ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!

..ዛሬ ደርባባዋ ቅዳሚት ነች....ለክብሯ ሲባል አንድ ሸላይ የሆነ ግጥም ነው ነው የምንገባበዘው....ስለ ግጥሙ ሀሳብ እና ስለ ግጥሙ የቃላት ውበት ላወራ ነበር ግን....እናንተው አንብባችሁት ተደመሙበት #ቅዳሚታቹን ግጥሙን ደጋግሞ በማንበብ እና ለወዳጆቻቹ በመጋበዝ ተገማሸሩበት....#ለኔም በአሪፍ ድምፅ ተነቦ ቢላክልኝ አልጠላም.. መቼም ምን አይነት ግጥም ቢሆነው እንዲህ በጠዋቱ ተነስቶ ሚሸልልብን ማለታቹ አይቀርም....እንግድያው ፍረዱኝ...ይኸው እንካቹ...



"ስራህ ?"ስባል
እንዲህ እመልሳለሁ
ሀዘንን ማባበል
ለሚያለቅሱ ነፍሶች በገና ማቀበል
" ስራ ?" ህ ስባል
ከደስታ መቃጠር
ለሰዓሊ ሸራ ዘርግቶ መወጠር
" ስራህ ? " ስባል
መቃ መጠራረብ
ላንድ ገጣሚ ነፍስ መድ ከፊት ማቅረብ
ከየት ስባል
ምን እመልሳለሁ
እንዴት ስባል ብቻ መናገረ አውቃለሁ
ብኩን ሰው ነበርኩኝ - ተሰበርኩ እንደ ገል
የማለውቀውን ነፍስ ጀመርኩኝ ማገልገል
ነፍሴንም
ገደልኳት
ሰውቼ አቀርብኳት
የቀላይ መታሪ - ታንኳ ሁኚ አልኳት
ያኔም ነው እንደ አረሆ- እንደኮከብ ጧሪ
ከፍ ብሎ ቋሚ - ናፍቆት አጋፋሪ
ብቻዬን የሆንኩት
እንደ እልፍኝ አስከልካይ ዘብ ሆኜ የቆምኩት
ጮራ የበተንኩት
ነፍስ ያገለገልኩት
አየህ አይገለፅም ማደሪያው
የወዲያ ወዲያው
ቅፅር ካለፈረሱ
ሀዘን ካልሰፈሩ
ያን እግረ ሙቅ ገንቦ - ደፍረው ካልሰበሩ
አይነገር
በቃል አይጋገር
ለተራ ተርታ ሰው - አለው ማደናገር
ይሄው ነው
በገናውን በስልት
ቀሰሙንም በስልት
ዋሽንቱንም በስልት
ሳቀርብ እያየህኝ
እኔ ነኝ የምፅፍ
እኔ ነኝ የማዜም
በዋሽንት የማፏጭ - በተብሳ መቃ
ብልህ እንዳትለኝ - አንትንገረኝ በቃ
እኔው እያጋፍርኩ
መሪ - ጌታ እያለኝ የጥበብ አለቃ ::

📝ሰለሀዲን አሊ

ደመቅመቅ ያለ ቅዳሜ ጀባታ!

@getem
@getem
@Nagayta
👍2