ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የስንብት ዑደት
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ቅር እያለው፤
የመለየት ሲቃ፤
የስንብት ዑደት፣ደልቆ እያመሰው፤
ደህና ሰንብች ብዬ ልሳኔን ስወቅሰው፤
"እንኳን ደህና መጣህ!" 'ምትል
አገኘሁ ሌላ ሰው!
የስንብት ዑደት፤
መለያያ መንገድ በርክቶ ባለበት፤
አዲስ ሆኖ አያውቅም
"ደህና ሰንብች" ማለት!
ስንብት ወንዝ ሆኖ. . .
የኋሊት እየናጠ ኑሮዬን ቢከልሰው፤
እንደ ገሃ አፈር ለሁለት ቢገምሰው፤
ጥያቄዬ ሌላ ነው. .
"ተክታሽ የመጣች፤
በምስራቄ የወጣች፤
የትዝታሽን አልቦ ከኔ የሰበረች
እሷ ግን ማን ነች?
የትስ ነበረች?"
መጥታ እስክትሄድ፤እስክትሰናበተኝ
የትዝታዎች አልቦ እያንከራተተኝ
ካንዷ ምህዋር ነቅሎ፣ሌላ ላይ ከተተኝ!
ቀድሞም. . .
ፍቅር በነፍሴ አድራ፤ትንቢቴን ስናገር
ሕይወት ይቀጥላል፤
ፍቅር ይቀጥላል፤ብዬሽም አልነበር?
.


@getem
@getem
@huluezih
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በአል በሰላም አደረሳችሁ።

Wishing my fellow Ethiopians a warm and happy Christmas!

@getem
@Wegoch
@seiloch
ክርስቲያን ወንድም እህቶቼ!
በገናው፣ "በእለተ-ሰላም ውልደቱ" ፊታችሁ ላይ የምናየው ሰላምና ደስታ ይቆይላችሁ፣
በቤታችሁና በቀያችን ይበርክት። ሳቅና ደስታ እድሜን የሚያረዝም፣ ጤናን የሚያለመልም
መድሃኒት ነውና፣ ዛሬ ስለገናው የምናየው የፍቅር ጭስ ሽታ በሁሉም ልብና በሚመጡት
ጊዜያት ይናኝ፥ ይበርክትልን!!💚💛❤️
ቅርርርርር ያሰኘናችሁና ያስከፋናችሁ ብትኖሩ ይቅር በሉን።
መልካም አውዳመት!!
ቀያችን ሰላም ይሁን።💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
Forwarded from Mykey
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
''መልካም የ '' ገና'' በዓል
Mikiyas liyew @Mykey21
------//---------
@Mykeypictures
#Mykeyምስሎች
<ደረት ላይ የተደረሰ የሌት ኪዳን>
|
°
[ትዝታ ኃያል፥
ትዝታ ሕያው ዘኢይመውት]

|
የከርሞን ቅራሪ፥
የካቻምናን እርሾ፥ያቆረ ቡሃቃ
ዛሬ በተጣደ፥
አፍላ ነዲድ አብሲት፥ ሊባረክ ቢበቃ
ለድሮ ዘንድሮ?
ለማን ያጋድላል፥ የእንጀራው ጣዕሙ
'ትናንት' ነው 'ዛሬ'?
'ትኩስ' ነው 'ያደረ'? የምጣድ ላይ ስሙ?
|
°
[ትዝታ ኃያል፥
ትዝታ ሕያው ዘኢይመውት
ዘተጠምቀ በፈልፈለ አንብዕ...]

|
ማወቅ የፈለገ፥ በእንጀራው ዓይን ያያል
እንኪ ተመልከቺ፥
እንደሎጥ ሚስት ሀውልት፥ 'ነበሯ' ይታያል?
ዛሬሽስ ከዛሬ፥ ተርፎ ተትረፍርፎ፥ ለነገ ይቆያል?
ከንፈርሽ ሀዲስ ነው፥ ትዝታዋ ኦሪት
የዛሬ ጠረንሽ፥
ያ'ምና የካቻምና፥ ማዕዛዋ ቅሪት!
|
°
[ትዝታ ኃያል፥
ትዝታ ሕያው ዘኢይመውት
ዘተጠምቀ በፈልፈለ አንብዕ
ወተሰቅለ ዲበ ኅሊና]

|
ጠምጄ ያረስኩት፥
ለምለም አፈርሽ ላይ፥በ'ምነት ዘሬን ዘራሁ
ወዲያው ተንዘፈዘፍሁ...
ሞቀና በረደኝ... በረደና ሞቀኝ...አንዳች ነገር ፈራሁ
ይህ ትዝታ እሚሉት፥
የበድኖች በድን፥ የሬሶች ሬሳ
እርሾ ነው አመሉ፥ ድሮን የማይረሳ
በአፈርሽ በዘሬ፥
የኛን ስንጠብቅ፥
የሷ ለምለም አረም፥ በቅሎ ቢያድርሳ?!
|
°
[ትዝታ ኃያል
ትዝታ ሕያው ዘኢይመውት
ተሣሃለነ እግዚኦ]

@getem
@getem
@lula_al_greeko
''ደ...ስ....''
--------------

ደስ ይለኛል ደ....ስ
የልብሽ ሲደርስ
ጭንቀትሽ ኮብልሎ
ላይመጣብሽ ምሎ
እንባሽን ላያፈስስ
ሲሄድ ላይመለስ
ደስ ይለኛል ደ....ስ

* * ***
ዳኒ.

@getem
@getem
@gebriel_19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የት ነበርሽ? ?!!

ከጦቢያ ሴት መሃል ፤
ፈልጌ ነበረ ፤
ልክ እንደተዋበች ልክ እንደጣይቱ ፤
ተራራ የሚያፈርስ ድብ የሚነቀንቅ ፤
በገሞራ ወኔ፤ በውብ አንደበቱ ።
አጥተን ተስፋ ቆርጠን በተቀመጥንበት፤
ፈልገን ፈልገን ከቆላ እክከ ደጋ ፤
በቀያችን ጠፍቶ ፤
ልክ እንደጣይቱ ፤
ሙልት ባለው ልቡ ፤
ጉም የሚተረትር ፤ ጨለማ ሚያስነጋ ።
ይቅር በቃ ብለን ፥
ደክሞን ተዝለፍልፈን ፤
እጅ ልንሰጥ ሲያምረን ፤
እንደ ማታ እንግዳ ፤
እንደ ብራ ኮከብ ድንገት የተገኘሽ ፤
ሰው አጥተን ስንባጅ ፥
እስከዛሬ ድረስ አንች ልጅ የት ነበርሽ? ??
እውነትም የት ነበርሽ? ???!!!!!


((( ጃኖ ))(💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ ምሽት!!!!💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
#መንቶክራሲ
.
ከትከሻችን ጋር ገጥመው የሚተሙ
ባረፍንበት መንደር አብረው የሚከትሙ፣
እኚህ ጥልፍ መንቶች
የቀናችን ጌቶች፣...
.
ጥጋብና - እርካታ
ፍቅርና - አዘኔታ፣
ተግሳፅና - ስድብ
ልፍያና - ድብድብ፣
መፍዘዝና - መስከን
መታተር -- መባከን፣
.
ፍራቻና - ክብር
ነውርና - ምስጢር፣
እድልና - ስኬት
ታሪክና - ድርሰት፣
ኩራትና - እብሪት
ትእቢት እና ትንቢት፣
.
ደግሞም ብ....ዙ ሌሎች
በጥንድ እየሆኑ
ትውልድ ያመከኑ
.... ...... እኚህን መሰሎች፣ ...
.
ባንድ ዳስ ነግደው
ባንዲት ምንጣፍ ሰግደው
አንድ እየለበሱ
አንድ እየጎረሱ
በጋራ እየሳቁ
በጋራ ሲያለቅሱ፣
ኖሩና .... ኖሩና ....
ከቆይታ ብዛት ገጠመ መልካቸው
እኛ መጤዎቹ በምን እንለያቸው??
------------------//----------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@gebriel_19
/////------/////

እንደ አባቴ ገዳይ ልክ እንደ ሉሲፈር ሁሌ እጠላሻለው፤

ድንገት ስቅ ሲለኝ እያነሳሺኝ መስሎኝ ፎቶሽን አያለው።
ይህው እስከዛሬ..........
ካንቺ ወይም ከኔ አለኝ ልቤ አልፀና፤
መጥላት እና መውደድ ሆነብኝ ፈተና።

[ በለጠ ተክሉ ]


@getem
@getem
@gebriel_19
እጣ ፈንታሽ ሲፃፍ ..!
«ዘውድአለም ታደሠ»


ድንገተኛ ነፋስ ባዘመመሽ ቁጥር
የመውደቂያሽን ቀን በስጋት ስቆጥር
ልክ እንደሰንበሌጥ፥
ነፋሱን ሸኝተሽ ስትቆሚ ዳግም
እኔም ከጭንቀቴ ለቅፅበት ሳገግም
ደግሞ ሌላ ነፋስ፥
ጉልበቱን ሰብስቦ ሊገፋሽ ሲመጣ
ፈተናሽ ጫፍ የለው አቤት ያንቺስ ጣጣ!!
እስቲ ልጠይቅሽ ..
በእርምጃሽ ቁጥር፥
ስትወላከፊ እግርሽ ተደናቅፎ
አበቃላት ሲባል፥
መልአክ ወርዶ ነው የሚያፀናሽ አቅፎ?
እስቲ መልሺልኝ ..
ገፍታሪሽ ብዙ ነው፥
እንደባህር አሳ ቆጥረንም አንዘልቀው
በምን ተአምር ነው፥
ጠላትሽ ጫማ ስር ጉልበትሽ ማይወድቀው?
ቅኔ ነሽ ሐገሬ፥
በሊቅ ማትፈቺ የምስጢር አዝመራ
ሊያጠፋሽ የመጣ፥
ጤዛ ነው ይተንናል ሁሉም በየተራ!
ማጭድሽ ከላይ ነው፥
የተነሳብሽን ይነቅላል እንዳረም
እጣ ፈንታሽ ሲፃፍ፥
መፍረስና መክሰም ላንቺ አልተፈጠረም!
ይኸው ነው!

@getem
@getem
@yeyhudaanbesa
~ ~ ~ ስሞትም ያንቺ ነኝ ~ ~ ~
( ዘላለማዊነት )
.
( # Mintesinot_waqo )
.
በኪዳናችን ዉል
በቃላችን ፅናት ፣
ዘላለማዊነት ፡ ለ'ኛ አንድ ቀን ናት ፡፡
.
ፍቅርሽ በፍሰሐ ፡ ማርኮ ስላስቀረኝ ፣
እንኳን በቁም ቀርቶ ፡ ስሞትም ያንቺ ነኝ ፡፡
.
.
# ተፈጠመ

@getem
@getem
@gebriel_19
»»» ቅኝት_ትዝታዬ ««

ገላሽ ሙዚቃ ነው ሰውነትሽ ኖታ
ሲነካኩት ዘፈን ሲለዩት ትዝታ።

#ezana

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ፍጥነት እና ነፃነት
(በላይ በቀለ ወያ )
.
.
አልጋ ባልጋ ሆኖ…
የጥንቸሎች ፍጥነት፤ ፍጥነት ከተባለ
በኤሊዎች ጫንቃ……..
እራሱን ያልቻለ፤ ግዙፍ ድንጋይ አለ፡፡
ያንን ግዙፍ ድንጋይ …
ከኤሊ ጫንቃ ላይ፤ ላፍታ ቢነሳላት
ከጥንቸሎች ፍጥነት...
አስር እጅ የሚሻል፤ በቂ ፍጥነት አላት፡፡
ያንን ግዙፍ ድንጋይ…
ለዘመናት ቀርቶ፤
ለሰዓታት ያህል፤ ጥንቸል ብትሸከም
መሮጡ ይቅርና ፤
መራመድ አትችልም፤ ነፃ ባልሆነ ዓለም፡፡
ፍትህ በጎደለው፤ ነፃ ባልሆነ ሀገር
ድንጋይ ተሸክሞ ፤
የፈጠነ የለም፤ ከኤሊ በስተቀር!!
ፍትህ በሞላበት፤ ነፃ በሆነ ሀገር
ይቻላል ቀላል ነው፤ ክንፍ አውጥቶ መብረር!!!!!!!!
@getem
@getem
@yeyhudaanbesa
👍2
አፈር ገብቷል አሉኝ...!

፨፨፨

ያ...አንደበተ ርቱዕ የብዕር ዓርበኛ
ቀልብ ይዞ አሳሪ የጥበብ አምደኛ
እውነትን ፍትህን ሲለፍፍ የኖረ
እኩልነትን ሲል ያለ እንቅልፍ ያደረ
የቃላት ባለቤት የሃሳቦች ፈታይ
የሰው ጭንቀት ጭንቁ...
..........አብሯቸው ተብሰልሳይ

አፈር ገብቷል አሉኝ...!

ያ...የምናደንቀው ያጨበጨብንለት
ውስጠትን ነቅናቂ ስሜቶት ያሉበት
ነፃነትን ያለው በግጥም በዜማ
ስሙን ያሳነፀው በማይጠፋ ማማ
የህዝብን እንባና ጭቆናን አንባቢ
በጥበብ መንደር ላይ ሽምጥ ጋላቢ

አፈር ገብቷል አሉኝ...!

ያ...ባለብሩሹ
ከቀለማት ውሕደት ስሜትን ቀማሪ
ከሥዕል ሸራ ላይ እውነታን ዘማሪ
የሰው ልጅን ባህል እምነት እና ስራ
ፈልፍሎ የሚያሳይ ከቀለማት ስፍራ
ውስጣዊውን ምስል ምናባዊውን ሰው
ገልጦና ገላልጦ ስጋን ያላበሰው

አፈር ገብቷል አሉኝ...!

እውነቱን ልንገርህ ወትሮም የጥበብ ሰው
ስለ ውስጠቱ እንጂ ስለ ዓለም ሙት ነው
ስንቱ የወደደው ያጨበጨበለት
የልቤ ነው ብሎ አድንቆ ያለፈለት
የጠላውም ጠልቶት ጥርስ የነከሰበት
ያንድ ሰሞን ወዳጅ ጠላት እየሆነ
አድናቂ ነኝ ብሎም ከክፋት ያልዳነ


ቀድሞም እኮ ሙት ነው! እነሱ ጋር ሞቷል
በምላስ ገድለውት በሆድ ቀብረውታል
የታተመ አሻራ ... የታነፀ ሃውልት
ለሁሉም የሚቀር ቋሚ ፅኑ እሴት
ነገን መመልከቻ አቅራቢ መነጽር
እነሱ ዘንድ አለ ከጠቢባን መንደር


እናማ ...
አፈር ገባ አትበል ያ..ጥበብ ቀማሪ
ገላማ አፈር ነው ... አይደል ቆሞ ቀሪ
የአፈር ዝግኖች ያነፁት ውብ ገላ
ተመልሶ አፈር ነው ትቢያ ነው በኋላ

እሱስ...
ቅሪት አለው አኑሮ ያለፈው
መጽሐፉ ሲገለጥ ሰው የሚያስታውሰው
ሙዚቃው ሲሰማ መንፈስ የሚያድሰው
ይብላኝ እንጂ
ለባለ ሀሜቱ ተረስቶ የቀረ
ኑሮ ያለፈ እንጂ ኑረትን ያልኖረ

፨፨፨

ኪነ ዳን

@getem
@getem
@getem
👍2
👍1
እንስቃለን!!!!

በቅዳሜ ሰማይ፤
በደጋጎቹ ሃገር ፤
በማር ዘነብ ቀዬ፤ በላይኛው ወሎ፤
ፍንሽንሽ ፍልቅልቅ፤
ፍንድቅድቅ ብለናል፤ እንደ ፋፎ ቆሎ።

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️


የሸገነ፤ የተሸባረቀ፤ የተገማሸረ ቅዳሜ ጀባ ብለናል!!!!!!!!!💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
1
እንኳን ደስ አለን!
ከጥር 6/2011 ጀምሮ ፍካት የስነ ልቦና ማማከር አገልግሎት ስራውን በይፋ ይጀምራል፡፡

6271 ላይ ቢደውሉማንነትዎ ሳይታወቅ ፣ባሉብት ቦታ ሆነው በባለሙያዎቻችን የስነ ልቦና ምክር አገልግሎት ማግኘት
ይችላሉ፡፡ለማንም ያልነገሩትንና በሚያስጨንቅዎ ጉዳይ ላይ መፍትሔ እንዲያገኙ እናስችልዎታለን፡፡
የስራ ሰአት ከ ጠዋቱ 3- ምሽቱ 12 ሰአት፡፡
ራእያችን ከስነልቦና ችግር የጸዳ ሁለንተናዊ ስኬት ያለው ትውልድ ማየት ነው፡፡

ይሄን መልእክት share በማድረግ የሚረዳቸው አጥተው ሞታቸውን የሚናፍቁ ወገኖችን ይታደጉ፡፡እናመሰግናለን፡፡