የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
40 subscribers
89 photos
1 video
Download Telegram
የጎፋ ዞን #የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈፃሚ #የፀጥታው_ግብረሃይል በአዋጁ ማስፈፀሚያ #ዕቅድ ዙሪያ ምክክር በማድረግ ዞናዊ ኮማንድ ፖስቱ በይፋ ስራ መጀመሩን አሳወቀ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በዞኑ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ሰብሳቢነት የሚመራውና የዞኑ ፖሊስ መምሪያ፣ ፍትህ መምሪያ፣ ሚሊሺያ ፅ/ቤትና ልዩ ሃይሉን ያካተተው ግብረኃይል አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በደነገጋቸው ግዴታዎችና በሰጣቸው ስልጣኖች ስር ሆኖ የህዝቡን ሠላም ሊያውኩ በሚችሉ በማንኛውም ስጋት ላይ የቀደመ እርምጃና ማስተካከያ በመውሰድ ፀጥታው እንደሚመራ የግብረሃይሉ ሰብሣቢና የሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጅፋሬ ገልፀዋል። ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ግብረኃይል አባላት የዕቅድ ኦሬንቴሽን፣ የአካባቢያዊ ሁኔታ ግምገማ፣ እስከአሁን በተደረጉ የህግ ማስከበር ተግባራት እና ቀጣይ በፍጥነት ሊሰሩ በሚገቡ ተግባራት ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።

በውይይቱ ላይም አዋጁን ለማስፈጸም የግብረኃይል አደረጃጀቱ እስከቀበሌ እንደሚወርድና ይህም አደረጃጀት በሁለት ቀናት ውስጥ አልቆ የንቃተህግ የህዝብ ንቅናቄ በየማህበራዊ መሠረቶች እየተደረገ እንደሚመራ በመግለጽ የታችኛው መዋቅር በፍጥነት ተልዕኮውን እንዲያሣኩ ስምሪት እንደተሠጠ ገልፀዋል። አዋጁ ከወጣበት ዕለት አንስቶ የአሸባሪውን ቡድን ተልዕኮ በመደገፍና በህዝብ ውስጥ በማስተጋባት ስጋት እንደፈጠሩ የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በህግ ቁጥጥር ስር ውለው እየተጠየቁ መሆናቸውንም ለአብነት በማንሳት ከዚህ በኋላም በጣም በተጠናከረ መልኩ የጥበቃ ስራዎች እንዲሰሩ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል።

እንደዚሁም ፖሊስ በማንኛውም ሰዓትና ቦታ ጥርጣሬ የሚያሳድሩ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና ተሽከርካሪዎችን እያቀረበ መጠየቁን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኃላፊው በአፅንዖት አስታውቀዋል። ለዚህም አጋዥ የሚሆኑ ኬላዎች በዞናች በአራት መስመሮች፣ መውጫና መግቢያዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ስራ እንዲጀምሩ መመሪያ ተሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በአከባቢ ሠላም ቀጣይነት ዙሪያ የህዝብ የተደራጀ ጥበቃና ፈቃደኝነት እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ከከዚህ ቀደሙ የተለየ ተነሳሽነት፣ ተባባሪነትና ንቃት የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ መሆናችን ግንዛቤ ተወስዶ በየቀጠናው ጠንካራ የህዝብ አደረጃጀቶች እንዲፈጠሩና በፍጥነት በሪፖርት እንዲገለፁ መመሪያ ተሰጥቷል። ለህዝቡም የአደራ መልዕክት ተላልፏል።

የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን
ጉዳዮች መምሪያ ነው።
ጥቅምት/27/2014 ዓ.ም
#ሣውላ