ግጥም ብቻ 📘
Photo
#የብር_አለም_ብሶት
፡
ማለዳ በነቁ
የንስር አይኖችሽ እኛ እያንቀላፋን
በከሰአት ጀንበር
በጠራራ ጠሀይ መሄጃው ቢጠፋን
ከገንዘብሽ ገፆች
መልካችን ታትሞ ገንዘቡን አተናል
ኑሮ በኛ ሲስቅ
በኑሮ እየሳቅን ግራ ተጋብተናል፡፡
፡
እንሳቅ እንጂ ቅሉ
በደሀ ፍቶአችን ያ'ፍታም ኪስ ከሞላን
መቼም አንከፋም
ለሌላው ደስታ ነን
እጣ ፈንታ ሆኖ እኛን ቀን ባይደላን፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@gebriel_19
፡
ማለዳ በነቁ
የንስር አይኖችሽ እኛ እያንቀላፋን
በከሰአት ጀንበር
በጠራራ ጠሀይ መሄጃው ቢጠፋን
ከገንዘብሽ ገፆች
መልካችን ታትሞ ገንዘቡን አተናል
ኑሮ በኛ ሲስቅ
በኑሮ እየሳቅን ግራ ተጋብተናል፡፡
፡
እንሳቅ እንጂ ቅሉ
በደሀ ፍቶአችን ያ'ፍታም ኪስ ከሞላን
መቼም አንከፋም
ለሌላው ደስታ ነን
እጣ ፈንታ ሆኖ እኛን ቀን ባይደላን፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@gebriel_19
#ነገ
**** የማይቀርበት የስነጥበብ ምሽት *****
የገጣሚና ደራሲ ኤፍሬም ሥዩም ጥበብ አዲስ( ART COCKTAIL) በሚል ስያሜ
የተለያዩ የጥበብ ግብአቶችን ስነ ግጥም ከፊልምና ሙዚቃ ጋር ፣ ስነ ስእል ( የእንቁጣጣሽ
ትውስታና ስጦታ)፣ ሙዚቃ በሃቲቱ ( solo music) ፣ ተውኔት፣ የአልባሳት ጥበብ፣ ነጻ ግዜ
ለታዳሚዎች(free mike)፣ የዲፕሎማቶች ግዜ እንደዚህም ሌሎቹም በአንድ መድረክ
ላይ በማጣመር እና በማዋሃድ ሰኞ ነሃሴ 27-2011 ፒያሳ በሚገኘው ግራንድ ኤልያና
ሆቴል ትልቁ አዳራሽ አመሻሽ 11፡30 የወርሃዊ መርሃ ግብሩን ደግሶ እንድንታደም
ጋብዞናል….. እነሆ አነጋፋና ወጣት የጥበብ ሰዎች ስራቸውን ይዘው ለመቅረብ
ተዘጋጅተዋል፡፡
የመግቢያ ዋጋ 100 ብር ብቻ፡፡
@getem
@balmbaras
**** የማይቀርበት የስነጥበብ ምሽት *****
የገጣሚና ደራሲ ኤፍሬም ሥዩም ጥበብ አዲስ( ART COCKTAIL) በሚል ስያሜ
የተለያዩ የጥበብ ግብአቶችን ስነ ግጥም ከፊልምና ሙዚቃ ጋር ፣ ስነ ስእል ( የእንቁጣጣሽ
ትውስታና ስጦታ)፣ ሙዚቃ በሃቲቱ ( solo music) ፣ ተውኔት፣ የአልባሳት ጥበብ፣ ነጻ ግዜ
ለታዳሚዎች(free mike)፣ የዲፕሎማቶች ግዜ እንደዚህም ሌሎቹም በአንድ መድረክ
ላይ በማጣመር እና በማዋሃድ ሰኞ ነሃሴ 27-2011 ፒያሳ በሚገኘው ግራንድ ኤልያና
ሆቴል ትልቁ አዳራሽ አመሻሽ 11፡30 የወርሃዊ መርሃ ግብሩን ደግሶ እንድንታደም
ጋብዞናል….. እነሆ አነጋፋና ወጣት የጥበብ ሰዎች ስራቸውን ይዘው ለመቅረብ
ተዘጋጅተዋል፡፡
የመግቢያ ዋጋ 100 ብር ብቻ፡፡
@getem
@balmbaras
ለ "አባ" ለአባማ "አባ ጨጓሬ"ም አባ ነው
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ሳያዩ የሚያምኑን ፣ አይተህ ተጠራጠር
ተአምር አየሁ አትበል
ጋንን ያህል ነገር ፣ ሲደገፍ በጠጠር
ይልቅ ተአምር ስራ
ከሚታይ መልስ ላይ ፣ጥያቄ በመፍጠር።
ሁሉንም አትመን ፣ ግን ሁሉን ተጠንቀቅ
ቤትህ በሰማይ ነው
ብሎ ለሰበከህ ፣ ምድርህን አትልቀቅ።
።።።
ከስጋ ፍላጎት
አርቀህ ስቀለው ፣ የነፍስያህን ልክ
የቄስ ቃል ስታምን ፣ ቄሱን ግን አታምልክ
ሁሉ ካህን አይደል
አስሮ የሚፈታ ፣ እየፈታ ሚያስር
ስንቶች በካህን ለምድ
እባብ ደብቀዋል፣ ከጥምጣማቸው ስር።
@getem
@getem
@gebriel_19
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ሳያዩ የሚያምኑን ፣ አይተህ ተጠራጠር
ተአምር አየሁ አትበል
ጋንን ያህል ነገር ፣ ሲደገፍ በጠጠር
ይልቅ ተአምር ስራ
ከሚታይ መልስ ላይ ፣ጥያቄ በመፍጠር።
ሁሉንም አትመን ፣ ግን ሁሉን ተጠንቀቅ
ቤትህ በሰማይ ነው
ብሎ ለሰበከህ ፣ ምድርህን አትልቀቅ።
።።።
ከስጋ ፍላጎት
አርቀህ ስቀለው ፣ የነፍስያህን ልክ
የቄስ ቃል ስታምን ፣ ቄሱን ግን አታምልክ
ሁሉ ካህን አይደል
አስሮ የሚፈታ ፣ እየፈታ ሚያስር
ስንቶች በካህን ለምድ
እባብ ደብቀዋል፣ ከጥምጣማቸው ስር።
@getem
@getem
@gebriel_19
"አማርኛ ቋንቋ እዚች አለም ላይ እስካለ ድረስ አማርኛ ቋንቋ የሚችል በህይወት ዘመኑ
ደግሞ ባይሰማት ወፍዬን አንድ ቀን ይሰማት ዘንድ ግድ አለበት።"
ገጣሚና ባለቅኔ ሙልጌታ ተስፋዬ
❤️:)
ጭራ ጭራ የምታድረው
ጭራ ለቅማ የምታድረው
ድምቢጥ አስናቀችኝ
ቀድማኝ ጎጆ ወጥታ ጎጆ አስተማረችኝ
ጎጆዋ ቤት ጎጆ እኔም ወፍዬ አስቀናችኝ
ምነው ባደረገኝ የሷ ጋሻ ጃግሬ
እንደ ምንም ብዬ እኔም ጥሬ ግሬ
ያገዳ ጎጆዬን ባቆምኩዋት ማግሬ
አጉል በቃኝ ላይል አይን አይቶ ገምቶ
ወይ ሞልቶ ላይሰላ ጆሮ አይችሉ ሰምቶ
እንዴት ጎጆ ይቅር አርሶና ሸምቶ
ገመና ከታቹ የሣር ቤት ያማረሽ
ምስጢረ መለኮት ማነው ያስተማረሽ '
ካፈር ክዳን ጎጆ መሬቱን ፈልፍሎ
ከሠማይ ቤት እጣሽ ማን በሠጠኝ ከፍሎ
እኔን እኔን እኔን ይብላኝ
እኔን አይ እኔን እኔን ይብላኝ
የቀን ሰው ሌት አፈር
ልቤ ሩቅ አሳቢው ቅርብ አድሮ ሲደፈር
ምን ነበር ቢቆጨው ጎጆ አቶ ከማፈር
ፈጣሪዋን አምና ያፏን ጥሬ ሰጥታ
ለጭሮ አዳር ውሎ በዝማሬ ወጥታ
አዳኝ እንዴት ያጥቃት ፍርድና ዳኛ አጥታ
አጣሁ ነጣሁ ብላ እንደ ሰው ባይከፋት
ምጽዋት ባትለምን ተርፎን ባንደግፋት
[ ጎጆዋ ለቻላት] ምን ነበር ባንገፋት
ታማ ትንፋሽ አጥሯት ደክማ ስታጣጥር
ማን ያቃናት ይሆን ውለታ ሳይቆጥር
ወልዶ ማሳደጉን ብዙ ሰው ቢያውቅበት
ያፉን ማን ይሠጣል የጁ ሲርቅበት...
ሰላም ዋሉ!💚
@getem
@getem
@balmbaras
ደግሞ ባይሰማት ወፍዬን አንድ ቀን ይሰማት ዘንድ ግድ አለበት።"
ገጣሚና ባለቅኔ ሙልጌታ ተስፋዬ
❤️:)
ጭራ ጭራ የምታድረው
ጭራ ለቅማ የምታድረው
ድምቢጥ አስናቀችኝ
ቀድማኝ ጎጆ ወጥታ ጎጆ አስተማረችኝ
ጎጆዋ ቤት ጎጆ እኔም ወፍዬ አስቀናችኝ
ምነው ባደረገኝ የሷ ጋሻ ጃግሬ
እንደ ምንም ብዬ እኔም ጥሬ ግሬ
ያገዳ ጎጆዬን ባቆምኩዋት ማግሬ
አጉል በቃኝ ላይል አይን አይቶ ገምቶ
ወይ ሞልቶ ላይሰላ ጆሮ አይችሉ ሰምቶ
እንዴት ጎጆ ይቅር አርሶና ሸምቶ
ገመና ከታቹ የሣር ቤት ያማረሽ
ምስጢረ መለኮት ማነው ያስተማረሽ '
ካፈር ክዳን ጎጆ መሬቱን ፈልፍሎ
ከሠማይ ቤት እጣሽ ማን በሠጠኝ ከፍሎ
እኔን እኔን እኔን ይብላኝ
እኔን አይ እኔን እኔን ይብላኝ
የቀን ሰው ሌት አፈር
ልቤ ሩቅ አሳቢው ቅርብ አድሮ ሲደፈር
ምን ነበር ቢቆጨው ጎጆ አቶ ከማፈር
ፈጣሪዋን አምና ያፏን ጥሬ ሰጥታ
ለጭሮ አዳር ውሎ በዝማሬ ወጥታ
አዳኝ እንዴት ያጥቃት ፍርድና ዳኛ አጥታ
አጣሁ ነጣሁ ብላ እንደ ሰው ባይከፋት
ምጽዋት ባትለምን ተርፎን ባንደግፋት
[ ጎጆዋ ለቻላት] ምን ነበር ባንገፋት
ታማ ትንፋሽ አጥሯት ደክማ ስታጣጥር
ማን ያቃናት ይሆን ውለታ ሳይቆጥር
ወልዶ ማሳደጉን ብዙ ሰው ቢያውቅበት
ያፉን ማን ይሠጣል የጁ ሲርቅበት...
ሰላም ዋሉ!💚
@getem
@getem
@balmbaras
አንድ ላይ ነን ብሎ፤
አዋጅ እያስወራ ለባዳው ለዘመድ፤
ይኸ ያገሬ ሰው፤
ለመደበት አሉ፤
ሁሉም በየራሱ በየፊናው ዙሮ በየልቡ መንጎድ፤
ይዘለቅ ይሆን ወይ ፤
የእንሂድ ጅማሮ፤ ያንጓዝም መንገድ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
አዋጅ እያስወራ ለባዳው ለዘመድ፤
ይኸ ያገሬ ሰው፤
ለመደበት አሉ፤
ሁሉም በየራሱ በየፊናው ዙሮ በየልቡ መንጎድ፤
ይዘለቅ ይሆን ወይ ፤
የእንሂድ ጅማሮ፤ ያንጓዝም መንገድ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
#ዝክረ ሙሉ ጌታ ተስፋዬ
ነገ የሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ ) የሞተበት 15 አመት ነው ቀኑን ሙሉ የአያ ሙሌን ስራዎች እያነሳን ስንዘክረው እንውላለን #በቻናላችን !!
የማታውቁትም እንድታውቁት እንድታከብሩት በጣም እፈልጋለሁኝ ንጉስም ቅዱስም ነኝ!!❤ ይላል ሙሌ ሀቅ ነው !❤❤
በነገራችን ላይ ባለ ቅኔዉ
# እንደ ሰይድ ከድር እንደ ነቢ ሙሳ
እያደር ገነነ እንኳንስ ሊረሳ
ወየዉላችሁ ሰርቆ አደሮቹ በዚህ ሳምንትኳ በየ fm ጣቢያወቹ እና በ fb መንደር በጣም
እየገነነ የሰወች ልብ እያንኳኳ ቀጥሏል ይበል ብለናል ግን ሌቦቹ ለናንተ
ይብላኝላችሁ የት እንደምትገቡ እናያለን።
ለምሽታችን ግን አብኞቻችን የምንወደው #ታምራት ደስታ የተጫወተውን "ሀኪሜነሽ " ይግረማቹ የዚህ ሸጋ የሙዚቃ ግጥም ባለቤቱ አያ ሙሌ ነው !!❤❤
# ድምጻዊ_ታምራት_ደስታ (ሀኪሜነሽ)
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
•
በናፍቆት ተይዤ ሲደክም ጉልበቴ
ደግሞ ይባስ ብሎ ታሰረ አንደበቴ
ስብር ያለ ለታ ስሜም እንደ ቅስሜ
እፅናናለሁ ሳይሽ እንኳንስ ተስሜ
እፅናናለሁ ሳይሽ እንኳንስ ተስሜ
ብክንክን ስል አደብ ሲያሳጣኝ
ትዝታሽ ደርሶ ከጭንቅ አዎጣኝ
አዬ መታደል አወይ መገፋት
ከሞት ያስጥላል እንኳን ከእንቅፋት
ብክንክን ስል አደብ ሲያሳጣኝ
ትዝታሽ ደርሶ ከጭንቅ አዎጣኝ
አዬ መታደል አወይ መገፋት
ከሞት ያስጥላል እንኳን ከእንቅፋት
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
•
አንቺን የመሰለ ሌላ ሰው ቢኖርም
ለአይን ይሞላል እንጂ የነፍስ አይዘምርም
ጠረንሽን ለምጄ እንደ ናርዶስ ሽቶ
ለሊቱ እንዴት ይንጋ ቀኑስ እንዴት መሽቶ
ለሊቱ እንዴት ይንጋ ቀኑስ እንዴት መሽቶ
ደበስበስ አርጊኝ በአለንጋ ጣትሽ
አንቺ ስትወጂ ሞት ነው ቅጣትሽ
ብታውቂበት ነው ገሎ ማሻሉን
እያስተማሩ ማሰማመሩን
ደበስበስ አርጊኝ በአለንጋ ጣትሽ
አንቺ ስትወጂ ሞት ነው ቅጣትሽ
ብታውቂበት ነው ገሎ ማሻሉን
እያስተማሩ ማሰማመሩን
•
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
•
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሰላም እደሩልኝ !!
---------------------------------------------------
@getem
@getem
@balmbaras
ነገ የሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ ) የሞተበት 15 አመት ነው ቀኑን ሙሉ የአያ ሙሌን ስራዎች እያነሳን ስንዘክረው እንውላለን #በቻናላችን !!
የማታውቁትም እንድታውቁት እንድታከብሩት በጣም እፈልጋለሁኝ ንጉስም ቅዱስም ነኝ!!❤ ይላል ሙሌ ሀቅ ነው !❤❤
በነገራችን ላይ ባለ ቅኔዉ
# እንደ ሰይድ ከድር እንደ ነቢ ሙሳ
እያደር ገነነ እንኳንስ ሊረሳ
ወየዉላችሁ ሰርቆ አደሮቹ በዚህ ሳምንትኳ በየ fm ጣቢያወቹ እና በ fb መንደር በጣም
እየገነነ የሰወች ልብ እያንኳኳ ቀጥሏል ይበል ብለናል ግን ሌቦቹ ለናንተ
ይብላኝላችሁ የት እንደምትገቡ እናያለን።
ለምሽታችን ግን አብኞቻችን የምንወደው #ታምራት ደስታ የተጫወተውን "ሀኪሜነሽ " ይግረማቹ የዚህ ሸጋ የሙዚቃ ግጥም ባለቤቱ አያ ሙሌ ነው !!❤❤
# ድምጻዊ_ታምራት_ደስታ (ሀኪሜነሽ)
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
•
በናፍቆት ተይዤ ሲደክም ጉልበቴ
ደግሞ ይባስ ብሎ ታሰረ አንደበቴ
ስብር ያለ ለታ ስሜም እንደ ቅስሜ
እፅናናለሁ ሳይሽ እንኳንስ ተስሜ
እፅናናለሁ ሳይሽ እንኳንስ ተስሜ
ብክንክን ስል አደብ ሲያሳጣኝ
ትዝታሽ ደርሶ ከጭንቅ አዎጣኝ
አዬ መታደል አወይ መገፋት
ከሞት ያስጥላል እንኳን ከእንቅፋት
ብክንክን ስል አደብ ሲያሳጣኝ
ትዝታሽ ደርሶ ከጭንቅ አዎጣኝ
አዬ መታደል አወይ መገፋት
ከሞት ያስጥላል እንኳን ከእንቅፋት
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
•
አንቺን የመሰለ ሌላ ሰው ቢኖርም
ለአይን ይሞላል እንጂ የነፍስ አይዘምርም
ጠረንሽን ለምጄ እንደ ናርዶስ ሽቶ
ለሊቱ እንዴት ይንጋ ቀኑስ እንዴት መሽቶ
ለሊቱ እንዴት ይንጋ ቀኑስ እንዴት መሽቶ
ደበስበስ አርጊኝ በአለንጋ ጣትሽ
አንቺ ስትወጂ ሞት ነው ቅጣትሽ
ብታውቂበት ነው ገሎ ማሻሉን
እያስተማሩ ማሰማመሩን
ደበስበስ አርጊኝ በአለንጋ ጣትሽ
አንቺ ስትወጂ ሞት ነው ቅጣትሽ
ብታውቂበት ነው ገሎ ማሻሉን
እያስተማሩ ማሰማመሩን
•
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
•
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
ፈዋሼ ነሽ እምነቴ
ሀኪሜ ነሽ መድሀኒቴ
እኔ አዳም ብሞት አንቺንስ አልከዳም
ሰላም እደሩልኝ !!
---------------------------------------------------
@getem
@getem
@balmbaras
👍1
Forwarded from Hana Hailu
በደብረዘይት ከተማ ለመጀምሪያ ጊዜ የአስተሳሰብ ልህቀት ስልጠና ቅዳሜ ጷጉሜ 2
-ለመቶ ሰው ብቻ
ቦታ ለመያዝ እዚህ ሊንክ ላይ ይመዝገቡ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdD7_VKBb1KmrThigVttOigdbGSRk0gpt4vKkCpVYbwlqFTYw/viewform?
@hanahailu
-ለመቶ ሰው ብቻ
ቦታ ለመያዝ እዚህ ሊንክ ላይ ይመዝገቡ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdD7_VKBb1KmrThigVttOigdbGSRk0gpt4vKkCpVYbwlqFTYw/viewform?
@hanahailu
ትዝታና ተስፋ(ልዑል ሀይሌ)
ያኔ ባዲስ ዓመት
በጥበብ ሳገኝሽ
ቅኔዬንም ባጣ
የሰው ስዘርፍልሽ
በልቤ የቋጠርኩት
ጅምር ስንኝ ይዤ
ወዳንቺ ስመጣ
ይታወቀኝ ነበር
ባንቺ መድፊያ ፍቅር
ውብ ግጥም ሲወጣ
..
.
ያ ውብ ጅምር ግጥም...
.
የኔ ጅምር ስንኝ
ያንቺ ውብ መድፊያዎች
ዘላለም ሊያቆዩን
ቃላት ሲያማምሉን
እልፍ መሃላዎች
..
ታዲያ ምን ያደርጋል
.
.
አዲስ ያልነው ዓመት
እርጅና ተጭኖት
ያን ውብ ግጥማችንን
አንድ አፍራሽ ቃል ሰብሮት
ከጅምር ስንኜ ጥለሺኝ ስትሄጂ
ቤት ደፊስ አልጠፋም
አንቺ ቀረሽ እንጂ
..
.
ዛሬ
.
በጳጉሜ ላይ ሆኜ
የትናንት ና ነገ
መስከረም ሳያቸው
ትዝታና ተስፋ
እኩል መዝኛቸው
ካለፈ ትዝታ ተስፋ በልጦብኛል
ካምናው መስከረምሽ
የነገው ናፍቆኛል
..
.
በጊዜ ሂደት ውስጥ...
...
.
ያንድ ኑሮ ግጥም
ርዝመት አውቄያለሁ
ግጥሜን ልቀጥል
ጅምር ስንኝ ይዤ
መድፊያው ጋ ሄጃለሁ
4-13-2008
@getem
@getem
@gebriel_19
Share....@getem
ያኔ ባዲስ ዓመት
በጥበብ ሳገኝሽ
ቅኔዬንም ባጣ
የሰው ስዘርፍልሽ
በልቤ የቋጠርኩት
ጅምር ስንኝ ይዤ
ወዳንቺ ስመጣ
ይታወቀኝ ነበር
ባንቺ መድፊያ ፍቅር
ውብ ግጥም ሲወጣ
..
.
ያ ውብ ጅምር ግጥም...
.
የኔ ጅምር ስንኝ
ያንቺ ውብ መድፊያዎች
ዘላለም ሊያቆዩን
ቃላት ሲያማምሉን
እልፍ መሃላዎች
..
ታዲያ ምን ያደርጋል
.
.
አዲስ ያልነው ዓመት
እርጅና ተጭኖት
ያን ውብ ግጥማችንን
አንድ አፍራሽ ቃል ሰብሮት
ከጅምር ስንኜ ጥለሺኝ ስትሄጂ
ቤት ደፊስ አልጠፋም
አንቺ ቀረሽ እንጂ
..
.
ዛሬ
.
በጳጉሜ ላይ ሆኜ
የትናንት ና ነገ
መስከረም ሳያቸው
ትዝታና ተስፋ
እኩል መዝኛቸው
ካለፈ ትዝታ ተስፋ በልጦብኛል
ካምናው መስከረምሽ
የነገው ናፍቆኛል
..
.
በጊዜ ሂደት ውስጥ...
...
.
ያንድ ኑሮ ግጥም
ርዝመት አውቄያለሁ
ግጥሜን ልቀጥል
ጅምር ስንኝ ይዤ
መድፊያው ጋ ሄጃለሁ
4-13-2008
@getem
@getem
@gebriel_19
Share....@getem
❤1
//// የማይቀርበት ልዮ የኪነ -ጥበብ ምሽት ////
"አብሮነት" በሚል ሪዕስ በእለተ ማክሰኞ ነሐሴ 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔታል
ሆቴል ትልቁ አዳራሽ ታላቅ የጥበብ ድግስ ተሰናድቷል። በዕለቱ ግጥም፣ ወግ፣ መነባንብ፣
ዲስኩርና የኮሜዲ ሥራዎች ይቀርባሉ። በኘሮግራሙ ላይ ኘሮፊሰር በየነ ጴጥሮስ፣
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ፣ ዶ/ር መስከረም ለቺሣ፣ ደራሲ ዘነበ ወላ፣ ዶ/ር
ገዛኸኝ ፀጋዉ፣ አርቲስት ገነት ንጋቱ፣ ደራሲ አንዷለም አባተ (የአፀደ ልጅ)፣ ደራሲ ሕይወት
እምሻዉ፣ መምህር ደረጄ ነጋሽ፣ ደራሲ ቃልኪዳን ኃይሉ እና ደራሲ እስጢፋኖስ በፍቃድ
ሥራዎቻቸዉ እና በተዘጋጁበት ሪዕሰ ጉዳይ ድግሱን ያደምቁታል። በዕለቱ ድንገቴዎች /
Surprise/ እና በርካታ አዝናኝ ትርዒቶች ይኖራሉ።
@@@የመርሃ ግብሩ /የጥበብ ምሽቱ/ ደጋሽ ----አብርሃም ግዛዉ ኢንተርቴመንት
@@@መግቢያ----- 100 ብር ብቻ
@@@ ትኬቱን በአይናለም መፅሐፍ መደብር፣ በጃፍር መፅሐፍ መደብር፣ በብሔራዊ
ቴአትር ዮናስ መፅሐፍ መደብር እና በቦሌ አትላስ ወደ ቺቺኒያ በሚወስደዉ መንገድ እሴት
ባርና ሬስቱራንት ያገኙታል።
////// እንደተለመደው በመርሃ ግብሩ አብዝተው እንደሚያተርፉ ባለሙሉ ተስፋ ነን ////
@@@ለበለጠ መረጃ 0912374014 ይደዉሉ።
@getem
@balmbaras
"አብሮነት" በሚል ሪዕስ በእለተ ማክሰኞ ነሐሴ 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔታል
ሆቴል ትልቁ አዳራሽ ታላቅ የጥበብ ድግስ ተሰናድቷል። በዕለቱ ግጥም፣ ወግ፣ መነባንብ፣
ዲስኩርና የኮሜዲ ሥራዎች ይቀርባሉ። በኘሮግራሙ ላይ ኘሮፊሰር በየነ ጴጥሮስ፣
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ፣ ዶ/ር መስከረም ለቺሣ፣ ደራሲ ዘነበ ወላ፣ ዶ/ር
ገዛኸኝ ፀጋዉ፣ አርቲስት ገነት ንጋቱ፣ ደራሲ አንዷለም አባተ (የአፀደ ልጅ)፣ ደራሲ ሕይወት
እምሻዉ፣ መምህር ደረጄ ነጋሽ፣ ደራሲ ቃልኪዳን ኃይሉ እና ደራሲ እስጢፋኖስ በፍቃድ
ሥራዎቻቸዉ እና በተዘጋጁበት ሪዕሰ ጉዳይ ድግሱን ያደምቁታል። በዕለቱ ድንገቴዎች /
Surprise/ እና በርካታ አዝናኝ ትርዒቶች ይኖራሉ።
@@@የመርሃ ግብሩ /የጥበብ ምሽቱ/ ደጋሽ ----አብርሃም ግዛዉ ኢንተርቴመንት
@@@መግቢያ----- 100 ብር ብቻ
@@@ ትኬቱን በአይናለም መፅሐፍ መደብር፣ በጃፍር መፅሐፍ መደብር፣ በብሔራዊ
ቴአትር ዮናስ መፅሐፍ መደብር እና በቦሌ አትላስ ወደ ቺቺኒያ በሚወስደዉ መንገድ እሴት
ባርና ሬስቱራንት ያገኙታል።
////// እንደተለመደው በመርሃ ግብሩ አብዝተው እንደሚያተርፉ ባለሙሉ ተስፋ ነን ////
@@@ለበለጠ መረጃ 0912374014 ይደዉሉ።
@getem
@balmbaras
#ዝክረ ሙሉ ጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ )❤
#ድምፃዊ አበበ ተካ የተጫወተው ሙሉጌታ ተስፋዬ“መቃብሬ ውስጥ ሆኜም እሰማታለው ” የሚላት
የታላቁ ባለቅኔ አያ ሙሌ 3ኛ ልጁ ወፊቱ
15ኛ ዓመቱ ሲዘከር
ወፊቱ❤️❤️❤️
ጭራ ጭራ የምታድረው
ጭራ ለቅማ የምታድረው
ጭራ ጭራ የምታድረው
ጭራ ለቅማ የምታድረው
እንዲህ አስናቀችኝ...
ቀድማኝ ጎጆ ወጥታ ጎጆ አስተማረችኝ
ጎጆ ...አቤት ጎጆን... ወፍዬ አስቀናችኝ፤
እህህ... ምነው ባደረገኝ
እህህ... የሷ ጋሻ ጃግሬ
እንደምንም ብዬ እኔም ጥሬ ግሬ
ያገዳ ጎጆዬን ባቆምኳት ማግሬ፤
እህህ... አጉል በቃኝ ላ'ይል
እህህ... አይን አይቶ ገምቶ
ወይ ሞልቶ ላይሞላ ጆሮ አይችሉ ሰምቶ
እንዴት ጎጆ ይቅር አርሶና ሸምቶ
ገመና ከታቹ የሣር ቤት ያማረሽ
ሚስጥረ መለኮት ማነው ያስተማረሽ
ካፈር ክዳን ጎጆ መሬቱን ፈልፍሎ
ከሰማይ ቤት እጣሽ ማን በሰጠኝ ከፍሎ
እኔን እኔን እኔን ይብላኝ
እኔን አይኔን እኔን ይብላኝ...
እኔን እኔን እኔን ይብላኝ
እኔን አይኔን እኔን ይብላኝ...
የቀን ሰው ሌጣ አፈር
ልቤ ሩቅ አሳቢው ቅርብ አድሮ ሲደፈር
ምን ነበር ቢቆጨው ጎጆ አጥቶ ከማፈር፤
እህህ... ፈጣሪዋን አምና
ያፏን ጥሬ ሰጥታ
ለጭሮ አዳር ውሎ በዝማሬ ወጥታ
አዳኝ እንዴት ያጥቃት ፍርድና ዳኛ አጥታ
እህህ... አጣሁ፣ ነጣሁ ብላ
እንደሰው ባይከፋት
ምፅዋት ባትለምን ተርፎን ባንደግፋት
ጎጆዋ ለቻላት ምን ነበር ባንገፋት
ታማ ትንፋሽ አጥሯት ደክማ ስታጣጥር
ማን ያቃናት ይሆን፥ ውለታ ሳይቆጥር
ማን ያቃናት ይሆን፥ ውለታ ሳይቆጥር
ወልዶ ማሳደጉን ብዙ ሰው ቢያውቅበት
ያፉን ማን ይሰጣል የእጁ ሲርቅበት
ያፉን ማን ይሰጣል የእጁ ሲርቅበት
እህህ... ወፊቱ፤
ኡሁሁ... ወፍዬ!
እህህ... ወፊቱ፤
ኡሁሁ... ወፍዬ
@getem
@balmbaras
#ድምፃዊ አበበ ተካ የተጫወተው ሙሉጌታ ተስፋዬ“መቃብሬ ውስጥ ሆኜም እሰማታለው ” የሚላት
የታላቁ ባለቅኔ አያ ሙሌ 3ኛ ልጁ ወፊቱ
15ኛ ዓመቱ ሲዘከር
ወፊቱ❤️❤️❤️
ጭራ ጭራ የምታድረው
ጭራ ለቅማ የምታድረው
ጭራ ጭራ የምታድረው
ጭራ ለቅማ የምታድረው
እንዲህ አስናቀችኝ...
ቀድማኝ ጎጆ ወጥታ ጎጆ አስተማረችኝ
ጎጆ ...አቤት ጎጆን... ወፍዬ አስቀናችኝ፤
እህህ... ምነው ባደረገኝ
እህህ... የሷ ጋሻ ጃግሬ
እንደምንም ብዬ እኔም ጥሬ ግሬ
ያገዳ ጎጆዬን ባቆምኳት ማግሬ፤
እህህ... አጉል በቃኝ ላ'ይል
እህህ... አይን አይቶ ገምቶ
ወይ ሞልቶ ላይሞላ ጆሮ አይችሉ ሰምቶ
እንዴት ጎጆ ይቅር አርሶና ሸምቶ
ገመና ከታቹ የሣር ቤት ያማረሽ
ሚስጥረ መለኮት ማነው ያስተማረሽ
ካፈር ክዳን ጎጆ መሬቱን ፈልፍሎ
ከሰማይ ቤት እጣሽ ማን በሰጠኝ ከፍሎ
እኔን እኔን እኔን ይብላኝ
እኔን አይኔን እኔን ይብላኝ...
እኔን እኔን እኔን ይብላኝ
እኔን አይኔን እኔን ይብላኝ...
የቀን ሰው ሌጣ አፈር
ልቤ ሩቅ አሳቢው ቅርብ አድሮ ሲደፈር
ምን ነበር ቢቆጨው ጎጆ አጥቶ ከማፈር፤
እህህ... ፈጣሪዋን አምና
ያፏን ጥሬ ሰጥታ
ለጭሮ አዳር ውሎ በዝማሬ ወጥታ
አዳኝ እንዴት ያጥቃት ፍርድና ዳኛ አጥታ
እህህ... አጣሁ፣ ነጣሁ ብላ
እንደሰው ባይከፋት
ምፅዋት ባትለምን ተርፎን ባንደግፋት
ጎጆዋ ለቻላት ምን ነበር ባንገፋት
ታማ ትንፋሽ አጥሯት ደክማ ስታጣጥር
ማን ያቃናት ይሆን፥ ውለታ ሳይቆጥር
ማን ያቃናት ይሆን፥ ውለታ ሳይቆጥር
ወልዶ ማሳደጉን ብዙ ሰው ቢያውቅበት
ያፉን ማን ይሰጣል የእጁ ሲርቅበት
ያፉን ማን ይሰጣል የእጁ ሲርቅበት
እህህ... ወፊቱ፤
ኡሁሁ... ወፍዬ!
እህህ... ወፊቱ፤
ኡሁሁ... ወፍዬ
@getem
@balmbaras
👍2