ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አስረሽ ፍችው
.
#Dave
/
አፍቅረሽ ስትተይኝ~አፍቅሬሽ ተቀጣሁ
እሱን ስትፈልጊ
እኔም በተራዬ ~ልፈልግሽ ወጣሁ
ክብር ይሁንና
አንችን ከሱ ጋራ~ላገናኘ ፍቅር
በመፈለጌ ውስጥ
ማንነቴን ጥዬ ~ሳላገኝሽ ብቀር
ለካስ ባንች ሰበብ
ራሴን ፈልጌ~እያገኘሁ ነበር

@getem
@getem
@getem
አስረሽ ፍችው
.
#Dave
/
አፍቅረሽ ስትተይኝ~አፍቅሬሽ ተቀጣሁ
እሱን ስትፈልጊ
እኔም በተራዬ ~ልፈልግሽ ወጣሁ
ክብር ይሁንና
አንችን ከሱ ጋራ~ላገናኘ ፍቅር
በመፈለጌ ውስጥ
ማንነቴን ጥዬ ~ሳላገኝሽ ብቀር
ለካስ ባንች ሰበብ
ራሴን ፈልጌ~እያገኘሁ ነበር

@getem
@getem
@gebriel_19
~ቅጣቴ~
ነፍስና ስጋዬን የምታማልጂ
ነይልኝ ያልኩሽ ለት አትቅሪብኝ እንጂ
በቀልም አስበሽ ከመጣሽ ከደጄ
እቀበልሻለው ጥላቻሽ ወድጄ
መርዝሽን በጥብጠሽ ያጠጣሽኝ ለታ
ጠረንሽ ብቻ ነው ለኔ የሚሸታ
አንቺው ከበረዝሺው ካልሆነ ሌላ ሰው
መርዝ ውስጥ ፍቅር አለ ልቤን የሚያርሰው
ባለንጋ ጣቶችሽ
ኩምትር ያለው ፊቴ በጥፊ ሲላጋ
ከውስጥ የሚሰማኝ
እልልታ ብቻ ነው
ሲቦርቅ ሲጨፍር ልቤ ከልብሽ ጋ
ጎኔም አልቆሰለ በሰይፍሽ ስለቱ
ይልቅ የሚሰማኝ
በወጋሽኝ ቁጥር
ሰይፉን አልፎ የመጣው መዳፍሽ ሙቀቱ
ልቤን የሚያቀልጠው የገላሽ ግለቱ
የሚያደነዝዘኝ የጡትሽ ንዝረቱ
እልፍ ቢዘንብበት የስድብሽ ናዳ
የሚያፈቅርሽ ልቤ መቼም አይጎዳ
ካፍሽ ከሚወጣው ከፀያፍ ቃል ጀርባ
ለኔ የሚሰማኝ
ሙዚቃ ብቻ ነው
ስርቅርቁ ድምፅሽ ደምስሬ ሲገባ
ካሻሽ ጋራ ብቶኝ ወደሽ ሌላ አፍቃሪ
ቅንጣት አይገኝም ከልቤ ስባሪ
ብቻ ላንቺ ገላ ሀሴት ይዝነብ እንጂ
ልቤ ደስተኛ ነው ያሻሽን ብትወጂ
ታዳሳ ቅዠቴ ብቸኛው ፍርሀቴ
ከቅጣቶች ሁሉ ሀያሉ ቅጣቴ
ስትቀሪ ብቻ ነው
የተዋበ አይንሽን ባይኔ አለማየቴ

@getem
@getem
@paappii

#dave zophist