ለምን አልሰለምኩም?
2.91K subscribers
51 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
እውነት አላህ የቁርኣን ጠባቂ ነው ተብሏልን? The Islamic Dilemma

ሙስሊሞች ከሚያነሱት ሙግቶች አንዱ፣ ቀጥሎ ያለው ነው:

"መፅሐፍ ቅዱስ የተበረዘው ሰዎች ጠባቂዎቹ ስለተባሉ ሲሆን የቁርአን ጠባቂ ግን አላህ ነው ተብሏል።"

የሚጠቅሱትም ሱራ ይሄ ነው: ሱራ 15:9

إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ

እኛ "ቁርኣንን" እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡

ነገር ግን እዚህ ላይ "ቁራኣን" ተብሎ የተተረጎመው - "አል-ዚክራ" የሚል ቃል እንጂ ቁርአን አይደለም

ዚክር- ማለት "reminder- ማስታወሻ፣ admonition- ምክር" ማለት ነው።

ታድያ መፅሐፍ ቅዱስ ዚክር አልተባለምን? መልሱ ተብሏል ነው።

ሱራ 21:48

وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ

ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን (ወዚክራ) በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡

ሱራ 16:43

وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِي إِلَيْهِمْ ۚ فَاسْأَلُوا أَهْلَ #الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

ከአንተም በፊት ወደእነሱ ወሕይን (ራእይን) የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ #የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡

በዚህ ክፍል ላይ أَهْل الذِّكْرِ (አህላል-ዚክሪ) የሚለውን- የዕውቀትን ባለቤቶች ብለው ተርጉሞውታል። ኢብኑ ከሢር ግን በተፍሲራቸው አህለል ዚክር ማለት "the people of the previous Books" " የቀድሞ መጽሓፍት ባለቤቶች" ማለት እንደሆነ አስቀምጧል ።

ስለዚህ ለሙሴ የወረደውና ከቁርኣን በፊት የወረዱት መፅሓፍት "ዚክር" ከሆኑ፣ ሙግቱ ቀጥሎ ያለው ይሆናል:

1- አላህ ዚክሩን ያወረድነው እኛው ነን፣ እኛው ጠባቂዎቹ ነን ካለ እና ተውራት ዚክር ከሆነ፣ ተውራት ተበርዟል ካልን አላህ ውሸታም መሆኑ ነው። ምክኒያቱም አልጠበቀውማ።

2- አይ፣ ተውራት አልተበረዘም ከተባለም፣ አላህ ውሸታም ይሆናል። ምክኒያቱም ፔንታቱክ የምንላቸው ወይም "ተውራት" ውስጥ እግዚአብሔር ያስተማረው የቁርአን ተቃራኒ ናቸው።

ለምሳሌ: ዘጸአት 4

23 እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤ ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ ትለዋለህ።

እንደ ቁርአን ትምህርት ግን አላህ ባሪያ እንጂ ልጅ የለውም!

3- አይ፣ ኦሪት ከተውራት ይለያል አልተጠበቀም ወይም አሁን ላይ ተውራት ጠፍቷል ከተባለም፣ አላህ መጀመሪያ ያወረደውን ዚክር አሁንም መጠበቅ አልቻለም ማለት ነው።

Hence, Islamic Dilemma! Damned if you do, damned if you don't!😄