Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul Mekonnen)
#Exhibition
Check out the great 'Blue' art show by Zelalem Merga at the etmetro gallery! Zelalem makes cool art pieces from things people throw away. There are nice portraits and pretty blue paintings. The show is open until August 15, 2024 - go see it!
@seiloch
Check out the great 'Blue' art show by Zelalem Merga at the etmetro gallery! Zelalem makes cool art pieces from things people throw away. There are nice portraits and pretty blue paintings. The show is open until August 15, 2024 - go see it!
@seiloch
👍12❤3
ፃድቅ አያደርግም፡
በገዳይ መቀደም
ዝም በይ ያ'ቤል ደም!
ደርሰሽ አትጩኺ፡ እንደተበደለ
ለሁለት የጣሉት፡ ላንዱ እየታደለ
ፍቅር መተማመን፡ በእጣ ከጎደለ
የፉክክር ሜዳ፡ ከተደለደለ
ከዚያ በኋላማ፡ ሞት በዘር አይደለ?
ለሟች እና ገዳይ፡ ምን ይሰራል ድንበር
መጮህ አስቀድሞ፡
የደረሱበት ጋር፡ ላለመድረስ ነበር።
ፅጌሬዳ ቀንበጥ ፡ እሾኋ ሲወጋት
ብትጮህ እሪ ብትል፡ ተካይ ምን ያድርጋት?
እንዴት ትፀድቃለች?
እሷ ብትለሰልስ፡ ሌላውን ባትጎዳ
በዘሯ አይደለም ወይ ፡የመጣባት እዳ?
ፃድቅ አያሰኝም
በገዳይ መቀደም
ደርሰሽ አትጩኺ፡ዝም በይ ያ'ቤል ደም
እየበጠበጠ፡ ለጣለው ወላጁ
አንዴ እንደ ብርሌ፡ ከተበጀ ልጁ
ቢነቃም ባይነቃም፡ ለጠጅ የሚጋጭ
ሟችም ያው ገዳይ ነው፡ አልቀናውም እንጂ።
red-8
@getem
@getem
በገዳይ መቀደም
ዝም በይ ያ'ቤል ደም!
ደርሰሽ አትጩኺ፡ እንደተበደለ
ለሁለት የጣሉት፡ ላንዱ እየታደለ
ፍቅር መተማመን፡ በእጣ ከጎደለ
የፉክክር ሜዳ፡ ከተደለደለ
ከዚያ በኋላማ፡ ሞት በዘር አይደለ?
ለሟች እና ገዳይ፡ ምን ይሰራል ድንበር
መጮህ አስቀድሞ፡
የደረሱበት ጋር፡ ላለመድረስ ነበር።
ፅጌሬዳ ቀንበጥ ፡ እሾኋ ሲወጋት
ብትጮህ እሪ ብትል፡ ተካይ ምን ያድርጋት?
እንዴት ትፀድቃለች?
እሷ ብትለሰልስ፡ ሌላውን ባትጎዳ
በዘሯ አይደለም ወይ ፡የመጣባት እዳ?
ፃድቅ አያሰኝም
በገዳይ መቀደም
ደርሰሽ አትጩኺ፡ዝም በይ ያ'ቤል ደም
እየበጠበጠ፡ ለጣለው ወላጁ
አንዴ እንደ ብርሌ፡ ከተበጀ ልጁ
ቢነቃም ባይነቃም፡ ለጠጅ የሚጋጭ
ሟችም ያው ገዳይ ነው፡ አልቀናውም እንጂ።
red-8
@getem
@getem
❤21👍20😢2
#ወደ_ግጥም__ወደ_ነብይ
ፈግታን ስለቸረን መነሱ ___ ስላስጠለለን ዋርካነቱ
ስለ አፅናኝ ጨዋታዎቹ ___ ሕይወት ስለሚያሞቁ ግጥሞቹ
ቅንነቱን ለማቀንቀን ___ አባትነቱን ለማወደስ
ስለ ግጥም _ _ _ ደግሞም ስለ ነብይ
ቅዳሜ እንሰበሰባለን። ፈንድቃ ቤተ ጥበብ [ ፈንድቃ የጥበባትና ባህል ማዕከል:Fendika Art & Cultural Center ]
• ውብ ግጥሞች ልዩ
• ልዩ የሙዚቃ ጨዋታዎች
• ነገረ ነብይ
• የጥበብ ቅማ ቅመም
የምትወዷቸው የምንወዳቸው ሁሉ አሉ። ስለ ግጥም _ ስለነብይ።
ከ8:00 ቀደም ብላችሁ ኑ።
ቡናውም ጨዋታውም ወዳጅ ትውውቁም እንዳይቀርባችሁ።
ቅዳሜ ሀምሌ 6 2016 ዓ.ም 😍🙏🙏🙏😍
@getem
@getem
ፈግታን ስለቸረን መነሱ ___ ስላስጠለለን ዋርካነቱ
ስለ አፅናኝ ጨዋታዎቹ ___ ሕይወት ስለሚያሞቁ ግጥሞቹ
ቅንነቱን ለማቀንቀን ___ አባትነቱን ለማወደስ
ስለ ግጥም _ _ _ ደግሞም ስለ ነብይ
ቅዳሜ እንሰበሰባለን። ፈንድቃ ቤተ ጥበብ [ ፈንድቃ የጥበባትና ባህል ማዕከል:Fendika Art & Cultural Center ]
• ውብ ግጥሞች ልዩ
• ልዩ የሙዚቃ ጨዋታዎች
• ነገረ ነብይ
• የጥበብ ቅማ ቅመም
የምትወዷቸው የምንወዳቸው ሁሉ አሉ። ስለ ግጥም _ ስለነብይ።
ከ8:00 ቀደም ብላችሁ ኑ።
ቡናውም ጨዋታውም ወዳጅ ትውውቁም እንዳይቀርባችሁ።
ቅዳሜ ሀምሌ 6 2016 ዓ.ም 😍🙏🙏🙏😍
@getem
@getem
👍28❤3
Forwarded from Ni
---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- -----
---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- -----
ስንሻገር፤ከጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ
ከድቅድቅ፤ወደ ብርሃን ስናልፍ
የልባችን እንዲሞላ፤ጉዞዐችን እንዲሰምር
ጠባቂያችን ማነው፤ ከሰማይ ነው ከምድር ?
📷 M3SH
✍️ ኒቆዲሞስ
@niko_nikodimos1
---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- ----
---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- ----
@getem
@getem
@getem
---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- -----
ስንሻገር፤ከጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ
ከድቅድቅ፤ወደ ብርሃን ስናልፍ
የልባችን እንዲሞላ፤ጉዞዐችን እንዲሰምር
ጠባቂያችን ማነው፤ ከሰማይ ነው ከምድር ?
📷 M3SH
✍️ ኒቆዲሞስ
@niko_nikodimos1
---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- ----
---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- ----
@getem
@getem
@getem
👍27❤12🔥5😁2
ሸፍኜው
ከሳቄ ጀርባ ላይ
የተሸከምኳቸው
ከጥርሶቼ መሀል
የሠገሠኳቸው
በሳቆቼ ድምፅ ውስጥ
ያጠራቀምኳቸው
ወጥተው እንዳይፈሱ
ታይተው እንዳያንሱ
ሀዘን እንዳያወረሱ
ያጠራቀምኳቸው
ችግሮች ብዙ አሉ፤
ከችግሬ በላይ ሣቄ እንዲጋባ
ከሀዘኔ በላይ ደስታዬ እንዲሞላ
አዎን እስቃለው፤
በፈተናዎቼ ደረጃ ሰርቼ
ለናንተ ታይቼ
ከፈተና በላይ እኔ እንዳለሁኝ
ከችግሬ በላይ ሣቅን እየሳኩኝ
በጥርሶቼ መሀል በሳቄ ጀርባ ላይ፤
ይዤ የምጓዛቸው ትልቅ ህመም ያለው
የሀዘኖች መዝሙር የማያልቀኝ ሳቅ ነው።
ተጣፈ(በኤደን ግርማ)
@getem
@getem
ከሳቄ ጀርባ ላይ
የተሸከምኳቸው
ከጥርሶቼ መሀል
የሠገሠኳቸው
በሳቆቼ ድምፅ ውስጥ
ያጠራቀምኳቸው
ወጥተው እንዳይፈሱ
ታይተው እንዳያንሱ
ሀዘን እንዳያወረሱ
ያጠራቀምኳቸው
ችግሮች ብዙ አሉ፤
ከችግሬ በላይ ሣቄ እንዲጋባ
ከሀዘኔ በላይ ደስታዬ እንዲሞላ
አዎን እስቃለው፤
በፈተናዎቼ ደረጃ ሰርቼ
ለናንተ ታይቼ
ከፈተና በላይ እኔ እንዳለሁኝ
ከችግሬ በላይ ሣቅን እየሳኩኝ
በጥርሶቼ መሀል በሳቄ ጀርባ ላይ፤
ይዤ የምጓዛቸው ትልቅ ህመም ያለው
የሀዘኖች መዝሙር የማያልቀኝ ሳቅ ነው።
ተጣፈ(በኤደን ግርማ)
@getem
@getem
❤37👍19😢3🔥1
ይሻላል አልሽ አሉ
ከኔ መነጠሉ
መነጠል ነጠለን
ልዩነት ዳር ጥሎ ውዴ ገፋኝ ካንቺ
እኔስ ደክሜ አለሁ
ባይሆን አንቺ በርቺ
ብር አላት ደሀ ነው
መባል ቀነሰልኝ ካንቺ ብርቅ ጊዜ
መሆኔ ግን ጎዳኝ
የሰርግሽ ለት ሚዜ
እንዳልሆን አስፈራኝ
በዚ አያያዝሽ ለልጅሽ ያይን አባት
አካሌስ ግድ የለው
ልቤን ፈረድሽባት
ልንገረው ታሪኬን
ለላይኛው ዳኛ
ወይ ይውረድ ወይ ይፍረድ
አያርገኝ እረኛ
ወይ ሀብት ያሸክመኝ
ከንደኔ አይነቱ አንቺን መሰል ልንጠቅ
ሄደች አመለጠች ብዬ እዳልሳቀቅ
አልያ ልብ ስጠኝ
ድህነቴን ልመን በነዋይ ማነሴን
ልቤን ሙላውና አጉድለው የኪሴን
ነቢሉ ✍
@getem
@getem
ከኔ መነጠሉ
መነጠል ነጠለን
ልዩነት ዳር ጥሎ ውዴ ገፋኝ ካንቺ
እኔስ ደክሜ አለሁ
ባይሆን አንቺ በርቺ
ብር አላት ደሀ ነው
መባል ቀነሰልኝ ካንቺ ብርቅ ጊዜ
መሆኔ ግን ጎዳኝ
የሰርግሽ ለት ሚዜ
እንዳልሆን አስፈራኝ
በዚ አያያዝሽ ለልጅሽ ያይን አባት
አካሌስ ግድ የለው
ልቤን ፈረድሽባት
ልንገረው ታሪኬን
ለላይኛው ዳኛ
ወይ ይውረድ ወይ ይፍረድ
አያርገኝ እረኛ
ወይ ሀብት ያሸክመኝ
ከንደኔ አይነቱ አንቺን መሰል ልንጠቅ
ሄደች አመለጠች ብዬ እዳልሳቀቅ
አልያ ልብ ስጠኝ
ድህነቴን ልመን በነዋይ ማነሴን
ልቤን ሙላውና አጉድለው የኪሴን
ነቢሉ ✍
@getem
@getem
❤63👍27🔥4😱2
[ስለ ልብሽ.....]
__
[ ፩ ]
¹
በዕድሜ ጎዳና ላይ
ብዙ መንገድ ሄደሽ ፤
ገደል ጉራንጉሩን
ተራራውን ወርደሽ ፤
ሽቅብ ያለፍሽውን
ቁልቁል ተመልሰሽ ፤
ባገኘሻት አፍታ —
ደረትሽን ዳብሰሽ.....
(ድለቃ - ሙዚቃ) ትርታ — ስታጪ ፤
“ልቤ ሞቷል” ብለሽ አትደናገጪ ።
_
ባይጮኽ እንደ'ኛ
ትርታ ቅኝት.....
ድቤ (ከበሮ) ባይሆን አጀቡ ፤
(ልብሽ ልብ አለው....)
ያንጎራጉራል እሱም በልቡ ።
(ሰምቼዋለሁ ....!)
እሰማዋለሁ....
ጊዜ ጌታው በቀለሙ
በቀኑ ላይ ፅልመት ሲስል
ጨለም መሸት ደንገዝ ሲል
በሌሊቱ በድቅድቁ
ሁሉም ሲተኙ ሲወድቁ
(አንቺም ..)
ተኛሁ ብለሽ ካረፍሽበት ...
እንደ መንፈስ ስውር ጥላ
በዘጋሽው በር አልፌ ፤
(እገባና....)
ደረትሽ ላይ ተለጥፌ ፤
(“የለም ጠፍቷል
ሞቷል” ያልሽው)
ዳብሰሽ ዳብሰሽ
ያልሰማሽው....
ያልተጨመረበት ድቤ
ያልታጀበ በከበሮ ፤
የልብሽን ለስለስ ያለ
የለሆሳስ እንጉርጉሮ ፤
ደስስ እያለኝ እሰማለሁ ....
(ሌሊት ሌሊት እመጣለሁ ።)
²
ዘምቶ ባይዋጋ ....
ባይሆን ፊታውራሪ ፤
«ጊዜ `ሚጠብቅ ሰው
ይባላል ወይ ፈሪ !?»
(እንዳለው አዝማሪ......)
የሚመስል ዘፈን እያንጎራጎረ ....
ተኝቶ (ድምፁን አጥፍቶ)
በዘዴ ሲያልፈው ወጀቡን ፤
ላይ ላዩን በረሃ መስሎ
ውስጥ ውስጡን አውቆ ማበቡን ፤
ማን አየው የልብሽ ልቡን !?
_
ያለም ሁካታ ሸፍኖት
ጫጫታው ጆሮውን ደፍኖት
ልብሽን ሳይሰማው ቢቀር
ውስጥሽም እየታለለ ፤
«ልብ አልባ ኦና !
ባዶ ነኝ » አለ ?!
ካንቺም ወዲያ “ሙሉ” የለ !!
ካንቺም ወዲያ “ልባም” የለ !!
[፪]
በዕድሜ ጎዳና ላይ
ብዙ መንገድ ሄደሽ ፤
ገደል ጉራንጉሩን
ተራራውን ወርደሽ ፤
ሽቅብ ያለፍሽውን
ቁልቁል ተመልሰሽ ፤
ባገኘሻት አፍታ —
ደረትሽን ዳብሰሽ ፤
የራቀብሽ ድምፁ
ያጣሽው ትርታ ፤
ይጠራሽ ይሆናል
የማታ የማታ ።
(አሁን ግን ይብቃሽ!)
አትድቂ ደረት — አቁሚ ለቅሶ ፤
(አውቆ በዘዴ ድምፁን ቀንሶ ...)
ቀን ጠበቀ እንጂ — ቀን ሊያወጣልሽ
ልብሽ ዝም ሲል — “ሙት” አይምሰልሽ ።
___
By @Bekalushumye
@getem
@getem
@getem
__
[ ፩ ]
¹
በዕድሜ ጎዳና ላይ
ብዙ መንገድ ሄደሽ ፤
ገደል ጉራንጉሩን
ተራራውን ወርደሽ ፤
ሽቅብ ያለፍሽውን
ቁልቁል ተመልሰሽ ፤
ባገኘሻት አፍታ —
ደረትሽን ዳብሰሽ.....
(ድለቃ - ሙዚቃ) ትርታ — ስታጪ ፤
“ልቤ ሞቷል” ብለሽ አትደናገጪ ።
_
ባይጮኽ እንደ'ኛ
ትርታ ቅኝት.....
ድቤ (ከበሮ) ባይሆን አጀቡ ፤
(ልብሽ ልብ አለው....)
ያንጎራጉራል እሱም በልቡ ።
(ሰምቼዋለሁ ....!)
እሰማዋለሁ....
ጊዜ ጌታው በቀለሙ
በቀኑ ላይ ፅልመት ሲስል
ጨለም መሸት ደንገዝ ሲል
በሌሊቱ በድቅድቁ
ሁሉም ሲተኙ ሲወድቁ
(አንቺም ..)
ተኛሁ ብለሽ ካረፍሽበት ...
እንደ መንፈስ ስውር ጥላ
በዘጋሽው በር አልፌ ፤
(እገባና....)
ደረትሽ ላይ ተለጥፌ ፤
(“የለም ጠፍቷል
ሞቷል” ያልሽው)
ዳብሰሽ ዳብሰሽ
ያልሰማሽው....
ያልተጨመረበት ድቤ
ያልታጀበ በከበሮ ፤
የልብሽን ለስለስ ያለ
የለሆሳስ እንጉርጉሮ ፤
ደስስ እያለኝ እሰማለሁ ....
(ሌሊት ሌሊት እመጣለሁ ።)
²
ዘምቶ ባይዋጋ ....
ባይሆን ፊታውራሪ ፤
«ጊዜ `ሚጠብቅ ሰው
ይባላል ወይ ፈሪ !?»
(እንዳለው አዝማሪ......)
የሚመስል ዘፈን እያንጎራጎረ ....
ተኝቶ (ድምፁን አጥፍቶ)
በዘዴ ሲያልፈው ወጀቡን ፤
ላይ ላዩን በረሃ መስሎ
ውስጥ ውስጡን አውቆ ማበቡን ፤
ማን አየው የልብሽ ልቡን !?
_
ያለም ሁካታ ሸፍኖት
ጫጫታው ጆሮውን ደፍኖት
ልብሽን ሳይሰማው ቢቀር
ውስጥሽም እየታለለ ፤
«ልብ አልባ ኦና !
ባዶ ነኝ » አለ ?!
ካንቺም ወዲያ “ሙሉ” የለ !!
ካንቺም ወዲያ “ልባም” የለ !!
[፪]
በዕድሜ ጎዳና ላይ
ብዙ መንገድ ሄደሽ ፤
ገደል ጉራንጉሩን
ተራራውን ወርደሽ ፤
ሽቅብ ያለፍሽውን
ቁልቁል ተመልሰሽ ፤
ባገኘሻት አፍታ —
ደረትሽን ዳብሰሽ ፤
የራቀብሽ ድምፁ
ያጣሽው ትርታ ፤
ይጠራሽ ይሆናል
የማታ የማታ ።
(አሁን ግን ይብቃሽ!)
አትድቂ ደረት — አቁሚ ለቅሶ ፤
(አውቆ በዘዴ ድምፁን ቀንሶ ...)
ቀን ጠበቀ እንጂ — ቀን ሊያወጣልሽ
ልብሽ ዝም ሲል — “ሙት” አይምሰልሽ ።
___
By @Bekalushumye
@getem
@getem
@getem
👍39❤29
አልቀጥርም ጠበቃ
ተጎዳሁኝ ብየ አልከስም በሸንጎ
ላንቺ ክፉ ሚመኝ
የሚያስፈርድብሽ ልቤ እንዴት አድርጎ
እንዳንቺ አይነት እንኮይ
ፈልጌ ላላገኝ ምትሆን ለእኔነቴ
ከስሼሽ ላልካስ
ዳኛ በመፈለግ አይዝልም ጉልበቴ
አይታገሉትም
ጦር አይመዘዝም አይገታው ጠብመንጃ
ምን ሹም ሊፈርድበት
ምን ችሎት ሊፈታው የማፍቀርን ፍርጃ
✍️✍️✍️ይቴ(@gtmwustie)
@getem
@getem
@gitimtm
ተጎዳሁኝ ብየ አልከስም በሸንጎ
ላንቺ ክፉ ሚመኝ
የሚያስፈርድብሽ ልቤ እንዴት አድርጎ
እንዳንቺ አይነት እንኮይ
ፈልጌ ላላገኝ ምትሆን ለእኔነቴ
ከስሼሽ ላልካስ
ዳኛ በመፈለግ አይዝልም ጉልበቴ
አይታገሉትም
ጦር አይመዘዝም አይገታው ጠብመንጃ
ምን ሹም ሊፈርድበት
ምን ችሎት ሊፈታው የማፍቀርን ፍርጃ
✍️✍️✍️ይቴ(@gtmwustie)
@getem
@getem
@gitimtm
👍39❤11🔥5