ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ቆሎነት እና ብልሐት
(ልዑል ሀይሌ)

ቆሎ ነው ጥሬ ነው የአንዳንድ ሰው እውነት፤
ቆርጣሚን መማጠን የተዘገኑ ዕለት፤
ዘጋኝ እጅ ከገቡ ምን ምን ሊያ'ረግ መማጠን፤
ፈጣሪ ሆይ ስማን
ከመዘገን በፊት
ከሰፌድ ማምለጫ አንዳች ብልሐት ስጠን፤
፬-፰-፳፻፲፩ ዓ.ም.

@getem
@getem
@gebriel_19
Forwarded from SPACE COMPUTER
Forwarded from SPACE COMPUTER
#ድምፃችን_ሁሉም_ጋር_ይደርስ_
ዘንድ_ሼር_በማድረግ_የበኩላችንን_እንወጣ !!
.
እስቲ በዘረኝነት በጠባብነት በወገንተኝነት የጠበበውን ዓይናችንን እና ጆሯችንን እንክፈትና የሰውን ልጅ ሰቆቃ የሰውን ልጅ ተማፅኖእናዳምጥበት!!...እንይበት!!...ብሩ ህ ተስፋ ትባላለች..ስትወለድ እንደስሟ ብሩህ የሆነ ተስፋን ይዛ ይህቺን ምድር የተቀላቀለች ነገር ግን ባላሰበችውና ባልገመተችው አጋጣሚ የውፍረት ሆርሞን ችግር ገጥሟት በ2 ወራት ውስጥ 90 ኪሎ የጨመረች ሕክምናውም ሐገር ውስጥ እንደማይገኝ እና የውጪ ሕክምና ለማድረግ ደግሞ
700,000 ብር የተጠየቀች እህታችንን ወደ ጤንነቷ ትመለስ ዘንድ የበኩላችንን ጥረት እያደረግን እንገኛለን። አግዙን!!...አግዙን!!
...አግዙን!!...እባካችሁ ሰኞ ሚያዚያ 7 በሚቀርበው የኪነ-ጥበብ ምሽት ላይ በመገኘት "እኔም ብሩህ ተስፋን ላድን የተቻለኝን አደርጋለሁ!!..." የሚል የአጋርነት ድጋፋችሁ አይለየን።

አዘጋጆች:- እንድቅትዮን የኪነ-ጥበብ ቤተሠብ፤አለን የበጎ አድራጎት
ማሕበር፤ኑሃሚን ፕሮዳክሽን፤ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጋር በመተባበር

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
Ethiopia: “ለውጥ መጣ ሲሉን ድጋፍ እየወጣን ነፃ አውጪ ነን ሲሉን በሰልፍ እየወጣን ለውጥ ወዴት……
Andafta
"ለውጥ መጣ ሲሉን ድጋፍ እየወጣን ነፃ አውጪ ነን ሲሉን በሰልፍ እየወጣን ለውጥ ወዴት አለ መቼ ነፃ ወጥን!!” በበላይ በቀለ ወያ
👤


🕕 10:02
💾 1.2 mb
ግጥም ብቻ

@getem
@getem
@getem
" ፅኑ እንባ"

አዝማች ያንቺ ገላ ለሙዚቃው ነብሴ
እንዴት ሆኜ ልኑር ልሸሸግ ከራሴ...???
......ፍቅርሽ ዶቃ አመድ ነው ተውቦ እማይጠቅም
እንቡጥ ለነበረው ለልጅ እግር ልቤ ማሸበቻ ቀለም
እንጂ አንቺ ምን ተዳሽ ምን በደልሽ እናቴ
ከጅሽ ስሞትብሽ ልቅበርህ አልሽ እንጂ ከአፈሩ አከላቴ፡፡

✍️.......አብርሀም <ልጅ ኤቢ>

@getem
@getem
@gebriel_19
"ትስብእት"

ጉራጌ ነህ ብሎ ሲነግረኝ አባቴ
አንተ ሲዳማ ነህ አለችኝ አክስቴ
ሴት አያቴ ደግሞ ይሉኛል አማራ
ትግሬ ነህ ይለኛል የኔ ባልንጀራ
የእናቴ ዘመዶች በአንድ ድምፅ ባድማ
አንተ ኦሮሞ ነህ ማንንም አትስማ
ሲሉኝ ስለሰሙ ወንድ አያቴ ፈጥነው
ሀረሪ ነህ አሉኝ አመጣጤን ቆጥረው
የዚኔ ሲጨንቀኝ ስለገባኝ ግራ
ገበሬ ባልሆንም ገባሁ ዘር ቆጠራ
ጉራጌ ነህ ብለው ነግረውኝ የኖሩ
ምንጅላቶቼ ግን አርጎባ ነበሩ
ቅም አያቴ ምዕራብ ነበረ መዠንገር
ቅድመ አያቴ ደግሞ ምስራቅ ነበር ሀረር
አጎቴ ከሰሜን አግብቶ ኩናማ
አክስቴም ለደቡብ ተዳረች ሲዳማ
ሴት አያቶቼማ ስለተዘናጉ
ብዙ ሰው ተላልፏል በራቸው ሳይዘጉ
አባቴ ጉራጌ እናቴ ኦሮሞ
ታዲያ አሁን ምን ልሁን ምንስ ነበርኩ ቀድሞ
ብሔሬን ለማወቅ ያረግኩት ዘመቻ
ሆኜ ያገኘሁት ኢትዮጵያዊ ብቻ !

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@getem
@getem
@getem
ሰውየው ሩሚ ነው ገጣሚ ብቻ ሳይሆን በራሱ ግጥም የሆነ ሰው። በፐርሺያ እና በፐርሺያዊያን ልብ ውስጥ የማይጠፋ ብርሀን። ምንም እንኳን በ1273 በ66 አመቱ ይህቺን ዓለም ቢሰናበታትም ዓለም ግን ጨክና ልትሰናበተው አልቻለችም ምክንያቱም ከዛሬ 700 አመት በፊት የፃፋቸው ግጥሞች ህያው አድርገውታልና፤ እንደ ወይን ጠጅ እያደር የሚጣፍጡ ስንኞቹ ዛሬም ድረስ የማስደመም አቅማቸው የሚናቅ አይደለም።

ጀላለዲን ሙሀመድ ሩሚ የፐርሺያ ቅኔ ልብ።

በረከት በላይነህ የመንፈስ ከፍታ በተሰኘው ስራው የሩሚን ግጥሞች በስፋት አካቷል እዛ ላይ ብዙ የሩሚን ግጥሞች ማግኘት ትችላላችሁ ለዛሬ ግን አንድ የሩሚን ግጥም ተገባብዘን እንሰነባበት

if You want the moon...
do not hide at night.
if you want a rose...
do not run
from the thorns.
if you want love...
do not hide
from yourself.
(ሩሚ አንደፃፈው)
:
:
ጨረቃዋን ካሻህ
ከጭለማ ታረቅ
አበባዋን ካሻህ
ከሾሗ ተዋደቅ
ፍ ቅ ርን ከፈለክ
ከራስህ አትደበቅ።

( ወደ አማርኛ እንደመለስኩት)

©rumi!

#eyoba

@getem
@getem
@getem
#እኛ_ጓደኛሞቹ
አቅራቢ :ትንቢት ዳንኤል
ገጣሚ ፦ትንቢት ዳንኤል

@getem
@getem
ግጥም ብቻ
Belay Bekele Weya
ፍካሬ እውነት የሚለው የክቡር ሰው በእውቀቱ ስዩም ግጥም ወደ ዘመናችን ፖለቲካ ቢቀየርስ?
(በላይ በቀለ ወያ) ፈገግ ብላችሁ እደሩ
.
.
ሰማዩን
የአፄዎቹ ነገስታቶች፥ ሳይወረውሩት አርቀው
ፀሐይ ጨረቃ ሳይመጡበት ፣ በቀን በሌት ተፈራርቀው
ከዋክብቱ ሳይሰፍሩበት ፣ ከገበሬው ቦታ ነጥቀው
የአያቴ ምድር ነበር ፣ ቅድመ አያቴ የሚያርሰው
የአፄው ዘመን በጉልበቱ
ፈጣሪና መላእክቱን ፣ ከኛ ላይ ነው የወረሰው "
ብለሽ የነገርሺኝን ፣ እውነት ነው ተቀብያለሁ
ምክንያቱም አንቺ ታጥቀሻል ፣ ባዶ እጄን እፈራሻለሁ
።።።
“አያቴ
ሶስት ሺህ አመት ታገለ
ገና ሀምሣ አመት እያለ
አንዲት ኢትዮጵያን ለማቆም ፣አንድ አለም በጥፊ ጣለ
አንድ ጥይት ተኩሶ፣ ቢልየን ጠላት ገደለ
እልፍ አእላፍ ጎልያዶችን ፣ በአንዲት ጠጠር ረታ
ለቡሔ ጅራፍ ሲተኩስ
ኒውክለር ታጣቂው ሁሉ ፣ ደንግጦ ትጥቆቹን ፈታ
ብለሽ የነገርሺኝን ፣ እውነት ነው ተቀብያለኹ
ምክንያቱም አንቺ ታጥቀሻል ፣ ባዶ እጄን እፈራሻለሁ
።።
“አባቴ
ትግሉ ከታጋይ ይለያል
አይኑን ጨፍኖ ሲተኩስ ፣ ጠብመንጃው ዐይን አለው ያያል
እሱ ለሠላም ሲታገል ፣ ሰላም ባስ በእሳት ይጋያል
ብለሽ የነገርሺኝን እውነት ነው ተቀብያለኹ
ምክንያቱም አንቺ ታጥቀሻል ፣ ባዶ እጄን እፈራሻለሁ
።።።
ግና ..
ጅል እንዳልመስልሽ ፣አይደለሁም በፍፁም ሞኝ
በእርግጥ እውነት ብዬሻለሁ ፣ በባዶ እጄ መሞት ደክሞኝ
እየሮጠ ያስታጠቀሽ ፣ ሲሮጥ ትጥቅሽ እስኪላላ
እውነት ማለት
ከገዳይ ጋር መሰንበት ነው ፣ ሟቹ ትጥቁን እስኪያሟላ

@getem
@getem
@Bebra48
👍1
እዛ ጋር ዝም በሉ ! 🤫

በፍርሃት ደውል የምትናውዙ
ብልጥ በበዛበት እናንት 'ምትፈዙ

🤫 እዛ ጋር ዝም በሉ !

በሆነው ባልሆነው ሽቅብ 'ምታናፉ
አቅም የሌለው ላይ ከምትደነፉ

🤫 እዛ ጋር ዝም በሉ !

ሁለት ፍቅረኛሞች የተቃቃራቹ የአብርሃም የሳራ ካልመሠለላቹ

🤫 እዛ ጋር ዝም በሉ !

ቆሼ የሚለቅም ፊደል ያለቆጠረ
አወኩ አወኩኝ ባይ ቆሻሻ 'ምትጥሉ

🤫 እዛ ጋር ዝም በሉ !

ለማይጠቅም ነገር በወንድምህ ላይ ተንኮል የምትሰራ
አጅሬን በለጥከው በክፋት በሴራ

ካለምከው ሆነሃል ልብህ የማይራራ
ክፋት ተቆልሎ ሆነልህ ተራራ

ለማይጠቅም ነገር በእህትሽ ላይ ተንኮል የምትሰሪ
ልዕልናሽ ወድቋል ጠንከር አርገሽ ስሪ
በጨለማ ሆነሽ ባትበሪ እንኳን ብሪ

እናንተም እናንተም በልባቹ ጓዳ ሴራ የምትጭሩ
ነቀፋ ትታቹ ጠቃሚውን አውሩ
የሰው ስም ተነስቶ ቅስም ከምትሰብሩ

🤫 እዛ ጋር ዝም በሉ !

ወንዶቹኔ በሙሉ የመሸትሞክሪ
ከዚኛው ከዛኛው እንዳሻሽ 'ምታድሪ

🤫 እዛ ጋር ዝም በይ !
......

ልጁን ከሚደፍር አባት ካልጠበቀን
የሰው ሆደሸ ዘርግፎ ከሚያድር ወመኔ ዐይን ካልሰወረን
እቅፍ ድግፍ አርጎ በዘር ከሚያባላን ነቅቶ ካልከለለን
በምላስ አታሎ ሴቶቹን ለሚፈጅ ከሌለ እንኳን ፈራጅ

🤫 እኔ ዝም ልበል !


(በሀይሉ አርጋው)

@getem
@getem
"ሰው" ሆሆሆሆ..ይይይይ !!!...."

ሰው" በመሆን ብቻ የምንግባትን ኩዳይ ስለሆነ እንብበህ "ሽር" !!!.....በማድርግ ግደታህን ትወጣ ዘንድ እንደእምነትህ እንደ አስተሳሰብህ በፈጣሪህ ስም
እንጠይቅሀለ!!!!................

በምስሉ ላይ የምትመለከቱዋት ወጣት ብሩህ ተስፋ ትባላለች። እንደማንኛውም ሰው ብሩህ ተስፋ ነበራት !!!አሁን ግን በደረሰባት ህመም የሆርሞን መጨመር የትነሳ ከ90 ኪሎ በላይ ጨምራለች የሰውነት ውፍረቶም እየጨመር በመሄድ ለተጎዳኝ በሽታውች ተጋልጣለች ይህንንም ህመም ለመታከም በሀገር ውስጥ ህክምና መዳን ስላልቻለች ከባህር ማዶ በሚገኙ ሀገራት ሂዳ ብትታከም እንደምትድን ከሀኪሞች ተነግሮታል። ብሩህን ለማሳገም የከቢ ማሰባሰቢያ በእንድቅትዮን የኪነ-ጥበብ ቤተሰብ፣ በአለን የጋዜጦች ማህበር ፣በኑሀሚን የፊልም ብሮዳክሽን እንድሁም ከቅን አጎሮች ጋር በመሆን ሚያዝያ 7 ሰኞ የኪነ-ጥበብ ምሽት እዘጋጂተናል። እረሶም በገቢ ማሳባስቢያው ምሽት በመታደም፣ሰውችን በመጋበዝ፣ሽር በማድረግ፣በምትችሉት ሁሉ በማድርግ ብሩህን እንታደጋት ዘንድ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን............





ሼር!!!
ሼር!!!
ሼር!!!.......

@getem
@getem
@getem
👍1
Ethiopia: ፈጣሪ ብሔሩ ምንድን ነዉ...?? 16k
Andafta
🎬 Ethiopia: ፈጣሪ ብሔሩ ምንድን ነዉ...?? በልዑል ሀይሌ

👤 Andafta
🕛 10:13
💾 1.2MB

@getem
@getem
@gebriel_19
ጣዕም
(( እዮብ ሰብስቤ ))

የውስጡን ጥፍጥና በሙሉ እያስላሰው
የማንነቱን ጣዕም ጨርሶ ቀነሰው፡፡
እረ ባክህ ንቃ!
በፍጹም አትሁን ግንድ አልባ ቅርንጫፍ
መሰልቸት እኮ ነው የመደጋገም ጫፍ፡፡

@getem
@getem
(ለአባቴ)
ደህና ነኝ፡፡
መንታላ ገላዬን ችጋር ቢደቁሰው
ፍቅር ስጠቀለል ክፋትን ብጎርሰው
ህልሜ ቢጨናገፍ መንገዴ ቢያደክመኝ
እንዳለኸኝ ሳስብ ተስፋ አለኝ ደና ነኝ፡፡

ማግኘትና ማጣት ቢፈራረቁብኝ
ዋዛ ሆኜ ብታይ ቁምነገር ቢያጡብኝ
ፈርሷል ብለው ሲያልፉ ሰባብረውት ውስጤን
አንተ የኔ ጋሻ ነገዬን በማጤን
በርታ 'እንጂ ስትለኝ
ተዛ እለት ጀምሮ ተስፋ አለኝ ደህና ነኝ፡፡
---
ምን አፍራሽ ቢበዛ ከየጎዳናው ጫፍ
ያዘን እንጉርጉሮ በአካላቴ ቢያልፍ
ብጎብጥ ባቀረቅር 'መላም የለህ' ብሰኝ
አባቴ ፊቴ ቁም
ስትኖረኝ ተስፋ አለኝ፡፡ ስትኖረኝ ደህና ነኝ፡፡

#ELU @Username_under_construction

@GETEM
@GETEM
#ኪርያላይሶ#

ታጥፎ፥ እንደ ድግ፥ወገቧን ዞሮ
እንደ ተረኛ ቄስ፥ሳይዘ'ጋ ያይኑ ጭራሮ
ሙሉ ሌሊት ከድሟት፥በፅናፅል በክበሮ
ተፈስሒ ዘምሮ
ለክብሯ፥ አጎንብሶ
ኪዳን፥ በስሟ አድርሶ
አልተሰረዬም ንስሃዉ፥ተመልሶ ኪርያላይሶ።

የጉም ፈትል ፈትሎ፥ቀጭን ክንዱ
አልቅሶ ወደ መሬት፥የሆዱን ይዞ በሆዱ...
ሆኖ ብኩን ፥እፉዬ ገላ
የዕብድ አሞራ፥ተከታይ፥ሲላ...
እንደ ሰንበሌጥ ጣሪያ፥የልብ ቋቱ አፍሶ
በቃኝ ብሎ፥ወይ ላይችለዉ፥ ጨርሶ
ነጋ መሸ ፥እሷን ብቻ ኪርያላይሶ።

#መሪጌታ
@getem
@getem
@gebriel_19
*አስማት *
ፀሀፈ ብሩህ

በትእዛዝ ወልዶት፣
መሪ አብዝቶበት፣
ቀኑን አርቆበት፣
ምስጋና ሸልሞት፣
እሺን መርቆለት፣
ጥሮ ግሮን ወርሶ፣
ህሊናን ሰውቶ
ለአንዲት ቀን አዳር፣
ሺ’ ቀናትን ገሎ
ካልቻለ ማሳደር፣
ነፍሱን ሳያሳርር
ሰው በእህል አይኖርም፣
እውነት ነች ክታቧ
አስማተኛ ይኖራል፣
የሆዱን ስልቻ በቃል የሚሞላ።

@getem
@getem
@Birukam
#Giday Kindaya
::ብርዱም ተነሳበት - ያው ዝናቡ መጣ '
ትውስ አለኝ ፍቅርሽ - አንቺን አለኝ አምጣ
#እርሷ_በንዴት :
የሄን ሁላ ጊዜ አንዴም - ትዝ ያላልኩህ !
ክረምቱ ሲገባ አሁን - የታወስኩህ '
ዘርተህ ያበቀልከኝ - በቆሎ መሰልኩህ !!😜😂
@getem
@getem
@kaleab_1888
Ethiopia: “የዘር ሀረግሽ ሲመዘዝ አፈር መሆኑን አትርሺ“በላይ በቀለ ወያ 16k
Andafta
“የዘር ሀረግሽ ሲመዘዝ አፈር መሆኑን አትርሺ“ በላይ በቀለ ወያ

👤 ግጥም ብቻ
🕡 10:04
💾 1.2 MB

@getem
@getem
@gebriel_19