ወሒድ በእየሱስ ተመላኪነት
ከዚህ በፊት የክርስቶስ መመለክ፣አለመመለክ ጉዳይ ላይ ወሒድ ከጅሆቫ ዊትነሶች ሰርቆ ያቀረበውን ሙግት ማፍረሳችን ይታወቃል። በተለይ ደግሞ λατρεύω (ላትሬይኦ፣ አምልኮ) በሚለው ቃለ ዙሪያ ሙግታችንን አቅርበናል። የኡስታዞቹ ሙግት ይህ ቃል አንዴም ለእየሱስ አለመግባቱን ሲሆን እኛ ደግሞ መግባቱን በደምብ አሳይተናል። ለምሳሌ:-
የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 22
3፤ ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል( λατρεύσουσιν ) ፊቱንም ያያሉ፥ 4፤ ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።
ከላይ በተጠቀሰው ጥቅስ ላይ ማብራሪያም ሰጥተናል (እዚው ቻናል ላይ ማግኘት ይችላሉ)።
ወሒድ ይሄ መልስ ሲሰጠው እንግዲህ ካፈርኩ አይመልሰኝ ይመስል ከስህተቱ ከመማር ይልቅ ሌላ ተደራራቢ ስህተት ያላቸው ፅሁፎችን ለጥፏል። እሱንም በማያውቀው ቋንቋ (ግሪክ) እየገባ። ለማንኛውም እስኪ እንመልከተው።
ሙግቱን እንዲህ ብሎ ይጀምራል፣
“….ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* αὐτῷ μόνῳ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
"አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። ይህ ጌታ አምላክ ለኢየሱስ የዳዊትን ዙፋን የሰጠው አብ ነው”
ምላሽ:
1. αὐτῷ የሚል ቃል በማቴዎስ ወንጌል የገባበት አወቃቀርና በዮሓኒስ ራእይ የገባበት አወቃቀር ፈፅሞ የተለያየ ነው። ማቴዎስ ላይ የአረፍተ ነገሩ object አንድ ስም ወይም noun ነው። እሱም “ጌታ አምላክ” ነው። ልብ በል፣ ጌታ እና አምላክ አይልም። ለዚህ ነው αὐτῷ ነጠላ የሆነቸው። ይሄ አንድ “essence” (ማንነትና ምንነት የሚሉ አማርኛ ቃላቶች essence የሚለውን ቃል በፊሎሶፊ ደረጃ ስለማያብራሩ አንጠቀምም) ብቻ እንደሚመለክ የሚያሳይ ነው። ልብ በል፣ አንድ “አካል” ወይም person መሆኑን ክፍሉ ምንም አይነግረንም። ምክኒያቱም “አምላክ” የሚለው ቃል “essence” ነው። ለምሳሌ “ሰው” የሚል ቃል የኛን essence የሚገልፅ ነው፣ ልክ እንደዛው “አምላክም” የፈጣሪ essence ነው። እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ የምናምነው አንድ essence ያለው አምላክ በሶስት አካል(person) መኖሩን ነው። ስለዚህ፣ እየሱስ ሰይጣንን “ጌታ አምላክህን ብቻ አምልክ” ሲለው፣ ስለ essence እንጂ ስለ አካል እያወራና እራሱን ከአምላክነት ክፍል(category) እያወጣ አይደለም። ስለዚህ፣ ከአንድ በላይ የሚመለክ essence ስለሌለ αὐτοῖς የሚለውን ቃል መጠቀም አያስፈልግም ማለት ነው። በነገራችን ላይ፣ ወሒድ እዚህ ክፍል ላይ ስለ እኛ እምነት የተጣመመ ሙግት ሰርቶ እራሱ የሰራውን ሙግት መልሶ ማፍረስ መሞከሩ በሎጂክ ውስጥ strawman fallacy እንለዋለን።
2. ልጁ የዮሓኒስን ራእይ አፃፃፍ በማቴዎስ ወንጌል አይን አይቶ ኤግዝጄስስ መስራት መሞከሩ አንድ ቃል (ምሳሌ፣ αὐτῷ) ሁሌም ተመሳሳይ አይነት ፊቺ በሁሉም ሁኔታ በመፅሓፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሚኖረው አድርጎ ማሰቡን ያሳያል። ይሄ ደግሞ በመፅሓፍ ቅዱስ አተረጓገም ውስጥ word study fallacy እንለዋለን። አንድ ክፍል ላይ ፍቺ ለመስጠት የፀሓፊውን አፃፃፍ ስልት፣ ኮንቴክስት እና የመሳሰሉትን ማየት ያስፈልጋል። ቀጥለን የልጁን ፅሁፍ እንመልከት።
ቀጥሎ እንዲህ ብሎ ፅፏል
“ይህ ጌታ አምላክ ከበጉ ማንነት በሰዋስው ተነጥሎ ተቀምጧል፦
ራእይ 21፥22 *"ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና"* መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።
ልብ አድርግ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት እንደሆኑ ለማሳየት "ናቸው" በሚል የብዜት አያያዥ ግስ ተቀምጧል፥ በተጨማሪም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። ስለዚህ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት ናቸው፥ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አብ ከሆነ "በጉ" ደግሞ ኢየሱስ ነው። በጉ የሚታረድ ማንነት ስለሆነ ፍጡር ነው”
ምላሽ
እዚህ ላይ ወይም ወሒድ ግሪክ ማንበብ አይችልም ወይ ደግሞ ውሸታም ነው። ግሪኩን እናንብብ
Καὶ ναὸν οὐκ εἶδον ἐν αὐτῇ· ὁ γὰρ Κύριος ὁ Θεὸς ὁ Παντοκράτωρ ναὸς αὐτῆς #ἐστιν, καὶ τὸ Ἀρνίον
በግሪኩ፣ “ናቸው” የሚል የብዜት አያያዝ #የለም። ἐστιν (estin) የሚለው ቃል የ “eimi, ‘is’,” ሶስተኛ መደብ ሆኖ ነጠላ ነው። ብዜትን ማሳየት ቢፈልግ ኖሮ ἐισιν (eisin) ይሆን ነበር። ስለዚህ፣ በአማርኛው የአማርኛን ግራመር እንጠብቃለን ብሎ ወደ “ናቸው” ተሮገሙት እንጂ ትክክለኛው ግሪክ “ነው” የሚል ነጠላ ትርጓሜ ይሰጣል። ልብ በል፣ እየሱስና አብን ጠርቶ በነጠላ እየገለፃቸው ነው ማለት ነው።
“በጉ የሚታረድ ስለሆነ ፍጡር ነው” ብሎ ወሒድ ተናግሯል። በዚህች አረፍተ ነገር ብቻ ሁለት ሓሰተኛ ሙግቶችን fallacies ሰርቷል። Begging the question እና straw man። ግዜውም ርዕሳችንም ስላልሆነ እነኚህ ሁለቱ fallacyዎችን እራሱ እንዲያጠናና ለሚቀጥለው እንዲያስተካክል ምክሬን እለግስለታለው።
ቀጥሎ ልጁ እንዲህ ይላል
“ራእይ 22፥3 *"የእግዚአብሔር እና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል"*፥ λατρεύσουσιν αὐτῷ ፊቱንም ያያሉ።
እግዚአብሔር እና በጉ ሁለት ማንነት መሆናቸው ለማሳየት አሁንም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። አሁንም "አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። "ያመልኩታል" እንጂ "ያመልኳቸዋል" አላለም፥ ይህ የሚመለክ እግዚአብሔር እንጂ በጉ አይደለም፦”
ምላሽ
1. በመጀመሪያ ደረጃ እግዚያብሔር እና በጉ ሁለት person እንጂ ሁለት essence አይደሉም። ስለዚህ “እና” ወይም kai ሁለት person መሆናቸውን ከማሳየት የዘለለ ምንም ለሙግትህ ጥቅም የለውም
2. “አውቶ” የሚለው ቃል፣ ነጠላ መሆኑ ይታወቃል። ቅድም እንዳየነውም estin የሚለውን ነጠላ verb to be ለአብና በጉ ዮሓኒስ ሲጠቀም አይተናል። እዚህም ክፍል ላይ ነጠላ pronoun ለሁለት አካል ሲጠቀም እናያለን። ብዙ ምሁራን የዮሓኒስን ራእይ ሲያጠኑ፣ የአብና ወልድን እና ሌሎች አንዳንድ ቴዎሎጂካል ነገሮችን አስመልክቶ ዮሓኒስ የግራመር ሕጎችን ለስን መሎኮት አላማ ሲያስተካክላቸው ተስተውሏል። ራዕይ ምዕ 1:4 ላይ ይሄንን ማስተዋል እንችላለን። ይሄ ግን ሌላ ትልቅ ርዕስ ስለሆነ ወደሱ አልገባም። ነገር ግን ራእይ 22:3 ላይ ምሁራን የፃፉትን ላስነብባቹ።
ቀጥለህ/ሽ አንብብ/ቢ....👇👇
✍Ναολ Τζιγι
@Jesuscrucified