ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እኔ ለሀገሬ.3gpp
3.5 MB
ግጥም ፡ በላይ በቀለ ወያ
ንባብ( አቅራቢ) ፡ መብረቁ ጥቁር ሰው(መባ)

@getem
@getem
@Bookfor
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (👋ገብረዬ)
ሠላም ለሁላችሁ
#የሥዕል_ዉድድር ሰሞኑን እምንጀምር ስለሆነ ለመወዳደርያችሁ የሚሆነውን ምርጥ የምትሉት ሥዕላችሁን ላኩልን!!!
ለውድድር ሚበቃውን እኛ መርጠን በመልቀቅ #vote_እናስደርጋለን

#ከፍተኛውን like ያገኙ 3 አሸናፊዎች
የ ሥዕል መሳያ እቃዎችና ፣ የኢንተርኔት pakage እና የካርድ ተሸላሚ ይሆናሉ።

#የራሳችሁ_ያለሆነ ሥዕል ማቅረብ ከቻናሉ ያስባርራል!!!

ሥዕላችሁን ምትልኩበትን አድራሻ
@gebriel_19 ነው

ሠአሊያን ተዘጋጁ መለካም እድል!!!

@seiloch
@seiloch
በሰላም መቃወም
እዮብ ሰብስቤ
:
ማርቲን ሉተር ኪንግ ሆይ
ማመፅ እንዴት ይሆን?
ኔልሰን ማንዴላ ሆይ
ማመፅ እንዴት ይሆን?
ባ'ካችሁ ስለ ሀገር፤
ስለ እናቶች ክብር፤
ማመፅ እንዴት ይሆን?
እኛ እንደው ስንሻ ለማግኘት ነፃነት
ጠብመንጃ አንግተን
ምርጫችን ነው መዝመት።
ውሀውን ተክቶ ደም በቦዩ ሳይፈስ
ጋሻ ጦሩን ሰብቆ ሰው ሳይጨራረስ
ተገምብቶ የቆመው ወድሞ ሳይፈራርስ
ክብሯ ሳይደፋ፤
ሀገር ሳትጠፋ፤
እንደ ጅረት ሆኖ ሳይንቆረቆር ደም
እንዴት ይሆን ማመፅ በሰላም መቃወም?

@getem
@getem
@gebriel_19
ፀሀፈ ብሩክ

ብረ–አብሔር
አባታችን ሆይ ሰማይ እርቆህ
በምድር የምትኖር
ስምህን የምንቀድስ
አንተም እኛን የምታድስ
መንግስትህ በኛ የከተመ
መሄድ መምጣት ያልቃረመ
ለፈቃድህ የማንፀልይ
የምንኖር አንዴ ፈቅደህ
የለት እንጀራ የማንጠይቅ
ባንተ ፍቅር የምንጠርቅ
የማንለምን ይቅርታህን
የለት በደል የሌለብን
አንተ ካለህ ከኪሳችን
የምን ፀሎት
የምን ምልጃ በደል ፅድቀት
እስክትጎል ካለህበት
እስኪያቅትህ ሰውን መግዛት።


@getem
@getem
@Birukam
"የኔታ መርቀኝ"
==
አኮፋዳ ባልይዝ የቅኔ ድብተሬን
ሃሁን ባላጠና የአድማስ ፍሬ ስንቄን
በለብቅህ ገርፈህ
በጣጦችህ አሽተህ
ባንደበትህ ቀልጽህ
ግዴለም ግረፈኝ መርቀኝ የኔታ
ያላዋቂ ልቤን አሳውቅው ቀርጸህ የፊደል ገበታ

እሷን ለኔ ይዤ መርቀኝ እስከሷ
በሻገተ ቆሎ በሻገተ ድርቆሽ ፍቅር ይሁን ምሷ
የልጀነት ወዜን በልጀነት ወዟ እንዳስታረቀችው
ጎዶሎ ግራዬን እንደሞላ ቀኜ ሞልታ ባሳየችው
መርቅልኝ እሷን መርቅልኝ እኔን
ቤታችን ግባልን ባርክልኝ ጎኔን

Mezin worku

@getem
@getem
@getem
Ethiopia: ዜጋ በሌለበት ምን ይሉት ፈሊጥ ነዉ የዜግነት ክብር!!” 16k
Andafta
ዜጋ በሌለበት ምን ይሉት ፈሊጥ ነዉ የዜግነት ክብር!!”

👤 አንዳፍታ
ግጥም ብቻ

🕢 10:20
💾 1።2 MB

@getem
@getem
@gebriel_19
መርጋት ምን ድረስ ነው?


ታገስ ተረጋጋ፣
ታግሶ የረጋ ወተት፣ቅቤ ይወጣዋል
ብላቹ ብትመክሩት፣
መታገሱ ብቻ፣ምንስ ይበጀዋል፥
ለቅቤው ቢረጋ፣
ቅቤውን የሚሻ፣አፍኖ ይንጠዋል።

ስለዚህ-
ምክራቸውን ትፋና፣
የኔን ምክር ዋጠው፥
ቅቤህ እንዲወጣ፣
እስኪንጡህ አትጠብቅ፣
ራስህን ናጠው።


ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
(@San2w)
08/08/2011 WOLDIA UNIVERSITY

@getem
@getem
@getem
#ኢዮሪካ
( አሚር የ ሸምስ )

የለሊት ጭንቀቴ ምናቤን አይቶልኝ
ፀሎቴን በመስማት አምላክ ፈረደልኝ
ከአንድ መሸታ ቤት ዳግም ተፈጠርኩ
እውነተኛ ፍቅርን ኢዮሪካ አልኩኝ::

ማንቆርቆሪያ ይዛ ብርሌ ምታድል
የቀሉ ጉንጮቿ ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል
በስርቅርቅ ድምፇ ቀልቤን ተነጠኩ
አግድም ላይ ቁጭ ብዬ ኮማሪት አፈቀርኩ::
አይን አይኗን እያየው በድንገት ፈዘዝኩኝ
ታሪክ ተለውጦ በገሀዱ አለም ሴት ልጅ አፈቀርኩኝ

.........መንገዴን ዘንግቼ በጠጅ ድንፋታ
.........በኮማሪት ፍቅር ነብሴ ተንገላታ
ጠጥቼ ጨርሼ ወደ ቤት ሄድኩ ስል
መንገዴን ተጉዤ ብዙ ርቀት ሄጄ
ኩርባዎችን ዞሬ ቤቴ ደረስኩ ስል
.....የፍቅሯ መአበል
አዙሮ ይጥለኛል እዛው ጠጅ ቤት ስር::

.......ደግሞም ከምግብ ቤት
ምግብ ለመመገብ ካፌ ጎራ ካልኩኝ
አስተናጋጅ ሁሉ እሷ እየመሰሉኝ
ከአስተናጋጆች ጋ እነታረካለው እዘባርቃለው
ምግብ በብርሌ ቅዱልኝ እላለው::
ያለመደብኝን ብርሌ ታቅፌ
ወደኔ ስትመጣ አንገቷን አቅፌ
ስትቀዳ አጎንብሳ ጡቶቿን አያለው
ሰከንድ ሳይሞላት ትንሽ ስትርቀኝ
የቀዳችው ሳያልቅ ድገሚኝ እላለው
ጡቶቿ ናፍቀውኝ መልሼ እጣራለው
ሰረቅ እያረኩኝ ደረቷን አያለው
ፍቅርን በማለት ኪሴን እያጎደልኩ ብርሌ አስሞላለው::

@getem
@getem
@getem
** ሄዱ በ1 ጊዜ! **
"""""""""፠"""""""""
@Johny_Debx
ነበር ቀርቶ መሆን በርትቶ
.... አይ~
መቼ እንዳምናው አቤት' ካልሠጠኸኝ "መቶ"!
"ወዴት" ሲቀይር ደርሶ "በእንዴት"?
መፃፍ ትዝ ቢለኝ~ ከድሮ ቢተወኝ፣
.....እኔም አልኩኝ ታዲያ~
ገንዘብ ተከምሮ ካልሆነ ተራራ!
ሠው አየው ይሉኛል ሄደው በየተራ?

@getem
@getem
@getem
''ክደት ያከባብረን''
~~~~~
እንኳን አንድ ገነት 'ሺ ገነት ይቅር
እንኳን አንድ በለስ 'ሺ በለስ ይረር
.....ብቻ አብረሽኝ ነይ
የኤዶምን ውሃ ይቅር ለፈጣሪ ካጠገቤ አትለይ
.....
በሰውነት ተርታ የጉልበቴ ክፋይ ከእንብርትሻ ባይወጣ
የአለምን ጣእም በምላስ ባልቀምሰው ማሩ ቢኮ'መጣ
የተጋረደው የፈጣሪን ሸማ
ቀምሰን ልንፋ'ትተው በ'ፀ-በለስ ጣዝማ
ደግሞ በዚህ ዘመን ዝሙትና ሴራ በበዛበት ጊዜ
እንዴት ይፈሩታል ያምላክን እርግማን የሰውን ኑዛዜ
ነይልኝ ዘበ'ናይ......!
ቆፍረን ሞንጭረን የጠፋውን ፍቅር በገሀዳ እናሳይ
አንቺ ግን ተከተይ
......
በቅጠሉ ክልል በሀፍረተ ገ'ላ
የተገለጠውን የ'ውነት አለም ሚስጥር በሀሰት ከለላ
በሚቀደድ እራፊ
ማንነት ክብራችን ከለበስነው ሸማ ቀድሞ እረጋፊ
ያውም ላንዲት ፍሬ ተቆርጣ ለምትወድቅ
እየሰሩ ማፍረስ አጣብቀው ማላቀቅ
እውነቴን ነው ምልሽ 'ክደት ያከባብረን'
እኔም ሀገር የለኝ አንቺም ጌታ የለሽ ፍቅር ያሳድረን
====
አንቺዬ......
አብሮ ለመኖር ግን አንድ ህግ እንስራ
አብረን የምንጾመው ቀለም ያልገለጸው ከብ'ራና ሼራ
የጋራ 'ፀ-በለስ የሞት አሪማሞ በሁለታችን ይብራ
እሱ ይሁን ቃሌ.....
አይንሽ ካይኔ ሌላ የሚያይ እንደሆ'ን
ይሄ ይሆን ቃልሽ....
አይኔ ካይንሽ ሌላ የሚያይ እንደሆ'ን
ግዴለም ነይልኝ ''ክደት ያከባብረ'ን''

mezin worku

@getem
@getem
@getem
👍1
እነርሱ!!!!

((እዮብ ሰብስቤ))

ሌባ ነበር አሉ!
ያጣ የገረጣ
የከሳ የነጣ
ቁራጭ ዳቦ ሰርቆ
አመት የተቀጣ፡፡
ዛሬ ግን ጀግና ነው
ሲሉ ያደንቁታል
ሀገር ሲመዘብር
መቼ ይነኩታል
ጭራሽ ይባስ ብለው
ድርሻዬን ይሉታል፡፡

@getem
@getem
ሀገር እና ግጥም
""""""""""""""""

እኔ ያለ ሀገሬ ቅኔ ብደረድር
በህብረ ቃል አስውቤ
ሰም ከወርቅ አድርጌ ፤ግጥሜን ብሰድር
ብቀምር......ባሳምር
የሚያምርብኝ በሀገር!

(ግና)

አንድ እግሬን ባነሳ
ልጥፋ ብል ከሀገሬ
የሰው ሀገር ብመኝ በተስፋ ሰክሬ
ቅኔዬም መከነ ጠፋ ቁም ነገሬ
ጦቢያዊ ነው 'ሚያውቀው
የሆድ ሆዴን ብሶት የቃላቴን ፍሬ።

አብርሃም

@getem
@getem
@gebriel_19
...የበስ ያጡ ነብሶች…
...ስምህን አላውቀው ስቃይህ ነው የጠራኝ
የሞት ሽረት ትግልህ ልቤን ሰብሮ ያስከፋኝ፤
ምስኪኑ ወንድሜ… እናስ ምን ልበልህ…
ያንተን ቦታ ይስጠኝ - እኔ ተስፋ ልጣ - ልንከራተትልህ፣
አየሩ ይጠረኝ - ምድርም ትካደኝ - ባህር ልውደቅልህ፡፡
---
ጋዝ ጋዝ ለሚል ኑሮ - ጨው ለሞላው ውሀ፣
የከበበው ፅልመት - የፈሳሽ በረሀ፣
ከጥልቁ ውቅያኖስ - ከማጣት ሸለቆ - ከሻርክ ሽርከታ፣
መድረሻ አልባዋ - ከርካሳዋ ጀልባ ፣
አጭቃ ያዘለች - የተስፋ ጭላጮች - የመለወጥ ዳባ፣
የብስ ያጡ ነብሶችን - ከኦና ላይ ጥላ፤
እሷም እንደኑሮ - ክዳቸው ስትሰምጥ - ወደስር ስትገባ
እንጀራ ፍለጋ - ቀሩ እንደወጡ - ለማይጨበጥ ተስፋ!
አበቦች ረገፉ - ልክ እንደገለባ ፥
...ምስኪን ወገኖቼን - ስደት አ’ረጋቸው የውሀ ሰለባ::
---
(ግጥሙ በቀይ ባህር ሰጥመው ህይወታቸውን ላጡ ከርታታ ወንድሞቼ በሙሉ ይሁን፤... የሐገሬ ሰው እባክህን ከዚህ የእርስ በርስ ሽኩቻና ፀብ ውጣ። ሩቅ ካለው የሐገርህ ዜጋ ጋር ከምትነቋቆር ከጎንህ ያለውን ወንድምህን እርዳ! ስሜታዊነታችንን እንተወውና ይህቺን ምስኪን ሐገር ከዚህ አንገት አስደፊ ድህነታችን እናውጣት!!)

-------(ገጣሚ ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)

@getem
@getem
@getem
አንቺን - ነበረ

( አበባው - መላኩ )

አበስኩ ገበርኩ ብያለሁ
በጾም ጡትሽን አይቻለሁ
በማማት ስወድቅ ስነሳ
ባንቺ ባዬሁት አበሳ
ልቤ ተሰብሮ ካልቀረ
መስቀልስ አንቺን ነበረ።

@getem
@getem
ለአንዳንድ ሰማዮች

((እዮብ ሰብስቤ))

ደመናማ ሰማይ!
ከንፋስ ተማክሮ እምቡጦች ሊያስደንስ፤
በውሀ መልክ ሲረጨው ሀብቱን ሲነሰንስ፤
ፅጌሬዳነትሽን ሊቀጥፍ ፈልጎ፤
በረዶውን ሲልክ፣ ውሽንፍሩን ሲልክ፣
አማላጅ አድርጎ፤
ቢራቢሮው እኔ!
ሰማዩ በቅናት!
ሲጠቁር ሲፈካ አሻቅቤ እያየሁ፤
ባበቦች ግዛት ላይ፣ እምነሸነሻለሁ፡፡
እስቅበታለሁ !
እ…..ስ……ቅ…..በ…..ታ…..ለ…..ሁ፡፡
በ…………..ቃአ!
እርሱ! በገፍ ይዞ
የኮከብን ውበት የጨረቃን ድምቀት
የፀሀይን ሙቀት በወጉ ካልረካ፤
ላጓጉል ነው እንጂ ቅስምን ለሚነካ፤
ምን ያደርግለታል ያበቦች መዓዛ፣ የእምቡጦቹ ቀለም፤
የሚያስጎመዥ ሁሉ የሚበላ አይደለም፡፡
ይልቅስ ንገሩት!
ተፈጥሮን አዛብቶ
ከቢራቢሮው ጋር ከንብ አይፋለም
በጨረቃ እቅፍ ነው የፈካው የእርሱ ዓለም፡፡
በወሰኑ ይንገስ በድንበሩ ይግዛ፤
ከፀሀይ ይጠጋ በኮከቦች ይውዛ፡፡
ከፍታውን ያስብ ለክብሩ ይጠንቀቅ፤
የራስን ያሳጣል የሌላውን መንጥቅ፤
ብላችሁ ንገሩት፡፡
አዎ ! ሂዱ ንገሩት፣ ጠፈር አምላኪዎች፤
ለረገፈ ገላ አበባ ላኪዎች፡፡

@getem
@getem
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (👋ገብረዬ)
#ለተወዳዳሪዎች

የመጀመርያው የመወዳደሪያ ፎቶ ይህ ነው።
ሥዕሉን በ #እርሳስ ነው እምትስሉት
የምታስገቡበት ቀን ከዛሬ ጀምሮ እስከ #ሚያዚያ_18 ነው።

ለጥያቄና ሥዕሉን ለመላክ @gebriel_19 ተጠቀሙ

#መልካም_እድል!!
ሥዕል ብቻ

@seiloch
@seiloch
እንደምነህ እግዜር?
(አሌክስ አብርሃም)
.
እንደምን ነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው ?
እኛማ .....
ለእልፍ አላፍ አለቃ
ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን
ፆለት ቤታችንን
እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ
ህግጋቱን አልፈን ደብዳቤ ላክንልህ፤
አይንህን ካየነው
ሁለት ሽ ዘመን
እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ
መቅረትህ ገዘፈ ...
እንደውም እንደውም ...
‹‹በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ሽ ዘመን
ቀጥሮን ከጠፋ
በቀጠሮው ሰአት
መምጣት ከተሳነው
እግዜር አበሻ ነው›› እያሉ ያሙሃል
እኔ ምን አውቃለሁ ...
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ
እግዚኦ በሉ ሲባል ...እንባየን የማፈስ
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ ...በሳቅ ልቤ እሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ ምን አውቃለሁ ...
ግን አንተ ደህና ነህ ?
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ !
ከሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው
አብረሃም ሰላም ነው ...
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው ?
እኛማ ይሄውልህ ...
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
‹‹ኤሎሄ›› እንላለን ጎጆ እንድጥልልን ....
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን
እንደጉድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን !!
አባታችን ሙሴ እነዴት ነው ለክብሩ
ውቂያኖስ መክፈያው ደህናናት ብትሩ ?
እኛማ ይሄውልህ ....
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ን ገ ር ል ን ና ብትሩን ያውሰን ....
እናልህ እግዜር ሆይ ....
ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን
...!
ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን ...
‹‹የመሄድ ዘመን ነው
ባህር የመሻገር
‹‹ዱላህን ላክልን›› ብሎሃል በልልኝ ...
ሰማይ ቤት እንዴት ነው ? ....ዳዊትስ ደህና ነው ?
ዛሬም ይዘምራል ...ዛሬም ይፎክራል ?
ሰላም ነው ጠጠሩ .... ሰላም ናት ወንጭፉ ?
እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ ?
እልፍ አላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ ?
ብሎሃል በልልኝ !!
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ
‹‹ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ››
ብለህ እዘዝልን !!
እንዴት ነህ ጌታ ሆይ ... ሰማይ ቤት እንዴት ነው ?
የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው ....
ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው ...
ያው እንደምታውቀው
አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው ...
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ ፀሃይ እያዘለ
የተሸመው ሁሉ ‹ፀሃይ ነኝ› እያለ
የአስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ
የአስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሃይ ሁኖ እንደመፈጠር ....
ኧረ እግዜር በናትህ ....
ኧረ እግዜር በናትህ ...በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና !
እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል ...
ጳውሎስ ሲሉን ...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ...ወይየ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን
ስማችንን ሸጠን ...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን
ተወው የኛን ነገር ...ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
ሂዋንስ ደህና ናት ?
ያው የልጅ ልጆቿ
በእግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ
ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም
ባይኑ ያገምጡታል
ሰይጣንም ደህና ነው
ኑሮ ተስማምቶታል

@getem
@getem
@getem
👍1
////የባልእንጀሬ ወግ///

የተፈጥሮ ውበት እውነት ነው ክስተቱ
አብቦ እንዳፈራ ከስሞ መተኛቱ
ይህን እያወጋኝ ከጎኑ ወሽቆ
እራሴን አስናፈቀኝ ከራሱ ደብቆ
ብላ የምትለኝ አለች ባል እንጀሬ
ላለመስማት እክል በህመም ታስሬ

ብዙውን በቃሏ ታወጋኝ ነበረ
ፍቅር ከጥላቻ እርቅ እንደ ጀመረ
ለማለት ፈልጌ ምን ነበር ቃላቱ
ሰብከት መጀመርያው መውረጃ ድርጊቱ
ልልህ የፈለኩት ከሰመ ሀሳቡ
ለምንም ምላሽ ነው የመጥፊያው ሰበቡ

ባዶነት ሲገዝፍ የማንነት ልኩ
መጥፋቱ ካልቀረ የመሰከርከው ቃል
አበው እንደሚሉት ከልጅ ቃል ይበልጣል
ዕዳ ነው አይጠፋም ውስጥን ያናውጣል
በዚህ አንድ ሀሳቤን ለማለት ፈልጌ ምን ነበር ቃላቱ
ስብከት መጀመርያው መውረጃው ድርጊቱ
መሄጃ እንዳጣ እንዳመለኛ ወንዝ
ቤቴን እንደሞላህ የውሸትህን መዘዝ
እንደ ደራሽ ውሃ ባከላቴ ፈሰህ
እርግማን አልወድም መነሻ ያሳጣህ ...!!!!
ተከተበ

በ ሮዚ የያቡ


@getem
@getem
@gebriel_19