የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
40 subscribers
89 photos
1 video
Download Telegram
"#የጎፋ #ዞንን #ብልጽግና#ልማትና #ዕድገት #ትልም #እውን #ለማድረግ #ግብርን #በእኔነት #ስሜት እና #በታማኝነት #መክፈል #የኛ #የዜጎች #ኃላፊነት #ነው" #የጎፋ #ዞን #ዋና #አስተዳዳሪ #ዶ/ር #ጌትነት #በጋሻው
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

የጎፋ ዞን የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርጫፍ መምሪያ ባካሄደው ሴክተር ጉባኤ የዞኑ አጠቃላይ ገቢ የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዳመላከተው በቀጣይ ሁሉንም የዞኑን መዋቅሮች በትኩረት ሊያሰራ የሚያስችል መሆኑ ተገምግሟል።

የሴክተሩን የሩብ ዓመት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ የመሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው እና የዞኑ የገቢዎች ዋና ቅርጫፍ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ጥሩነሽ ወዛ ሲሆኑ የሁሉም መዋቅሮች የሩብ ዓመት የገቢ አሰባሰብ አፈፃፀም ደረጃ የሚያመላክት ሰነድ ቀርቦ በጥንካሬና በድክመት በባለድርሻ አካላት ተገምግሟል።

ሀገራችን ከምትገኝበት ወቅታዊ ውስብስብ የፖለቲካ ነባራዊ ሆኔታ አንጻር ለዞኑ ገቢ አሰባሰብ ስኬትም ሆነ ድክመት የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት በዋናነት ሴክተሩን የሚመራው አመራሩና የገቢ አሰባሰብ ባለሙያው ሲሆን አመራሩና ባለሚያው በቁርጠኝነትና በቅንጅት በመሩበት ውስን የዞናችን መዋቅሮች ከነድክመቱም ቢሆን ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል ያሉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው አገልግሎት አሰጣጣችንን ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ ግብር ከፋዮቻችንን ተሳትፎ ማሳደግ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ልማት ማስመዝገብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የተቀናጀ ዕድገትና ልማት መገለጫ ጠንካራ ግብር ከፋይ ህዝብ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የዞኑ ገቢዎች ዋና ቅርጫፍ መመሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ጥሩነሽ ወዛ ሲሆኑ የግብር ማጭበርበርን መከላከል እና ማጋለጥ የሁሉም ዜጋ አገራዊ ግዴታና ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን
ጉዳዮች መምሪያ ነው።
ጥቅምት/24/2014 ዓ.ም
#ሣውላ
#በጎፋ #ዞን #በአራተኛው #ዙር #የሀገር #መከላከያ #ሰራዊት #ድጋፍ #በዓይነት #እና #በገንዘብ #ከ16.5 #ሚሊዮን #ብር #በላይ #ለማሰባሰብ #በዕቅድ #ተይዞ #እየተሰራ #እንደሚገኝ #የዞኑ #ዋና #አስተዳዳሪ #ዶ/ር #ጌትነት #በጋሻው #ገለፁ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በጎፋ ዞን ሀገርን ለማደን በህልውና ዘመቻ ለተሠማራው ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት እየተደረገ ባለው የተቀናጀ ጥረት አራተኛ ዙር የሀብት አሰባሰብ ሥራ በህዝቡ የተባበረ ክንድ ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ገለፁ።
የዞኑ ህዝብ ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት የተለያዩ ድጋፎችን በአይነት፣ በጉልበት እና በገንዘብ የማሰባሰቡ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዞኑ ሀገርን የማደን የህልውና ዘመቻን ለማሳካት እየተደረገ ባለው የተቀናጀ ጥረት በየደረጃው የሚገኘው ማህበረሰብ በተለይም ወጣቱ ኃይል በሁሉ አቀፍ ድጋፎች በሁሉም ዙሮች የነቀ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በዚህም የእናት ጡት ነካሹ የሆነው አሸባሪው ቡድን ህወሃት ሀገራችንን የመበተን ተልዕኮን አንግቦ የሀገር መከታና ጋሻ የሆነውን የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ መንግስት ተግበራዊ ያደረገውን ህግ የማስከበር ዘመቻ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የዞኑ ህዝብ ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብሎ ጁንታውን የመደምሰስ ህልውና ዘመቻ ላይ እየተዋደቀ ላለው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነቱን አስመስክሯል።

በተለይም የዞናችን ህዝቦች የእናት ሀገራቸውን ክብርና ሉዓላዊነት ለማስከበር ግንባር ለዘመተው የመከላከያ ሠራዊታችን በአስፈላጊው ሁሉ በመደገፍ ያላቸውን ደጀንነት በውል ለማረጋገጥ አራተኛ ዙር የሀብት አሰባሰብ ሥራ በአሁኑ ሰዓትም ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

በአሁኑ ወቅትም በዞኑ በየመዋቅሩ በጠንካራ የህዝብ ተሳትፎ በዓይነት የተለያዩ ግብዓቶች እየተሰበሰበ እንደሚገኝ ከሁሉም መዋቅሮች ባገኛነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

በተጨማሪም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ምልምል መደበኛ የመከላከያ ሰራዊት፣ የቀድሞ የደርግ ሰራዊት፣ የተቀናሽ ሰራዊት፣ ብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል እና ሚሊሺያዎች የሀገርን ጥሪ ተቀብለው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ለመሰለፍ ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል።

ዘገባው:- #የጎፋ #ዞን #መንግስት #ኮሚኒኬሽን
#ጉዳዮች #መምሪያ #ነው

#ህዳር /02/2014 ዓ.ም
#ሣውላ