#እምወድሽዋ!❤ ቅዳሜዋ!❤ ሸጋዬዋ!❤
ሰውነት!!!!!
የመቅደሱ ማእጠንት፤
የዛውያው ሃጃ፤
በጨለማው ዘመን ፤
በሰው በላው ወራት፣
ጸዳል እየረጨ፤
በእዝነት ወጋገን ላይ፤ ካልሰራ ብርሃን ፤
ምን ሊረባኝ ከቶ ፤
ሰው አልባ መሻኢክ፤ አልቦ ፍቅር ካሃን።።
ጽና ሰውነቴ፤
በርታ አዳምነቴ፤
ቱባ ወረትህን፤
ውብ ሰውነትህን፤
በሰውአዊ ልክህ ፤ መልክህን አስከብር፤
ከሰው ልኬት ወርዷል ፤
በእኔ ብቻ ዜማ፤
በእኔ ብቻ ስሙኝ፤ ሰው እያዳፈነ ፣ ዛውያና ደብር።
አለም አስጠልቶን፤
ዱኒያ እየነጀሰን፤
ልንጣዳ ብለን፤
ብንገባ ከለዋ ፤ ብንሸሽ ወደ ገዳም ፤
ኑ ያለን ከዳሚ፤
ኑ ያለን ዘካሪ፣
በዚያም ገፍቶ ጣለን፤ በዚያም ገፍቶ አስወጣን።
የቤተስኪያኑ ራስ፤
የመስጂዱ ሚናር ፤
ከሰው ስፍር በታች፤
ከሰው ድካ በታች ፤ ከሆነ ሚዛኑ፤
እነ አባ ግርታ፤
ቅዳሴውን ተውት፤
ሶላቱንም ተውት፤
በጉድል ስፍራችሁ፤
በዘንባላው ቁና፤ ተበላሽቷል ቀኑ ፤
ለሰማይ ያሰበው፤
ሸቃጭ ሆኖ ቀርቷል፤
ሃቅን እየሸጠ ፤ ሃቅን እየገፋ ሁሉም ለወገኑ ፤
የአምልኮ ጸበኞች፤
ትሰሙኝ እንደሆን፤
ዛውያውን ተውት ፤
ደብሩን ልቀቁና ፤
ሰው በጎደለበት ሰው የሚል ሰው ሁኑ፤
አለበለዚያማ፤
ሰውን ለማፋረስ፤
ሃገር ለመነጀስ ፤ ጠማማና ክፉ መች አነሰው ቀኑ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
"ናካይታ"💚
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤
#3ቀን🎂🎂
@getem
@getem
@Nagayta
ሰውነት!!!!!
የመቅደሱ ማእጠንት፤
የዛውያው ሃጃ፤
በጨለማው ዘመን ፤
በሰው በላው ወራት፣
ጸዳል እየረጨ፤
በእዝነት ወጋገን ላይ፤ ካልሰራ ብርሃን ፤
ምን ሊረባኝ ከቶ ፤
ሰው አልባ መሻኢክ፤ አልቦ ፍቅር ካሃን።።
ጽና ሰውነቴ፤
በርታ አዳምነቴ፤
ቱባ ወረትህን፤
ውብ ሰውነትህን፤
በሰውአዊ ልክህ ፤ መልክህን አስከብር፤
ከሰው ልኬት ወርዷል ፤
በእኔ ብቻ ዜማ፤
በእኔ ብቻ ስሙኝ፤ ሰው እያዳፈነ ፣ ዛውያና ደብር።
አለም አስጠልቶን፤
ዱኒያ እየነጀሰን፤
ልንጣዳ ብለን፤
ብንገባ ከለዋ ፤ ብንሸሽ ወደ ገዳም ፤
ኑ ያለን ከዳሚ፤
ኑ ያለን ዘካሪ፣
በዚያም ገፍቶ ጣለን፤ በዚያም ገፍቶ አስወጣን።
የቤተስኪያኑ ራስ፤
የመስጂዱ ሚናር ፤
ከሰው ስፍር በታች፤
ከሰው ድካ በታች ፤ ከሆነ ሚዛኑ፤
እነ አባ ግርታ፤
ቅዳሴውን ተውት፤
ሶላቱንም ተውት፤
በጉድል ስፍራችሁ፤
በዘንባላው ቁና፤ ተበላሽቷል ቀኑ ፤
ለሰማይ ያሰበው፤
ሸቃጭ ሆኖ ቀርቷል፤
ሃቅን እየሸጠ ፤ ሃቅን እየገፋ ሁሉም ለወገኑ ፤
የአምልኮ ጸበኞች፤
ትሰሙኝ እንደሆን፤
ዛውያውን ተውት ፤
ደብሩን ልቀቁና ፤
ሰው በጎደለበት ሰው የሚል ሰው ሁኑ፤
አለበለዚያማ፤
ሰውን ለማፋረስ፤
ሃገር ለመነጀስ ፤ ጠማማና ክፉ መች አነሰው ቀኑ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
"ናካይታ"💚
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤
#3ቀን🎂🎂
@getem
@getem
@Nagayta
#እምወድሽዋ!❤ ቅዳሜዋ!❤ ሸጋዬዋ!❤
አድዋን ስትዘፍኚው!!!!
የአድዋን ተራሮች፤
የአምባላጌን ታምር፤
የሰው መሆን ትግሉን፤
የኔነቴን ቀመር ፤ስፍርና ልኩን የኢትዮጳያዊነቴን፤
እንደምን አወቅሽው፤
እንደምን ሰጠሽኝ፤
የመልኬን ማሰሪያ፤ የወገቤን ስፍር ድርብ መቀነቴን???
አንችማ ልጅቱ፤
በአድዋ ብራና፤
መልካ መልኬን ሁሉ፣ በማይጠፋ ቀለም በደማቁ ጽፈሽ፤
በመላኢክት ቋንቋ፤
በማህሌታይ ድምጽ፤
በየጎራው አናት የአርበኞቹን ቅኔ ወርቅሰሙን ዘርፈሽ፤
በእስትንፋስሽ ቃና፣
በምናብሽ ሽታ፣ከአድዋ ቁመት ላይ አድዋን ጨምረሽ፤
በሰገነቱ ላይ፤
አድዋን ስትዘፍኚው፤ በጣይቱ ቀሚስ ፤ በእጅ አምባሯ ደምቀሽ፤
ይኸው ይህን ሰሞን፤
ስንቱን ሰው ነፍጠኛ፤
ስንቱን ሰው አርበኛ፤ስንቱን ሰው ጀብራራ አድርገሽው ቀረሽ።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤
@getem
@getem
@Nagayta
አድዋን ስትዘፍኚው!!!!
የአድዋን ተራሮች፤
የአምባላጌን ታምር፤
የሰው መሆን ትግሉን፤
የኔነቴን ቀመር ፤ስፍርና ልኩን የኢትዮጳያዊነቴን፤
እንደምን አወቅሽው፤
እንደምን ሰጠሽኝ፤
የመልኬን ማሰሪያ፤ የወገቤን ስፍር ድርብ መቀነቴን???
አንችማ ልጅቱ፤
በአድዋ ብራና፤
መልካ መልኬን ሁሉ፣ በማይጠፋ ቀለም በደማቁ ጽፈሽ፤
በመላኢክት ቋንቋ፤
በማህሌታይ ድምጽ፤
በየጎራው አናት የአርበኞቹን ቅኔ ወርቅሰሙን ዘርፈሽ፤
በእስትንፋስሽ ቃና፣
በምናብሽ ሽታ፣ከአድዋ ቁመት ላይ አድዋን ጨምረሽ፤
በሰገነቱ ላይ፤
አድዋን ስትዘፍኚው፤ በጣይቱ ቀሚስ ፤ በእጅ አምባሯ ደምቀሽ፤
ይኸው ይህን ሰሞን፤
ስንቱን ሰው ነፍጠኛ፤
ስንቱን ሰው አርበኛ፤ስንቱን ሰው ጀብራራ አድርገሽው ቀረሽ።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤
@getem
@getem
@Nagayta
#እምወድሽዋ! ❤ቅዳሜዋ!❤ ሸጋዬዋ!❤
እንደ ሃምሌ ዝናብ፤
እያስገመገመ፣
የመጣውን ጠላት፤
የሚመክትበት ባለ አንድ ቀልሃ ጠበንጃው ባርቆበት፣
በባዶ ሜዳ ላይ፤
በብላኔ ሞይዘር ፤ ጥይት በሌለበት፤
ያነ ሰው ፎከረ ፤
ያ ጎበዝ ሸለለ፤ ኧረ ጎራው ማለት ኧረ ደኑ ማለት የአባቱ ሆኖበት።
ዳሩ ምን ዋጋ አለው፤
ኧረ ጎራው ማለት፤በባዶ ጠበንጃ በባዶ ጥይት ፤
ምርኮኛ አያስገብር አይገድል ጠላት፤
እዩልኝ ይኸን ሰው፣
ባዶ ጠበንጃውን፤
ርግፍ አርጎ ጥሎ ምሽጉን ቆፍሮ አምልጧል ከሞት!!!
ወትሮም ቢቸግር ነው፤ የሰው ተኳሽነት የሰው ጀግንነት፤
ከሰማይ ሲመጣ፤
እንኳን አተኳኮስ ይገዳል ይሉኛል አሻግሮ ማየት።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
እንደ ሃምሌ ዝናብ፤
እያስገመገመ፣
የመጣውን ጠላት፤
የሚመክትበት ባለ አንድ ቀልሃ ጠበንጃው ባርቆበት፣
በባዶ ሜዳ ላይ፤
በብላኔ ሞይዘር ፤ ጥይት በሌለበት፤
ያነ ሰው ፎከረ ፤
ያ ጎበዝ ሸለለ፤ ኧረ ጎራው ማለት ኧረ ደኑ ማለት የአባቱ ሆኖበት።
ዳሩ ምን ዋጋ አለው፤
ኧረ ጎራው ማለት፤በባዶ ጠበንጃ በባዶ ጥይት ፤
ምርኮኛ አያስገብር አይገድል ጠላት፤
እዩልኝ ይኸን ሰው፣
ባዶ ጠበንጃውን፤
ርግፍ አርጎ ጥሎ ምሽጉን ቆፍሮ አምልጧል ከሞት!!!
ወትሮም ቢቸግር ነው፤ የሰው ተኳሽነት የሰው ጀግንነት፤
ከሰማይ ሲመጣ፤
እንኳን አተኳኮስ ይገዳል ይሉኛል አሻግሮ ማየት።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
#እምወድሽዋ!❤ ቅዳሜዋ!❤ ሸጋዬዋ!❤
ሸጊቷ ቅዳሜ!!!!!
ዘበናይ ቅዳሜ!!!!!!!!!
ሽሙንሙን ፣
ሽሙንሙን፣
ሽቅርቅር፣
ፍንድቅድቅ፣
ፍልቅልቅ በይልኝ፣
ሳቄ ይቀድመኛል፣
ሰማዩ ሲገለጥ፣ አንች ስትመጭልኝ።
እስክስ ቅዳሜ! !!!!!!
ከሰኞ እስከ አርብ ፤
ባለቃ በምንዝር ፣ ታምሜ ተምሜ ፤
የምታከምብሽ ፤
ባለሟል፤ እንዴት ነሽ ቅዳሜ! !!!!!!
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ቅዳሜያችን፣
የቅኔ ጎርፍ የሚጎርፍባት፣ የእሁድን እረፍት እያሰብን
የምንወዳቸውን መፅሃፍት
የምናነብባት፣ ነፍስያችንን በቅጡ ለማዳመጥ ፋታ
የምንወስድባት፣ ከወዳጅ ዘመድ የምንዘያየርባት ደርባባ
ቀናችን ናት!!!!!
@getem
@getem
@Nagayta
ሸጊቷ ቅዳሜ!!!!!
ዘበናይ ቅዳሜ!!!!!!!!!
ሽሙንሙን ፣
ሽሙንሙን፣
ሽቅርቅር፣
ፍንድቅድቅ፣
ፍልቅልቅ በይልኝ፣
ሳቄ ይቀድመኛል፣
ሰማዩ ሲገለጥ፣ አንች ስትመጭልኝ።
እስክስ ቅዳሜ! !!!!!!
ከሰኞ እስከ አርብ ፤
ባለቃ በምንዝር ፣ ታምሜ ተምሜ ፤
የምታከምብሽ ፤
ባለሟል፤ እንዴት ነሽ ቅዳሜ! !!!!!!
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ቅዳሜያችን፣
የቅኔ ጎርፍ የሚጎርፍባት፣ የእሁድን እረፍት እያሰብን
የምንወዳቸውን መፅሃፍት
የምናነብባት፣ ነፍስያችንን በቅጡ ለማዳመጥ ፋታ
የምንወስድባት፣ ከወዳጅ ዘመድ የምንዘያየርባት ደርባባ
ቀናችን ናት!!!!!
@getem
@getem
@Nagayta
❤1
#እምወድሽዋ!❤ ቅዳሜዋ!❤ ሸጋዬዋ!❤
ቸኩሎ ሟችና፤ የሃምሌ ደመና፤
ከእንጣል በስተቀር፤
ከእንውረድ በስተቀር፤ ሌላ ምን ያውቁና።
ስማኝማ ጓዴ፤
ኧረ ገዳይ ሲሉህ ፤
ሰማይ ሸና ሲሉህ ፤ ደንብረህ አትፍለስ፤
አህላቁ ከነዳው፤
ችኩልም ይቻኮል፤ ደመናውም ይፍሰስ፤
እኔ የቱፍታው ልጅ፤
እኔ የጉፍታው ልጅ፤
ሶብር እንዲሆነኝ፤ የዱኣ ገሳየን ብርድልብሴን ልልበስ፤
አላየሁምና ፤
ተቻኩሎ የሞተ፤ አይለምደኝም ብሎ ከቀብር ሲመለስ።
እመዋ! እመዋ!!!
እነየ እነየ!!!
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሽብርቅርቅ ያለች ቅዳሚች ጀባ!❤
@getem
@getem
@Nagayta
ቸኩሎ ሟችና፤ የሃምሌ ደመና፤
ከእንጣል በስተቀር፤
ከእንውረድ በስተቀር፤ ሌላ ምን ያውቁና።
ስማኝማ ጓዴ፤
ኧረ ገዳይ ሲሉህ ፤
ሰማይ ሸና ሲሉህ ፤ ደንብረህ አትፍለስ፤
አህላቁ ከነዳው፤
ችኩልም ይቻኮል፤ ደመናውም ይፍሰስ፤
እኔ የቱፍታው ልጅ፤
እኔ የጉፍታው ልጅ፤
ሶብር እንዲሆነኝ፤ የዱኣ ገሳየን ብርድልብሴን ልልበስ፤
አላየሁምና ፤
ተቻኩሎ የሞተ፤ አይለምደኝም ብሎ ከቀብር ሲመለስ።
እመዋ! እመዋ!!!
እነየ እነየ!!!
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሽብርቅርቅ ያለች ቅዳሚች ጀባ!❤
@getem
@getem
@Nagayta
#እምወድሽዋ!❤ ቅዳሜዋ!❤ ሸጋዬዋ!❤
ዛሬ ከድር ናቸዉ ይሏል ወሎየ !
ከቅዳሜ ቆሌ የተዳረ ለታ ፥
የትኛዉ ቀን ይደብርሃል ብባል ፥ የትኛዉም ልል እችላለሁ ። ሸገር ካለሁ ግን ምን መዓት
ቢመጣ ቅዳሜ አይደብረኝም ።
የአዲስ አበባ ቡና ቅዳሜ ቅዳሜ ይለያል ፥ ወላ ለምን በጨዉ አትጠጣዉም ( ሃሃ ወዮ
ክባድ ! ) ። የለመድከዉን አሰልች ሰዉ እየተመለከትክ ፥ ያን ሰዉ በቅዳሜ ስትመለከተዉ
አትጠግበዉም ፥ ብርቅ ይኾንብሃል ። መፅሔቱ ፣ ጋዜጣዉ ይጎርፋል ፥ በቅዳሜ ። ሳምንቱን
በስራ ተጠፍሮ የነበረዉ ከተሜ ፥ በእለተ ቅዳሜ የወሬ ጋኑን ይፈታል ፣ ወገቡን ለሳቅ እና
ለጨዋታ ያዘጋጃል ። ሀብታም ከባንኮኒዉ ፤ ድሀም ከስኒዉ ስር ይለገታል ፥ በቅዳሜ ።
እንደኛ ያለ የገጠር ልጅ አዲሲቷን ልብሱን የሚለብሰዉ ለበዓል ነዉ ሃሃ ፥ የአዲስ አበቤ
ቆንጆዎችስ በቅዳሜ ቀሚስ ላይ የፈሰሱ የአልማዝ ፈርጦች መስለዉ ይዉላሉ ።
በቅዳሜ የጓደኞች ሳቅ ይጎርፋል ፣ ከሩቅ ሀገር ጨዋታ ይሰማል ። ሁላማ ስትራመድ
ትነጥራለህ ስልህ ፥ ስለምነጥር ነዉ ።
የዛሬዉ ቅዳሜ ደግሞ በቃ ይለያል ፥ አይንህ ስትገልጥ ሀገሩ ፍስለታን ሞሽሮ ቁሟል ።
አንተስ ምን ታደርጋለህ ደጀ ሰላሙን ትሳለምና ፣ ከመፀሀፍት ደንበኛህ አለላ መፅሔትን
ትገዛና ( ፍትህ የምትሉ ፥ ነገር አትፈልጉኝ ) ፣ የኤፍሬም ስዩምን 'ምክንያቱም ዛሬ ቀኑ
ቅዳሜ ነዉ ግጥም ' በቃልህ ትወጣዉና ፣ የጠዋት አጃኢበኛ የዶሮ አይን ቡናህን ትልፍና ፣
ከሰዐት ሸገር ኤፍ ኤምን አሻግረህ እየናፈቅህ ፥ ቀኑን የሚያረዝምልህን አምላክ
ትጋተተዋለህ ።
ኤፍሬምን ትንሽ እናዉርደዉ እስኪ
-
ቀጭን ወገቧ ላይ
ከእንብርቷ በላይ ልብሷ ተንጠልጥሏል
የወርቅ መስቀሏ
ጡቶቿ መካከል ዘንበል ብሎ ወድቋል
መንገድ ላይ ያየኃት
የማላዉቃት ሴት ናት ።
ወዴት እንደምትሄድ ባሳቤ ገመትኩኝ
አንድ የቀጠራትን ወንደላጤ አሰብኩኝ
ሠባት እንቁላሎች
ግማሽ ኪሎ ሥጋ....( ገዝቶ )
ከርሷ ጋር ካልሆነ
ቡና አልጠጣም ብሎ አሥሬ እያዛጋ
መጽሐፏን ከፍቶ
በሩን ክፍት ትቶ
መልሶ መላልሶ ሠዓቱን እያየ
የሚጠብቃት ሠዉ
ሐሳቤ ዉል አለዉ
ምክንያቱም ዛሬ ቀኑ ቅዳሜ ነዉ ።
-
ይችን የቅዳሜ ከረሜላ እንዳታልቅብኝ እየሳሳሁ መምጠጥ ጀምሬያለሁ ፥ መልካም ቅዳሜ
ይሁንላችሁ ወዳጆች ።
አለላን አንብቡት ፣ በቃ ምርጥ ነዉ
ወላ ከመፀሀፍ እኩል ነዉ
አጃኢበኛ ብዕረኞች ዘምተዉበታል
ጋብዣለሁ ።
ደግሞ ደግሞ " ማርሲላስ " የሚል መፀሀፍ ገዝታችኃል ፥ በሉ ቶሎ ግዙ ። ደራሲዉ ነፍሱን
ሰጥቷል። በአንድ ሰሞን ሙሉጌታ ተስፋየ ለቅሶ ሄዶ ማስተዛዘኛ " ግጥም ሰጠ " ሲባል
ሰምቸ ጉድ ብያለሁ ። የዚህኛዉ ደግሞ ባሰ ፥ ጊዜዉን ፣ ነፍሱን ፣ መጣፈጡን ሁሉ ነዉ
የቸረዉ ። አህመድ ሁስ ፥ መልካም ቅዳሜ ኸይር አሳብየዋ ። የቅዳሜን ቡና በጋበዝኩህ
በወደድኩ ነበር ።
#ቴዎድሮስ ካሳ
@getem
@getem
@balmbaras
ዛሬ ከድር ናቸዉ ይሏል ወሎየ !
ከቅዳሜ ቆሌ የተዳረ ለታ ፥
የትኛዉ ቀን ይደብርሃል ብባል ፥ የትኛዉም ልል እችላለሁ ። ሸገር ካለሁ ግን ምን መዓት
ቢመጣ ቅዳሜ አይደብረኝም ።
የአዲስ አበባ ቡና ቅዳሜ ቅዳሜ ይለያል ፥ ወላ ለምን በጨዉ አትጠጣዉም ( ሃሃ ወዮ
ክባድ ! ) ። የለመድከዉን አሰልች ሰዉ እየተመለከትክ ፥ ያን ሰዉ በቅዳሜ ስትመለከተዉ
አትጠግበዉም ፥ ብርቅ ይኾንብሃል ። መፅሔቱ ፣ ጋዜጣዉ ይጎርፋል ፥ በቅዳሜ ። ሳምንቱን
በስራ ተጠፍሮ የነበረዉ ከተሜ ፥ በእለተ ቅዳሜ የወሬ ጋኑን ይፈታል ፣ ወገቡን ለሳቅ እና
ለጨዋታ ያዘጋጃል ። ሀብታም ከባንኮኒዉ ፤ ድሀም ከስኒዉ ስር ይለገታል ፥ በቅዳሜ ።
እንደኛ ያለ የገጠር ልጅ አዲሲቷን ልብሱን የሚለብሰዉ ለበዓል ነዉ ሃሃ ፥ የአዲስ አበቤ
ቆንጆዎችስ በቅዳሜ ቀሚስ ላይ የፈሰሱ የአልማዝ ፈርጦች መስለዉ ይዉላሉ ።
በቅዳሜ የጓደኞች ሳቅ ይጎርፋል ፣ ከሩቅ ሀገር ጨዋታ ይሰማል ። ሁላማ ስትራመድ
ትነጥራለህ ስልህ ፥ ስለምነጥር ነዉ ።
የዛሬዉ ቅዳሜ ደግሞ በቃ ይለያል ፥ አይንህ ስትገልጥ ሀገሩ ፍስለታን ሞሽሮ ቁሟል ።
አንተስ ምን ታደርጋለህ ደጀ ሰላሙን ትሳለምና ፣ ከመፀሀፍት ደንበኛህ አለላ መፅሔትን
ትገዛና ( ፍትህ የምትሉ ፥ ነገር አትፈልጉኝ ) ፣ የኤፍሬም ስዩምን 'ምክንያቱም ዛሬ ቀኑ
ቅዳሜ ነዉ ግጥም ' በቃልህ ትወጣዉና ፣ የጠዋት አጃኢበኛ የዶሮ አይን ቡናህን ትልፍና ፣
ከሰዐት ሸገር ኤፍ ኤምን አሻግረህ እየናፈቅህ ፥ ቀኑን የሚያረዝምልህን አምላክ
ትጋተተዋለህ ።
ኤፍሬምን ትንሽ እናዉርደዉ እስኪ
-
ቀጭን ወገቧ ላይ
ከእንብርቷ በላይ ልብሷ ተንጠልጥሏል
የወርቅ መስቀሏ
ጡቶቿ መካከል ዘንበል ብሎ ወድቋል
መንገድ ላይ ያየኃት
የማላዉቃት ሴት ናት ።
ወዴት እንደምትሄድ ባሳቤ ገመትኩኝ
አንድ የቀጠራትን ወንደላጤ አሰብኩኝ
ሠባት እንቁላሎች
ግማሽ ኪሎ ሥጋ....( ገዝቶ )
ከርሷ ጋር ካልሆነ
ቡና አልጠጣም ብሎ አሥሬ እያዛጋ
መጽሐፏን ከፍቶ
በሩን ክፍት ትቶ
መልሶ መላልሶ ሠዓቱን እያየ
የሚጠብቃት ሠዉ
ሐሳቤ ዉል አለዉ
ምክንያቱም ዛሬ ቀኑ ቅዳሜ ነዉ ።
-
ይችን የቅዳሜ ከረሜላ እንዳታልቅብኝ እየሳሳሁ መምጠጥ ጀምሬያለሁ ፥ መልካም ቅዳሜ
ይሁንላችሁ ወዳጆች ።
አለላን አንብቡት ፣ በቃ ምርጥ ነዉ
ወላ ከመፀሀፍ እኩል ነዉ
አጃኢበኛ ብዕረኞች ዘምተዉበታል
ጋብዣለሁ ።
ደግሞ ደግሞ " ማርሲላስ " የሚል መፀሀፍ ገዝታችኃል ፥ በሉ ቶሎ ግዙ ። ደራሲዉ ነፍሱን
ሰጥቷል። በአንድ ሰሞን ሙሉጌታ ተስፋየ ለቅሶ ሄዶ ማስተዛዘኛ " ግጥም ሰጠ " ሲባል
ሰምቸ ጉድ ብያለሁ ። የዚህኛዉ ደግሞ ባሰ ፥ ጊዜዉን ፣ ነፍሱን ፣ መጣፈጡን ሁሉ ነዉ
የቸረዉ ። አህመድ ሁስ ፥ መልካም ቅዳሜ ኸይር አሳብየዋ ። የቅዳሜን ቡና በጋበዝኩህ
በወደድኩ ነበር ።
#ቴዎድሮስ ካሳ
@getem
@getem
@balmbaras
ግጥም ብቻ 📘
ለ2013 የእንኳን ደህና መጣህ ማያ ፣ ለቅዳሚታችን ደግሞ እንደመዳረሻ! 🌻❤🌻❤🌻❤ የድልና የስኬት ዓመት!!!!!! ማሸነፍና መሸነፍ ያለው በገዛ ልብ ውስጥ ነው!!!!! ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚሁ ይሆናል። የተፈጠርነው ለድልና ለስኬት ነውና ዓመቱን በሩጫው መስመር የመጀመሪያው ረድፍ ላይ የምንወጣበት ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው!!🌻 እነሆ ዛሬን ሳቅ በሳቅ በጀመርነው ጊዜ ዓመቱን ከኛ…
#እምወድሽዋ!❤ ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!❤
ዛሬ ቅዳሚታችንን ትላንት ለቀናቸው የነበሩትን ሶስት ፎቶዎች አይታቹ የተሰማቹን የምትልኩልን (እኛም መልሰን ወደ ቻናል የምናመጣው ) ቅዳሚት ትሆናለች ማለት ነው።
ዘመኑ ይሳቅላቹ!🌻❤️ ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤
@getem
@getem
@balmbaras👈
@Nagayta👈
ዛሬ ቅዳሚታችንን ትላንት ለቀናቸው የነበሩትን ሶስት ፎቶዎች አይታቹ የተሰማቹን የምትልኩልን (እኛም መልሰን ወደ ቻናል የምናመጣው ) ቅዳሚት ትሆናለች ማለት ነው።
ዘመኑ ይሳቅላቹ!🌻❤️ ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤
@getem
@getem
@balmbaras👈
@Nagayta👈
#እምወድሽዋ!❤ ቅዳሜዋ!❤ ሸጋዬዋ!
..ዛሬ ደርባባዋ ቅዳሚት ነች....ለክብሯ ሲባል አንድ ሸላይ የሆነ ግጥም ነው ነው የምንገባበዘው....ስለ ግጥሙ ሀሳብ እና ስለ ግጥሙ የቃላት ውበት ላወራ ነበር ግን....እናንተው አንብባችሁት ተደመሙበት #ቅዳሚታቹን ግጥሙን ደጋግሞ በማንበብ እና ለወዳጆቻቹ በመጋበዝ ተገማሸሩበት....#ለኔም በአሪፍ ድምፅ ተነቦ ቢላክልኝ አልጠላም..☺ መቼም ምን አይነት ግጥም ቢሆነው እንዲህ በጠዋቱ ተነስቶ ሚሸልልብን ማለታቹ አይቀርም....እንግድያው ፍረዱኝ...ይኸው እንካቹ...❤
"ስራህ ?"ስባል
እንዲህ እመልሳለሁ
ሀዘንን ማባበል
ለሚያለቅሱ ነፍሶች በገና ማቀበል
" ስራ ?" ህ ስባል
ከደስታ መቃጠር
ለሰዓሊ ሸራ ዘርግቶ መወጠር
" ስራህ ? " ስባል
መቃ መጠራረብ
ላንድ ገጣሚ ነፍስ መድ ከፊት ማቅረብ
ከየት ስባል
ምን እመልሳለሁ
እንዴት ስባል ብቻ መናገረ አውቃለሁ
ብኩን ሰው ነበርኩኝ - ተሰበርኩ እንደ ገል
የማለውቀውን ነፍስ ጀመርኩኝ ማገልገል
ነፍሴንም
ገደልኳት
ሰውቼ አቀርብኳት
የቀላይ መታሪ - ታንኳ ሁኚ አልኳት
ያኔም ነው እንደ አረሆ- እንደኮከብ ጧሪ
ከፍ ብሎ ቋሚ - ናፍቆት አጋፋሪ
ብቻዬን የሆንኩት
እንደ እልፍኝ አስከልካይ ዘብ ሆኜ የቆምኩት
ጮራ የበተንኩት
ነፍስ ያገለገልኩት
አየህ አይገለፅም ማደሪያው
የወዲያ ወዲያው
ቅፅር ካለፈረሱ
ሀዘን ካልሰፈሩ
ያን እግረ ሙቅ ገንቦ - ደፍረው ካልሰበሩ
አይነገር
በቃል አይጋገር
ለተራ ተርታ ሰው - አለው ማደናገር
ይሄው ነው
በገናውን በስልት
ቀሰሙንም በስልት
ዋሽንቱንም በስልት
ሳቀርብ እያየህኝ
እኔ ነኝ የምፅፍ
እኔ ነኝ የማዜም
በዋሽንት የማፏጭ - በተብሳ መቃ
ብልህ እንዳትለኝ - አንትንገረኝ በቃ
እኔው እያጋፍርኩ
መሪ - ጌታ እያለኝ የጥበብ አለቃ ::
📝ሰለሀዲን አሊ
ደመቅመቅ ያለ ቅዳሜ ጀባታ!❤
@getem
@getem
@Nagayta
..ዛሬ ደርባባዋ ቅዳሚት ነች....ለክብሯ ሲባል አንድ ሸላይ የሆነ ግጥም ነው ነው የምንገባበዘው....ስለ ግጥሙ ሀሳብ እና ስለ ግጥሙ የቃላት ውበት ላወራ ነበር ግን....እናንተው አንብባችሁት ተደመሙበት #ቅዳሚታቹን ግጥሙን ደጋግሞ በማንበብ እና ለወዳጆቻቹ በመጋበዝ ተገማሸሩበት....#ለኔም በአሪፍ ድምፅ ተነቦ ቢላክልኝ አልጠላም..☺ መቼም ምን አይነት ግጥም ቢሆነው እንዲህ በጠዋቱ ተነስቶ ሚሸልልብን ማለታቹ አይቀርም....እንግድያው ፍረዱኝ...ይኸው እንካቹ...❤
"ስራህ ?"ስባል
እንዲህ እመልሳለሁ
ሀዘንን ማባበል
ለሚያለቅሱ ነፍሶች በገና ማቀበል
" ስራ ?" ህ ስባል
ከደስታ መቃጠር
ለሰዓሊ ሸራ ዘርግቶ መወጠር
" ስራህ ? " ስባል
መቃ መጠራረብ
ላንድ ገጣሚ ነፍስ መድ ከፊት ማቅረብ
ከየት ስባል
ምን እመልሳለሁ
እንዴት ስባል ብቻ መናገረ አውቃለሁ
ብኩን ሰው ነበርኩኝ - ተሰበርኩ እንደ ገል
የማለውቀውን ነፍስ ጀመርኩኝ ማገልገል
ነፍሴንም
ገደልኳት
ሰውቼ አቀርብኳት
የቀላይ መታሪ - ታንኳ ሁኚ አልኳት
ያኔም ነው እንደ አረሆ- እንደኮከብ ጧሪ
ከፍ ብሎ ቋሚ - ናፍቆት አጋፋሪ
ብቻዬን የሆንኩት
እንደ እልፍኝ አስከልካይ ዘብ ሆኜ የቆምኩት
ጮራ የበተንኩት
ነፍስ ያገለገልኩት
አየህ አይገለፅም ማደሪያው
የወዲያ ወዲያው
ቅፅር ካለፈረሱ
ሀዘን ካልሰፈሩ
ያን እግረ ሙቅ ገንቦ - ደፍረው ካልሰበሩ
አይነገር
በቃል አይጋገር
ለተራ ተርታ ሰው - አለው ማደናገር
ይሄው ነው
በገናውን በስልት
ቀሰሙንም በስልት
ዋሽንቱንም በስልት
ሳቀርብ እያየህኝ
እኔ ነኝ የምፅፍ
እኔ ነኝ የማዜም
በዋሽንት የማፏጭ - በተብሳ መቃ
ብልህ እንዳትለኝ - አንትንገረኝ በቃ
እኔው እያጋፍርኩ
መሪ - ጌታ እያለኝ የጥበብ አለቃ ::
📝ሰለሀዲን አሊ
ደመቅመቅ ያለ ቅዳሜ ጀባታ!❤
@getem
@getem
@Nagayta
👍2