ከወዳደቁ ነገሮች የተሠራ ሕይወት 2
(ያዴል ትዕዛዙ)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አሮጌ መሰንቆ
ሕይወት የገፋቸው ግጥም ሰጭ ጠጪዎች
ተቀምጠው ማያውቁ ቋሚ አዝማሪዎች
እና ደግሞ ተራ
የመንገድ ኩታራ...
እነኚህ ባሉበት
ግጥም ሰቆቃ ነው አሳር ሚበሉበት።
፣
ጠጪ አንድ
"ተቀበል አዝማሪ
መግፋት ቢከብደኝም
የእንጀራዬን ወፍጮ የሕይወቴን መጅ
እድሜ ለስካሬ
በተስፋ እኖራለሁ እየጠጣሁ ጠጅ።
እግዜር ይረሳኛል አይልም ድሀ አምልጦት
እምነቱን ይገምዳል ይፈትላል በእጦት።
ብቻ በቀደም ለት
እንዲህ እንደዛሬው መጠጫ አቶ ኪሴ
ቤት በጊዜ ገባሁ
ጨብጠው አገኘሁ
ሴት ልጄ ባሕር ዛፍ ሚስቴ ዳማ ከሴ።"
፣
ሕይወት አንድ የተሰራበት ቁስ አካል እና አዘገጃጀቱ
ነጭ ባሕር ዛፍ!
(ልክ እንደስሙና ልክ እንደታሪኩ
የባሕር ዛፍ ነገር ሁለት ነው መልኩ!)
ሳል ያሰቃየን ቀን
ይህን ነጭ ባህር ዛፍ መንደሬው ቀቅሎ
ፈውስ ነው ይለዋል
ሳምባህን አፍኖ "ጉነፋኑን ነቃቅሎ።"
ደግሞ እንደሰማነው
ባህር ዛፍ ተፈጥሮው ባህር ዛፍ አመሉ
የምድርን ሆድ መጦ
ለራሱ ሲፋፋ ሌላውን እፅዋት እድገት መከልከሉ።
፣
መንገድ ላይ የቀረ ምስኪንዬ ህጣን
መንገድ ዳር ተቀምጦ
ጠጅ ቤቱን እያየ
የግጥሙን አስኳል በመተርጎም ቀጣን።
"በየብርዱ ግንባር
ተሰጥቼ ምኖር
እኔ የዓለም ቅዳጅ የቀዬው እራፊ
ከቀን ጣቃ መሃል
ሳይመትሩ ቀደው
ቧጭሮኝ የምባክን የቀን ሽርፍራፊ
መኖርና ነፋስ
ነፍስያዬን ጨንቋት
ሳል እያጣደፈኝ ለጩኸት ባልበቃም
ፈውስ ነው አትበሉኝ
ስም በማቀያየር ሕይወት አይጠረቃም።
፣
እንደየባሕሩ እንደየዛፉ አቅም
ከደረቅ መሬት ላይ ፈውስ ስንለቅም
ሁለትዜ ሳትን
አንዴም ባሕር ዛፉን
ባሕር በሌለበት የብስ ላይ ስንተክለው
አንዴም ፈውስ ሽተን
ውኃችንን ግተን በ‘ሳት ስንቀቅለው።
እንዲህ ነው ልጅ መሆን እያደሩ ማነስ
ዳማ ከሴው ሲሻር
ባንዱ ነጩን ይዞ
በየተገኘው ላይ ጥውለጋን መነስነስ።
በየደረሱበት ኅልፈትን ማነፍነፍ
ስም እየቀየሩ ሁለቴ መሸነፍ።
እኔ ያለም ቅዳጅ
የቀዬው እራፊ
የዶፍ ብርዱ ወዳጅ
የሰው ትርፍራፊ
መጥቀሚያ መርፌና ክሬን አንጠልጥዬ
"እሰፋለሁ" ስል ነው የቀረሁ ተጥዬ።"
፣
ጠጪ ሁለት
"ተቀበል አዝማሪ
ምነው ይሄ ጎጆ
ምን ጠቢብ ቢያንፀው
ለመዳመን ሰፋ ማባራት ጠበበው
ገና ሲያጉረመርም የሚያንጠባጥበው?
አወይ አለማወቅ
የጎጆን አሰራር በቅጡ አለመማር
ቆርቆሮ ጣራውን
አጓጉል ቦታ ላይ
ሳይበሳው አይቀርም ሀሳብ አልባ ሚስማር!"
፣
ሕይወት ሁለት የተሰራበት ቁስ አካልና አዘጋጀጀቱ
ሀሳብ አልባ ሚስማር!
(በመጠን ይለያይ
ባለቆብ ተብሎ በክብር ይከፈል
በየተሰካበት
መቼም አንሶ አያውቅም
ጣራ ለመሸንቆር ሕይወት ለመፈልፈል!)
አለ አንዳንድ ሚስማር
ባለቆብ ተብሎ ቆቡን ያወለቀ
ና ድፈነን ሲሉት
ራሱ በበሳው ሾልኮ የወደቀ።
አለ አንዳንድ ሚስማር
በዛቻ በቁጭት
ገላምጠው የሚሉት
"ቀን የወጣልኝ ቀን እኔ እሱን እያርገኝ"
ቀጥ ባሉ መሃል
ቆንጅዬ ጣራ ላይ ተጣሞ የሚገኝ።
አለ አንዳንድ ሚስማር
የጨነቀው መሳይ መላ ቅጥ የሌለው
ጭንቅላቱ እና እግሩ
መሾል መዶልዶሙ የሚያመሳስለው።
፣
መንገድ ላይ የቀረ ምስኪንዬ ህጣን
ያዝማሪውን ግጥም
የልባችንን ጌጥ በመተርጎም ቀጣን።
"በየመንገዱ ላይ
ተረግጬ ምኖር
የሰው በረባሶ እኔ የሰው ጎማ
ሊያድሰኝ የመጣ
ኩርንችት ሲወጋኝ አሞኝ እንደዶማ
ከየሚስማሩ ጋር
አካሌና ነፍሴ ለክስ በወጣን
ሚስማር አድር ባዩ
አሳልፎ ሰጠን ለመዶሻ ሥልጣን።
፣
መዶሻ ቃል አባይ ባለሁለት ልሳን
"ሚስማር ላይ የተሾምኩ
እኔ ነኝ" እያለ መድረሻ እንዳልነሳን
ላይረገጥ ደፉ
ላንደርስ ደጃፉ
አሳልፎ ሰጠን ለባለመዳፉ።
፣
አንዱ አንዱን ሲሰይም
አንዱ ላንዱ ሲያዘም
ኃላፊነት ሽሽት እያጎበደደ
ኪሳራ እንዳጨቀው እድሜያችን ነጎደ።
አቤት ባይ ፍለጋ
ቢሰለች ቢመረን ነፍስ፣ እግር ማቅጠኑ
ኑሯችን ሌላ ነው
እንደሚስማሩ አይነት ልክ እንደመጠኑ።
ቀን እንጠብቃለን
ባለቆብ ነኝ ብሎ ቆቡን ያወለቀ
ራሱ በበሳው ሾልኮ በወደቀ!"
፣
ጠጪ ሦስት
"ተቀመጥ አዝማሪ
አታጎልድፍ ግጥም
በጨቀየ ሕይወት ባረጀ መሰንቆ
ሞትህ ሲሳብ እየው
በምትገርፈው ጭራ ሊሰቅልህ ነው አንቆ።
በሰቆቃ ግጥም
በደቃቃ ዜማ
አግዜሩን አትጨቅጭቅ ኑሮን አትነዝንዘው
ባይሆን ቁጭ በልና ሞትን ጠጅ ጋብዘው።"
፣
ሕይወት ሦስት የተሰራበት ቁስ አካል
ያረጀ መሰንቆ!
አዝማሪው ቁጭ አለ!
መሰንቆውን አየው።
ምስጥ የበላት እንጨት የዜማ መቃኛ
የታጠፈች ደጋን የዜማው መገኛ
በነዚህ መካከል
ተወጥሮ ያለ
የተበጣጠሰ የተንጨፈረረ ቀጭን የዜማ ክር
በሁለት ጽንፎች መሃል
(በኑሮና በሞት)
እንግልት ሲገርፈው
ተወጥሮ የሚያልቅ የሕይወት ምስክር።
አዝማሪው ቁጭ ብሎ
ወደ ሆነ ጥጋት መሰንቆውን ጥሎ
ግጥም ባቀበሉት
በሚንጫጩ መሃል እየፈነጠዘ
ከሞት ከኑሮ ጋር
ጠጅ ቺርስ እያለ መገባበዝ ያዘ።
፣
መንገድ ላይ የቀረ ምስኪንዬ ህጣን
ግጥም በመተርጎም ቆይቶ ሲቀጣን
ጠጪው መሃል ገብቶ
መሰንቆዋን ይዞ ወደ ውጭ ሲበር
ከዛ ሁሉ ሰው ውስጥ ያየውም አልነበር።
ህፃኑ እንዳነሳው
ልክ እንደመሰንቆው ደግሞም እንደጭራው
አንዱ በጣለው ነው ሌላው የሚሠራው።
@getem
@getem
@lula_al_greeko
(ያዴል ትዕዛዙ)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አሮጌ መሰንቆ
ሕይወት የገፋቸው ግጥም ሰጭ ጠጪዎች
ተቀምጠው ማያውቁ ቋሚ አዝማሪዎች
እና ደግሞ ተራ
የመንገድ ኩታራ...
እነኚህ ባሉበት
ግጥም ሰቆቃ ነው አሳር ሚበሉበት።
፣
ጠጪ አንድ
"ተቀበል አዝማሪ
መግፋት ቢከብደኝም
የእንጀራዬን ወፍጮ የሕይወቴን መጅ
እድሜ ለስካሬ
በተስፋ እኖራለሁ እየጠጣሁ ጠጅ።
እግዜር ይረሳኛል አይልም ድሀ አምልጦት
እምነቱን ይገምዳል ይፈትላል በእጦት።
ብቻ በቀደም ለት
እንዲህ እንደዛሬው መጠጫ አቶ ኪሴ
ቤት በጊዜ ገባሁ
ጨብጠው አገኘሁ
ሴት ልጄ ባሕር ዛፍ ሚስቴ ዳማ ከሴ።"
፣
ሕይወት አንድ የተሰራበት ቁስ አካል እና አዘገጃጀቱ
ነጭ ባሕር ዛፍ!
(ልክ እንደስሙና ልክ እንደታሪኩ
የባሕር ዛፍ ነገር ሁለት ነው መልኩ!)
ሳል ያሰቃየን ቀን
ይህን ነጭ ባህር ዛፍ መንደሬው ቀቅሎ
ፈውስ ነው ይለዋል
ሳምባህን አፍኖ "ጉነፋኑን ነቃቅሎ።"
ደግሞ እንደሰማነው
ባህር ዛፍ ተፈጥሮው ባህር ዛፍ አመሉ
የምድርን ሆድ መጦ
ለራሱ ሲፋፋ ሌላውን እፅዋት እድገት መከልከሉ።
፣
መንገድ ላይ የቀረ ምስኪንዬ ህጣን
መንገድ ዳር ተቀምጦ
ጠጅ ቤቱን እያየ
የግጥሙን አስኳል በመተርጎም ቀጣን።
"በየብርዱ ግንባር
ተሰጥቼ ምኖር
እኔ የዓለም ቅዳጅ የቀዬው እራፊ
ከቀን ጣቃ መሃል
ሳይመትሩ ቀደው
ቧጭሮኝ የምባክን የቀን ሽርፍራፊ
መኖርና ነፋስ
ነፍስያዬን ጨንቋት
ሳል እያጣደፈኝ ለጩኸት ባልበቃም
ፈውስ ነው አትበሉኝ
ስም በማቀያየር ሕይወት አይጠረቃም።
፣
እንደየባሕሩ እንደየዛፉ አቅም
ከደረቅ መሬት ላይ ፈውስ ስንለቅም
ሁለትዜ ሳትን
አንዴም ባሕር ዛፉን
ባሕር በሌለበት የብስ ላይ ስንተክለው
አንዴም ፈውስ ሽተን
ውኃችንን ግተን በ‘ሳት ስንቀቅለው።
እንዲህ ነው ልጅ መሆን እያደሩ ማነስ
ዳማ ከሴው ሲሻር
ባንዱ ነጩን ይዞ
በየተገኘው ላይ ጥውለጋን መነስነስ።
በየደረሱበት ኅልፈትን ማነፍነፍ
ስም እየቀየሩ ሁለቴ መሸነፍ።
እኔ ያለም ቅዳጅ
የቀዬው እራፊ
የዶፍ ብርዱ ወዳጅ
የሰው ትርፍራፊ
መጥቀሚያ መርፌና ክሬን አንጠልጥዬ
"እሰፋለሁ" ስል ነው የቀረሁ ተጥዬ።"
፣
ጠጪ ሁለት
"ተቀበል አዝማሪ
ምነው ይሄ ጎጆ
ምን ጠቢብ ቢያንፀው
ለመዳመን ሰፋ ማባራት ጠበበው
ገና ሲያጉረመርም የሚያንጠባጥበው?
አወይ አለማወቅ
የጎጆን አሰራር በቅጡ አለመማር
ቆርቆሮ ጣራውን
አጓጉል ቦታ ላይ
ሳይበሳው አይቀርም ሀሳብ አልባ ሚስማር!"
፣
ሕይወት ሁለት የተሰራበት ቁስ አካልና አዘጋጀጀቱ
ሀሳብ አልባ ሚስማር!
(በመጠን ይለያይ
ባለቆብ ተብሎ በክብር ይከፈል
በየተሰካበት
መቼም አንሶ አያውቅም
ጣራ ለመሸንቆር ሕይወት ለመፈልፈል!)
አለ አንዳንድ ሚስማር
ባለቆብ ተብሎ ቆቡን ያወለቀ
ና ድፈነን ሲሉት
ራሱ በበሳው ሾልኮ የወደቀ።
አለ አንዳንድ ሚስማር
በዛቻ በቁጭት
ገላምጠው የሚሉት
"ቀን የወጣልኝ ቀን እኔ እሱን እያርገኝ"
ቀጥ ባሉ መሃል
ቆንጅዬ ጣራ ላይ ተጣሞ የሚገኝ።
አለ አንዳንድ ሚስማር
የጨነቀው መሳይ መላ ቅጥ የሌለው
ጭንቅላቱ እና እግሩ
መሾል መዶልዶሙ የሚያመሳስለው።
፣
መንገድ ላይ የቀረ ምስኪንዬ ህጣን
ያዝማሪውን ግጥም
የልባችንን ጌጥ በመተርጎም ቀጣን።
"በየመንገዱ ላይ
ተረግጬ ምኖር
የሰው በረባሶ እኔ የሰው ጎማ
ሊያድሰኝ የመጣ
ኩርንችት ሲወጋኝ አሞኝ እንደዶማ
ከየሚስማሩ ጋር
አካሌና ነፍሴ ለክስ በወጣን
ሚስማር አድር ባዩ
አሳልፎ ሰጠን ለመዶሻ ሥልጣን።
፣
መዶሻ ቃል አባይ ባለሁለት ልሳን
"ሚስማር ላይ የተሾምኩ
እኔ ነኝ" እያለ መድረሻ እንዳልነሳን
ላይረገጥ ደፉ
ላንደርስ ደጃፉ
አሳልፎ ሰጠን ለባለመዳፉ።
፣
አንዱ አንዱን ሲሰይም
አንዱ ላንዱ ሲያዘም
ኃላፊነት ሽሽት እያጎበደደ
ኪሳራ እንዳጨቀው እድሜያችን ነጎደ።
አቤት ባይ ፍለጋ
ቢሰለች ቢመረን ነፍስ፣ እግር ማቅጠኑ
ኑሯችን ሌላ ነው
እንደሚስማሩ አይነት ልክ እንደመጠኑ።
ቀን እንጠብቃለን
ባለቆብ ነኝ ብሎ ቆቡን ያወለቀ
ራሱ በበሳው ሾልኮ በወደቀ!"
፣
ጠጪ ሦስት
"ተቀመጥ አዝማሪ
አታጎልድፍ ግጥም
በጨቀየ ሕይወት ባረጀ መሰንቆ
ሞትህ ሲሳብ እየው
በምትገርፈው ጭራ ሊሰቅልህ ነው አንቆ።
በሰቆቃ ግጥም
በደቃቃ ዜማ
አግዜሩን አትጨቅጭቅ ኑሮን አትነዝንዘው
ባይሆን ቁጭ በልና ሞትን ጠጅ ጋብዘው።"
፣
ሕይወት ሦስት የተሰራበት ቁስ አካል
ያረጀ መሰንቆ!
አዝማሪው ቁጭ አለ!
መሰንቆውን አየው።
ምስጥ የበላት እንጨት የዜማ መቃኛ
የታጠፈች ደጋን የዜማው መገኛ
በነዚህ መካከል
ተወጥሮ ያለ
የተበጣጠሰ የተንጨፈረረ ቀጭን የዜማ ክር
በሁለት ጽንፎች መሃል
(በኑሮና በሞት)
እንግልት ሲገርፈው
ተወጥሮ የሚያልቅ የሕይወት ምስክር።
አዝማሪው ቁጭ ብሎ
ወደ ሆነ ጥጋት መሰንቆውን ጥሎ
ግጥም ባቀበሉት
በሚንጫጩ መሃል እየፈነጠዘ
ከሞት ከኑሮ ጋር
ጠጅ ቺርስ እያለ መገባበዝ ያዘ።
፣
መንገድ ላይ የቀረ ምስኪንዬ ህጣን
ግጥም በመተርጎም ቆይቶ ሲቀጣን
ጠጪው መሃል ገብቶ
መሰንቆዋን ይዞ ወደ ውጭ ሲበር
ከዛ ሁሉ ሰው ውስጥ ያየውም አልነበር።
ህፃኑ እንዳነሳው
ልክ እንደመሰንቆው ደግሞም እንደጭራው
አንዱ በጣለው ነው ሌላው የሚሠራው።
@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍2
እንዲህ ነኝ!(ልዑል ሀይሌ)
“እንዴት ነህ?” ከምትሉ
እስቲ እንደዚህ ሁኑ!
.
የቁስሌን መጠን ቁሰሉና ለኩ ፤
የሚያሳክከኝን ውሰዱና እከኩ፤
የሚያመኝን ሕመም ታመሙና ኑሩት፤
የልቤን ፍላሎት
አይገልፀውምና እንዲሁ ሲናገሩት።
.
“እንዴት ነህ?” ከምትሉ
እስቲ እንደዚህ ሁኑ!
.
’ሚነፍሰውን ንፋስ
በጎኔ ሚዘልቀው በጎናችሁ አዝልቁት፤
’ሚዘንበውን ዝናብ
’ሚያበሰብሰኝን በጉንጫችሁ አውርዱት፤
.
የሚያንገበግበኝ
የወዳጄን ክህደት በወዳጅ ተካዱ፤
እሾህ ላይ ስራመድ በእሾህ ላይ ሂዱ።
.
ያኔ ነው ምታውቁት
የኔን የሕይወት ፈር፤
“ደህና ነው” በሚል ቃል ይህ ሁሉ ሲሰፈር።
፲፪.፩.፲፩ ዓ.ም.
@getem
@getem
@gebriel_19
“እንዴት ነህ?” ከምትሉ
እስቲ እንደዚህ ሁኑ!
.
የቁስሌን መጠን ቁሰሉና ለኩ ፤
የሚያሳክከኝን ውሰዱና እከኩ፤
የሚያመኝን ሕመም ታመሙና ኑሩት፤
የልቤን ፍላሎት
አይገልፀውምና እንዲሁ ሲናገሩት።
.
“እንዴት ነህ?” ከምትሉ
እስቲ እንደዚህ ሁኑ!
.
’ሚነፍሰውን ንፋስ
በጎኔ ሚዘልቀው በጎናችሁ አዝልቁት፤
’ሚዘንበውን ዝናብ
’ሚያበሰብሰኝን በጉንጫችሁ አውርዱት፤
.
የሚያንገበግበኝ
የወዳጄን ክህደት በወዳጅ ተካዱ፤
እሾህ ላይ ስራመድ በእሾህ ላይ ሂዱ።
.
ያኔ ነው ምታውቁት
የኔን የሕይወት ፈር፤
“ደህና ነው” በሚል ቃል ይህ ሁሉ ሲሰፈር።
፲፪.፩.፲፩ ዓ.ም.
@getem
@getem
@gebriel_19
''እንፋሎት''
---------
በፀሐይ ወበቅ ተለብልቦ
በስሜት እሳት ተከቦ
እንደሚጎፈላ በ'ሳት ግመት
እንደፈላ ትኩስ ወተት
አለ ለካ..የወዳጅም ተን እንፋሎት
ክዳን ሲገፋ እንጂ፣ሲርቅ የማያዩት
.
«ሚኪ እንዳለ»
@getem
@getem
@gebriel_19
---------
በፀሐይ ወበቅ ተለብልቦ
በስሜት እሳት ተከቦ
እንደሚጎፈላ በ'ሳት ግመት
እንደፈላ ትኩስ ወተት
አለ ለካ..የወዳጅም ተን እንፋሎት
ክዳን ሲገፋ እንጂ፣ሲርቅ የማያዩት
.
«ሚኪ እንዳለ»
@getem
@getem
@gebriel_19
ልመና
መቅደሱ ስር ሆኜ እንባዬን ሳነባ
መፈጠሬን ስረግም ሆዴንም ሳባባ
አንዱ ጠጋ አለ ከልቡ ሊያወራኝ
ላስቸግርህ! አለ ፈቃዴን ጠየቀኝ
እሺ! አልኩ ከልቤ
ችግሬንም ስማኝ
እራትም አልበላዉ ለዛሬም የለኝ
ካለህ ላይ ቆንጥረህ
እባክህ አካፍለኝ?
ድንጋጤ ሞላኝ ልቤም ተሸበረ
ላይበቃው በመስጠቴ
ውስጤ እያፈረ
...ይበቃል አለ ውስጡ እየፈነደቀ
የሱን ደስታ አይቼ ምኔ ተደነቀ
ችግር ላይ መሆኔን
ልቤም እያወቀ
እግዜር ይስጥህ! በወጣው ይተካ!
መረቀኝ ከልቡ በጌታው ተመካ!
ይስጠኝ መና እሱ
ሳይወስድ መልሶ
ይምራኝ በመንገዱ
ይውሰደኝ ቀልሶ
ይህን እያሰብኩኝ!
ጭንቀቴን ረሳውኝ!
ማማረሬን ተውኩኝ!
አዲስ ቀን ጀመርኩኝ!
ገጣሚ ዳዊት አለሙ/dave ak
@getem
@getem
@gebriel_19
መቅደሱ ስር ሆኜ እንባዬን ሳነባ
መፈጠሬን ስረግም ሆዴንም ሳባባ
አንዱ ጠጋ አለ ከልቡ ሊያወራኝ
ላስቸግርህ! አለ ፈቃዴን ጠየቀኝ
እሺ! አልኩ ከልቤ
ችግሬንም ስማኝ
እራትም አልበላዉ ለዛሬም የለኝ
ካለህ ላይ ቆንጥረህ
እባክህ አካፍለኝ?
ድንጋጤ ሞላኝ ልቤም ተሸበረ
ላይበቃው በመስጠቴ
ውስጤ እያፈረ
...ይበቃል አለ ውስጡ እየፈነደቀ
የሱን ደስታ አይቼ ምኔ ተደነቀ
ችግር ላይ መሆኔን
ልቤም እያወቀ
እግዜር ይስጥህ! በወጣው ይተካ!
መረቀኝ ከልቡ በጌታው ተመካ!
ይስጠኝ መና እሱ
ሳይወስድ መልሶ
ይምራኝ በመንገዱ
ይውሰደኝ ቀልሶ
ይህን እያሰብኩኝ!
ጭንቀቴን ረሳውኝ!
ማማረሬን ተውኩኝ!
አዲስ ቀን ጀመርኩኝ!
ገጣሚ ዳዊት አለሙ/dave ak
@getem
@getem
@gebriel_19
ጠብቆ ሚበላ
——————
እረኛውን አምኖ፣ተኩላን መስጋቱ
ያደርገዋል የዋህ፣በግን በሕይወቱ
የዋህነት አድጎ፣ካለፈ ከደርዙ
ጅልነት ይሆናል፣መዳረሻ ጠርዙ
ማ'እንዳለ ከጎኑ፣በጉ መቼ ያውቃል
ከበዪ ለመዳን፣በ'በይ ይጠበቃል
ጠላትን ፍራቻ፣ከጠላት ይውላል
ግና ምን ያደርጋል !!!
የኋላ ኋላውን፣ሰውነቱ ያድጋል
በተኩላው ሳይሆን...
ዘላልም ባመነው፣በረኛው ይበላል
ቆመው ከጎናችን.…
እንቅልፍን ሳይተኙ ፣ ተግተው ሚጠብቁን
ለካስ አስበው ነው .…
ከሌሎች አድነው፣እነሱው ሊበሉን
እሩቅ የምናየው፣በቅርቡ ሲተካ
መውደድ ለራስ ጥቅም፣ በሚለው ሲለካ
የኔ በግ እያለ..…
ከጠላት ሚጠብቅ፣ጠላት አለ ለካ !!!
.
( ሚኪ እንዳለ )
@getem
@getem
——————
እረኛውን አምኖ፣ተኩላን መስጋቱ
ያደርገዋል የዋህ፣በግን በሕይወቱ
የዋህነት አድጎ፣ካለፈ ከደርዙ
ጅልነት ይሆናል፣መዳረሻ ጠርዙ
ማ'እንዳለ ከጎኑ፣በጉ መቼ ያውቃል
ከበዪ ለመዳን፣በ'በይ ይጠበቃል
ጠላትን ፍራቻ፣ከጠላት ይውላል
ግና ምን ያደርጋል !!!
የኋላ ኋላውን፣ሰውነቱ ያድጋል
በተኩላው ሳይሆን...
ዘላልም ባመነው፣በረኛው ይበላል
ቆመው ከጎናችን.…
እንቅልፍን ሳይተኙ ፣ ተግተው ሚጠብቁን
ለካስ አስበው ነው .…
ከሌሎች አድነው፣እነሱው ሊበሉን
እሩቅ የምናየው፣በቅርቡ ሲተካ
መውደድ ለራስ ጥቅም፣ በሚለው ሲለካ
የኔ በግ እያለ..…
ከጠላት ሚጠብቅ፣ጠላት አለ ለካ !!!
.
( ሚኪ እንዳለ )
@getem
@getem
የልቤ ትርታ
እኔ ካንች ስርቅ ይሰማሻል ደስታ
ኣይኔን ካላየሽው ይጠፋል ትውስታ?
ከኔ ጋር የሆነው ይቀበራል ላፍታ
አይመስለኝም ነበር የልቤ ትርታ
እኔማ በኔ ቤት
ሃሳብ ኣስሬበት
ምኞት እንደስጋ በውኔ እያየሁት
ላገኝሽ ነው ብየ ጥዋት ካነጋሁት
ሲመሽ ገና ገባኝ ጨረቃን እንዳየሁት
ተፃፈ በከድር
የካቲት 2011
@getem
@getem
@gebriel_19
እኔ ካንች ስርቅ ይሰማሻል ደስታ
ኣይኔን ካላየሽው ይጠፋል ትውስታ?
ከኔ ጋር የሆነው ይቀበራል ላፍታ
አይመስለኝም ነበር የልቤ ትርታ
እኔማ በኔ ቤት
ሃሳብ ኣስሬበት
ምኞት እንደስጋ በውኔ እያየሁት
ላገኝሽ ነው ብየ ጥዋት ካነጋሁት
ሲመሽ ገና ገባኝ ጨረቃን እንዳየሁት
ተፃፈ በከድር
የካቲት 2011
@getem
@getem
@gebriel_19
ልብኛ ጉዞ(ልዑል ሀይሌ)
ምስል:-ከ Zuki Shewa ግድግዳ የተዘረፈ
በጉዞዬ መሐል
ምስልሽ እየታየኝ ፅልመት ማይጋርደው፤
መች ይታወቀኛል
የመንገዱ ርዝመት እልፍ ምራመደው፤
.
እኔ መንገደኛው
እሾኅ እየወጋኝ በጨለማው መንገድ፤
አንቺን እያሰብኩኝ
ሰርክ እማፀናለሁ ህመሜን ለመልመድ፤
.
ይህ ልቤ
ካሰበበት ሊደርስ
ለሚሄደው እርምጃ ለሚሄደው ጉዞ፤
መታመም ባይቀርም
ስቃይ ይሻገራል ሚወደውን ይዞ፤
.
(ይለኛል ይህ ልቤ...)
ተነስ አንተ አካሌ
ይልቅ ተነስልኝ
መጓዝ ላይቀርልህ
እሾኅ ላይቀርልህ ህመም ልመድልኝ፤
.
ተላመድ ከስቃይ
ተላመድ ከቁስል፤
በቆሰለው እግርህ
ሳለው ያንተን ምስል፤
.
ሳለው በጨለማ
ሳለው በመንገዱ፤
ንጋት ይገልጠዋል
የሚወዱትን ሰው
ብለው ሲራመዱ፤
(ይለኛል ይህ ልቤ...)
.
ተራመድ!
ወደፊት
ተወው ያን እንቅፋት፤
ናፍቆት ትዝታህን
አሸንፈህ አልፈህ
ፍቅርህን እቀፋት፤
.
ይለኛል
ይህ ልቤ ከእግር የተጣላ፤
አካሌን ሊያስከዳኝ ሊያላምደኝ ሌላ፤
.
ይህ ልቤ ብርቱ ነው
አለት ነው ያነፅኩት፤
ግን እንዴት ልመነው
ስንቴ ከሳት ጥዶኝ እየተማፀንኩት
፲፬-፰-፳፻፲፩ ዓ.ም.
@getem
@getem
@Lula_al_greeko
ምስል:-ከ Zuki Shewa ግድግዳ የተዘረፈ
በጉዞዬ መሐል
ምስልሽ እየታየኝ ፅልመት ማይጋርደው፤
መች ይታወቀኛል
የመንገዱ ርዝመት እልፍ ምራመደው፤
.
እኔ መንገደኛው
እሾኅ እየወጋኝ በጨለማው መንገድ፤
አንቺን እያሰብኩኝ
ሰርክ እማፀናለሁ ህመሜን ለመልመድ፤
.
ይህ ልቤ
ካሰበበት ሊደርስ
ለሚሄደው እርምጃ ለሚሄደው ጉዞ፤
መታመም ባይቀርም
ስቃይ ይሻገራል ሚወደውን ይዞ፤
.
(ይለኛል ይህ ልቤ...)
ተነስ አንተ አካሌ
ይልቅ ተነስልኝ
መጓዝ ላይቀርልህ
እሾኅ ላይቀርልህ ህመም ልመድልኝ፤
.
ተላመድ ከስቃይ
ተላመድ ከቁስል፤
በቆሰለው እግርህ
ሳለው ያንተን ምስል፤
.
ሳለው በጨለማ
ሳለው በመንገዱ፤
ንጋት ይገልጠዋል
የሚወዱትን ሰው
ብለው ሲራመዱ፤
(ይለኛል ይህ ልቤ...)
.
ተራመድ!
ወደፊት
ተወው ያን እንቅፋት፤
ናፍቆት ትዝታህን
አሸንፈህ አልፈህ
ፍቅርህን እቀፋት፤
.
ይለኛል
ይህ ልቤ ከእግር የተጣላ፤
አካሌን ሊያስከዳኝ ሊያላምደኝ ሌላ፤
.
ይህ ልቤ ብርቱ ነው
አለት ነው ያነፅኩት፤
ግን እንዴት ልመነው
ስንቴ ከሳት ጥዶኝ እየተማፀንኩት
፲፬-፰-፳፻፲፩ ዓ.ም.
@getem
@getem
@Lula_al_greeko
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቀንዲል ዲጂታል መፅሔት.pdf
6 MB
ብኩን አፍቃሪ ፪
(ሚካኤል አስጨናቂ)
.
አንቺን ያጣሁ ጊዜ...
ፀሀይቷ ጠልቃ ምድሩ ያልገለጠ
ጨረቃ ተሠብራ ጎኗ ያገጠጠ
ከዋክብት አብረው የታባህ የሚሉኝ
በከንቱ አጀባቸው አንጓጠው የናቁኝ
መስሎ ይታየኛል።
።።።
አንቺን ያጣሁ ጊዜ...
ቀድማ የጠለቀች ፀሀይ የማትወጣ
ጨረቃ ምታፍረኝ ክበቧን ስታጣ
አንጓጣጭ ከዋክብት ስቀው 'ማያበቁ
በዓይኔ እንባ ማዕበል የሚንቦራጨቁ
መስሎ ይሰማኛል።
።።።
አንቺን ያጣሁ ጊዜ
እኒያ አላዋቂዎች...
ወፈፈ እያሉ ይነክሩኛል ጠበል
መድሀኒት ቀይጠው ያጎርሱኛል ቅጠል
እጣን አጣጢሰው ቄጠማ ጎዝጉዘው
ይለማመናሉ...
ለራሱ የማያውቅ አዋቂ ጋር ሄደው ።
።።።
አይገርምም ዓለሜ?
አይገርምም የኔ ውድ?
.
እነዛ የዋሆች...
አይረዱኝም እንጂ ፥ ደርሰው ቢያውቁኝማ
መድሀኒቴ አንቺ ፥ መምጣትሽን ሳልሰማ
.
በክንድሽ ታቅፌ ከጉያሽ ሳልገባ
ከጡቶችሽ ዋሻ....
እመሀል ዘልቄ ፥ ናፍቆት ሳላነባ
.
በሎጋ ጣቶችሽ ፀጉሬ ሳይዳበስ
በትንፋሽሽ ንዝረት ልቤ ሳትታመስ
ፈገግታሽ ደምቆልኝ ደስታ በኔ ሳይነግስ
.
ፀሊሜ ተገፎ ፀሀይ ሳትወጣ
ጨረቃ ላታፍረኝ በክበብ ሳትመጣ
አንጓጣጭ ከዋክብት ...
መምጣትሽን አይተው አንገት ሳይደፉ
በፀበል አልድንም...
በቅጠል አልሽርም፥ ከንቱ ነው 'ሚለፉ!!
@getem
@getem
@gebriel_19
(ሚካኤል አስጨናቂ)
.
አንቺን ያጣሁ ጊዜ...
ፀሀይቷ ጠልቃ ምድሩ ያልገለጠ
ጨረቃ ተሠብራ ጎኗ ያገጠጠ
ከዋክብት አብረው የታባህ የሚሉኝ
በከንቱ አጀባቸው አንጓጠው የናቁኝ
መስሎ ይታየኛል።
።።።
አንቺን ያጣሁ ጊዜ...
ቀድማ የጠለቀች ፀሀይ የማትወጣ
ጨረቃ ምታፍረኝ ክበቧን ስታጣ
አንጓጣጭ ከዋክብት ስቀው 'ማያበቁ
በዓይኔ እንባ ማዕበል የሚንቦራጨቁ
መስሎ ይሰማኛል።
።።።
አንቺን ያጣሁ ጊዜ
እኒያ አላዋቂዎች...
ወፈፈ እያሉ ይነክሩኛል ጠበል
መድሀኒት ቀይጠው ያጎርሱኛል ቅጠል
እጣን አጣጢሰው ቄጠማ ጎዝጉዘው
ይለማመናሉ...
ለራሱ የማያውቅ አዋቂ ጋር ሄደው ።
።።።
አይገርምም ዓለሜ?
አይገርምም የኔ ውድ?
.
እነዛ የዋሆች...
አይረዱኝም እንጂ ፥ ደርሰው ቢያውቁኝማ
መድሀኒቴ አንቺ ፥ መምጣትሽን ሳልሰማ
.
በክንድሽ ታቅፌ ከጉያሽ ሳልገባ
ከጡቶችሽ ዋሻ....
እመሀል ዘልቄ ፥ ናፍቆት ሳላነባ
.
በሎጋ ጣቶችሽ ፀጉሬ ሳይዳበስ
በትንፋሽሽ ንዝረት ልቤ ሳትታመስ
ፈገግታሽ ደምቆልኝ ደስታ በኔ ሳይነግስ
.
ፀሊሜ ተገፎ ፀሀይ ሳትወጣ
ጨረቃ ላታፍረኝ በክበብ ሳትመጣ
አንጓጣጭ ከዋክብት ...
መምጣትሽን አይተው አንገት ሳይደፉ
በፀበል አልድንም...
በቅጠል አልሽርም፥ ከንቱ ነው 'ሚለፉ!!
@getem
@getem
@gebriel_19
❤1
ዘረኛ ገጣሚ በሱፍቃድ ዲባባ 2
<unknown>
በየቀነኑ በዘረኝነት ምክንያት ስለሚደርስ ችግር በሀገራችን ስላለው ሁኔታ የሚያስለቅስ ግጥም
በ #በሱፍቃድ
@Getem 😫😩😩😩😩
@getem 😫😩😩😩😩?
ከ @Yewahpictures ?😰😰😰?
Yewahpictures😩😩😩😩😩
በ #በሱፍቃድ
@Getem 😫😩😩😩😩
@getem 😫😩😩😩😩?
ከ @Yewahpictures ?😰😰😰?
Yewahpictures😩😩😩😩😩
👍1
መሼ ደሞ
(አቤል ምሕረት Barich)
መሸ ደሞ ልትናፍቂኝ
በስስት ሃይቅ ልታጠልቂኝ
መሼ ደሞ
መሼ
መሼ
ምሽት መጣ ፀሃይ ሸሼ
....
በደብዛዛው መብራት ግርጌ....
.
ጎዳናው ላይ
.
ተጣምረው ሳይ
.
ተቃቅፈው ሳይ
ልቤ አንችው ጋር አዝግሞ.....
የት ናት ይላል የኔን ሲሳይ
የት ነሽ?
☞FB አቤል ባርች
@getem
@getem
@gebriel_19
(አቤል ምሕረት Barich)
መሸ ደሞ ልትናፍቂኝ
በስስት ሃይቅ ልታጠልቂኝ
መሼ ደሞ
መሼ
መሼ
ምሽት መጣ ፀሃይ ሸሼ
....
በደብዛዛው መብራት ግርጌ....
.
ጎዳናው ላይ
.
ተጣምረው ሳይ
.
ተቃቅፈው ሳይ
ልቤ አንችው ጋር አዝግሞ.....
የት ናት ይላል የኔን ሲሳይ
የት ነሽ?
☞FB አቤል ባርች
@getem
@getem
@gebriel_19
ቀብር ሞት ቀደመ
መኖር ቡቱቶ ተጀቡኖ
በባዶ ዝና ተጀንኖ
በምላስ ዶፍ መኖር ገኖ
በሀብት ነሮ ጠሪያ አህሎ
አፈር ቢሸሽ ካፈር በቅሎ
ድሎት በዝቶ ቢመሰል አለሎ
አይ ሰው ከንቱ
ዛሬን ለነገ መሰዋቱ
ለማያቀው ለመጪው መረታቱ
ትቢያነቱ መርሳት መዘንጋቱ
ለመያስከፍለው ለፍቅር መሰሰቱ
መወቅ መወቅን ከሰወረ
አይናማው ብሌን ከወረ
የሰላም ጠቅሙ ከዋቂ ከተሰወረ
በሰዉኛ ቀመር ትውልድ ነው የከሰረ
የተመረው መክኖ አንገቱን ከደፋ
መሀይ በርትቶ በአንባው ካናፋ
በታሪክ ተቀብረን ድንጋይ ከዘከርን
ዘንድሮ ሞተን አምና ተቀበርን፡፡
ብሌን አሰላ
@getem
@getem
@gebriel_19
መኖር ቡቱቶ ተጀቡኖ
በባዶ ዝና ተጀንኖ
በምላስ ዶፍ መኖር ገኖ
በሀብት ነሮ ጠሪያ አህሎ
አፈር ቢሸሽ ካፈር በቅሎ
ድሎት በዝቶ ቢመሰል አለሎ
አይ ሰው ከንቱ
ዛሬን ለነገ መሰዋቱ
ለማያቀው ለመጪው መረታቱ
ትቢያነቱ መርሳት መዘንጋቱ
ለመያስከፍለው ለፍቅር መሰሰቱ
መወቅ መወቅን ከሰወረ
አይናማው ብሌን ከወረ
የሰላም ጠቅሙ ከዋቂ ከተሰወረ
በሰዉኛ ቀመር ትውልድ ነው የከሰረ
የተመረው መክኖ አንገቱን ከደፋ
መሀይ በርትቶ በአንባው ካናፋ
በታሪክ ተቀብረን ድንጋይ ከዘከርን
ዘንድሮ ሞተን አምና ተቀበርን፡፡
ብሌን አሰላ
@getem
@getem
@gebriel_19
///////// #ፍቅር_የሸንፋል_¡ //////
ጥላቻ ፣ በርትቶ፣
#ዘረኝነት 'ሚባል ፣ ቆንጆ ስም አግኝቶ።
ጡንቻውን አፈርጥሞ ፣ እንደ ድልብ በሬ፣
ይንጎማለል ጀመር በ'ያደባባዩ ፣ እዚም እመንደሬ።
ብዙን አሳንሶ ፣ አንድ እያነገሰ፣
ከእኔ ውጭ ወዲያ ፣ ብሎ እያፈረሰ።
በፈርጣማ ጡንቻው ፣ አምሳሉን እረግጦ፣
'እኔ' ና 'የእኔ' ፣ በሚሉ ፈሊጦች ሌላውን ደፍጥጦ።
እንሰማለን ከዛ
ከ'ያቅጣጫው ዜና
ቅስምን የሚሰብር ፣ ፍቅርን የሚያሳዝን፣
የሚያለብስ ፍርሃት ፣ የሚያቆስል ልብን።
ነፍስን የሚ'ያሸብር ፣ ቀኑን የሚያጨልም፣
ባዶ የሚያረጋት ፣ የመኖርን ትርጉም።
እንሰማለን ከዛ
እዚ'ጋ ብጥብጥ ፣ እዛ ሰው አለቀ፣
ይህን የሚያህል ህዝብ ፣ መኖሪያ ለቀቀ።
ኑሮን እየኖረ ፣ 'ካገር ወጦ ያለው የተሞላቀቀ፣
አለሁ ባይ 'ባገሬ ፣ ቀን ውሎ ለመግባት እየተሳቀቀ።
ሁሉም አንድም ሳይቀር ፣ ተዋልዶ ከሁሉም ሲኖር እነዳልነበር፣
በጥላቻ ወኔ ፣ በዘር ጎሳ ስካር፣
ቤተሰብ በትኖ ፣ ውጣ ከሀገሬ ድንበርህን አስምር።
#ጥላቻ ፍቅርን ፣ በዚ በዚ ምክንያ፣
ቁመትም ክብደትም ፣ በደጋፊም በልጦት።
#ፍቅር በአንጻሩ ፣ ጉልበቱ ጠንፍፎ፣
በረሀብ በጥማት ፣ ብርታቱ ተገ'ፎ።
የሃይሉን ተራራ ፣ የማይናድ ግርማው፣
ትንሿ ድማሚት ፣ ጥላቻ ደርምሳው።
ከጎኑ 'ሚቆሙ ፣ የልቤ 'ሚላቸው፣
ትተውት ሄደዋል ፣ ጥላቻ ገዝቷቸው።
እናም ቀኑ ደርሶ ፣ መፋለሚያው ሰዓት፣
አሸዋ ከሆነው፣አእላፍ ከሆነው ፣ #ከጥል ደጋፊ ፊት።
#በፍቅርም በኩል ፣ በጣት 'ሚቆጠሩ ቢሞቱም 'ማይከዱት፣
ነበሩ የቆሙ ፣ እኛ አለን ብለውት።
የጥል ደጋፊዎች ፣ ሞቆ ጭፈራቸው፣
የፍቅርን ሜዳ ፣ አርገው የራሳቸው።
#ፍቅር_ከ_ጥላቻ ፣ ፍልሚያው ተጀምሮ፣
ፍቅር በሃገሩ ፣ እነደ ባዕድ ተቆጥሮ።
ባላወቁ ሰዎች ፣ የፍቅርን መዛል፣
#ፍቅር_ያሸንፋል ፣ በየቦታው ሲባል፣
እንኳንስ ማሸነፍ ፣ መቆምም አቅቶታል።
#ፍቅር_ያሸንፋል_¡
@DannyShy
@getem
@getem
ጥላቻ ፣ በርትቶ፣
#ዘረኝነት 'ሚባል ፣ ቆንጆ ስም አግኝቶ።
ጡንቻውን አፈርጥሞ ፣ እንደ ድልብ በሬ፣
ይንጎማለል ጀመር በ'ያደባባዩ ፣ እዚም እመንደሬ።
ብዙን አሳንሶ ፣ አንድ እያነገሰ፣
ከእኔ ውጭ ወዲያ ፣ ብሎ እያፈረሰ።
በፈርጣማ ጡንቻው ፣ አምሳሉን እረግጦ፣
'እኔ' ና 'የእኔ' ፣ በሚሉ ፈሊጦች ሌላውን ደፍጥጦ።
እንሰማለን ከዛ
ከ'ያቅጣጫው ዜና
ቅስምን የሚሰብር ፣ ፍቅርን የሚያሳዝን፣
የሚያለብስ ፍርሃት ፣ የሚያቆስል ልብን።
ነፍስን የሚ'ያሸብር ፣ ቀኑን የሚያጨልም፣
ባዶ የሚያረጋት ፣ የመኖርን ትርጉም።
እንሰማለን ከዛ
እዚ'ጋ ብጥብጥ ፣ እዛ ሰው አለቀ፣
ይህን የሚያህል ህዝብ ፣ መኖሪያ ለቀቀ።
ኑሮን እየኖረ ፣ 'ካገር ወጦ ያለው የተሞላቀቀ፣
አለሁ ባይ 'ባገሬ ፣ ቀን ውሎ ለመግባት እየተሳቀቀ።
ሁሉም አንድም ሳይቀር ፣ ተዋልዶ ከሁሉም ሲኖር እነዳልነበር፣
በጥላቻ ወኔ ፣ በዘር ጎሳ ስካር፣
ቤተሰብ በትኖ ፣ ውጣ ከሀገሬ ድንበርህን አስምር።
#ጥላቻ ፍቅርን ፣ በዚ በዚ ምክንያ፣
ቁመትም ክብደትም ፣ በደጋፊም በልጦት።
#ፍቅር በአንጻሩ ፣ ጉልበቱ ጠንፍፎ፣
በረሀብ በጥማት ፣ ብርታቱ ተገ'ፎ።
የሃይሉን ተራራ ፣ የማይናድ ግርማው፣
ትንሿ ድማሚት ፣ ጥላቻ ደርምሳው።
ከጎኑ 'ሚቆሙ ፣ የልቤ 'ሚላቸው፣
ትተውት ሄደዋል ፣ ጥላቻ ገዝቷቸው።
እናም ቀኑ ደርሶ ፣ መፋለሚያው ሰዓት፣
አሸዋ ከሆነው፣አእላፍ ከሆነው ፣ #ከጥል ደጋፊ ፊት።
#በፍቅርም በኩል ፣ በጣት 'ሚቆጠሩ ቢሞቱም 'ማይከዱት፣
ነበሩ የቆሙ ፣ እኛ አለን ብለውት።
የጥል ደጋፊዎች ፣ ሞቆ ጭፈራቸው፣
የፍቅርን ሜዳ ፣ አርገው የራሳቸው።
#ፍቅር_ከ_ጥላቻ ፣ ፍልሚያው ተጀምሮ፣
ፍቅር በሃገሩ ፣ እነደ ባዕድ ተቆጥሮ።
ባላወቁ ሰዎች ፣ የፍቅርን መዛል፣
#ፍቅር_ያሸንፋል ፣ በየቦታው ሲባል፣
እንኳንስ ማሸነፍ ፣ መቆምም አቅቶታል።
#ፍቅር_ያሸንፋል_¡
@DannyShy
@getem
@getem