ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
34 “”በዘጠኝ ሰዓትም”” ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤
በዚህ ሁለም ይስማማል፤ ኢየሱስ ተሰቀለ የተባለው ከ ቀኑ ጠዋት 3 ሰአት ነው፤ ከዮሃንስ ዘገባ ጋር ፍጭቱን ከማየታችን በፊት ዮሃንስ የሚጠቀመው የዕብራውያን አቆጣጠር መሆኑን በአፅንኦትና በአንክሮት እንመልከት፦
ዮሐንስ 1፥40 መጥታችሁ እዩ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ “አሥር ሰዓት” ያህል ነበረ።}}}}}
———
#መልስ
ይህ ዮሐንስ የሮማውያንን አቆጣጠር መጠቀሙን ከሚያሳዩ አጋጣሚዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ አንዳንድ ተርጓሚዎች የተጠቀሰው ሰዓት ከሰዓት በኋላ አሥር ሰዓት እንደሆነ ቢገምቱም በግሪኩ ንባብ ጠዋት ይሁን ከሰዓት አልተነገረም፡፡ አስር ሰዓት (ከኛ አቆጣጠር ጋር ተመሳሳይነት ባለው የአይሁድ አቆጣጠር ከጠዋቱ አራት ሰዓት) የተባለው የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ከኢየሱስ ጋር የተገናኙበት ሰዓት በመሆኑ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተገናኝተው ቀኑን ሙሉ አብረውት እንደ ዋሉ መናገር ይቻላል፡፡ የአማርኛው ትርጉም ግልፅ ባይሆንም ኪንግ ጀምስና ሌሎች ትርጉሞች ሰዓቱ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን ያገኙበት ሰዓት መሆኑን በሚያመለክት መንገድ ተርጉመውታል፡-
“He saith unto them, Come and see. They came and saw where he dwelt, and abode with him that day: for it was about the tenth hour.” (KJV)
He said to them, “Come and you will see.” So they came and saw where he was staying, and they stayed with him that day, for it was about the tenth hour. (ESV)
He said to them, "Come, and you will see." So they came and saw where He was staying; and they stayed with Him that day, for it was about the tenth hour. (NASB)
"Come and you'll see," He replied. So they went and saw where He was staying, and they stayed with Him that day. It was about 10 in the morning. (HCSB)
ከነዚህ ትርጉሞች በተለየ መንገድ የተረጎሙ ቢኖሩም አሥር ሰዓት ከተገናኙና አብረውት እንደዋሉ ከተነገረ በሮማውያን አቆጣጠር ጠዋት አሥር ሰዓት (በአይሁድ አራት ሰዓት) እንጂ ከሰዓት በኋላ ሊሆን አይችልም፡፡
———
{{{{{ዮሐንስ 4፥6 በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ “”ጊዜውም ስድስት ሰዓት”” ያህል ነበረ።
ድካም ያለበት ቀትር ስድስት ሰአት የዕብራውያን አቆጣጠር እንጂ የሮማውያን አቆጣጠር አይደለም፤ ምክንያቱም የሮማውያን ስድስት ሰአት የዕብራውያን ከምሽቱ 12 ሰአት አሊያም ከጎህ 12 ሰአት ነው፤}}}}}
———
#መልስ
በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 4 ላይ የተጠቀሰው ስድስት ሰዓት ቀትር ስድስት ሰዓት እንደሆነ በብዙዎች ዘንድ ቢታመንም ማስረጃ የለውም፡፡ በሮማውያን አቆጣጠር ምሽት ስድስት ሰዓት (በአይሁድና በእኛ ደግሞ ምሽት አስራ ሁለት ሰዓት) እንዳይሆን የሚያደርገው ምንም ነገር የለም፡፡ በጠራራ ፀሐይ ውኀ ለመቅዳት መሄድ ያልተለመደ ስለሆነ (ዘፍ. 24፡11) ብዙ ሰባኪዎች የሳምራዊቷን ሴት በዚያ ሰዓት ውኀ ለመቅዳት መሄድ ሲያብራሩ ጥሩ ታሪክ ስላልነበራት ከሰዎች ዕይታ ለመሰወር በማሰብ ሰዎች ውኀ ለመቅዳት የማይሄዱበትን አሳቻ ሰዓት እንደመረጠች በመናገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተባለ ታሪክ ፈጥረዋል፡፡ ይህ ግን ማስረጃ ሊቀርብለት የማይችል ግምት ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ደክሞት በውኀ ጉድጓድ አጠገብ መቀመጡ ቀኑን ሙሉ መጓዙን የሚያመለክት ሲሆን ፀሐይ ስታዘቀዝቅ ውኀ ለመቅዳት መሄድ ደግሞ የተለመደ ነበር፡፡ ስለዚህ በዚህ ስፍራ ላይ 6 ሰዓት የተባለው በኛና በአይሁድ አቆጣጠር እኩለ ቀን 6 ሰዓት ሳይሆን በሮማውያን አቆጣጠር 6፣ በኛና በአይሁዶች አቆጣጠር ደግሞ አመሻሽ 12 ሰዓት አካባቢ ነበር፡፡
———
{{{{{ይህን ሃቅ ይዘን የዮሃንስ ዘጋቢ ጋር ኢየሱስ ስድስት ሰአት ላይ እንኳን ሊሰቀል ይቅርና ገና ህዝቡ ስቀለው እያሉ ይጮኹ እንደነበር ይተርካል፦
ዮሃንስ 19፥14-15 ለፋሲካም የማዘጋጀት ቀን ነበረ፤ “ስድስት ሰዓትም” የሚያህል ነበረ፤ አይሁድንም፦ እነሆ ንጉሣችሁ አላቸው። እነርሱ ግን፦ አስወግደው፥ አስወግደው፥ “”ስቀለው”” እያሉ ጮኹ።
ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? በሰቀሉት ጊዜ 3 ሰአት ነበረ ብሎ የሚተርከው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ 6 ሰአት ላይ ገና አልተሰቀለም ብሎ የሚተርከው የዮሃንስ ዘጋቢ?}}}}}
———
#መልስ
የቱን ሃቅ ይዘህ ነው እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረስከው? አይሁድ ኢየሱስን ወደ ጲላጦስ የወሰዱት በሮማውያን አቆጣጠር ማለዳ 6 ሰዓት ማለትም በአይሁድ አቆጣጠር ጠዋት 12 ሰዓት ነበር፤ በአይሁድ አቆጣጠር 3 ሰዓት ላይ ተሰቀለ፡፡ ኢየሱስ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ ለፍርድ ከቀረበ 3 ሰዓት ላይ ተሰቀለ ቢባል ምንም ግጭት አይፈጥርም፡፡ ዮሐንስ የሮማውያንን አቆጣጠር መጠቀሙን ከምንም ዓይነት ጥርጣሬ በጸዳ ሁኔታ እንድናምን የሚያደርገን ማስረጃ እዚያው በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ይገኛል፡-
“ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።” (ዮሐንስ 20፡19)
በአይሁድ የሰዓት አቆጣጠር መሠረት ቀን የሚቆጠረው ከምሽት በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ እሑድ ከ 12 ሰዓት በኋላ ሰኞ ነው፡፡ ዮሐንስ የአይሁድን የሰዓት አቆጣጠር ቢጠቀም ኖሮ “ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ…” ከማለት ይልቅ “ያም ቀን ካለፈ በሳምንቱ በሁለተኛው…” ማለት ነበረበት፡፡ ነገር ግን በሮማውያን የሰዓት አቆጣጠር ቀጣዩ ቀን የሚጀምረው ከእኩለ ሌሊት በመሆኑ ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ሲገለጥ ገና እሑድ ነበር ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የተገለጠው ፀሐይ ከገባችና በአይሁድ አቆጣጠር ሁለተኛው ቀን ከገባ በኋላ መሆኑን ሉቃስ 24፡19-40 ላይ ከሚገኘው ተጓዳኝ ትራኬ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ጥቅስ ዮሐንስ የሮማውያንን አቆጣጠር መጠቀሙን ከጥርጣሬ በጸዳ ሁኔታ ያረጋግጥልናል፡፡ ስለዚህ ያንተ ሙግት ቦታ የሚሰጠው አይደለም፡፡
———
{{{{{ነጥብ ሶስት “ሶስት ቀን”
ኢየሱስ የአላህ ነብይ ነው አይዋሽም፤ መቼም አራቱ ወንጌላት ላይ ያሉት ቃላት አይደለም የኢየሱስ ይቅርና የመጀመሪያዎቹ ፀሃፊያን ያልሆኑ ንግግሮች በእማኝነትና በአስረኝነት ማቅረብ ይቻላል፤ ነገር ግን ነጥባችን እርሱ አይደለም፤ ኢየሱስ ተናገረ ተብሎ የተቀጠፈበት ነገር እርስ በእርሱ ይጋጫል፤ እንደ ማርቆስ ዘጋቢ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በኃላ” የሚለው መስተዋድድ በአራተኛው ቀን አሊያም በአምስተኛው ቀን ሊሆን ይችላል፤ ግን ሶስኛውን ቀን አይጨምርም፦
ማርቆስ 8፥31 የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ሊነሣ” እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Beltshazar)
የማቴዎ ዘጋቢ ደግሞ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በ” የሚለው መስተዋድድ ሶስተኛውን ቀን ብቻ የሚያመለክት ነው፦
ማቴዎስ 16፥21 ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ “”በሦስተኛውም ቀን” ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።
ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ነው ብሎ የሚተርከው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ነው ብሎ የሚተርከው የማቴዎስ ዘጋቢ?}}}}}
———
#መልስ
በመጀመርያው ክፍለ ዘመን ለነበረ አይሁዳዊ “በሦስተኛው ቀን” እና “ከሦስት ቀን በኋላ” የሚሉት አባባሎች ልዩነት አልነበራቸውም፡፡ ይህንን ለመረዳት የአይሁድ መሪዎች ለጲላጦስ የተናገሩትን ማየት በቂ ነው፡-
“ጌታ ሆይ፥ ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ፦ ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን። እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም፦ ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ፥ የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ አሉት።” (ማቴ. 27፡63-64)
የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስ ከሦስት ቀን በኋላ እንደሚነሳ መናገሩን ያስታወቁ ሲሆን መቃብሩ ግን እንዲጠበቅ የጠየቁት እስከ ሦስተኛው ቀን ነው፡፡ ስለዚህ በመጀመርያው ክፍለ ዘመን ለነበሩት አይሁድ ከሦስት ቀን በኋላ ማለት አራተኛው ወይንም አምስተኛ ቀን ማለት ሳይሆን እስከ ሦስተኛው ቀን ማለት ነው፡፡ በዚያን ዘመን በነበሩት አይሁድ አቆጣጠር ደግሞ ማንኛውም የቀን ክፍል እንደ ሙሉ ቀን ስለሚቆጠር አርብ ፀሐይ ከመግባቷ በፊት አንድ ቀን፣ ፀሐይ ከገባች በኋላ እስከ ቅዳሜ ምሽት ሁለተኛው ቀን፣ ከቅዳሜ ምሽት እስከ እሑድ ማለዳ ሦስተኛው ቀን ይሆናል፡፡ ቀጣዩ ቀን የሚገባው ፀሐይ ከገባች በኋላ ነው፡፡ ከዛሬ 2000 ዓመታት በፊት የነበረውን አነጋገር ወደ ራሳችን ዘመን አምጥተን በኛ ባሕልና አነጋገር መተርጎም ለስህተት ይዳርጋል፡፡
—————
ለበለጠ መረጃ 👉 www.ewnetlehulu.org ይጎብኙ፡፡
----------------
ወንድም ዳንኤል፡፡
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ሱረቱ አል ሐቅ (የእውነት ምዕራፍ)
፩) ከታላቁ ንጉስ ከጥልቁ ተልኬ
አዲስ አስተምህሮ በጥበብ ፈብርኬ
ግሩም የሞት መንገድ ይዤ መጥቻለው
ሙሐመድ ሆይ ተነስ አንብብ ብዬሃለው
፪) ከአዋቂ አልዋልኩኝ ኑሮዬ መደዴ
ጥንት እረኛ ነበርኩ አሁንም ነጋዴ
የግመልን ጭራ ከመከተል በቀር
እንዴት አነባለሁ አላውቅ የፊደል ዘር
፫) ማንበብ ትችል አትቻል ምን አውቅልሀለው
አንብብ ተብለሃል ተነስ ብዬሃለው
ኋላ ጉሮሮህን አንገትህን አንቄ
ኃይሌን ሳላሳይህ ከምድር ደባልቄ
ታነብ እንደው አንብብ ምንድነው ሙግቱ
የክህደት መንግሥት ሲጣል መሰረቱ
፬) ይኸው አነበብኩኝ ሌላ ምን ምርጫ አለ
ነፍሴ ተጨነቀች ጉልበት ክንዴ ዛለ
የወራቃ ምክር የከድጃ ቀሚስ
ከደወሉ ሥቃይ ከአስጨናቂው መንፈስ
ተስማምቼ እንድኖር የግዴን ከገፋኝ
ስጠኝ አነባለሁ እኔ ምን አለፋኝ
፭) በፈጣሪ ባሮች በነቢያት ትንቢት
ከዓለም አስቀድሞ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት
አብ ወልድን ወልዶታል ተብሎ የተፃፈው
ጠንቅ ስለሆነ በቸልታ እለፈው
ይልቅ ይህን እውነት ጥንት የተነገረው
አይወልድ አይወለድ በልና ቀይረው
፮) ጌታ ነው አምላክ ነው የሚሉት ኢየሱስ
ነውር የሌለበት ቢሆን እንኳ ቅዱስ
እንኳን ቃል ተናግሮ ክንዱ ተዘርግቶ
ተዐምራት ቢፈፀም ስሙን ብቻ ጠርቶ
የመንግሥቴ ሥጋት አጥፊ በመሆኑ
ክብሩን በማጓደል ሰዎች እንዳይድኑ
መለኮቱን ክደህ በሰውነት ፃፈው
ከነቢያት ተርታ አርገህ አሰልፈው
፯) በደም ተዋጅተናል ይሉት አማርኛ
ላመኑበት ቤዛ ለእኔ ግን ጠንቀኛ
ነውና የሚያፈርስ የሲኦልን ደጃፍ
ይህንን ለማስካድ በፍፁም እንዳትሰንፍ
ተመሳሰለ እንጂ መሲሁ መች ሞተ
በጥርጣሬ ነው ወሬ የተዛመተ
ብለህ ስበካቸው ለሚሰሙህ ሁሉ
ችላ እንዲባል ትጋ ነገረ መስቀሉ
፰) ይሄን ታላቅ ሥራ ሰፊ ተልዕኮ
ጅብሪል ሲሰጥህ ከእኔ ዘንድ ተልኮ
በርትተህ ሥራ እንጂ በትጋት ፈጽመው
ኃጢአት በደልህን ከጉዳይ አልፅፈው
ብትፈልግ ፈት ሴት አሊያም ድንግሊቱን
ከማደጎ ልጅህ ብትቀማ ሚስቲቱን
የነቢያት ራስ እኔ ነኝ ብትልም
የዘረፋን ገንዘብ ለብቻህ ብትወስድም
ሀላል ነው በአንተ ዘንድ ነውር የለብህም
ሙሐመድ ሆይ ፅና ፈፅሞ አልተውህም
ከቅዱስ መጽሐፍ የተገለበጠው
ከጥንት ተረቶች የተሸቃቀጠው
ተነቅሶ ሲወገድ ሲገለጥ እውነቱ
የመሐመድ ቁራን ይኸው ነው መልዕክቱ !!!
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ሱረቱ አል ሐቅ (የእውነት ምዕራፍ)
፩) ከታላቁ ንጉስ ከጥልቁ ተልኬ
አዲስ አስተምህሮ በጥበብ ፈብርኬ
ግሩም የሞት መንገድ ይዤ መጥቻለው
ሙሐመድ ሆይ ተነስ አንብብ ብዬሃለው
፪) ከአዋቂ አልዋልኩኝ ኑሮዬ መደዴ
ጥንት እረኛ ነበርኩ አሁንም ነጋዴ
የግመልን ጭራ ከመከተል በቀር
እንዴት አነባለሁ አላውቅ የፊደል ዘር
፫) ማንበብ ትችል አትቻል ምን አውቅልሀለው
አንብብ ተብለሃል ተነስ ብዬሃለው
ኋላ ጉሮሮህን አንገትህን አንቄ
ኃይሌን ሳላሳይህ ከምድር ደባልቄ
ታነብ እንደው አንብብ ምንድነው ሙግቱ
የክህደት መንግሥት ሲጣል መሰረቱ
፬) ይኸው አነበብኩኝ ሌላ ምን ምርጫ አለ
ነፍሴ ተጨነቀች ጉልበት ክንዴ ዛለ
የወራቃ ምክር የከድጃ ቀሚስ
ከደወሉ ሥቃይ ከአስጨናቂው መንፈስ
ተስማምቼ እንድኖር የግዴን ከገፋኝ
ስጠኝ አነባለሁ እኔ ምን አለፋኝ
፭) በፈጣሪ ባሮች በነቢያት ትንቢት
ከዓለም አስቀድሞ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት
አብ ወልድን ወልዶታል ተብሎ የተፃፈው
ጠንቅ ስለሆነ በቸልታ እለፈው
ይልቅ ይህን እውነት ጥንት የተነገረው
አይወልድ አይወለድ በልና ቀይረው
፮) ጌታ ነው አምላክ ነው የሚሉት ኢየሱስ
ነውር የሌለበት ቢሆን እንኳ ቅዱስ
እንኳን ቃል ተናግሮ ክንዱ ተዘርግቶ
ተዐምራት ቢፈፀም ስሙን ብቻ ጠርቶ
የመንግሥቴ ሥጋት አጥፊ በመሆኑ
ክብሩን በማጓደል ሰዎች እንዳይድኑ
መለኮቱን ክደህ በሰውነት ፃፈው
ከነቢያት ተርታ አርገህ አሰልፈው
፯) በደም ተዋጅተናል ይሉት አማርኛ
ላመኑበት ቤዛ ለእኔ ግን ጠንቀኛ
ነውና የሚያፈርስ የሲኦልን ደጃፍ
ይህንን ለማስካድ በፍፁም እንዳትሰንፍ
ተመሳሰለ እንጂ መሲሁ መች ሞተ
በጥርጣሬ ነው ወሬ የተዛመተ
ብለህ ስበካቸው ለሚሰሙህ ሁሉ
ችላ እንዲባል ትጋ ነገረ መስቀሉ
፰) ይሄን ታላቅ ሥራ ሰፊ ተልዕኮ
ጅብሪል ሲሰጥህ ከእኔ ዘንድ ተልኮ
በርትተህ ሥራ እንጂ በትጋት ፈጽመው
ኃጢአት በደልህን ከጉዳይ አልፅፈው
ብትፈልግ ፈት ሴት አሊያም ድንግሊቱን
ከማደጎ ልጅህ ብትቀማ ሚስቲቱን
የነቢያት ራስ እኔ ነኝ ብትልም
የዘረፋን ገንዘብ ለብቻህ ብትወስድም
ሀላል ነው በአንተ ዘንድ ነውር የለብህም
ሙሐመድ ሆይ ፅና ፈፅሞ አልተውህም
ከቅዱስ መጽሐፍ የተገለበጠው
ከጥንት ተረቶች የተሸቃቀጠው
ተነቅሶ ሲወገድ ሲገለጥ እውነቱ
የመሐመድ ቁራን ይኸው ነው መልዕክቱ !!!
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ተዋወቋቸው!
እኚህ ሰው አባ ዘካርያ ቦትሮስ (Father Zakaria Botros) በመባል ይታወቃሉ፡፡ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቄስ ሲሆኑ ነዋሪነታቸው በአሜሪካን አገር ነው፡፡ በሙስሊም ሊቃውንት ዘንድ እጅግ ከሚፈሩና ከሚጠሉ ሰዎች መካከል የመጀመርያውን ደርጃ ይይዛሉ፡፡ እንዲህ የመፈራታቸውና የመጠላታቸው ምስጢር ሌላ ሳይሆን የእስልምናን ድብቅ ሚስጢራት አደባባይ በማውጣትና የክርስቶስን ወንጌል በመመስከር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን ወደ ብርሃን ማምጣት መቻላቸው ነው፡፡ በእሳቸው አገልግሎት ብቻ በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ 6 ሚሊየን የሚሆኑ ሙስሊሞች ክርስትናን እንደሚቀበሉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን “የዳንኤል ሽልማት” በመባል የሚታወቀውን ዓመታዊ ሽልማት አበርክታላቸዋለች፡፡ የእስልምና አሸባሪ ቡድን የሆነው አልቃኢዳ እሳቸውን ለሚገድል ሰው የ 60 ሚሊየን ዶላር ስጦታ ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡ ይህንን አሜሪካ ኦሳማ ቢንላደንን ለሚጠቁም ሰው እሰጣለሁ ካለችው የ 30 ሚሊየን ዶላር ጋር ስናነፃፅር እኚህ ሰው ለእስልምና ምን ያህል ስጋት እንደሆኑ እንገነዘባለን፡፡ በአረብኛ ቋንቋና አልፎ አልፎም በእንግሊዘኛ የሚተላለፈው የቴሌቪዥን ጣቢያቸው Alfady በመባል የሚታወቅ ሲሆን NileSat ላይ ይገኛል፡፡
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
የጠፉ የቁርአን ክፍሎች
ቁርአንን በአንድ ጥራዝ ለማሰባሰብ ጥረት በተደረገበት ወቅት ከመሐመድ የተማሩ የተባሉት ሙስሊሞች ብዙ የቁርአን ክፍሎችን መርሳታቸውን ተናዘዋል፡፡ አንድ ምሳሌ ከሳሂህ ሙስሊም ሐዲስ እንጥቀስ፡-

“አቡ ሀርብ ቢን አቡ አል-አስዋድ አባታቸውን ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት አቡ ሙሳ አል-ሸዐሪ የበስራ ቁርአን አነብናቢዎችን አስጠሯቸው፡፡ ቁጥራቸው ወደ ሦስት መቶ የሚሆኑቱ መጡ፡፡ ቁርአንን አነበነቡት፤ እርሳቸውም እንዲህ አሏቸው ‹‹እናንተ አነብናቢዎች እንደመሆናችሁ ከበስራ ነዋሪዎች ሁሉ ምርጦች ናችሁ፡፡ ማነብነባችሁን ቀጥሉ፡፡ (ነገር ግን) ለረጅም ጊዜ ማነብነባችሁ ከናንተ በፊት የነበሩትን ሰዎች ልቦች እንዳደነደነ ልቦቻችሁን እንዳያደነድን ተጠንቀቁ፡፡ በርዝመትና በጥንካሬ ከሱራ በረዓት ጋር የሚነፃፀር ሱራ እናነበንብ ነበር፡፡ ነገር ግን ከተከታዩ ውጪ የተቀረውን ረስቼዋለሁ፡- ‹‹የአደም ልጅ በኃብት የተሞሉ ሁለት ሸለቆዎች ቢኖሩት ሦስተኛውን ይመኛል፡፡ ከአፈር ውጪ የአደምን ልጅ ሆድ የሚሞላ ምንም ነገር የለም፡፡›› ከሱረት ሙሰቢሃት መካከል ከአንዱ ጋር የሚመሳሰል ሌላ ሱራም እናነበንብ ነበር ነገር ግን ከተከታዩ ውጪ የተቀረውን ረስቼዋለሁ፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ የማትፈፅሙትን ነገር ስለምን ትናገራላችሁ? እርሱም በናንተ ላይ ምስክር እንዲሆንባችሁ በአንገቶቻችሁ ላይ ተጽፏል፤ በዕለተ ትንሣኤም ከእርሱ ትጠየቃላችሁ፡፡››” Sahih Muslim 5:2286; Jalal al Din `Abdul Rahman b. abi Bakr al Suyuti. Al Itqan fi `ulum al Qur’an; Halabi, Cairo, 1935/1354, part 2, p. 25

በዚህ ሐዲስ ውስጥ የተጠቀሱት ሁለቱ “መገለጦች” በዛሬው ቁርአን ውስጥ አይገኙም፡፡ ሱራ በረዓት (አት-ተውባ) 129 አንቀፆች ያሉት ሲሆን ይህን ያህል ርዝመት ያለው አንድ ሙሉ ምዕራፍና ሌላ ርዝመቱ ምን ያህል እንደሆነ ያልተገለፀ፤ ነገርግን ‹ሙሰቢሃት› በመባል ከሚታወቁት በቁርአን ውስጥ ከሚገኙ ሱራዎች ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው ሱራ መረሳቱ ተነግሯል፡፡

ታድያ የመጀመርያዎቹ ሙስሊሞች በዚህ ሁኔታ የቁርአንን ክፍሎች ከመርሳታቸው የተነሳ በዛሬው ቁርአን ውስጥ ያልተካተቱ “መገለጦች” መኖራቸውን ከተናዘዙ ሙስሊም ሰባኪያን ቁርአን በትክክል ተሸምድዶ ሳይጨመርበትና ከላዩ ላይ ሳይቀነስ ለዚህ ዘመን እንደበቃ በማስመሰል የሀሰት ፕሮፓጋንዳ የሚነዙት ለምን ይሆን?
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
የቁርአን_ግጭቶች_ለሙስሊሞች_ምላሽ_የተሰጠ_ምላሽ_ክፍል.pdf
580.8 KB
የቁርአን ግጭቶች ለሙስሊሞች ምላሽ የተሰጠ ምላሽ (ክፍል 9)
(በወንድም ዳንኤል)
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ዶ/ር ዛኪር ናይክ ምንም ዓይነት የሃይመኖት ትምህርት ሳይኖረው የክርክር ልምድ የሌላቸውን ወገኖች ከዲዳት በኮረጃቸው ሙግቶች በመግጠምና ልምድ ካላቸው ምሑራን በመሸሽ ታዋቂነትን ያተረፈ አወናባጅ ነው። በቅርቡ በስሪላንካ ውስጥ ከ300 በላይ ክርስቲያኖችን የገደሉትን ጨምሮ የብዙ አሸባሪዎች መንፈሳዊ አባት ነው። አሁን ደግሞ በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ክስ ተመሥርቶበታል። https://bbc.in/2GS0aFg
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
የቁርአን_ግጭቶች_ለሙስሊሞች_ምላሽ_የተሰጠ_ምላሽ_ክፍል.pdf
569.9 KB
የቁርአን ግጭቶች ለሙስሊሞች ምላሽ የተሰጠ ምላሽ (ክፍል 10)
(በወንድም ዳንኤል)
👍1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ከሊመቱላህ
የኢየሱስን አምላክነት የሚያረጋግጥ ስያሜ
http://www.ewnetlehulu.org/am/kalimatullah/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (toolkit)
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (toolkit)
ሩሁላህ
የኢየሱስን አምላክነት የሚያረጋግጥ ሌላኛው ስያሜ http://www.ewnetlehulu.org/am/ruhullah/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ሙስሊሞች በኢየሱስ ያምናሉ? ክርስቲያኖችም በመሐመድ ያምናሉ!

የሙስሊሞችን ሙግት መሠረተ ቢስነት የሚያስረዳ ምሳሌ

===============
ሙስሊም ወገኖች በኢየሱስ እንደሚያምኑና አንድ ሙስሊም በኢየሱስ ካላመነ ሙስሊም ተብሎ ሊጠራ እንደማይችል ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው፡፡ ዒሳ በዘንባባይቱ ዛፍ ስር የተወለደ፣ ለሙሐመድ መንገድን ለመጥረግ የመጣ፣ ነቢይ ብቻ የነበረ፣ ሙስሊም የነበረ፣ ሐዋርያቱም ሙስሊሞች የነበሩ፣ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ ያረገና መስቀልን ለመሰባበር፣ አሳማዎችን ለመግደልና ክርስትናን ለማጥፋት ወደ ምድር ተመልሶ የሚመጣ መሆኑን እንደሚያምኑ ይነግሩናል፡፡ ይህ ትራኬ ስለ ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈውና በታሪክ ከታወቀው እውነታ ጋር እንደሚጣረስ ስንነግራቸው የኢየሱስን ታሪክ ጳውሎስ የተባለ ሰው ስለበረዘው እንጂ እውነቱ በቁርአን ውስጥ ከተጻፈው የተለየ እንዳልሆነ ይነግሩናል፡፡

ይህ እምነት “ዐፄ ቴዎድሮስ የተባለ አሣ አስጋሪ በጂንካ ምድር ተወልዶ አርባምንጭ ሄዶ በአዞ ተበልቶ ሞተ” ብሎ የዐፄ ቴዎድሮስን ታሪክ የማጣመም ያህል ነው፡፡ የትኛውንም የታሪክ ድርሳን ብናገላብጥ ዐፄ ቴዎድሮስ ጂንካ ውስጥ አልተወለዱም፣ ሥራቸውም አሣ ማስገር አልነበረም፣ ወደ አርባምንጭም አልሄዱም የሞቱትም በአዞ ተበልተው አይደለም፡፡ በዐይን ምስክሮችና በታሪክ መዛግብት ከተረጋገጠው በተጻራሪ እንዲህ ባለ መንገድ ታሪክን ማጣመም የሚቻል ከሆነ ክርስቲያኖች የሙሐመድን ታሪክ ቀጥሎ በተቀመጠመው መንገድ በማጣመም ቢያቀርቡ የሙስሊሞች ምላሽ ምን ይሆን?

በቁርአን፣ በሐዲሳትና በሲራ ውስጥ የሚገኙት የሙሐመድ ታሪኮች በሙስሊም ሊቃውንት ስለተበረዙ እንጂ ሙሐመድ በወጣትነቱ በሀገረ የመን ወንጌል ተመስክሮለት ክርስቲያን የሆነ፣ በኋላም ወንጌልን በአረብ በተለይም በመካና በመዲና ያስፋፋ፣ የኢየሱስን ሁሉን ቻይነት ያስተማረ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በወዳጆቹ ወደ አረብኛ ያስተረጎመና በክርስቶስ ላይ ስለነበረው እምነት ሰማዕት ሆኖ በፋርስ ወታደሮች አንገቱን የተሰየፈ ፅኑ ክርስቲያን ነበር፡፡ ነገር ግን ከእርሱ ሞት በኋላ ኻሊፋ ነኝ ብሎ የተነሳው ኡሥማን ሙሐመድ ያስተማራቸውን ትምህርቶች በመቀየር፣ የጻፋቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎች በሙሉ አንድ ላይ ሰብስቦ በማቃጠል፣ በሙሐመድ ስብከት ያመኑ ክርስቲያኖችን በማሳደድና ከአገር በማባረር ቁርአን የሚባል አዲስ መጽሐፍና እስልምና የሚባል አዲስ እምነት መሥርቷል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሙሐመድ በሥላሴ የሚያምን ፅኑ ክርስቲያን ነበር፡፡

ትክክለኛ ስሙ እንዲያውም አብድ አል-መሲህ (የመሲሁ ባርያ) የሚል እንጂ “ሙሐመድ” አልነበረም፡፡ “ሙሐመድ” ማለት “የተመሰገነ” ወይም “ምስጋና የተገባው” የሚል ነው፡፡ ከአንዱ አምላክ በስተቀር ምስጋና የተገባው ማን አለ? ይህ በራሱ የሙሐመድ (አብድ አል-መሲህ) ታሪክ ስለመበረዙ አንዱ ማረጋገጫ ነው፡፡

ኡሥማንና ተባባሪዎቹ የዚህን ቅዱስ ሰው ታሪክ ለማጉደፍ ያልፈበረኩት የታሪክ ዓይነት የለም፡፡ ለምሳሌ ያህል “ገብርኤል በተገለጠለት ጊዜ ከምድር ጋር አጣብቆ እንደ ጠቦት ግመል አረፋ አስደፍቆታል” በማለት በሐዲሳትና በሲራ ውስጥ ጽፈዋል፡፡ ይህ ሙሐመድን “ሰይጣን ይዞት ነበር” ለማስባል የተፈበረከ ታሪክ ነው፡፡ ከዚህም አልፈው ድግምት ተሠርቶበት ሚስቶቹ በሌሉበት ቦታ ከሚስቶቹ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት እየፈፀመ እንዳለ ይመስለው እንደነበር ጽፈውበታል፡፡ ኡሥማንና ተባባሪዎቹ የሙሐመድን ስም ለማጉደፍ ያልፈበረኩት ታሪክ ምን አለና! ከ9 ዓመት ህፃን ጋር ወሲብ እንደፈፀመ ሁሉ ጽፈውበታል፡፡ ነፍሰ ገዳይና ጨፍጫፊም አስመስለውታል፡፡ የሰው ዐይን በጋለ ብረት ጎልጉሎ የሚያወጣ፣ እጅና እግር የሚቆርጥ በቀለኛና ክፉ ሰው አስመስለው ስለውታል፡፡ ትምሕርቶቹንም ከቀደሙት ነቢያት ትምሕርቶች ጋር እንዲጋጭ አድርገው በርዘውታል፡፡

ቁርአን፣ ሐዲሳትና የሲራ መጻሕፍት በሙሉ ከኸሊፋው በኋላ የተጻፉ የተበረዙ መጻሕፍት ስለሆኑ አንቀበላቸውም፡፡ በተለይም ደግሞ ኡሥማን ቀደም ሲል የነበሩትን ጽሑፎች ሰብስቦ ማቃጠሉ የመሐመድን ትክክለኛ ታሪክ ለማጥፋት ያደረገው ሸፍጥ መሆኑ ግልፅ አይደለምን?

ይህ ምሳሌ የሙስሊሞች ሙግት ምን ያክል መሠረተ ቢስ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ እኛ ክርስቲያኖች እንዲህ ዓይነቱ እምነት ከእውነት የራቀና ማስረጃ የሌለው መሆኑን እናውቃለን፡፡ ዳሩ ግን ሙስሊሞች ስለ ኢየሱስ እናምናለን በሚሉት መንገድ ከተኬደ የገዛ እምነታቸው ሐሰትና ፈጠራ መሆኑን ሳያረጋግጡ ከእንዲህ ዓይነቱ አጣብቂኝ የሚወጡበት መንገድ ፈፅሞ ሊኖር አይችልም፡፡

የኢየሱስ መሰቀልና መሞት፣ በዕለቱም የተከሰቱ ተዓምራት (የፀሐይ መጨለምና የምድር መናወጥ) በክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ክርስቲያን ባልሆኑ የግሪክና የአይሁድ የታሪክ ጸሐፊያንም ጭምር ተዘግበው ይገኛሉ፡፡ በዘመኑ የነበሩት ጸሐፊያን የሰጡትን ምስክርነት በመካድና ክርስቲያኖችን በብረዛ በመወንጀል ምንም ዓይነት ማስረጃና ማረጋገጫ የሌለውን የቁርአንን የፈጠራ ታሪክ የተቀበሉት ሙስሊም ወገኖች በሙሐመድ ታሪክ ላይ ተመሳሳይ ተግባር ቢፈጸምና እነርሱም በብረዛ ቢወነጀሉ የሚቃወሙበት ሃቀኛ ሚዛንና ግብረ ገባዊ መሠረት የላቸውም፡፡

መልዕክት ለሙስሊም ወገኖች
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በአባይ ሚዛን መጠቀማችሁ የቆማችሁበት መሠረት ዐለት ሳይሆን አሸዋ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ለእውነት ግድ የሚላችሁ ከሆነ ክርስትናን በምትመዝኑበት ሚዛን እስልምናንም ለመመዘን ዝግጁዎች መሆን ያስፈልጋችኋል፡፡ ለእውነት እውነተኞ ሁኑ! እውነትን ካገኛችሁ ለመቀበል አታቅማሙ፡፡ እውነት ደግሞ የነፍሳችሁ ቤዛ የሆነው፣ ስለ እናንተ ነፍሱን አሳልፎ የሰጠው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሐንስ 14፡6)

ከገሃነም ፍርድ ሊያድናችሁ የሚችለው ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ማናችንም ብንሆን የዘለዓለም ሕይወት ሊኖረን አይችልም፡፡ ስለዚህ ወደ ነፍሳችሁ ጌታና ወደ ፈጣሪያችሁ ወደ ኢየሱስ ኑ!

መልዕክት ለክርስቲያኖች
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ሙስሊም ወገኖች ሙግታቸው ትክክል እንዳልሆነ እንዲገነዘቡ ለመርዳት ውጤታማው መንገድ የገዛ ሙግቶቻቸውን በሃይማኖታቸው ላይ መጠቀም ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል “ሥላሴ የሚል ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጥታችሁ አሳዩን” ብለው ሲጠይቁ “ተውሒድ የሚል ቃልና ሦስቱ ክፍሎቹ የተጠቀሱበትን ከቁርአን አሳዩን” ብሎ መጠየቅ፤ የነቢያትና የሐዋርያትን ምስክርነት በማጣጣል “ኢየሱስ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝና አምልኩኝ ያለበትን አሳዩን” ብለው ሲጠይቁ በተመሳሳይ ዒሳ በቁርአን ውስጥ “እኔ መሲህ ነኝ፣ ከድንግል ነው የተወለድኩት፣ ጌታ አይደለሁም፣ አልሰቀልም” ያለበትን ቦታ እንዲያሳዩን መጠየቅ፣ ወዘተ.፡፡ ሙስሊሞች የታሪክ መዛግብትንና ቅዱሳት መጻሕፍትን በፈለጉበት መንገድ እየተረጎሙና እያጣመሙ፣ እጅግ የከረሩ መስፈርቶችን እየተጠቀሙ የገዛ መጻሕፍታቸውን ግን እንደ አይነኬ በመቁጠር ከምርመራ ነፃ እንዲሆኑ ዕድል መስጠት የለብንም፡፡

————

ለበለጠ መረጃ
www.ewnetlehulu.org
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar) via @like
“የበርናባስ ወንጌል” እውነተኛ ወንጌል ነውን?
ሙስሊም ወገኖች የኢየሱስን ስቅለት ለማስተባበል ከሚጠቀሙባቸው ምንጮች መካከል አንዱ “የበርናባስ ወንጌል” የተሰኘው ሲሆን ብዙዎቹ በጳውሎስ ወዳጅ በበርናባስ እን
ደተጻፈ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን ይህ መሰረት የለሽና ተስፋ የመቁረጥ ሙግት ነው፡፡ የበርናባስ ወንጌል በመካከለኛው ዘመን በጣልያን አገር በአንድ ሙስሊም የተጻፈ የፈጠራ ጽሑፍ ሲሆን ከአንደኛው ክፍለ ዘመን ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም፡፡ ሙስሊም ወገኖች ብዙ ጊዜ “የበርናባስ ወንጌል” የተሰኘውን ጽሐፍ ከበርናባስ መልዕክት ጋር ሲያም ታቱ ይስተዋላል፡፡ የበርናባስ መልዕክት ተብሎ የተሰየመው መጽሐፍ በበርናባስ የተጻፈ ባይሆንም ነገር ግን “ከበርናባስ ወንጌል” በተፃራሪ ፍፁም ክርስቲያናዊ ነው፡፡ [የበርናባስን መልዕክት አማንበብ ይችላል፡- http://answeringislam.net/Barnabas/epistleb.html] የበርናባስ ወንጌል የአንደኛው ክፍለ ዘመን ጽሑፍ አለመሆኑን የሚያሳዩ ብዙ ነጥቦች በውስጡ ይገኛሉ፡-
• “ክርስቶስ” የሚለው የግሪክ ቃል እና “መሲህ” የሚለው የእብራይስጥ ቃል “የተቀባ” የሚል ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በአንደኛው ክፍለ ዘመን የኖረ የትኛውም አይሁዳዊ ሁለቱ ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም እንዳላቸው ያውቃል፡፡ በርናባስን የመሰለ የግሪክ ቋንቋ ከሚነገርባት ከአሌክሳንደርያ የመጣ አይሁዳዊ ይህንን ቀላል እውነታ ይዘነጋል ተብሎ በፍፁም ሊታሰብ አይችልም፡፡ ነገር ግን የበርናባስ ወንጌል ገና ሲጀምር ኢየሱስን “ክርስቶስ” ብሎ የጠራው ሲሆን (ገፅ 2) ነገር ግን ምዕራፍ 42 ላይ ኢየሱስ መሲህ መሆኑን መካዱን ይነግረናል፡፡
• ምዕራፍ 3 ላይ ሄሮድስ እና ጲላጦስ በአንድ ዘመን የይሁዳ ገዢዎች እንደነበሩ ይናገራል፡፡ ነገር ግን ሄሮድስ ከ37-4 ዓ.ዓ. ይሁዳን ብቻውን የገዛ ሲሆን ጲላጦስ ደግሞ ከ26-36 ዓ.ም. ነበር የገዛው፡፡[ FF Bruce. Israel and the Nations, Exeter: Paternoster Press, 1973, p. 240] በርናባስ ይህንን የታሪክ ቅጥፈት ሊፈፅም የሚችልበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም፡፡
• በምዕራፍ 20-21 ላይ ኢየሱስ በጀልባ ወደ ናዝሬት ከተማ እንደሄደና የከተማይቱ ጀልባ ቀዛፊዎች እንደተቀበሉት ይናገራል፡፡ ነገር ግን ናዝሬት ከገሊላ ባሕር 14 ኪ.ሜ. ርቃ በተራሮች ተከባ የምትገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡[“Nazareth”, New Bible Dictionary, England: IVP, 1987, p. 819] በዚሁ ቦታ ኢየሱስ ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ሽቅብ እንደወጣ የሚናገር ሲሆን ይህም ሌላ ጂኦግራፍያዊ ስህተት ነው፡፡ የቅፍርናሆም ከተማ አቀማመጥ ከናዝሬት በላይ ከፍታ ላይ ሳይሆን ታች የገሊላ ባሕር አጠገብ ነው፡፡ ኢየሱስ በተደጋጋሚ ወደ እነዚህ ከተሞች በመሄዱ ምክንያት ደቀ መዛሙርቱ በሚገባ ያውቋቸዋል (ማቴዎስ 2:23፣ 4:13፣ 8:5፣ 11:23፣ 17:24፣ 21:11፣ 26:71፣ ሉቃስ 4:16 )፡፡ ነገር ግን የበርናባስ “ወንጌል” ጸሐፊ ይህንን ስህተት በመስራት አጭበርባሪነቱን ይፋ አውጥቷል፡፡
የበርናባስ ወንጌል የእስልምናን ትምህርቶች የሚደግፍባቸው ብዙ ቦታዎች ቢኖሩም ነገር ግን ደግሞ ሙስሊሞች በእርሱና በቁርአን መካከል እንዲመርጡ የሚያስገድዱ የሚጣረስባቸው ብዙ ነጥቦች በውስጡ ይገኛሉ፡፡
• ቁርአን መርየም ዒሳን የወለደችው በምጥ እንደሆነ የሚናገር ሲሆን (ሱራ 19፡22-23) የበርናባስ ወንጌል ግን ያለ ምንም ምጥ እንደወለደችው ይናገራል (ም. 3)፡፡
• ቁርአን ዒሳ መሲህ መሆኑን በተደጋጋሚ የሚናገር ሲሆን (ሱራ 3፡45) የበርናባስ ወንጌል ግን ዒሳ መሲህ መሆኑን መካዱን (ም. 42) እና መሐመድ መሲህ መሆናቸውን መመስከሩን ይናገራል (ም. 97)፡፡ በቁርአን ውስጥም ሆነ በየትኛውም እስላማዊ ጽሑፍ ውስጥ መሐመድ መሲህ መሆናቸው አልተጻፈም፡፡
• ቁርአን አንድ ሙስሊም ወንድ እስከ አራት ሚስቶች እንዲያገባ የሚፈቅድ ሲሆን (ሱራ 4፡3) የበርናባስ ወንጌል ግን ድርብ ጋብቻን አጥብቆ በመቃወም አንድ ወንድ ለአንዲት ሴት የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ያንጸባርቃል (ም. 115)፡፡
• ቁርአን ሰባት ሰማያት ብቻ እንዳሉ የሚናገር ሲሆን (ሱራ 17፡44) የበርናባስ ወንጌል ግን ዘጠኝ መኖራቸውን ይናገራል (ም. 178)፡፡
የበርናባስ ወንጌል የመካከለኛው ዘመን ፈጠራ መሆኑን የሚያሳዩ ጠቋሚ ምልክቶች በውስጡ ይገኛሉ፡፡
• በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ኢዮቤ ልዩ በየ ሃምሳ ዓመቱ እንዲከበር ትዕዛዝ የተሰጠ ሲሆን (ዘሌዋውያን 25፡10-11) በ1300 ዓ.ም. የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ የነበሩት ቦኒፌስ ስምንተኛ በየ መቶ አመቱ እንዲከበር አውጀው ነበር፡፡ ነገር ግን ቀጣዩ ጳጳስ ክሌመንት አራተኛ አዋጁን በመሻር ተመልሶ በየ ሃምሳ ዓመቱ እንዲከበር ስላወጁ በ1350 ዓ.ም. ተከብሯል፡፡[ Herbert Thurston. The Holy Year of Jubilee, London: Sands & Co., 1900, p. 5] የበርናባስ ወንጌል ግን ይህንን የጳጳሱን የተሳሳተ አዋጅ በመቀበል በምዕራፍ 82 ላይ የኢዮቤ ልዩ በዓል በየ መቶ ዓመቱ እንደሚከበር ይናገራል፡፡ ይህም መጽሐፉ በመካከለኛው ዘመን የተጻፈ ስለመሆኑ ትልቅ ማስረጃ ነው፡፡
• ይህ መጽሐፍ የመካከለኛው ዘመን ፈጠራ መሆኑን የሚያመለክተው ሌላው ነጥብ ከዘመኑ ጸሐፊ ከዳንቴ ሥራዎች ላይ የተቀዱ ሐሳቦች በውስጡ መገኘታቸው ነው፡፡ [Dante Alighieri. The Divine Comedy, section: Paradiso] ለምሳሌ ያህል ከገነት በፊት ዘጠኝ ሰማያት መኖራቸውን ጸሐፊው ከዳንቴ ልበ ወለድ ላይ መውሰዱ ግልፅ ነው (ም. 178)፡፡
• የበርናባስ ወንጌል ቀዳሚያን የእጅ ጽሑፎች በጣልያንኛና በእስፓኒሽ የተጻፉ ሲሆኑ ምርመራ ተደርጎባቸው ከአሥራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ የተጻፉ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ [Geislere. Encyclopedia of Christian Apologetics, p. 67] እውነተኛው በርናባስ ጽፎት ቢሆን ኖሮ በእብራይስጥ፣ በግሪክ ወይንም ደግሞ በአረማይክ ነበር መጻፍ የነበረበት፡፡
የጠለቀ ዕውቀት የሌላቸው ሙስሊሞች ይህንን መጽሐፍ እንደ ተዓማኒ ወንጌል ቢያራግቡትም ነገር ግን ጉዳዩን በጥንቃቄ ያጠኑ ሙስሊም ሊቃውንት ሳይቀሩ ሐሰተኛ መጽሐፍ መሆኑን ዕውቅና ይሰጣሉ፡፡[ Cyril Glassé, The Concise Encyclopedia of Islam, San Francisco: Harper & Row, 1989, p. 65]
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar) via @like
መሐመድና ጥቁር ሴት
የዘረኛ ሰው የህልም ትርጓሜ
==============

መሐመድ ለጥቁሮች ከፍተኛ ንቀት እንደነበረውና የዘረኝነት አንድምታ ያላቸውን ንግግሮች መናገሩን እንዲሁም አድሏዊ ተግባራትን መፈፀሙን ከዚህ ቀደም ተመልክተናል፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ ይህንኑ የሚያጠናክር ተጨማሪ ማስረጃ እናስነብባችኋለን፡፡ ተከታዮቹ ዘገባዎች ሙስሊሞች ከቁርአን ቀጥሎ ከፍተኛ ቦታ በሚሰጡት ሳሂህ አል-ቡኻሪ በተሰኘው የሐዲስ ስብስብ ውስጥ የሚገኙ ናቸው (“ሳሂህ” ማለት የታመነ ወይም ትክክለኛ ማለት ነው)፡-


አብደላህ እንዳወራው ነቢዩ እንዲህ አሉ፣ “(በህልም) አንዲት ፀጉሯ ያልተበጠረ ጥቁር ሴት ከመዲና በመውጣት በመሐኢዓ ማለትም በአል-ጁፋ ስትቀመጥ አየሁ፡፡ የመዲና የበሽታ ወረርሽኝ ወደዚያ ቦታ (አል-ጁፋ) መዛመቱ ነው ብዬ ተረጎምኩት፡፡” (ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅፅ 9፣ መጽሐፍ 87፣ ቁጥር 161)


ነቢዩ በመዲና ሆነው ስላዩት ህልም አብዱላህ ቢን ዑመር እንዳወራው፤ ነቢዩ እንዲህ አሉ “(በህልም) አንዲት ፀጉሯ ያልተበጠረ ጥቁር ሴት ከመዲና በመውጣት በመሐኢዓ ስትቀመጥ አየሁ፡፡ የመዲና የበሽታ ወረርሽኝ ወደ መሐኢዓ ማለትም ወደ አል-ጁፋ የመዛመቱ ምልክት ነው ብዬ ተረጎምኩት፡፡” (ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅፅ 9፣ መጽሐፍ 87፣ ቁጥር 162)

ተመሳሳይ ዘገባ ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅፅ 9፣ መጽሐፍ 87፣ ቁጥር 163 ላይ ይገኛል፡፡

እንዲህ ያለ ንግግር በአንድ ተራ ሰው ቢነገር አቅልሎ ማለፍ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከፈጣሪ ዘንድ የተላከ እንደሆነ በተነገረለት “ነቢይ” መነገሩና በመንፈሳዊ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ መገኘቱ ጉዳዩን በቸልታ እንዳናልፈው ያስገድደናል፡፡ የዘረኝነት ምስል ከሳች የሆኑ መሰል ንግግሮች በቢሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ሲደመጡና ለክፍለ ዘመናት ሲነገሩ የሚያሰርፁት ዘረኛ አመለካከት በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ይህንን ንግግር የሰማና አምኖ የተቀበለ ሰው ፀጉሯ የተንጨባረረ ምስኪን ጥቁር ሴት ሲመለከት የሚፈጠርበትን መጥፎ ስሜት ማሰብ አያዳግትም፡፡ ፈጣሪ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ በመሆኑ እንዲህ ያለ አደገኛ መዘዝ ያለውን ሕልም አያሳይም፡፡ የበሽታ ወረርሽኝ ከአንዱ ወደ ሌላ ቦታ መዛመቱን “ለነቢዩ” ማሳየት ቢፈልግ የሆነ ዓይነት አስፈሪ አውሬ ወይም ዕብድ ውሻ ሊያሳየው እየቻለ ሴትን የመሰለች የከበረች ፍጥረት “ጥቁርና ፀጉሯ የተንጨባረረ” የሚል ዘረኛ መግለጫ አክሎ ማሳየት ለምን አስፈለገ? በዚህ ህልምና በፍቺው ውስጥ የመሐመድ ዘረኛ አመለካከት እንጂ የፈጣሪ ጥበብና ዕውቀት አይታይም!
————————-

መሐመድ ለጥቁሮች የነበረው ንቀት

ሴቶች በእስልምና
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar)
ለምን አልሰለምሁም – ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ሞገስ ክፍለ 1 ክፍል 2
ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማውረድ http://www.ewnetlehulu.org/am/books/ ይጎብኙ፡፡
አሸባሪዎችና ሙስሊሞች ወይንስ ሽብርተኝነትና እስልምና?
የበኃይሉ ሚዴቅሳ ስሁት አመክንዮ 👉👇 http://www.ewnetlehulu.org/am/behaylu-response/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar) via @like
ረመዳን ከተጀመረ 18 ቀናት አለፉ፡፡ እስከ አሁን ድረስ በዓለም ዙርያ 95 የሽብር ጥቃቶች የደረሱ ሲሆን 488 ንፁኀን ሰዎች በሙስሊም አሸባሪዎች ተገድለዋል፡፡ አብዛኞቹ ሙስሊሞች ሰላም ወዳዶችና በዚህ ሁኔታ ልባቸው የሚያዝን መሆኑን እናውቃለን፡፡ ነገር ግን እስልምና የሰላም ሃይማኖት ከሆነ ከሌሎች ሃይማኖታት በተለየ ሁኔታ የሽብርና የእልቂት ምንጭ ስለ ምን ሆነ? የሚለውን ጥያቄ ለገዛ ህሊናቸው ሊመልሱ ይገባል፡፡
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net (Dan Balthazar) via @like
መጽሐፍ ቅዱስ ምንድነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቲያኖች ቅዱስ መጽሐፍ ነው፡፡ በእንግሊዝኛ ባይብል የሚለው “ቢብሊያ” ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “መጻሕፍት” ማለት ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ አንድ መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ነቢያት፣ በተለያዩ ቦታዎችና በተለያዩ ቋንቋዎች በ1500 ዓመታት ውስጥ የተጻፉ የተለያዩ መጻሕፍት ስብስብ ነው፡፡ የሙሴን ሕግ (ቶራ)፣ የዳዊትን መዝሙር፣ የሰለሞንን መጻሕፍት፣ ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዳንኤል፣ ሆሴዕ፣ ኢዩኤል፣ አሞፅ፣ አብድዩ፣ ዮናስ፣ ኢዮብ፣ ሚክያስ፣ ናሆም፣ ዕንባቆም፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ዘካርያስ፣ ሚልክያስና የመሳሰሉትን ነቢያት መጻሕፍት አካቷል፡፡ በማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ የተጻፈውን የኢየሱስን ወንጌል ይዟል፡፡ የሐዋርያትም ጽሑፎች በውስጡ ይገኛሉ፡፡

ቁርአን ስለ ተውራትና ወንጌል (ኢንጂል) (3፡3)፣ የነቢያት መጻሕፍት (3፡84)፣ እና መዝሙራት (ዘቡር) (4፡163) ይናገራል፤ ክርስቲያኖችንም “የመጽሐፉ ሰዎች” በማለት ይጠራቸዋል (5፡68)፡፡

ክርስቲያኖች እነዚህ ሁሉ መጽሐፍት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለምን ኖሯቸው?

ክርስቲያኖች ሁሉንም ነቢያት ስለሚቀበሉና በመካከላቸው አድልዎን ስለማያደርጉ ሁሉም መጽሐፍት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሏቸው፤ ያነቧቸዋልም፡፡

ሁለተኛ እግዚአብሔር በብዙ ነቢያት በኩል ተናግሮናል፡፡ መጻሕፍታቸው አንዳቸው በሌላቸው ላይ የተገነቡ ሲሆኑ በጋራ እንዲነበቡ የታሰቡ ናቸው፡፡ በጋራ በመሆንም የተሟላውን አምላካዊ መመርያ ይሰጡናል፡፡

ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሔር የሚያምኑት ሁሉ አጠቃላዩን የነቢያት መጽሐፍት ያገናዘበ ነው፡፡

የኢየሱስ ሐዋርያት ወንጌልን የተቀበሉ የነበሩ ቢሆኑም ከሙሴ ሕግ፣ ከነቢያትና ከመዝሙራት እየጠቀሱ ያስተምሩ ነበር፤ መጻሕፍቱንም ያነብቡ ነበር፡፡

ከተለያዩ አገራት የሆኑ ብዙ ሕዝቦች ክርስትናን ሲቀበሉ እንደ ሐዋርያት ሁሉ የሙሴን ሕግ፣ ነቢያትን፣ መዝሙራትንና ወንጌልን ተቀብለው ማንበባቸውን ቀጠሉ፡፡ ዛሬም ቢሆን አንድ ሰው ክርስቲያን ሲሆን ወንጌልን ብቻ ሳይሆን የነቢያትን መጻሕፍት ሁሉ ይማራል፡፡ በክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሁሉም የነቢያት መጻሕፍት በአደባባይ ይነበባሉ፣ ይሰበካሉ፡፡

ክርስትና ሰዎች የሙሴን ሕግ፣ ነቢያትንና መዝሙራትን ከወንጌል ጋር በማጣመር እንዲያነብቡና እንዲቀበሉ በማስተማር ነው የተስፋፋው፡፡ የነቢያት ሁሉ መጻሕፍት በሰው ልጆች ሁሉ ይታወቁ ዘንድ ክርስቲያኖች እነዚህን መጻሕፍት ወደ አብዛኞቹ ቋንቋዎች ተርጉመዋል፡፡

እርስዎና ነቢያት

ነቢያትን በሙሉ ማክበር ይፈልጋሉን? ትክክለኛው ነቢያትን የማክበርያ መንገድ እነርሱን መስማትና መጻሕፍታቸውን ማንበብ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ሁሉንም መልእክቶች ማወቅ ይፈልጋሉን? አንዱን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የነቢያት መጻሕፍት ማንበብ ይጠበቅቦታል፡፡

እነዚህ ነቢያት በገዛ ቋንቋዎ ተተርጉመዋል፡፡ ክርስቲያኖች ቅዱሱን መጽሐፍ እንዲሰጡዎ ይጠይቁ፤ ወይንም ኦንላይን ፍለጋ ያድርጉ፡፡ የእግዚአብሔርን ነቢያት መጻሕፍት እንዳያነብቡ ማንም ሰው እንዲያሳስትዎት ወይንም እንቅፋት እንዲሆንብዎት አይፍቀዱ፡፡

ይህንን ጸሎት መጻለይ ይሻሉን?

ሁሉን ቻዩ አምላካችን በነቢያቶችህ ልትናገረን ፈቃድህ ስለሆነ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሁላቸውንም ማድመጥ እችል ዘንድ እርዳኝ፡፡ አሜን፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ