#እምወድሽዋ!❤ ቅዳሜዋ!❤ ሸጋዬዋ!❤
ሰውነት!!!!!
የመቅደሱ ማእጠንት፤
የዛውያው ሃጃ፤
በጨለማው ዘመን ፤
በሰው በላው ወራት፣
ጸዳል እየረጨ፤
በእዝነት ወጋገን ላይ፤ ካልሰራ ብርሃን ፤
ምን ሊረባኝ ከቶ ፤
ሰው አልባ መሻኢክ፤ አልቦ ፍቅር ካሃን።።
ጽና ሰውነቴ፤
በርታ አዳምነቴ፤
ቱባ ወረትህን፤
ውብ ሰውነትህን፤
በሰውአዊ ልክህ ፤ መልክህን አስከብር፤
ከሰው ልኬት ወርዷል ፤
በእኔ ብቻ ዜማ፤
በእኔ ብቻ ስሙኝ፤ ሰው እያዳፈነ ፣ ዛውያና ደብር።
አለም አስጠልቶን፤
ዱኒያ እየነጀሰን፤
ልንጣዳ ብለን፤
ብንገባ ከለዋ ፤ ብንሸሽ ወደ ገዳም ፤
ኑ ያለን ከዳሚ፤
ኑ ያለን ዘካሪ፣
በዚያም ገፍቶ ጣለን፤ በዚያም ገፍቶ አስወጣን።
የቤተስኪያኑ ራስ፤
የመስጂዱ ሚናር ፤
ከሰው ስፍር በታች፤
ከሰው ድካ በታች ፤ ከሆነ ሚዛኑ፤
እነ አባ ግርታ፤
ቅዳሴውን ተውት፤
ሶላቱንም ተውት፤
በጉድል ስፍራችሁ፤
በዘንባላው ቁና፤ ተበላሽቷል ቀኑ ፤
ለሰማይ ያሰበው፤
ሸቃጭ ሆኖ ቀርቷል፤
ሃቅን እየሸጠ ፤ ሃቅን እየገፋ ሁሉም ለወገኑ ፤
የአምልኮ ጸበኞች፤
ትሰሙኝ እንደሆን፤
ዛውያውን ተውት ፤
ደብሩን ልቀቁና ፤
ሰው በጎደለበት ሰው የሚል ሰው ሁኑ፤
አለበለዚያማ፤
ሰውን ለማፋረስ፤
ሃገር ለመነጀስ ፤ ጠማማና ክፉ መች አነሰው ቀኑ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
"ናካይታ"💚
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤
#3ቀን🎂🎂
@getem
@getem
@Nagayta
ሰውነት!!!!!
የመቅደሱ ማእጠንት፤
የዛውያው ሃጃ፤
በጨለማው ዘመን ፤
በሰው በላው ወራት፣
ጸዳል እየረጨ፤
በእዝነት ወጋገን ላይ፤ ካልሰራ ብርሃን ፤
ምን ሊረባኝ ከቶ ፤
ሰው አልባ መሻኢክ፤ አልቦ ፍቅር ካሃን።።
ጽና ሰውነቴ፤
በርታ አዳምነቴ፤
ቱባ ወረትህን፤
ውብ ሰውነትህን፤
በሰውአዊ ልክህ ፤ መልክህን አስከብር፤
ከሰው ልኬት ወርዷል ፤
በእኔ ብቻ ዜማ፤
በእኔ ብቻ ስሙኝ፤ ሰው እያዳፈነ ፣ ዛውያና ደብር።
አለም አስጠልቶን፤
ዱኒያ እየነጀሰን፤
ልንጣዳ ብለን፤
ብንገባ ከለዋ ፤ ብንሸሽ ወደ ገዳም ፤
ኑ ያለን ከዳሚ፤
ኑ ያለን ዘካሪ፣
በዚያም ገፍቶ ጣለን፤ በዚያም ገፍቶ አስወጣን።
የቤተስኪያኑ ራስ፤
የመስጂዱ ሚናር ፤
ከሰው ስፍር በታች፤
ከሰው ድካ በታች ፤ ከሆነ ሚዛኑ፤
እነ አባ ግርታ፤
ቅዳሴውን ተውት፤
ሶላቱንም ተውት፤
በጉድል ስፍራችሁ፤
በዘንባላው ቁና፤ ተበላሽቷል ቀኑ ፤
ለሰማይ ያሰበው፤
ሸቃጭ ሆኖ ቀርቷል፤
ሃቅን እየሸጠ ፤ ሃቅን እየገፋ ሁሉም ለወገኑ ፤
የአምልኮ ጸበኞች፤
ትሰሙኝ እንደሆን፤
ዛውያውን ተውት ፤
ደብሩን ልቀቁና ፤
ሰው በጎደለበት ሰው የሚል ሰው ሁኑ፤
አለበለዚያማ፤
ሰውን ለማፋረስ፤
ሃገር ለመነጀስ ፤ ጠማማና ክፉ መች አነሰው ቀኑ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
"ናካይታ"💚
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤
#3ቀን🎂🎂
@getem
@getem
@Nagayta