ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ሳቅና_እንባ😁😭

አትላወስ ፡ ሆዴ
እባክህ ፡ ሁን ፡ ደስተኛ
ዘንድሮ ፡ አልተገኘም
አርፎ ፡ የሚተኛ
አትጭስ ፡ አትብገን
አትላወስ ፡ ሆዴ
ኑሮና ፡ ተራራ
ይገፋል ፡ በዘዴ
ኸረ ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር
ፍቅር ፡ ጠፋ ፡ ይላሉ
አፍቃሪ ፡ አይደለም
ጓደኛ ፡ የሆነ ፡ ሁሉ
የዚህ ፡ አለም ፡ ነገር
በጣም ፡ ይገርመኛል
ልሙትልህ ፡ እንዳላለ
ሊገልህ ፡ ይመጣል
በክፉ ፡ ቀን ፡ ጊዜ
ፍቅር ፡ የት ፡ ይገኛል ።
አንድ ፡ ሁለት
እያለ ፡ እያለሳለሰ
ፍቅርም ፡ ጠፋ
ትንቢቱ ፡ ደረሰ
መከራና ፡ ደስታ
ማግኘትና ፡ ማጣት
ሰማይና ፡ ምድር
ጨለማና ፡ ንጋት
ፅድቅና ፡ ኩነኔ
አዝመራና ፡ አበባ
ወትሮም ፡ የነበረ ፡ ነው
ድሮም ፡ ሳቅናእንባ


ግጥም ፡- ኢሳ ፡ ሙሀመድ ፡ (ዳና)

@getem
@getem
@getem
👍1