ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ስቅታ

ስቅ ባለኝ ቁጥር ውዴ ደስ ይለኛል
ስሜን እያነሳህ ምታወራ ይመስለኛል
አነሳኝ እያልኩኝ ልቤን የማሞኘው
አረሳኝም ብዬ በማሰቤ እኮ ነው
እንጂማ ውዴ...
ትዝ እንዳላልኩህ ቀድሞንስ መች አጣሁት
ያፈቅረኛል ብዬ ፍቅሬን አታለልኩት
መረሳቴን ባይወድ ልቤ ቅር ቢለው ነው
ስቅ ባለኝ ቁጥር የሚለኝ እሱ ነው
እሱ ነው ...እሱ ነው....
ስምሽን ያነሳው ቢወድስ እኮ ነው
ይለኛል ይህ ልቤ....
መረሳቱን መርሳት እጅጉን ቢከብደው።
5-6-2011

#ፅዮን_ተፈራ

@getem
@getem
@gebriel_19