ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
»»» ቅኝት_ትዝታዬ ««

ገላሽ ሙዚቃ ነው ሰውነትሽ ኖታ
ሲነካኩት ዘፈን ሲለዩት ትዝታ።

#ezana

@getem
@paappii
»»» ቅኝት_ትዝታዬ ««

ገላሽ ሙዚቃ ነው ሰውነትሽ ኖታ
ሲነካኩት ዘፈን ሲለዩት ትዝታ።

#ezana

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
======​ለሟቹ ወዳጄ======

ይሄው ትላንትና
ያመንክበት ሚስትህ ባንተም የተመካች
ሙት አመትህ ሳይደርስ ፈጥና ሌላ ተካች።
የመስክህ አበቦች አንተን ባጡ ግዜ ጠውልገው ረገፉ
የልብህ ወዳጆችህ
የሙት ደጃፍህን እያዩት አለፉ።
ግን ዛሬም ታምኖ፣
በናፍቆትህ ታሞ፣ በቁምህ የሞተው
የቀድሞ ፍቅርህን፣ መውደድህን ባይተው
ያ ታማኙ ውሻህ ሰው መልመድ አቃተው።


@getem
@getem
@paappii

#Ezana mesfin
ላገኝሽ ካልሆነ የመንቃቴ ትርፉ
ተኝቼ ሳልምሽ ዘመናት ይለፉ።

@getem
@getem
@paappii

#Ezana
# ከአጥሩ_ባሻገር
:
በአንዱ መቁረሻው ፣
መዓት ዳቦ ቆጥሮ ፣
እልፍም ወዳጅ ፈጥሮ ፣
"ካንቺ ወዲያ..." ይላል
ድብቅ ውሽማውን ፣ በይለፍ ቃል አጥሮ::

#Ezana_Mesfin

@getem
@getem
❀ፍርሃት

የህይወት ዛፍ አድጎ
ተስፋን ካላፈራ
ከመሞትም ይልቅ
መኖር ነው 'ሚያስፈራ።
.
#Ezana_Mesfin
.
@getem
@getem
#ኣንድ_ያልተረዳኸው

በሴት ልጅ እንባዋ
ከሞላው ገምቦዋ
ከዚያ ከምታዝለው ስትል ላንተው ጥማት
ክብሯን ማጉደልህ ነው እህቴን ያመማት

#Ezana_Mesfin

@getem
@getem