(በላይ በቀለ ወያ)
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር
ስቅለት እና ጁመአ ፣ ሲውሉ ባንድ ቀን
በስግደት በፀሎት ፣ በዱአ ማይለቀን
ምን አይነት ጋኔን ነው
በዘር በጎጥ ከፍሎን ፣ አስሮ ሚያፏቅቀን?!
።።።
@getem
@getem
@gebriel_19
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር
ስቅለት እና ጁመአ ፣ ሲውሉ ባንድ ቀን
በስግደት በፀሎት ፣ በዱአ ማይለቀን
ምን አይነት ጋኔን ነው
በዘር በጎጥ ከፍሎን ፣ አስሮ ሚያፏቅቀን?!
።።።
@getem
@getem
@gebriel_19
መሰቀሉን እንጃ
"""""""""""""""""""
አብርሃም
ህይወት ተከርብቶ
ታሪክ ተገልብጦ
በዚህ ዘመን ትውልድ፤
ለአለም ቤዛ የሆነው
ይህን ቀን ቢመጣ
ይህን ዘመን ቢወለድ..
(ቢያስተምር....)
ስለ ፍቅር ብሎ
እራሱ ዝቅ ብሎ
ተዋደዱ ብሎ...ስለ እውነት ብሎ
(ቢገስፅ...)
አትጣሉ ብሎ
ስርህና ስርሽ ገንዘብ አይሁን ብሎ
ብር አታምልክ ብሎ
አትዋሹ ብሎ
ቁጣውን ቢያሳየን
የእኛው ቤዛ ድ'ነት
ብሩን ቢበትነው
በጎቹንም ቢለቅ ገበያውን ቢያውክ
እያለም ቢናገር...
አትከፋፈሉ በጎሳ በብሄር
አታሲሩ ለሰው ተባባሉ ይቅር
ማመንዘሩም ይቅር
ስሜት አይግዛችሁ መስረቃችሁ ይቅር
ብሎ እኛን ቢያስተምር
ይሄ ዋሾ ትውልድ
ይሄ ሌባ ትውልድ
ስቆና አንጓጦ አይሰቅለውም ነበር?
(እንጃ....ብቻ)
@getem
@getem
@getem
"""""""""""""""""""
አብርሃም
ህይወት ተከርብቶ
ታሪክ ተገልብጦ
በዚህ ዘመን ትውልድ፤
ለአለም ቤዛ የሆነው
ይህን ቀን ቢመጣ
ይህን ዘመን ቢወለድ..
(ቢያስተምር....)
ስለ ፍቅር ብሎ
እራሱ ዝቅ ብሎ
ተዋደዱ ብሎ...ስለ እውነት ብሎ
(ቢገስፅ...)
አትጣሉ ብሎ
ስርህና ስርሽ ገንዘብ አይሁን ብሎ
ብር አታምልክ ብሎ
አትዋሹ ብሎ
ቁጣውን ቢያሳየን
የእኛው ቤዛ ድ'ነት
ብሩን ቢበትነው
በጎቹንም ቢለቅ ገበያውን ቢያውክ
እያለም ቢናገር...
አትከፋፈሉ በጎሳ በብሄር
አታሲሩ ለሰው ተባባሉ ይቅር
ማመንዘሩም ይቅር
ስሜት አይግዛችሁ መስረቃችሁ ይቅር
ብሎ እኛን ቢያስተምር
ይሄ ዋሾ ትውልድ
ይሄ ሌባ ትውልድ
ስቆና አንጓጦ አይሰቅለውም ነበር?
(እንጃ....ብቻ)
@getem
@getem
@getem
.☜አውቃለሁ ~አታውቅም☞ (በሔለን ፋንታሁን)
.
አውቃለሁ...
አልወዛም በቅባት
የምስሌ ገፅ ቀለም ፣
ባልታረዝ እንኳን...
በዘመኑ ቀሚስ
አካሌ አልደመቀም፡፡
...............
አውቃለሁ...
ከ'ነሱ አንሳለሁ
ባንተ ቀመር ስሌት ፣
ልብን ለማሸፈት
አልሆንኩም እንደ ሴት፡፡
................
አውቃለሁ...
ዕርቃን ገላ የለኝ
ቀልብን የሚነሳ ፣
በስሜት አስክሮ
ነፍስን የሚያሳሳ፡፡
...................
አውቃለሁ...
አልመረጥኩም ባይነት
ከአዳም ዘር ተርታ ፣
ስጋዬን ቸርችሬ
ለመክፈል ውለታ ፡፡
..................
አንተ ግን አታውቅም...
ሰ 'ቶ ለመቀበል
ራሴን አላረክስም ፣
አፅናኝ ለማባባት
ዕንባ አላፈስም፡፡
.................
አንተ ግን አታውቅም...
ኩሩ ሴትነቴን
የነፍሴን ልክ ጥጋት ፣
የመኖሬን ትርጉም
የኔነቴን ስሌት ፡፡
.................
አንተ ግን አታውቅም...
ስውር ቅኔነቴን
ልባም ሠውነቴን ፣
አዳኝም ገዳይም
የመሆን ጥበቤን ።
...................
አታውቅም እመነኝ
ገዳይህ እኔ ነኝ ።
~~~~//~~~~
@getem
@getem
@getem
.
አውቃለሁ...
አልወዛም በቅባት
የምስሌ ገፅ ቀለም ፣
ባልታረዝ እንኳን...
በዘመኑ ቀሚስ
አካሌ አልደመቀም፡፡
...............
አውቃለሁ...
ከ'ነሱ አንሳለሁ
ባንተ ቀመር ስሌት ፣
ልብን ለማሸፈት
አልሆንኩም እንደ ሴት፡፡
................
አውቃለሁ...
ዕርቃን ገላ የለኝ
ቀልብን የሚነሳ ፣
በስሜት አስክሮ
ነፍስን የሚያሳሳ፡፡
...................
አውቃለሁ...
አልመረጥኩም ባይነት
ከአዳም ዘር ተርታ ፣
ስጋዬን ቸርችሬ
ለመክፈል ውለታ ፡፡
..................
አንተ ግን አታውቅም...
ሰ 'ቶ ለመቀበል
ራሴን አላረክስም ፣
አፅናኝ ለማባባት
ዕንባ አላፈስም፡፡
.................
አንተ ግን አታውቅም...
ኩሩ ሴትነቴን
የነፍሴን ልክ ጥጋት ፣
የመኖሬን ትርጉም
የኔነቴን ስሌት ፡፡
.................
አንተ ግን አታውቅም...
ስውር ቅኔነቴን
ልባም ሠውነቴን ፣
አዳኝም ገዳይም
የመሆን ጥበቤን ።
...................
አታውቅም እመነኝ
ገዳይህ እኔ ነኝ ።
~~~~//~~~~
@getem
@getem
@getem
...የጌታ ትንሳኤ...
ከተከመረብን የመከራ ህንፃ
እሱ ቤዛ ሆኖ እኛን ሊያነፃ
የኛን ሃጥያት ወስዶ የኛኑ ሞት ሊሞት
ክብሩን ትቶ ወረደ ከሰማየ ሰማያት
ግድ ነውና ሊፈፀም የአምላክ ቃሉ
ይሰቀል ይሰቀል ይሰቀል እያሉ
የሚሰሩት ስራ ሳይገባቸው ቅሉ
እያንገላቱ ወሰዱት አምላክን ሊሰቅሉ
ፀሃይ በሃዘን ብዛት በጠቆረችበት
ሰማይ ባነባበት
ልክ በአርብ ዕለት
እንጨት አመሳቅለው አምላክን ሰቀሉት
እናም በዚያች ዕለት
ለአዳም ልጆች ሁሉ ሆነልን ድነት
ያኔ ሃዋርያቱን ሰብስቦ ሲያስተምር
እስከ ሞት ድረስ እኛን እንደሚያፈቅር
ከሞቱም በኧላ እንድንጠብቀው አውቀን
እነሳለው ብሎ ነበር በ3ተኛዋ ቀን
እናም
ያለ አንዳች የሃጥያት ጠባሳ
ተሰርዞ ሲያበቃ የአዳም ልጅ አበሳ
ያቺ ቅድስት ዕለት 3ተኛዋ ቀን ደርሳ
መቃብር ፈንቅሎ ጌታችን ተነሳ
እዮብ ጌታሁን
@getem
@getem
@getem
ከተከመረብን የመከራ ህንፃ
እሱ ቤዛ ሆኖ እኛን ሊያነፃ
የኛን ሃጥያት ወስዶ የኛኑ ሞት ሊሞት
ክብሩን ትቶ ወረደ ከሰማየ ሰማያት
ግድ ነውና ሊፈፀም የአምላክ ቃሉ
ይሰቀል ይሰቀል ይሰቀል እያሉ
የሚሰሩት ስራ ሳይገባቸው ቅሉ
እያንገላቱ ወሰዱት አምላክን ሊሰቅሉ
ፀሃይ በሃዘን ብዛት በጠቆረችበት
ሰማይ ባነባበት
ልክ በአርብ ዕለት
እንጨት አመሳቅለው አምላክን ሰቀሉት
እናም በዚያች ዕለት
ለአዳም ልጆች ሁሉ ሆነልን ድነት
ያኔ ሃዋርያቱን ሰብስቦ ሲያስተምር
እስከ ሞት ድረስ እኛን እንደሚያፈቅር
ከሞቱም በኧላ እንድንጠብቀው አውቀን
እነሳለው ብሎ ነበር በ3ተኛዋ ቀን
እናም
ያለ አንዳች የሃጥያት ጠባሳ
ተሰርዞ ሲያበቃ የአዳም ልጅ አበሳ
ያቺ ቅድስት ዕለት 3ተኛዋ ቀን ደርሳ
መቃብር ፈንቅሎ ጌታችን ተነሳ
እዮብ ጌታሁን
@getem
@getem
@getem
👍1
እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡
በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡
በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡
መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡
ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡
መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡
ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡
በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡
ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤ ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!
ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@getem
@wegoch
በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡
በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡
መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡
ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡
መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡
ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡
በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡
ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤ ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!
ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@getem
@wegoch
በጭድ ላይ ጭነት
"""""""''''፠""""""""፠""""""""
ተከምሮ ቁልል ጭድ ታይቶ ለእሳት
ተቃጥሎ ከቀረ አለፉት አመታት
*
ያ ሁሉ ተንዶ... ጭድ 'ና ጭነቱ
ሞልቶ አያቅ "ክምር" ቢለኝ ባለቤቱ
*
እኔም አልኩ ታዲያ~
ከስር ከስሩ መዘህ ፣ ከላይ ተመንምኖ
ጭድ እ'የት ያቅና መክበድ ተመዝኖ?
.
@Johny_Debx
@getem
@getem
@getem
"""""""''''፠""""""""፠""""""""
ተከምሮ ቁልል ጭድ ታይቶ ለእሳት
ተቃጥሎ ከቀረ አለፉት አመታት
*
ያ ሁሉ ተንዶ... ጭድ 'ና ጭነቱ
ሞልቶ አያቅ "ክምር" ቢለኝ ባለቤቱ
*
እኔም አልኩ ታዲያ~
ከስር ከስሩ መዘህ ፣ ከላይ ተመንምኖ
ጭድ እ'የት ያቅና መክበድ ተመዝኖ?
.
@Johny_Debx
@getem
@getem
@getem
///ለሰከንድ አልኖርም///
አንድ ጊዜ በቀኝ አንድ ጊዜ በግራ
የያዝኩትን ሳሊዝ ያልያዝኩትን ልይዝ መከራ ስበላ
ጠዋቴም አለፈ መሸታው ላይ ደረስኩ
የምይዘው ጠፍቶኝ እንዲሁ እንደባዘንኩ
በዘላለም መሀል ቢጠልቅ እድሜዬ
የሚወስደውን እጅ ሳሰላው ቁጭ ብዬ
የሰከንዶች ሽርፍራፊ ደቂቃ ማይሞላ
መሆኑ ቢገባኝ ደርሶ ትርጉም የለሽ ምንም የማይረባ
የአለምን ጋጋታ ላልሰማ ቸል ብዬ
ፍለጋዬን ሁሉ ወደ ዃላ ጥዬ
ጤዛውን እድሜዬን ለእርሱ ሰዋውለት
ሰከንድን ለመኖር
ዘላለም እንዳልሞት
ግጥም-ምህረት ሻውል(Mሬ)
@Getem
@getem
@gebriel_19
አንድ ጊዜ በቀኝ አንድ ጊዜ በግራ
የያዝኩትን ሳሊዝ ያልያዝኩትን ልይዝ መከራ ስበላ
ጠዋቴም አለፈ መሸታው ላይ ደረስኩ
የምይዘው ጠፍቶኝ እንዲሁ እንደባዘንኩ
በዘላለም መሀል ቢጠልቅ እድሜዬ
የሚወስደውን እጅ ሳሰላው ቁጭ ብዬ
የሰከንዶች ሽርፍራፊ ደቂቃ ማይሞላ
መሆኑ ቢገባኝ ደርሶ ትርጉም የለሽ ምንም የማይረባ
የአለምን ጋጋታ ላልሰማ ቸል ብዬ
ፍለጋዬን ሁሉ ወደ ዃላ ጥዬ
ጤዛውን እድሜዬን ለእርሱ ሰዋውለት
ሰከንድን ለመኖር
ዘላለም እንዳልሞት
ግጥም-ምህረት ሻውል(Mሬ)
@Getem
@getem
@gebriel_19
# ጠይቅ !!??
¿
እውነት ማለት ውሸት
ፍቅር ማለት ተረት ፡
ፍትህ በወረቀት ፡
አለሁ ሲሉ መሞት ፡
በሆነባት መሬት ።
ቆሞ እንደ መቀመጥ ፡
ኑሮ ሲርመጠመጥ ፡
እየሄድክ የቆምከው ፡
ጠርጥር ያገሬ ሰው ፡
ሰውነት የት ሄደ ፡
ጤና የት ለመደ ።
አለሁኝ ለማለት ፡
ተኝቶ መነሳት ፡
ላይሆንህ መስካሪ ፡
ጠይቅ አንተ ኗሪ !!!
~~~~~ ~~~
መዳፌን አደማሁ በስለት ወግቼ ፡
ፍቅሬን ከተብኩልህ በፍቅር ጣቶቼ ፡
ትለኛለች # ውዴ ፡
ይታመናል እንዴ !!?
ዳቦ ለሚሻ ሆድ ለደረቀ አንጀቱ ፡
ባንቺ የፍቅር ስንኝ ይሞላል ወይ ቤቱ!!
ያንቺ የፍቅር ግጥም ፡
የራብ ቤት አይመታም ፡
ብየ እንዳልደመድም ፡
በደሌን አንፅቶ ስሜን ያስቀየረ ፡
በፍቅሩ ነው'ንጂ ዳቦው መች ነበረ ።
****
ክብሩን የቀደደ ፡
እርቃን የወለደ ፡
ሰውነት የት ሔደ !!!!!
?
ጠይቅ! ያገሬ ሰው !!!! ....
መብትህን መናድ ፡
ወረቀት ከመቅደድ ፡
አንሶ ሲታያቸው ፡
መረገጥም ሞት ነው ፡
ፈርተህ አትለፈው !!!
!!!!!!?????
****
✍
ዮናስ ፈንታው
@getem
@getem
@gebriel_19
¿
እውነት ማለት ውሸት
ፍቅር ማለት ተረት ፡
ፍትህ በወረቀት ፡
አለሁ ሲሉ መሞት ፡
በሆነባት መሬት ።
ቆሞ እንደ መቀመጥ ፡
ኑሮ ሲርመጠመጥ ፡
እየሄድክ የቆምከው ፡
ጠርጥር ያገሬ ሰው ፡
ሰውነት የት ሄደ ፡
ጤና የት ለመደ ።
አለሁኝ ለማለት ፡
ተኝቶ መነሳት ፡
ላይሆንህ መስካሪ ፡
ጠይቅ አንተ ኗሪ !!!
~~~~~ ~~~
መዳፌን አደማሁ በስለት ወግቼ ፡
ፍቅሬን ከተብኩልህ በፍቅር ጣቶቼ ፡
ትለኛለች # ውዴ ፡
ይታመናል እንዴ !!?
ዳቦ ለሚሻ ሆድ ለደረቀ አንጀቱ ፡
ባንቺ የፍቅር ስንኝ ይሞላል ወይ ቤቱ!!
ያንቺ የፍቅር ግጥም ፡
የራብ ቤት አይመታም ፡
ብየ እንዳልደመድም ፡
በደሌን አንፅቶ ስሜን ያስቀየረ ፡
በፍቅሩ ነው'ንጂ ዳቦው መች ነበረ ።
****
ክብሩን የቀደደ ፡
እርቃን የወለደ ፡
ሰውነት የት ሔደ !!!!!
?
ጠይቅ! ያገሬ ሰው !!!! ....
መብትህን መናድ ፡
ወረቀት ከመቅደድ ፡
አንሶ ሲታያቸው ፡
መረገጥም ሞት ነው ፡
ፈርተህ አትለፈው !!!
!!!!!!?????
****
✍
ዮናስ ፈንታው
@getem
@getem
@gebriel_19
*ቋንቋ ነው *
ገና ከጥንስሱ፣
ሳለ በእሳቤ
መሰረት ሻያሻ፣እንጨት ሳያስፈልጥ፣
ጭቃ ሳያስቦካ ;ማደርያ አበጅቶ
ስጋውን ሲሰፋ፣አጥንቱን ሰክቶ
እርዳታ ሳይፈልግ፣ሳይንሳዊ ጥበብ
ማደሪያውን ብቻ፣ከሔዋን ተውሶ
መሬቷን ፈቅዳለት፣በደስታ አስረክባው
ጥበብ ሲዘራበት፣አምና ተቀብላው
የተፈጥሮን ስቃይ፣ፈቅዳ ተሰቃይታ
የጥበብን ውጤት፣ላሳየች ከስታ
ስጋን ከስጋዋ፣መንጭቀው ለይተው፣
ስቃይን አምክነው
ምድር ላስገኘችው፣
ቀድሞ ለተሰጠው፣ዕድሉ አበድረው
ቤቱን አመስግነው፣መሬቱን ንቀውት
መወለድ ቋንቋ ነው፣ብለው አቀለሉት።
ፀሃፈ ብሩህ
@getem
@getem
@Birukam
ገና ከጥንስሱ፣
ሳለ በእሳቤ
መሰረት ሻያሻ፣እንጨት ሳያስፈልጥ፣
ጭቃ ሳያስቦካ ;ማደርያ አበጅቶ
ስጋውን ሲሰፋ፣አጥንቱን ሰክቶ
እርዳታ ሳይፈልግ፣ሳይንሳዊ ጥበብ
ማደሪያውን ብቻ፣ከሔዋን ተውሶ
መሬቷን ፈቅዳለት፣በደስታ አስረክባው
ጥበብ ሲዘራበት፣አምና ተቀብላው
የተፈጥሮን ስቃይ፣ፈቅዳ ተሰቃይታ
የጥበብን ውጤት፣ላሳየች ከስታ
ስጋን ከስጋዋ፣መንጭቀው ለይተው፣
ስቃይን አምክነው
ምድር ላስገኘችው፣
ቀድሞ ለተሰጠው፣ዕድሉ አበድረው
ቤቱን አመስግነው፣መሬቱን ንቀውት
መወለድ ቋንቋ ነው፣ብለው አቀለሉት።
ፀሃፈ ብሩህ
@getem
@getem
@Birukam
👍1
~ ~ _ _ እንዴት ብዬ ልይሽ ?_ _ ~ ~
(ያለችዉ ባህር ማዶ)
.
# ምንተስኖት_ዋቆ
.
ስሚኝ የኔ እመቤት ፣
የሳሎኔ ዉበት ፣
የህይወቴ ድምቀት ፤
.
ባካል ላላገኝሽ በረሀዉ አይሏል ፣
ከየብሱ ለጥቆ ባህሩ ተኝቷል ፣
ባህሩ ሲታለፍ ፡ አድማስ ተዘርግቷል ፡፡
.
እንዴት ብዬ ልኑር ፡ አይንሽን ሳላየዉ ፣
በሀሳብ ሸራ ላይ ፡ ገላሽን እያየዉ ፡፡
እንዴት ልቋቋመዉ ፡ የናፍቆትሽን በትር ፣
በምን ልሻገረዉ ፡ የለየንን ድንበር ? ::
.
መቼም እጅ አልሰጥም ፣
መቼም ተስፋ አልቆርጥም ፣
አይገድልም ህመም ነዉ
.. .. _ _ _ .. .. የናፍቆት ዉሀ ጥም ::
.
ተስፋ መቀመር ነዉ፡ ተራርቆ ፍቅር ፣
ፈንድቶ የማይለይ፡ በልብ ዉስጥ 'ሚቀር፡፡
ታዲያ እንዴት ልይሽ ?
ድንበሩን አልፌ ፣
ባህሩን ቀዝፌ ፣
ከሀሳብ እንድድን ፡ ገላሽን አቅፌ ፡፡
( ከንፈርሽን ስሜ ::)
.
.
.
# ተፈጠመ
@getem
@getem
@gebriel_19
(ያለችዉ ባህር ማዶ)
.
# ምንተስኖት_ዋቆ
.
ስሚኝ የኔ እመቤት ፣
የሳሎኔ ዉበት ፣
የህይወቴ ድምቀት ፤
.
ባካል ላላገኝሽ በረሀዉ አይሏል ፣
ከየብሱ ለጥቆ ባህሩ ተኝቷል ፣
ባህሩ ሲታለፍ ፡ አድማስ ተዘርግቷል ፡፡
.
እንዴት ብዬ ልኑር ፡ አይንሽን ሳላየዉ ፣
በሀሳብ ሸራ ላይ ፡ ገላሽን እያየዉ ፡፡
እንዴት ልቋቋመዉ ፡ የናፍቆትሽን በትር ፣
በምን ልሻገረዉ ፡ የለየንን ድንበር ? ::
.
መቼም እጅ አልሰጥም ፣
መቼም ተስፋ አልቆርጥም ፣
አይገድልም ህመም ነዉ
.. .. _ _ _ .. .. የናፍቆት ዉሀ ጥም ::
.
ተስፋ መቀመር ነዉ፡ ተራርቆ ፍቅር ፣
ፈንድቶ የማይለይ፡ በልብ ዉስጥ 'ሚቀር፡፡
ታዲያ እንዴት ልይሽ ?
ድንበሩን አልፌ ፣
ባህሩን ቀዝፌ ፣
ከሀሳብ እንድድን ፡ ገላሽን አቅፌ ፡፡
( ከንፈርሽን ስሜ ::)
.
.
.
# ተፈጠመ
@getem
@getem
@gebriel_19