ቅዋ!!!!!!
ከቅዋቸው በላይ ፤
ትልቅ ካቦርታ ውስጥ ፤
ውቂያኖስ ጫማ ውስጥ ፤ ወቅት አስገብቷቸው ፣
ባሉበት ቆመዋል ፤
በልክ መራመድ፣ መሄድ ተስኗቸው ።
////////:::::::////////:::::::///////::::::
ጭብጨባ ሲያሰክረው፤
ውቂያኖስ ገብቼ ፤
ባህሩን ሰንጥቄ ፤ እዋኛለሁ ብሎ፤
ያለ ልኩ ለባሽ ፤
ውሃ በልቶት ቀረ ያንን ዘባተሎ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
አረ ጥጋብ አብራጁን ጀባ !!!!
@balmbaras
@getem
@getem
ከቅዋቸው በላይ ፤
ትልቅ ካቦርታ ውስጥ ፤
ውቂያኖስ ጫማ ውስጥ ፤ ወቅት አስገብቷቸው ፣
ባሉበት ቆመዋል ፤
በልክ መራመድ፣ መሄድ ተስኗቸው ።
////////:::::::////////:::::::///////::::::
ጭብጨባ ሲያሰክረው፤
ውቂያኖስ ገብቼ ፤
ባህሩን ሰንጥቄ ፤ እዋኛለሁ ብሎ፤
ያለ ልኩ ለባሽ ፤
ውሃ በልቶት ቀረ ያንን ዘባተሎ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
አረ ጥጋብ አብራጁን ጀባ !!!!
@balmbaras
@getem
@getem
ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ
( በእውቀቱ ስዩም)
የድሜ ነፋስ በገላየ : ተረማምዶ ኮበለለ
ልቤን ክንዴን እያዛለ
ያቀፍኩትን እየቀማ : የያዝኩትን እያስጣለ::
እድል በኔ ጨከነ ስል-በምረት እጅ ደባበሰኝ
አንቺ ነጥቆ ከቅፌ ላይ-በትውስታ ደሞ ካሰኝ::
አሰታወሰኝ
አስታወሰኝ::
ወድያው ታይቶ :ጠፊ ኩርፍያሽ
ገራም ሳቅሽ : ልዝብ ልፍያሽ
ያለም ዘፋኝ የማያውቀው
የግልሽ ዳንስ ውዝዋዜ
ትውስ ትውስ ባለኝ ጊዜ
ከግር ጥፍሬ
እስከ ጠጉሬ
ደስታ ነው የሚያቀልመኝ
ያንቺ ነገር ባሰብሁ ቁጥር :ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ::
በሰጠሽኝ ፀጋ መጠን: የሰራሽኝ ጉድ አያልቅም::
እኔ ባንች ትዝታ እንጂ: በተራቢ ቀልድ አልስቅም::
ማፍቀር ማለት ለካ ፍቺው : መጃጃል ነው አውቆ ፈቅዶ
ከገደል ላይ መወርወር ነው ተጨፍኖ በራስ ፈርዶ::
አፈቀርኩሽ በየቀኑ :ተጃጃልሁኝ ደጋግሜ
ከገደል ላይ ተከስክሼ: ሞተ ሲሉኝ አገግሜ
ያጥንቶቼን ርጋፊ: እንደዛጎል ለቃቅሜ
እንደ ቆሎ : ጥርሴን ቅሜ
ያደረኩሽ ሲደንቀኝ: ያደረግሺኝ ሲገርመኝ
እፍረት ፀፀት አይደለም: ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ !
አውቃለሁኝ ጊዜ ሂዷል :ታሪካችን ተጠቅልሏል::
በሄድንበት ጎዳና ላይ: የመለየት ዝናብ ጥሏል
በርምጃችን ምልክት ላይ: ረጃጅም ሰርዶ በቅሏል
ብቻ ምሾ ቢደረደር: የሆነውን ላይለውጠው
ለንባየማ ፊት አልሰጠው::
ያሳሳምሽ ለዛ ቀርቶ :እንደ እንጎቻ እሚጥመኝ
የነከሽኝ የቧጨርሽኝ: አገርሽቶ ቁስሉ ሲያመኝ
ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ!!
ፍልቅልቅ ቅዳሜ!!!💚💛❤️
@getem
@getem
@getem
( በእውቀቱ ስዩም)
የድሜ ነፋስ በገላየ : ተረማምዶ ኮበለለ
ልቤን ክንዴን እያዛለ
ያቀፍኩትን እየቀማ : የያዝኩትን እያስጣለ::
እድል በኔ ጨከነ ስል-በምረት እጅ ደባበሰኝ
አንቺ ነጥቆ ከቅፌ ላይ-በትውስታ ደሞ ካሰኝ::
አሰታወሰኝ
አስታወሰኝ::
ወድያው ታይቶ :ጠፊ ኩርፍያሽ
ገራም ሳቅሽ : ልዝብ ልፍያሽ
ያለም ዘፋኝ የማያውቀው
የግልሽ ዳንስ ውዝዋዜ
ትውስ ትውስ ባለኝ ጊዜ
ከግር ጥፍሬ
እስከ ጠጉሬ
ደስታ ነው የሚያቀልመኝ
ያንቺ ነገር ባሰብሁ ቁጥር :ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ::
በሰጠሽኝ ፀጋ መጠን: የሰራሽኝ ጉድ አያልቅም::
እኔ ባንች ትዝታ እንጂ: በተራቢ ቀልድ አልስቅም::
ማፍቀር ማለት ለካ ፍቺው : መጃጃል ነው አውቆ ፈቅዶ
ከገደል ላይ መወርወር ነው ተጨፍኖ በራስ ፈርዶ::
አፈቀርኩሽ በየቀኑ :ተጃጃልሁኝ ደጋግሜ
ከገደል ላይ ተከስክሼ: ሞተ ሲሉኝ አገግሜ
ያጥንቶቼን ርጋፊ: እንደዛጎል ለቃቅሜ
እንደ ቆሎ : ጥርሴን ቅሜ
ያደረኩሽ ሲደንቀኝ: ያደረግሺኝ ሲገርመኝ
እፍረት ፀፀት አይደለም: ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ !
አውቃለሁኝ ጊዜ ሂዷል :ታሪካችን ተጠቅልሏል::
በሄድንበት ጎዳና ላይ: የመለየት ዝናብ ጥሏል
በርምጃችን ምልክት ላይ: ረጃጅም ሰርዶ በቅሏል
ብቻ ምሾ ቢደረደር: የሆነውን ላይለውጠው
ለንባየማ ፊት አልሰጠው::
ያሳሳምሽ ለዛ ቀርቶ :እንደ እንጎቻ እሚጥመኝ
የነከሽኝ የቧጨርሽኝ: አገርሽቶ ቁስሉ ሲያመኝ
ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ!!
ፍልቅልቅ ቅዳሜ!!!💚💛❤️
@getem
@getem
@getem
ቅዳሜና ደሴ!!!!!
በአረብ ገንዳ ሪጋ፤ በላይኛው ጦሳ፤
ደሴ ሸሞንሟኒት፤ ደሴ ደንገላሳ፤
ቅዳሜና ደሴ፤ ሸጋና ሳቢሳ፤
ይች የዳውዶ ልጅ፤
ዛሬም ሰበር ሰካ፤ አደረጋትሳ፤
ከርቤና ሉባንጃ፤ እጣን አጫጭሳ፤
አህሪቡ ትላለች፤ ፍቅር ራት ምሳ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ሽብርቅርቅ ቅዳሜ!!💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
በአረብ ገንዳ ሪጋ፤ በላይኛው ጦሳ፤
ደሴ ሸሞንሟኒት፤ ደሴ ደንገላሳ፤
ቅዳሜና ደሴ፤ ሸጋና ሳቢሳ፤
ይች የዳውዶ ልጅ፤
ዛሬም ሰበር ሰካ፤ አደረጋትሳ፤
ከርቤና ሉባንጃ፤ እጣን አጫጭሳ፤
አህሪቡ ትላለች፤ ፍቅር ራት ምሳ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ሽብርቅርቅ ቅዳሜ!!💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
ዝንጋዔ(ልዑል ሀይሌ)
ራሴን ያመኛል
እግሬንም ያመኛል
ምኔንም ያመኛል
ይላል ደፋር ፍጡር እንደኔ ያለ ሰው፤
ነገሩን ዘንግቶ
ራስም እግርም 'ምን' ም
ከፈጣሪ ፍቃድ ባምሳል የተዋሰው።
.
ስለዚህ ፈጣሪ.,
አምሳልህ ነውና..
እጅህን ማርልኝ፣
እግርህን ማርልኝ፣
ሁሉንም አካልህን ማርልኝ ማርልኝ፤
የኔ ምለው የለም፣
አልመፃደቅም አንተ እስክትደርስልኝ።
15-12-2010
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ራሴን ያመኛል
እግሬንም ያመኛል
ምኔንም ያመኛል
ይላል ደፋር ፍጡር እንደኔ ያለ ሰው፤
ነገሩን ዘንግቶ
ራስም እግርም 'ምን' ም
ከፈጣሪ ፍቃድ ባምሳል የተዋሰው።
.
ስለዚህ ፈጣሪ.,
አምሳልህ ነውና..
እጅህን ማርልኝ፣
እግርህን ማርልኝ፣
ሁሉንም አካልህን ማርልኝ ማርልኝ፤
የኔ ምለው የለም፣
አልመፃደቅም አንተ እስክትደርስልኝ።
15-12-2010
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ሸረኛ ከይረኛ ባልንጀር ሆኑና ፤
ሜዳውን በሙሉ አብረው ዘለቁና ፤
ከገደሉ ደርሰው ከዚያ ከፈፋው ፥
ሸረኛ ከይረኛን ገደል ላይ ገፋው፥
እንደው ሆኖ ሆኖ ፤
የሸረኛን ገደል ማነው የሚያልፈው???
((Traditional WOLLO menzumma lyric))💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
ሜዳውን በሙሉ አብረው ዘለቁና ፤
ከገደሉ ደርሰው ከዚያ ከፈፋው ፥
ሸረኛ ከይረኛን ገደል ላይ ገፋው፥
እንደው ሆኖ ሆኖ ፤
የሸረኛን ገደል ማነው የሚያልፈው???
((Traditional WOLLO menzumma lyric))💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
የበጎቹ ፎቶ
..
ልክ የዛሬ ሳምንት !
በደረቀች ወንዝ ~ ፈጣሪ በረሳት
ሰባት ወይም ስምንት
በጎች ተሰብስበው ~ ፎቶ ለመነሳት
የማለዳ ፀሀይ ~ ጨለማውን ገፋ ~ ብርሀን ስትዘራ
ጨረሯን እየሞኩ ~ ሲነሱ አይ ነበር ~ በአሮጌ ካሜራ
.
ኣንዱ በግ ተጋድሞ
ጥያ መስለው ቁመው ~ ሌሎቹ ከጀርባ
አንዷ በግ ስትስመው
ጆሮው የቆመውን ~ አንገቱ ስር ቀርባ
እየተሳሳቁ
እየፈነደቁ ~ጊዜ ሲያሳልፉ
አለት ተደግፈው
በደስታ ማእበል ~ ገብተው ሲንሳፈፉ
ከመንጋቸው መሀል
አንዱ ተገንጥሎ ~ አንገቱን በመድፋት
ተክዞ አየሁት
ባቀረዘዙ አይኖች ~ የሳቁን ቀን ሲያልፋት ።
~
እመረምር ጀምርሁ
ስለምን ይሄ በግ ~ ተለይቶ አልሳቀም ?
ለምን ሲባል ፊቱ
ካሜራ ፊት ቀርቦ ~ ከሀዘን አልራቀም ?
የራሴን መላምት ~ ጀመርኩ መደርደር
.
.
አንድም … ከበግ መንደር
ሾልኮ የሚገባ ~ የጠላት ሸረኛ
ሲደክም ዋይ አባት
እርሙን ቢያንቀላፋ ~ ሳት ብሎት ቢተኛ
ሚስትና ልጆቹን
በልቶበት ይሆናል ~ እንዲህ የተከዘው
ይህንን እያሰብኩ
አንዳች ሀዘን ልቤን ~ እየመዘመዘው
ቀጭን የህመም ጉም
ነፍሴን እየወጋ ~ በሹል ሲያሰቃያት
ልስልስ ያለ ልቤ
እየቆረፈደ ~ ሲያወጣ ማድያት
የእንባዬ ጠብታ
በጉንጮቼ ወርዶ ~ ቢሞት ከንፈሬ ላይ
በጸሃይ የፈካው~ ፍንትው ያለ ሰማይ
እየደብዘዘ ምሽት ተቃረበ
ድንገት ከአይምሮዬ
እንደ እባብ የሚሳብ
ሌላ አስፈሪ ሃሳብ~ ዶፍ ሁኖ ዘነበ
….
ምናልባትስ ደግሞ
ይሄ የማዝንለት ~ ማየው አጎንብሶ
እንባ የሚያወርደው ~ግንባሩን ከስክሶ
ተኩላ ቢሆንሳ
ሊነጥቅ የመጣ ~የበግ ለምድ ለብሶ ?
.
.
የበጎች ፎቶ አንሺ
ፎቶ ሲያነሳቸው ~ ፈገግ በሉ እያለ
ቦታ እና አቀማመጥ~ እያቀያየረ
ምስኪን ነው ያልኩት በግ
ሀዘንና እንባ ~ የሚተናነቀው
የሾሉት ጥሮቹን
ሊደብቅ ቢሆንስ~ ተሳስቶ 'ማይስቀው ?
…
ምክንያቱም ያ ተኩላ
በግን ተመስሎ
ታዳኞቹ መሀል ~እንዳሻው ያደባል
በጎች ሲስቁ ግን
የሾሉ ጥርሶቹን ~ ሊደብቅ ይገባል !!
…..
ይህንን እንዳሰብኩ
የምሽቱ ንፋስ ~እያንዘፈዘፈኝ
በባዶ እግሬ እየሮጥኩ
ለሌሎች የመጣው~ ለእኔም እንዳይተርፈኝ
ወደቤቴ ገባሁ
አንድም እየፈራሁ
አንድም እያነባሁ.
.
.
ምናልባት ያነ በግ
ምስኪን አባት ነበር ~ አልያም ደግሞ ተኩላ
እነዚያን በጎች ግን
አይቻቸው አላውቅም ~ ከዚያች ቀን በኋላ
.
( ናትናኤል ጌቱ )
@getem
@getem
@gebriel_19
..
ልክ የዛሬ ሳምንት !
በደረቀች ወንዝ ~ ፈጣሪ በረሳት
ሰባት ወይም ስምንት
በጎች ተሰብስበው ~ ፎቶ ለመነሳት
የማለዳ ፀሀይ ~ ጨለማውን ገፋ ~ ብርሀን ስትዘራ
ጨረሯን እየሞኩ ~ ሲነሱ አይ ነበር ~ በአሮጌ ካሜራ
.
ኣንዱ በግ ተጋድሞ
ጥያ መስለው ቁመው ~ ሌሎቹ ከጀርባ
አንዷ በግ ስትስመው
ጆሮው የቆመውን ~ አንገቱ ስር ቀርባ
እየተሳሳቁ
እየፈነደቁ ~ጊዜ ሲያሳልፉ
አለት ተደግፈው
በደስታ ማእበል ~ ገብተው ሲንሳፈፉ
ከመንጋቸው መሀል
አንዱ ተገንጥሎ ~ አንገቱን በመድፋት
ተክዞ አየሁት
ባቀረዘዙ አይኖች ~ የሳቁን ቀን ሲያልፋት ።
~
እመረምር ጀምርሁ
ስለምን ይሄ በግ ~ ተለይቶ አልሳቀም ?
ለምን ሲባል ፊቱ
ካሜራ ፊት ቀርቦ ~ ከሀዘን አልራቀም ?
የራሴን መላምት ~ ጀመርኩ መደርደር
.
.
አንድም … ከበግ መንደር
ሾልኮ የሚገባ ~ የጠላት ሸረኛ
ሲደክም ዋይ አባት
እርሙን ቢያንቀላፋ ~ ሳት ብሎት ቢተኛ
ሚስትና ልጆቹን
በልቶበት ይሆናል ~ እንዲህ የተከዘው
ይህንን እያሰብኩ
አንዳች ሀዘን ልቤን ~ እየመዘመዘው
ቀጭን የህመም ጉም
ነፍሴን እየወጋ ~ በሹል ሲያሰቃያት
ልስልስ ያለ ልቤ
እየቆረፈደ ~ ሲያወጣ ማድያት
የእንባዬ ጠብታ
በጉንጮቼ ወርዶ ~ ቢሞት ከንፈሬ ላይ
በጸሃይ የፈካው~ ፍንትው ያለ ሰማይ
እየደብዘዘ ምሽት ተቃረበ
ድንገት ከአይምሮዬ
እንደ እባብ የሚሳብ
ሌላ አስፈሪ ሃሳብ~ ዶፍ ሁኖ ዘነበ
….
ምናልባትስ ደግሞ
ይሄ የማዝንለት ~ ማየው አጎንብሶ
እንባ የሚያወርደው ~ግንባሩን ከስክሶ
ተኩላ ቢሆንሳ
ሊነጥቅ የመጣ ~የበግ ለምድ ለብሶ ?
.
.
የበጎች ፎቶ አንሺ
ፎቶ ሲያነሳቸው ~ ፈገግ በሉ እያለ
ቦታ እና አቀማመጥ~ እያቀያየረ
ምስኪን ነው ያልኩት በግ
ሀዘንና እንባ ~ የሚተናነቀው
የሾሉት ጥሮቹን
ሊደብቅ ቢሆንስ~ ተሳስቶ 'ማይስቀው ?
…
ምክንያቱም ያ ተኩላ
በግን ተመስሎ
ታዳኞቹ መሀል ~እንዳሻው ያደባል
በጎች ሲስቁ ግን
የሾሉ ጥርሶቹን ~ ሊደብቅ ይገባል !!
…..
ይህንን እንዳሰብኩ
የምሽቱ ንፋስ ~እያንዘፈዘፈኝ
በባዶ እግሬ እየሮጥኩ
ለሌሎች የመጣው~ ለእኔም እንዳይተርፈኝ
ወደቤቴ ገባሁ
አንድም እየፈራሁ
አንድም እያነባሁ.
.
.
ምናልባት ያነ በግ
ምስኪን አባት ነበር ~ አልያም ደግሞ ተኩላ
እነዚያን በጎች ግን
አይቻቸው አላውቅም ~ ከዚያች ቀን በኋላ
.
( ናትናኤል ጌቱ )
@getem
@getem
@gebriel_19
ናቲዮስ
ጭላንጭል ተስፋ
ከአድማስ ይሻገራል ከሰማይ ሰማያት
ፋና እና ወገግታ የብርሃን ፍጥነት
ታፍኖ ያልተያዘ ከእልፍኙ የዘለቀ
ፍላጎት ድሪቶን በውስጡ ያጨቀ
ፍንጣሪ ስሜት አውቆ የደበቀ
በጊዜ ፈረስ ላይ ዘመን ተሻጋሪ
ተቃራኒ ሀሳብ ሁሌ አደናጋሪ
ከበድን አስክሬን እንደመነጋገር
ያልተፈጨ እህል ወጥቶ እንደመጋገር
ሲመዘዝ ለበጣ ከፍ ሲልም ስላቅ
ጭላንጭሉ ተስፋ ሀሳቡ ረቂቅ
ጉም ነው ጠፊ ብናኝ
ደራሲ ብዙ ነው ትንሽ ነው አቀንቃኝ
በጎምጂ ማንነት ፍላጎት ሲራመድ
ረመጥ ተዳፍኖ እንዳልበረደ አመድ
ከላቀ ሀሳብ ጋር ሞጋች ነብስ ማትጠፋ
አሻግራ ጠባቂ በጭላንጭል ተስፋ
ርካሽ ሀሳብን ወደ ዳር ምትገፋ
ለመቆም ተገዳ ካሊሟን ተነጥቃ
በቁርና በውርጭ አካሏን ሰንጥቃ
ተራማጅ አካሏን በመዳፏ አዙራ
ቀድሟት የሄደውን ቆማ ምትጣራ
ተልካሻ ማንነት የነተበ ስጋ
ለመታረቅ ስትል ከራሷ አፈግፍጋ
ለነብሷ ያልቆመች በአንድ አቅጣጫ ገፊ
ምታስፈነድቃት ቅንጣት ዝንጣፊ
ናዋዥ ሌትና ቀን ሩቅ አሻጋሪ
ጭላንጭሉም ተስፋ ሳይዳፈን ብሪ
@getem
@getem
@gebriel_19
ጭላንጭል ተስፋ
ከአድማስ ይሻገራል ከሰማይ ሰማያት
ፋና እና ወገግታ የብርሃን ፍጥነት
ታፍኖ ያልተያዘ ከእልፍኙ የዘለቀ
ፍላጎት ድሪቶን በውስጡ ያጨቀ
ፍንጣሪ ስሜት አውቆ የደበቀ
በጊዜ ፈረስ ላይ ዘመን ተሻጋሪ
ተቃራኒ ሀሳብ ሁሌ አደናጋሪ
ከበድን አስክሬን እንደመነጋገር
ያልተፈጨ እህል ወጥቶ እንደመጋገር
ሲመዘዝ ለበጣ ከፍ ሲልም ስላቅ
ጭላንጭሉ ተስፋ ሀሳቡ ረቂቅ
ጉም ነው ጠፊ ብናኝ
ደራሲ ብዙ ነው ትንሽ ነው አቀንቃኝ
በጎምጂ ማንነት ፍላጎት ሲራመድ
ረመጥ ተዳፍኖ እንዳልበረደ አመድ
ከላቀ ሀሳብ ጋር ሞጋች ነብስ ማትጠፋ
አሻግራ ጠባቂ በጭላንጭል ተስፋ
ርካሽ ሀሳብን ወደ ዳር ምትገፋ
ለመቆም ተገዳ ካሊሟን ተነጥቃ
በቁርና በውርጭ አካሏን ሰንጥቃ
ተራማጅ አካሏን በመዳፏ አዙራ
ቀድሟት የሄደውን ቆማ ምትጣራ
ተልካሻ ማንነት የነተበ ስጋ
ለመታረቅ ስትል ከራሷ አፈግፍጋ
ለነብሷ ያልቆመች በአንድ አቅጣጫ ገፊ
ምታስፈነድቃት ቅንጣት ዝንጣፊ
ናዋዥ ሌትና ቀን ሩቅ አሻጋሪ
ጭላንጭሉም ተስፋ ሳይዳፈን ብሪ
@getem
@getem
@gebriel_19
ጨረቃ ጨረቃ ጨረቃ ጨረቃ ጨረቃ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ምነው ክብሽ ሰፋ ፀሀይ መሆን ዳዳሽ
ልክ እንደ አገሬ ልጅ በጊዜ ፈነዳሽ
. ሃ.ሃ.
አይጠቅምሽም ተዪው ሳይመሽልሽ ውበት
....መደበቅ ነው ሀቁ ብዙ ለመሰንበት....
@ሰሙ
12/04/2+0+0+1+1
ተጻፈ በ.Holly Caffe
#Dire
@semuuuuuu
@getem
@getem
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ምነው ክብሽ ሰፋ ፀሀይ መሆን ዳዳሽ
ልክ እንደ አገሬ ልጅ በጊዜ ፈነዳሽ
. ሃ.ሃ.
አይጠቅምሽም ተዪው ሳይመሽልሽ ውበት
....መደበቅ ነው ሀቁ ብዙ ለመሰንበት....
@ሰሙ
12/04/2+0+0+1+1
ተጻፈ በ.Holly Caffe
#Dire
@semuuuuuu
@getem
@getem
የምንሰፋው ጠፋ!!!!
ሁሉም በየቤቱ፤
እጁ እንደመራለት፤
ልቡ እንደፈቀደው፤
ቅዳጁን ሽንቁሩን፤
በድሪቶ ትብታብ፤
በቁጢት በወስፌ፤
እያጨማደደ፤
ይህ ቀዳዳ ሁላ፤
ቅድ አገኘሁ ብሎ፤
ስፍ በማያውቅ እጁ፤
እየተበተበ እየደራረተ፤ አጥብቦ እየሰፋ፤
"ሽንቁር "በበዛበት፤
"ቅዳጅ" በሞላበት፤
እኛ ሰፊዎቹ ፤የምንሰፋው ጠፋ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
በሰፋ ሀገር ጠበን ኢትዮጵያን አንሰጥመም !! አይደል ያለችው ( ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ )
@balmbaras
@getem
@getem
ሁሉም በየቤቱ፤
እጁ እንደመራለት፤
ልቡ እንደፈቀደው፤
ቅዳጁን ሽንቁሩን፤
በድሪቶ ትብታብ፤
በቁጢት በወስፌ፤
እያጨማደደ፤
ይህ ቀዳዳ ሁላ፤
ቅድ አገኘሁ ብሎ፤
ስፍ በማያውቅ እጁ፤
እየተበተበ እየደራረተ፤ አጥብቦ እየሰፋ፤
"ሽንቁር "በበዛበት፤
"ቅዳጅ" በሞላበት፤
እኛ ሰፊዎቹ ፤የምንሰፋው ጠፋ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
በሰፋ ሀገር ጠበን ኢትዮጵያን አንሰጥመም !! አይደል ያለችው ( ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ )
@balmbaras
@getem
@getem
እንድቅትዩን የስነፅሁፍ ምሽት
ምርጥ ምርጥ የጥበብ ሰዎች ስራቸውን ያቀርባሉ
በዋቢ ሸበሌ ሆቴል
መግብያ 50 ብር
ሐሙስ ታህሳስ 18/2011 አ.ም
በ 11:30
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ምርጥ ምርጥ የጥበብ ሰዎች ስራቸውን ያቀርባሉ
በዋቢ ሸበሌ ሆቴል
መግብያ 50 ብር
ሐሙስ ታህሳስ 18/2011 አ.ም
በ 11:30
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ይህን ያገር አድባር ፤
በግርማ ሞገስ ላይ ፣ ሙሃባ አጀበው ፤
ይመርብህ ብሎ ፤
ከእናቱ ማህጸን ገና ሲሰራው ፤
እንኳን ከግንባሩ፤ ያምራል ከጀርባው ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
በግርማ ሞገስ ላይ ፣ ሙሃባ አጀበው ፤
ይመርብህ ብሎ ፤
ከእናቱ ማህጸን ገና ሲሰራው ፤
እንኳን ከግንባሩ፤ ያምራል ከጀርባው ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
❤1
ለመለስ የተፃፈ ደብዳቤ
****************
.
እንደምን ነህ ጋሼ ፣እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ፣ ቀረህ ሳትመለስ?!
.
እኛማ ይሔውልህ
ባንተ ሌጋሲና ባንተ ትልቅ ራዕይ
በየአደባባዩ ስንል ነበር ዋይ ዋይ
አዎ ትዝ ይለናል
ጀነራልህ ሁሉ ፣ ተኩስ ነው ትእዛዙ
ወገን ይጥል ነበር ፣ የግፍ አፈሙዙ
ለምንድን ነው ስንል? ስምክን አስቀድመው
ከክርስቶስ በላይ ፣ምስልህን አትመው
ቅዱስ መፅሐፍ ይመስል
ባንተ ራዕይና በሌጋሲህ ምለው
ቢረፈርፉንም አላለቅንምና
ደብዳቤ ላክንልህ ከሞት የተረፍነው!
~
የሆነስ ሆነና ግን አንተ ደህና ነህ
እኛማ ይኸውልህ
ደርሰህ ስትናፍቀን
አይሞትም የምትል ሙዚቃ ሞዝቀን
መቃብርህን ልንስም ፣አበባ ልናኖር ፣ስላሴ ብንመጣ
ፌደራል ያይሃል ፣ እስረኛ ይመስል ፣ ሾልከህ እንዳትወጣ
መቼም ስላሴ ውስጥ...
ባለስም ነውና ፣ የሚቀበርበት
አንተን አየት አርገን ፣ ዞር ስንል ድንገት
እነፊታውራሪ
ግራ'ዝማች
ቀኝ'ዝማች
ፊተኛ ባለስም ፣ የሆኑት አባቶች
ያለዘብ ቆመዋል ፣ እነ አብዲሳአጋ
ጀግና መሃል ሳለህ ፣ ምነው በድንህ ሰጋ?!
~
የሆነስ ሆነና
ሃየሎም ደህና ነው
እዛም ትግል ይመራል?
እስር ቤት ሰባብሮ ፣ታራሚ ያስፈታል
እዛም ከፊት ሆኖ ፣ ጭቁን ያታግላል
እዛም በጀግንነት ፣ በለኮሳት ሻማ
ነፃ ነኝ ባለባት ፣ ርዕሰ ከተማ
ትንሽ ግሮሰሪ ፣ ይገባ ይሆን ደፍሮ?
እዛስ ጀማል ያሲን ፣ ፈጠረ አምባጓሮ?
ሃየሎምን ሰዋው ፣ በሐሺሽ ናላው ዞሮ?
።።
እኛማ ይኸውልህ
ብዙ ሃየሎሞች ፣ ፈጥረን ስናበቃ
እልፍ ጀማል ያሲን ፣ ይሆናል ጥበቃ
ይኸው ባደባባይ
የጀግኖቻችን ደም ፣ በየቦታው ፈሶ
አለ ጀማል ያሲን ፣ ሞት ሚበይንበት ፣ ፍርድ ቤቱ ፈርሶ!!
~
ግን አንተ ደህና ነህ
አቡነ ጳውሎስስ ፣ብፁው እንዴት ናቸው
እዚያም እንደምድሩ
አንድ አንቀፅ ያክላል ፣ መጠሪያ ስማቸው?
ደረታቸው ግድም "ሽጉጥ" የሚያደርጉት ፣ አለ መስቀላቸው?
።።።
እኛማ ይኸውልህ
ጳጳሳት አስታርቀን ፣ ሾመን በአደባባይ
ቃላቸውን እንጂ ፣ ዘራቸውን ሳናይ
አለን በአንድ ላይ።
የሆነው ሆነና...
አቡነ ጳውሎስ ፣ ጳጳሱ እንዴት ናቸው
ደረታቸው ግድም ሽጉጥ የሚያደርጉት አለ መሥቀላቸው?
እዛም ትውልድ ሲያልቅ
ወገን ደሙ ሲፈስ
እምነትሲተራመስ ፣ አያውቁም ግሳጤ?
እዛም ታጋይ ናቸው?
ቆባቸው የጳጳስ ነብሳቸው የአጤ?
~
እንደምን ነህ ጋሼ እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ቀረህ ሳትመለስ
~
~
~
ከቻልክ ፃፍልን ለደብዳቤያችን መልስ!!
።።።።
።።።
.( ፍቃዱ ጌታቸው የፃፍትን በላይ በቀለ ወያ ትንሽ እንዲ ጠምዘዝ አርጓታል)
@getem
@getem
@lula_al_greeko
****************
.
እንደምን ነህ ጋሼ ፣እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ፣ ቀረህ ሳትመለስ?!
.
እኛማ ይሔውልህ
ባንተ ሌጋሲና ባንተ ትልቅ ራዕይ
በየአደባባዩ ስንል ነበር ዋይ ዋይ
አዎ ትዝ ይለናል
ጀነራልህ ሁሉ ፣ ተኩስ ነው ትእዛዙ
ወገን ይጥል ነበር ፣ የግፍ አፈሙዙ
ለምንድን ነው ስንል? ስምክን አስቀድመው
ከክርስቶስ በላይ ፣ምስልህን አትመው
ቅዱስ መፅሐፍ ይመስል
ባንተ ራዕይና በሌጋሲህ ምለው
ቢረፈርፉንም አላለቅንምና
ደብዳቤ ላክንልህ ከሞት የተረፍነው!
~
የሆነስ ሆነና ግን አንተ ደህና ነህ
እኛማ ይኸውልህ
ደርሰህ ስትናፍቀን
አይሞትም የምትል ሙዚቃ ሞዝቀን
መቃብርህን ልንስም ፣አበባ ልናኖር ፣ስላሴ ብንመጣ
ፌደራል ያይሃል ፣ እስረኛ ይመስል ፣ ሾልከህ እንዳትወጣ
መቼም ስላሴ ውስጥ...
ባለስም ነውና ፣ የሚቀበርበት
አንተን አየት አርገን ፣ ዞር ስንል ድንገት
እነፊታውራሪ
ግራ'ዝማች
ቀኝ'ዝማች
ፊተኛ ባለስም ፣ የሆኑት አባቶች
ያለዘብ ቆመዋል ፣ እነ አብዲሳአጋ
ጀግና መሃል ሳለህ ፣ ምነው በድንህ ሰጋ?!
~
የሆነስ ሆነና
ሃየሎም ደህና ነው
እዛም ትግል ይመራል?
እስር ቤት ሰባብሮ ፣ታራሚ ያስፈታል
እዛም ከፊት ሆኖ ፣ ጭቁን ያታግላል
እዛም በጀግንነት ፣ በለኮሳት ሻማ
ነፃ ነኝ ባለባት ፣ ርዕሰ ከተማ
ትንሽ ግሮሰሪ ፣ ይገባ ይሆን ደፍሮ?
እዛስ ጀማል ያሲን ፣ ፈጠረ አምባጓሮ?
ሃየሎምን ሰዋው ፣ በሐሺሽ ናላው ዞሮ?
።።
እኛማ ይኸውልህ
ብዙ ሃየሎሞች ፣ ፈጥረን ስናበቃ
እልፍ ጀማል ያሲን ፣ ይሆናል ጥበቃ
ይኸው ባደባባይ
የጀግኖቻችን ደም ፣ በየቦታው ፈሶ
አለ ጀማል ያሲን ፣ ሞት ሚበይንበት ፣ ፍርድ ቤቱ ፈርሶ!!
~
ግን አንተ ደህና ነህ
አቡነ ጳውሎስስ ፣ብፁው እንዴት ናቸው
እዚያም እንደምድሩ
አንድ አንቀፅ ያክላል ፣ መጠሪያ ስማቸው?
ደረታቸው ግድም "ሽጉጥ" የሚያደርጉት ፣ አለ መስቀላቸው?
።።።
እኛማ ይኸውልህ
ጳጳሳት አስታርቀን ፣ ሾመን በአደባባይ
ቃላቸውን እንጂ ፣ ዘራቸውን ሳናይ
አለን በአንድ ላይ።
የሆነው ሆነና...
አቡነ ጳውሎስ ፣ ጳጳሱ እንዴት ናቸው
ደረታቸው ግድም ሽጉጥ የሚያደርጉት አለ መሥቀላቸው?
እዛም ትውልድ ሲያልቅ
ወገን ደሙ ሲፈስ
እምነትሲተራመስ ፣ አያውቁም ግሳጤ?
እዛም ታጋይ ናቸው?
ቆባቸው የጳጳስ ነብሳቸው የአጤ?
~
እንደምን ነህ ጋሼ እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ቀረህ ሳትመለስ
~
~
~
ከቻልክ ፃፍልን ለደብዳቤያችን መልስ!!
።።።።
።።።
.( ፍቃዱ ጌታቸው የፃፍትን በላይ በቀለ ወያ ትንሽ እንዲ ጠምዘዝ አርጓታል)
@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍2
ስድ ፎቶዎችሽ
ከፌስብክ መስኮት ላይ
ተለጠፉ አሉ
ያዪት ወንዶች ሁሉ
በምናብ ሊዳሩሽ
ፎቶሽን ባውራ ጣት
like ያረጋሉ።
.ተፈጥሮን አድናቂ
ሁሉም ይመስላሉ
.
. እኔ ግን ገልጣለው
የ post አልበምሽን
ተመስጬ አያለው
ገልጣለው ገልጣለው
ደሞ ባንንና
ምን ነካት እላለው
.
.
ዝሞ በል! ፋራ እያለ
ሲጋጨኝ ስሜቴ
ደሞ ያባንነኛል
ከጨዋ እኔነቴ።
.
ደግሜ ገልጣለው
ባለጌ ፎቶሽን
ጡትሽን ጠግቤ
ስፈልግ ጭንሽን።
ጡትሽም ሲጣራ
ጭንሽም ሲጣራ
ቂ' 'ም ሲጣራ
ዳሌሽም ሲጣራ
የት አባቱ ይሂድ
ቦቅቧቃ ወንድነቴ
ተጨነቀ ፈራ!
አዬ ካሜራ man
ወይ selfie እራቁት
ከእርቃን አልበም ውስጥ
ለካ እንዲ ከባድ ነው
ሰው ፈልጎ ማግኘት
ለካ እንዲህ ከባድ ነው
ራስ ፈልጎ ማግኘት
.
አምላከኛ ጭቃ
በፎቶ እያማረ
ሴቱ ጨርቁን ጣለ
ወንዱ ደጅ አደረ
.
.
ወይ ሶሻል ሚድያ
አዬ ቴክኖሎጂ
ቀን ሰርቶ የደከመው
ይረፍበት እንጂ
.
.
ሀበሻ ስለጡኑ
ፈረንጅ የቀደመ
ቁጭ ብሎ ያነጋል
ገላ እየተመኘ
እርቃን እየሳመ።
ሀበሺት ዘመናይ
ካለም የዘመነች
ለነፃ ገበያ
ገላ ታቀርባለች
በselfie ካሜራ
ፎቶ ትነሳለች።
comment ክፈሏት
like ክፈሏት
የፌስቡክ ዋጋዋን
የተተመነላት።
.
.
.
እንቺም ምርት አቅርቢ
ሰልፊውን ቀጭ አርጊው
በ like ሚተመን
በ comment ሚተመን
facebook ገበያ ነው።
ዮናታን ሻረው 20/03/11
@getem
@getem
@gebriel_19
ከፌስብክ መስኮት ላይ
ተለጠፉ አሉ
ያዪት ወንዶች ሁሉ
በምናብ ሊዳሩሽ
ፎቶሽን ባውራ ጣት
like ያረጋሉ።
.ተፈጥሮን አድናቂ
ሁሉም ይመስላሉ
.
. እኔ ግን ገልጣለው
የ post አልበምሽን
ተመስጬ አያለው
ገልጣለው ገልጣለው
ደሞ ባንንና
ምን ነካት እላለው
.
.
ዝሞ በል! ፋራ እያለ
ሲጋጨኝ ስሜቴ
ደሞ ያባንነኛል
ከጨዋ እኔነቴ።
.
ደግሜ ገልጣለው
ባለጌ ፎቶሽን
ጡትሽን ጠግቤ
ስፈልግ ጭንሽን።
ጡትሽም ሲጣራ
ጭንሽም ሲጣራ
ቂ' 'ም ሲጣራ
ዳሌሽም ሲጣራ
የት አባቱ ይሂድ
ቦቅቧቃ ወንድነቴ
ተጨነቀ ፈራ!
አዬ ካሜራ man
ወይ selfie እራቁት
ከእርቃን አልበም ውስጥ
ለካ እንዲ ከባድ ነው
ሰው ፈልጎ ማግኘት
ለካ እንዲህ ከባድ ነው
ራስ ፈልጎ ማግኘት
.
አምላከኛ ጭቃ
በፎቶ እያማረ
ሴቱ ጨርቁን ጣለ
ወንዱ ደጅ አደረ
.
.
ወይ ሶሻል ሚድያ
አዬ ቴክኖሎጂ
ቀን ሰርቶ የደከመው
ይረፍበት እንጂ
.
.
ሀበሻ ስለጡኑ
ፈረንጅ የቀደመ
ቁጭ ብሎ ያነጋል
ገላ እየተመኘ
እርቃን እየሳመ።
ሀበሺት ዘመናይ
ካለም የዘመነች
ለነፃ ገበያ
ገላ ታቀርባለች
በselfie ካሜራ
ፎቶ ትነሳለች።
comment ክፈሏት
like ክፈሏት
የፌስቡክ ዋጋዋን
የተተመነላት።
.
.
.
እንቺም ምርት አቅርቢ
ሰልፊውን ቀጭ አርጊው
በ like ሚተመን
በ comment ሚተመን
facebook ገበያ ነው።
ዮናታን ሻረው 20/03/11
@getem
@getem
@gebriel_19
እንድቅትዩን የስነፅሁፍ ምሽት
ምርጥ ምርጥ የጥበብ ሰዎች ስራቸውን ያቀርባሉ
በዋቢ ሸበሌ ሆቴል
መግብያ 50 ብር
ሐሙስ ታህሳስ 18/2011 አ.ም
በ 11:30
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ምርጥ ምርጥ የጥበብ ሰዎች ስራቸውን ያቀርባሉ
በዋቢ ሸበሌ ሆቴል
መግብያ 50 ብር
ሐሙስ ታህሳስ 18/2011 አ.ም
በ 11:30
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ሰላማዊ ትግል
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ጠብመንጃና ክላሽ ፣ ሳልታጠቅ መውዜር
የኢትዮጵያ ጠላት
አሳልፌ ሰጠሁ ፣ ለአላህ እና ለ'ግዜር ።
።።
አንተም ልክ እንደኔ ፣ ከምትጨልም በቀን
አሸናፊ ሰው ሁን!
ዘር ዘር በሚሉ ፊት ፣ ሰውን በማቀንቀን
እንዲያ ያረክ ቀን...
.
ጠላትህ ምን ቢገዝፍ ፣ ምን ጦር ቢደረድር
ከጠጠር አያልፍ!
"እርዳኝ" ያልከው አምላክ ፣ ወንጭፍህ ላይ ሲያድር ።
...... ...................................
እንዲያ ነው ስልጡን ህዝብ
ሳይታገል ጥሎ ፣ ሳይፎክር ሚረካው
በጦር ብዛት ሳይሆን...
በነፍሱ ሀቅ ነው ፣ አቅሙን የሚለካው ።
።።።።
@getem
@getem
@gebriel_19
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ጠብመንጃና ክላሽ ፣ ሳልታጠቅ መውዜር
የኢትዮጵያ ጠላት
አሳልፌ ሰጠሁ ፣ ለአላህ እና ለ'ግዜር ።
።።
አንተም ልክ እንደኔ ፣ ከምትጨልም በቀን
አሸናፊ ሰው ሁን!
ዘር ዘር በሚሉ ፊት ፣ ሰውን በማቀንቀን
እንዲያ ያረክ ቀን...
.
ጠላትህ ምን ቢገዝፍ ፣ ምን ጦር ቢደረድር
ከጠጠር አያልፍ!
"እርዳኝ" ያልከው አምላክ ፣ ወንጭፍህ ላይ ሲያድር ።
...... ...................................
እንዲያ ነው ስልጡን ህዝብ
ሳይታገል ጥሎ ፣ ሳይፎክር ሚረካው
በጦር ብዛት ሳይሆን...
በነፍሱ ሀቅ ነው ፣ አቅሙን የሚለካው ።
።።።።
@getem
@getem
@gebriel_19
ሳቄን መልሽልኝ .☞(ሳሙኤል አዳነ)
ተግባር ላይ ያልታየ
ቃልሽን አምኜ ፤
እንችን ብቻ እያሰብኩ
ሰማይ ምድር ሁኜ ፤
ፊደል አሳምረሽ
የሰጠሽን ተስፋ፤
ድንገት ብትለይኝ
ሳቄን ይዞት ጠፋ።
ሳቄን መልሽልኝ
ልቤን ትቸዋለሁ፤
ልብ ማለት ቀርቶ
መስማት ጠልቻለሁ።
07/07/2010
3:30am
WDU
@getem
@getem
@gebriel_19
ተግባር ላይ ያልታየ
ቃልሽን አምኜ ፤
እንችን ብቻ እያሰብኩ
ሰማይ ምድር ሁኜ ፤
ፊደል አሳምረሽ
የሰጠሽን ተስፋ፤
ድንገት ብትለይኝ
ሳቄን ይዞት ጠፋ።
ሳቄን መልሽልኝ
ልቤን ትቸዋለሁ፤
ልብ ማለት ቀርቶ
መስማት ጠልቻለሁ።
07/07/2010
3:30am
WDU
@getem
@getem
@gebriel_19