ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ዝክረ ሙሉ ጌታ ተስፋዬ

ነገ የሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ ) የሞተበት 15 አመት ነው ቀኑን ሙሉ የአያ ሙሌን ስራዎች እያነሳን ስንዘክረው እንውላለን #በቻናላችን !!

የማታውቁትም እንድታውቁት እንድታከብሩት በጣም እፈልጋለሁኝ ንጉስም ቅዱስም ነኝ!! ይላል ሙሌ ሀቅ ነው !

በነገራችን ላይ ባለ ቅኔዉ
# እንደ ሰይድ ከድር እንደ ነቢ ሙሳ
እያደር ገነነ እንኳንስ ሊረሳ
ወየዉላችሁ ሰርቆ አደሮቹ በዚህ ሳምንትኳ በየ fm ጣቢያወቹ እና በ fb መንደር በጣም
እየገነነ የሰወች ልብ እያንኳኳ ቀጥሏል ይበል ብለናል ግን ሌቦቹ ለናንተ
ይብላኝላችሁ የት እንደምትገቡ እናያለን።

ለምሽታችን ግን አብኞቻችን የምንወደው #ታምራት ደስታ የተጫወተውን "ሀኪሜነሽ " ይግረማቹ የዚህ ሸጋ የሙዚቃ ግጥም ባለቤቱ አያ ሙሌ ነው !!



# ድምጻዊ_ታምራት_ደስታ (ሀኪሜነሽ)
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም

በናፍቆት ተይዤ ሲደክም ጉልበቴ
ደግሞ ይባስ ብሎ ታሰረ አንደበቴ
ስብር ያለ ለታ ስሜም እንደ ቅስሜ
እፅናናለሁ ሳይሽ እንኳንስ ተስሜ
እፅናናለሁ ሳይሽ እንኳንስ ተስሜ
ብክንክን ስል አደብ ሲያሳጣኝ
ትዝታሽ ደርሶ ከጭንቅ አዎጣኝ
አዬ መታደል አወይ መገፋት
ከሞት ያስጥላል እንኳን ከእንቅፋት
ብክንክን ስል አደብ ሲያሳጣኝ
ትዝታሽ ደርሶ ከጭንቅ አዎጣኝ
አዬ መታደል አወይ መገፋት
ከሞት ያስጥላል እንኳን ከእንቅፋት
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም

አንቺን የመሰለ ሌላ ሰው ቢኖርም
ለአይን ይሞላል እንጂ የነፍስ አይዘምርም
ጠረንሽን ለምጄ እንደ ናርዶስ ሽቶ
ለሊቱ እንዴት ይንጋ ቀኑስ እንዴት መሽቶ
ለሊቱ እንዴት ይንጋ ቀኑስ እንዴት መሽቶ
ደበስበስ አርጊኝ በአለንጋ ጣትሽ
አንቺ ስትወጂ ሞት ነው ቅጣትሽ
ብታውቂበት ነው ገሎ ማሻሉን
እያስተማሩ ማሰማመሩን
ደበስበስ አርጊኝ በአለንጋ ጣትሽ
አንቺ ስትወጂ ሞት ነው ቅጣትሽ
ብታውቂበት ነው ገሎ ማሻሉን
እያስተማሩ ማሰማመሩን

ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም

ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም


ሰላም እደሩልኝ !!
---------------------------------------------------

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
#ዝክረ ሙሉ ጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ )

#ድምፃዊ አበበ ተካ የተጫወተው ሙሉጌታ ተስፋዬ“መቃብሬ ውስጥ ሆኜም እሰማታለው ” የሚላት
የታላቁ ባለቅኔ አያ ሙሌ 3ኛ ልጁ ወፊቱ
15ኛ ዓመቱ ሲዘከር


ወፊቱ❤️❤️❤️

ጭራ ጭራ የምታድረው
ጭራ ለቅማ የምታድረው
ጭራ ጭራ የምታድረው
ጭራ ለቅማ የምታድረው
እንዲህ አስናቀችኝ...
ቀድማኝ ጎጆ ወጥታ ጎጆ አስተማረችኝ
ጎጆ ...አቤት ጎጆን... ወፍዬ አስቀናችኝ፤
እህህ... ምነው ባደረገኝ
እህህ... የሷ ጋሻ ጃግሬ
እንደምንም ብዬ እኔም ጥሬ ግሬ
ያገዳ ጎጆዬን ባቆምኳት ማግሬ፤
እህህ... አጉል በቃኝ ላ'ይል
እህህ... አይን አይቶ ገምቶ
ወይ ሞልቶ ላይሞላ ጆሮ አይችሉ ሰምቶ
እንዴት ጎጆ ይቅር አርሶና ሸምቶ
ገመና ከታቹ የሣር ቤት ያማረሽ
ሚስጥረ መለኮት ማነው ያስተማረሽ
ካፈር ክዳን ጎጆ መሬቱን ፈልፍሎ
ከሰማይ ቤት እጣሽ ማን በሰጠኝ ከፍሎ
እኔን እኔን እኔን ይብላኝ
እኔን አይኔን እኔን ይብላኝ...
እኔን እኔን እኔን ይብላኝ
እኔን አይኔን እኔን ይብላኝ...
የቀን ሰው ሌጣ አፈር
ልቤ ሩቅ አሳቢው ቅርብ አድሮ ሲደፈር
ምን ነበር ቢቆጨው ጎጆ አጥቶ ከማፈር፤
እህህ... ፈጣሪዋን አምና
ያፏን ጥሬ ሰጥታ
ለጭሮ አዳር ውሎ በዝማሬ ወጥታ
አዳኝ እንዴት ያጥቃት ፍርድና ዳኛ አጥታ
እህህ... አጣሁ፣ ነጣሁ ብላ
እንደሰው ባይከፋት
ምፅዋት ባትለምን ተርፎን ባንደግፋት
ጎጆዋ ለቻላት ምን ነበር ባንገፋት
ታማ ትንፋሽ አጥሯት ደክማ ስታጣጥር
ማን ያቃናት ይሆን፥ ውለታ ሳይቆጥር
ማን ያቃናት ይሆን፥ ውለታ ሳይቆጥር
ወልዶ ማሳደጉን ብዙ ሰው ቢያውቅበት
ያፉን ማን ይሰጣል የእጁ ሲርቅበት
ያፉን ማን ይሰጣል የእጁ ሲርቅበት
እህህ... ወፊቱ፤
ኡሁሁ... ወፍዬ!
እህህ... ወፊቱ፤
ኡሁሁ... ወፍዬ

@getem
@balmbaras
👍2
#ዝክረ ሙሉ ጌታ ተስፋዬ❤️❤️...!!!

የወፍዬ ግጥም ደራሲ ነው ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ...ወፍዬን ከሁለት ልጆቹ ቀጥላ 3ተኛ ልጄ ናት ይላል አያ ሙሌ። ማንም አማርኛ ተናጋሪ ፍጡር በህይወት ዘመኑ ወፍዬን ቢያንስ አንድ ግዜ ሊሰማ ግድ አለበት ይል ነበር አያ ሙሌ። አያ ሙሌ በተለይም የባለቅኔ ምህላ በሚል ስራው በጣም ይታወቃል። ወፍዬ ከሙዚቃም በላይ ነው...ይህ ግጥም በህይወት ተክለሰውነት ላይ ያለን የፍትህ መጓደል በስንኞቹ መነፅር ያሳያል...ስለህይወት ውጣውረድና እንግልት ይተርካል.....ተመስገን ብሎ ስለማደር ሰማያዊ ህይወትን ስለመሻት ያትታል...ስለ ሰው ከንቱነት ይፈላሰፋል....አንዲትን ከመንጋው የተገፋች ሴት እውነት....ፍትህ ስላጣች ሴት ያወጋል በሰውኛና ተምሳሌታዊ ዘይቤም ተቀንብቧል ይህን ሁሉ በውስጡ ያዘለው ይህ ያያ ሙሌ ግጥም ዜማ ታክሎበት በአበበ ተካ ሲንጎራጎር ደግሞ በስንጥቅ ገላችን ላይ ሰርጎ የመቅረት የሆነ አንዳች የህይወትን ስንክሳር በመንገር ጥምን የማርካት ባህሪ አለው እስቲ እናንተስ ምን ትላላችሁ? ይችትላችሁ ሙሉ የሙዚቃዋ ስንኝ።

(ወፍዬ)
ከአበበ ተካ ዘፈን
......
ጭራ ጭራ የምታድረው (2)
ጭራ ለቅማ የምታድረው (2)
እንዴት አስናቀችኝ
ቀድማኝ ጎጆ ወጥታ ጎጆ አስተማረችኝ
ጎጇቤት ጎጆ እኔን ወፍዬ አስቀናችኝ
……..
ምነው ባደረገኝ
የሷ ጋሻ ጃግሬ
እንደምንም ብዬ እኔም ጥሬ ግሬ
ያገዳ ጎጆዬን ባቆምኳት ማግሬ
አጉል በቃኝ ላይል
አይን አይቶ ገምቶ
ወይ ሞልቶ ላይሞላ
ጆሮ አይችሉ ሰምቶ
እንዴት ጎጆ ይቅር
አርሶና ሸምቶ
……..
ገመና ከታቹን የሳር ቤት ያማረሽ
ሚስጥረ መለኮት ማነው ያስተማረሽ (2)
ካፈር ክዳን ጎጆ መሬቱን ፈልፍሎ
ከሰማይ ቤት እጣሽ ማን በሰጠኝ ከፍሎ (2)
………..
እኔን እኔን እኔን ይብላኝ (2)
እኔን አይኔን እኔን ይብላኝ (2)
የቀን ሰው ሌት አፈር
ልቤ እሩቅ አሳቢው
ቅርብ አድሮ ሲደፈር
ምን ነበር ቢቆጨው ጎጆ አጥቶ ከማፈር
………
ፈጣሪዋን አምና ያፏን ጥሬ ሰጥታ
ለጭሮ አዳር ውሎ በዝማሬ ወጥታ
አዳኝ እንዴት ያጥቃት ፍርድና ዳኛ አጥታ
አጣው ነጣው ብላ እንደሰው ባይከፋት
ምፅዋት ባትለምን ትርፉን ባንደግፋት
ጎጆዋ ለቻላት ምን ነበር ባንገፋት
………
ታማ ትንፋሽ አጥሯት ደክማ ስታጣጥር
ማን ያቃናት ይሆን ውለታ ሳይቆጥር (2)
ወልዶ ማሳደጉን ብዙ ሰው ቢያውቅበት
ያፉን ማን ይሰጣል የጁ ሲርቅበት (2)
እህህ ወፊቱ እሁሁ ወፊቱ እህህ ወፍዬ እህህ ወፊቱ እህህ ወፍቱ (8)

#ምንጭ:-ስንታየሁ እንደከተበው

እሱ ወፊቱን❤️የአያ ሙሌን ስራ አስታውሶ ሲዘክርልን ሲከትብልን ነፍሳችን ደስ ደስ አላትና...በሚጎመዝዘው ድምፃችን ተጫወትናት👇👇👇

@balmbaras
#ዝክረ ሙሉ ጌታ ተስፋዬ

ለሰዓት እላፊ !
❤️❤️❤️

በመጨረሻም ሁለት ግጥም በድምፅም በፅሁፍም ጀባ ብለን እንሰናበት🙏


ሙሌ አባ መንገዴ


አስያ አስያ፣
ንኡድ ቃል አምሳያ፣
እንኪ ስላንትያ፣
እሸትሽ ቅኔ ነዉ፣ ገላሽ ቦለቅያ፣
አቦ በየጁ ሞት፣ አቦ በወልዲያ፣
አቀብይኝ ዛሬ፣
ቅኔ እምኩልበት ፤ ቅኔ መሞሸሪያ፤
ትመጫለሽ አሉ፣
በ “ሙልየ..” ሲሉሽ ፣
የጁ ኪቢ ቃሉ፤ ማክሰኞ ገበያ፡፡
አስያ ጨብራሪት፣
የሃራ ወበሎ ፤ የታች ቆላይቱ፣
ጨብረር ጨብረር በይ፣
ተንጎማለይበት ፤ ነይማ ሸጊቱ፣
ወፈፍ ወፈፍ በይ፣
በጎጆየ ታዛ፣ አልፈሽ በምርጊቱ፡፡
ሀድራዉ ከሞቀበት፣
ቱፍታው ከሞላበት ፤ ከእነ ኩሌ ማጀት፣
ሀቂቃ አይደለም ወይ?
ካ'ስያ ጋር ኑሮ ፤ ካ'ስያ ጋር ማርጀት።
አውገረድ አስያ ፤
በበልጅግሽ ባሩድ፣ ባልቤንሽ ማንገቻ፣
እንደ ንጉስ አሽከር ፤
አሻቅቦ ያያል ፤ ቀልቤ አንችኑ ብቻ፤
ምን ያድርግ ብለሽ ነው፤
ወትሮም ከላይ ቤት ነዉ፣ ቅኔና ኮርቻ፡፡
ተገማሸሪበት ፤
ቀብረር ቀብረር በይ፣ አስያ በሞቴ፣
አህሪቡ ስትይኝ ፤
ጅስሜ ይበረታል ፤ ይጠናል ጉልበቴ ።
ከሙሉጌታ ጋር፣
ከሙሉ ሸጋ ጋር፣
ጉባርጃ ማርያም ላይ ፤ ያሰርሽዉ ቃል ኪዳን፣
እኔንም ዘንድሮ ፤
ጠራኝ ግጠም አለኝ፣ አወደኝ እንደእጣን፡፡
እኔም እንደ ሙሌ፣ እንደሙሉጌታ፣
ቀየዉ እንዳስከፋዉ፣ እንደቆላ ሽፍታ፣
ግጠም ግጠም አለኝ፣ የያዘኝ በሽታ፡፡
እገጥማለሁ እንጅ፣
በየበራበሩ ቅኔ ዛር አለብኝ፣
ላዩን በውድመን ፤
ታቹን በሶደማ ፤
አስያ ጨብራሪት፣ ወስዳ ሸሽጋብኝ፡፡
ልለማመን እስቲ፣
በእነነየ ጉፍታ ፤ በየጁ ቀለበት፣
ልመጀነዉ እስቲ፣
በአውገረድ ሹምባሽ ቤት ፤የላስቴን አቀበት፣
እንደግሽር ገላ፣ እንደወዳጅ እብለት፣
ምርኩዝ የሚሆነዉ፣ ለታፈረ ጉልበት፣
ጠብቆ ሲሰፋ ነው ፤ ቅኔና ዘለበት፡፡
ሀየ በል ገለሌ፣ እምቢ በል ጃዉሳ፣
ልቤ “..ቸ..” በል አለኝ “..ቸ..” በል ደንገላሳ፣
ብረር ብረር አለኝ፣ ቅኔ ቀለም አንሳ፣
ወትሮም ወደ ላይ ነዉ፣ ቅኔና ግሪሳ፣
ግጠም ግጠም አለኝ ፣ በልጅግህን አንሳ፣
አውቃለሁ አምናለሁ፤
የሞት ባልንጀር ነዉ፣ ቅኔና ወሳንሳ፡፡
አስያ ከገባች፣ ከማጀቷ ወጥታ፣
ጎዝጉዙልኝ ካለች፣ ወዳጃ ተጠርታ፣
ጀማዉ ከደመቀ፣ ቅጥሩ ከተፈታ፣
ግጠም ግጠም አለኝ፣ እንደሙሉጌታ፡፡
አያ ሙሌ ሆዴ፣
ቅኔ እሳት አመዴ፣
ከርታታዉ ዘመዴ፣
እኔ አለሁህ ልበል? አንተ አለሀኝ እንዴ?
ሰገነት ባትወጣ፣ ግብርህ ባይታወቅ፣
በሺህ ጋዜጠኛ፣ ስምህ ባይዳመቅ፣
በቲፎዞ ባሩድ፣ ባይሞቅ ያንተ ሽታ፣
በጭብጨባ ባይድን፣ ያንተ ሆድ በሽታ፣
ቃል አልተሸነፈም፣ ቅኔህ አልተረታ፣
“ታላቁ ሰዉ መጣ”፣
“ባለቅኔዉ መጣ”፣
“ያ ደራሲዉ መጣ”፣
ብለዉ ባይሰግዱልህ፣
ብለዉ ባይጮሁልህ፣ ምን ግድህ ምን ግዴ፣
አትንሰፈሰፍም ፣ለሹመት ለጓንዴ
ስሙልኝ አያምርህ፣ እንደቆላ ገዴ፣
አቦ ሆድ ይመርቅ፣ ሙሌ አባ መንገዴ፡፡

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

(( ማስታወሻነቱ ለባለቅኔው
ሙሉጌታ ተስፋዬ ❤️❤️❤️) )



@balmbaras
@getem
@getem
👍1
#ዝክረ ሙሉጌታ ተስፋዬ ( አያ ሙሌ )❤️


ሙሉ-- ጌታ!!!!!!!


ቅኔን ያህል ክህነት፤
አረሆን ያህል ሹመት፤
ካማልክቶቹ ዘንድ፤ ተሰጥቶት በደቦ፤
የብእሩ ልሳን፤
ሰው በሚባል ቅኔ፤
ሰው በሚባል ታምር፤ ዙሪያውን ተከቦ፤
በሰው ሳቅ ረብቶ፤ በሰው እንባ ባክኖ፤
ያም ለኔ ያም ለኔ፤
ለኔ ሁን እያለ፤
ግብር ቢደረደር፤ በጎጥ ልቡ ባዝኖ፤
እሱማ አጃኢብ ነው፤
ሰም ቅኔውን ፈታው፤ ለሁሉም ዘብ ሆኖ።


ዘብ እንጅ ዘብ አደር፤
ቋሚ እንጅ፤ ወጥቶ አደር፤
ያዳም ጎጆ ሲፈርስ፤
ሰብቅታኒ ብሎ፤ በእምባው የሚገደር፤
ዘማች የቀናው ቀን፤
ዳቦውን አግምጦ፤
ስለ ስሟ ማርያም፤
ቀን የሚሸኝበት፤ ቆሎ የሚበደር።


ሰውን ያህል ሰማይ፤ ሰብን ያህል ፀጋ፤
ኑሮን ያህል እንቅልፍ፤ ሞትን ያህል አልጋ፤
ተሸክሞ ሚዞር፤ በነጋ በጠባ፤
በጥውልግ ነፍስያ፤ በንጣት ሲላጋ፤
መዳኒት በራቀው፤ በማይቆም ፍለጋ፤
ህመሙ ሚሽረው፤
ወይ በቅንጣት ቅኔ፤ ወይ በድፍርስ እንባ።


ሰማያት ተቀደው፤ እንባ ካላዋሱ፤
አእዋፍ በማለዳ፤
አፍ መሻሪያ ቅኔ፤
እጅ መንሻ አምሃ፤ ዜማ ካልደረሱ፤
ይኸ ባለቅኔ፤
ቅኔ ማር ካልነካው፤ ካልደረሰ ምሱ፤
ዝናብ ቢጥል እንኳ፤
መልካው አይወረዛ፤ ወንዞችም አይፈሱ።


ምን ጎተራ ቢጎድል፤ አውድማው ቢሳሳ፤
ምን መሬት ብትከዳ፤ ሰማይ ጠል ቢነሳ፤
አፍ ሳይሽር ማለዳ፤
ከማእዱ በፊት፤
የህጣናት እምባ፤ ሲቃ እየቀደመ፤
አባት በልጁ ፊት፤
አባትነት ጎድሎት፤ከፈን እያለመ፤
ይህን ባዬ ጊዜ፤
ምስኪን ባለቅኔ፤
ጎደለ ወይ ብሎ ፤
ፈረሰ ወይ ብሎ፤ ልቡ ይጨነቃል፤
ስማኝ ኧረ ስማኝ፤
እያለ አዶናይን፤ ሰርክ ይጨቀጭቃል፤
ከጭቅጨቃው ወርዶ፤
ከመንበረህ የለህ፤
የለህም እያለ፤
ዘመን ሚያሻግር፤ ውብ ቅኔ ያፈልቃል።


ስለ ፍቅር መፃፍ፤
ስለ እንባ መቀኘት፤
ስለ ርሃብ መደስኮር፤ ምን ያቅታል ወጉ፤
ምን ያቅታል ደግሞ፤
ስለ እርሻው መንደቅደቅ፤
ስለ በሬው ማውራት፤ ከተማ መሃል ላይ እያረገረጉ።
ውነቴን ውነቴን፤
ሽርፍራፊ ቃላት፤
ማዳወር አይከብድም፤
የቃል ጮማ መቁረጥ፤ በየጥጋጥጉ፤
አዳ ምን ዋጋ አለው፤
ስለ ውጋት መፃፍ፤
ውጋት አያክምም፤ አብረው ካልተወጉ።


ግን ፤
ደግሞ ግን፤
ፍቅር መሆን እንጅ፤
እንባ መሆን እንጅ፤
ሩህሩህ እንስፍስፍ፤በብእርም በእውንም፤
በብእር ደግ ሆኖ፤
በሩን የሚዘጋ፤
እሱም አይፈልገን፤ እኛም አንከጅልም።


ብእር ቀለም ቢያጥረው፤ በላቡ እየፃፈ፤
ላቡ ሲደርቅበት፤ ደም እየቀፈፈ፤
ህላዌና ተስፋ፤
ቅኔና ሰውነት፤ እየተጠራሩ፤
ከደም የተቀዳ፤
ከመቅኖ ያደረ፤ ህያው ቅኔ ሰሩ፤
በቃ፤
ይኸው ነው ማጀቱ፤ ይኸው ነው ትዳሩ።


ርስቱን፤
ጠፍ ድስቱን፤
ልጅ ሚስቱን፤
በፊደል ተክቶ፤
ያባትነት እጁን፤
በቅኔ እያሰላ፤ ምስኪን ልቡን ሰጥቶ፤
የዘረ ሰብ ቀልቡን፤ ዳር ከዳር ዘርግቶ፤
በነፍስያ ሀቂቅ፤
የቀልብያን ስስት፤ በቸር ቅኔ ዘግቶ፤
በክፋት ምንዳ ላይ፤
የተንኮልን ጫካ፤ በሳቅ ጦር ረቶ፤
ከጉድለት ባርነት፤
በምህላ በአርምሞ፤ ራሱን አንፅቶ፤
ሙሉ-ጌታ ሆነ፤
በእንባና በቅኔ፤ ጎዶሎውን ሞልቶ።


(((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

(((ለባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ))

@balmbaras
@getem
@getem

አያ ሙሌ በሀይል ነፍፍፍፍፍ ብዙዙዙዙ እልፍ አእላፍ ወድሀለው❤️❤️❤️ ነፍስህን በገነት ያኑራት ! !!!!!!
#ዝክረ_ቫለንቲኖ

በሮማኖች...አገር
ይሄውልሽ #ውዴ...በፊት ድሮ ድሮ
ሴት ሴቱን ሲከተል ፥ በዘቡ ተማሮ
ንጉስ... #ክላውዲዎስ
ለክተት ዘመቻ....
#ልጄን #ሚስቴን...በሚል ስስት እያነቀው
እንዴት ነው ጦረኛ ፥ ላገር የሚወድቀው ?
ብሎ ስለራደ...
ተባእቱን ሁላ.... ከተራክቦ አገደ
አሻፈረኝ ያለ .. #ሰማዕቱ_ቄስም
በንጉሱ ፈቃድ ስለተናደደ
#እስከተቀላበት...ህይወቱ እስካለፈ
በሚስጥር ፥ ስንቱን ጥንድ ፥ አጋብቶት አረፈ
እናም ዛሬ ዛሬ.......ባገርሽ ፣ ባገሬ
ቀይ....ቀዩ #ነገር ......እየተማገደ
ቫለንቲኖን ማሰብ ....ስለተለመደ
ምን ከኔ ባትኖሪ...
የት እንደሆንሽ እንኳን ፥ ባይጠረጠርም
ግራ ጎኔን #ለራት...ለደስታው ባልቀጥርም
እስክትመጪ ድረስ
#በቀይ ደምቄ........ቤቴን አሸብርቄ
አንቺ መናፈቄ
አስቤሽ መዝለቄ
በ ከማን አንሼ...እንዲያው ለነገሩ
ከማላውቀው አገር ፥ የነበሩት አባት ፥ እንዲህ ሲዘከሩ
ለማላውቅሽ አንቺ
#happy_valentine ...
የተባለ ምኞት ፥ ምኑ ላይ ነው #ነውሩ?

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

" #Happy_valentine_my_Love "
( #ባለሽበት_ቦታ)

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
1👍1