ግጥም በSAM:
#የሴት_ልጅ
(በስሜነህ አማረ- SAM)
በወንድነት ልኬት~ ሴትነት ካነሰ
የሰው ልጅ ለራሱ~ ራሱን አሳነሰ።
እኔን ግን...
ሁለት ሶስት ጊዜ
ድጋሚ ደጋግመህ~ ና 'የሴት ልጅ' በለኝ
እናቴን ስትጠራት
በክብሯ ስትነግስ~ ልጇን ደስ ይበለኝ
ስሟን ልታሳንስ
መጥራትህ ከሆነ~ እንዲህ ብለህ ያልከኝ
ይግረምህ ሞተሃል
እኔ ግን እንዳልከው~ አዎ የሴት ልጅ ነኝ።
ገበሬ ዘር ይዞ
መዝሪያ ቦታ ካጣ~ ምን ላይ ነው ግብርናው?
ዘሩ ፍሬ ሆኖ
አፍሰህ የምትቅመው~ በልስልስ ማሳ ነው
ስለዚህ...
እናትህ አፈር ነች
ለስላሳዋ ማሳ~ ያንተነት መብቀያ
እናትህ ውሃ ነች
ያለሷ ድርቅ ነው~ ህይወት የ'ልም ቋያ
እናትህ አየር ነች
እስትንፋስ 'ምትለግስ~ የሷ ትንፋሽ ሲያጥራት
እናትህ እሳት ነች
ለራሷ ተቃጥላ~ ላንተ ስትል 'ምትሞት
ያንተን የት መጤነት
ሰው የመሆን ምስጢር~ ልክህን ብታውቀው
ሁሉም ማንነትህ
አፈርና ውሃ~ ነፋስና 'ሳት ነው።
:
:
ማነው...?
ሴት ያላረገዘው
ሴት ያላማጠችው~ ሴት ያልወለደችው
ሴት ያላቀፈችው
ሴት ያላጠባችው~ ሴት ያላዘለችው
ወንድ ነኝ ባይ ሁላ~ ክፍት አፉን ሲከፍተው
የውስጡ ባዶነት~ ጎልቶ የሚታየው
ከሴት ያልተገኘ~ እርሱ ራሱ ማነው???
:
:
እኔን ግን...
ሁለት ሶስት ጊዜ
ድጋሚ ደጋግመህ~ ና 'የሴት ልጅ' በለኝ
እናቴን ስትጠራት
በክብሯ ስትነግስ~ ልጇን ደስ ይበለኝ::
አ
ዎ
የሴት ልጅ ነኝ።
:
:
@SAM
@getem
@getem
@getem
#የሴት_ልጅ
(በስሜነህ አማረ- SAM)
በወንድነት ልኬት~ ሴትነት ካነሰ
የሰው ልጅ ለራሱ~ ራሱን አሳነሰ።
እኔን ግን...
ሁለት ሶስት ጊዜ
ድጋሚ ደጋግመህ~ ና 'የሴት ልጅ' በለኝ
እናቴን ስትጠራት
በክብሯ ስትነግስ~ ልጇን ደስ ይበለኝ
ስሟን ልታሳንስ
መጥራትህ ከሆነ~ እንዲህ ብለህ ያልከኝ
ይግረምህ ሞተሃል
እኔ ግን እንዳልከው~ አዎ የሴት ልጅ ነኝ።
ገበሬ ዘር ይዞ
መዝሪያ ቦታ ካጣ~ ምን ላይ ነው ግብርናው?
ዘሩ ፍሬ ሆኖ
አፍሰህ የምትቅመው~ በልስልስ ማሳ ነው
ስለዚህ...
እናትህ አፈር ነች
ለስላሳዋ ማሳ~ ያንተነት መብቀያ
እናትህ ውሃ ነች
ያለሷ ድርቅ ነው~ ህይወት የ'ልም ቋያ
እናትህ አየር ነች
እስትንፋስ 'ምትለግስ~ የሷ ትንፋሽ ሲያጥራት
እናትህ እሳት ነች
ለራሷ ተቃጥላ~ ላንተ ስትል 'ምትሞት
ያንተን የት መጤነት
ሰው የመሆን ምስጢር~ ልክህን ብታውቀው
ሁሉም ማንነትህ
አፈርና ውሃ~ ነፋስና 'ሳት ነው።
:
:
ማነው...?
ሴት ያላረገዘው
ሴት ያላማጠችው~ ሴት ያልወለደችው
ሴት ያላቀፈችው
ሴት ያላጠባችው~ ሴት ያላዘለችው
ወንድ ነኝ ባይ ሁላ~ ክፍት አፉን ሲከፍተው
የውስጡ ባዶነት~ ጎልቶ የሚታየው
ከሴት ያልተገኘ~ እርሱ ራሱ ማነው???
:
:
እኔን ግን...
ሁለት ሶስት ጊዜ
ድጋሚ ደጋግመህ~ ና 'የሴት ልጅ' በለኝ
እናቴን ስትጠራት
በክብሯ ስትነግስ~ ልጇን ደስ ይበለኝ::
አ
ዎ
የሴት ልጅ ነኝ።
:
:
@SAM
@getem
@getem
@getem