የጎፋ ዞን #የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈፃሚ #የፀጥታው_ግብረሃይል በአዋጁ ማስፈፀሚያ #ዕቅድ ዙሪያ ምክክር በማድረግ ዞናዊ ኮማንድ ፖስቱ በይፋ ስራ መጀመሩን አሳወቀ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በዞኑ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ሰብሳቢነት የሚመራውና የዞኑ ፖሊስ መምሪያ፣ ፍትህ መምሪያ፣ ሚሊሺያ ፅ/ቤትና ልዩ ሃይሉን ያካተተው ግብረኃይል አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በደነገጋቸው ግዴታዎችና በሰጣቸው ስልጣኖች ስር ሆኖ የህዝቡን ሠላም ሊያውኩ በሚችሉ በማንኛውም ስጋት ላይ የቀደመ እርምጃና ማስተካከያ በመውሰድ ፀጥታው እንደሚመራ የግብረሃይሉ ሰብሣቢና የሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጅፋሬ ገልፀዋል። ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ግብረኃይል አባላት የዕቅድ ኦሬንቴሽን፣ የአካባቢያዊ ሁኔታ ግምገማ፣ እስከአሁን በተደረጉ የህግ ማስከበር ተግባራት እና ቀጣይ በፍጥነት ሊሰሩ በሚገቡ ተግባራት ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።
በውይይቱ ላይም አዋጁን ለማስፈጸም የግብረኃይል አደረጃጀቱ እስከቀበሌ እንደሚወርድና ይህም አደረጃጀት በሁለት ቀናት ውስጥ አልቆ የንቃተህግ የህዝብ ንቅናቄ በየማህበራዊ መሠረቶች እየተደረገ እንደሚመራ በመግለጽ የታችኛው መዋቅር በፍጥነት ተልዕኮውን እንዲያሣኩ ስምሪት እንደተሠጠ ገልፀዋል። አዋጁ ከወጣበት ዕለት አንስቶ የአሸባሪውን ቡድን ተልዕኮ በመደገፍና በህዝብ ውስጥ በማስተጋባት ስጋት እንደፈጠሩ የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በህግ ቁጥጥር ስር ውለው እየተጠየቁ መሆናቸውንም ለአብነት በማንሳት ከዚህ በኋላም በጣም በተጠናከረ መልኩ የጥበቃ ስራዎች እንዲሰሩ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል።
እንደዚሁም ፖሊስ በማንኛውም ሰዓትና ቦታ ጥርጣሬ የሚያሳድሩ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና ተሽከርካሪዎችን እያቀረበ መጠየቁን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኃላፊው በአፅንዖት አስታውቀዋል። ለዚህም አጋዥ የሚሆኑ ኬላዎች በዞናች በአራት መስመሮች፣ መውጫና መግቢያዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ስራ እንዲጀምሩ መመሪያ ተሰጥቷል።
ከዚህ በተጨማሪ በአከባቢ ሠላም ቀጣይነት ዙሪያ የህዝብ የተደራጀ ጥበቃና ፈቃደኝነት እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ከከዚህ ቀደሙ የተለየ ተነሳሽነት፣ ተባባሪነትና ንቃት የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ መሆናችን ግንዛቤ ተወስዶ በየቀጠናው ጠንካራ የህዝብ አደረጃጀቶች እንዲፈጠሩና በፍጥነት በሪፖርት እንዲገለፁ መመሪያ ተሰጥቷል። ለህዝቡም የአደራ መልዕክት ተላልፏል።
የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን
ጉዳዮች መምሪያ ነው።
ጥቅምት/27/2014 ዓ.ም
#ሣውላ

የጎፋ ዞን ገቢዎች ዋና ቅርንጫፍ መመሪያ የሩብ ዓመት አፈጻፀሙን ግምገማውን ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጥልቀት ገመገመ።
"#የጎፋ #ዞንን #ብልጽግና፣ #ልማትና #ዕድገት #ትልም #እውን #ለማድረግ #ግብርን #በእኔነት #ስሜት እና #በታማኝነት #መክፈል #የኛ #የዜጎች #ኃላፊነት #ነው" #የጎፋ #ዞን #ዋና #አስተዳዳሪ #ዶ/ር #ጌትነት #በጋሻው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
የጎፋ ዞን የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርጫፍ መምሪያ ባካሄደው ሴክተር ጉባኤ የዞኑ አጠቃላይ ገቢ የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዳመላከተው በቀጣይ ሁሉንም የዞኑን መዋቅሮች በትኩረት ሊያሰራ የሚያስችል መሆኑ ተገምግሟል።
የሴክተሩን የሩብ ዓመት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ የመሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው እና የዞኑ የገቢዎች ዋና ቅርጫፍ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ጥሩነሽ ወዛ ሲሆኑ የሁሉም መዋቅሮች የሩብ ዓመት የገቢ አሰባሰብ አፈፃፀም ደረጃ የሚያመላክት ሰነድ ቀርቦ በጥንካሬና በድክመት በባለድርሻ አካላት ተገምግሟል።
ሀገራችን ከምትገኝበት ወቅታዊ ውስብስብ የፖለቲካ ነባራዊ ሆኔታ አንጻር ለዞኑ ገቢ አሰባሰብ ስኬትም ሆነ ድክመት የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት በዋናነት ሴክተሩን የሚመራው አመራሩና የገቢ አሰባሰብ ባለሙያው ሲሆን አመራሩና ባለሚያው በቁርጠኝነትና በቅንጅት በመሩበት ውስን የዞናችን መዋቅሮች ከነድክመቱም ቢሆን ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል ያሉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው አገልግሎት አሰጣጣችንን ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ ግብር ከፋዮቻችንን ተሳትፎ ማሳደግ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ልማት ማስመዝገብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የተቀናጀ ዕድገትና ልማት መገለጫ ጠንካራ ግብር ከፋይ ህዝብ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የዞኑ ገቢዎች ዋና ቅርጫፍ መመሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ጥሩነሽ ወዛ ሲሆኑ የግብር ማጭበርበርን መከላከል እና ማጋለጥ የሁሉም ዜጋ አገራዊ ግዴታና ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።
የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን
ጉዳዮች መምሪያ ነው።
ጥቅምት/24/2014 ዓ.ም

በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ በነገው ዕለት ዞናዊ አሸባሪውን ህወኃት የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ ይካሄዳል
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ በነገው ዕለት ዞናዊ አሸባሪውን ህወሓት የሚያወግዝ እንዲሁም የአገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ የጎፋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው እንደገለጹት ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል የገጠማትን ፈተና በህዝቦቿ የተባበረ ክንድ አልፋልች ብለዋል።
ሀገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ በመገኘቷ ሁሉም የዞኑ ነዋሪዎች የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ ይዘው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው የገለጹት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሁሉም የጎፋ ዞን ነዋሪዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በሞራል፣ በደጀንነት እና በጉልበት እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቧል።
በመጨረሻም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መምሪያ የሚተላለፉ መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነው የክልል መንግስት በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ እንዲደረጉ የሚከተሉትን የክልከላ መመሪያዎችን ከዚህ በታች እደሚከተለው አውጥቷል፡-
1. በዞኑ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ማንኛውም ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ ከቀኑ 12፡00 ሰዓት በኋላ እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ ነው፤
2. ማንኛውም የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ባለ ሶስት እግርን ጨምሮ ከምሽቱ 2፡00 በኋላ ማንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
3. የምርት ዕንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎል የጭነት መኪኖች በየኬላው ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገባቸው እንዲንቀሳቀሱ የተፈቀደላቸው ሆኖ ከረዳቱና ካሽከርካሪው ውጪ መጫን የተከለከለ ነው፤
4. ከፀጥታ አካላት ውጪ ማንኛውም እግረኛ በክልሉ ውስጥ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
5. ከጤና ተቋማት፣ ከነዳጅ ማደያዎች እና ከፖሊስ ጣቢያዎች ውጪ ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ተቋም ከምሽቱ 3፡00 በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችልም፤
6. ማንኛውም ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪና አሽከርካሪ የመንግስትን ጨምሮ ከቀን ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ባለ የፖሊስ ተቋም ቀርበው መመዝገብ አለባቸው፤
በመሆኑም ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት ስለማያስመልጥ ሁሉም የዞናችን ነዋሪዎች ከላይ የተቀመጡ የክልከላ ድንጋጌዎች ተግባራዊ በማድረግ ለሰላም ዘብ በመቆም የተለመደውን ትብብራችሁን እንድታደርጉ እናሳስባለን የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው።