ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ጥለት ያጣች ሀገር
ሀገሬ ሀገሬ ፣ ሀገሬ አትበሉኝ፤
እናንተው ቀብራቹ ፣ ትንሳኤ አታሳዩኝ፤
ጥለቴ አንድ ነው ፣ የመኖሬ አርማ፤
የአረን (ዴ ቢጫ ቀይ ፣ የአንድነት ሸማ፡፡
ግን……
አንድ አልባስ እንስፋ ፣ስትሉ ከርማቹ፤
ዘጠኝ ሆኜ ቀረው ፣ ጥለቴን ቀዳቹ፤
ደግሞም ይባስ ብሎ ፣ ሌላውም ይጎመጃል፤
ሰፋውላት እያለ ፣ መልሶ ይቀዳል፤
እኔስ ምን እላለው ፣ እግዜሩ ይስጣቸው፤
እርቃኔን እንደ ቀረው ፣ ምነው ባሳያቸው፡፡

በበዛብህ ብርሃኑ
ከ የይሁዳ ገመድ ላይ የተወሰደ

@getem
@getem
@getem
ያስተሰርያል ቁጥር ሶስት "
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ወያኔነታቸው ፣ ከዚህ ሰረገላ
ስልጣን ሀክ ተደርገው ፣ ሲተኩ በሌላ
በአፈሙዞች ራስ ፣ ያስወጣችው ጠብሳ
ኦነግን ጋበዘች ፣ መቀሌ ላይ ምሳ
ጃ ያስተሰርያል ፣ ጃ ያስተርያል
ጃ -war አደራጅቶ ፣ ቤተ እምነት ያጋያል
አክቲቪስቱን ረግሞ ፣ መንግስት ይፀልያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
አስራ ሰባት መርፌው ፣ ሲለቅ በህዝ ቁጣ
አስራ ሰባት ባንኮች ፣ የሚዘርፈው መጣ
እንደ አምናው ባለቀን ፣ ያምናውን ባይቀጣም
ራሱን ካላወጣ ፣ ከተረኞች ጥምጣም
አዲስ ነውጥ እንጂ ፣ አዲስ ለውጥ አልመጣም
ይቅር በለውና ፣ ያለፈውን ወቅሰህ
ድምር አስተምረን ፣ ጨካኙን ቀንሰህ።
ጃ ያስተሰርያል ፣ጃ ያስተሰርያል
ጃ war-አደራጅቶ ፣ ቤተ እምነት ያጋያል
አክቲቪስቱ ረግሞ ፣
ለህዝቦቹ ሰላም ፣ መንግስት ይፀልያል
።።።።
እስቲ ተደመሩ ፣ እርስ በእርሳችሁ
እናንተን እያየ ፣ ህዝብ ይማርባችሁ
አንድ ሀገር አድኑ ፣ በልዩነታችሁ
አለበለዚያማ
በምን ያስታውቃል ፣ እንዳልቀነሳችሁ?
።።።
አቤት ስቃይ ፣ አቤት ጠኔ
ኡንዱ ኬኛ ፣ ሁሉ የኔ
አልቅሰን ሳናባራ ፣ በወያኔ
እዚ ደግሞ ፣ ሌላ ትኩሳት
ለአንዱ ጨክኖ ፣ ለአንዱ መሳሳት
ወዲህ አፈናቃይ ፣ ወዲያ እድሳት
ወገኔ አለቀ ፣ በዘረኞ እሳት
እሳት
እሳት
እሳት
ኧረ አይነጋም ወይ ኢትዮጵያዬ


@getem
@getem
@getem
እባክሽ!!!!!
(ልብ አልባው ገጣሚ)


ታከተኝ እምዬ
ጣና ዳር ተቀምጦ ንጹህ ውሃ መጠማት
ጥቁር አፈር ኖሮኝ
ለካናዳ ስንዴ ሰርክ እጄን መዘርጋት
ለባእዳን ደስታ
የጭንቄን ተካፋይ ወንድሜን መዋጋት
አቃተኝ ሀገሬ
ኮሽ ባለ ቁጥር በምን ሰበብ መስጋት፡፡

እናም ስጦታዬ
ክብርሽ ወዲያ ሆኖ ወዲህ ስብሰለሰል
መጥፋቴ ነውና
ህልሜን የሚጋራ አጥቼ እኔን መሰል
ማበዴን ሳትሰሚ
እባክሽ ንቂና
ተባልተን ሳናልቅ ልጆችሽ እንብሰል፡፡

@getem
@getem
@getem
#የላይ ሰፈር ስሌት!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።
የጨመቅነው እንባ ፥ ከምድር ወረደ
ጠሀይ ስትበረታ.. .
ዳግም ለመዳመን ወደ ሰማይ ሄደ
ላስለቀሰን በዳይ...
ቀዝቃዛ ውሀ ሆኖ ፥ ገላውን አበረደ።
ይሄ የኛ በዳይ..
መርዝ እየጋተን ፥ ወተት እየሰጠ
ላስቲክ ለመለጠፍ ፥ ቆዳ እየላጠ
ህመም ሲሆንብን ፥ ኪኒን እየሸጠ
አመፁ ለማለት ራሱ እያመፀ
ቀብሮ ባፈረሰው...
የስጋችን አፈር ፥ ጎጆውን አነፀ።

@getem
@getem
@paappii
ለምሽታችን እራት💚 የምትሆን ሸጋ ግጥም እንካቹ


-ግም ህይወት ግም ኑሮ
ሰምሮ ያልሰመረ
አምሮ ያላማረ
ሽንቁራም ሸንከሎ
ሲያፈስ ሲያጎል እንጂ
ሲሞላ ማን አየው ?
እያለ በቤቱ ሁሉም ረገመው
1968 .ዓ/ም ዶ/ር ፈቃደ አዘዘ

@getem
@getem
@balmbaras
1
አለ የማጠብቀው አለ የምጥለው
የማንጠለጥለው
ኮተት ተሸክሜ..... ብወድቅም ብነሳም
እንኳን ለ ስጋዬ..... ለነብሴም አልሳሳም
ጭራሽ ቃል አልገባም..... ነገን ስለማላውቅ
ምን ይሆናል ብዬ...... አልችልም መጠየቅ
ሲመራኝ ስከተል...... ሲነግረኝ ስ ሰማው
እሱ ራሱን ሰጥቶ..... የኔን ልብ ቀማው
በፍቅር ሰክሬ ስሰግር እየዋልኩኝ
አይችሉ ቻል ሲለኝ ምኑን ችዬ ቻልኩኝ
ያለመሰናክል ሰው ያላንዳች እክል
ማንም ማንም የለም... . የልብን የሚያክል
አጋንንት አውጥቶ.... ስሜ ሞት ላያስጥል
ምን ሊያደምቀኝ ብዬ ግንጥል ጌጥላንጠለጥል
እኔ እንዳሻኝ ልኑር.... እንዳመሌ ልደር
ወዳጆቼም አዩኝ... በቅኔ ስሰደር.....
አዳኝ ቆንጥር ፈርቶ.. ጭቃ ተጠይፎ
አይወረወርም..... ቀስቱ ደጋን አልፎ


ሙሉጌታ ተስፋዬ ❤️❤️ ትንግርቴ

@getem
@getem
@balmbaras
ሙስጠፋ ለገዱ እንደዚህ እያለ በጆሮው ነገረው !!!!!!!


ስማኝማ ገዱ ፤
ምንም እንኳን ዛሬ፤
የወሎ አማርኛ ፤
አፌ ባይናገር ለዛውን አጣፍጦ ወዙን አሰማምሮ ፤
ቀብሪ ዳሃር ድረስ ፤
ደገሃቡር ጎዴ ፤
ደሙን ያፈሰሰው፤
ጃውሳው ወሎየ ፤ የነገረኝ እውነት አልጠራጠርም ይሰማል ለቀልብህ ይደርሳል ለጆሮ ።
የዚያድ ባሬ እብሪት ፤
በጦቢያ ምድር ላይ ዘርቶ ሲያስነቅለን የስስት ገበሎ ፤
ያነደደው እሳት ጅጅጋ ላይ ሲነድ በሞት ተጠቅልሎ ፤
ጀግና የጦቢያ ልጅ ፤
በእናት ሃገር ቁጭት ካስመራ እስከ ጎዴ ሲነሳ ሆ ብሎ፤
ያ ኩሩ ሃበሻ ፤
አዋሽ ከወንዙ ዳር ፤
ጦቢያ ከምትሞት እኔን ያስቀድመኝ ብሎ እያለቀሰ በእንባው ተማምሎ ፤
እስከሞት ኮረብታ ሃገሬን እያለ ባንዲራውን አንቆ በልጅጉን ወልውሎ ፤
ገበረ ህይወቱን ተሰዋ ያ ጀግና፤
ገንጣይና አስገንጣይ የጀግኖቹን እናት አይወስዳትም ብሎ ።
የጅግጅጋ አርበኛ ፤
የቀብሪዳር ዘማች ፤
መሬው አማራ ጋር ፤
ደሙ ከደሙ ጋር ፤ በአሸዋው ተሳርጎ ባንድ ጅረት ወርዶ ነፃነት ሲሰራ ፤
ያ የጫካው ንጉስ ፤
ደገሃቡር ማዶ ፤
ወንድሜን ሲነኩት እኔን ነው የሚያመኝ እያለ ሲያቅራራ ፤
በጥይቱ መሃል ባንዲራዋን ሳመው በቁስሉ እየሳቀ በሞቱ እየኮራ ፤
ያነ የዱር አውሬ ፤
ወራሪ ሚበላ ባንዳ ሚዘነጥል ፎክሮ እያቅራራ ፤
እኔ ልሙትልሽ የሚላት ሃገሩን ስሟን እየጠራ ፤
ቀርቷል በየሜዳው ስጋው አፈር ሆኖ ጎዴ ካራማራ ።
ለዚህ ነው ገዳችን ፤
ጆሮህ ስር ገብቼ ፤
ጠረንህን ስቤ የማንሾካሹከው ይሉኝታን ሳልፈራ ፤
ጎዴ ከወንዙ ዳር ፤
ጅጅጋ ሜዳው ላይ ፤ ባሩድ እያጨሰ ደሙን እያዘራ ፤
ላንዲት ሃገር ክብር ለጦቢያነት ማእረግ ለጀግና ባንዲራ ፤
መሆኑን ባውቅ ነው ፤
በደም የተኳለ ቃልኪዳን መፃፉን ፤ ሶማሌና አማራ ።

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
/★ተስፋ★/
/★ካሊድ ሁሴን★/

ብርሀን ውስጥ ጨለማ አ‘ለ
ጨለማው ስር ጭል“‘‘‘'ም ያለ
ድቅድቅ ጥቁር ጨለማ አ‘ለ
ከጥቁሩ ስር ቁ"‘ጥር አ‘ለ
ቁ"‘ጥሩ ላይ ውሉም አ‘ለ
ዉሉ ጫፍ ላይ ው“ል ካለህ?
ከው“ሉ ፊት አንተ ካለ‘ህ?
ተስፋ አትቁረጥ
ጨለማህ ውስጥ ብርሀን አለህ!!!።

@getem
@getem
@getem
ከሞት ጋር ተቃጥረን
ከሞት ጋር ተቃጥረን፥ የቆራጥ ቀጠሮ
ካምናም ብሶበታል ዘገየ ዘንድሮ።
ወትሮም እንዲህ ነዉ የአበሻ ቀጠሮ !!
ሞት ለካ አበሻ ነዉ ?!
ግና ምን ሆኖ ነዉ ?
እንዴት ቢንቀኝ ነዉ ?
እንዴት ቢፈራኝ ነዉ ?
መንገዱ ረዘመ ወይ መንገዱ ጠፋዉ ?
የህይወትን አጥር፥ ዳር ዳሩን ይዞራል !
ዕድሜን ደጅ ይጠናል።
ሞትም እንደሰዉ ልጅ ቀን ይጐድልበታል ?
በለስ የቀናት ለት
ህይወት እንደዚህ ናት
ሞትን መገነዣ፥ ስዉር ስፌት አላት !!
--------------------------------------------
ነብይ መኰንን💚💛❤️
ምንጭ : <ስዉር-ስፌት> ፥ ገፅ 114
@getem
@getem
@getem
የወሎ አይነ ኩሌ!!!!!


ወንዛችን ቦርከና ፤ እርሻችን ታች ቃሉ ፤
የወሎየን ፍቅር ፤
እንኳን ያደም ልጆች ፤ ወፎቹም ያውቃሉ ።
መገን ጃኖ ሙሄ ፤
መድሃኒቴ እኮ ናት እንደዳማ ከሴ ፤
ባይሆን ተቸገርኩኝ ፤
ቤቷ ጨፋ ሆኖ ፤ አልጋዋ ከሚሴ ።
አገሯ ወሎ ነው ፤ ደወይ ራህማቶ ፤
ልዘይር እያለ ፤
ሁሉም ቀልጦ ቀረ ፤ ከማጀቷ ገብቶ ።
በአንቻሮ በገዳም ፤
ካንጀቴ የገባች ፤ አንዲት ኮረዳ አለች ፤
ሃርቡ ተሜዳው ላይ፤
ልቤን ወሰደችው ከረሚሌ ዳማ ሽቱ ብሬ እያለች ።
ይሻለኝ እንደሆን ፤
ይቀለኝ እንደሆን ፤
በደዋ በጨፋ ፤አምጧት ፈልጋችሁ ፤
አልከጀለች እንደሁ ፤
ሶደቃ ላኩልኝ ከንፈሯን ቆርሳችሁ ፤
አለበለዚያማ ፤
ካቲማየ ፈርሶ ፤
ጅስሜ ተደባልቆ እንዳልሞትባችሁ ።
ስንቱን በውጅግራ ፤
ስንቱን በምንሽር ፤ ገድለን ስናበቃ ፤
ጃኖየ መሃመድ ፤
እኛን ገደለችን ፤
በእርጎ ዳማይ ጥርሷ ፤ ከምከም ብላ ስቃ ።
በዚህ በኛ መንደር፤
ኸልቁን የሚፈጀው ረሃብ ነበረ ፤
ጉድ አጃኢብ በሉ፤
በቃሉ በአንቻሮ ከንፈር ሰው ገደለ ።
ሞይዘሬን ባነግት ፤
ዝናሬን ብታጠቅ ፤
ፊትም አልሰጠችኝ ፤ ኧረ መቼ ሰምታ ፤
እኔም መለኛ ነኝ ፤
መዳኒት አውቃለሁ ለመውደድ በሽታ፤
በገታ በመጂት ፤
ወዳጃ አስገብቼ ፤ ወሰድኳት ባንዳፍታ ።
ኧረ መጂት መጂት ፤ ኧረ ገታ ገታ ፤
ታስሮ የከረመው ፤ በመውደድ በሽታ ፤
ዱኣ ያስደረገ፤
ቱፍታ የደረሰው ስንቱ ጎበዝ ሻረ ስንት ሰው ተፈታ ።

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
👍2
" አንቺን "
( በአምባዬ ጌታነህ )
የዝናቡ ግምግምታ
ብልጭ ጓ ድርግም ሲል፣
ልቤ በሀሴት ሲርድ
አንችን መስሎኝ የሚጥል፣
ከእልፍኝ ጎጆየ ሳልወጣ
መደቤ ላይ ተቀምጨ፣
በበረዶው ቅልቅል ዝናብ፣
ቀየየ አንችን መነጨ።

ደግሞ ከቤቴ ወጥቼ
ከባድማው ተለይቼ
የወረድኹ እንደሁ
ወንዝ ላይ፣
ሽቅብ ከክትካታው ስር
ለምዱን አርጎ ከጀርባው ላይ፣
እረኛው በዋሽንቱ
ከገደሉ አፋፍ ሆኖ
ሲያንጎራጉር ሲቀኝ ባይ፣
የእምባዬ ግት አስቸገረኝ
በትዝታ ተዋጥኩልሽ
ዜማው የአንቺ መሰለኝ።
አይኖቹን ክድን ግልጥ
ትንፋሹን ቀነስ ጨመር፣
ከዋሽንቱ ቀዳዳ ላይ
መሀል ጣቱን ከሌባ
ጣት ሲቀያይር፣
ባየው ከታች ሽቅብ እሱን፣
ይወስድሻል ያመጣሻል
ይሳሳሻል ሲቀኝ አንቺን።

SHARE & JOIN

👇👇👇👇👇
@amba88
@getem
@getem
ምን አለ ብንተክል ፣
ምን አለው ቢተክሉትስ ፣
የተፈጥሮን ግብር ሀቂቃን አንፍራ
ዛፍ እንደሰው አይደል በተካይው ሃሳብ ነገር አያፈራ።

(( መሀመድ ሙፍቲ ))💚💛❤️

ሸጋ ጁምኣ!!💚

@getem
@getem
👍1
#ለምን_እንዳትይኝ

የሚያምር ስብእና
እንደ ውብ አበባ የሚማርክ ገላ
የሰው ውሃ ልኩ
ሁለመናሽ ሙሉ ሌላን የሚያስጠላ
አንቺን ባየሁ ቁጥር
ውስጤ ቢከብደውም ራሴን ተጠይፌ
ስተክዝ ውላለሁ
አይንሽን ለማየት ዘወትር ከደጃፌ
ግና ምንም ያህል
ከራሴ አስበልጬ አንቺን ብወድሽም
ካየሁሽ በቂ ነው
ሺ ዘመን ላፍቅርሽ እኔ አላገባሽም፡፡

ለምን እንዳትይኝ !
ሳላይሽ አልደር
አይምሽብኝ ቀኑ አይንጋ ለሊቱ
እጆችሽን ይዤ
ዶፍ በላዬ ውረድ አትውጣ ጠሃይቱ
አየሽልኝ አይደል
የመውደዴን ልኬት የፍቅሬን መስፈርያ
ሕይወቴ የምልሽ
ያድርግሽ የምለው የሴት መጀመሪያ
እኔ አንቺን ያወቁት
ትላንት ወይም ዛሬ ቀኑን ባልነግርሽም
ስወድሽ ስወድሽ
የድሜ ጀምበር ትጥለቅ አኔ አላገባሽም፡፡

ለምን እንዳትይኝ !
ሳላገኝሽ በፊት
ድምጽሽን ሳልሰማ ሳትሆኝ አጠገቤ
አቅሜን አውቀዋለሁ
ምግብ እያላመጥኩ ይጠናል ረሃቤ
ብቻ እኔ አላውቀውም
ምንሽን እንደሆን የወደደው ነፍሴ
ከአጠገቤ አትራቂ
ያሻሽን አድርጊኝ አልጣሽ ከራሴ
ይሄን ሁሉ ብዬ
እያሞጋገስኩኝ አለሜ ብልሽም
ለፍቅሬ አይመጥንም
ምን አባቴ ላድርግ እኔ አላገባሽም፡፡

ለምን እንዳትይኝ !
ገንዘብ ሃብት ዝና
አለማዊ ነገር ካንቺ ዘንድ ሳይጠፋ
ነፍስሽን የሰጠሽ
ታትረሽ የምትኖሪ በፈጣሪሽ ተስፋ
ማንም ያልተቸረው
እውቀት እና ጥበብ ከአካልሽ ውበት ጋር
ልብሽ ፍቅር ያዘንባል
ጌታ ባረፈበት በመስቀሉ ችንካር
ይሄ ቢሆን እንኳን
በመውደዴ መስፈርት ንግስት ብትሆኚም
ሳከብርሽ ልኑረው
አንቺ ብትወጂኝም እኔ አላገባሽም፡፡

ለምን እንዳትይኝ !
ሰው በዙሪያሽ ሳለ
በሄድሽበት ሚሄድ አጃቢሽ ቢበዛ
ከራሱ አስበልጦ
ስላንቺ ቢለፍፍ ወሬውን ቢነዛ
ፍቅርን የሚያስተምር
ሺ መፅሃፍ ቢገለጥ ቢኖረው ሰባኪ
እኔን አይገባኝም
ቃላት አይገልፅሽም አንቺ ተባለኪ
ጉዳዬ አይደለም
ስጋዬ እና ነፍሴ አንቺን ቢያፈቅሩሽም
ብቻ ከአቅሜ በላይ
ሳፈቅርሽ ልኑረው እኔ አላገባሽም ፡፡
ለምን እንዳትይኝ !

#እንደራሴ

(Kibrom G Mariam)


@getem
@getem
@getem
👍1
ህይወት የእኔ ኬላ

(ቡሩክ ካሳሁን)

እንቅልፍና እረፍት ድካም በማያውቁ
እጅግ በጣም ጥንቁቅ እጅግ በጣም ንቁ
ጠባቂዎች ባላት በህይወቴ ኬላ
ደና ነገር ይዤ ማለፍ ቸግሮኛል ወዴት ላግኝ መላ?

@getem
@getem
@burukassahunc
ለቅዳሜታችን እንካቹ ማኪያቶ😍

አስቴር አወቀ ውድድ የሚለው ዘፈኗን አደመጥኩት ። የወሎየን የፍቅር ሃድራ
ተገማሽራበታለች ። ሸግየ ነው ። እንዲህ ያለም የለ ።እኔ ደግሞ እንዲህ ገጠምኩ፤


ከሩቅ የሚታየው እንደ አዝማች ባንዲራ ፤
የውድመን ጉብል የየጁ ቀብራራ ፤
በጀማው መሃከል ያ ስሙ ሲጠራ፤
አበረረኝ ደግሞ ጎብየና ሃራ ።
ወንዛቸው አላውሃ እርሻቸው አይገብር ፤
ወይ እሱ አይመጣልኝ እኔ ወይ አልሶብር ፤
ሂጅ ሂጅ ይለኛል፤ ብርርር ብርርር፤
ሲያሻኝ ጥቁር ውሃ ሲያሻኝ ዶሮግብር ።
ቅኔ ነው እያሉ ፍቺው የማይላላ፤
መጥሃፍ ነው እያሉ ፊደሉ እማይገራ፤
ፍቺው ቢጠናብኝ ፤ቢቸግረኝ መላ፤
ቅኔ ፍቱ ብየ፥ ሙጃ ማርያም ገባሁ መቄትና ዋድላ ።
የአባቱ ሃገር የጁ የእናቱም ራያ፤
ያደገው ውድመን ርስቱ ወልድያ፤
ጥንቅሹን መቻሬ ሲኮረሽም አድጎ፤
ያ የፍቅር ወተት ያ የፍቅር እርጎ፤
ልግመጥሽ እያለ ወሰደኝ ኩማንዳ አገባኝ አዳጎ ።
ኧረ ተንታ ተንታ ኧረ በሽሎ በሽሎ፤
ውድድ በባቲ ውድድ በወሎ ፤
ሰው እንዴት ይፀድቃል ሰው በፍቅር ገድሎ።
ያባቶቹ መንደር አይና ቡግና ነው፤
ወዶ ያበደ ሰው ርሃብተኛ ነው፤
አይኑን ብቻ አይቼ ይቅርብኝ ገላው፤።
ውድድ ነው ገላው ፍቅር ነው ከንፈሩ ፤
ደግሞ ተነሳብኝ ስሙን ስትጠሩ፤
ሰው ነው መዳረሻው ፤ ፍቅር ነው ድንበሩ፤
ከመዋደድ መንደር ወሎ ነው ሃገሩ ።
የራያው ጢነኛ የወሎ ጃውሳ፤
ዘለቀ ይሉኛል በቃሉ በመርሳ ፤
ውድድድ አረገኝ በሱ የተነሳ ።
ዋድላና ደላንታ ሂመኖ ቦረና፤
ልጃችሁን ስጡኝ ባንድ እግር ልምጣና፤
እንደ ወሎ ውድድ አልተገኘምና ።
እንደ ልጅ ኢያሱ ግርማው የሚያስፈራ፤
አምጡልኝ ያንን ልጅ በጠሎት በሃድራ፤
ጀባ በለኝ ወሎ በል አርገኝ ሙሽራ፤
ቢጎርሱት አይሰለች ወሎየና እንጀራ ።
ውድድ ውድድ ውድድ አምባሰል፤
ህመም ነው በሽታ ያልናፈቁ መምሰል።
ወጣሁኝ አምባሰል ፤ ሂጄ ነበር ጎልቦ ፤
አመለኛው እግሬ ያን ሸጋ ተርቦ ።
የለም አልተገኘም፤ አልተያዘም እግሩ፤
ዘበናይ ወሎየ ፤ ያበረኛል ፍቅሩ፤
ያዥለት ብላችሁ፤ ለጊሸን ተሳሉ።
አልቡኮ ነው ቤቱ ጀማ ነው ንጉሱ፤
እንደ አባ ጀቦ ቤት ያስካካል ፈረሱ፤
ውድድ ነው ምሳው ውድድ ነው ቁርሱ፤
እንዴት ነህ በሉልኝ ደሴ ስትደርሱ ።

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️


የሚለውን ግጥም ውድድ በሚለው ዜማ ስታቀነቅነው በአይነ ልቡናየ አሰብኩት ።
እናንተም ይህንን ግጥም በሷ ውድድድድ ዜማ ውስጥ ጥመቁና ጠጡ ። እኔ ግን
ግጥሙንም ዜማውንም ገመጥኩት ።

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
ፍቅሯ ቀለል ሲል...

ነገሰ በቀለ (ናኒ)
........................

ፍቅሯ ቀለል ሲል፦እሱዋን አዘዘብኝ ልታንገላታኝ ነው
አለ ያ ገጣሚ ምን ማለት ፈልጎ መሆኑን ባላውቅም🤔
.
.
ፍቅሯ ከቀለለ እሱዋ ምን ልትብጅው?
የዚን ጥያቄ ምልስ
ሆድ ይፍጀው ሆድ ይፍጀው

ብዬ ሳልደመድም 1 ነገር ታየኝ
ለገላዋ እንጂ ለፍቅሯ ግድ የለኝ
የሚል መልስ ሰጠኝ።

ታድያ ለገላዋ ምን ግጥም አፃፈው
ሞልቶለት የለወይ ህሊናው ካዘዘው
ስሜቱ ካሰኘው😏
ነይ ቆንጆ ወደዚ ጠጋበይ.ልጋብዝሽ
ጠጪ እንደፈለግሽ🍾🍷🍺🥃
እኔጋር ተቀምጠሽ
ቤቱንም እንቀይር አንቺን ከደበረሽ?
ብሎ እየጠየቀ
በ ጡት በዳሌዋ እየተደነቀ😋
አንድ ሁለት እያለ
ስሜቱ እየጋለ
በሙዚቃ በዳንስ በሲጋራ ባ'ልኮል
በሴት ዳሌ'ና ቂጥ እየተማለለ
ያቺን አብሩዋት ሊያድር
ሊገዛት ያላትን ሴት እያታለለ🌺🤑
ነይ ጠጋበይ እስኪ
በጆሮሽ ልንገርሽ
ስንት ነው የምትይው
ለዛሬው አዳርሽ???

ያጠረ ቀሚሱዋን ..
ወደላይ በማሸሽ
እሷም ስትመልስ የአንድን ምስኪን
ደመወዝ እስክነ አበሉነው የምትጠይቀው..
እሱም ለሴት እንጂ ለገንዘብ አይጨንቀው፧
ታድያ ምን ዋጋ'ለው
ካደረ ነው እንጂ የዛኔ አያውቀው

የሚስቱን መጨነቅ የልጆቹን ማዘን
እንዴት ይታወሰው🤔
የወሩን አስቤዛ እዚ እያፈሰሰው፤

ታድያ በጥዋቱ ከ'ንቅልፉ ሊነቃ
ብንን እንዳለ...
የማታው ጭፈራ ያ ሁሉ ሁካታ🎤
ከወደየት አለ🤔

አቤት🙊 የሰው ቅሌት
አቤት የሰው ውርደት🙈

ቀና ሲል ወደላይ
የኮርኒሱ ማማር የአምፖሉ ድምቀት👁👁

የቤቱ አቀማመጥ ያ'ለመደው ነገር
ይሆንበትና👦
አሁንም ተኝቶ😴አሁንም ለመንቃት
ሲያስብ እንደገና...

በል ተነስ እንውጣ ብላ አባነነችው
ያቺ ይዟት ያደረው ብሏት እንዝናና



አላለቀም...............
እናንተው ጨርሱት👍


@getem
@getem
@getem
1👍1