****እኔና አንቺ****
(በረከት በላይነህ)
በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ።
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል፣
ፍራፍሬው ይከበናል፤
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል።
ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ።
ኮከቦቹ!
" ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ።
በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ።
‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣
ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።
@getem
@getem
@gebriel_19
(በረከት በላይነህ)
በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ።
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል፣
ፍራፍሬው ይከበናል፤
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል።
ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ።
ኮከቦቹ!
" ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ።
በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ።
‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣
ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።
@getem
@getem
@gebriel_19
እግር ባይኖርህ መሄጃ፣
ወዳሻህ ቦታ መንጎጃ፣
እንደልብ ባትችል መራመድ፣
የሱን ዉሳኔ ግን ውደድ ።
እይታ ነስቶህ ጨልሞ፣
አለምን ባታይ ፈፅሞ፣
እንዳሳነሰህ ቆጥረኋው፣
ፀጋዉን እንዳትክድ ከስረኋው።
ህመም ፀንቶብህ ክፉኛ፣
ብትሆን ያልጋ ቁራኛ፣
ጨክኖብኛል ብለህ፣
እንዳትሄድ ከሱ ርቀህ።
ሰውን በምድር ሲፈጥር፣
ለሰበብ ነውና ሊሞክር፣
በትዕግስት ላይ ሳትፀና ፣
አትችልም ማለፍ ፈተና።
አካል ቢጎልህ ሰውነት፣
ቢርቅህ ፍፁም ጤንነት፣
በልብህ ተስፋ እስካለ ፣
ብስራት ያዘለ ቀን አለ።
አመስግን በግልፅ በስውር፣
የሱ ነውና ተአምር፣
ተንትነህ ጠልቀህ ካየኸው፣
ያለህ ይበልጣል ካጣኸው።
(Hiku)
@getem
@getem
@getem
ወዳሻህ ቦታ መንጎጃ፣
እንደልብ ባትችል መራመድ፣
የሱን ዉሳኔ ግን ውደድ ።
እይታ ነስቶህ ጨልሞ፣
አለምን ባታይ ፈፅሞ፣
እንዳሳነሰህ ቆጥረኋው፣
ፀጋዉን እንዳትክድ ከስረኋው።
ህመም ፀንቶብህ ክፉኛ፣
ብትሆን ያልጋ ቁራኛ፣
ጨክኖብኛል ብለህ፣
እንዳትሄድ ከሱ ርቀህ።
ሰውን በምድር ሲፈጥር፣
ለሰበብ ነውና ሊሞክር፣
በትዕግስት ላይ ሳትፀና ፣
አትችልም ማለፍ ፈተና።
አካል ቢጎልህ ሰውነት፣
ቢርቅህ ፍፁም ጤንነት፣
በልብህ ተስፋ እስካለ ፣
ብስራት ያዘለ ቀን አለ።
አመስግን በግልፅ በስውር፣
የሱ ነውና ተአምር፣
ተንትነህ ጠልቀህ ካየኸው፣
ያለህ ይበልጣል ካጣኸው።
(Hiku)
@getem
@getem
@getem
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5.pdf
3.2 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5
💰 ፓኬጅ ከገዙ በ 0.70 ብር ብቻ 💰
💰 ፓኬጅ ከገዙ በ 0.70 ብር ብቻ 💰
= ጀግና ያረገኞል=
የወደድሽ ሰምን.......
ፋቅርሽ ሰባኪ ነው ሺህ መናኝ ያስጎዛል
የመነኑት ሁሉ ገድልሽን ይከትባል
ምእመን በሙሉ መናኝ እየሆኑ
ዉዳሴዉ ላንች ነው አቋቋም ሲቆሙ
ዉዳሴው ላንች ነው ቅዳሴ ሲገቡ
እኔም የወደድኩሽ ሰምን....ጀግና ያረገኛል
የምድር ክብነት ውጥቅጡ ጠፍቶኝ
ባንችነት ጥልቀት ውስጥ ተውጨ ቀረሁኝ
አንችነት የጠማው ድርሳኔ በሙሉ
ብራናየ ሳይቀር ብእሬም ተለክፎ ገድልሽን ከተብ
የወደድኩሽ ሰምን..ጀግና ያረገኛል
አንችን የሚነካ ያገፈግፈኛል
የወደድኩሽ ሰምን አያርግብኝ እና.....
ዉዴ ሰይጣን ብቶኝ ጌታም ቢዘምትብሽ
ምእመን ሳይቀሩ በፀበል በፀሎት በውህደት ቢያባሩሽ
የመላክታ ጦር በፈጣሪ ትዛዝ በመብረቅ ቢያሮጡሽ
እንዲህ ያደርገኛል የባቢሉን ዘር ዳግም ነካክቸ
አጣንን በሙሉ በብርጌድ ሰብስቤ ጦር አሰማርቸ
የባቢሎን ዘር ምሽግ አስገብቸ
ለጎልያድ ሹመት ጀነራልን ሹሜ
ለፈርኦን ሳይቀር ሹመትን ሰጥቸ
ጦሬን እሰብቃለው
በጌታ ዘምታለው
የወደድኩሽ ሰምን ...ጀግና ያረገኛል
ኢህአዲግም ባቅሙ ስንት ሰዉ ሲቀጥፍ
የስንት የወንድ ብልት አስልቦ ሲያጠፍ
በማእከላዊ ወህኔ ሄዋን እርቃን ቁማ
እልፍ ሴት ሲደፈር እልፈ ሴት ሲደማ
ህዝቡም በቃኝ ብሎ ለአመፅ ሲወጣ
ስንቱ በምት ብትር በድላ ተቀጣ
ገና ከጥስሱ ይህን ሁሉ ዓመት ህዝቡን ከሚቀጣ
ምናለ አንችየ የወደድኩሽ ሰምን አንችኑ በነካ
ኢህአዲግ የሚባል ድራሹ በጠፋ
እናም የወደድኩሽ ሰምን...ጀግና ያረገኛል
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
✍ገጣሚ ቢኒ እጠየ
19/07/2011
@getem
@getem
የወደድሽ ሰምን.......
ፋቅርሽ ሰባኪ ነው ሺህ መናኝ ያስጎዛል
የመነኑት ሁሉ ገድልሽን ይከትባል
ምእመን በሙሉ መናኝ እየሆኑ
ዉዳሴዉ ላንች ነው አቋቋም ሲቆሙ
ዉዳሴው ላንች ነው ቅዳሴ ሲገቡ
እኔም የወደድኩሽ ሰምን....ጀግና ያረገኛል
የምድር ክብነት ውጥቅጡ ጠፍቶኝ
ባንችነት ጥልቀት ውስጥ ተውጨ ቀረሁኝ
አንችነት የጠማው ድርሳኔ በሙሉ
ብራናየ ሳይቀር ብእሬም ተለክፎ ገድልሽን ከተብ
የወደድኩሽ ሰምን..ጀግና ያረገኛል
አንችን የሚነካ ያገፈግፈኛል
የወደድኩሽ ሰምን አያርግብኝ እና.....
ዉዴ ሰይጣን ብቶኝ ጌታም ቢዘምትብሽ
ምእመን ሳይቀሩ በፀበል በፀሎት በውህደት ቢያባሩሽ
የመላክታ ጦር በፈጣሪ ትዛዝ በመብረቅ ቢያሮጡሽ
እንዲህ ያደርገኛል የባቢሉን ዘር ዳግም ነካክቸ
አጣንን በሙሉ በብርጌድ ሰብስቤ ጦር አሰማርቸ
የባቢሎን ዘር ምሽግ አስገብቸ
ለጎልያድ ሹመት ጀነራልን ሹሜ
ለፈርኦን ሳይቀር ሹመትን ሰጥቸ
ጦሬን እሰብቃለው
በጌታ ዘምታለው
የወደድኩሽ ሰምን ...ጀግና ያረገኛል
ኢህአዲግም ባቅሙ ስንት ሰዉ ሲቀጥፍ
የስንት የወንድ ብልት አስልቦ ሲያጠፍ
በማእከላዊ ወህኔ ሄዋን እርቃን ቁማ
እልፍ ሴት ሲደፈር እልፈ ሴት ሲደማ
ህዝቡም በቃኝ ብሎ ለአመፅ ሲወጣ
ስንቱ በምት ብትር በድላ ተቀጣ
ገና ከጥስሱ ይህን ሁሉ ዓመት ህዝቡን ከሚቀጣ
ምናለ አንችየ የወደድኩሽ ሰምን አንችኑ በነካ
ኢህአዲግ የሚባል ድራሹ በጠፋ
እናም የወደድኩሽ ሰምን...ጀግና ያረገኛል
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
✍ገጣሚ ቢኒ እጠየ
19/07/2011
@getem
@getem
◍ አ ል ረ ሳ ሁ ት ም ◍
(© ቸርነት ኃይሉ)
-
እዝጌር ሥራው ብዙ
ሊያጠናኝ ፈልጎ ወይስ ምናውቄ
ተመንጋው ነጥሎኝ ተጭንጫ ወድቄ
ባለቀስኩ ጊዜ ትጮህ በነበረ
ማነው ለጠሎቴ ክንዱን የገበረ
ማነው ታንቺ ቀድሞ ደርሶ የነበረ?
-
ይሄ ሁለት እግር...
ሰው የሚባል ፍጡር፣ ዐለሙን የሞላ
መለገስን ያልሻ ተምራቁ ሌላ
የከንፈሩ መምጠጥ ሙዚኣዬ ሆኖ
ትቆጥር እንዳልዋልኩ ስንት የምራቅ ቦኖ
እንደ ክርስቶስ ፊት፣ የደሙ ወለላ
እንባዬን ያበሰ ማነው ታንቺ ሌላ?
-
አልረሳም አልረሳም...
የኔ ቬሮኒካ፣ የኔ ባለ በፍታ
እራፊ ጨርቅሽን አሽትቻለሁ ላፍታ
ያ ነጭ አንገትልብስሽ ዐይኖቼን ያበሰ
ለነበዘ ፊቴ
ባ'ዳም ልጆች ዐይን፥ ግርፊያ ለኮሰሰ
ተምን ብታሰሪው እንዲያ ለሰለሰ?
-
ሀገር ሙሉ ቢላ፤ ሰማይ ሙሉ ህንጣ
ሺ የመብል ዐይነት፣ እንጢቅ የሚጠጣ
በሞላበት ህዋ፣ በሞላበት ቀየ
ጉምዣው ቲያታግለኝ
ባለቀስኩ ጊዜ ዐይኔ በጨቀየ
ታንቺ የቀደመ ተ'ዝጌር የዘገየ
ማነው እንደንስር ተሩቅ ቁስሌን ያየ?
-
ሰማይ በሮቢላ፣ የብሱ በመሂና
በታንኳ ተሞልተው አባይና ጣና
እኔ የዝጌር ቁጫጭ፣ ያምሳ'ግር ጓደኛ
ስጓዝ ውየ'ማድር የጊዜ ምርኮኛ
አንሸራቶኝ ትወድቅ ወደ ጥልቁ ስ'ላክ
ማን ቀድሞሽ አወጣኝ፣ ማን የሚሉት መላክ?
-
ፈፋ ብቻ ቲሆን ሀገሩ ጠቅላላ
ተጭኖችሽ ወዲያ ~ እንጠላጠልበት ~ የት አገኘሁ ባላ?
ክረምት አልፏል ብዬ
ያስጠለለችኝን ጎጆሽን አልዘልፍም
በ'ግሬ ቆምሁ ብዬ
የተሸከመኝን እግርሽን አልጠልፍም
ምንስ ጊዜ ቢሄድ፣ ምንስ ቀኖች ቢያልፉ
ምንስ ክፉ እጣዎች
እንደ በጋ ቅጠል ተፊቴ ቢረግፉ
እኔ ማን ነኝና፥ ማን ብባል ነውሳ
ተኒያ ዘንዶ ቀኖች
ያመለጥኩበትን ጉያሽን ምረሳ!?
@getem
@getem
@gebriel_19
(© ቸርነት ኃይሉ)
-
እዝጌር ሥራው ብዙ
ሊያጠናኝ ፈልጎ ወይስ ምናውቄ
ተመንጋው ነጥሎኝ ተጭንጫ ወድቄ
ባለቀስኩ ጊዜ ትጮህ በነበረ
ማነው ለጠሎቴ ክንዱን የገበረ
ማነው ታንቺ ቀድሞ ደርሶ የነበረ?
-
ይሄ ሁለት እግር...
ሰው የሚባል ፍጡር፣ ዐለሙን የሞላ
መለገስን ያልሻ ተምራቁ ሌላ
የከንፈሩ መምጠጥ ሙዚኣዬ ሆኖ
ትቆጥር እንዳልዋልኩ ስንት የምራቅ ቦኖ
እንደ ክርስቶስ ፊት፣ የደሙ ወለላ
እንባዬን ያበሰ ማነው ታንቺ ሌላ?
-
አልረሳም አልረሳም...
የኔ ቬሮኒካ፣ የኔ ባለ በፍታ
እራፊ ጨርቅሽን አሽትቻለሁ ላፍታ
ያ ነጭ አንገትልብስሽ ዐይኖቼን ያበሰ
ለነበዘ ፊቴ
ባ'ዳም ልጆች ዐይን፥ ግርፊያ ለኮሰሰ
ተምን ብታሰሪው እንዲያ ለሰለሰ?
-
ሀገር ሙሉ ቢላ፤ ሰማይ ሙሉ ህንጣ
ሺ የመብል ዐይነት፣ እንጢቅ የሚጠጣ
በሞላበት ህዋ፣ በሞላበት ቀየ
ጉምዣው ቲያታግለኝ
ባለቀስኩ ጊዜ ዐይኔ በጨቀየ
ታንቺ የቀደመ ተ'ዝጌር የዘገየ
ማነው እንደንስር ተሩቅ ቁስሌን ያየ?
-
ሰማይ በሮቢላ፣ የብሱ በመሂና
በታንኳ ተሞልተው አባይና ጣና
እኔ የዝጌር ቁጫጭ፣ ያምሳ'ግር ጓደኛ
ስጓዝ ውየ'ማድር የጊዜ ምርኮኛ
አንሸራቶኝ ትወድቅ ወደ ጥልቁ ስ'ላክ
ማን ቀድሞሽ አወጣኝ፣ ማን የሚሉት መላክ?
-
ፈፋ ብቻ ቲሆን ሀገሩ ጠቅላላ
ተጭኖችሽ ወዲያ ~ እንጠላጠልበት ~ የት አገኘሁ ባላ?
ክረምት አልፏል ብዬ
ያስጠለለችኝን ጎጆሽን አልዘልፍም
በ'ግሬ ቆምሁ ብዬ
የተሸከመኝን እግርሽን አልጠልፍም
ምንስ ጊዜ ቢሄድ፣ ምንስ ቀኖች ቢያልፉ
ምንስ ክፉ እጣዎች
እንደ በጋ ቅጠል ተፊቴ ቢረግፉ
እኔ ማን ነኝና፥ ማን ብባል ነውሳ
ተኒያ ዘንዶ ቀኖች
ያመለጥኩበትን ጉያሽን ምረሳ!?
@getem
@getem
@gebriel_19
የቀበሮ ፀሎት
(ታገል ሰይፉ)
------
እባክህ አምላኬ- ብትሬን ቀባና
እኔም ልወዝወዘው-የሙሴን ጎዳና
ያላንዳች ፍርሃት-ያለምንም ችግር
ባህሩን ከፍዬ- ህዝቤን እንዳሻግር፡፡
*
አቤት የኔ ጌታ ይህም አያረካም
በቃልህ ታምኜ -ከሆንኩልህ መልካም
ለእኔም ፍቀድልኝ-ያብራምን ምልክት
ከምድር አሸዋ-ዘሬ እንዲበረክት፡፡
*
አቤቱ ምን ልሁን-ይህም አልጠቀመኝ
እስቲ እንደ ዮናስ-ህዝብ ፊት አቁመኝ
*
ትንቢቴን ሰምቶልኝ-ሀገር ይተራመስ
ሰው እህል ይጡም-ከብቱም ሳር አይቅመስ፡፡
ይህም አያረካም-ይልቅ እንደዳዊት
አንተን በሚፈራ-ብዙ ሺህ ሠራዊት
ዙፋኔ ተከቦ-በደስታ እንዳመልክህ
የዚህን ሰው ኮከብ -አውጣልኝ እባክህ
*
አደራህን ታዲያ- ጭንቅ አትወድም ነፍሴ
ልመናዬን ሰምተህ-ካደረግከኝ ሙሴ
መከራውን ማረኝ-ያርባ ዓመት ስደቱን
በሲና በረሃ-መራብ መጠማቱን፡፡
*
ነቢዩ ዮናስን -አርገህም ስትፈጥረኝ
የባህሩን ፍዳ- ያሳውን ሆድ ማረኝ፡፡
*
አብረሃምን ሆኜም-በደስታ ሳመልክህ
ልጅህን እረደው-አትበለኝ እባክህ፡፡
***
የዲዊትም ኮከብ-በኔ ላይ ሲወጣ
እባክህ አምላኬ -ጎልያድ አይምጣ፡፡
@getem
@getem
@gebriel_19
(ታገል ሰይፉ)
------
እባክህ አምላኬ- ብትሬን ቀባና
እኔም ልወዝወዘው-የሙሴን ጎዳና
ያላንዳች ፍርሃት-ያለምንም ችግር
ባህሩን ከፍዬ- ህዝቤን እንዳሻግር፡፡
*
አቤት የኔ ጌታ ይህም አያረካም
በቃልህ ታምኜ -ከሆንኩልህ መልካም
ለእኔም ፍቀድልኝ-ያብራምን ምልክት
ከምድር አሸዋ-ዘሬ እንዲበረክት፡፡
*
አቤቱ ምን ልሁን-ይህም አልጠቀመኝ
እስቲ እንደ ዮናስ-ህዝብ ፊት አቁመኝ
*
ትንቢቴን ሰምቶልኝ-ሀገር ይተራመስ
ሰው እህል ይጡም-ከብቱም ሳር አይቅመስ፡፡
ይህም አያረካም-ይልቅ እንደዳዊት
አንተን በሚፈራ-ብዙ ሺህ ሠራዊት
ዙፋኔ ተከቦ-በደስታ እንዳመልክህ
የዚህን ሰው ኮከብ -አውጣልኝ እባክህ
*
አደራህን ታዲያ- ጭንቅ አትወድም ነፍሴ
ልመናዬን ሰምተህ-ካደረግከኝ ሙሴ
መከራውን ማረኝ-ያርባ ዓመት ስደቱን
በሲና በረሃ-መራብ መጠማቱን፡፡
*
ነቢዩ ዮናስን -አርገህም ስትፈጥረኝ
የባህሩን ፍዳ- ያሳውን ሆድ ማረኝ፡፡
*
አብረሃምን ሆኜም-በደስታ ሳመልክህ
ልጅህን እረደው-አትበለኝ እባክህ፡፡
***
የዲዊትም ኮከብ-በኔ ላይ ሲወጣ
እባክህ አምላኬ -ጎልያድ አይምጣ፡፡
@getem
@getem
@gebriel_19
❤3
ቅድሚያ!
~~~~~~
ባልተኛው ልባችን ~ ቀልደኛው ልባችን ~ ከእውነት ቢታረቅም
ተጓዥ ያናንቃል ~ ጉዞ ካልጀመሩ ~ ለሀሳብ አይርቅም
ፊት እየቀደመ ~ ምኞት ከእርምጃ ~ ንግግር ከስራው
የዘመኔ ዳዊት
ጎልያድን ሳይሆን ~ ጠጠር መልቀሙን ነው ~ በብርቱ ሚፈራው
(በረከት ታደሰ)
@getem
@getem
@lula_al_greeko
~~~~~~
ባልተኛው ልባችን ~ ቀልደኛው ልባችን ~ ከእውነት ቢታረቅም
ተጓዥ ያናንቃል ~ ጉዞ ካልጀመሩ ~ ለሀሳብ አይርቅም
ፊት እየቀደመ ~ ምኞት ከእርምጃ ~ ንግግር ከስራው
የዘመኔ ዳዊት
ጎልያድን ሳይሆን ~ ጠጠር መልቀሙን ነው ~ በብርቱ ሚፈራው
(በረከት ታደሰ)
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ሲገባህ ውደደኝ
✍(ገነት ሽብሩ)
.
.
ወርቁ ሞኝነት ነው ፣ ሰም ያጣ ቅኔ
በስም አልባ ስሜቶች
ከህሊናህ ጓዳ....
መውደድ ይሁን ፣ መጥላት
መላቅ ይሁን ፣ መዝቀጥ
መኖር ይሁን ፣ መጥፋት፡
ድሎት አይሉት ፍዳ
ሀሴት አይሉት ፣ ዋይታ
ልብህን እያመሠ ፣ መንፈስህን ሲረታ
አከላትህ ዝሎ ፣ ፍቅር ትርጉም ሲያጣ
ካንድ ወገን ላልሆነ ፣ ለስሜት ዲቃላ
በግድድር ልሳን ፣ መኖርን ላነጋ
ቃላቴ ሳሱብኝ ፣ ምን ብዬ ላውጋህ?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እስቲ ጌታን ሹፈው....
በሰራቸው እጆች ፣ በጥፊ ሲመታ
የጠፋን ሊያገኝ ፣ ማንነቱን ሲያጣ
ተንቆ ጌታ ፣ ተገፍቶ መምህሬ
ፍቅሩን አስረዳ ፣ በደሙ ጠመኔ፡፡
ግን ለምን ስትል...
አጀብ ነው ብለው ፣ ጊንየስ ላይ መዝግበው
ሊፈምስ አይደለም
ያው...ፍቅር....ነው
ያው....መውደድ...ነው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለጊዜ ስትል ፣ ባልገባህ ስሜት
ባላየህ ባልኖርክበት ፣ ወድሻለው አትበለኝ
ይልቅ ሌላውን ትተህ ፣ ሲገባህ ውደደኝ፡፡
★★★
✍(ገነት ሽብሩ)
@getem
@getem
@gebriel_19
✍(ገነት ሽብሩ)
.
.
ወርቁ ሞኝነት ነው ፣ ሰም ያጣ ቅኔ
በስም አልባ ስሜቶች
ከህሊናህ ጓዳ....
መውደድ ይሁን ፣ መጥላት
መላቅ ይሁን ፣ መዝቀጥ
መኖር ይሁን ፣ መጥፋት፡
ድሎት አይሉት ፍዳ
ሀሴት አይሉት ፣ ዋይታ
ልብህን እያመሠ ፣ መንፈስህን ሲረታ
አከላትህ ዝሎ ፣ ፍቅር ትርጉም ሲያጣ
ካንድ ወገን ላልሆነ ፣ ለስሜት ዲቃላ
በግድድር ልሳን ፣ መኖርን ላነጋ
ቃላቴ ሳሱብኝ ፣ ምን ብዬ ላውጋህ?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እስቲ ጌታን ሹፈው....
በሰራቸው እጆች ፣ በጥፊ ሲመታ
የጠፋን ሊያገኝ ፣ ማንነቱን ሲያጣ
ተንቆ ጌታ ፣ ተገፍቶ መምህሬ
ፍቅሩን አስረዳ ፣ በደሙ ጠመኔ፡፡
ግን ለምን ስትል...
አጀብ ነው ብለው ፣ ጊንየስ ላይ መዝግበው
ሊፈምስ አይደለም
ያው...ፍቅር....ነው
ያው....መውደድ...ነው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለጊዜ ስትል ፣ ባልገባህ ስሜት
ባላየህ ባልኖርክበት ፣ ወድሻለው አትበለኝ
ይልቅ ሌላውን ትተህ ፣ ሲገባህ ውደደኝ፡፡
★★★
✍(ገነት ሽብሩ)
@getem
@getem
@gebriel_19
*እጦት*
አንዳች ስሜት ነገር ነፍስያዬን ከባት ናፍቆት ሲናፍቀኝ
ካቀረቀርኩበት ቀና ብዬ ባየው ሠማዮ ቀረበኝ
............................
በጠራው ሠማይ ላይ በአምላክ እጅ ያጌጠ ምስልህ እየታየኝ
ነፍስህ በሀሴት ረቃ ፈገግታ ስትጭር ውብ ሣቅህ ናፈቀኝ
............................
የሣቅህ ውብ ዜማ የጥርሶችህ ድርድር
ዕንባዬን አብሶት ከደስታ ማማ ላይ ነፍሴን ሲያንደረድር
...........................
ደመናው ከለለኝ ጉም ጋረደው ዓይኔን ሠማዮ 'ራቀኝ
የማግኘት ጣረ ሞት ንጋቴን አፅልሞት ካንተ ሊያራርቀኝ
...........................
ለካስ...
በዕምነት የተኳለ ያፍቃሪ ልብ እውነት ስቃይ ነው ማለፊያው
ጎጆ ያልቀለሠ ማደሪያ ያጣ ወፍ ክንፉ ነው ማረፊያው
............................
አንተ ትቀርብ እንደው ላምላክ ንገርልኝ የማይቻል ያስችለኝ
የናፈኸኝ ለታ ሠማይ ዝቅ ብላ ካንተ ታገናኘኝ
............................
ግና ...
አልሠመረም መሠል
የቃየል እርግማን በኔ ላይ ደረሠ ምድር ፍሬ ነሣኝ
አይኖቼ ተራቡህ ነፍሴ ተጨነቀ ተቅበዝብዥ አረነኝ
.............................
ምነው ባትናፍቀኝ ነፍሴን ባታርደው
ምናለ ብረሣህ ብጠላህ አንተ ሠው
............................
እንዴውም ጠላሁህ አትውደደኝ ይቅር
ሠማይ በጥፍ ይራቅ እዛው ይበል ጥንቅር
............................
ፍቅር ማለት ምነው በጥላቻ አለም
የምን እንባ ማፍሰስ ዘላለም መታመም
...........................
ክህደት እያለ ምን ያረጋል ዕምነት
በሐሠት እያወጉ ምን ይረባል እውነት
..........................
ደግሞም ጠልተኸኛል ይህንን አውቃለሁ
በአንተ ትርጓሜ እምነት ክህደት ነው
...........................
ታምነኝ ይሆን ብዬ እጄን ብዘረጋ
አንተ ጠርጣሪ ሠው ልብህ የማይረጋ
...........................
አትውደደኝ ይቅር ...
እንድትወደኝ ብዬ ህልሜን ከምገፋ
ጠልተኸኝ ልታመም ዘመኔን ልገፋ
............................
እንደውም ጠላሁህ አልውደድህ ይቅር
ሠማይ በጥፍ ይራቅ እዛው ይበል ጥንቅር
............................
ግና...
በአፍቃሪ ልክ ዕምነት
ጥላቻ ፍቅር ነው ያልመተረው ልኬት
...................//...................
ተፃፈ በሔለን ፋንታሁን
@getem
@getem
አንዳች ስሜት ነገር ነፍስያዬን ከባት ናፍቆት ሲናፍቀኝ
ካቀረቀርኩበት ቀና ብዬ ባየው ሠማዮ ቀረበኝ
............................
በጠራው ሠማይ ላይ በአምላክ እጅ ያጌጠ ምስልህ እየታየኝ
ነፍስህ በሀሴት ረቃ ፈገግታ ስትጭር ውብ ሣቅህ ናፈቀኝ
............................
የሣቅህ ውብ ዜማ የጥርሶችህ ድርድር
ዕንባዬን አብሶት ከደስታ ማማ ላይ ነፍሴን ሲያንደረድር
...........................
ደመናው ከለለኝ ጉም ጋረደው ዓይኔን ሠማዮ 'ራቀኝ
የማግኘት ጣረ ሞት ንጋቴን አፅልሞት ካንተ ሊያራርቀኝ
...........................
ለካስ...
በዕምነት የተኳለ ያፍቃሪ ልብ እውነት ስቃይ ነው ማለፊያው
ጎጆ ያልቀለሠ ማደሪያ ያጣ ወፍ ክንፉ ነው ማረፊያው
............................
አንተ ትቀርብ እንደው ላምላክ ንገርልኝ የማይቻል ያስችለኝ
የናፈኸኝ ለታ ሠማይ ዝቅ ብላ ካንተ ታገናኘኝ
............................
ግና ...
አልሠመረም መሠል
የቃየል እርግማን በኔ ላይ ደረሠ ምድር ፍሬ ነሣኝ
አይኖቼ ተራቡህ ነፍሴ ተጨነቀ ተቅበዝብዥ አረነኝ
.............................
ምነው ባትናፍቀኝ ነፍሴን ባታርደው
ምናለ ብረሣህ ብጠላህ አንተ ሠው
............................
እንዴውም ጠላሁህ አትውደደኝ ይቅር
ሠማይ በጥፍ ይራቅ እዛው ይበል ጥንቅር
............................
ፍቅር ማለት ምነው በጥላቻ አለም
የምን እንባ ማፍሰስ ዘላለም መታመም
...........................
ክህደት እያለ ምን ያረጋል ዕምነት
በሐሠት እያወጉ ምን ይረባል እውነት
..........................
ደግሞም ጠልተኸኛል ይህንን አውቃለሁ
በአንተ ትርጓሜ እምነት ክህደት ነው
...........................
ታምነኝ ይሆን ብዬ እጄን ብዘረጋ
አንተ ጠርጣሪ ሠው ልብህ የማይረጋ
...........................
አትውደደኝ ይቅር ...
እንድትወደኝ ብዬ ህልሜን ከምገፋ
ጠልተኸኝ ልታመም ዘመኔን ልገፋ
............................
እንደውም ጠላሁህ አልውደድህ ይቅር
ሠማይ በጥፍ ይራቅ እዛው ይበል ጥንቅር
............................
ግና...
በአፍቃሪ ልክ ዕምነት
ጥላቻ ፍቅር ነው ያልመተረው ልኬት
...................//...................
ተፃፈ በሔለን ፋንታሁን
@getem
@getem
#ኡስታዙ_እና_ቄሱ
ከውሰር[ጋዜጠኛው ዶክተር]
.
በዚህች ጠባብ ሀገር፣በዚህች በአንድ ምድር፤
ቄሱ እና ኡስታዙ አይተናኮስም፣በወል ነው የሚያድር።
.
ይሄ ጀግና ኡስታዝ አማማውን ታጥቆ፣ሙደወሩን ለብሶ፤
ፂሙን አስረዝሞ ሱሪውን አሳጥሮ፤ከቁርአን አጣቅሶ፤
ከመስጂዱ ቅጥር፣ሲያሰግድ ይውላል ኻምሴ ተመላልሶ።
ከሰላት ቡሀላም ዲስኩር ይጀምራል፣ወደ ኡማው ዞሮ፤
የአንድዬን እዝነት፣የአምላክን ቀጪነት፣ይነግራል ዘርዝሮ።
፡
ይሄም ጀግና ፓፓስ፣መስቀሉን ጨብጦ፣ካባውን ደርቦ፤
ውቡን አክሊል ለብሶ፣ይገባል ቤተስቲያን፣ከምእመናን ቀርቦ።
መርጌታው ሲያስተምር፣የያሬድን ዜማ፤
ዲያቆኑ ይቀድሳል፣የእግዜርን ቃላት፣ለህዝቡ ሊያሰማ።
መምህሩም ለህዝቡ፣ሠላም ይሰብካሉ፤
ቄሱም ፀበል ረጭተው፣በስም አብ ይላሉ።
፡
እንዲህ ናት ሀገሬ፣ይህች ጠባብ ምድር፤
ቄሱ እና ኡስታዙ፣አይተናኮልም፣በወል ነው የሚያድር።
፡
አሀዱ አምላክ ብለው፣ቤተስቲያን ገብተው፣ሲቀድሱ ቄሱ፤
ከመስጂዱ ቅጥር፣አላሁ አክበር አሉ፣ጌታን ሲያወድሱ፤
በስም አብ ብለው፣ስብከት ሲጀምሩ፣ቄሱ ለምእመናን፤
ቢስሚላህ ብለው ነው፣ኡስታዝ የሚያሰሙት፣ሚጀምሩት ዳእዋን።
፡
እንዲህ ናት ሀገሬ፣ይህች ጠባብ ምድር፤
ሙስሊም ክርስቲያኑ አይተናኮስም፣በወል ነው የሚያድር።
፡
#Kewser
@getem
@getem
@getem
ከውሰር[ጋዜጠኛው ዶክተር]
.
በዚህች ጠባብ ሀገር፣በዚህች በአንድ ምድር፤
ቄሱ እና ኡስታዙ አይተናኮስም፣በወል ነው የሚያድር።
.
ይሄ ጀግና ኡስታዝ አማማውን ታጥቆ፣ሙደወሩን ለብሶ፤
ፂሙን አስረዝሞ ሱሪውን አሳጥሮ፤ከቁርአን አጣቅሶ፤
ከመስጂዱ ቅጥር፣ሲያሰግድ ይውላል ኻምሴ ተመላልሶ።
ከሰላት ቡሀላም ዲስኩር ይጀምራል፣ወደ ኡማው ዞሮ፤
የአንድዬን እዝነት፣የአምላክን ቀጪነት፣ይነግራል ዘርዝሮ።
፡
ይሄም ጀግና ፓፓስ፣መስቀሉን ጨብጦ፣ካባውን ደርቦ፤
ውቡን አክሊል ለብሶ፣ይገባል ቤተስቲያን፣ከምእመናን ቀርቦ።
መርጌታው ሲያስተምር፣የያሬድን ዜማ፤
ዲያቆኑ ይቀድሳል፣የእግዜርን ቃላት፣ለህዝቡ ሊያሰማ።
መምህሩም ለህዝቡ፣ሠላም ይሰብካሉ፤
ቄሱም ፀበል ረጭተው፣በስም አብ ይላሉ።
፡
እንዲህ ናት ሀገሬ፣ይህች ጠባብ ምድር፤
ቄሱ እና ኡስታዙ፣አይተናኮልም፣በወል ነው የሚያድር።
፡
አሀዱ አምላክ ብለው፣ቤተስቲያን ገብተው፣ሲቀድሱ ቄሱ፤
ከመስጂዱ ቅጥር፣አላሁ አክበር አሉ፣ጌታን ሲያወድሱ፤
በስም አብ ብለው፣ስብከት ሲጀምሩ፣ቄሱ ለምእመናን፤
ቢስሚላህ ብለው ነው፣ኡስታዝ የሚያሰሙት፣ሚጀምሩት ዳእዋን።
፡
እንዲህ ናት ሀገሬ፣ይህች ጠባብ ምድር፤
ሙስሊም ክርስቲያኑ አይተናኮስም፣በወል ነው የሚያድር።
፡
#Kewser
@getem
@getem
@getem
-------አበሱዳ----------
==================
ልቤ አረገደ -ላንዲት ወሸባ ፣
ለመልከ ልዩ- ለወር ቀዘባ ፣
-------------—-------------------
----------
ወሸኔ ናት እሷ-የወርቅ ፍልቃቂ፣
አይን የምትሞላ ሴት - የሰው ቀልብ ሰራቂ።
----------------------------
የአትክል ስፍራ - እንደሚያምረው ሁላ፣
አይንን እንደሚስበው-እንደ ወይን ዘለላ፣
----------------
እንዴው ባንድ ቦታ - ድንገት ካገደመች፣
የሰው አይን ማረፊያ -ጉዳይ ትሆናለች።
------------------
መዳኒት ነች እሷ -እንደ ወርቅ በሜዳ፣
እንደ ጥቁሩ ፍሬ -ልክ እንዳበሱዳ፣
-----------------------
ከሷ ፈውስ ፈላጊ-ታማሚው በዛና፣
እልፍ ሆነ ከቤቷ-ደጇን የሚጠና።
-----------------
ከተለየ ጭቃ ውብ አድርጎ ፈጥሯት፣
ያያት ፈዞ ቀረ -እንኳን ያፈቀራት።
----------------------
ፈላጊዋ አሸን -ብዙ ነው ሚመኛት ፣
ጠበበኝ መንገዱ - ከሷ ምደርስበት።
------------------
ድምቀት ሆናቸው- ብርሃን ለሰፈር፣
ቆሌያቸው ሆና - ለነሱ አድባር፣
እንዳይናቸው ብሌን -ያዩዋታል በፍቅር ።
-------------
አንዋር እሁድ 13/08/11
@getem
@getem
@getem
==================
ልቤ አረገደ -ላንዲት ወሸባ ፣
ለመልከ ልዩ- ለወር ቀዘባ ፣
-------------—-------------------
----------
ወሸኔ ናት እሷ-የወርቅ ፍልቃቂ፣
አይን የምትሞላ ሴት - የሰው ቀልብ ሰራቂ።
----------------------------
የአትክል ስፍራ - እንደሚያምረው ሁላ፣
አይንን እንደሚስበው-እንደ ወይን ዘለላ፣
----------------
እንዴው ባንድ ቦታ - ድንገት ካገደመች፣
የሰው አይን ማረፊያ -ጉዳይ ትሆናለች።
------------------
መዳኒት ነች እሷ -እንደ ወርቅ በሜዳ፣
እንደ ጥቁሩ ፍሬ -ልክ እንዳበሱዳ፣
-----------------------
ከሷ ፈውስ ፈላጊ-ታማሚው በዛና፣
እልፍ ሆነ ከቤቷ-ደጇን የሚጠና።
-----------------
ከተለየ ጭቃ ውብ አድርጎ ፈጥሯት፣
ያያት ፈዞ ቀረ -እንኳን ያፈቀራት።
----------------------
ፈላጊዋ አሸን -ብዙ ነው ሚመኛት ፣
ጠበበኝ መንገዱ - ከሷ ምደርስበት።
------------------
ድምቀት ሆናቸው- ብርሃን ለሰፈር፣
ቆሌያቸው ሆና - ለነሱ አድባር፣
እንዳይናቸው ብሌን -ያዩዋታል በፍቅር ።
-------------
አንዋር እሁድ 13/08/11
@getem
@getem
@getem
#እንድቅትዮን ፬
ዕንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው በገነት መናፈሻ
#ማክሰኞ ሚያዚያ 29 2011ዓ.ም.
አመሻሹ 11:30
መግቢያ ዋጋ 50 ብር
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ዕንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው በገነት መናፈሻ
#ማክሰኞ ሚያዚያ 29 2011ዓ.ም.
አመሻሹ 11:30
መግቢያ ዋጋ 50 ብር
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja