ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
የተወገረችው ዝንጀሮን አስመልክቶ ሙሓመዳውያን የሰጡት ምላሽ ሲገመገም


ከቀናት በፊት ወንድም ዳንኤል በእስላማዊ ሓዲሳት ውስጥ ሰፍሮ ስለሚገኘው ስለአንድ አስቂኝ አፈ ታሪክ ፅፎልን ነበር። እሱንም አስመልክቶ ሎጂካል በሆነ መንገድ ጥያቄ ጠይቋል። ሓዲሱ እንዲህ የሚል ነው:-

Narrated 'Amr bin Maimun:
During the pre-Islamic period of ignorance I saw a she-monkey surrounded by a number of monkeys. They were all stoning it, because it had committed illegal sexual intercourse. I too, stoned it along with them. (Sahih al-Bukhari, Volume 5, Book 58, Number 188)

“ዓምር ቢን ማዕሙና እንደተናገረው፡-
‹‹ከእስልምና በፊት በነበረው ያለማወቅ ዘመን አንዲት ሴት ጦጣ በብዙ ጦጣዎች ተከባ አየኋት፡፡ ሕገ ወጥ የወሲብ ግንኙነት በመፈፀሟ ምክንያት በድንጋይ ሲወግሯት ነበር፡፡ እኔም አብሬያቸው ወገርኳት፡፡››” (ሳሂህ አል-ቡኻሪ፣ ቅፅ 5፣ መጽሐፍ 58፣ ቁጥር 188)

ከኛ የተጠየቀውን ጥያቄ በኋላ እንመጣበታለን፣ አሁን ግን የአንዱን የሙስሊም አፖሎጄቲክስ ተማሪ መልስ እንመልከት።

እንዲህ ይላል:

“እውን ነብዩ ”ﷺ” ጨካኝና ዝንጀሮ ወጋሪ ነበሩን?......
ግን እስከመቼ ነው ነገሩ? የዛሬው ቅጥፈት ደግሞ ነብዩ ”ﷺ” ዝንጀሮ ወግረዋል ጨካኝ ናቸው ምናምን የሚል ሂስ ነው።............ይህንን ሃዲስ ነው አጣመው በሌለ ትርጉም ነብዩን የሚወነጅሉትና የሚቀጥፉበት ይህ ነው። አሁንስ አበዙትና ጠቅላላ ሙኽ ማፊ ሆነው አረፉት።እዚህ ሃዲስ ውስጥ ምንም ስለነብዩ ”ﷺ” ማንም ያወራ የለም። ድርጊቱን የሚተርክልን *አምር* ነው።ዝንጀሮዋንም ወገርኩኝ ያለው *አምር* ነው። እርሱ የራሱን ታሪክ የሚነግረን ያለው።

ከቁርአን መውረድ በፊት በጃሂልያው ዘመን አንዲት ዝንጀሮ በዙሪያዋ በዝንጀሮዎች ተከባ አየሁ።ህገ ወጥ የወሲብ ግንኙነትን ፈፅማለች ብለው በድንጋይ እየወገሯት ነበር።እኔም ከእነርሱ ጋር በመሆን ወገርኳት።

ከኢስላም በፊት ይላል እንግሊዝኛው ላይ እና አረብኛው فِي الْجَاهِلِيَّةِ *ፊል ጃሂሊየቲ* ነው የሚለው ይህም ማለት በድንቁርናቸው ዘመን በዝቅጠታቸው ዘመን ማለት ነው።”

በአጭሩ መልሳቸው ይሄን ነው የሚመስለው። ነገር ግን #የኛ_ጥያቄ_ይሄ_ነበር_ወይ? በፍፁም አልነበረም። በእርግጥ ፀሓፊው መልሱ “ከሶስት አመት በፊት ለኦርቶዶክስ መምህራን የተሰጠ” መሆኑን ገልጿል። ቢሆንም የአሁኑን ምላሽ የሰጠው፣ ልክ እኛ ጥያቄውን እዚህ ቻናል ላይ ከለጠፍን በኋላ እንደ ምላሽ ተደርጎ ነው። ለማንኛውም የኛ ጥያቄ የነበረው እንዲህ የሚል ነው:

“ይህንን(ሐዲስ) የተናገረው ከሙሐመድ ተከታዮች መካከል አንዱ ሲሆን ተዓማኒ ሐዲስ ተደርጎ በአል-ቡኻሪ ስብስብ ውስጥ ተካቷል፡፡ ጥቂት ጥያቄዎች ስለዚህ ሐዲስ፡-

1. ይህ የሙሐመድ ተከታይ ጦጢት ስለፈፀመችው ኃጢአት ሊያውቅ የቻለው እንዴት ነው? ጦጣዎቹን ጠይቆ ወይንስ ወንጀሉን ስትፈፅም ተከታትሎ አይቷት? አይቷትስ ቢሆን ወንዱ ጦጣ ሕጋዊ ባሏ እንዳልሆነ በምን መንገድ አወቀ?

2. ወንዱ ጦጣ የት ገባ? ሮጦ አምልጦ ይሆን?

3. በእንስሳት ዓለም በተለይም በጦጣዎች ዘንድ እንዲህ ያለ ልማድ ስለመኖሩ ሙስሊሞች ማስረጃ ሊያቀርቡልን ይችላሉ?

አሁን ወደ ቁም ነገሩ፡፡ ይህ ሐዲስ አፈ ታሪክ መሆኑ ምንም ጥርጥ የለውም፡፡ ነገር ግን እንደ ተዓማኒ ታሪክ ተቆጥሮ ከቁርአን ቀጥሎ ትልቅ ጀረዳ በተሰጠው የሐዲስ ስብስብ ውስጥ ሰፍሯል፡፡ እንዲህ ያሉ ታሪኮችን እንደ እውነተኛ ታሪክ የሚቆጥሩ ሰዎች የአስተሳሰብ ደረጃቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡....”

እንግዲህ እኛ፣ ነብዩ ሙሓመድ ዝንጀሮ ወገሩ #አላልንም። እኛ ያልነው፣ የሐዲሱ ዘጋቢ ከእውነት የራቀ ዘገባ ሰቷል። ነገር ግን እጅግ ተአማኒ የሚባል ሓዲስ ውስጥ ሰፍሯል። ጦጣ ዬት ሃገር ነው ተጋብቶ፣ ሕግ አውጥቶ፣ ያመነዘረች ጦጢት ትገደል ብሎ የሚኖረው? ለማንኛውም ጥያቄዎቹን መድገም ስለሚሆንብኝ እተወዋለው።

በሎጂክ ውስጥ፣ #ፋላሲ (fallacy) የሚባሉ አሉ። #ሓሰተኛ_ሙግቶች እንደማለት ነው። ከእንዚህ ውስጥ፣ ሙስሊሞች ብዙ ግዜ #straw_man_fallacy የሚባለውን ሓሰተኛ ሙግት ሲያቀርቡ እናያለን። ይህ ማለት፣ አንድ ሰው የተናገረውን ነገር አጣሞ፣ መልሶ የተጣመመውን ሙግት ማፍረስ ሲሆን፣ ሰውዬው መጀመሪያ ላይ ከተናገረው ነገር ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ምላሽ ነው። ይሄው ነው እንግዲ ከላይ የሰጡን ምላሽ።

ፍየል ወዲህ፣ ቅዝምዝም ወዲያ!

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified