ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል
(ልዑል ሀይሌ)
.
አንድ ሐሙስ ቀርቶታል ይላሉ
አዎ አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል
ጌታ በመጨረሻው እራት
በትህትና አጥቦኛል
.
አዎ አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል
.
ጌታዬን በ30 ዲናር ልሸጥ
ተደራድሬ መጥቻለሁ
ግን እንደሚያነፃኝ ስለማምን
እንደሚነሳ ስለማውቅ
ይሁን ስቀሉት ብያለሁ
.
አዎ አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል!.
.
የሐጢያትን ቀንበር ላወርድ
በስቅላቱ ልነፃ
በስጋ ደሙ ሊያጥበኝ
የአዳምን የዕዳ ደብዳቤ
ቀዶ አዳምን ነፃ ሊያወጣ
የዕዳ ደብዳቤው ክታብ
ከጀርባዬ ላይ አርፎ
ክፉ ልቤ ጌታን ሸጠው
30 ዲናር አትርፎ
.
አዎ አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል!
.
የትንቢቱ መፈፀሚያ
ጊዜው እንዳይርቃችሁ
የመጨረሻው ሐሙስ ቀን
ዛሬ ጌታዬን ሼጬ
ጌታዬን ሰቅዬ ነው
ተዓምሩን ማሳያችሁ
.
አዎ አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል!
.
ሐጢያቴ ሊደመሰስ
ልታጠብ በአዲስ ህይወት
መድህን ይሆን ዘንድ ሊቸነከር
ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሊሞት
.
ይኸው ሰማዪ ጠቋቁሯል
ጌታ ለመጨረሻው እራት ጠርቶኛል
አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል!!
27-07-2010

@getem
@getem
@gebriel_19
እርቃን
-------
ጨረቃውም ቀላ፣ፀሐዩም ጠቆረ
ግዑዝ ባምላኩ ቃል...
እርቃን የመደበቅ፣ሚስጥርን ተማረ
.
ሰውም ሰለጠነ፣መጠቀ በረረ
ነገር ግን እሳቤው፣ከግዑዝ አጠረ
እንኳን የሰው እርቃን…
የራሱን መሸፈን፣ ይሳነው ጀመረ
.
« ሚኪ እንዳለ »

@getem
@getem
ቃል
#ፀሀፈ ብሩህ

የአካሌ ንዝረት
ስሜቴ ተዋቅሮ
ለልሳን ከሳቹ
ከንፈሬ አቀብሎ
ነበር የኔ ቃል
አካልሽን ገንቢ፣ከስሜትሽ አልፎ
ከኔ እኩል ያረገሽ፣ጎደሎሽን ሞልቶ
ነበር የደረስነው
ለቆየው ፍቅራችን
ፍቅርን በገነባ
በቃል ሳይበተን።

@Birukam

@getem
@getem
🙏እለተ ሀሙስ🙏
------------------
የህዝባችን ልቡ በክፍት ስለጓደፈ
የአባቶች ማንነት
በልጅ ልጆች ሀሳብ
ዘቅጦ ስላደፈ
ከዚህ ሁሉ ጥፋት
የወንበሩ አለቃ
እራሱን ለማንጻት
እጁን ከሚታጠብ፤
ጥቂት ወረድ በሎ
የምእመናኑን ልብ
እስከ ስሩ ይጠብ።

ፀጋየ ግርማ እረቲ(ሜሎስ)

@getem
@getem
#ሴይጣን_ሆይ_ዛሬ_ትቃጠላለህ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም የሚሰግዱበት ያመቱ ጁወዓ ነው።
ሄለን ፋንታሁን

ሳሚኝ ሳሚኝ አትበል መሣም እፈራለሁ
የተሣመ ታሞ ተሠቅሎ ስላየሁ



@getem
@getem
@gebriel_19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
...ፍረደን...
ስማኝማ አንድዬ
አራት መቶ ጅራፍ ተቆጥሮ የማያልቅ ስፍር የለሽ በደል
ለከፈልክባት ቀን እንኳን አደረሰህ አይባልም አይደል
የሰማዕታት ሀገር የፃድቃን ከተማ
ፅርሐዓርያም እንዴት ነው በበዓል ዋዜማ
ከዙፋንህ ግርጌ ቄጠማ ጎዝጉዘው እያሸበሸቡ
ሰውና መላእክት በአንድ ሲሰበሰቡ
ከመላእክት ምግብ ፃድቃን ሲመገቡ
ሰማይ ቤት እንዴት ነው የበዓል ድባቡ
ትዝ ይልሀል አይደል ?
አልጋውን አስይዘህ ያ'ዘለልከው ድኩም
አላውቀውም ብሎ የመታህ በኩርኩም
እንዴት ነው መፃጉ ኑሮ እንዴት ይዞታል
ቸርነትህ ደርሶት እርሱም ገነት ገብቷል
ወይስ የሲዖል ፍም እሣት ተስማምቶታል
ኑሮ ከተባለ እኛ አለን እንዳለን
አንተን መስለንና ያንተን አስመስለን
እንደ ኮሶ እንደ ሬት ኑሮ እየመረረን
እኔን ምሰሉ ሚል ቃልህን አክብረን
ሰውን ያክል ክቡር ነፍስ ተሸክመን
ታክሞ የማይድን ስልጡን ከብት አክመን
አድናለሁ ስንል እራሳችን ታመን
ሰርዷችንን ግጦ የጠገበ ኮርማ ዞሮ እየረገጠን
ወርቅ የሰፈርንለት አመድና ትቢያ አፈር እየሰጠን
ኑሮ ከተባለ እኛ አለን እንዳለን
አንተን መሆን ባንችል ያንተን አስመስለን
እናልህ አንድዬ
እንዳይጎርስ ለጉመው እንዳይሄድ ቀይደው
ከቤት እንዳይወጣ በጥዋት ጥመደው
የሚል ህግና ደንብ በዝባዥ አዋጅ ወጥቶ
ተመጥምጦ አለቀ ጉልበታችን ሟሙቶ
በራሳቸው ችሎት
ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ዳኛ ሆነው እየቀጡን
ውኃ ጠማን ስንል ሆምጣጤ እያጠጡን
ከኩንታል ሙሉ ማር ሸክማችን ከበደ
ወዳንተ እንዳንመጣ ጉልበታችን ራደ
እንደ ልባሽ ጋቢ ዋጋችን ቀለለ
እባክህ ቶሎ ና ትክሻችን ዛለ
ልብሳችንን ነክተው ደማቸው ቀጥ ያለ ከሞት የተረፉ
ሀኪም ድሮ ቀረ እያሉ ለፈፉ
በእኛ መስዋዕትነት ከመቅሰፍት የዳኑ
በፈውሳቸው ማግስት እኛ ላይ ጀገኑ
መንግሥት!?
መንግሥትማ አለ እንጅ ስራውን ይሰራል
ዘላለም የመንገሥ መብቱን ያስከብራል
የተቃዋሚውን ጀርባ አጥንት ይሰብራል
በጠብመንጃው አረር የደቀቁ እግሮችን ሆስፒታል ይልካል
እንቶኔና እንትና በፈጠሩት ግጭት እያለ ይሰብካል
ተሰባሪው ታዲያ ሰባሪውን ፈርቶ አዳኙን ይከ'ሳል
የሀኪሞች ስህተት ውጤት ነው እያል አቧራ ያስነሳል
በርግጥ ሰው ይስታል እውነቱ አይካድም
በማካሮ ሽጉጥ መስበሩ ባይከብድም
ለዜና ካልሆነ
የተሰበረ እግር በጥገናው ማግሥት ቆሞ አይራመድም
እናልህ አንድዬ በዚች የጉድ ሀገር
ባልታደለ ዘመን በግም ወቅት ተፈጥረን
አንድ ቀን ከግማሽ ያለምንም ዋጋ ዱቲ ተወጥረን
በእለተ ትንሳኤ ላባችን ገብረን በደማችን ሰክረን
ካሣ' መሉ ፈጅቶ የመጣ ሰካራም እያደነቆረን
ልዝብ ያልከው ቀንበር ሸክሙ ከበደን
ነፃ አውጭ ላክልን ወይ መጥተህ ፍረደን

መታሰቢያነቱ፦ የትንሳኤ በዓልን ከቤተሰብ ተለይታችሁ ሆስፒታል ውስጥ ለምታሳልፉ የጤና ባለሙያዎች በተለይ በአውደ ዓመት ምድር ያለምንም ክፍያ ላብና ደማችሁን ለምትገብሩ ኢንተርን ሀኪሞች ይሁንልኝ ።

ዶ/ር ጌታነህ ካሴ
ዝቋላ ሆስፒታል

በዚሁ አጋጣሚ ለመላው የዚህ ቻናል ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቴ ይድረስልኝ!!!

@getem
@getem
@getem
ስቀለው ስቀለው ደጉን ስው ስቀለው
ግደለው ግደለው በርባንን ግን ማረው
አዳኝነቱንም በክደት ሽፈጡ
ጌታቸውን ትተው በርባንን መረጡ
ያመጻን ጎዳናን ፈትፍተው የበሉ
ለርባና ቢስ አለም ደፍ ቀና እሚሉ
በርባን ወዳድ ትውልድ ይኸው ዛሬም አሉ።


@getem
@getem
@Bebra48
ቀርቶብን መመለስ
ያምላክን ውለታ
በመስቀል ተሰቅለን
ቢያንስ እንዋልለት
ክፉ ልባችን ላይ
ቅንጣት ፍቅር ዘርተን።

@Birukam
#ፀሀፈ ብሩህ

@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)

በኢትዮጵያ ሰማይ ስር
ስቅለት እና ጁመአ ፣ ሲውሉ ባንድ ቀን
በስግደት በፀሎት ፣ በዱአ ማይለቀን
ምን አይነት ጋኔን ነው
በዘር በጎጥ ከፍሎን ፣ አስሮ ሚያፏቅቀን?!
።።።

@getem
@getem
@gebriel_19
     በምን ይሆን የዳንኩት? 
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ትናንት እመም አርጎኝ
የራስ ምታት ይዞኝ
በአንዲት ቅጠል ብጤ ዳብሰሽው ግንባሬን
ሞት፣ ሞት ያሰኘኝን አጣሁት ህመሜን
እኔ ግን ያልገባኝ ነገረ ብሂሉ
በአንቺ ነው የዳንኩት ወይስ በቅጠሉ? ።

@getem
@getem
@paappii

ሰለሞን ሞገስ
መሰቀሉን እንጃ
"""""""""""""""""""
አብርሃም

ህይወት ተከርብቶ
ታሪክ ተገልብጦ
በዚህ ዘመን ትውልድ፤
ለአለም ቤዛ የሆነው
ይህን ቀን ቢመጣ
ይህን ዘመን ቢወለድ..

(ቢያስተምር....)
ስለ ፍቅር ብሎ
እራሱ ዝቅ ብሎ
ተዋደዱ ብሎ...ስለ እውነት ብሎ

(ቢገስፅ...)
አትጣሉ ብሎ
ስርህና ስርሽ ገንዘብ አይሁን ብሎ
ብር አታምልክ ብሎ
አትዋሹ ብሎ

ቁጣውን ቢያሳየን
የእኛው ቤዛ ድ'ነት
ብሩን ቢበትነው
በጎቹንም ቢለቅ ገበያውን ቢያውክ

እያለም ቢናገር...
አትከፋፈሉ በጎሳ በብሄር
አታሲሩ ለሰው ተባባሉ ይቅር
ማመንዘሩም ይቅር
ስሜት አይግዛችሁ መስረቃችሁ ይቅር
ብሎ እኛን ቢያስተምር
ይሄ ዋሾ ትውልድ
ይሄ ሌባ ትውልድ
ስቆና አንጓጦ አይሰቅለውም ነበር?
(እንጃ....ብቻ)



@getem
@getem
@getem
በርባን

((እዮብ ሰብስቤ))

ይሔ ከንቱ አፌ!
‹‹በርባን›› ነው ‘ሚያባባኝ
ክርስቶስ አይደለም እኔን የሚያስነባኝ
ብሎ ይፎክርና!
መከራ አልቆስቁሶ፣ ሲቀጣው ደቁሶ
‹‹ክርስቶስ ሆይ›› ድረስ ይላል ተመልሶ፡፡

@getem
@getem
@getem
.☜አውቃለሁ ~አታውቅም☞ (በሔለን ፋንታሁን)
.
አውቃለሁ...
አልወዛም በቅባት
የምስሌ ገፅ ቀለም ፣
ባልታረዝ እንኳን...
በዘመኑ ቀሚስ
አካሌ አልደመቀም፡፡
...............
አውቃለሁ...
ከ'ነሱ አንሳለሁ
ባንተ ቀመር ስሌት ፣
ልብን ለማሸፈት
አልሆንኩም እንደ ሴት፡፡
................
አውቃለሁ...
ዕርቃን ገላ የለኝ
ቀልብን የሚነሳ ፣
በስሜት አስክሮ
ነፍስን የሚያሳሳ፡፡
...................
አውቃለሁ...
አልመረጥኩም ባይነት
ከአዳም ዘር ተርታ ፣
ስጋዬን ቸርችሬ
ለመክፈል ውለታ ፡፡
..................
አንተ ግን አታውቅም...
ሰ 'ቶ ለመቀበል
ራሴን አላረክስም ፣
አፅናኝ ለማባባት
ዕንባ አላፈስም፡፡
.................
አንተ ግን አታውቅም...
ኩሩ ሴትነቴን
የነፍሴን ልክ ጥጋት ፣
የመኖሬን ትርጉም
የኔነቴን ስሌት ፡፡
.................
አንተ ግን አታውቅም...
ስውር ቅኔነቴን
ልባም ሠውነቴን ፣
አዳኝም ገዳይም
የመሆን ጥበቤን ።
...................
አታውቅም እመነኝ
ገዳይህ እኔ ነኝ ።
~~~~//~~~~
@getem
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)

ፍቅር ያሸንፋል እያላችሁ ፣ የምትጠሉትን አታብዙ
ገንዘብ እንጂ ቂም አትያዙ
በግ ሆናችሁ እንዳትጠፉ ፣ በተኩላ ፊት አትፍዘዙ
እጮኛሞች የሆናችሁ ፣ ባህላችሁን አትበርዙ
መንገድ ላይ ከምትሳሳሙ ፣ ጊዜያዊ አልጋ ያዙ
ባለስልጣን የሆናችሁ ፣ ከሀገር በፊት ልብ ግዙ
ጎዳና ያሉትን አትርሱ ፣ ቤት ስትሰሩ ቤት ስትገዙ
በውስኪ ከምትራጩ ፣ለምስኪኖች ውሃ ጋብዙ ።።።

መልካም ዋዜማ።

@getem
@getem
@getem
...የጌታ ትንሳኤ...
ከተከመረብን የመከራ ህንፃ
እሱ ቤዛ ሆኖ እኛን ሊያነፃ
የኛን ሃጥያት ወስዶ የኛኑ ሞት ሊሞት
ክብሩን ትቶ ወረደ ከሰማየ ሰማያት

ግድ ነውና ሊፈፀም የአምላክ ቃሉ
ይሰቀል ይሰቀል ይሰቀል እያሉ
የሚሰሩት ስራ ሳይገባቸው ቅሉ
እያንገላቱ ወሰዱት አምላክን ሊሰቅሉ

ፀሃይ በሃዘን ብዛት በጠቆረችበት
ሰማይ ባነባበት
ልክ በአርብ ዕለት
እንጨት አመሳቅለው አምላክን ሰቀሉት
እናም በዚያች ዕለት
ለአዳም ልጆች ሁሉ ሆነልን ድነት

ያኔ ሃዋርያቱን ሰብስቦ ሲያስተምር
እስከ ሞት ድረስ እኛን እንደሚያፈቅር
ከሞቱም በኧላ እንድንጠብቀው አውቀን
እነሳለው ብሎ ነበር በ3ተኛዋ ቀን
እናም
ያለ አንዳች የሃጥያት ጠባሳ
ተሰርዞ ሲያበቃ የአዳም ልጅ አበሳ
ያቺ ቅድስት ዕለት 3ተኛዋ ቀን ደርሳ
መቃብር ፈንቅሎ ጌታችን ተነሳ

እዮብ ጌታሁን

@getem
@getem
@getem
👍1
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew (Mykey))
መልካም በዓል!
@Mykeyliyew