ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ሰዓት እላፊ!
😊 ደሞ እርዕስ አይደለም


ሁለት ጂስም _
ሁለት ነፍስ _
ሁለት ሳቅ _
ሁለት ሀቅ _
ሁለት _ _ ሁለት _ _ ሁለት _
ይህን አንድ ማድረግ ነው የጥበብ ሰው መልኩ የከያኒ ሀለት

@getem
@getem
@balmbaras
#ሰው_በመሆን_ጥጋት

በግብረ ክርስቶስ
እስከሞት ማፍቀርን ነፍሳቸው ታድላ
ብፁአን መዳፎች
ማቀፍ ሳይታክቱ የበዳይን ገላ
ላ'ረመኔው ልብህ
የይቅርታን ፀጋ መስጠት ካልነፈጉ
ሞኞች እንዳይመስሉህ
አቅፈው ሲማፀኑህ በ'ጅህ እየተወጉ፡፡

ይልቅ ያንተን ቋንቋ
በጦረኛ ጆሮ ከውስጥህ አድምጠው
ለክፋትህ ምላሽ
ልብህን ሲሰብሩት ፍቅርህን አብልጠው
የይቅርታን ብርታት
እንድታይ ነውና ከደማው ጀርባቸው
ሰው መሆን ከገባህ
ቀስትህን ጣልና በ'ጅህ እቀፋቸው፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@getem
አሳዲ ሙናዋ ፤
ገምሻራየዋየ ፤
ዋጃ ከመንገድ ላይ ስልክ ስትመቺ ታይተሻል እያሉ፤
ያች ገምሻራ ልጅ፤
አልደወለችም ወይ ??
ስልክ አልመታችም ወይ? ይለኛል ሰው ሁሉ ።
ደውለሺ ተሆነ ፤
እንጃልኝ ሸጋዋ፤
ስልኬም ሞኝ ሆነ መብራት መች ይመጣል፤
አቦ ደውይብኝ
ቻርጁ ቢጠፋ እንኳን፤
አንች ስትደውይ ፤
የሰራ አካላቴ ፤
ሃሎ በል እያለ ጅስሜ መልስ ይሰጣል ።
አንች ያገሬ ታቦት ፤
የጀመዶ ማርያም ፤
ውለታ ዋይሊኝ አንች ያንዱየ እናት፤
እንደሞባይሏ፤
አሳዲ ሙናዋን ጆሮዋ ስር ሁኜ እንዳነጋግራት።
ያኢስ!!!አስቤኮ!!!

(( ጃ ኖ )))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
አልወድሽም_እንጂ ..

አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ያዩሽም አይኖሩ ይቅርና የነኩሽ
አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽማ
አደባባይ ቆሜ ከመሃል ከተማ
በጂጉ በሚልቅ ከወፎቹ ዜማ
አዜምልሽ ነበር ህዝብ ሁሉ እንዲሰማ
ያው እንደነገርኩሽ
አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ፅሀይ ትቆማለች ጨርቃም አትወጣም
ነፋሱም ፅጥ ይላል ብርዱም አይበረታም
ወንዞችም አይፈሱም ቆመው ይሰማሉ
የፍቅራቸው ነገር ዕፁብ ነው ዕያሉ
ከፍቅራችን በላይ እጅግ የሚገርመው
እኛ ስንጎዳ ህዝቡን ነው የሚያመው
አልወድሽም እንጂ
አልወድሽም እንጂ
እኔ ከወደድኩሽ
ያው እንደነገርኩሽ
አመት አንድ ቀን ነው በፊትሽ በፊቴ
ምድርም አንድ እርምጃ ላንቺ ና ኔ ኮቴ
እኔማ ስወድሽ
ሰማይ ትጠባለች በፍቅራችን ደስታ
እኛ ከፈለግን ቀን ይሆናል ማታ
እምልልሻለሁ "አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽ ብዬ"
ደስ አሰኝሻለሁ ሰጎንን ቀድሜ አንበሳን ታግዬ
እኔ ከወደድኩሽ
እየተራመድን ነፋስ እንቀድማለን
እየተናገርን ዓለት እንሰብራለን
ከደመና መሃል ደመና እንፈጥራለን
አትጠራጠሪ
አልወድሽም እንጂ የወደድኩሽ ዕለት
ብረት እና ሳት ነን አንቺ ና ኔ ማለት
እሳት ና ብረት ግጥም እና ዜማ
ንጉስ እና ንግስት እግር እና ጫማ
አንድ መሆን ታውቂያለሽ አንድ መልክ አንድ ቀለም
እኔ አንችን ስወድሽ የሚመስለን የለም
ግን
እኔ ከማልኩልሽ በሚበልጥ መሃላ
ከምድራዊው ፍቅር ባይደለ በሌላ
የሚወዱሽ አሉ
እኔ ከወደድኩሽ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ምንድን ይሆናሉ

🚏

@getem
@getem
@getem
👍31🔥1
እንኳን አደረሰሽ ኢትዮጵያ!!
በክብረት መልቲ ሚዲያ የሚዘጋጀውና በአንጋፋው የሀገር ፍቅር ትያትር ቤት የሚቀርበው "በንባብ እንኑር" የኪነጥበብ ምሽት 2ኛው ዙር አርብ ጷጉሜ 1 ቀን 11:00 (ሰዓት) ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴያትር ቤት 'እንኳን አደረሰሽ ኢትዮጵያ!' በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሲሆን በዕለቱም አንጋፋና ወጣት የኪነ ጥበብ ሰዎች ይገኙበታል፣ ጋዜጠኛ ማርቆስ ባህሩ፣ ዓለም አቀፍ ፀሐፊ ግርማ ጌታሁን፣ በዛብህ ፣ ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ: ተስፋዬ አየለ: ገጣሚ ሌዊ እና ኪዳኔ መካሻ እንዲሁም ማህሌት ሌሎችም ዲስኩር ስለ አክቲቪስቶቻችን: በተጋባዥ እንግዶች ሽሙጥና ወግም ይደመጣል። በዕለቱ ግጥም ፣ ለስላሳ ሙዚቃ በድምፃዊ ዳዊት ሚደቅሳ እንዲሁም ሌሎች አማተር ሙዚቀኞች ጋር በልዩ አቀራረብ ከሀገር ፍቅር ሙዚቀኞች ጋር መድረኩን ያደምቁታል፡፡ የአንድ ሰው ትያትር 'ሰተቴ' በቁምላቸው አዱኛ ይመደረካል። መድረኩን ጋዜጠኛ ሊያ ረጋሳ ትመራዋለች፡፡
'በዶ/ር ኤሊያስ ገብሩ የተፃፈው 'አንድ ሀገር-ቢያ ቶኮ' እና በገጣሚ በዛብህ ብርሃኑ የተዘጋጀው 'የይሁዳ ገመድ' መፅሐፍቶች በዝግጅቱ ላይ በልዩ ሁኔታ ይመረቃሉ።
አንጋፋው አርቲስት ክቡር ዶ/ር ጋሽ ተስፋዬ (ፋዘር) የእለቱ ክብር እንግዳ ናቸው።
መግቢያ 100 ብር ብቻ። ለተማሪዎች በነፃ፡፡
አሐዱ ቴሌዥን ብቸኛው የሚዲያ አጋር።
ለበለጠ መረጃ ፦0917163155 ይደውሉ፡፡
////'እኔ ኣንቺን ለመርሳት'///
(ሀብታሙ ያለዉ)

ያስጠላሻል ባልሁት በረከሰው ሁሉ ይዤሽ ተንከራተትሁ፣
ቦታ እንድትለቂልኝ በጠበበው ልቤ ብዙ ኮረት ከተትሁ፣
የልቤ ጭቅቅት ምንም ባይደላሽም፣
አፀዳሽው እንጂ ጥለሽ አልወጣሽም፡፡


@getem
@getem
@getem
ከዛውያው ግርጌ፤
አለቅሳለሁ እንጅ አንጀቴን አጥ ፌ፤
እንዴት እንቅልፍ ይምጣኝ ገዳይና ሟቹን በማጀቴ አቅፌ።


ውረድ ተወራረድ ይለኛል ክፉ ሰው፤
እሱን ምን ገደደው ፥
ይብላኝልህ በሉኝ ለኔ ለማለቅሰው።


ማሽላየን ሽጨ፤
ሞፈርን ቆስቁሸ ዶክተር ፕሮፌሰር አስተምሬ ነበር፤
ያኖረኝን ጎጆ ላፍርስ ብለው መጡ መገን የኔ ነገር።
ልጅህን አስተምር ፊደል የቆጠረ አይከፋም ብላችሁ፤
ሂዱ ተመልከቱት፤
የአንገት መግቢያ ቤቴን በተሳለ ምላስ አፈረሰላችሁ።
ይብላኝ እንጅ ላንተ ብራናውን ቀደህ ቃልህን ለምትበላ፤
ፊደል ቆጣሪ ሆይ፤
ተስፋ ቆርጫለሁ ካንተ ጥቁር ምላስ ሃገርን የሚያድን አይገኝም መላ፤
አላህ ይርዳኝ በለኝ፤
በጁምኣ ሰማይ ስር ዱኣየን ይዣለሁ ከእንግዲህ በዃላ ።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
ግጥም ብቻ 📘
Photo
ቃል የለኝም ላንቺ
ከቃላት ይገዝፋል የልቦናሽ ወጉ
ክፍያሽ ይለያል
ከምድር አይደለም ሰማይ ነው ማረጉ

እናትነት ቅኔ
እናትነት ሚስጥር በደም የተዋጀ
ከህይወት ተጋፍጦ
የእልፎችን ገላ በዘመን ያበጀ፡፡

መሆኑ ሲገባኝ
ለክብርሽ ሚመጥን አንድ ቃል አጥቼ
እድሜ እንዲሰጥሽ
ፈጣሪን ለመንኩት ግጥም መፃፍ ትቼ፡፡

ክብር ስለኛ ከሰው በታች ሆነው ላኖሩን ኢትዮጲያዊ እናቶች፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@gebriel_19
ለቅዳሚታችን(ቅዳሜን የምትመስል ግጥም )
❤️


ስርፀት-2
፨፨፨፨፨
ውዴ የምወድሽ!!
በሸሪዓ ቁሞ፡ በዱዓ እንደመፅናት፣
በሙሀባ አጊጦ፡ በኢልም እንደመንቃት፣
አምሬ...!!
ሰምሬ...!
ደምቄ...!!
መጥቄ...!!
.
ስቶ እንደመታረም፡ ጎብጦ እንደመቃናት፣
ወዶ እንደመመንመን፡ አፍቅሮ እንደመክሳት፣
ገርጥቸ...!!
ወርዝቸ...!!
አምጨ...!!
ታንጨ...!!
.
እንደልብ ሀገር፡ እንደሐቅ ማተብ፣
እንደእምነት ብርሃን፡ እንደፅድቅ ቀለብ፣
በርትቸ...!!
በርክቸ...!!
ነፅቸ...!
ፀንቸ...!!
.
ካለኢምንት እንከን፡ ካለቁንፅል ክፋት፣
ስቶ እንደመታረም፡ ቆሽሾ እንደመንጻት፣
ደፍርሼ...!!
ታድሼ...!!
.
ተገፍቶ ተረግጦ፡
የማእዘን ማገር፡ ሁኖ እንደመመረጥ፣
ወድቆ ተንከላውሶ፡
ያሰቡትን ስኬት፡ ልክ እንደመጨበጥ፣
ኮስምኘ...!!
ደንድኘ...!!
ለፍቸ...!!
ደርጅቸ...!!
.
ለልሳንሽ ዜማ፡ ልብ ብቻ ሁኘ፣
ለምግባርሽ አባር፡ በክብር ታድኘ፣
በእቅፍሽ ሙቀት፣
በፈገግታሽ ድምቀት፣
ማፍቀሬን አፍቅሬ፣
ችግሬን መንጥሬ፣
ሱናሜ ፌዝሽን!!
ባህር ንቀትሽን!!
ዳገት ኩራትሽን!!
ይህን ሁሉ ቀዝፌ፣
በልብሽ ተፅፌ፣
ለፍቅር ዝማሬ፣
ባንገትሽ ታስሬ፣
ባመንሽው ተጉዠ፡ በወደድሽው መሞት፣
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥ይህ ነው የኔ ምኞት።
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥ያፍቅሮቴ አፍቅሮት፣
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥የህይወቴ ሂዎት።
አ ፈ ቅ ር ሻ ለ ሁ !!
.
.
ይህ የእብዱ ስነትንፋሰ ብእር ነው!!
ሸጋ መዓልት!!

@getem
@getem
@balmbaras
ሀሳብ እና ደቦ
(በድሉ ዋቅጅራ)

አባቶች ፣
በደቦ እያረሱ - ክፉን ቀን ተሻግረው
በ ደቦ እያጠሩ - ቅጽር አስረክበው
ነፃነት ፈጠሩ
በ ነፃነት ኖሩ።

ልጆች፣
በ ደቦ እያሰቡ ፣
በ ደቦ አፍቅረው ፣ በ ደቦ እየጠሉ
ከ ነፃነት ማማ ይሽቀነጠራሉ

ያሳዝናል!!!

@getem
@getem
@getem
( በላይ በቀለ ወያ )
.
አቤቱ
እንሆ እንዲከፍቱልኝ፣ ሳንኳኳ የሰዎችን በር
ማን ልበል ይሉኛል ሁሉም
ማንነት ማለት ምን ነበር?
ማነኝ ብላቸው ያምኑኛል?፣ እኔ ነኝ ማለት ተሳነኝ
እኔጋር እኔ የለሁም
አላህ አንተ ጋር ፣ ቆይ ማን ነኝ
እግዜር አንተ ጋር ፣ ቆይ ማን ነኝ?
።።።
አቤቱ
ሰው ተሰባሪ እንደንጨት ፣ ሰው ደቃቂ እንደሸክላ
የማለት ድፍረት የለኝም ፣ በአምሳልህ ስለተሞላ
በእጆችህ ስለተበጀ ፣ ትንፋሽህ ስለዳሰሰው
ሰው አልፈልግም ከስጋ ፣
ብርቱነት ስለተቸረ ፣ ነፍሱ ላይ ስለሚገኝ ሰው።
።።።።
አቤቱ
ከአእዋፎች እንቁላል ፣ ክንፎችን የምትዘረጋ
እግሮቼን ወደ ፅድቅ አቅና ፣ ከንፈሬን ለምስጋና አትጋ
እንዴት ነህ ይሉኛል ሰዎች
እንዴት ነኝ አላህ አንተጋ ?
እንዴት ነኝ እግዜር አንተጋ?
።።።

( በላይ በቀለ ወያ )

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@getem
@getem
@getem
አንዳንዱ
በባዶ እግሩ ሮጦ ፣ ሀገሩን ያስጠራል
ትውልዱን ያኮራል ፣ ታሪክ ይዘክራል
አንዳንዱ
በባዶ ጭንቅላት ፣ ሀገር ያሸብራል
ትውልድ ያቃቅራል።
።።።
የእናት ሆድ ዥንጉርጉር
ለሚል ብሒላችን ፣ ብናጣም ምሳሌ
ከባዶ ጭንቅላት
ሚሻሉ ባዶ እግሮች ፣ እሉ እላለሁ ሁሌ።
።።።፣

(በላይ በቀለ ወያ)


@getem
@getem
@getem