ለሰንበታችን
💚💚💚
ወይ ግሩም!!!
( ደረጀ ሀ)
ነገ ቀጠሮ አለን፣ ረፋዱ ግድም፣
ቅንጣት አታስቢ፣ደቂቃ አላረፍድም።
ልክ እንዳገኘሁሽ፣ እንዳየሁሽ ገና፣
በሁለት እጆቼ ፣እቅፍ አደርግና፣
ወደ ያዝኩት ቦታ፣ በ"ወክ" እንሄድና ....
በስተቀኜ በኩል፣ አጋድምሻለሁ፣
አንቆ የያዘሽን፣
የታቹን ልብስሽን፣
በራሴ እጅ አውልቄ፣ ዘና አደርግሻለሁ።
ከዚያማ .....
በወንድ ጉልበቴ፣
በሞቀው ስሜቴ፣
በእጆቼ ጫር ጫር፣ ትንሽ ቆፈር ቆፈር፣
ያለ አንዳች መለገም፣ያለምንም ማፈር።
በእንዲህ ያለ ጥበብ፣ ህዋስሽ ሲነቁም፣
ከዚያ በኋላ ነው፣ የምትክልሽ በቁም።
ወይ ግሩም!!!
ከሰው ህይወት ጋራ አቻ ' ሚስተካከል፣
ግሩም " አርት " ኖሯል፣ ለካ ችግኝ መትከል።
መልካም ሰንበት !!!💚💚💚
@getem
@getem
@balmbaras
💚💚💚
ወይ ግሩም!!!
( ደረጀ ሀ)
ነገ ቀጠሮ አለን፣ ረፋዱ ግድም፣
ቅንጣት አታስቢ፣ደቂቃ አላረፍድም።
ልክ እንዳገኘሁሽ፣ እንዳየሁሽ ገና፣
በሁለት እጆቼ ፣እቅፍ አደርግና፣
ወደ ያዝኩት ቦታ፣ በ"ወክ" እንሄድና ....
በስተቀኜ በኩል፣ አጋድምሻለሁ፣
አንቆ የያዘሽን፣
የታቹን ልብስሽን፣
በራሴ እጅ አውልቄ፣ ዘና አደርግሻለሁ።
ከዚያማ .....
በወንድ ጉልበቴ፣
በሞቀው ስሜቴ፣
በእጆቼ ጫር ጫር፣ ትንሽ ቆፈር ቆፈር፣
ያለ አንዳች መለገም፣ያለምንም ማፈር።
በእንዲህ ያለ ጥበብ፣ ህዋስሽ ሲነቁም፣
ከዚያ በኋላ ነው፣ የምትክልሽ በቁም።
ወይ ግሩም!!!
ከሰው ህይወት ጋራ አቻ ' ሚስተካከል፣
ግሩም " አርት " ኖሯል፣ ለካ ችግኝ መትከል።
መልካም ሰንበት !!!💚💚💚
@getem
@getem
@balmbaras
👍1
አዋጅ አዋጅ አዋጅ!!!
የብጹዕ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ ሰምዐትነት ቀን ይከበራል።
ከዘመናት በኋላ አስታዋሽ አግኝተዋል።
"ለኹሉም ግዜ አለው" እንዲል
በነገው እለት ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን ከጠዋቱ 3፥30 ጀምሮ 82ኛውን የብጹዕ አባታችን አቡነ
ጴጥሮስ ዕለተ ሰማዕትነት በአደባባያቸው እና በአዲስ አበባ ከተማ አዳራሽ ቅጥር ግቢ
በደማቅ ስነሥርዓት እናከብራለን።
ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ትገኙ ዘንድ በአክብሮት ጠርተናችኋል።
# አቡነ_ጴጥሮስ_ሰማዕተ_ጽድቅ
ሼር በማድረግ የበኩልዎን ይወጡ
@getem
@getem
የብጹዕ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ ሰምዐትነት ቀን ይከበራል።
ከዘመናት በኋላ አስታዋሽ አግኝተዋል።
"ለኹሉም ግዜ አለው" እንዲል
በነገው እለት ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን ከጠዋቱ 3፥30 ጀምሮ 82ኛውን የብጹዕ አባታችን አቡነ
ጴጥሮስ ዕለተ ሰማዕትነት በአደባባያቸው እና በአዲስ አበባ ከተማ አዳራሽ ቅጥር ግቢ
በደማቅ ስነሥርዓት እናከብራለን።
ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ትገኙ ዘንድ በአክብሮት ጠርተናችኋል።
# አቡነ_ጴጥሮስ_ሰማዕተ_ጽድቅ
ሼር በማድረግ የበኩልዎን ይወጡ
@getem
@getem
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
☘የአረንጓዴ አሻራ ቀን☘
🌴 ኑ!! በጋራ ሀገራችንን ውብ እናድርግ!!
ቅን-ድል ኢትዮጲያ በነገው ዕለት በሚኒሊክ ጎዳና አርንጓዴ አሻራ ያኖራል፡፡
በዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የችግኝ መትከል ዘመቻ ላይ አብራችሁን #አሻራችሁን እንድታሳርፉ ጥሪ እናቀርባለን🌴
✅ውብ አስተሳሰብ በውብ ተፈጥሮ እንገነባለን‼️
🌳 ሐምሌ 22, 2011🌳
Via @KendelM
https://tttttt.me/KenDelM/120
🌴 ኑ!! በጋራ ሀገራችንን ውብ እናድርግ!!
ቅን-ድል ኢትዮጲያ በነገው ዕለት በሚኒሊክ ጎዳና አርንጓዴ አሻራ ያኖራል፡፡
በዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የችግኝ መትከል ዘመቻ ላይ አብራችሁን #አሻራችሁን እንድታሳርፉ ጥሪ እናቀርባለን🌴
✅ውብ አስተሳሰብ በውብ ተፈጥሮ እንገነባለን‼️
🌳 ሐምሌ 22, 2011🌳
Via @KendelM
https://tttttt.me/KenDelM/120
አረንጓዴ አሻራ
(ሙለታ ሀሰን)
ያ አረንጓዴ ጎርፍ ዘመቻ
የስኬታችን ዋዜማ የ ምጥቀታችን መባቻ
ነገ ላንራብ ካያት ቤት
ጭራሽ ላይጠፋ እንጐቻ
ታሪካችንን ልንፅፍ ባረንጓዴ ጎርፍ ዘመቻ
ሀምሌ ወር ላይ ተገኝቷል የጓጉንቸሩ መክፈቻ
የ ስኬታችን ዋዜም የ ምጥቀታችን መባቻ
አለቃችንን ሳናጅብ በ አለቃችን ታጅበን
ሽቅብ ሳንወጣ ዳገቱን አካፋ ዶማ ሸክፈን
በ ህብረ-ብሔር ተውበን ሚሊየኖች ዛፍ ስንተክል
ለ ልጆቻችን የሚቆይ ትልቅ መሠረት ሰንጥል
ከፀብ ከቁርሾ ልንርቅ በፍቅር ስሜት ልንግል
በ ህሳቢያችን መደመር ከ በለፀጉት ልንውል
ከቶ ማጋነን አይሆን አግዝፌ ስዕሉን ብስል
እናም እምዬ ኢትዮጵያ ከዲክሽነሪ ልትወጪ
በረሀብ ስቃይ እንግልት ዳግም ወዳለም ላትመጪ
በምንም አይነት ስጦታ በማንም ሳትለወጪ
ይበቃል አረፍ በይና እስቲ ተቀምጠሽ አድምጪ
ጥጋብን መሸከም ሲያቅተን ተመልከቺና ተቆጪ
ቡናም ከ ጅማ ይመጣል ብርታት ይሁንሽ ተጎንጪ
ዳግም አብይን ለመውለድ ያለማቋረጥ አምጪ
መውለድሽ ካልጨነገፈ በዛፎች ጥላ ስር ሆነሽ ከልጆችሽ ጋር አምጪ።
@getem
@getem
@getem
(ሙለታ ሀሰን)
ያ አረንጓዴ ጎርፍ ዘመቻ
የስኬታችን ዋዜማ የ ምጥቀታችን መባቻ
ነገ ላንራብ ካያት ቤት
ጭራሽ ላይጠፋ እንጐቻ
ታሪካችንን ልንፅፍ ባረንጓዴ ጎርፍ ዘመቻ
ሀምሌ ወር ላይ ተገኝቷል የጓጉንቸሩ መክፈቻ
የ ስኬታችን ዋዜም የ ምጥቀታችን መባቻ
አለቃችንን ሳናጅብ በ አለቃችን ታጅበን
ሽቅብ ሳንወጣ ዳገቱን አካፋ ዶማ ሸክፈን
በ ህብረ-ብሔር ተውበን ሚሊየኖች ዛፍ ስንተክል
ለ ልጆቻችን የሚቆይ ትልቅ መሠረት ሰንጥል
ከፀብ ከቁርሾ ልንርቅ በፍቅር ስሜት ልንግል
በ ህሳቢያችን መደመር ከ በለፀጉት ልንውል
ከቶ ማጋነን አይሆን አግዝፌ ስዕሉን ብስል
እናም እምዬ ኢትዮጵያ ከዲክሽነሪ ልትወጪ
በረሀብ ስቃይ እንግልት ዳግም ወዳለም ላትመጪ
በምንም አይነት ስጦታ በማንም ሳትለወጪ
ይበቃል አረፍ በይና እስቲ ተቀምጠሽ አድምጪ
ጥጋብን መሸከም ሲያቅተን ተመልከቺና ተቆጪ
ቡናም ከ ጅማ ይመጣል ብርታት ይሁንሽ ተጎንጪ
ዳግም አብይን ለመውለድ ያለማቋረጥ አምጪ
መውለድሽ ካልጨነገፈ በዛፎች ጥላ ስር ሆነሽ ከልጆችሽ ጋር አምጪ።
@getem
@getem
@getem
ዝቅ ባልክ ቁጥር
ባንተ መተናነስ ሌሎች ከከበሩ
በሰውነት ዙፋን
የመኖር ንግስናው ላንተ ነው መንበሩ፡፡
እመነኝ ወዳጄ
አንተ ቁልቁል ወርደህ ከቸርካቸው ፀጋ
መውደቅ ማሸነፍ ነው
ከእግዜር የሚሸለም የንፁሀን ዋጋ፡፡
(ልብ አልባው ገጣሚ)
@getem
@getem
@gebriel_19
ባንተ መተናነስ ሌሎች ከከበሩ
በሰውነት ዙፋን
የመኖር ንግስናው ላንተ ነው መንበሩ፡፡
እመነኝ ወዳጄ
አንተ ቁልቁል ወርደህ ከቸርካቸው ፀጋ
መውደቅ ማሸነፍ ነው
ከእግዜር የሚሸለም የንፁሀን ዋጋ፡፡
(ልብ አልባው ገጣሚ)
@getem
@getem
@gebriel_19
አለሁ እኔ ደግሞ
።።።።።።።።።።።።
ከሰማየሰማይ፥
በፍቅር ተስቦ ፥ ሞቴን በሞቱ እየገደለ
የሞት ሸለቆዬን፥
በህይወት ፅኑ አለት ፥ እየደለደለ
አለኝ አንድ ንጉስ፥ሳልወደው ሚወደኝ
ዘወትር በፍቅር ድምጽ፥
ማልዶ ሚቀሰቅስ ፥ ደጁ የሚወስደኝ።
ደግሞ አለኝ አንድ ሰው፥
ሳይወደኝ ምወደው ፥ ሲሸሸኝ አጥብቆ
ልቤን መርጋት ከልካይ፥
በሱ፥በፍቅሩ እና ፥ በናፍቆቱ ሰብቆ።
አመታት አልፈዋል ፥
በሄደበት ሁሉ ፥ስሄድ ስከተለው
እግሬ በጉልበቱ፥
ነግቶ ማረፊያዬን ፥ በሩ ላይ ተከለው።
ይኼው እዚህ ደግሞ፥
ባለንፁሕ ልቡ፥ ፍቅሬን ብቻ ሽቶ
ከበሬ ማይጠፋ፥ቀን ጠብቶና መሽቶ።
"አንጀትን ባንጀት ነው"፥
የሚል ዘዬ አንግቦ ፥ ክራር ከጁ አያጣም
ክራሩን ሲገርፈው፥
ሆዴ የገባ ብርድ ፥ እስካመት አይወጣም።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
ማረፊያ መርከቤ ፥ ቀድማ የሰጠመች
ባይዋሯ ነፍሴ፥
ከሀኪሟ ርቃ ፥
(በመነጠል ደዌ ፥ ላትድን የታመመች።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
ከሶስት አንዳቸውን፥ማመስገን ያልታደልኩ
ከአምላኬም መቅደስ፥
ባዶነት አናውጾኝ ፥ ወጥቼ የኮበለልኩ።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
መሻቴን ሳሳድድ፥
ብርቱ ናፋቂዬን ፥ በርትቼ ምገፋ
በወዳቂው 'ምትስቅ፥
ተስፋ ቆራጭ ነፍሴ፥ ሞትን ተደግፋ።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
ከእግዜሬ ጋራ ፥ ሙግት የምገጥም
የህይወትን ባህር፥
ላላይ እየሸሸሁ፥
የምኞት ባህር ውሰጥ፥ ገብቼ ምሰጥም።
በቃኝ ኧረ በቃኝ!
መሻቴን ቀብሬ ፥
ስጦታዬን ላንሳ ፥ ሻቼን ግባ ልበል
የገፋኝ ይገፋ፥
ስወድቅ ያነሳኝን ፥ በደስታ ልቀበል።
ግባ ሙሽራዬ፥
የኔ ጽኑ ወዳጅ ፥ ያነጸህ መገፋት
አድሳት ህይወቴን፥
ከሙታን ባህር ላይ፥ ለህይወት ጭለፋት።
እንሆ መቅደሴ፥
እጆቼ ይቀጡ፥ በሩን የዘጉብህ
ልቤ ይቅረብ ለፍርድ፥
ፍቅርን ስትዘምር ፥ ስላቅ የሳቀብህ።
እግዜሩም ታረቀኝ፥
ግብዝ ሰውነቴ ፥
ባርከህ በሰጠኸው ፥ ሳይልህ ተመስገን
ሲባክን መኖሩ፥
እርቃኑን ሊሸሽግ፥ ሽቶ ሌላ ተገን።
ያልከውን ሊቀበል፥
ፍቃድህን አምኖ ፥ ፍስሃን ሸምቷል
ተመስገን አምላኬ፥
አዲሱ እኔነቴ
በሙላት ተሰርቶ ፥ ባዶነቴ ሞቷል።
@getem
@getem
@paappii
#dagim hiwot
።።።።።።።።።።።።
ከሰማየሰማይ፥
በፍቅር ተስቦ ፥ ሞቴን በሞቱ እየገደለ
የሞት ሸለቆዬን፥
በህይወት ፅኑ አለት ፥ እየደለደለ
አለኝ አንድ ንጉስ፥ሳልወደው ሚወደኝ
ዘወትር በፍቅር ድምጽ፥
ማልዶ ሚቀሰቅስ ፥ ደጁ የሚወስደኝ።
ደግሞ አለኝ አንድ ሰው፥
ሳይወደኝ ምወደው ፥ ሲሸሸኝ አጥብቆ
ልቤን መርጋት ከልካይ፥
በሱ፥በፍቅሩ እና ፥ በናፍቆቱ ሰብቆ።
አመታት አልፈዋል ፥
በሄደበት ሁሉ ፥ስሄድ ስከተለው
እግሬ በጉልበቱ፥
ነግቶ ማረፊያዬን ፥ በሩ ላይ ተከለው።
ይኼው እዚህ ደግሞ፥
ባለንፁሕ ልቡ፥ ፍቅሬን ብቻ ሽቶ
ከበሬ ማይጠፋ፥ቀን ጠብቶና መሽቶ።
"አንጀትን ባንጀት ነው"፥
የሚል ዘዬ አንግቦ ፥ ክራር ከጁ አያጣም
ክራሩን ሲገርፈው፥
ሆዴ የገባ ብርድ ፥ እስካመት አይወጣም።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
ማረፊያ መርከቤ ፥ ቀድማ የሰጠመች
ባይዋሯ ነፍሴ፥
ከሀኪሟ ርቃ ፥
(በመነጠል ደዌ ፥ ላትድን የታመመች።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
ከሶስት አንዳቸውን፥ማመስገን ያልታደልኩ
ከአምላኬም መቅደስ፥
ባዶነት አናውጾኝ ፥ ወጥቼ የኮበለልኩ።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
መሻቴን ሳሳድድ፥
ብርቱ ናፋቂዬን ፥ በርትቼ ምገፋ
በወዳቂው 'ምትስቅ፥
ተስፋ ቆራጭ ነፍሴ፥ ሞትን ተደግፋ።
አለሁ እኔ ደግሞ፥
ከእግዜሬ ጋራ ፥ ሙግት የምገጥም
የህይወትን ባህር፥
ላላይ እየሸሸሁ፥
የምኞት ባህር ውሰጥ፥ ገብቼ ምሰጥም።
በቃኝ ኧረ በቃኝ!
መሻቴን ቀብሬ ፥
ስጦታዬን ላንሳ ፥ ሻቼን ግባ ልበል
የገፋኝ ይገፋ፥
ስወድቅ ያነሳኝን ፥ በደስታ ልቀበል።
ግባ ሙሽራዬ፥
የኔ ጽኑ ወዳጅ ፥ ያነጸህ መገፋት
አድሳት ህይወቴን፥
ከሙታን ባህር ላይ፥ ለህይወት ጭለፋት።
እንሆ መቅደሴ፥
እጆቼ ይቀጡ፥ በሩን የዘጉብህ
ልቤ ይቅረብ ለፍርድ፥
ፍቅርን ስትዘምር ፥ ስላቅ የሳቀብህ።
እግዜሩም ታረቀኝ፥
ግብዝ ሰውነቴ ፥
ባርከህ በሰጠኸው ፥ ሳይልህ ተመስገን
ሲባክን መኖሩ፥
እርቃኑን ሊሸሽግ፥ ሽቶ ሌላ ተገን።
ያልከውን ሊቀበል፥
ፍቃድህን አምኖ ፥ ፍስሃን ሸምቷል
ተመስገን አምላኬ፥
አዲሱ እኔነቴ
በሙላት ተሰርቶ ፥ ባዶነቴ ሞቷል።
@getem
@getem
@paappii
#dagim hiwot
👍1
ሀገሬ እና ችግኝ
ስማኝ የ አገሬ ሰው የዋህ ገራገሩ
ትከል ችግኝህን እስኪለማ አገሩ
የ ሀገሬን ለምነት በሪክ ስናየዉ
ጥላዋ ነበረ ለ ሁሎም መፍትሔው
ሽምግልናው ዛፍ ስር
ንጉሱም ሲፈርድም ሆነው ነበር ዛፍ ስር
አስካላው ቤታችን ነበር ከዋልካዋ ስር
ሀጂ እና ዲያቆኑ ሰውን ሲያስተምሩ እዛው ነበር ዛፍ ስር
ታሪክ ሆና ቀረ ዛፎችን ጨፈጨፈን ገንብተን መናርያ
ተጨፉጭፎ አለቀ ዛፍ ይናፈቅ ጀመር ምን ይቅረጥ መጥረቢያ
የ አገርህ ለምነት ታሪክ ሁና እንዳይቀር
ችግር እየነቀልክ ችግኛችን ትከል
ስለዚህ ወገኔ የ ሰው ዘር ብሔሩን ማማረጥ ትተህ
ዛፍ ከ እነ ዝርያው በየቦታው ተከለህ ዘረኝነት ንቀል ከ ራስ ከ አገርህ
ወገኔ የ አገር ሰው ሁሎም ሰላም ሲሆን ሁሎም ሲረጋጋ
የ ሳለፍንው ታሪክ ባጣም የስደስታል ከተከልንው ዛፍ ስር ሆነን ስናወጋ
#abuka
@getem
@getem
ስማኝ የ አገሬ ሰው የዋህ ገራገሩ
ትከል ችግኝህን እስኪለማ አገሩ
የ ሀገሬን ለምነት በሪክ ስናየዉ
ጥላዋ ነበረ ለ ሁሎም መፍትሔው
ሽምግልናው ዛፍ ስር
ንጉሱም ሲፈርድም ሆነው ነበር ዛፍ ስር
አስካላው ቤታችን ነበር ከዋልካዋ ስር
ሀጂ እና ዲያቆኑ ሰውን ሲያስተምሩ እዛው ነበር ዛፍ ስር
ታሪክ ሆና ቀረ ዛፎችን ጨፈጨፈን ገንብተን መናርያ
ተጨፉጭፎ አለቀ ዛፍ ይናፈቅ ጀመር ምን ይቅረጥ መጥረቢያ
የ አገርህ ለምነት ታሪክ ሁና እንዳይቀር
ችግር እየነቀልክ ችግኛችን ትከል
ስለዚህ ወገኔ የ ሰው ዘር ብሔሩን ማማረጥ ትተህ
ዛፍ ከ እነ ዝርያው በየቦታው ተከለህ ዘረኝነት ንቀል ከ ራስ ከ አገርህ
ወገኔ የ አገር ሰው ሁሎም ሰላም ሲሆን ሁሎም ሲረጋጋ
የ ሳለፍንው ታሪክ ባጣም የስደስታል ከተከልንው ዛፍ ስር ሆነን ስናወጋ
#abuka
@getem
@getem
የሳድስ እርግማን
(ልዑል ሀይሌ)
.
ገጣሚው
በገጠመው ግጥም ህይወትን ሲገልጣት
እርግማን ነው ይላል
ጨረቃን አውርዶ በሳድስ ቃል መምታት
.
እኔ ግን ቀልብ የለኝ
ባንቺ ተለክፌ ፍርሃቴ ተገፏል
ኩነኔውን ትቼ
በሳድስ ስገጥም ጨረቃ ኮከቡ ከሰማይ ላይ ረግፏል
.
ምን ይሉት ፅድቅ ነው?
ሳድስን ገድፌ ጨረቃ ኮከቡን
በወገብሽ ልኬት ዙሪያ ሳልጠመጥም
ምን ይሉት ጥበብ ነው ምን የሚሉት ግጥም
.
ጨረቃን ጠቅሼ በሳድስ መምቻ ቃል
ግጥም ካልገጠምኩኝ
ምኑን ላንቺ ኖርኩኝ ምኑን አፈቀርኩኝ?
.
እነሆ ይውቀሰኝ እነሆ ይዝለፈኝ ገጣሚ የተባለው
ለነሱ ግድ የለኝ ግድ ያለኝ ላንቺ ነው
.
እቴ አንቺን ስወድሽ ጨረቃ እስከማውረድ
ኮከብ እስከማርገፍ በሳድስ መድፊያ ነው
ገጣሚውን እርሺው
የፃፍኩት ላንቺ ነው
.
ልክ እንደሚናከስ አላዋቂ ሳሚ ስጋ እንደሚነክሰው
ልክ እንደ ጨረቃ በእልፍ አእላፍ ርቀት ተሰቅላ ምታርሰው
አንተም ውሸታም ነህ እንዳትገጥም ብሎ ከሚለኝ ገጣሚ
ከሚርመሰመሰው
ግጥሜን ውደጂልኝ
ላንቺ ነው የፃፍኩት ግድ የለኝም ለሰው
አይ ሰው!!
@getem
@getem
@gebriel_19
(ልዑል ሀይሌ)
.
ገጣሚው
በገጠመው ግጥም ህይወትን ሲገልጣት
እርግማን ነው ይላል
ጨረቃን አውርዶ በሳድስ ቃል መምታት
.
እኔ ግን ቀልብ የለኝ
ባንቺ ተለክፌ ፍርሃቴ ተገፏል
ኩነኔውን ትቼ
በሳድስ ስገጥም ጨረቃ ኮከቡ ከሰማይ ላይ ረግፏል
.
ምን ይሉት ፅድቅ ነው?
ሳድስን ገድፌ ጨረቃ ኮከቡን
በወገብሽ ልኬት ዙሪያ ሳልጠመጥም
ምን ይሉት ጥበብ ነው ምን የሚሉት ግጥም
.
ጨረቃን ጠቅሼ በሳድስ መምቻ ቃል
ግጥም ካልገጠምኩኝ
ምኑን ላንቺ ኖርኩኝ ምኑን አፈቀርኩኝ?
.
እነሆ ይውቀሰኝ እነሆ ይዝለፈኝ ገጣሚ የተባለው
ለነሱ ግድ የለኝ ግድ ያለኝ ላንቺ ነው
.
እቴ አንቺን ስወድሽ ጨረቃ እስከማውረድ
ኮከብ እስከማርገፍ በሳድስ መድፊያ ነው
ገጣሚውን እርሺው
የፃፍኩት ላንቺ ነው
.
ልክ እንደሚናከስ አላዋቂ ሳሚ ስጋ እንደሚነክሰው
ልክ እንደ ጨረቃ በእልፍ አእላፍ ርቀት ተሰቅላ ምታርሰው
አንተም ውሸታም ነህ እንዳትገጥም ብሎ ከሚለኝ ገጣሚ
ከሚርመሰመሰው
ግጥሜን ውደጂልኝ
ላንቺ ነው የፃፍኩት ግድ የለኝም ለሰው
አይ ሰው!!
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1🔥1
ሰቆቃው ጴጥሮስ
________
< ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን >
፧
አዬ ምነው እመ ብርሃን ?
ኢትዮጵያን ጨከንሽባት ?
ምነው ቀኝሽን ረሳሻት ?
እስከመቼ ድረስ
እንዲህ መቀነትሽን ታጠብቂባት?
ልቦናሽን ታዞሪባት?
ፈተናዋን፣ ሰቀቀኗን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት?
አላንቺ እኮ ማንም የላት….
•••
አውሮጳ እንዲሁ
ትናጋዋን ፣ በፋሽስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ፣ ተምሳ፣ በስብሳ
ሂትለራዊ እባጭ
ጫንቃዋን፣ እንደኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ
አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት
ሥልጡን ፣ ብኩን ፣ መፃጉዕ ናት
•••
እና ፈርቼ እንዳልባክን
ሲርቀኝ የኃይልሽ ውጋገን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ
በርታ በይኝ እመ ብርሃን
ቃል ኪዳኔን እንዳልረሳት
እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን
•••
አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ
ተፈትቶ እንዳይከዳት ሠጋሁ …
አዋጅ፣ የምሥራች ብዬ
የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማኅፀን አርፌ
ከአፈርዋ አጥንቴን ቀፍፌ
ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟ ወዜን ቀፍፌ
•••
በሕፃን እግሬ ድሄባት፣ በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ፣ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ፣ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ፤
በጋው የእረኛ አደባባይ፣ ክረምት እንደወንዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ፣ በገደል ሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅ እና ከሚዳቋ፣ ከዥግራ ጠረን ስተሻሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ፣ መወርወር መንጠልጠል ጥሎሽ
ከፍልፈል ጋር ሩጫ ስገጥም፣ ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከናዳ ጫፍ ሣር አጨዳ፣ ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎች ራት፣ ለማታቸው ትንሽ ድርቆሽ
ለግልገሌ ካውሬ ከለል
እማሳው ሥር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል፣ ለዝናብ የገሳ ጠለል
•••
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ፣ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሣር ሲለመልም፣ ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከንበል ሲል፣ ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ፣ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ፣ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ …..
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመ ብርሃን እረሳሻት?
•••
ያቺን የልጅነት የምሥራች? የሕፃንነት ብሥራት
የሣቅ የፍንደቃ ዘመን፣ የምኞት የተስፋ ብፅአት
ያቺን የልጅነት እናት?
አዛኚቱ እንዴት ብለሽ፣ ጥርሶችሽን ትነክሺባት?
ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ባገልግሎትሽ ስዋትት
ከዜማ ቤት እቅኔ ቤት፣ ከድጓ ቤት እመጻሕፍት
ካንቺ ተቆራኝታ ዕድሌ፣ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ
ከቀፈፋ ደጀሰላም፣ ከቤተልሔም ቅዳሴ
እኰ፣ ቀፎ ዳባ ለብሶ
ቅኔ ዘርፎ ግስ ገሦ
መቅደስ አጥኖ ማኅሌት ቆሞ
በልብስ ተክህኖ አጊጦ፣ በብር አክሊል ተሸልሞ
እመ ብርሃን ያንች ጽላት፣ ነፍስ ላይ በእሳት ታትሞ
የመናኒው ያባ ተድላ፣ ረድ ሆኜ፣ አብሮኝ ታድሞ
ሕይወቴ እምነትሽን ጸንሶ
ሥጋ ፈቃዴ ተድሶ
ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ፣ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ
ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ሆነሺኝ የእምነቴ ፋኖስ
ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም፣ ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ
ስሮጥ በወንበሩ አኖርሺኝ
በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ
ታዲያ ዛሬ ኢትዮጵያ ስትወድቅ
ከምትሰጪኝ የፍርሃት ጦስ
ምነው በረኝነት እድሜ፣ ዓይኔን በጓጎጣት የሎስ
የጋኔል ጥንብ አንሳ ከንፎ፣ ወርዶ በጨለማ በርኖስ
•••
ባክሽ እመ ብርሃን ይብቃሽ
ባክሽ ምስለ ፍቁር ወልዳ
ጽናት ስጪኝ እንድካፈል
የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ
ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ ፤ ከነደደችበት እቶን
የሷን ሞት እኔ እንድሞታት ፤ ገላዋ ገላዬ እንዲሆን
@getem
@getem
@paappii
________
< ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን >
፧
አዬ ምነው እመ ብርሃን ?
ኢትዮጵያን ጨከንሽባት ?
ምነው ቀኝሽን ረሳሻት ?
እስከመቼ ድረስ
እንዲህ መቀነትሽን ታጠብቂባት?
ልቦናሽን ታዞሪባት?
ፈተናዋን፣ ሰቀቀኗን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት?
አላንቺ እኮ ማንም የላት….
•••
አውሮጳ እንዲሁ
ትናጋዋን ፣ በፋሽስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ፣ ተምሳ፣ በስብሳ
ሂትለራዊ እባጭ
ጫንቃዋን፣ እንደኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ
አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት
ሥልጡን ፣ ብኩን ፣ መፃጉዕ ናት
•••
እና ፈርቼ እንዳልባክን
ሲርቀኝ የኃይልሽ ውጋገን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ
በርታ በይኝ እመ ብርሃን
ቃል ኪዳኔን እንዳልረሳት
እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን
•••
አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ
ተፈትቶ እንዳይከዳት ሠጋሁ …
አዋጅ፣ የምሥራች ብዬ
የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማኅፀን አርፌ
ከአፈርዋ አጥንቴን ቀፍፌ
ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟ ወዜን ቀፍፌ
•••
በሕፃን እግሬ ድሄባት፣ በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ፣ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ፣ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ፤
በጋው የእረኛ አደባባይ፣ ክረምት እንደወንዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ፣ በገደል ሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅ እና ከሚዳቋ፣ ከዥግራ ጠረን ስተሻሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ፣ መወርወር መንጠልጠል ጥሎሽ
ከፍልፈል ጋር ሩጫ ስገጥም፣ ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከናዳ ጫፍ ሣር አጨዳ፣ ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎች ራት፣ ለማታቸው ትንሽ ድርቆሽ
ለግልገሌ ካውሬ ከለል
እማሳው ሥር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል፣ ለዝናብ የገሳ ጠለል
•••
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ፣ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሣር ሲለመልም፣ ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከንበል ሲል፣ ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ፣ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ፣ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ …..
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመ ብርሃን እረሳሻት?
•••
ያቺን የልጅነት የምሥራች? የሕፃንነት ብሥራት
የሣቅ የፍንደቃ ዘመን፣ የምኞት የተስፋ ብፅአት
ያቺን የልጅነት እናት?
አዛኚቱ እንዴት ብለሽ፣ ጥርሶችሽን ትነክሺባት?
ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ባገልግሎትሽ ስዋትት
ከዜማ ቤት እቅኔ ቤት፣ ከድጓ ቤት እመጻሕፍት
ካንቺ ተቆራኝታ ዕድሌ፣ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ
ከቀፈፋ ደጀሰላም፣ ከቤተልሔም ቅዳሴ
እኰ፣ ቀፎ ዳባ ለብሶ
ቅኔ ዘርፎ ግስ ገሦ
መቅደስ አጥኖ ማኅሌት ቆሞ
በልብስ ተክህኖ አጊጦ፣ በብር አክሊል ተሸልሞ
እመ ብርሃን ያንች ጽላት፣ ነፍስ ላይ በእሳት ታትሞ
የመናኒው ያባ ተድላ፣ ረድ ሆኜ፣ አብሮኝ ታድሞ
ሕይወቴ እምነትሽን ጸንሶ
ሥጋ ፈቃዴ ተድሶ
ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ፣ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ
ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ሆነሺኝ የእምነቴ ፋኖስ
ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም፣ ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ
ስሮጥ በወንበሩ አኖርሺኝ
በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ
ታዲያ ዛሬ ኢትዮጵያ ስትወድቅ
ከምትሰጪኝ የፍርሃት ጦስ
ምነው በረኝነት እድሜ፣ ዓይኔን በጓጎጣት የሎስ
የጋኔል ጥንብ አንሳ ከንፎ፣ ወርዶ በጨለማ በርኖስ
•••
ባክሽ እመ ብርሃን ይብቃሽ
ባክሽ ምስለ ፍቁር ወልዳ
ጽናት ስጪኝ እንድካፈል
የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ
ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ ፤ ከነደደችበት እቶን
የሷን ሞት እኔ እንድሞታት ፤ ገላዋ ገላዬ እንዲሆን
@getem
@getem
@paappii
❤1👍1
ያሳበዱኝ ሳሉ አሳባጅ ተብዬ
በፍቅርሽ ወላፈን ካልጋዬ ተጥዬ
ሴትስ እንደ አንቺ ከየት አገኛለው
የግጥሜ ርዕስ ይሄ ነው እላለው
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
እብድ ናት ይሉኛል ማየት ተስኗቸዉ
እኔው እዳሳበድኩ ማን በነገራቸው
ትቅርብህ ይሉኛል እርግፍ አርገህ ተዋት
ማን በነገራቸው እንደተሰቃየው በፍለጋ ብዛት
ማንስ ሹክ ባላቸው ስላንቺ መሳይ ሴት
ከለታት ባንዱ ቀን እደዚህም ሆኗል
ማን እንደሆን እጃ በክልል ጥያቄ እራሱንም ሞልቷል
ከኔ ለመገንጠል መሳሪያውን ታጥቇል
ውስጥሽ ባለው ፍቅሬ እኔን ለመገንጠል?
እንኩዋን ዘረኝነት ፍቅር ራሱ ከብዷል
እውነቱን ልገርሽ መውደድ ሳይሆነ ፍቅር በውስጤ ተወልዷል
እናልሽ አለሜ
ብርሀን በሌለው በተስፋ ውስጥ ሳለዉ
እንደ አምሳለ ሲኦል ታቦት እየጠራው
ቅኔ እየተቀኘው
ከነብሴ ደብር ውስጥ አንቺን ስፈልግሽ
ጧፉን እያበራው ከጨለማዉ ገፅሽ
በፍቅርሽ ቅኔ ውስጥ ተገኘው ከልብሽ
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ፀሀፊ:-ሳምሶን ጌቱ
@getem
@getem
@paappii
በፍቅርሽ ወላፈን ካልጋዬ ተጥዬ
ሴትስ እንደ አንቺ ከየት አገኛለው
የግጥሜ ርዕስ ይሄ ነው እላለው
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
እብድ ናት ይሉኛል ማየት ተስኗቸዉ
እኔው እዳሳበድኩ ማን በነገራቸው
ትቅርብህ ይሉኛል እርግፍ አርገህ ተዋት
ማን በነገራቸው እንደተሰቃየው በፍለጋ ብዛት
ማንስ ሹክ ባላቸው ስላንቺ መሳይ ሴት
ከለታት ባንዱ ቀን እደዚህም ሆኗል
ማን እንደሆን እጃ በክልል ጥያቄ እራሱንም ሞልቷል
ከኔ ለመገንጠል መሳሪያውን ታጥቇል
ውስጥሽ ባለው ፍቅሬ እኔን ለመገንጠል?
እንኩዋን ዘረኝነት ፍቅር ራሱ ከብዷል
እውነቱን ልገርሽ መውደድ ሳይሆነ ፍቅር በውስጤ ተወልዷል
እናልሽ አለሜ
ብርሀን በሌለው በተስፋ ውስጥ ሳለዉ
እንደ አምሳለ ሲኦል ታቦት እየጠራው
ቅኔ እየተቀኘው
ከነብሴ ደብር ውስጥ አንቺን ስፈልግሽ
ጧፉን እያበራው ከጨለማዉ ገፅሽ
በፍቅርሽ ቅኔ ውስጥ ተገኘው ከልብሽ
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ፀሀፊ:-ሳምሶን ጌቱ
@getem
@getem
@paappii
ፍቅርና ጫካ!!!
የአባ መፍቀሬ አገር፤ የነ ሸህ በረካ፤
መትከል ያውቅበታል፤
መውደድና ማበር፤ ፍቅርና ጫካ ።
አልሃምዱሊላሂ ታቦታችን ገባ፤
እግዚሃር ይመስገን ኢዳችን ደረሰ፤
የሚለው ወሎየ ፤
እርጥብ ቅጠል ይዞ ፤
አሻራውን ሊያኖር ፤ መሬቱን ገመሰ፤
እንኳን የኛ ገላ፤
ጦሳም ቀን ወጥቶለት አረንጓዴ ጉፍታ መቀነት ለበሰ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
የአባ መፍቀሬ አገር፤ የነ ሸህ በረካ፤
መትከል ያውቅበታል፤
መውደድና ማበር፤ ፍቅርና ጫካ ።
አልሃምዱሊላሂ ታቦታችን ገባ፤
እግዚሃር ይመስገን ኢዳችን ደረሰ፤
የሚለው ወሎየ ፤
እርጥብ ቅጠል ይዞ ፤
አሻራውን ሊያኖር ፤ መሬቱን ገመሰ፤
እንኳን የኛ ገላ፤
ጦሳም ቀን ወጥቶለት አረንጓዴ ጉፍታ መቀነት ለበሰ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
ይች ዘሙ ሙሄን፤
ሰው አያይም ብየ ፤
ከሰዋራው ቦታ ከንፈሯን ብጎርሳት፤
ባለ ፎቶዎቹ እኔንም አነሱኝ እሷንም አነሷት፤
መሆኑን ለየነው፤
ጤቅ የተሰራነው በጫካው መመንጠር በደኑ መሳሳት።
በአዋጅ በነጋሪ ትከሉ ስንባል ጫካው ቢናፍቀን እኔና ዘሙየ፤
አሻራ አኑሬያለሁ ግማሹን ቆፍሬ ግማሹን ተክየ ።
የተተከለው ዛፍ ከዘመን በዃላ ማንም ሰው ቢመጣ አይጠፋውም ከቶ ፤
ታገኙታላችሁ እንደተካዮቹ በአግድመት ተኝቶ ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ምሽት!!
@getem
@getem
@balmbaras
ሰው አያይም ብየ ፤
ከሰዋራው ቦታ ከንፈሯን ብጎርሳት፤
ባለ ፎቶዎቹ እኔንም አነሱኝ እሷንም አነሷት፤
መሆኑን ለየነው፤
ጤቅ የተሰራነው በጫካው መመንጠር በደኑ መሳሳት።
በአዋጅ በነጋሪ ትከሉ ስንባል ጫካው ቢናፍቀን እኔና ዘሙየ፤
አሻራ አኑሬያለሁ ግማሹን ቆፍሬ ግማሹን ተክየ ።
የተተከለው ዛፍ ከዘመን በዃላ ማንም ሰው ቢመጣ አይጠፋውም ከቶ ፤
ታገኙታላችሁ እንደተካዮቹ በአግድመት ተኝቶ ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ምሽት!!
@getem
@getem
@balmbaras