ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አልገጥምም


ጦረኛ ተዋጊ
የጎሳ ነፃ አውጪ ፥ #በቀፈቀፈ አገር
ከብዕር በዘለል
ባፈሙዝ ቃታ ነው ፥ ብዙ የሚነገር
በኔ.....አገር
ሲወድ ፣ ሲጠላ
ለሀዘን ለደስታው ፥ ባሩድ እየማገ
ሲፎክር ፣ ሲሸልል ፥ በጥይት ላደገ
ካደባየው በላይ
ከመግደሉ በላይ ፥ አፈር ከከተተው
የጣለው ሲነሳ
ተኩሶ ሲስት ነው ፥ ፀፀት የሚያኝከው ።
ይህንን ስታውቂ...
አጠገቤ ቆሞ ፥ የቀኑ ጃዊሳ
አረ ጎራው ሲለኝ ......ሊሸልል ሲነሳ
ስለ #ሀገር ግጠም
ለምን ትይኛለሽ ? ሸጉበሽ ከክንዴ
ቃልሽን የሰማ...
እንጋጠም ቢለኝ
ማስታወሻ ደብተር ፥ ጋሻ ይሆናል እንዴ?

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh


@getem
@getem
@getem