እንዲህ ነኝ!(ልዑል ሀይሌ)
“እንዴት ነህ?” ከምትሉ
እስቲ እንደዚህ ሁኑ!
.
የቁስሌን መጠን ቁሰሉና ለኩ ፤
የሚያሳክከኝን ውሰዱና እከኩ፤
የሚያመኝን ሕመም ታመሙና ኑሩት፤
የልቤን ፍላሎት
አይገልፀውምና እንዲሁ ሲናገሩት።
.
“እንዴት ነህ?” ከምትሉ
እስቲ እንደዚህ ሁኑ!
.
’ሚነፍሰውን ንፋስ
በጎኔ ሚዘልቀው በጎናችሁ አዝልቁት፤
’ሚዘንበውን ዝናብ
’ሚያበሰብሰኝን በጉንጫችሁ አውርዱት፤
..
የሚያንገበግበኝ
የወዳጄን ክህደት በወዳጅ ተካዱ፤
እሾህ ላይ ስራመድ በእሾህ ላይ ሂዱ።
..
ያኔ ነው ምታውቁት
የኔን የሕይወት ፈር፤
“ደህና ነው” በሚል ቃል ይህ ሁሉ ሲሰፈር።
፲፪.፩.፲፩ ዓ.ም.
@getem
@getem
@gebriel_19
“እንዴት ነህ?” ከምትሉ
እስቲ እንደዚህ ሁኑ!
.
የቁስሌን መጠን ቁሰሉና ለኩ ፤
የሚያሳክከኝን ውሰዱና እከኩ፤
የሚያመኝን ሕመም ታመሙና ኑሩት፤
የልቤን ፍላሎት
አይገልፀውምና እንዲሁ ሲናገሩት።
.
“እንዴት ነህ?” ከምትሉ
እስቲ እንደዚህ ሁኑ!
.
’ሚነፍሰውን ንፋስ
በጎኔ ሚዘልቀው በጎናችሁ አዝልቁት፤
’ሚዘንበውን ዝናብ
’ሚያበሰብሰኝን በጉንጫችሁ አውርዱት፤
..
የሚያንገበግበኝ
የወዳጄን ክህደት በወዳጅ ተካዱ፤
እሾህ ላይ ስራመድ በእሾህ ላይ ሂዱ።
..
ያኔ ነው ምታውቁት
የኔን የሕይወት ፈር፤
“ደህና ነው” በሚል ቃል ይህ ሁሉ ሲሰፈር።
፲፪.፩.፲፩ ዓ.ም.
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ለ 10ኛ ክፍል የማትሪክ ተፈታኞች በሙሉ ውጤት ዛሬ 10:00
ስላሚወጣ በቀላሉ ውጤቶን ለማየት @neaea_neaea_bot ተጠቀሙ ፣ ቀላል ፣ ቀልጣፋ እና ታአማኒ ያለምንም የሰው ጣልቃ ገበነት 24/7 የሚሰራ ።
@neaea_neaea_bot
የእርሶን እና የጓደኞዎቾ ለማየት ይህን bot ይጠቀሙ
12 ኛ ምድብ ምት ጠብ ቁም እዚሁ bot ላይ ታገኙታላችሁ
@getem
@getem
ስላሚወጣ በቀላሉ ውጤቶን ለማየት @neaea_neaea_bot ተጠቀሙ ፣ ቀላል ፣ ቀልጣፋ እና ታአማኒ ያለምንም የሰው ጣልቃ ገበነት 24/7 የሚሰራ ።
@neaea_neaea_bot
የእርሶን እና የጓደኞዎቾ ለማየት ይህን bot ይጠቀሙ
12 ኛ ምድብ ምት ጠብ ቁም እዚሁ bot ላይ ታገኙታላችሁ
@getem
@getem
#እንቁ_ለጌጥሽ
🌼🌼🌼🌼🌼
እንዴት ያለ እድል ፥ አወይ ጥቁር ምላስ
ባከላትሽ ታዞ
በትንታግ ዘመንሽ አዲስ እጣሽ ሲላስ
ምርቃት ይሁን እርግማን
ዋርሳ ይሁን ስጦታ .....ሳይገባሽ
እንቁ-ለጣጣሽ ብትባይ
ስለምን ለቤ'ክ አልሽ?
እልፍ አዲስ አመት ፥ አያሌ መባቻ
ጌጡ የት ሄዶብሽ ?
ችጋር የተረፈሽ ፥ ባያትሽ ስልቻ
አንድ ቀን እልልታ ፥ ሶስት መቶ ቀን ለቅሶ
ዘረኛ ቋቁቻ
እንደ ሸማ ጥለት ፥ ሰውነትሽን ወርሶ
አንጀቱ የቀናው ፥ መብሉን አስመልሶ
የሚበላው ያጣም
ጥሬውን ቆርጥሞ ፥ በምራቅ ለውሶ
እኩል ...እየ-ዬ ነው !!!
ባሳለፍነው ዘመን ፥ ከእልልታው ለጥቆ
ለነብስ እየሰጉ ፥ ለስጋ ተሳቆ
አይሻገር የለ ፥ ሶስት መቶ ቀን አልቆ
አዲስ ዘመን መጣ
ካለንበት ቡኮ ፥:ከማጡ ሳንወጣ።
አዲስ አመት በሚል ፥ ደስታ ልትቃርሚ
ጭቃ መደላድል ፥ ምን አምነሽ ትቆሚ?
ጣትሽ ሳይጠነከር እድፍሽ ሳይጠራ
ሽንሽን ብትለብሺ ከሀር የተሰራ
ያዳለጠሽ ግዜ
መሬት ባለጌ ነው ስጋሽን አይፈራ
ለቀን አያውልሽ የጥበብሽ ጮራ።
እና ከተረዳሽ ከገባሽ መልእክቴ
እርግማንሽን አንሺ !!!
ላይተር ሳያጠፉ ፥ መመፃደቅ ይቅር ፥ መዘወሩ ቦቴ
የተመረቀ ቀን
እንኳንስ በእንቁ ፥ ይከብራል በአርቴ
እንቁ ለጣጣሽ ይታጠፍ
እንቁ ለጌጥሽ #እናቴ !! ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
#መልካም_አዲስ_አመት_ጣጣችን_ይፈንገል_በሰላም_በፍቅር_በደስታ_በብልፅግና_ማጌጫ_2012_ይሁንልን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
@getem
@getem
@getem
🌼🌼🌼🌼🌼
እንዴት ያለ እድል ፥ አወይ ጥቁር ምላስ
ባከላትሽ ታዞ
በትንታግ ዘመንሽ አዲስ እጣሽ ሲላስ
ምርቃት ይሁን እርግማን
ዋርሳ ይሁን ስጦታ .....ሳይገባሽ
እንቁ-ለጣጣሽ ብትባይ
ስለምን ለቤ'ክ አልሽ?
እልፍ አዲስ አመት ፥ አያሌ መባቻ
ጌጡ የት ሄዶብሽ ?
ችጋር የተረፈሽ ፥ ባያትሽ ስልቻ
አንድ ቀን እልልታ ፥ ሶስት መቶ ቀን ለቅሶ
ዘረኛ ቋቁቻ
እንደ ሸማ ጥለት ፥ ሰውነትሽን ወርሶ
አንጀቱ የቀናው ፥ መብሉን አስመልሶ
የሚበላው ያጣም
ጥሬውን ቆርጥሞ ፥ በምራቅ ለውሶ
እኩል ...እየ-ዬ ነው !!!
ባሳለፍነው ዘመን ፥ ከእልልታው ለጥቆ
ለነብስ እየሰጉ ፥ ለስጋ ተሳቆ
አይሻገር የለ ፥ ሶስት መቶ ቀን አልቆ
አዲስ ዘመን መጣ
ካለንበት ቡኮ ፥:ከማጡ ሳንወጣ።
አዲስ አመት በሚል ፥ ደስታ ልትቃርሚ
ጭቃ መደላድል ፥ ምን አምነሽ ትቆሚ?
ጣትሽ ሳይጠነከር እድፍሽ ሳይጠራ
ሽንሽን ብትለብሺ ከሀር የተሰራ
ያዳለጠሽ ግዜ
መሬት ባለጌ ነው ስጋሽን አይፈራ
ለቀን አያውልሽ የጥበብሽ ጮራ።
እና ከተረዳሽ ከገባሽ መልእክቴ
እርግማንሽን አንሺ !!!
ላይተር ሳያጠፉ ፥ መመፃደቅ ይቅር ፥ መዘወሩ ቦቴ
የተመረቀ ቀን
እንኳንስ በእንቁ ፥ ይከብራል በአርቴ
እንቁ ለጣጣሽ ይታጠፍ
እንቁ ለጌጥሽ #እናቴ !! ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
#መልካም_አዲስ_አመት_ጣጣችን_ይፈንገል_በሰላም_በፍቅር_በደስታ_በብልፅግና_ማጌጫ_2012_ይሁንልን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
@getem
@getem
@getem
"ፈርተን እንዳይመስለው ስላቀረቀርን"
(ይኸው ነው!)
"የዘመን ዕውነት ነን በደግነት ሰማይ በጥበብ የኖርን
ትግስትም ልክ አለው ፈርተን እንዳይመስለው ስላቀረቀርን
ማተብ አስሮን እንጂ ተጣልተን እንዳንቀር በክፍፍል ገደል
ካገር ፍቅር በልጦ ሞት ብርቃችን አይደል
ንገሩት_ለዛ_ሰው
ከአለም ጫፍ እስከ ጫፍ
ሀይል እንደተራራ ገዝፎ ቢከመርም
ክንዱን አፈርጥሞ
እልፍ የሰገደለት ጀግና ቢሰደርም
ዓለም የሞተበት
የጠላት ማርከሻ ጦር ቢደረድርም
በአንድ አይናችን ሰላም
በኢትዮጵያችን ክብር አንደራደርም "
ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ
@getem
@getem
@getem
(ይኸው ነው!)
"የዘመን ዕውነት ነን በደግነት ሰማይ በጥበብ የኖርን
ትግስትም ልክ አለው ፈርተን እንዳይመስለው ስላቀረቀርን
ማተብ አስሮን እንጂ ተጣልተን እንዳንቀር በክፍፍል ገደል
ካገር ፍቅር በልጦ ሞት ብርቃችን አይደል
ንገሩት_ለዛ_ሰው
ከአለም ጫፍ እስከ ጫፍ
ሀይል እንደተራራ ገዝፎ ቢከመርም
ክንዱን አፈርጥሞ
እልፍ የሰገደለት ጀግና ቢሰደርም
ዓለም የሞተበት
የጠላት ማርከሻ ጦር ቢደረድርም
በአንድ አይናችን ሰላም
በኢትዮጵያችን ክብር አንደራደርም "
ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ
@getem
@getem
@getem
ግጥም ሲፃፍበት!!!
ሲሄድ እያየነው ፤
እንደ ደራሽ ውሃ በስሜት ገንፍሎ፤
ጉልፍልፍ እያለ፤
ትልቁን ትንሹን በጉያው አጅሎ፤
ሃገሬው እያየው፤
ይሉኝታ ጠፍቶበት በአጀብ በሆሆታ ሲሄዴ ተግተልትሎ፤
ወንድሙን እንደ በግ፤
ሆ ብሎ በደቦ ዛፍ ላይ አንጠልጥሎ፤
በመንጋ ጉባኤ፤ ንፁሃንን ሰቅሎ፤
የገዛ ወገኑን በድንጋይ ውርጅብኝ በአደባባይ ወግሮ፤
በሜንጫ በዱላ ምስኪኖቹን ቀብሮ፤
መኪና እያስቆመ ፤
የገዛ ወገኑን ንብረት እየቀማ በሽፍትነት አድሮ፤
ዘሎ እየዘረፈ የሰው ድንኳን ሰብሮ፤
ወንድሙን ሲያደማ ሙቅ ውሃ እየደፋ ጀበና ወርውሮ፤
እንዴት መንጋ ይክፋው ፤
ግጥም ሲፃፍበት መንጋ ነህ ተብሎ???
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
ሲሄድ እያየነው ፤
እንደ ደራሽ ውሃ በስሜት ገንፍሎ፤
ጉልፍልፍ እያለ፤
ትልቁን ትንሹን በጉያው አጅሎ፤
ሃገሬው እያየው፤
ይሉኝታ ጠፍቶበት በአጀብ በሆሆታ ሲሄዴ ተግተልትሎ፤
ወንድሙን እንደ በግ፤
ሆ ብሎ በደቦ ዛፍ ላይ አንጠልጥሎ፤
በመንጋ ጉባኤ፤ ንፁሃንን ሰቅሎ፤
የገዛ ወገኑን በድንጋይ ውርጅብኝ በአደባባይ ወግሮ፤
በሜንጫ በዱላ ምስኪኖቹን ቀብሮ፤
መኪና እያስቆመ ፤
የገዛ ወገኑን ንብረት እየቀማ በሽፍትነት አድሮ፤
ዘሎ እየዘረፈ የሰው ድንኳን ሰብሮ፤
ወንድሙን ሲያደማ ሙቅ ውሃ እየደፋ ጀበና ወርውሮ፤
እንዴት መንጋ ይክፋው ፤
ግጥም ሲፃፍበት መንጋ ነህ ተብሎ???
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
ሚሌ ወዲህ ሃራ መጋሌ ስመራ፤
ኩርሚንጋፎ ቆቦ ዳዩ መንደፈራ፤
አቧራው ጨሰ አሉ፤
ከመሆኒ ጨርጨር ፤ ከዋጃ እስከ ጉራ ፤
መቼም ራያ ላይ፤
ወትሮም በሽበሽ ነው ልብና ተራራ።
ያች የራያ ልጅ ባለ ጥርቅ ጫማ ባለመልጎሚቱ ፤
ባለ ኩሌ ከንፈር ባለወተቲቱ ፤
የአባቶቿ ድንበር፤
ከዳዩ እስከ ራማ፤
ከኢቦ እስከ አላውሃ ፤ ታይቷት ምልክቱ፤
ራያ ነኝ ብላ ስመራ ስመራ ስመራ ልጅቱ ፤
ቦፌዋን ታቅፋ ፤
ጎንቢሶዋን ይዛ ለቀየው ተረፈች እንኳን ለማጀቱ።
ይኸ የራያ ሰው ፤
ይኸ የጨርጨር ሰው፤ ሁለትና ሶስቱ ፤
ድብ ይደረምሳል ፤
ሺ ቡከን ቢሰለፍ አይታጠፍ ፊቱ፤
ራቁት ያስኬዳል ደርሰው ከመጡበት በርስቱ በሚስቱ።
እንካ ልበስማ ፤
ማይ ማዩን ደርበው ጎንቢሶውን ታጠቅ፤
ለእነዚያ ሆዳሞች፤
ብለህ ንገርልኝ ፤
እዳው ለልጅ ልጅ ነው ራያን መዳፈር ማንነቱን መስረቅ።
ይህን ሸጋ ቦፌ፤
ይህንን ጎንቢሶ ታጠቅ በወገብህ፤ ዱላም ጨምርበት፤
ይኸው ነው ሰንደቁ፤
ይኸው ነው ባንዲራው የራያ ነፃነት የሚታወጅበት!!
አላ ዝናብ ባይጥል፤ ጎሊና ጅረቱ ቢሞላ ባይሞላ፤
አትጠራጠረኝ፤
ራያ ወሎ እንጅ፤ ራያ ራያ እንጅ አይደለም የሌላ።
ሃበከው !!!!ሃበከው!!!! ሃበከው !!!!!
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
እምወድሽዋ እንኳን መጣሽልኝ ❤️ ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!❤️
በነገራችን ላይ ዛሬ ከ 7:00 ጀምሮ ሸገር ሬድዮ ብትሰሙ ጋዜጠኛ መኣዛ ብሩ ከጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ያደረገችው ቃለመጠይቅ ትሰማላቹ ...ሁሌም ቅዳሜ ከሰዓታችን ገምሸርሸር የሚያደርግልን #ሸገር ሬድዮ ነው !! ይኸው ነው!!
@getem
@getem
@balmbaras
ኩርሚንጋፎ ቆቦ ዳዩ መንደፈራ፤
አቧራው ጨሰ አሉ፤
ከመሆኒ ጨርጨር ፤ ከዋጃ እስከ ጉራ ፤
መቼም ራያ ላይ፤
ወትሮም በሽበሽ ነው ልብና ተራራ።
ያች የራያ ልጅ ባለ ጥርቅ ጫማ ባለመልጎሚቱ ፤
ባለ ኩሌ ከንፈር ባለወተቲቱ ፤
የአባቶቿ ድንበር፤
ከዳዩ እስከ ራማ፤
ከኢቦ እስከ አላውሃ ፤ ታይቷት ምልክቱ፤
ራያ ነኝ ብላ ስመራ ስመራ ስመራ ልጅቱ ፤
ቦፌዋን ታቅፋ ፤
ጎንቢሶዋን ይዛ ለቀየው ተረፈች እንኳን ለማጀቱ።
ይኸ የራያ ሰው ፤
ይኸ የጨርጨር ሰው፤ ሁለትና ሶስቱ ፤
ድብ ይደረምሳል ፤
ሺ ቡከን ቢሰለፍ አይታጠፍ ፊቱ፤
ራቁት ያስኬዳል ደርሰው ከመጡበት በርስቱ በሚስቱ።
እንካ ልበስማ ፤
ማይ ማዩን ደርበው ጎንቢሶውን ታጠቅ፤
ለእነዚያ ሆዳሞች፤
ብለህ ንገርልኝ ፤
እዳው ለልጅ ልጅ ነው ራያን መዳፈር ማንነቱን መስረቅ።
ይህን ሸጋ ቦፌ፤
ይህንን ጎንቢሶ ታጠቅ በወገብህ፤ ዱላም ጨምርበት፤
ይኸው ነው ሰንደቁ፤
ይኸው ነው ባንዲራው የራያ ነፃነት የሚታወጅበት!!
አላ ዝናብ ባይጥል፤ ጎሊና ጅረቱ ቢሞላ ባይሞላ፤
አትጠራጠረኝ፤
ራያ ወሎ እንጅ፤ ራያ ራያ እንጅ አይደለም የሌላ።
ሃበከው !!!!ሃበከው!!!! ሃበከው !!!!!
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
እምወድሽዋ እንኳን መጣሽልኝ ❤️ ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!❤️
በነገራችን ላይ ዛሬ ከ 7:00 ጀምሮ ሸገር ሬድዮ ብትሰሙ ጋዜጠኛ መኣዛ ብሩ ከጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ያደረገችው ቃለመጠይቅ ትሰማላቹ ...ሁሌም ቅዳሜ ከሰዓታችን ገምሸርሸር የሚያደርግልን #ሸገር ሬድዮ ነው !! ይኸው ነው!!
@getem
@getem
@balmbaras
ሲነጋ ልንገርሽ
።።።።።።።።።።።
(ከድር መሀመድ)
ገለጥ ሲልልኝ
ድርብርቡ አፈና፤ጨለማው ተገፎ፤
ሽኩቻ ለትግል
እንቅልፍ ሲነሳ፤በሀገሩ ለፍፎ፤
ምንም አትበይ
ዛሬ ቃላት አጥተሽ፤አፍሽ ቢቀየድም፤
አትስጊ ግዴለም
ዶሮ ጮኸ አልጮኸ፤መንጋቱ አይቀርም፤
እንደነቃሁ ገና
ሲነጋ ልነግርሽ ፤ከንፈሬን ላልሼ ቃላት ፈልግና፤
ሳስብ እፈራለው
ሚስጥር እንዳይሾልከኝ፤ቃል እንዳላዛባ ሳላስብሆነና፤
ምን አልባት
በነገርሽ መሃል ሌላን፤ብተነፍስ ከመሀል ቆይቼ፤
ቃል ግቢልኝ!
አዝልቀሽ ላትሰጪኝ ላሳደኳቸው ነፍስ ወስደሽ ለጅቦቼ፤
በነገርሽ መሀል?
አትስጊ ግዴለም!
ዶሮ ጮኸ አልጮኸም መንጋቱ አይቀርም፤
ይሄው ነው
በጅ ያሳደጉት ጅብ አጉራሽ እጁን ቢነክስ መልሶ፤
ዘመኑ ይሆናል!
ወላጁን ሰዉቶ ተሹሞ የሚኖር መንጎችን ገርስሶ፤
ይሁና ከሆነ?
በመገርሰስ መሀል ራስ ሆኖ ከኖረ፤
መስማቱን ዘንግቶ
ወራጅ አለ እያሉት ዘግቶ ከበረረ፤
ለምን እንዳትይ?
አትስጊ ግዴለም
ዶሮ ጮኸ አልጮኸም መንጋቱ አይቀርም።
@getem
@getem
@kedir
።።።።።።።።።።።
(ከድር መሀመድ)
ገለጥ ሲልልኝ
ድርብርቡ አፈና፤ጨለማው ተገፎ፤
ሽኩቻ ለትግል
እንቅልፍ ሲነሳ፤በሀገሩ ለፍፎ፤
ምንም አትበይ
ዛሬ ቃላት አጥተሽ፤አፍሽ ቢቀየድም፤
አትስጊ ግዴለም
ዶሮ ጮኸ አልጮኸ፤መንጋቱ አይቀርም፤
እንደነቃሁ ገና
ሲነጋ ልነግርሽ ፤ከንፈሬን ላልሼ ቃላት ፈልግና፤
ሳስብ እፈራለው
ሚስጥር እንዳይሾልከኝ፤ቃል እንዳላዛባ ሳላስብሆነና፤
ምን አልባት
በነገርሽ መሃል ሌላን፤ብተነፍስ ከመሀል ቆይቼ፤
ቃል ግቢልኝ!
አዝልቀሽ ላትሰጪኝ ላሳደኳቸው ነፍስ ወስደሽ ለጅቦቼ፤
በነገርሽ መሀል?
አትስጊ ግዴለም!
ዶሮ ጮኸ አልጮኸም መንጋቱ አይቀርም፤
ይሄው ነው
በጅ ያሳደጉት ጅብ አጉራሽ እጁን ቢነክስ መልሶ፤
ዘመኑ ይሆናል!
ወላጁን ሰዉቶ ተሹሞ የሚኖር መንጎችን ገርስሶ፤
ይሁና ከሆነ?
በመገርሰስ መሀል ራስ ሆኖ ከኖረ፤
መስማቱን ዘንግቶ
ወራጅ አለ እያሉት ዘግቶ ከበረረ፤
ለምን እንዳትይ?
አትስጊ ግዴለም
ዶሮ ጮኸ አልጮኸም መንጋቱ አይቀርም።
@getem
@getem
@kedir
#ጥማት
በኮርማ ፣ በርችት ፣ ከምንቀበለው የዘመን መባቻ
ባርቲ ቡርቲ ወሬ ፥ በወገን ጥላቻ
እንደ ሀገር ኖሮ ፥ መሞት ለየብቻ
ምን አውቅልሽ በዝቶ.....
ውሎ ማደር ፈርተን ፥ በማጀት ጉልቻ
ቀናችንን ሳናምን
ጠጥተን ሳንረካ ፥ ጎርሰን ሳንጠግብ
ዛሬ ሳያከትም ፥ ለነገ ስናስብ
የሰቀቀን ጉርሻ ፥ ደጋግሞ እያነቀን
የኑሮ ውድነት ፥ በጠኔ እየናጠን
ዝም ባለ ሰፈር ፥ በፍርሀት ተጣብቀን
በጠራራ ፀሀይ ፥ ጨለማ አውሮን ፥ ምርኩዝ ተስፋ እያጣን
በልተን እንዳልበላ ፥ ስጋት እያከሳን
ካዲስ አመት በላይ ፥ ሰላም ነው የጠማን።
እንጂ!!
አሻፈረን ብንል ፥ ዘመን መች ይቆማል
ሲሻው የሳት እራት ፥ አልያ ዶሴ ገድል
የምንከትብበት
ባለ ሶስት መቶ ገፅ ፥ ብራና ያበጃል።
#ሰላማችን_ይብዛ
✍ #አብርሀም_ተክሉ
@getem
@getem
@lula_al_greeko
በኮርማ ፣ በርችት ፣ ከምንቀበለው የዘመን መባቻ
ባርቲ ቡርቲ ወሬ ፥ በወገን ጥላቻ
እንደ ሀገር ኖሮ ፥ መሞት ለየብቻ
ምን አውቅልሽ በዝቶ.....
ውሎ ማደር ፈርተን ፥ በማጀት ጉልቻ
ቀናችንን ሳናምን
ጠጥተን ሳንረካ ፥ ጎርሰን ሳንጠግብ
ዛሬ ሳያከትም ፥ ለነገ ስናስብ
የሰቀቀን ጉርሻ ፥ ደጋግሞ እያነቀን
የኑሮ ውድነት ፥ በጠኔ እየናጠን
ዝም ባለ ሰፈር ፥ በፍርሀት ተጣብቀን
በጠራራ ፀሀይ ፥ ጨለማ አውሮን ፥ ምርኩዝ ተስፋ እያጣን
በልተን እንዳልበላ ፥ ስጋት እያከሳን
ካዲስ አመት በላይ ፥ ሰላም ነው የጠማን።
እንጂ!!
አሻፈረን ብንል ፥ ዘመን መች ይቆማል
ሲሻው የሳት እራት ፥ አልያ ዶሴ ገድል
የምንከትብበት
ባለ ሶስት መቶ ገፅ ፥ ብራና ያበጃል።
#ሰላማችን_ይብዛ
✍ #አብርሀም_ተክሉ
@getem
@getem
@lula_al_greeko
#ሳቅና_እንባ😁😭
አትላወስ ፡ ሆዴ
እባክህ ፡ ሁን ፡ ደስተኛ
ዘንድሮ ፡ አልተገኘም
አርፎ ፡ የሚተኛ
አትጭስ ፡ አትብገን
አትላወስ ፡ ሆዴ
ኑሮና ፡ ተራራ
ይገፋል ፡ በዘዴ
ኸረ ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር
ፍቅር ፡ ጠፋ ፡ ይላሉ
አፍቃሪ ፡ አይደለም
ጓደኛ ፡ የሆነ ፡ ሁሉ
የዚህ ፡ አለም ፡ ነገር
በጣም ፡ ይገርመኛል
ልሙትልህ ፡ እንዳላለ
ሊገልህ ፡ ይመጣል
በክፉ ፡ ቀን ፡ ጊዜ
ፍቅር ፡ የት ፡ ይገኛል ።
አንድ ፡ ሁለት
እያለ ፡ እያለሳለሰ
ፍቅርም ፡ ጠፋ
ትንቢቱ ፡ ደረሰ
መከራና ፡ ደስታ
ማግኘትና ፡ ማጣት
ሰማይና ፡ ምድር
ጨለማና ፡ ንጋት
ፅድቅና ፡ ኩነኔ
አዝመራና ፡ አበባ
ወትሮም ፡ የነበረ ፡ ነው
ድሮም ፡ ሳቅና ፡ እንባ ።
ግጥም ፡- ኢሳ ፡ ሙሀመድ ፡ (ዳና)
@getem
@getem
@getem
አትላወስ ፡ ሆዴ
እባክህ ፡ ሁን ፡ ደስተኛ
ዘንድሮ ፡ አልተገኘም
አርፎ ፡ የሚተኛ
አትጭስ ፡ አትብገን
አትላወስ ፡ ሆዴ
ኑሮና ፡ ተራራ
ይገፋል ፡ በዘዴ
ኸረ ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር
ፍቅር ፡ ጠፋ ፡ ይላሉ
አፍቃሪ ፡ አይደለም
ጓደኛ ፡ የሆነ ፡ ሁሉ
የዚህ ፡ አለም ፡ ነገር
በጣም ፡ ይገርመኛል
ልሙትልህ ፡ እንዳላለ
ሊገልህ ፡ ይመጣል
በክፉ ፡ ቀን ፡ ጊዜ
ፍቅር ፡ የት ፡ ይገኛል ።
አንድ ፡ ሁለት
እያለ ፡ እያለሳለሰ
ፍቅርም ፡ ጠፋ
ትንቢቱ ፡ ደረሰ
መከራና ፡ ደስታ
ማግኘትና ፡ ማጣት
ሰማይና ፡ ምድር
ጨለማና ፡ ንጋት
ፅድቅና ፡ ኩነኔ
አዝመራና ፡ አበባ
ወትሮም ፡ የነበረ ፡ ነው
ድሮም ፡ ሳቅና ፡ እንባ ።
ግጥም ፡- ኢሳ ፡ ሙሀመድ ፡ (ዳና)
@getem
@getem
@getem
👍1
ፎቶ በ ቀለም እንዲሁም በ drawing ለማሳል
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 ማዘዝ ይቻላል ።
ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
ይህን እድል ይጠቀሙበት!
@seiloch
@seiloch
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 ማዘዝ ይቻላል ።
ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
ይህን እድል ይጠቀሙበት!
@seiloch
@seiloch
♡ ስሞት አትቅበረኝ ♡♡♡
በሂወት እያለሁ እንባዬን ካልጠረግህ ፣
በእኔ እንባ ማንባት ካላዘነ ልብህ ፣
ሰታመም ዝም ካልህ ፣
እራቤ ካልገባህ ፣
ጭንቀቴም ብሶቴም ከመሰለህ ተራ ፣
ድፍርሱ ሂወቴ በፍቅርህ ካልጠራ ፣
ደብዛዛዉ ሂወቴ በፍቅርህ ካልበራ ፣
ተልካሻዉ ኑሮዬን
ካላሰናዳከዉ ፣
የተደላደለ ቦታ ካላሲያዝከዉ ፣
ማየት የተሳነዉ
ፍቅሬን ካልመራሀዉ ፣
እዉነት እልሃለሁ ዉዴ...
ስሞት አትቅበረኝ ፣
እንባም አታንባልኝ ፣
ፀፀትም አትግባ
ይልቁንስ ፍቅሬ...
እንደ ሻማ ቀልጦ ፍቅሬ ሳያልቅብህ ፣
እጂጉን አምሮ ልቤ ሳይቆርጥብህ ፣
ስታመም አስታመኝ ፣
ሰከፋ አፅናናኝ ፣
ስወድቅ ደግፈኝ ፣
የጭንቀቴን ብሶት
የዉስጤን ተረዳኝ ፣
ድፍርሱን ሂወቴን
በፍቅርህ አጥራልኝ ፣
ደብዛዛዉ ሂወቴን
በፍቅርህ አብራልኝ ፣
ተልካሻዉ ኑሮዬ
ፈጥነህ አሰናዳዉ ፣
የተደላደለ ቦታዉን አሲዘዉ ፣
ማየት የተሳነዉ
ልቤን ይዘሀ ምራዉ ፣
ደስታና ፍቅርን ከልብ አስተምረኝ ፣
ሁል ጊዜ ሳቅልኝ ፣
ይሄ ካልሆነ ግን
ስሞት አትቅበረኝ ::
ምንጭ፦ ወንጌላዊት እሙ
=======================
ለ "ስሞት አትቅበረኝ" ግጥም ምላሽ
ከአያልቅበት ሰለሞን
እሙ በህይወት እስካለሽ እንባሽን አብሼ
ስታለቅሺ ሳይሽ ተንሰቅስቄ አልቅሼ
ስትዝኚ ዕያየሁ እጥፍ ካላዘንኩኝ
ምኑን ሰው ተባልኩኝ
ሢያምሽ ካላመመኝ
እራብሽ ካልራበኝ
ምኑን አፈቀርኩሽ ምኑን ወዳጅ ሆንኩኝ
ጭንቀትሽ ብሶትሽ ከመሰለኝ ተራ
ድፍርሱ ህይወትሽ በፍቅሬ ካልጠራ
ተልካሻው ኑሮሽን ካላሰናዳሁት
የተደላደለ ቦታ ካላሲያዝኩት
ምናል ባልተዋወቅን እላለሁኝ ዕኔ
ለፍቅርሽ መከታ ስላለመሆኔ
ይልቅስ አታስቢ ፍቅሬ
ቃል ልግባልሽ ዛሬ
ስታለቅሺ አልቅሼ ስታዝኝም አዝናለው
ባስለቀሰሽ ጉዳይ ዳኛም እሆናለው
እፋረደዋለው።
ፍቅርሽን ቀንበቀን በፍቅሬ አድሳለው
ምስቅልቅል ህይወትሽን ዘውትር አድሳለው
እታመንሻለው
አይንሽ አያለቅስም
ልብሽ አይቆዝምም
ፈገግታሽ አይፈዝም
የፊትሽም ፀዳል ከቶ አይደብዝዝም
ይኸውልሽ ፍቅሬ ቃል ልግባ ደግሜ
ፍቅርሽ ተሰራጭቷል ባካልና ደሜ
ሲያምሽ ያምመኛል ሥታዝኚም አዝናለው
ስታለቅሺ አልቅሼ ስትስቂም ስቃለው
በፊትሽ ብርሐን እኔም እደምቃለው
ነገርግን ፍቅሬ ሆይ ስሚኝ በጽሞና
ምናልባት ሚሆነውን አላውቀውምና
አድምጭ እንደገና
ምናልባት ይህ ቃሌን መጠበቅ ቢያቅተኝ
ለፍቅርሽ መከታ መሖን ቢያታክተኝ
ህይወትሽን ማቃናት ባልችል በስንፍና
ይሄ ወዳጅነት ከቶ አይሆንምና
አድምጭ እንደገና
በፍቅሬ ፍቅርሽን መፈውስ ቢሳነኝ
ሀዘንሽን ማዘን ከቶ ባይቻለኝ
ዕንባሽን አብሼ
ባንቺ ፈንታ አልቅሼ
ሀዘንሽን አዝኜ
ሥታባክኝ ባክኜ
ካልተገኝኁ እኔ
ስትሞች አላለቅስም
ለቅሶ አልቀመጥም
በሞትሽ አላዝንም
ይልቅስ አድምጭ ነግርሻለው
ስትሞቺ ሞታለው
እከተልሻለው
እዚሕ በበደልኩሽ ላይ ቤት እክስሻለው
እመኝኝ ቃሌ ነው።
ምንጭ፦ አያልቅበት ሰለሞን
@getem
@getem
@getem
በሂወት እያለሁ እንባዬን ካልጠረግህ ፣
በእኔ እንባ ማንባት ካላዘነ ልብህ ፣
ሰታመም ዝም ካልህ ፣
እራቤ ካልገባህ ፣
ጭንቀቴም ብሶቴም ከመሰለህ ተራ ፣
ድፍርሱ ሂወቴ በፍቅርህ ካልጠራ ፣
ደብዛዛዉ ሂወቴ በፍቅርህ ካልበራ ፣
ተልካሻዉ ኑሮዬን
ካላሰናዳከዉ ፣
የተደላደለ ቦታ ካላሲያዝከዉ ፣
ማየት የተሳነዉ
ፍቅሬን ካልመራሀዉ ፣
እዉነት እልሃለሁ ዉዴ...
ስሞት አትቅበረኝ ፣
እንባም አታንባልኝ ፣
ፀፀትም አትግባ
ይልቁንስ ፍቅሬ...
እንደ ሻማ ቀልጦ ፍቅሬ ሳያልቅብህ ፣
እጂጉን አምሮ ልቤ ሳይቆርጥብህ ፣
ስታመም አስታመኝ ፣
ሰከፋ አፅናናኝ ፣
ስወድቅ ደግፈኝ ፣
የጭንቀቴን ብሶት
የዉስጤን ተረዳኝ ፣
ድፍርሱን ሂወቴን
በፍቅርህ አጥራልኝ ፣
ደብዛዛዉ ሂወቴን
በፍቅርህ አብራልኝ ፣
ተልካሻዉ ኑሮዬ
ፈጥነህ አሰናዳዉ ፣
የተደላደለ ቦታዉን አሲዘዉ ፣
ማየት የተሳነዉ
ልቤን ይዘሀ ምራዉ ፣
ደስታና ፍቅርን ከልብ አስተምረኝ ፣
ሁል ጊዜ ሳቅልኝ ፣
ይሄ ካልሆነ ግን
ስሞት አትቅበረኝ ::
ምንጭ፦ ወንጌላዊት እሙ
=======================
ለ "ስሞት አትቅበረኝ" ግጥም ምላሽ
ከአያልቅበት ሰለሞን
እሙ በህይወት እስካለሽ እንባሽን አብሼ
ስታለቅሺ ሳይሽ ተንሰቅስቄ አልቅሼ
ስትዝኚ ዕያየሁ እጥፍ ካላዘንኩኝ
ምኑን ሰው ተባልኩኝ
ሢያምሽ ካላመመኝ
እራብሽ ካልራበኝ
ምኑን አፈቀርኩሽ ምኑን ወዳጅ ሆንኩኝ
ጭንቀትሽ ብሶትሽ ከመሰለኝ ተራ
ድፍርሱ ህይወትሽ በፍቅሬ ካልጠራ
ተልካሻው ኑሮሽን ካላሰናዳሁት
የተደላደለ ቦታ ካላሲያዝኩት
ምናል ባልተዋወቅን እላለሁኝ ዕኔ
ለፍቅርሽ መከታ ስላለመሆኔ
ይልቅስ አታስቢ ፍቅሬ
ቃል ልግባልሽ ዛሬ
ስታለቅሺ አልቅሼ ስታዝኝም አዝናለው
ባስለቀሰሽ ጉዳይ ዳኛም እሆናለው
እፋረደዋለው።
ፍቅርሽን ቀንበቀን በፍቅሬ አድሳለው
ምስቅልቅል ህይወትሽን ዘውትር አድሳለው
እታመንሻለው
አይንሽ አያለቅስም
ልብሽ አይቆዝምም
ፈገግታሽ አይፈዝም
የፊትሽም ፀዳል ከቶ አይደብዝዝም
ይኸውልሽ ፍቅሬ ቃል ልግባ ደግሜ
ፍቅርሽ ተሰራጭቷል ባካልና ደሜ
ሲያምሽ ያምመኛል ሥታዝኚም አዝናለው
ስታለቅሺ አልቅሼ ስትስቂም ስቃለው
በፊትሽ ብርሐን እኔም እደምቃለው
ነገርግን ፍቅሬ ሆይ ስሚኝ በጽሞና
ምናልባት ሚሆነውን አላውቀውምና
አድምጭ እንደገና
ምናልባት ይህ ቃሌን መጠበቅ ቢያቅተኝ
ለፍቅርሽ መከታ መሖን ቢያታክተኝ
ህይወትሽን ማቃናት ባልችል በስንፍና
ይሄ ወዳጅነት ከቶ አይሆንምና
አድምጭ እንደገና
በፍቅሬ ፍቅርሽን መፈውስ ቢሳነኝ
ሀዘንሽን ማዘን ከቶ ባይቻለኝ
ዕንባሽን አብሼ
ባንቺ ፈንታ አልቅሼ
ሀዘንሽን አዝኜ
ሥታባክኝ ባክኜ
ካልተገኝኁ እኔ
ስትሞች አላለቅስም
ለቅሶ አልቀመጥም
በሞትሽ አላዝንም
ይልቅስ አድምጭ ነግርሻለው
ስትሞቺ ሞታለው
እከተልሻለው
እዚሕ በበደልኩሽ ላይ ቤት እክስሻለው
እመኝኝ ቃሌ ነው።
ምንጭ፦ አያልቅበት ሰለሞን
@getem
@getem
@getem
ድምፃዊ #ሙሉአለም_ተክሌ ወንድማችን ነው። ከጎን ለመቆም ሁላችንም ጊዜ አንጠብቅ
ዛሬ አሁን ለምንወደው ድምፃዊ እገዛችንን እናድርግ !
ሙሌ #በኩላሊት ህመም #ዲያልሲስ ጀምሯል
ለጥያቄ እና ለመርዳት
ስልክ:- +251911572276
ንግድ ባንክ (CBE)
mulualem takele
1000182044184
ከጎን ሆናችሁ ሀሳብ ለመስጠት ይሄን
group ተጠቀሙ https://tttttt.me/joinchat/JSJyPhNcOTNP5V8x4LOXOw
ዛሬ አሁን ለምንወደው ድምፃዊ እገዛችንን እናድርግ !
ሙሌ #በኩላሊት ህመም #ዲያልሲስ ጀምሯል
ለጥያቄ እና ለመርዳት
ስልክ:- +251911572276
ንግድ ባንክ (CBE)
mulualem takele
1000182044184
ከጎን ሆናችሁ ሀሳብ ለመስጠት ይሄን
group ተጠቀሙ https://tttttt.me/joinchat/JSJyPhNcOTNP5V8x4LOXOw