‘እኔ እና ቤቴ’
(መላኩ አላምረው)
...
‘ቤቴ’ የኪራይ ናት፡-
ከወር ደመወዜ፣ በወር ምታስከፍል፤
‘እኔ’ ስደተኛ፡-
በገዛ ሀገሬ፣ ‘ለገዛ ወገኔ’፣ ለቤት የምከፍል፤
ይኸው በኑሯችን፡-
‘ቤቴ’ን አላምናትም፣ እርሷም አታምነኝም፣
አብረን እንኑር እንጂ፡-
‹በየኔ ነው ስሜት›፣ ከቶ አንገናኝም፡፡
በእርሷ አልፈርድባትም፡-
ድሮስ ስደተኛን፣ ማን አምኖ ያኖራል?
በእኔም አትፍረዱ፡-
የራስ ያልሆነን ቤት፣ ማን አምኖ ይኖራል?
ይህን እናውቃለን፡-
ፈጽሞ እንደማንችል፣ መኖር ተለያይቶ፣
እንዴትስ ይኖራል?
ቤት ሰው አልባ ሆኖ፣ ሰውም መኖሪያ አጥቶ፤
ዘመናችን ይህ ነው፡-
አብረው እየኖሩ፣ አለመተማመን…
ቆይ ግን ምን ነክቶናል?
መለያየት ማንችል፣ አብሮነት ያመመን?
@getem
@getem
@gebriel_19
(መላኩ አላምረው)
...
‘ቤቴ’ የኪራይ ናት፡-
ከወር ደመወዜ፣ በወር ምታስከፍል፤
‘እኔ’ ስደተኛ፡-
በገዛ ሀገሬ፣ ‘ለገዛ ወገኔ’፣ ለቤት የምከፍል፤
ይኸው በኑሯችን፡-
‘ቤቴ’ን አላምናትም፣ እርሷም አታምነኝም፣
አብረን እንኑር እንጂ፡-
‹በየኔ ነው ስሜት›፣ ከቶ አንገናኝም፡፡
በእርሷ አልፈርድባትም፡-
ድሮስ ስደተኛን፣ ማን አምኖ ያኖራል?
በእኔም አትፍረዱ፡-
የራስ ያልሆነን ቤት፣ ማን አምኖ ይኖራል?
ይህን እናውቃለን፡-
ፈጽሞ እንደማንችል፣ መኖር ተለያይቶ፣
እንዴትስ ይኖራል?
ቤት ሰው አልባ ሆኖ፣ ሰውም መኖሪያ አጥቶ፤
ዘመናችን ይህ ነው፡-
አብረው እየኖሩ፣ አለመተማመን…
ቆይ ግን ምን ነክቶናል?
መለያየት ማንችል፣ አብሮነት ያመመን?
@getem
@getem
@gebriel_19
ደሴና ሸጋ ልጅ ፤ክረምትና ደሴ!!!!!!
መንበረ ፀሃይ ላይ፤
አይጠየፍ ጋራው፤
ከሚካኤል ቀዬ፤
ኢያሱ ሚካኤል፤
እግሩን እንዳይበርደው፤
ብቻውን ሲያመሽ፤
ጃኖ ደርቤለት፤
በርኖስ ቀጥየለት፤
ሸዋ በር በታች ተቀምጬልሽ፤
እኔን ቆፈን ፈጀኝ፤
እኔን ብርድ ቆጋኝ፤
አንች ቦለቂያ፤ ብርጉድ እየሞቅሽ።
እትትትትት እትቱ በረደኝ፤ ካለሁበት ቦታ፤
ወይ መጥተሽ አልሳምሽኝ፤ አላክሽልኝ ኩታ፤
ያንዘፈዝፈኛል፤
ክረምትና ናፍቆት፤ ብርድና ትዝታ።
ብርድ ነው እያሉ፤
ውርጭ ነው እያሉ፤ ድዴን ያደረቀው፤
ለካስ መቅረትሽ ነው፤
የአንገትሽን ግርጌ፤ መሳም የናፈቀው።
ጦሳን ያህል ጋቢ፤
ጀሜን ያህል ኩታ፤
ዳውዶን ያህል ጃኖ፤
አረብ ገንዳን ያህል፤
የተንተረከከ የመከከ ከንፈር፤ ቤት አስቀምጠሽ፤
መንበረ ፀሃይ ላይ፤
የሚካኤል አሽከር፤
ዘብ ልጠብቅ ብዬ፤ እኔ ሞትኩልሽ።
ሀኪሞቹ ሁላ፤
ብርድ ነው እያሉ፤
ውርጭ ነው እያሉ፤
ቆፈን ነው እያሉ፤ የያዘኝ በሽታ፤
መገን እርጎ ሙሄ፤
ያሽርህ ልትለኝ፤
ታቹን ከሳላይሽ፤ ካገር ግዛት መጥታ፤
ገምሸርሸር ብትል፤ አንገቴ ስር ገብታ፤
ጅስሜ ተሟሟቀ፤ ወገቤ ተፈታ።
በክረምት ቆፈን፤ በደሴ ሰማይ፤
የሸጋ ልጅ ትንፋሽ፤ ይጠገባል ወይ????
((ጃ ኖ)))💚💛❤ በአበራ ሞላ style
@getem
@getem
@balmbaras
መንበረ ፀሃይ ላይ፤
አይጠየፍ ጋራው፤
ከሚካኤል ቀዬ፤
ኢያሱ ሚካኤል፤
እግሩን እንዳይበርደው፤
ብቻውን ሲያመሽ፤
ጃኖ ደርቤለት፤
በርኖስ ቀጥየለት፤
ሸዋ በር በታች ተቀምጬልሽ፤
እኔን ቆፈን ፈጀኝ፤
እኔን ብርድ ቆጋኝ፤
አንች ቦለቂያ፤ ብርጉድ እየሞቅሽ።
እትትትትት እትቱ በረደኝ፤ ካለሁበት ቦታ፤
ወይ መጥተሽ አልሳምሽኝ፤ አላክሽልኝ ኩታ፤
ያንዘፈዝፈኛል፤
ክረምትና ናፍቆት፤ ብርድና ትዝታ።
ብርድ ነው እያሉ፤
ውርጭ ነው እያሉ፤ ድዴን ያደረቀው፤
ለካስ መቅረትሽ ነው፤
የአንገትሽን ግርጌ፤ መሳም የናፈቀው።
ጦሳን ያህል ጋቢ፤
ጀሜን ያህል ኩታ፤
ዳውዶን ያህል ጃኖ፤
አረብ ገንዳን ያህል፤
የተንተረከከ የመከከ ከንፈር፤ ቤት አስቀምጠሽ፤
መንበረ ፀሃይ ላይ፤
የሚካኤል አሽከር፤
ዘብ ልጠብቅ ብዬ፤ እኔ ሞትኩልሽ።
ሀኪሞቹ ሁላ፤
ብርድ ነው እያሉ፤
ውርጭ ነው እያሉ፤
ቆፈን ነው እያሉ፤ የያዘኝ በሽታ፤
መገን እርጎ ሙሄ፤
ያሽርህ ልትለኝ፤
ታቹን ከሳላይሽ፤ ካገር ግዛት መጥታ፤
ገምሸርሸር ብትል፤ አንገቴ ስር ገብታ፤
ጅስሜ ተሟሟቀ፤ ወገቤ ተፈታ።
በክረምት ቆፈን፤ በደሴ ሰማይ፤
የሸጋ ልጅ ትንፋሽ፤ ይጠገባል ወይ????
((ጃ ኖ)))💚💛❤ በአበራ ሞላ style
@getem
@getem
@balmbaras
[ "የባይተዋሮች ወግ]
።።።።።።።።።።።።።።
ጨረቃዋን ሰብሮ፥ነጎድጓደ ወረደ ፥
መሬት ተርበድብዳ ፥መሰረቷ ራደ።
እንኳን ዝናብ ያህል ፥ ነጎድጓድ ታክሎ
ከብዶኛል ውድቅቱ፥
በላይ ተጭኖ ፥ ልክ እንዳክንባሎ።
ልክ እንዳክንባሎ ፥
ምጣድ እኔነት ላይ ፥ ክንዱን ያበረታል
ሸክም የከበደው፥
የኔ አይነት ድኩም ሰው ፥ መች ታግሎ ይረታል።
መች ታግሎ ይረታል፥
ሕይወት ምድጃ ላይ ፥ ተጥዶ መንቀልቀል
ላልተቦካ ቡኮ፥
ለማይሰፋ ሊጥ ፥ በ'እሳት መቀቀል።
በእሳት መቀቀል ፥
በሀሳብ ወላፈን ፥ በሰው እቅፍ ናፍቆት
ሌት ተቀን መበረድ ፥
ልብስ መሀል ሁኖ ፥ መገፈፍ መራቆት።
መገፈፍ መራቆት ፥
ነጠላነት ውሉ ፥ ብቻነት መቅኑ
የትራሱ ላይ ውርጭ፥ ያንሶላው ቅንቅኑ።
ያንሶላው መቀንቀን፥
እንቅልፌን ሰርቆኛል ፥
ጅራታም ሌሊት ስር ፥ ሀሳብ እየፈተልኩ
በምኞቴን ዳና ፥
እየተቅዘመዘምኩ ፥ እየተክተለተልኩ
እየተክተለተልኩ ፥
በማይመልስ መንገድ ፥
ስነጉድ ስነጉድ ፥ ማጣቴን እያማሁ
በግርግዳዬ ስር፥
ሰርስሮ የገባ ፥ አንድ ድምጽ ሰማሁ።
አንድ ድምጽ ሰማሁ፥ ትኩረቴን የሚሰብ
ጆሮዬ የሚያስጥል ፥ ቀልቤን ሚሰበስብ።
ከኔ ኩታ ገጠም ፥ ግርግዳ ሚጋራኝ
በአስፈሪው ሌሊት ፥ በክራሩ አወራኝ።
በክራሩ አወራኝ፥
የማያውቀኝን ሰው ፥ በቅኔው ነካካኝ
አላወቀም እሱ፥
ሕመሙን ሲያስታምም ፥ ቁስሌን እንደነካኝ።
(ቁስሌን እንደነካኝ፥
የጋራ ግርግዳ ፥ ብቻ እንዳልተጋራን
አልገባውም እሱ፥
እኔንም እሱንም ፥ ሌሊቱ እንዳስፈራን።
ሌሊቱ እንዳስፈራን፥
መንታ 'መም እንዳለን ፥
ቢረዳማ ኖሮ ፥ እንዲህ ባልተቀኝ…
"አልጋው አያስተኛ ፥ ናፍቆትሽ በቅሎበት
ሰማዩ አያባራ ፥ ብሶት ገንፎሎበት
እኔ ያንቺ ነዳይ ፥ የፍቅርሽ ምንዱባን
ልክ እንደሰማዩ ፥ አነባሁ ዕንባን"
ሳላስበው ድንገት፥ ግርግዳ ደቅቼ
የምኞት መንገዴን ፥ ለአፍታ ገትቼ
ስንኝ አቀበልኩት፥
አነባለሁ እንባ፥
ውድቅቱ አስፈርቶኝ ፥ የሰው እቅፍ 'ርቦኝ
አያሳዝንም ወይ፥
ሚዘረጋ ሳጣ ፥ እልፍ ክንድ ከቦኝ።
ክራሩን ገረፈ፥
ከትዝታ መንደር ፥
ተስፈንጦሮ ወጣ ፥ አግባባን ቅኝቱ
ብቻነትን ገሶ፥
ቅኔ አቀባበለን ፥ ስሜት ቁርኝቱ።
እንዲህ ሲል ቀጠለ……
እልፍ ክንድ ከቦኝ፥
ደመና ለብሼ
ቆፈንን ታጥቄ ፥ ውርጭ ሳገለድም
ህመምሽ ቢገባኝ፥
የሄደ አልናፍቅም ፥ ከነጎደ አልነጉድም።
ይለኛል ወዳጄ፥
ምስኪን ጎረቤቴ ፥ ትራስ አቅፎ አዳሪው
የማይመጣ ቀጥሮ፥
ሚጠብቅ እንደኔ ፥ ከምኞት ጋር ኗሪው።
እንዲህ አቀበልኩት።
ከነጎደ አልነጉድም ፥
ብለህ ራስህን ፥ በከንቱ አትውቀሰው
በፍቅር የከበረ ፥ በፍቅር ነው ሚያንሰው።
ሰገር ጦር ሰብቄ፥
ባልፎክርም እንኳን ፥ እንደባለ ገድል
ስንቱን በፍቅር ቀስት፥ ኑሪያለሁ ስገድል።
ዛሬ ተራ ደርሶኝ፥
መውደድ መቀናጆ ፥ ከሩቅ ሰው አጠምዶኝ
ሲያስለቅሰኝ ያድራል ፥ ናፍቆት አቆራምዶኝ።
ይልቅ ባለክራር ፥ ምስኪን ጎረቤቴ
እንካ አንዲት ቅኔ ፥ለቤትህ ለቤቴ።
ናፍቆት አቆራምዶት፥
ህመም አቅፎ ሚያድር ፥ ከብርዳም ማክዳው
ማፍረስ ስላቃተው፥
እየከለለው ነው፥ "ሕይወትን" ግርግዳው።
ይገባሃል መቼም!!
#Dagim_Hiwet
@getem
@getem
@gebriel_19
።።።።።።።።።።።።።።
ጨረቃዋን ሰብሮ፥ነጎድጓደ ወረደ ፥
መሬት ተርበድብዳ ፥መሰረቷ ራደ።
እንኳን ዝናብ ያህል ፥ ነጎድጓድ ታክሎ
ከብዶኛል ውድቅቱ፥
በላይ ተጭኖ ፥ ልክ እንዳክንባሎ።
ልክ እንዳክንባሎ ፥
ምጣድ እኔነት ላይ ፥ ክንዱን ያበረታል
ሸክም የከበደው፥
የኔ አይነት ድኩም ሰው ፥ መች ታግሎ ይረታል።
መች ታግሎ ይረታል፥
ሕይወት ምድጃ ላይ ፥ ተጥዶ መንቀልቀል
ላልተቦካ ቡኮ፥
ለማይሰፋ ሊጥ ፥ በ'እሳት መቀቀል።
በእሳት መቀቀል ፥
በሀሳብ ወላፈን ፥ በሰው እቅፍ ናፍቆት
ሌት ተቀን መበረድ ፥
ልብስ መሀል ሁኖ ፥ መገፈፍ መራቆት።
መገፈፍ መራቆት ፥
ነጠላነት ውሉ ፥ ብቻነት መቅኑ
የትራሱ ላይ ውርጭ፥ ያንሶላው ቅንቅኑ።
ያንሶላው መቀንቀን፥
እንቅልፌን ሰርቆኛል ፥
ጅራታም ሌሊት ስር ፥ ሀሳብ እየፈተልኩ
በምኞቴን ዳና ፥
እየተቅዘመዘምኩ ፥ እየተክተለተልኩ
እየተክተለተልኩ ፥
በማይመልስ መንገድ ፥
ስነጉድ ስነጉድ ፥ ማጣቴን እያማሁ
በግርግዳዬ ስር፥
ሰርስሮ የገባ ፥ አንድ ድምጽ ሰማሁ።
አንድ ድምጽ ሰማሁ፥ ትኩረቴን የሚሰብ
ጆሮዬ የሚያስጥል ፥ ቀልቤን ሚሰበስብ።
ከኔ ኩታ ገጠም ፥ ግርግዳ ሚጋራኝ
በአስፈሪው ሌሊት ፥ በክራሩ አወራኝ።
በክራሩ አወራኝ፥
የማያውቀኝን ሰው ፥ በቅኔው ነካካኝ
አላወቀም እሱ፥
ሕመሙን ሲያስታምም ፥ ቁስሌን እንደነካኝ።
(ቁስሌን እንደነካኝ፥
የጋራ ግርግዳ ፥ ብቻ እንዳልተጋራን
አልገባውም እሱ፥
እኔንም እሱንም ፥ ሌሊቱ እንዳስፈራን።
ሌሊቱ እንዳስፈራን፥
መንታ 'መም እንዳለን ፥
ቢረዳማ ኖሮ ፥ እንዲህ ባልተቀኝ…
"አልጋው አያስተኛ ፥ ናፍቆትሽ በቅሎበት
ሰማዩ አያባራ ፥ ብሶት ገንፎሎበት
እኔ ያንቺ ነዳይ ፥ የፍቅርሽ ምንዱባን
ልክ እንደሰማዩ ፥ አነባሁ ዕንባን"
ሳላስበው ድንገት፥ ግርግዳ ደቅቼ
የምኞት መንገዴን ፥ ለአፍታ ገትቼ
ስንኝ አቀበልኩት፥
አነባለሁ እንባ፥
ውድቅቱ አስፈርቶኝ ፥ የሰው እቅፍ 'ርቦኝ
አያሳዝንም ወይ፥
ሚዘረጋ ሳጣ ፥ እልፍ ክንድ ከቦኝ።
ክራሩን ገረፈ፥
ከትዝታ መንደር ፥
ተስፈንጦሮ ወጣ ፥ አግባባን ቅኝቱ
ብቻነትን ገሶ፥
ቅኔ አቀባበለን ፥ ስሜት ቁርኝቱ።
እንዲህ ሲል ቀጠለ……
እልፍ ክንድ ከቦኝ፥
ደመና ለብሼ
ቆፈንን ታጥቄ ፥ ውርጭ ሳገለድም
ህመምሽ ቢገባኝ፥
የሄደ አልናፍቅም ፥ ከነጎደ አልነጉድም።
ይለኛል ወዳጄ፥
ምስኪን ጎረቤቴ ፥ ትራስ አቅፎ አዳሪው
የማይመጣ ቀጥሮ፥
ሚጠብቅ እንደኔ ፥ ከምኞት ጋር ኗሪው።
እንዲህ አቀበልኩት።
ከነጎደ አልነጉድም ፥
ብለህ ራስህን ፥ በከንቱ አትውቀሰው
በፍቅር የከበረ ፥ በፍቅር ነው ሚያንሰው።
ሰገር ጦር ሰብቄ፥
ባልፎክርም እንኳን ፥ እንደባለ ገድል
ስንቱን በፍቅር ቀስት፥ ኑሪያለሁ ስገድል።
ዛሬ ተራ ደርሶኝ፥
መውደድ መቀናጆ ፥ ከሩቅ ሰው አጠምዶኝ
ሲያስለቅሰኝ ያድራል ፥ ናፍቆት አቆራምዶኝ።
ይልቅ ባለክራር ፥ ምስኪን ጎረቤቴ
እንካ አንዲት ቅኔ ፥ለቤትህ ለቤቴ።
ናፍቆት አቆራምዶት፥
ህመም አቅፎ ሚያድር ፥ ከብርዳም ማክዳው
ማፍረስ ስላቃተው፥
እየከለለው ነው፥ "ሕይወትን" ግርግዳው።
ይገባሃል መቼም!!
#Dagim_Hiwet
@getem
@getem
@gebriel_19
ትርጉም !
(በረከት በላይነህ)
..
"አስቀያሚ፣
አሰጠሊታ ፣
መልከ ጥፉ፤
እንደ ደሀ ቀዬ መስቦችህ የረገፉ!
የማትባል እዚህ ግባ ፣
የሰው ፍራሽ ፣ ማማር አልባ!
ፊተ መአት ፣ ያመድ ክምር!
የጭራቅ ሳቅ ያይጥ ፞ ድምር
ባትታይም የማታምር! !!"
እረ ! ሌላም፣ ሌላም፣
ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ ፤
አቤት ሀሴት ፣ አቤት ደስታ!
ለምን ብትይ?
መልኬ ከሸለመሽ የማይሽር ጥላቻ ፤
ደስታ አሰከረኝ 'ስላየሺኝ' ብቻ
Share for others.
@getem
@getem
@gebriel_19
(በረከት በላይነህ)
..
"አስቀያሚ፣
አሰጠሊታ ፣
መልከ ጥፉ፤
እንደ ደሀ ቀዬ መስቦችህ የረገፉ!
የማትባል እዚህ ግባ ፣
የሰው ፍራሽ ፣ ማማር አልባ!
ፊተ መአት ፣ ያመድ ክምር!
የጭራቅ ሳቅ ያይጥ ፞ ድምር
ባትታይም የማታምር! !!"
እረ ! ሌላም፣ ሌላም፣
ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ ፤
አቤት ሀሴት ፣ አቤት ደስታ!
ለምን ብትይ?
መልኬ ከሸለመሽ የማይሽር ጥላቻ ፤
ደስታ አሰከረኝ 'ስላየሺኝ' ብቻ
Share for others.
@getem
@getem
@gebriel_19
ዘ – ም – ዘ – ም !
በዚያ ሐሩር ምድር፣ በዚያ ጠፍ በረሐ
ከደም ተቆራርጠው የሰው ልጅና ውሃ
ሕይወት ልታከትም ተይዛ ገርገራ
በዘምዘም ጠብታ ሕላዌዋ በራ።
ሃጀር ተራወጠች ሰፍዋና መርዋ
ለአንድ ልጇ ጥማት መች ዛለ ገላዋ
እሪ በል እስማኢል አልቅስ ተንዘፍዝፈህ
በእንባህ ዘለላዎች በል ያዛት ቀስፈህ።
እናት ዓለም ልፊ፣ ወዲህ ወዲያ ቃኚ፤
ያንቺን ጥማት ሽረሽ፣
በአሸዋው ዳክረሽ፣
ለአብራክሽ ክፋይ፣ ለእስትንፋስሽ ባክኚ።
በመካከል ሩጪ፣ በላይ ተራመጂ
ከወደዚህ ማትሪ፣ ደግሞም ከዚያ ሂጂ፤
ጠብቂው በዓይንሽ፣
ፈልጊው በእግርሽ፣
ርሃብ ጥማትሽን ለልጅ ፍቅርሽ ማግጂ።
አንድ! ሁለት! ሶስት! አራት!
ጉልበት እያጠራት . . .
አምስት! ስድስት! ሰባት!
ሕልሟ እየራቀባት …
ቀልቧ እየሳሳባት …
እ – ና – ት!
አቤት እናት!
በዚያ ሐሩር ምድር፣ በዚያ ጠፍ በረሐ
ከደም ተቆራርጠው የሰው ልጅና ውሃ
በዘምዘም አገኙት የነፍስን ፍሰኃ።
በል እስማኢል ጠጣ፣ ሃጀር ሆይ ጥገቢ
ላንቺም ለልጅሽም ዘምዘምን መግቢ።
እፈሽው በእጅሽ፣
አዳርሽው በዓይንሽ፣
ርኪበት በነፍስሽ፣
በአሸዋ፣ በኮረት፣ ከልይው በድንጋይ
የ’ናትነትሽ ጥግ ዝንታለም እንዲታይ።
“ዞሚ!” … “ዝሚ!” … “ዞሚ!” …
ድምፅሽን አሰሚ!
ትውልድሽን ካድሚ።
ተጓዥ መንገደኛው ይረፍ ባንቺ መንደር
“ሻባእ” “ሻባእህ” እያለ መርካቱን ይናገር።
ኃይል ብርታት ይሁን ለመኖርሽ ተስፋ
የጤናሽ ምልክት ይኑር እንዳይጠፋ።
“ዞሚ!”… “ዝሚ!”… “ዞሚ!”
ድምፅሽን አሰሚ!
ዓለምሽን ካድሚ።
_______
2006 E.C
አብዲ ሰዒድ
ለእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለዙልሂጃ ፆም በሰላም አደረሳቹ!!
ሸጋ ጁምኣ!!💚💚💚
@getem
@getem
@balmbaras
በዚያ ሐሩር ምድር፣ በዚያ ጠፍ በረሐ
ከደም ተቆራርጠው የሰው ልጅና ውሃ
ሕይወት ልታከትም ተይዛ ገርገራ
በዘምዘም ጠብታ ሕላዌዋ በራ።
ሃጀር ተራወጠች ሰፍዋና መርዋ
ለአንድ ልጇ ጥማት መች ዛለ ገላዋ
እሪ በል እስማኢል አልቅስ ተንዘፍዝፈህ
በእንባህ ዘለላዎች በል ያዛት ቀስፈህ።
እናት ዓለም ልፊ፣ ወዲህ ወዲያ ቃኚ፤
ያንቺን ጥማት ሽረሽ፣
በአሸዋው ዳክረሽ፣
ለአብራክሽ ክፋይ፣ ለእስትንፋስሽ ባክኚ።
በመካከል ሩጪ፣ በላይ ተራመጂ
ከወደዚህ ማትሪ፣ ደግሞም ከዚያ ሂጂ፤
ጠብቂው በዓይንሽ፣
ፈልጊው በእግርሽ፣
ርሃብ ጥማትሽን ለልጅ ፍቅርሽ ማግጂ።
አንድ! ሁለት! ሶስት! አራት!
ጉልበት እያጠራት . . .
አምስት! ስድስት! ሰባት!
ሕልሟ እየራቀባት …
ቀልቧ እየሳሳባት …
እ – ና – ት!
አቤት እናት!
በዚያ ሐሩር ምድር፣ በዚያ ጠፍ በረሐ
ከደም ተቆራርጠው የሰው ልጅና ውሃ
በዘምዘም አገኙት የነፍስን ፍሰኃ።
በል እስማኢል ጠጣ፣ ሃጀር ሆይ ጥገቢ
ላንቺም ለልጅሽም ዘምዘምን መግቢ።
እፈሽው በእጅሽ፣
አዳርሽው በዓይንሽ፣
ርኪበት በነፍስሽ፣
በአሸዋ፣ በኮረት፣ ከልይው በድንጋይ
የ’ናትነትሽ ጥግ ዝንታለም እንዲታይ።
“ዞሚ!” … “ዝሚ!” … “ዞሚ!” …
ድምፅሽን አሰሚ!
ትውልድሽን ካድሚ።
ተጓዥ መንገደኛው ይረፍ ባንቺ መንደር
“ሻባእ” “ሻባእህ” እያለ መርካቱን ይናገር።
ኃይል ብርታት ይሁን ለመኖርሽ ተስፋ
የጤናሽ ምልክት ይኑር እንዳይጠፋ።
“ዞሚ!”… “ዝሚ!”… “ዞሚ!”
ድምፅሽን አሰሚ!
ዓለምሽን ካድሚ።
_______
2006 E.C
አብዲ ሰዒድ
ለእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለዙልሂጃ ፆም በሰላም አደረሳቹ!!
ሸጋ ጁምኣ!!💚💚💚
@getem
@getem
@balmbaras
የሰማይ ቤት ግሮሰሪ
.
.
"ጨረቃ" ምንላት
ግሮሰሪ ቤት ናት!!!
"ሰማይ" ለምንለው ፣ ቀውጢ ከተማ
ሥራ ምትጀምረው ፣ሲሆን ነው ጨለማ!!!
..................................................
በር እንደከፈተች ፣ አብረው የሚወጡ
ከዋክብት ደሞ...
ሰካራሞች ናቸው ፣ እሷ ጋ ሚጠጡ!!!
*****************
በጣም የሰከረው...
ከሰማይ ፈጥፍጦ ፣ ራሱን ሲገድል
"ተወርዋሪ ኮከብ" ..
ማለት ነው የኛ እድል!!!
****************
ተወርዋሪ ጠርሙስ ሊሆንም ይችላል!
ማን ያውቃል?
@getem
@getem
@getem
.
.
"ጨረቃ" ምንላት
ግሮሰሪ ቤት ናት!!!
"ሰማይ" ለምንለው ፣ ቀውጢ ከተማ
ሥራ ምትጀምረው ፣ሲሆን ነው ጨለማ!!!
..................................................
በር እንደከፈተች ፣ አብረው የሚወጡ
ከዋክብት ደሞ...
ሰካራሞች ናቸው ፣ እሷ ጋ ሚጠጡ!!!
*****************
በጣም የሰከረው...
ከሰማይ ፈጥፍጦ ፣ ራሱን ሲገድል
"ተወርዋሪ ኮከብ" ..
ማለት ነው የኛ እድል!!!
****************
ተወርዋሪ ጠርሙስ ሊሆንም ይችላል!
ማን ያውቃል?
@getem
@getem
@getem
#ለዚህ_ነው_ማላምንሽ
.
(እዮብ ዘ ማርያም)
.
ቃላት አሳምረው፣
ስለ ዝናብ ውበት አድንቀው የፃፉ
ዝናብ የመጣ 'ለት፣
ዣንጥላ ዘርግተው ተጠልለው አለፉ
ልክ እንደዚህ ሁሉ
ንፋስ ነው ዘመዴ ምናምን የሚሉ
ንፋሱ ሲነፍስ መስኮት ይዘጋሉ
ያንቺም ልብ እንዲህ ነው፣
ይቀበል ይመስል ፍቅር ፍቅር ብሎ
ፍቅር ያካፋ ቀን ያልፋል ተጠልሎ
@getem
@getem
.
(እዮብ ዘ ማርያም)
.
ቃላት አሳምረው፣
ስለ ዝናብ ውበት አድንቀው የፃፉ
ዝናብ የመጣ 'ለት፣
ዣንጥላ ዘርግተው ተጠልለው አለፉ
ልክ እንደዚህ ሁሉ
ንፋስ ነው ዘመዴ ምናምን የሚሉ
ንፋሱ ሲነፍስ መስኮት ይዘጋሉ
ያንቺም ልብ እንዲህ ነው፣
ይቀበል ይመስል ፍቅር ፍቅር ብሎ
ፍቅር ያካፋ ቀን ያልፋል ተጠልሎ
@getem
@getem
አጀባ ግጥም፤ አጀብ አጀብ
--
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
መገን ጉራ ወርቄ!!!!
ውረድ አለኝ ደግሞ፣ ገስግስ በማለዳ፣
ከራማ ደፋብኝ፣
እሸት እንዳዘለ፣
ልክ እንደጃምዮ፣ ልክ እንደዘንጋዳ።
ተጥፎብኝ ክታብ፣
ተዘርፎልኝ ቅኔ፣ ከጉራ እስከ ወርቄ፣
ይኸው ከትብ አለኝ፣
ይኸው ሰልቅ አለኝ፣
ባንተው መጀን አልኩት፣ ዱኣየን ሰድቄ።
ኸረ በሸሆቼ፣
በኢሉዋ ማርያም፣ ላዮን በበላጎ፣
ይካድመኝ ይዟል፣
ድፍን ጉራ ወርቄ፣
እየፈተፈተ፣ መንገሌውን በእርጎ።
ከደፈረሰው ወንዝ፣ ጥል ካግመለመለው፣
ከጎሸው ጓደና፣ ቂም ካሽመለመለው፣
ቀርሞ ጉራ ወርቄ፣
እሱ ምን በወጣው፣ እሱ ምን ከጀለው፣
ሰማይ ከረዘቀ፣ ምድሩ ካበሸረው፣
አፉታ እንደ ጅረት፣ ቀልቡን ካጣጠበው፣
ጉራ እንደሁ ጉረኛ፣ ወርቄ እንደሁ ወርቅ ነው።
ይመር ንጉሴ ኣገር፣ ምንጫ ምንጩ መሌ፣
የሳቁ በረካ፣
ከሞትም ያድናል፣ እንኳን ከሙጀሌ።
ከጀማው መሃከል፣ መገን ጉራ ወርቄ፣
በሃድራው ዲሞፍተር፣
በነሸጋ ከንፈር፣ በጀማው ደምቄ፣
ልሞትላችሁ ነው፣
ባንገታቸው ማእጠንት፣ ቦለቂያ ሞቄ።
ይች ማርያም ማለት፣ የበላጎይቱ፣
አሁን በያ ሰሞን፣
ያጎቴ ሸህ ኢብሬ፣ ሙጥቅና እህቱ፣
ተመኪናው መንገድ፣
ሀኪም በሌለበት፣ ምጥ ይዟት ልጅቱ፣
ጉራ በመንደሩ፣ ወለል ታለው ሜዳ፣
ማርያም ድረሽልኝ፣
የምጢቱ አዋላጅ፣ የምጢቱ እንግዳ፣
እያሉ ሸሆቼ፣ ዱኣውን ቢያወርዱ፣
አርመን የመሰለ፣ ህጣን አቅፈው ሄዱ።
መገን ጉራ ወርቄ፣
የመውደዱ በልጅግ፣ የጎራው ሃቂቃ፣
የሚበራይበት፣
የዱኣው መዘውር፣ የኢልሙ ሰደቃ፣
እንኳን ለበላጎ፣
እንኳን ለጎብዬ፣ ላገር እሚበቃ።
እየውልህ ጓዴ፣
ስማኝማ ስማ፣
ይኸው በያ ሰሞን፣ በሃምሌ ጨለማ፣
የቄስ አበጀ ልጅ፣ ሁለት አይኗን ታማ፣
ቆቦ ልሄድ ብየ፣ ልገዛ ጠብታ፣
አውገረድ ፋጡማ፣ መጨነቄን ሰምታ፣
ዱኣ አስደርጋላት፣ ዱበርቴ አስገብታ፣
አይኗ ተመለሰ፣ በሸህ ያሲን ቱፍታ።
መገን ጉራ ወርቄ፣ ጃምዮ ምላሹ፣
ሰው ነው አሰቃቃይ፣ ሰው ነው አደፍራሹ፣
እሱው ነው በሽታው፣ እሱው ነው ፈዋሹ።
ይኸው ዛሬ ደግሞ፣
በላይኛው ወርቄ፣ በታችኛው ዳና፣
ዝናብ ታወርዳለች፣
ናብኝ እያለችኝ፣ በከንፈር ደመና።
ኧረ ጉራ ወርቄ፣
መገን ተረተሩ፣ የቅብቅቡ ድካ፣
ይጋገረኝ ጀመር፣
ከጃምዮ ከንፈር፣ መሳም እያቦካ።
ጉራ ወንዛ ወንዙ፣ጥንቅሽ ነው ቀለቡ፣
ሰው ነው ማጣፈጫው፣ሰው ነው ማር ዘነቡ።
በጁምአ ሰማይ፣ ሃድራየን ታቅፌ፣
ከደጋጎቹ ጋር፣
አሜን አሜን ብዬ፣ ሻሚያ ተሰልፌ፣
የዘር ቂም ላመመው፣
ዘር ላጥመለመለው፣
የእምነት ደም ላዞረው፣ ጀብራራ ወፈፌ፣
አመጣለታለሁ፣
ኢሉ ከደብሩ ስር፣
"ሰው መሆን" የሚባል፣ ጠበሉን ጨልፌ፣
እመርቀዋለሁ፣
ከዳንዮች መንደር፣ ጀማ ተሰልፌ፣
አቀብለዋለሁ፣
ሰው መሆን የሚባል፣ኪታቡን አስጥፌ።
አዳሳ!!! ምን ይላል ይኸ አንተ!!!!
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ፍልቅልቅ ፣ ፍንድቅድቅ ፣ ሽብርቅርቅ ያለች ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!💚
@getem
@getem
@balmbaras
--
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
መገን ጉራ ወርቄ!!!!
ውረድ አለኝ ደግሞ፣ ገስግስ በማለዳ፣
ከራማ ደፋብኝ፣
እሸት እንዳዘለ፣
ልክ እንደጃምዮ፣ ልክ እንደዘንጋዳ።
ተጥፎብኝ ክታብ፣
ተዘርፎልኝ ቅኔ፣ ከጉራ እስከ ወርቄ፣
ይኸው ከትብ አለኝ፣
ይኸው ሰልቅ አለኝ፣
ባንተው መጀን አልኩት፣ ዱኣየን ሰድቄ።
ኸረ በሸሆቼ፣
በኢሉዋ ማርያም፣ ላዮን በበላጎ፣
ይካድመኝ ይዟል፣
ድፍን ጉራ ወርቄ፣
እየፈተፈተ፣ መንገሌውን በእርጎ።
ከደፈረሰው ወንዝ፣ ጥል ካግመለመለው፣
ከጎሸው ጓደና፣ ቂም ካሽመለመለው፣
ቀርሞ ጉራ ወርቄ፣
እሱ ምን በወጣው፣ እሱ ምን ከጀለው፣
ሰማይ ከረዘቀ፣ ምድሩ ካበሸረው፣
አፉታ እንደ ጅረት፣ ቀልቡን ካጣጠበው፣
ጉራ እንደሁ ጉረኛ፣ ወርቄ እንደሁ ወርቅ ነው።
ይመር ንጉሴ ኣገር፣ ምንጫ ምንጩ መሌ፣
የሳቁ በረካ፣
ከሞትም ያድናል፣ እንኳን ከሙጀሌ።
ከጀማው መሃከል፣ መገን ጉራ ወርቄ፣
በሃድራው ዲሞፍተር፣
በነሸጋ ከንፈር፣ በጀማው ደምቄ፣
ልሞትላችሁ ነው፣
ባንገታቸው ማእጠንት፣ ቦለቂያ ሞቄ።
ይች ማርያም ማለት፣ የበላጎይቱ፣
አሁን በያ ሰሞን፣
ያጎቴ ሸህ ኢብሬ፣ ሙጥቅና እህቱ፣
ተመኪናው መንገድ፣
ሀኪም በሌለበት፣ ምጥ ይዟት ልጅቱ፣
ጉራ በመንደሩ፣ ወለል ታለው ሜዳ፣
ማርያም ድረሽልኝ፣
የምጢቱ አዋላጅ፣ የምጢቱ እንግዳ፣
እያሉ ሸሆቼ፣ ዱኣውን ቢያወርዱ፣
አርመን የመሰለ፣ ህጣን አቅፈው ሄዱ።
መገን ጉራ ወርቄ፣
የመውደዱ በልጅግ፣ የጎራው ሃቂቃ፣
የሚበራይበት፣
የዱኣው መዘውር፣ የኢልሙ ሰደቃ፣
እንኳን ለበላጎ፣
እንኳን ለጎብዬ፣ ላገር እሚበቃ።
እየውልህ ጓዴ፣
ስማኝማ ስማ፣
ይኸው በያ ሰሞን፣ በሃምሌ ጨለማ፣
የቄስ አበጀ ልጅ፣ ሁለት አይኗን ታማ፣
ቆቦ ልሄድ ብየ፣ ልገዛ ጠብታ፣
አውገረድ ፋጡማ፣ መጨነቄን ሰምታ፣
ዱኣ አስደርጋላት፣ ዱበርቴ አስገብታ፣
አይኗ ተመለሰ፣ በሸህ ያሲን ቱፍታ።
መገን ጉራ ወርቄ፣ ጃምዮ ምላሹ፣
ሰው ነው አሰቃቃይ፣ ሰው ነው አደፍራሹ፣
እሱው ነው በሽታው፣ እሱው ነው ፈዋሹ።
ይኸው ዛሬ ደግሞ፣
በላይኛው ወርቄ፣ በታችኛው ዳና፣
ዝናብ ታወርዳለች፣
ናብኝ እያለችኝ፣ በከንፈር ደመና።
ኧረ ጉራ ወርቄ፣
መገን ተረተሩ፣ የቅብቅቡ ድካ፣
ይጋገረኝ ጀመር፣
ከጃምዮ ከንፈር፣ መሳም እያቦካ።
ጉራ ወንዛ ወንዙ፣ጥንቅሽ ነው ቀለቡ፣
ሰው ነው ማጣፈጫው፣ሰው ነው ማር ዘነቡ።
በጁምአ ሰማይ፣ ሃድራየን ታቅፌ፣
ከደጋጎቹ ጋር፣
አሜን አሜን ብዬ፣ ሻሚያ ተሰልፌ፣
የዘር ቂም ላመመው፣
ዘር ላጥመለመለው፣
የእምነት ደም ላዞረው፣ ጀብራራ ወፈፌ፣
አመጣለታለሁ፣
ኢሉ ከደብሩ ስር፣
"ሰው መሆን" የሚባል፣ ጠበሉን ጨልፌ፣
እመርቀዋለሁ፣
ከዳንዮች መንደር፣ ጀማ ተሰልፌ፣
አቀብለዋለሁ፣
ሰው መሆን የሚባል፣ኪታቡን አስጥፌ።
አዳሳ!!! ምን ይላል ይኸ አንተ!!!!
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ፍልቅልቅ ፣ ፍንድቅድቅ ፣ ሽብርቅርቅ ያለች ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!💚
@getem
@getem
@balmbaras
በሀገሬ ሰማይ ላይ
የእናቴ መቀነት ቀለሙ አሸብርቋል
ትሙት ትዳን እንጃ
ልጆቿን አዝላበት ውሉ አፈትልኳል
ጠበቅ አርጋ አስራለች
አይፈታም እና የተፈተለበት የጥጡ ፍታይ
አንገትክን ቀና አርገህ
ልታየው ብትሻም አንጋጠህ ወደ ላይ
ቁልቁል ተምዘግዝጎ
ወርዶ ከሰማዩ ከደመናው በታች
ከመሬት አትደርስም
ትሰበር ይመስል ብርጭቆ ብትመስልም
ከፍጥረታት አናት
ከበላይ ከበላይ
ከከፍታ ወጥታ
ቁልቁል ወደ መሬት ወደ ታች ወደታች
ብትሰበር እንጂ ጉዳቷ ቢፀና
ሀገሬ አትሞትም ተሰባብራም ቢሆን ትቆማለችና!!
@joiamant22
መልካም ቅዴ!!
@getem
@getem
@getem
የእናቴ መቀነት ቀለሙ አሸብርቋል
ትሙት ትዳን እንጃ
ልጆቿን አዝላበት ውሉ አፈትልኳል
ጠበቅ አርጋ አስራለች
አይፈታም እና የተፈተለበት የጥጡ ፍታይ
አንገትክን ቀና አርገህ
ልታየው ብትሻም አንጋጠህ ወደ ላይ
ቁልቁል ተምዘግዝጎ
ወርዶ ከሰማዩ ከደመናው በታች
ከመሬት አትደርስም
ትሰበር ይመስል ብርጭቆ ብትመስልም
ከፍጥረታት አናት
ከበላይ ከበላይ
ከከፍታ ወጥታ
ቁልቁል ወደ መሬት ወደ ታች ወደታች
ብትሰበር እንጂ ጉዳቷ ቢፀና
ሀገሬ አትሞትም ተሰባብራም ቢሆን ትቆማለችና!!
@joiamant22
መልካም ቅዴ!!
@getem
@getem
@getem
👍1
#የወፈፌው ቃላት!!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
ደግሞ ተነሳብኝ!
የአምና ካቻምናው ፥ የፊቱ እብደቴ
አንቺን ባየው ቁጥር.. .
ወፈፈ ሚያስብለኝ ፥ ህመም ምልክቴ።
ይኸው ፌስታል ሸረብሁ !
ቡልኮዬን ቀደድሁ
ገረባዬን ሸከፍሁ
ካላፊ ካግዳሚው ...
ቅጥሬን ለይቼ ፥ በፅኑ ተኳረፍሁ።
ብልሀት በራቀው ፥ መላ በሌለበት
ህመምን የሚያብስ...
ከንፈር መጣጭ ሀኪም ፥ ደጁን በሞላበት
ከተማ ሸሽቼ ...
ብቻዬን ወጥቼ...
ለሚሰግር ፍቅር ፥ መንገድ ላበጅለት
አበድሁ ስላንቺ ...
ያለ አንዳች ከልካይ ፥ ተመላለሺበት ።
ይኸው እንኪ ሰበዙን
የልምዱ እብደቴን...
በወስፌ ለይተሽ ፥ መሶቡን አበጂ
ተቀበይ ህመሜን!
አንጀትሽ እንዲርስ...
ከዳሩ ላይ ጨልፈሽ ፥ ወይንሽን ቅጂ ።
እንኪ ንሽማሽን!
ዘርጊው መዳፍሽን ...
ጠያቂው በተርታ ፥ በሰልፍ ተሰድሮ
ምን ክፉ አጊንቶህ
ከጤናህ ተሽረህ ፥ ሆንህ እንደ ድሮ ?
ብለው ሳይጠይቁኝ ....
#እኔም በተራዬ
"አዎን እንደዚህ ነው !
ሰው ፍቅርን ሊያነግስ ፥
ልቡን ተሸክሞ ፥ ሲወርድ ከገበያ
አቅልን የመሳት ፥ የእብደት መጀመርያ
ደግሞም የእውነት ህመም ...
መላወሻ አልባው ፥ ሀቀኛው በሽታ
ሰው ልቡን አቅርቦ ፥ ዘርግቶ በፎጣ
ሸማች ሲርቀው ነው ፥ የሚገዛው ሲያጣ "
ብዬ ሳልመልስ ፥ ሳይገለጥ ምክንያቴ
ፈጥነሽ ድረሽልኝ ፥ ተሿሚ ልዕልቴ ።
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
ደግሞ ተነሳብኝ!
የአምና ካቻምናው ፥ የፊቱ እብደቴ
አንቺን ባየው ቁጥር.. .
ወፈፈ ሚያስብለኝ ፥ ህመም ምልክቴ።
ይኸው ፌስታል ሸረብሁ !
ቡልኮዬን ቀደድሁ
ገረባዬን ሸከፍሁ
ካላፊ ካግዳሚው ...
ቅጥሬን ለይቼ ፥ በፅኑ ተኳረፍሁ።
ብልሀት በራቀው ፥ መላ በሌለበት
ህመምን የሚያብስ...
ከንፈር መጣጭ ሀኪም ፥ ደጁን በሞላበት
ከተማ ሸሽቼ ...
ብቻዬን ወጥቼ...
ለሚሰግር ፍቅር ፥ መንገድ ላበጅለት
አበድሁ ስላንቺ ...
ያለ አንዳች ከልካይ ፥ ተመላለሺበት ።
ይኸው እንኪ ሰበዙን
የልምዱ እብደቴን...
በወስፌ ለይተሽ ፥ መሶቡን አበጂ
ተቀበይ ህመሜን!
አንጀትሽ እንዲርስ...
ከዳሩ ላይ ጨልፈሽ ፥ ወይንሽን ቅጂ ።
እንኪ ንሽማሽን!
ዘርጊው መዳፍሽን ...
ጠያቂው በተርታ ፥ በሰልፍ ተሰድሮ
ምን ክፉ አጊንቶህ
ከጤናህ ተሽረህ ፥ ሆንህ እንደ ድሮ ?
ብለው ሳይጠይቁኝ ....
#እኔም በተራዬ
"አዎን እንደዚህ ነው !
ሰው ፍቅርን ሊያነግስ ፥
ልቡን ተሸክሞ ፥ ሲወርድ ከገበያ
አቅልን የመሳት ፥ የእብደት መጀመርያ
ደግሞም የእውነት ህመም ...
መላወሻ አልባው ፥ ሀቀኛው በሽታ
ሰው ልቡን አቅርቦ ፥ ዘርግቶ በፎጣ
ሸማች ሲርቀው ነው ፥ የሚገዛው ሲያጣ "
ብዬ ሳልመልስ ፥ ሳይገለጥ ምክንያቴ
ፈጥነሽ ድረሽልኝ ፥ ተሿሚ ልዕልቴ ።
@getem
@getem
@getem
ጫማህ ስር!!!!!
አበሻ ምስኪን ነው፤
አበሻ ቡቡ ነው፤
ሽበቱን ለፍቅር፤
እርጅናውን ለእዝነት፤
አይኑን ላዘን እምባ፤
ልቡን ለርህራሄ፤
እንካችሁ እያለ፤ የገበረለታ፤
ትህትናው ይደንቃል፤
የደግነት ቅኔው፤
ሩህሩህ አንጀቱ፤ ምስጢሩ ይረቃል፤
ስለ ወገን ብሎ፤
ኩርምትምት ብሎ፤ ጫማህ ስር ይወድቃል።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
((ደበበ እሸቱ ለጌርጌሴኖን መረዳጃ እርዳታ ለመሰብሰብ
ጫማ እየጠረገ )))
ጋሽ ደበበ እሽቱ መልካም ልደት!🎂🎂🎂
@getem
@getem
@balmbaras
አበሻ ምስኪን ነው፤
አበሻ ቡቡ ነው፤
ሽበቱን ለፍቅር፤
እርጅናውን ለእዝነት፤
አይኑን ላዘን እምባ፤
ልቡን ለርህራሄ፤
እንካችሁ እያለ፤ የገበረለታ፤
ትህትናው ይደንቃል፤
የደግነት ቅኔው፤
ሩህሩህ አንጀቱ፤ ምስጢሩ ይረቃል፤
ስለ ወገን ብሎ፤
ኩርምትምት ብሎ፤ ጫማህ ስር ይወድቃል።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
((ደበበ እሸቱ ለጌርጌሴኖን መረዳጃ እርዳታ ለመሰብሰብ
ጫማ እየጠረገ )))
ጋሽ ደበበ እሽቱ መልካም ልደት!🎂🎂🎂
@getem
@getem
@balmbaras
ለሰኞ ምሽታችን ስጦታ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ሰኞ ምሽት ሁላችሁም በነጻ ተጋብዛችኋል!!!!!
ገጣሚና ደራሲ ኤፍሬም ሥዩም ጥበብ አዲስ( ART COCKTAIL) በሚል ስያሜ የተለያዩ
የጥበብ ግብአቶችን ስነ ግጥም ከፊልምና ሙዚቃ ጋር ፣ ስነ ስእል፣ ሙዚቃ በሃቲቱ ( solo
music) ፣ ተውኔት፣ የአልባሳት ጥበብ ነጻ ግዜ፣ ለታዳሚዎች(free mike)፣
የዲፕሎማቶች ግዜ እንደዚህም ሌሎቹም በአንድ መድረክ ላይ በማጣመር እና በማዋሃድ
ሐምሌ 29-2011 በኢንተር ኮንቲኔንታል ትልቁ አዳራሽ አመሻሽ 11፡30 የወርሃዊ መርሃ
ግብሩን የደመቀ መክፈቻ ደግሶ እነሆ ታደሙልኝ ይለናል….. አንጋፋና ወጣት የጥበብ ሰዎች
ስራቸውን ይዘው ለመቅረብ ተዘጋጅተዋል
የሚመቻቹ ብትመጡ ብዙ አትርፋቹ ትሄዳላችሁ
#በነፃ ነው 😊 ከፈለጋችሁ ከፍቅረኞቻቹ ጋር ከፈለጋቹ ከጓደኞቻቹ ጋር ሸጋ ምሽት ታሳልፋላቹ🙏
እዛው እንገናኝ ወርቆቼ!!👑
-----------------------------------------------
እንደምነው ሰኞ፤ የእሁድ ጓደኛ ፤
እንገጥማለን ብለን፤ ሸዋ ገባን እኛ! !!!!
ነገር የመጣኝ ቀን ፤ ነገር እገጥማለሁ ፤
ግጥም የመጣኝ ቀን፤ ግጥም እገጥማለሁ ፤
ያገጣጠመኝ ቀን ግጣም እገጥማለሁ ፤
መግጠም ነው እንግዲህ ፤
ከዚህ ወዲያ ስራ ከወዴት ተገኝቶ ፤
አለም አይደለም ወይ ፤
መግጠም መገጣጠም ቁሞና ተኝቶ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ሰኞ ምሽት ሁላችሁም በነጻ ተጋብዛችኋል!!!!!
ገጣሚና ደራሲ ኤፍሬም ሥዩም ጥበብ አዲስ( ART COCKTAIL) በሚል ስያሜ የተለያዩ
የጥበብ ግብአቶችን ስነ ግጥም ከፊልምና ሙዚቃ ጋር ፣ ስነ ስእል፣ ሙዚቃ በሃቲቱ ( solo
music) ፣ ተውኔት፣ የአልባሳት ጥበብ ነጻ ግዜ፣ ለታዳሚዎች(free mike)፣
የዲፕሎማቶች ግዜ እንደዚህም ሌሎቹም በአንድ መድረክ ላይ በማጣመር እና በማዋሃድ
ሐምሌ 29-2011 በኢንተር ኮንቲኔንታል ትልቁ አዳራሽ አመሻሽ 11፡30 የወርሃዊ መርሃ
ግብሩን የደመቀ መክፈቻ ደግሶ እነሆ ታደሙልኝ ይለናል….. አንጋፋና ወጣት የጥበብ ሰዎች
ስራቸውን ይዘው ለመቅረብ ተዘጋጅተዋል
የሚመቻቹ ብትመጡ ብዙ አትርፋቹ ትሄዳላችሁ
#በነፃ ነው 😊 ከፈለጋችሁ ከፍቅረኞቻቹ ጋር ከፈለጋቹ ከጓደኞቻቹ ጋር ሸጋ ምሽት ታሳልፋላቹ🙏
እዛው እንገናኝ ወርቆቼ!!👑
-----------------------------------------------
እንደምነው ሰኞ፤ የእሁድ ጓደኛ ፤
እንገጥማለን ብለን፤ ሸዋ ገባን እኛ! !!!!
ነገር የመጣኝ ቀን ፤ ነገር እገጥማለሁ ፤
ግጥም የመጣኝ ቀን፤ ግጥም እገጥማለሁ ፤
ያገጣጠመኝ ቀን ግጣም እገጥማለሁ ፤
መግጠም ነው እንግዲህ ፤
ከዚህ ወዲያ ስራ ከወዴት ተገኝቶ ፤
አለም አይደለም ወይ ፤
መግጠም መገጣጠም ቁሞና ተኝቶ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
(ፋሲል_ስዩም)
©
"ጭስ_አለ"
.
.
በመንቃ'ተ ማዕጠንት
በቅጠል 'ሚላወስ፣
መኖሬን ቀምቶ
ባ'ለመኖር 'ሚያነግስ፣
ድኩም አረቄ ጋር
ነፍስን አጨቅይቶ
ትውልድን የገዛ፣
በምርቃና ጥበብ
መኖሬን ሸምኖ
መሞቴን ያወዛ፣
ነገዬን ያከሳ፡፡
...
...
ጭስ አለ
...
...
ፀጉሩን ያጎፈረ
የትውልድ ጥያቄን
በ'ሳት የሰፈረ፣
የማሰነ የወረዛ
ቃሬዛ አውራሽ
ክምር ጤዛ!
ተደውሮ......ተስመንምኖ፣
ተሽመንሙኖ......ተስመናጥኖ፣
ተሽመጥምጦ.....ተንደቅድቆ፣
ስጋን አልፎ.....ከነፍስ ወርዶ፣
ካ'ናት 'ሚወጣ......."ነዶ-ንዶ"!
...
...
"ጭስ አለ"
...
...
የ'ሳት ክምር
የሳት ላንቃ፣
የእንባ ስፍር
የሀዘን ሲቃ፡፡
በጉልትልትል አጀብ ከብሮ
ከሰማይ አክናፍ ካ'የር ቀሮ፣
በዝምታ አሰገምግሞ
አደንዝዞ
የሚያስቀራት 'ህይወቴን ባዶ፡፡
.
.
"ጭስ አለ"
.
.
ማንነትን የገደለ፣
ውብ ገፆችን የሸፈነ፣
ድልህን በሽንፈት የከደነ፣
ያልኖረ....ግን የኖረ፣
ያለፈ....ግን የቆመ፣
.
.
"ጭስ አለ"
.
.
የተሰጠ ለ'ነ ነቄ፣
የተዋዛ በአረቄ፣
የሸመኑት እነ ድንቄ፣
ጭስ አለ
ሞት አለ
በንዋይ ተገዝቶ ትውልድ የገደለ፣
ባ'ፍ ባ'ፍ ተምጎ ነፍስን ያሰለለ፡፡
.
.
.
ሞት አለ...
ጭስ አለ...
...///....
@getem
@getem
@lula_al_greeko
©
"ጭስ_አለ"
.
.
በመንቃ'ተ ማዕጠንት
በቅጠል 'ሚላወስ፣
መኖሬን ቀምቶ
ባ'ለመኖር 'ሚያነግስ፣
ድኩም አረቄ ጋር
ነፍስን አጨቅይቶ
ትውልድን የገዛ፣
በምርቃና ጥበብ
መኖሬን ሸምኖ
መሞቴን ያወዛ፣
ነገዬን ያከሳ፡፡
...
...
ጭስ አለ
...
...
ፀጉሩን ያጎፈረ
የትውልድ ጥያቄን
በ'ሳት የሰፈረ፣
የማሰነ የወረዛ
ቃሬዛ አውራሽ
ክምር ጤዛ!
ተደውሮ......ተስመንምኖ፣
ተሽመንሙኖ......ተስመናጥኖ፣
ተሽመጥምጦ.....ተንደቅድቆ፣
ስጋን አልፎ.....ከነፍስ ወርዶ፣
ካ'ናት 'ሚወጣ......."ነዶ-ንዶ"!
...
...
"ጭስ አለ"
...
...
የ'ሳት ክምር
የሳት ላንቃ፣
የእንባ ስፍር
የሀዘን ሲቃ፡፡
በጉልትልትል አጀብ ከብሮ
ከሰማይ አክናፍ ካ'የር ቀሮ፣
በዝምታ አሰገምግሞ
አደንዝዞ
የሚያስቀራት 'ህይወቴን ባዶ፡፡
.
.
"ጭስ አለ"
.
.
ማንነትን የገደለ፣
ውብ ገፆችን የሸፈነ፣
ድልህን በሽንፈት የከደነ፣
ያልኖረ....ግን የኖረ፣
ያለፈ....ግን የቆመ፣
.
.
"ጭስ አለ"
.
.
የተሰጠ ለ'ነ ነቄ፣
የተዋዛ በአረቄ፣
የሸመኑት እነ ድንቄ፣
ጭስ አለ
ሞት አለ
በንዋይ ተገዝቶ ትውልድ የገደለ፣
ባ'ፍ ባ'ፍ ተምጎ ነፍስን ያሰለለ፡፡
.
.
.
ሞት አለ...
ጭስ አለ...
...///....
@getem
@getem
@lula_al_greeko
...ተይ ግን እንታረቅB...
#የበእውቀቱ_ስዩም_ልጅ😉
እኔ ስለማመጥ፤ አንቺ ስትይ እንቢ
ማር እየላስሽልኝ፤ እየበላኝ ቢንቢ
መልኬ መስሎ ቡግር፤
ልቤን ይዞት ፍቅር...
አይተሽ አትለፊ፤ ውዴ ሆይ ተረጂ
እኔ ላግባሽና፤ ከሌላ ውለጂ😂
(ብዬ ባልልሽም)
እና ያንቺ መቅበጥ፤
የኔ መለማመጥ
የልቤ መልጥመጥ፤
የልብሽ መቁረጥ-ቀጥ
ትንፋሽ እያሳጣኝ-እየካደኝ ልቤ
ሀኪም ላያድነኝ-ቀይ ደሜን ታልቤ
በላመ ምርመራ-በተረጋገጠ
የህመሜን ሚዛን-ፍቅርሽ እረገጠ፡፡
መድሀኒት ስለሆንሽ፤ ፈዋሽ ለህመሜ
በአካል ካልሆነ፤ አትምጪ በህልሜ
እንቢ ካልሺም እሺ
እሺ ካልሺም እሺ
ብቻ ልለምንሽ፤ ልብስ ግን ልበሺ
በቅዠት እርቃንሽ- ሲያወልቅብኝ ሱሪ
በእውን ውበትሽ- እያስባለኝ እሪ..
እንዴት እኔ ልበድ-አንቺ ተናገሪ።
አሁን ስለገባኝ፤ ለማበድም ምቾት
ለማልቀስም ብሶት፤
ስለ-ማስፈለጉ
ቅርብ ስለማይሆን፤ ለመሀልም ጥጉ
ቀረብ በይኝና፤ ሁነሽ አጠገቤ
የተንቀዠቀዠው፤ ይረጋጋ ልቤ፡፡ቀልቤ።
[አብርሃም ሙሉ]
@getem
@getem
@gebriel_19
#የበእውቀቱ_ስዩም_ልጅ😉
እኔ ስለማመጥ፤ አንቺ ስትይ እንቢ
ማር እየላስሽልኝ፤ እየበላኝ ቢንቢ
መልኬ መስሎ ቡግር፤
ልቤን ይዞት ፍቅር...
አይተሽ አትለፊ፤ ውዴ ሆይ ተረጂ
እኔ ላግባሽና፤ ከሌላ ውለጂ😂
(ብዬ ባልልሽም)
እና ያንቺ መቅበጥ፤
የኔ መለማመጥ
የልቤ መልጥመጥ፤
የልብሽ መቁረጥ-ቀጥ
ትንፋሽ እያሳጣኝ-እየካደኝ ልቤ
ሀኪም ላያድነኝ-ቀይ ደሜን ታልቤ
በላመ ምርመራ-በተረጋገጠ
የህመሜን ሚዛን-ፍቅርሽ እረገጠ፡፡
መድሀኒት ስለሆንሽ፤ ፈዋሽ ለህመሜ
በአካል ካልሆነ፤ አትምጪ በህልሜ
እንቢ ካልሺም እሺ
እሺ ካልሺም እሺ
ብቻ ልለምንሽ፤ ልብስ ግን ልበሺ
በቅዠት እርቃንሽ- ሲያወልቅብኝ ሱሪ
በእውን ውበትሽ- እያስባለኝ እሪ..
እንዴት እኔ ልበድ-አንቺ ተናገሪ።
አሁን ስለገባኝ፤ ለማበድም ምቾት
ለማልቀስም ብሶት፤
ስለ-ማስፈለጉ
ቅርብ ስለማይሆን፤ ለመሀልም ጥጉ
ቀረብ በይኝና፤ ሁነሽ አጠገቤ
የተንቀዠቀዠው፤ ይረጋጋ ልቤ፡፡ቀልቤ።
[አብርሃም ሙሉ]
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1