ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አዲስ አድማስ !!

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!! የመደመርና የፍቅር የኪነ ጥበብ ምሽት!!
ነገ#💚
ሰኞ የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም በብሔራዊ ቴያትር ከቀኑ 11 ሰዓት እስከ ምሽት 2 ሰዓት በመደመር፣በይቅርታ፣በአንድነት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ግጥሞች፣ወጎች፣ዲስኩሮች፣........ይቀርቡበታል!

የስነፅሁፍ አቅራቢዎች

* ገጣሚ ነብይ መኮንን
*ገጣሚና የሥነልሳን ምሁር ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
*ገጣሚ ምስራቅ ተረፈ
*የፍልስፍና ምሁር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
*ሰዓሊ፣ቀረፂ ገጣሚ በቀለ መኮንን ❤️
*ደራሲና ሀያሲ አለማየሁ ገላጋይ
*ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ

የመድረኩ አጋፋሪ:- ተዋናይና፣ገጣሚ ፈለቀ አበበ

የምትችሉ ሰዎች ይህን ከባድ ሚዛን የሆኑ የጥበብ ሰዎች የሚገማቸሩበት የኪነጥበብ ምሽት ብትታደሙ እና በብዙ አትርፋቹ ብትመለሱ ምኞቴ ነው......

በጣም የምወደው በተለይ ደሞ በአንድ ድንቅ ግጥሙ ያስደመመኝን #በቀለ መኮንን ( ቼ በለው ) በሚለው ግጥሙ ያወኩትን ሰው ለማየት ጎጉቻለው እናም እታደማለሁኝ ......እናተም እንዳትቀሩ.....!!

---------------------------

ቼ በለው

ሕይወት ጎዳናው ገፁ ሲለወጥ
በጭነት ታክቶ ጀርባው ሲመለጥ
የእንቅፋት አፅሙ ቋጥኙ ሲገጥ
ሸክም ዘንቦበት ትቢያው ሲላቁጥ
ሲሆን ድጥ በድጥ
ሾህ ጭቃ ቅይጥ
ልብህ አይደንግጥ፡፡

በምኞት ቅዠት በስጋት ርዶ
አይፍረስ ግንቡ ወኔህ ተንዶ
ከቆመው ቆመህ ከንፈር ከመምጠጥ
በተስፋ ፈረስ በልጓም ሸምጥጥ፡፡
አያረጅ የለም አይለዋወጥ
ነገን ተማምነህ በመጓዝ ቁረጥ...
ከሩቅ አልመህ ቅርብ አትርመጥመጥ
ሰግተህ ከምትቆይ ስትጋልብ ፍረጥ፡፡

ሰዓሊ ቀራፂ፡ በቀለ መኮንን

ሰላም እደሩልኝ!!!💚💛

@balmbaras
@getem
@getem