ ላይ የጻፍነው ጽሑፍ ብዙ ወገኖች እጅ ገብቶ የመወያያ ርዕስ በመሆኑ ምክንያት ሙስሊም አፖሎጂስቶች መልስ ለመስጠት እየዳከሩ ይገኛሉ፡፡ http://www.ewnetlehulu.org/am/whats-wrong-with-islamic-bank/ አራት ግልፅ ነጥቦችን በማስቀመጥ አቋማችንን እናሳውቃል፡-

1. “እስላማዊውን” የፋይናንስ ሥርዓት በአገራችን ውስጥ መዘርጋት ምን መዘዞች እንዳሉትና ለምን እንደማያስፈልግ በቀደመው ጽሑፋችን ውስጥ በዐሥር ነጥቦች አሳይተናል፡፡ ሙስሊም ሰባኪያን ከዐሥሩ ነጥቦች መርጠው እየተሟገቱ የሚገኙት “ቁርአናችን አይፈቅድም” በሚለው ላይ ነው፡፡ “ይፈቅዳል ወይንስ አይፈቅድም?” በሚለው ላይ እነርሱ ራሳቸው አልተስማሙም፡፡ ሙስሊሞች ሁሉ ያልተስማሙበትን የጥቂት አክራሪዎችን አቋም የብዙኀኑ ሕዝበ ሙስሊም አቋም አስመስሎ “እስላማዊው አቋም ይህ ነው” ብሎ ማለት ተቀባይነት የለውም፡፡

2. በእስላማዊው የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ ወለድ የለም የሚለው አባባል ግልፅ ቅጥፈት ነው፡፡ እስላማዊ ባንኮች “ወለድ” የሚለውን ቃል ላለመጠቀም ከተበዳሪዎች የሚቀበሉትን ወለድ “ኪራይ” “ትርፍ” ወዘተ. እያሉ ቢሰይሙም ዞሮ ዞሮ ከወለድ ጋር የሚመጣጠን አንዳንዴም የበለጠ ገንዘብ ያስከፍላሉ፡፡ ለዚህ ነው ከገዛ ሊቃውንቶቻቸው መካከል አንዱ እንዲህ ሲል የጻፈው፡- “ዋነኛ የገንዘብ ማንሸራሸርያ ስልታቸው በሆነው በሙራባሃ የገንዘብ ልውውጥ ውስጥ በግዢና በሽያጭ ዋጋዎች መካከል ያለው ልዩነት የሚሰላው ከወለድ ጋር ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ሲሆን እርሱም ገንዘብ በጊዜ ውስጥ ባለው ዋጋ ነው፡፡ የበለጠ ግልፅ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ ያህል፣ እስላማዊ ባንኮች 95% በሆነው የገንዘብ ልውውጣቸው ውስጥ ወለድን የሚያስከፍሉ ሲሆን በእስላማዊ ካባ የተሸፈነ ነው፡፡ በተለያዩ ሽፍንፍን ዘዴዎች ወለድን ማስከፈላቸው ምርቶችን ለማድበስበስ የታለመ ሲሆን እስላማዊ ባንኮች በማጭበርበርና በማታለል አለመታመንን ያበረታታሉ፡፡ በአላህ ፊት የከፋው ኃጢአት የትኛው ነው? በግልፅ ወለድን ማስከፈል ወይንስ በማጭበርበር ተግባራት ውስጥ ተሳታፊ መሆን?” Muhammad Saleem, Islamic Banking - a $300 Billion Deception (Xlibris, 2005), 68-69.

3. መጽሐፍ ቅዱስ ወለድን ይከለክላል የሚለው አባባል በአንድ ጎኑ ሲታይ እውነት ቢሆንም በሌላ ጎኑ ግን ውሸት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወለድን የሚከለክሉት ጥቅሶች ለእስራኤላውያን በተሰጡት የብሉይ ኪዳን ትዕዛዛት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በጭፍን ወለድን የሚከለክሉ አይደሉም፡፡ በብሉይ ኪዳን መሠረት እስራኤላውያን አንዳቸው ከሌላቸው ወለድን እንዳይቀበሉ ቢታዘዙም በውጪ አገራት ሰዎች ግን ወለድን መቀበል እንደሚገባቸው ተነግሯቸዋል፡- “ለወንድምህ በወለድ አታበድር፤ የብር ወይም የእህል ወይም የማናቸውንም ነገር ሁሉ ወለድ አትውሰድ። ለእንግዳው በወለድ አበድረው፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት በምትገባባት ምድር በሥራህ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ ለወንድምህ በወለድ አታበድር።” (ዘዳግም 23፡19-20) ያለ ወልድ ማበደር የሚለው ፅንሰ ሐሳብ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ድኾችን አለመበደልና መርዳት ከሚል ፅንሰ ሐሳብ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በሒደቱ ውስጥ ድኾች እንዳይበደሉ የተሰጠ ትዕዛዝ እንጂ ወለድ መቀበል ኃጢአት ወይንም ኢ-ፍትሃዊ ስለሆነ አይደለም የተከለከለው፡፡ እንደርሱ ቢሆን ኖሮ ከባዕዳን ወልድ መቀበል ባልተፈቀደ ነበር፡፡

4. ወለድን ማስከፈል ኢ-ፍትሃዊ ነው የሚለው የአላዋቂዎች አባባል ነው፡፡ ማንኛውም ስለ ምጣኔ ኃብትና ስለ ገንዘብ መሠረታዊ ዕውቀት ያለው ሰው ይህ ሃቅ አይጠፋውም፡፡ የገንዘብ ዋጋ የሚሰላው በጊዜ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የዛሬ ዐሥር ዓመት የነበረው የ100,000 ብር ዋጋና ዛሬ ያለው ዋጋ እኩል አይደለም፡፡ ምናልባትም ከግማሽ በላይ ዋጋው ወርዶ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው የዛሬ ዐሥር ዓመት ያበደረው ወይንም ባንክ ያስቀመጠው ገንዘብ ዛሬ ያለ ምንም ጭማሪ ተመላሽ ቢሆንለት ኪሳራ ውስጥ ይገባል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ገንዘብ በጊዜ ውስጥ ያለውን ዋጋ እንዲሁም ተያያዥ የሆኑ ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወለድ መቀበል ፍትሃዊ እንጂ ኢ-ፍትሃዊ አይደለም፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ለድኻ ጎረቤቶቻችን በእምነት ቢመስሉንም ባይመስሉንም በወልድ አናበድርም፡፡ ይህ የህሊናና የክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ጉዳይ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳችን እንዲያውም ብድር ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ስናበድር እንደሚመለስልን ተስፋ በማድረግ ሳይሆን እንደ ስጦታ እንድናበድር ነው የሚያስተምረን (ሉቃስ 6፡35)፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ማሰብያ አእምሮ ስለሰጠን ገንዘባችንን ባንክ ስናስቀምጥ ወለድ የመቀበል ፍትሃዊ መብታችንን እንጠቀማለን፤ ምክንያቱም ተቋማቱ በገንዘባችን ለመጠቀም የተደራጁ ነጋዴዎች እንጂ ድኾች አይደሉምና፡፡ ፍትሃዊ ወለድ ከሚያስከፍሉ የፋይናንስ ተቋማትም እንበደራለን፤ ምክንያቱም ድኻ አደጎችን ለመርዳት የተቀመጡ እጓለ ሙታን አይደሉምና፡፡ ድኾችን መርዳትን ታሳቢ ያደረገውንና በእስራኤላውያን መካከል ብቻ የተወሰነውን የብሉይ ኪዳንን የወለድ ክልከላ ሕግ ከዚህ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፡፡ ሙስሊም የፋይናንስ ተቋማትም ቢሆኑ ይህንን ሊካድ የማይችል የምጣኔ ኃብት እውነታ ስለተገነዘቡ “ወለድ” የምትለዋን ስም ላለመጠቀም በተለያዩ ዘወርዋራ ዘዴዎችና ስያሜዎች ከወለድ ጋር የሚመጣጠን አንዳንዴም የሚበልጥ ክፍያን ያስከፍላሉ፡፡ ቀደም ባለው ጽሑፋች እንደገለፅነው የእስላማዊ ፋይናንስ ተቋማት ዓላማ የወለድ ጉዳይ አይደለም፡፡ አጀንዳቸው ክርስቲያኑንም ሆነ ሙስሊሙን የማይጠቅም ሙስሊሞችን ከሌላው ማሕበረሰብ ለመነጠል ያለመ ዓለም አቀፍ የአክራሪዎች አጀንዳ ነው፡፡ ስለዚህ በፅኑ እናወግዛለን፡፡
የተወገረችው ዝንጀሮን አስመልክቶ ሙሓመዳውያን የሰጡት ምላሽ ሲገመገም


ከቀናት በፊት ወንድም ዳንኤል በእስላማዊ ሓዲሳት ውስጥ ሰፍሮ ስለሚገኘው ስለአንድ አስቂኝ አፈ ታሪክ ፅፎልን ነበር። እሱንም አስመልክቶ ሎጂካል በሆነ መንገድ ጥያቄ ጠይቋል። ሓዲሱ እንዲህ የሚል ነው:-

Narrated 'Amr bin Maimun:
During the pre-Islamic period of ignorance I saw a she-monkey surrounded by a number of monkeys. They were all stoning it, because it had committed illegal sexual intercourse. I too, stoned it along with them. (Sahih al-Bukhari, Volume 5, Book 58, Number 188)

“ዓምር ቢን ማዕሙና እንደተናገረው፡-
‹‹ከእስልምና በፊት በነበረው ያለማወቅ ዘመን አንዲት ሴት ጦጣ በብዙ ጦጣዎች ተከባ አየኋት፡፡ ሕገ ወጥ የወሲብ ግንኙነት በመፈፀሟ ምክንያት በድንጋይ ሲወግሯት ነበር፡፡ እኔም አብሬያቸው ወገርኳት፡፡››” (ሳሂህ አል-ቡኻሪ፣ ቅፅ 5፣ መጽሐፍ 58፣ ቁጥር 188)

ከኛ የተጠየቀውን ጥያቄ በኋላ እንመጣበታለን፣ አሁን ግን የአንዱን የሙስሊም አፖሎጄቲክስ ተማሪ መልስ እንመልከት።

እንዲህ ይላል:

“እውን ነብዩ ”ﷺ” ጨካኝና ዝንጀሮ ወጋሪ ነበሩን?......
ግን እስከመቼ ነው ነገሩ? የዛሬው ቅጥፈት ደግሞ ነብዩ ”ﷺ” ዝንጀሮ ወግረዋል ጨካኝ ናቸው ምናምን የሚል ሂስ ነው።............ይህንን ሃዲስ ነው አጣመው በሌለ ትርጉም ነብዩን የሚወነጅሉትና የሚቀጥፉበት ይህ ነው። አሁንስ አበዙትና ጠቅላላ ሙኽ ማፊ ሆነው አረፉት።እዚህ ሃዲስ ውስጥ ምንም ስለነብዩ ”ﷺ” ማንም ያወራ የለም። ድርጊቱን የሚተርክልን *አምር* ነው።ዝንጀሮዋንም ወገርኩኝ ያለው *አምር* ነው። እርሱ የራሱን ታሪክ የሚነግረን ያለው።

ከቁርአን መውረድ በፊት በጃሂልያው ዘመን አንዲት ዝንጀሮ በዙሪያዋ በዝንጀሮዎች ተከባ አየሁ።ህገ ወጥ የወሲብ ግንኙነትን ፈፅማለች ብለው በድንጋይ እየወገሯት ነበር።እኔም ከእነርሱ ጋር በመሆን ወገርኳት።

ከኢስላም በፊት ይላል እንግሊዝኛው ላይ እና አረብኛው فِي الْجَاهِلِيَّةِ *ፊል ጃሂሊየቲ* ነው የሚለው ይህም ማለት በድንቁርናቸው ዘመን በዝቅጠታቸው ዘመን ማለት ነው።”

በአጭሩ መልሳቸው ይሄን ነው የሚመስለው። ነገር ግን #የኛ_ጥያቄ_ይሄ_ነበር_ወይ? በፍፁም አልነበረም። በእርግጥ ፀሓፊው መልሱ “ከሶስት አመት በፊት ለኦርቶዶክስ መምህራን የተሰጠ” መሆኑን ገልጿል። ቢሆንም የአሁኑን ምላሽ የሰጠው፣ ልክ እኛ ጥያቄውን እዚህ ቻናል ላይ ከለጠፍን በኋላ እንደ ምላሽ ተደርጎ ነው። ለማንኛውም የኛ ጥያቄ የነበረው እንዲህ የሚል ነው:

“ይህንን(ሐዲስ) የተናገረው ከሙሐመድ ተከታዮች መካከል አንዱ ሲሆን ተዓማኒ ሐዲስ ተደርጎ በአል-ቡኻሪ ስብስብ ውስጥ ተካቷል፡፡ ጥቂት ጥያቄዎች ስለዚህ ሐዲስ፡-

1. ይህ የሙሐመድ ተከታይ ጦጢት ስለፈፀመችው ኃጢአት ሊያውቅ የቻለው እንዴት ነው? ጦጣዎቹን ጠይቆ ወይንስ ወንጀሉን ስትፈፅም ተከታትሎ አይቷት? አይቷትስ ቢሆን ወንዱ ጦጣ ሕጋዊ ባሏ እንዳልሆነ በምን መንገድ አወቀ?

2. ወንዱ ጦጣ የት ገባ? ሮጦ አምልጦ ይሆን?

3. በእንስሳት ዓለም በተለይም በጦጣዎች ዘንድ እንዲህ ያለ ልማድ ስለመኖሩ ሙስሊሞች ማስረጃ ሊያቀርቡልን ይችላሉ?

አሁን ወደ ቁም ነገሩ፡፡ ይህ ሐዲስ አፈ ታሪክ መሆኑ ምንም ጥርጥ የለውም፡፡ ነገር ግን እንደ ተዓማኒ ታሪክ ተቆጥሮ ከቁርአን ቀጥሎ ትልቅ ጀረዳ በተሰጠው የሐዲስ ስብስብ ውስጥ ሰፍሯል፡፡ እንዲህ ያሉ ታሪኮችን እንደ እውነተኛ ታሪክ የሚቆጥሩ ሰዎች የአስተሳሰብ ደረጃቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡....”

እንግዲህ እኛ፣ ነብዩ ሙሓመድ ዝንጀሮ ወገሩ #አላልንም። እኛ ያልነው፣ የሐዲሱ ዘጋቢ ከእውነት የራቀ ዘገባ ሰቷል። ነገር ግን እጅግ ተአማኒ የሚባል ሓዲስ ውስጥ ሰፍሯል። ጦጣ ዬት ሃገር ነው ተጋብቶ፣ ሕግ አውጥቶ፣ ያመነዘረች ጦጢት ትገደል ብሎ የሚኖረው? ለማንኛውም ጥያቄዎቹን መድገም ስለሚሆንብኝ እተወዋለው።

በሎጂክ ውስጥ፣ #ፋላሲ (fallacy) የሚባሉ አሉ። #ሓሰተኛ_ሙግቶች እንደማለት ነው። ከእንዚህ ውስጥ፣ ሙስሊሞች ብዙ ግዜ #straw_man_fallacy የሚባለውን ሓሰተኛ ሙግት ሲያቀርቡ እናያለን። ይህ ማለት፣ አንድ ሰው የተናገረውን ነገር አጣሞ፣ መልሶ የተጣመመውን ሙግት ማፍረስ ሲሆን፣ ሰውዬው መጀመሪያ ላይ ከተናገረው ነገር ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ምላሽ ነው። ይሄው ነው እንግዲ ከላይ የሰጡን ምላሽ።

ፍየል ወዲህ፣ ቅዝምዝም ወዲያ!

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
በወንድም ዳንኤል የተዘጋጀ ተጨማሪ ምላሽ
————
አምር ቢን ማዕሙና የተባለ የሙሐመድ ሰሐባ ከእስልምና ዘመን በፊት አንዲት ጦጣ ዝሙት በመፈጸሟ ምክንያት ሌሎች ጦጣዎች ሲወግሯት ተመልክቶ እርሱም አብሯቸው እንደወገራት የተናገረበትን ሐዲስ ጠቅሰን ጥያቄ ማንሳታችን ይታወሳል። ይህንን ያነበበ አንድ አብዱል "መልስ" ብሎ የለጠፈውን "እውን ነቢዩ ጨካኝና ዝንጀሮ ወጋሪ ነበሩን?" በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሑፍ አንብበናል። ጸሐፊው የኦርቶዶክ መምህራንን ሲሳደብ ይታያል። ለዚህ ሥርኣት አልበኝነቱ መልስ መስጠቱን እናቆየውና የነገሩን አስኳል እንመልከት። ባጠቃላይ በጽሑፉ ውስጥ የኛን ሙግት የሚጠቅስ ምንም ነገር የለም።

1. ጦጢትን የወገራት ሙሐመድ ነው የሚል ነገር እኛ በጻፍነው ጽሑፍ ውስጥ የሌለ ቢሆንም ጸሐፊው "ሙሐመድ ነው ብለዋል!" በሚል መነሻ ልክ እንደተቆጣ ዝንጀሮ ያገኛውን ሰው ሁሉ ሲቧጭርና መንደሩን ሲያመሰቃቅል ይታያል። ይህ ጽሑፍ ከ 3 ዓመታት በፊት የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል። መቼስ መልሶ የለጠፈው ሰው የኛን ጽሑፍ ታሳቢ በማድረግ መሆኑ ግልጽ ነውና እኛ "ሙሐመድ ነው" ያልንበትን ቦታ እንዲያሳየን እንጠይቀዋለን። አለማንበብ "የነቢዩ" ሱና ቢሆንም ትዝብት ላይ ላለመውደቅ በተቻለ መጠን ማንበብ ጥሩ ነው።

2. እንዳየነው የጽሑፉ ርዕስ "እውን ነቢዩ ጨካኝና ዝንጀሮ ወጋሪ ነበሩን?" ይላል። ኋላ ላይም ሙሐመድ "የተላከበትን" ዓላማ ሲገልጽ "ከዚህ ሰይጣናዊ ተግባር ሊያወጣቸው" እንደሆነ ይገልጻል። ስለዚህ ዝንጀሮ መውገር ሰይጣናዊ ተግባር ከሆነ ሙሐመድ ሰውን የሚያክል ክቡር ፍጥረት ያለ በቂ ምክንያት ሲገድልና ሲያስገድል የኖረ፣ እራሱም ዝሙተኛ ሆኖ ሳለ ሌሎችን ሲወግር የነበረ በመሆኑ ይህንን ድርጊቱን ምን ልትለው ነው? ዝንጀሮ መውገርን "ሰይጣናዊ" ስላልከው ሌላ የከፋ ቃል ፈልግለት። ደግሞም እንስሳትን ያለ በቂ ምክንያት መግደል ትክክል ካልሆነ ሙሐመድ ጥቁር ውሾችን፣ እባቦችንና እንሽላሊቶችን ያለ ምንም ምክንያት እንዲገድሉ ሙስሊሞችን ማዘዙን እንዴት ትመለከተዋለህ? እንዲያውም እንሽላሊትን በአንድ፣ በሁለት ወይንም በሦስት ምት የገደለ ሰው እንደየደረጃው ከአላህ ዘንድ ምንዳ እንደሚጠብቀው ተናግሯል። (Muslim, Book 026, Number 5562; Muslim Book 026, Number 5564; Sunan of Abu Dawud Book 41, Number 5229; Bukhari 4.526)

3. ይህንን ድርጊት የጥንቶቹም ሆኑ የዘመኑ ሙስሊም ሊቃውንት ዝሙት የሰሩትን ሰዎች መውገር አስፈላጊ መሆኑን ለማሳየት ሲጠቅሱት ኖረዋል። ሐዲሱም ቢሆን በእስልምና የታረመ የተሳሳተ ተግባር እንደሆነ አይገልጽም። "ከዚህ ሰይጣናዊ ተግባር ሊያወጣቸው" ያልከው ምን ማስረጃ ይዘህ ነው? ዝሙት የሰሩትን ሰዎች መውገር ጥሩ ሆኖ ዝሙት የሰሩትን ጦጣዎች መውገር ሰይጣናዊ ድርጊት የሚሆንበት ምክንያትስ ምንድነው?

4. የኛ ሙግት ታሪኩ ሲጀመር ተረት እንጂ እውነት ባለመሆኑ "በተዓማኒ" ሐዲስ ውስጥ መካተቱ በሙሐመድ አጠቃላይ ታሪክ ላይ ጥያቄን ያስነሳል የሚል ነው። እንዲህ ያሉ ተረታ ተረቶችን ከእውነት የሚቆጥሩ ሰዎች ትክክለኛ ታሪክ ማስተላለፍ ይችላሉ ብሎ ማለት ዘበት ነው። ለዚህ ሙግት ምላሽ እንደሌለህ ስለምታውቅ ነው Strawman fallacy የሸከፈ ኮተት የለጠፍከው። መልስ መስጠት ካልቻሉ ዝም ማለት አንድ ነገር ነው። እንዲህ ያለ አርቲ ቡርቲ ከየትም አምጥቶ መለጠፍ ግን አንባቢን መናቅ ነው። ኧረ ወገናችን፤ አድማጮችህን የሚመጥን ነገር ጻፍ አለበለዚያ ደግሞ ለአቅመ ማስተማር እስክትበቃ ድረስ ጊዜ ወስደህ ተማር።
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
የሕያ የተባለ አንድ ሙሐመዳዊ እኛ ላቀረብናቸው የቁርአን ግጭቶች ዝርዝር ምላሽ የመስጠቱን ኃላፊነት ወስዶ ከዐሥረኛው ተራ ቁጥር ጀምሯል፡፡ የኛን ቅደም ተከተል ከመከተል ይልቅ Answering Islam ላይ የሚገኘውን የግጭት ዝርዝር ተራ ቁጥር ለመከተል እንደወሰነም ያስረዳል፡፡ በገጹ ላይ ከ 160 በላይ ግጭቶች ስለተዘረዘሩና በያንዳንዱ ግጭት ስርም አያሌ ንዑሳን ግጭቶች ስለሚገኙ አቅሙን ተረድቶ እኛ ላቀረብናቸው አጫጭር ጥያቄዎች መልስ ቢሰጥ ያዋጣው ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም ወሒድ የተባለ ሰለምቴ ነኝ ባይ እጅ እጅ በሚለው የጻጻፍ ስልቱ ተጠቅሞ ለጻፈው ጽሑፍ በከፊል መልስ መስጠታችን ይታወሳል፡፡ የወሒድ አካሄድ እንደማያዛልቅ ተረድቷል መሰል የሕያ ቁርአንን ለመታደግ እየተጣጣረ ይገኛል፡፡ ፅናቱን ይስጥህ ብለነዋል፡፡
ወደ መልሱ ስንገባ፡- ምላሽ ለመስጠት የሞከረው ሙሐመድ ሱራ 34፡50 ላይ “ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው ብመራም ጌታዬ ወደኔ በሚያወርደው ነው” በማለት የተናገረውን በተመለከተ ነው፡፡ በዚህ ጥቅስ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ሙሐመድ “እኔ ያመንኩትን እመኑ ተከተሉኝ” እያለ መለስ ብሎ ደግሞ “ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው” ማለቱ ትክክል አይደለም የሚል ነው፡፡ አራት ነጥቦችን በማንሳት መልስ ለመስጠት ሞክሯል፡-
የመጀመርያው ያነሳው ነጥብ ጥያቄው የተኮረጀ ነው የሚል ነው፡፡ የሕያ ስቅለትን በተመለከተ የጻፈውን “መጽሐፍ” በቀጥታ ከድረ ገፅ ላይ ገልብጦ ያሳተመ መሆኑን ስላጋለጥንበት እፍረቱን ለመሸፈን እንዲህ ያለ አፀፋዊ ክስ ማንሳቱ አያስገርምም፡፡ ሙሐመድ ቁርአን የተባለውን መጽሐፍ ማቀናበር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከቁርአን ግጭቶች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ያልተጠየቁበት ዘመን አልነበረም፡፡ በሙሐመድ ዘመን የነበሩ ብዙ ሰዎች የሙሐመድ መገለጥ እርስ በርሱ እንደሚጣረስ ተረድተው እንደነበርና በዚህም ምክንያት አላህ (በትክክለኛ ማንነቱ ሙሐመድ) ማስተባበያ “ማውረድ” አስፈልጎት እንደነበር ከቁርአን እንረዳለን (ሱራ 16፡101 አስባብ አን-ኑዙል ይመልከቱ)፡፡ ስለዚህ እነዚህ ጥያቄዎች ቁርአን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ሲጠየቁ የነበሩ በመሆናቸው እኛ በጠየቅናቸው ጥያቄዎችና ሌላ ቦታ በሚገኙት ጥያቄዎች መካከል የሚመሳሰል ነገር መኖሩ ያን ያህል ሊያስደንቀው አይገባም፡፡ ብዙ ጥያቄዎች ከኛ በፊት የተነሱ በመሆናቸው የሌሎች ወገኖች ጽሑፎች መነሻ ቢሆኑንም በራሳችን አባባል ለማስቀመጥ ሞክረናል፡፡ እኛ እንደ የሕያ የሰው ሥራ መቶ በመቶ ገልብጠን ቃል በቃል በመተርጎም “በግል ጥናት ያገኘነው” ከሚል መግለጫ ጋር በመጽሐፍ አሳትመን ለሽያጭ አላቀረብንም፡፡ በግል ጥናቶቻችን የተማርናቸውንም ሆነ ከሌሎች ሰዎች የተማርናቸውን ጉዳዮች ለወገኖች ጥቅም ስንል የማንንም የቅጂ መብት በማይነካ መንገድ በራሳችን አቀራረብ በነፃ እናስነብባለን፡፡ ምንጭ መጥቀስም ወሳኝ ሆኖ ሲገኝ ምሑራዊ ሥርዓትን በጠበቀ መንገድ እንጠቅሳለን፡፡ የሰው ሥራ መቶ በመቶ ገልብጦ፣ ቃል በቃል ተርጉሞ፣ አንድ ምንጭ እንኳ ሳይጠቅስ “በግል ጥናት ያገኘሁት ነው” የሚል መግለጫ በመግቢያው ላይ አክሎ ለሽያጭ ገበያ ላይ ያወጣ እንደ የሕያ ያለ ሰው እኛን የመተቸትና በኛ ደረጃ ቆሞ የመናገር የሞራል ብቃት የለውም፡፡ የየሕያን ድረ ገፅ የተመለከተ ሰው ልጁ ምንም ዓይነት ኦሪጅናል ሥራ እንደሌለውና ሁሉም ነገር ከሌሎች ድረ ገፆች ላይ የተኮረጀ መሆኑን በቀላሉ መገንዘብ ይችላል፡፡ (“ድህረ ገፅ” ብሎ የሚጽፍ ሰው ድረ ገፅ ለመክፈት የበቃ ሆኖ ራሱን መቁጠሩ በራሱ አስገራሚ ነው፡፡) “የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” የሚለው ብሒል የሕያን ጥሩ አድርጎ ይገልፀዋል፡፡ ሁኔታው በአጠቃላይ ጥንብር ብሎ ሰክሮ ጤነኛውን ሰው “ሰካራም!” ብሎ እንደሚሳደብ ሰካራም ሰው ዓይነት ነው፡፡
ሁለተኛ ላይ ያነሳው ነጥብ ሙሐመድን በቀጥታ እያናገሩ በሚመስል መልኩ የተቀመጡ የቁርአን አንቀፆች ሁሌም እርሱን ብቻ የሚገልፁ እንዳልሆኑና እርሱን እንደማሳያ በማንሳት ለሁሉም ሙስሊሞች መልዕክትን የሚያስተላልፉ መሆናቸውን የሚገልፅ ነው፡፡ ለዚህም ምሳሌ ይሆነኛል በማለት የተወሰኑ የቁርአን ጥቅሶችን ጠቅሷል፡፡ ሙሐመድን ብቻ የተመለከቱ ጥቅሶች እንዳሉም በመግለፅ የተወሰኑትን ከቁርአን አስነብቦናል፡፡ እኛ ጥያቄ ያነሳንበት ጥቅስ፣ ማለትም ሱራ 34፡50 ሙሐመድን የተመለከተ መሆኑን በማመን ከዚያ አንጻር ምላሽ የሰጠ በመሆኑ እዚህ ሐተታ ውስጥ መግባቱ ምን ፋይዳ እንዳለው ግልፅ አይደለም፡፡ እዲህ ሲል ትችቱን ይሰነዝራል፡- “እንደ ጠያቂው እሳቤ መሠረት ነብዩን ጠቅሶ የሚገለፅ ቃል ሁሉ እሳቸውን ብቻ የሚመለከት ነው ማለት ነው። ይህ ለቁርአን ባይተዋር የሆነ ሰው የሚፈጽመው ስህተት ነው፡፡” በኛ ጥያቄ ውስጥ እንደዚህ ያልንበትን ቦታ ወይንም እንዲህ ያለ እሳቤ ያንፀባረቅንበትን ነጥብ እንዲያሳየን እንጠይቀዋለን፡፡ እርሱ ራሱ ጥቅሱ ሙሐመድን የተመለከተ መሆኑን አምኖ ተቀብሎ ምላሹን ከዚያ አንፃር እስካዘጋጀ ድረስ ይህንን ነጥብ ማንሳቱም ሆነ በኛ ላይ ትችትን መሰንዘሩ የአንባቢን ሐሳብ ከመበተን የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡ የተጠቀማት አካሄድ የተለመደች የሙስሊም ሰባኪያን ማወናበጃ ናት፡፡
በሦስተኛ ደረጃ እንዲህ የሚል ምላሽ ይሰጣል፡- “አንቀፁ የሚያወራው ስለመለኮታዊ ራዕይ ወይንም ስለ አስተምህሮ መዛነፍ ሳይሆን እንደ ሰው በነበራቸው የግል ህይወት ዙሪያ ስለሚፈጠሩ ስህተቶች ነው። አንቀጹ "ብሳሳት" ብሎ የሚገልፀው የሳቸውን ሰብአዊ ባህሪይ ነው። ነብዩ መለኮታዊ ራዕይ የሚወርድላቸው ነብይ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ማንኛውም ሰው የግል ህይወት ያላቸው ሰውም ነበሩ። እንደሚታወቀው ደግሞ ነብያት ሰውኛ ባህሪያትንም የተጎናፀፉ ግለሰቦች እንጅ ከስህተት የተጠበቁ መላዕክት አይደሉም። በዚህም ሳቢያ በዕለትተዕለት ህይወታቸው ዙሪያ እንደማንኛውም ሰው ግላዊ ስህተቶችን ሊፈጽሙ ይችላሉ። ያ ስህተት ከሀይማኖታዊ እይታ አንፃር ሳይሆን ከግላዊ ስህተት አኳያ ብቻ ሊታይ እንደሚገባ ቁርአን በዚህ ክፍሉ ይነግረናል። ከኢማም ኢብን ከሲር ጀምረን የተለያዩ የተፍሲር ሊቃውንትን ስራ ብንመለከት ከዚህ ውጭ የተለየ ፍችን ሰጥተው አናገኝም።”

የሕያ ከተናገረው በተጻራሪ የተለያዩ ተፍሲሮችን ስንመለከት ጥቅሱ ስለ መለኮታዊ መገለጥ እየተናገረ ስለመሆኑ መገንዘብ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ያህል ተፍሲር ኢብን አባስ እንዲህ ይላል፡- (Say) to them, O Muhammad: (If I err) from the Truth and guidance, (I err only to my own loss) he says: the punishment of that is against my soul, (and if I am rightly guided) to the Truth and guidance (it is because of that which my Lord hath revealed unto me) that I am guided. … https://www.altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=0&tTafsirNo=73&tSoraNo=34&tAyahNo=50&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=2
በኢብን አባስ ማብራርያ መሠረት ጥቅሱ እያወራ ያለው ነፍስን ለጥፋት ስለሚዳርግ ስህተትና ነፍስን ስለሚያድን ምሪት ነው፡፡ ሙሐመድ እያለ ያለው ከመለኮታዊ ምሪት ስቶ ነፍሱን ለጥፋት በሚዳርግ ስህተት ውስጥ ቢገኝ ጥፋቱ ከእርሱ ውጪ ሌላ ማንንም ሰው ሊጎዳ እንደማይችል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ስህተት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ሙሐመድ ራሱን ለሰው ልጆች ሁ
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ሉ ምርጡና ወደር የለሽ ምሳሌ አድርጎ ስላቀረበ ነፍስን በሚያጠፋ ስህተት ውስጥ ቢገኝ እርሱን የተከተለ ሰው ሁሉ ለጥፋት መዳረጉ የማይቀር ነው፡፡
በየሕያ መሠረት ሙሐመድ እያወራ ያለው ነፍስን ለጥፋት ሊዳርጉ ስለማይችሉ ከሰው ልጅ የዕውቀት ውሱንነቶች የተነሳ ስለሚያጋጥሙ ተራ ስህተቶች ነው፡፡ በተነጻጻሪነትም ያቀረበው ጌታችን ኢየሱስ ከበለሲቱ ፍሬ ፍለጋ ሄዶ እንዳላገኘባት የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ነው (ማርቆስ 11:13)፡፡ የታሪኩን ትክክለኛ ትርጉምና የሚሰጠንን ጥልቅ መንፈሳዊ ትምሕርት በተመለከተ ከዚህ ቀደም በድረ ገፃችን ላይ አስፍረናል፤ ስለዚህ ለየሕያ አጀንዳን የማስለወጥ አካሄድ ቦታ መስጠት አንፈልግም፡፡ ሐሳቡ ሲጠቃለል ከዕውቀት ማነስ የተነሳ የሚፈጠሩ ስህተቶች ከመለኮታዊ ምሪት ጋር የሚገናኙ ወይንም ከኃጢአት የሚቆጠሩ ስህተቶች አይደሉም፤ ከሰብዓዊ ውሱንነት የተነሳ የሚፈጠሩ ከግለሰቡ ያለፈ ጉዳት የማያስከትሉ ተራ ስህተቶች ናቸው የሚል ነው፡፡ እንዲህ ያሉ ስህተቶች ኃጢአት እንዳልሆኑና የአንድን ነቢይ እውነተኛነትም ጥርጣሬ እንደማይጥሉ ያስማማናል፡፡ ነገር ግን ሙሐመድ እያለ ያለው “መሳሳት” ይህ ነው ወይ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ “አይደለም” የሚል ነው፡፡ ይህንን አስመልክቶ የአል-ጃለላይን ተፍሲር እንዲህ ይላል፡- Say ‘If I go astray from the truth I will be going astray only to my own loss that is to say the sin of my going astray shall be held against me… https://www.altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=0&tTafsirNo=74&tSoraNo=34&tAyahNo=50&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=2
በሁለቱ ጃለሎች ተፍሲር መሠረት ሙሐመድ “ብሳሳት” ያለው ኃጢአትን ሊያስከትል የሚችል ከመለኮታዊ ምሪት መሳትን የተመለከተ ስህተት እንጂ የሕያ እንዳለው በዕውቀት ውሱንነት ሳብያ ዕለት ዕለት የሚያጋጥሙ ጥቃቅን ግላዊ ስህተቶች አይደሉም፡፡ የሕያ ተፍሲሮችን ተመልክቶ ሳይሆን በመሰለኝና በደሳለኝ እያወራ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ከታወቁት ተፍሲሮች መካከል አንዱም እንኳ ሙሐመድ እያለ ያለው “ስህተት” ጥፋትን የማያስከትል ተራ የየዕለት ስህተት እንደሆነ የሚገልፅ አላየንም፡፡
ስናጠቃልል ሙስሊሞች ሙሐመድን ከትልልቅ ጉዳዮች እስከ ጥቃቅን ጉዳዮች ሊመስሉት ስለሚሞክሩ (አለባበስ፣ ጢም አቆራረጥ፣ ሽንትቤት አገባብ፣ አስተጣጠብ፣ አተኛኘት፣ ጥርስ አፋፋቅ፣ ወዘተ.) ጥቃቅን በተባሉት ጉዳዮች እንኳ ስህተት ሠርቶ ቢገኝ ራሱን ብቻ ሳይሆን የተከተሉትን ሰዎች በሞላ ያሳስታል፡፡ ሙሐመድ ከተሳሳተ ስህተቱና ጉዳቱ የመላው ሕዝበ ሙስሊም እንጂ የሙሐመድ ብቻ አይደለም፤ ስለዚህ “ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው…” ብሎ ማለቱ የተሳሳተ ንግግር ነው፡፡ ፈጣሪ እንዲህ ያለ ኢ-አመክንዮአዊ ንግግር ስለማይናገር ቁርአን የሙሐመድና የተባባሪዎቹ ፈጠራ እንጂ እውነተኛ የአምላክ ቃል ሊሆን አይችልም፡፡ ለየሕያና ለመሰሎቹ ያለን መልእክት እስልምናን በጭፍን ይከተሉታል እንጂ አይሟገቱለትም፤ ስለዚህ አሳማኝ መልስ ማምጣት ላትችሉ ነገር በከንቱ ዘመናችሁን አትፍጁ፤ ራሳችሁንም ለትዝብት አትዳርጉ፡፡
---------
በመጨረሻም፡- ኩረጃ ሱሱ የሆነው የሕያ ይህንን “መልስ” ከሞላ ጎደል የኮረጀው Answering Christianity ከተባለ ቅራቅንቦ ድረ ገፅ ላይ ነው፡፡ እባክህን “አይደለም” በለኝና እንደተለመደው ላጋልጥህ፡፡
---------
ዳንኤል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM