"ከአያት ቅድም አያቴ ፣ ሞያ እንጂ ቁምነገር
ቀልድን አልተማርኩም ፣ በእምነት እና በሀገር
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ጠብመንጃን ፣ቆንጨራን ፣ ገጀራን ፣ ዱላን፣ የፈላ ውሃን ፣ ዛቻን እና ስድብን ስለምን ከዚህ ሰልፍ ትፈልጋላችሁ? መሥቀል እና ዝማሬ እንጂ ሌላው በዚህ የለም!!!
#መሥከረም_አራት!!!
።።።
""ወይ መካ ላይ ልምጣ ፣ ወይ ነይ ጎሎጎታ
ፍቅር የትም አለ ፣ ሳይወስነው ቦታ !!!"
።።።።
💚💛❤️
ለሀገራችን ሠላም ለህዝቧም ፍቅር ይብዛ!!!
@getem
@getem
@getem
ቀልድን አልተማርኩም ፣ በእምነት እና በሀገር
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ጠብመንጃን ፣ቆንጨራን ፣ ገጀራን ፣ ዱላን፣ የፈላ ውሃን ፣ ዛቻን እና ስድብን ስለምን ከዚህ ሰልፍ ትፈልጋላችሁ? መሥቀል እና ዝማሬ እንጂ ሌላው በዚህ የለም!!!
#መሥከረም_አራት!!!
።።።
""ወይ መካ ላይ ልምጣ ፣ ወይ ነይ ጎሎጎታ
ፍቅር የትም አለ ፣ ሳይወስነው ቦታ !!!"
።።።።
💚💛❤️
ለሀገራችን ሠላም ለህዝቧም ፍቅር ይብዛ!!!
@getem
@getem
@getem
🔥1
እንቁ ዕጣሽ ጣጣሽ
^^^^¿^^^^^¿^^^^^^
ድሮ … ጥንት
ጥሩ መሬት እህል የሚያፈራ
ብርቱ አራሽ ዘር የሚዘራ
አማኝ ምዕመን አምላኩን ሚፈራ
አስተዋይ መሪ ህዝቡን የሚመራ
በነበረሽ ጊዜ
ረሀብ ኮስሶ ጥጋብ ተኮፍሶ
የጎረቤት ጓዳ
የራስ እስኪመስል ሰቆቃ ተደርምሶ
በአብሮ መብላት ባህል
በመተሳሰብ ብሂል ክብርሽ ታድሷል
ዕጣሽ ሰምሮ ፍቅር ነግሷል
ዛሬ …
ክረምት ገብቶ
ከቤትህ ስትወጣ እህል ልትዘራ
ሲለፈፍ ትሰማለህ ስለህዝብ ቆጠራ
ግንቦት ደርሶልህ
ክንድህን አበርትተህ ሞፈር ስታነሳ
ማረሻ ማፈሻ
አርማ ይሆናል ለምርጫ ቅስቀሳ
ምትመርጠውን ሳታውቅ
የተመራጭ ብዛት ከብሔር ይበልጣል
በዚህ ስትወዛገብ
ክረምቱ ጠልቆ ፀደይ ይወጣል
ለሀገር ሲታሰብ
ማረስ ተረስቶ ጓሮ ይሳሳል
የኑሮ ውድነት ጣሪያ ይደርሳል
የት ተሂዶ
አቤት ይባላል ማንስ ይከሰሳል
በሚል ጥያቄ
የመረረው ልጅሽ በቁጭት ይታመሳል
እንቁ ዕጣሽ ሲላሽቅ
እንቁ ጣጣሽ ይነግሳል
ኢትዮጵያዬ …
ተባረኪ ሲልሽ
እጆችሽን እንድትዘረጊ አምላክ ይፈቅዳል
የሰንደቅሽን አርማ
በማርያም መቀነት ሰማይ ላይ ይወልዳል
ዕጣሽን ሲያሳምር
የፍቅር ማማ ላይ ጎህ ይቀዳል
በብርሀን ፋና ህዝብሽን አጥምቆ
በእምነት ዘውድ ሰላምሽን አድምቆ
ያኖረሽ አምላክ ዕጣሽን ሲያጠፋ
ለማስመሰል ያጨሽው ዕጣንሽ ከረፋ
የአንድነትሽ ቅዳሴ ልዩነቱ ሰፋ
በዚህም በዚያም መጥፊያሽን ሚያስሱ
የግላቸውን ቤተ ክህነት ሊያቋቁሙ ተነሱ
ሀገሬ …
ጥፊ ያለሽ ጊዜ እምነትሽ ይፈርሳል
እንቁ ዕጣሽ ሲከዳሽ
እንቁ ጣጣሽ ይነግሳል
በፊት …
ለሰው ልጅ
ክብር ይሰጣል ከሁሉም ልቆ
ሁሉን ከዋኝ
ሁሉን አድራጊ መሆኑ ታውቆ
ዛሬ …
ለልማት ተብሎ ቤት ይፈርሳል
የሰው ልጅ ታንቆ ከተማ ይታደሳል
መጠለያ ያጣ
የዋህ ወገኔ ጎዳና ይፈሳል
የከተማን ውበት
አጠለሸ ተብሎ ተጋፎ ይነሳል
ሚዲያ ይለፍፋል
ለአረንጓዴ ልማት ተሰማራ ብሎ
በውሃ ናፍቆት ህዝብን በጥም ገሎ
ይታለፍ ይመስል
ከችግር አረንቋ ችግኝ ተጠልሎ
እምዬ …
ብዙ ነው ፈታኝሽ
ከባድ ነው ፈተናሽ
ብዙ ነው መካሪሽ
ከባድ ነው መከራሽ
ብዙ ነው ጣይˆሽ
ብሩህ ነው ፀሀይሽ
ብዙ ነው ጨማቂሽ
ጣፋጭ ነው ጭማቂሽ
ያውም … ካልመረረ
… ካልናረ
ሀገሬ …
ተተኪሽን ተኪ
የትምህርት ስርዓትሽ ፍኖቱ ተጣሟል
መርቆ ሸኝ እንጅ
የተመረቀ ተቀባይ እጅ ከስሟል
ፈተና ይሰረቃል
ውጤት ይሰረዛል
የሰው ህይወት ለቁማር ይረከዛል
ይኼውልሽ …
የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ተፈታኝ
በማሽን ስህተት ውጤቱ ሲናኝ
ስህተትን ለማረም
የትምህርት አይነት ተለይቶ ይቀነሳል
እንቁ ዕጣሽ ሲከስም
እንቁ ጣጣሽ ይነግሳል
የኳስሽ እድገት ቁልቁል ይፈሳል
የክለብሽ ስም
የክልል ካባ በላዩ ለብሷል
ደጋፊሽ ሁሌ
ክለቡን ወግኖ ለጥል ይነሳል
ይኸውልሽ …
በቱርክ ወረራ ህዝባችን መክኖ
በኳስ ቁማር ልቡ በግኖ … ስራ አቁሞ
ያለፋበትን ገንዘብ እያሳደደ
በከንቱ ተስፋ
ጨጓራውን ልጦ ህመም ወለደ
መከረኛው ልጅሽ
ለውድቀት ክብር ይኸው ተዘጋጅቷል
እንቁ ዕጣሽን ትቶ
እንቁ ጣጣሽን ይጠብቃል
@getem
@getem
@getem
^^^^¿^^^^^¿^^^^^^
ድሮ … ጥንት
ጥሩ መሬት እህል የሚያፈራ
ብርቱ አራሽ ዘር የሚዘራ
አማኝ ምዕመን አምላኩን ሚፈራ
አስተዋይ መሪ ህዝቡን የሚመራ
በነበረሽ ጊዜ
ረሀብ ኮስሶ ጥጋብ ተኮፍሶ
የጎረቤት ጓዳ
የራስ እስኪመስል ሰቆቃ ተደርምሶ
በአብሮ መብላት ባህል
በመተሳሰብ ብሂል ክብርሽ ታድሷል
ዕጣሽ ሰምሮ ፍቅር ነግሷል
ዛሬ …
ክረምት ገብቶ
ከቤትህ ስትወጣ እህል ልትዘራ
ሲለፈፍ ትሰማለህ ስለህዝብ ቆጠራ
ግንቦት ደርሶልህ
ክንድህን አበርትተህ ሞፈር ስታነሳ
ማረሻ ማፈሻ
አርማ ይሆናል ለምርጫ ቅስቀሳ
ምትመርጠውን ሳታውቅ
የተመራጭ ብዛት ከብሔር ይበልጣል
በዚህ ስትወዛገብ
ክረምቱ ጠልቆ ፀደይ ይወጣል
ለሀገር ሲታሰብ
ማረስ ተረስቶ ጓሮ ይሳሳል
የኑሮ ውድነት ጣሪያ ይደርሳል
የት ተሂዶ
አቤት ይባላል ማንስ ይከሰሳል
በሚል ጥያቄ
የመረረው ልጅሽ በቁጭት ይታመሳል
እንቁ ዕጣሽ ሲላሽቅ
እንቁ ጣጣሽ ይነግሳል
ኢትዮጵያዬ …
ተባረኪ ሲልሽ
እጆችሽን እንድትዘረጊ አምላክ ይፈቅዳል
የሰንደቅሽን አርማ
በማርያም መቀነት ሰማይ ላይ ይወልዳል
ዕጣሽን ሲያሳምር
የፍቅር ማማ ላይ ጎህ ይቀዳል
በብርሀን ፋና ህዝብሽን አጥምቆ
በእምነት ዘውድ ሰላምሽን አድምቆ
ያኖረሽ አምላክ ዕጣሽን ሲያጠፋ
ለማስመሰል ያጨሽው ዕጣንሽ ከረፋ
የአንድነትሽ ቅዳሴ ልዩነቱ ሰፋ
በዚህም በዚያም መጥፊያሽን ሚያስሱ
የግላቸውን ቤተ ክህነት ሊያቋቁሙ ተነሱ
ሀገሬ …
ጥፊ ያለሽ ጊዜ እምነትሽ ይፈርሳል
እንቁ ዕጣሽ ሲከዳሽ
እንቁ ጣጣሽ ይነግሳል
በፊት …
ለሰው ልጅ
ክብር ይሰጣል ከሁሉም ልቆ
ሁሉን ከዋኝ
ሁሉን አድራጊ መሆኑ ታውቆ
ዛሬ …
ለልማት ተብሎ ቤት ይፈርሳል
የሰው ልጅ ታንቆ ከተማ ይታደሳል
መጠለያ ያጣ
የዋህ ወገኔ ጎዳና ይፈሳል
የከተማን ውበት
አጠለሸ ተብሎ ተጋፎ ይነሳል
ሚዲያ ይለፍፋል
ለአረንጓዴ ልማት ተሰማራ ብሎ
በውሃ ናፍቆት ህዝብን በጥም ገሎ
ይታለፍ ይመስል
ከችግር አረንቋ ችግኝ ተጠልሎ
እምዬ …
ብዙ ነው ፈታኝሽ
ከባድ ነው ፈተናሽ
ብዙ ነው መካሪሽ
ከባድ ነው መከራሽ
ብዙ ነው ጣይˆሽ
ብሩህ ነው ፀሀይሽ
ብዙ ነው ጨማቂሽ
ጣፋጭ ነው ጭማቂሽ
ያውም … ካልመረረ
… ካልናረ
ሀገሬ …
ተተኪሽን ተኪ
የትምህርት ስርዓትሽ ፍኖቱ ተጣሟል
መርቆ ሸኝ እንጅ
የተመረቀ ተቀባይ እጅ ከስሟል
ፈተና ይሰረቃል
ውጤት ይሰረዛል
የሰው ህይወት ለቁማር ይረከዛል
ይኼውልሽ …
የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ተፈታኝ
በማሽን ስህተት ውጤቱ ሲናኝ
ስህተትን ለማረም
የትምህርት አይነት ተለይቶ ይቀነሳል
እንቁ ዕጣሽ ሲከስም
እንቁ ጣጣሽ ይነግሳል
የኳስሽ እድገት ቁልቁል ይፈሳል
የክለብሽ ስም
የክልል ካባ በላዩ ለብሷል
ደጋፊሽ ሁሌ
ክለቡን ወግኖ ለጥል ይነሳል
ይኸውልሽ …
በቱርክ ወረራ ህዝባችን መክኖ
በኳስ ቁማር ልቡ በግኖ … ስራ አቁሞ
ያለፋበትን ገንዘብ እያሳደደ
በከንቱ ተስፋ
ጨጓራውን ልጦ ህመም ወለደ
መከረኛው ልጅሽ
ለውድቀት ክብር ይኸው ተዘጋጅቷል
እንቁ ዕጣሽን ትቶ
እንቁ ጣጣሽን ይጠብቃል
@getem
@getem
@getem
ግጥም እንደዚህ ሲሆን እንዴት የልብ ያደርሳል❤️ለነፍስም ይቀርባል.... ግጥሙ ውስጥ ያለው ፍልስፍናው ሲጣፍጥ ፣ ያገማሽራልም ባነበው ባነው አልጠገብኩትም ....ማሜዋ በረካ ሁን አቦ!!!
( እልል አሮጌ ዓመት)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሃበሻ እና ዘመን
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በሃበሻ ምድር
ከኑባሬ አዳም እስከዛሬ ድረስ
ያደስንውን ዓመት ውሉን ስናጤነው ።
በዘመን አዙሪት የአድስ አመት መምጣት
ሲገባኝ ተፍሲሩ ፍቹን ስተምነው፣
ከአምና የተረፈ የልጅነት ወዝን የኛነትን እሸት
ለተራበው አዲስ ወስዶ መገበር ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እናም ይገርማል ሃበሻ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እንደ አደይ አበባ ኑረቱ ሳይፈካ
በፈኩ ወራቶች ታደስኩኝ ይልሃል፣
በእግረ መንገድ ኑሮ ቀናቶች ሸምነው
አመት ሆነህ ሲሉት እልልታ ያቀልጣል፣
ዳግም ለሚመጣ ለዘመን ቋጠሮ
ድጋሜ እማይመጣ እራሱን ይሰዋል፣
ከእድሜው ተቀንሶ የተወራረደ
የእድሜውን ጎደሎ በፌሽታ ያውጃል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዋህ ነው ሃበሻ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዘመን ሩጫ ከትላንት አባሮ ለማያውቀው
ነገ ለመጪው ዘንድሮ ሲድረው ጎትቶ፣
ባድስ አመት ብስራት ማርጀት ይሉት ሸማ
ወዶ መደረቡን መልበሱን ዘንግቶ።
እ
ል
ል
አድስ ዓመት
እ
ል
ል
እንቁጣጣሽ
ማለት ይቀናዋል፣
በአድስ አመት ጀርባ እርጅናና ሞቱን
በእልልታ እያጀበ ያወራርደዋል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሞኝ ነው ሃበሻ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ተመለስ ብትለው ለማይሰማ ዘመን
እንኳን መጣህ ብሎ ድግስ ያሰናዳል፣
ያልተደካን ዘመን ቁጥር ለመጨመር
የዘመኑን ድካ እድሜውን ይንዳል።
ይሄው እስከዛሬ
ሃበሻና እልልታ በያድስ አመቱ
ቀጠሮ እየያዙ እኩል ቢታደሱም፣
ከአንዱ እየቀነሱ በተቀናሽ ሂሳብ
አንዱን ከማፈርጠም ተሻግረው አያውቁም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እናም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እ
ል
ል
አሮጌ ዓመት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሃበሻን ኑረት ከፍታ እሚያሳየን
ፍካት የሚያስዋጀን ቅፅበት እስኪመጣ፣
የዘመን ትከሻ አየገፈተረኝ እድሜየን ገብሬ
ከኖርኩበት ዘመን ከአሮጌው ስወጣ።
ባዶ እጁን ለመጣ ላልኖርኩበት አድስ
አሮጌውና አምና አላማውምና፣
ከአድስነቱ ጋር አድስ እስኪያመጣ
እ
ል
ል
አሮጌ ዓመት
እንኳን ኖርኩኝ አምና።
እ
ል
ል
አሮጌ ዓመት!!!!!!!!!!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሙሃመድ ሰኢድ💚💛❤️
ጷግሜ 5/13/2011
@getem
@getem
@balmbaras
( እልል አሮጌ ዓመት)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሃበሻ እና ዘመን
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በሃበሻ ምድር
ከኑባሬ አዳም እስከዛሬ ድረስ
ያደስንውን ዓመት ውሉን ስናጤነው ።
በዘመን አዙሪት የአድስ አመት መምጣት
ሲገባኝ ተፍሲሩ ፍቹን ስተምነው፣
ከአምና የተረፈ የልጅነት ወዝን የኛነትን እሸት
ለተራበው አዲስ ወስዶ መገበር ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እናም ይገርማል ሃበሻ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እንደ አደይ አበባ ኑረቱ ሳይፈካ
በፈኩ ወራቶች ታደስኩኝ ይልሃል፣
በእግረ መንገድ ኑሮ ቀናቶች ሸምነው
አመት ሆነህ ሲሉት እልልታ ያቀልጣል፣
ዳግም ለሚመጣ ለዘመን ቋጠሮ
ድጋሜ እማይመጣ እራሱን ይሰዋል፣
ከእድሜው ተቀንሶ የተወራረደ
የእድሜውን ጎደሎ በፌሽታ ያውጃል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዋህ ነው ሃበሻ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዘመን ሩጫ ከትላንት አባሮ ለማያውቀው
ነገ ለመጪው ዘንድሮ ሲድረው ጎትቶ፣
ባድስ አመት ብስራት ማርጀት ይሉት ሸማ
ወዶ መደረቡን መልበሱን ዘንግቶ።
እ
ል
ል
አድስ ዓመት
እ
ል
ል
እንቁጣጣሽ
ማለት ይቀናዋል፣
በአድስ አመት ጀርባ እርጅናና ሞቱን
በእልልታ እያጀበ ያወራርደዋል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሞኝ ነው ሃበሻ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ተመለስ ብትለው ለማይሰማ ዘመን
እንኳን መጣህ ብሎ ድግስ ያሰናዳል፣
ያልተደካን ዘመን ቁጥር ለመጨመር
የዘመኑን ድካ እድሜውን ይንዳል።
ይሄው እስከዛሬ
ሃበሻና እልልታ በያድስ አመቱ
ቀጠሮ እየያዙ እኩል ቢታደሱም፣
ከአንዱ እየቀነሱ በተቀናሽ ሂሳብ
አንዱን ከማፈርጠም ተሻግረው አያውቁም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እናም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እ
ል
ል
አሮጌ ዓመት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሃበሻን ኑረት ከፍታ እሚያሳየን
ፍካት የሚያስዋጀን ቅፅበት እስኪመጣ፣
የዘመን ትከሻ አየገፈተረኝ እድሜየን ገብሬ
ከኖርኩበት ዘመን ከአሮጌው ስወጣ።
ባዶ እጁን ለመጣ ላልኖርኩበት አድስ
አሮጌውና አምና አላማውምና፣
ከአድስነቱ ጋር አድስ እስኪያመጣ
እ
ል
ል
አሮጌ ዓመት
እንኳን ኖርኩኝ አምና።
እ
ል
ል
አሮጌ ዓመት!!!!!!!!!!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሙሃመድ ሰኢድ💚💛❤️
ጷግሜ 5/13/2011
@getem
@getem
@balmbaras
ግጥም ብቻ 📘
Photo
የተረት መሠረት
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አባቶች እናቶች
በፍቅር ተጋግዘው ፣ ያቆሙልን እውነት
በዘመን ጠልሽቶ...
ለእኛ ለልጆች ፣ ይመስለናል ተረት፡፡
።።።።።።
የኛ ትልቅ ችግር ፣ የኛ ትልቅ ህመም
መሰረት ሳንይዝ.
"የመሰረት" ብሎ ፣" እሺ" እያሉ ማዝገም፡፡
።።።።።።፣
ተረት ተረት
"የመሰረት"
አንድ ሀገር ነበረች
"እሺ"
እምነትን ከፍቅር ፣ ገምዳ ያስተማረች፡፡
"እሺ"
አናም በዚች ሀገር...
ሙስሊሞች በእምነት ፣ መስጅድ ሲገነቡ
ክርስቲያኖች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ምሶሶ ሲያቀርቡ፡፡
"እሺ"
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናም በዚች ሀገር...
ክርስቲያኖች በምነት ፣ ቤተስኪያን ሲያንፁ
ሙስሊሞች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ጉልላት ሲቀርፁ፡፡
"እሺ"
እናም በዚ መልኩ ፣ ሲኖሩ ሰኖሩ
እንደተዋደዱ እንደተፋቀሩ
እንደተጋገዙ እንደተባበሩ
መሰረት እንድናይ...
አንዋር ከራጉኤል ፣ ተጎራብተው ቀሩ
"እሺ"
"እሺ" ማለት ጥሩ
መሰረት ሳይዙ ...
የመሰረት ብሎ ፣ መኖር ነው ችግሩ!!!
።።።።።
።።።።።
በኮልፌ ጠሮ የሚገኝ የኡስማን በስጅድ እና የስላሴ ቤተ ክርስቲያን ጉርብትና።
#ሼር ለሁሉም!!!
@getem
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አባቶች እናቶች
በፍቅር ተጋግዘው ፣ ያቆሙልን እውነት
በዘመን ጠልሽቶ...
ለእኛ ለልጆች ፣ ይመስለናል ተረት፡፡
።።።።።።
የኛ ትልቅ ችግር ፣ የኛ ትልቅ ህመም
መሰረት ሳንይዝ.
"የመሰረት" ብሎ ፣" እሺ" እያሉ ማዝገም፡፡
።።።።።።፣
ተረት ተረት
"የመሰረት"
አንድ ሀገር ነበረች
"እሺ"
እምነትን ከፍቅር ፣ ገምዳ ያስተማረች፡፡
"እሺ"
አናም በዚች ሀገር...
ሙስሊሞች በእምነት ፣ መስጅድ ሲገነቡ
ክርስቲያኖች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ምሶሶ ሲያቀርቡ፡፡
"እሺ"
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናም በዚች ሀገር...
ክርስቲያኖች በምነት ፣ ቤተስኪያን ሲያንፁ
ሙስሊሞች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ጉልላት ሲቀርፁ፡፡
"እሺ"
እናም በዚ መልኩ ፣ ሲኖሩ ሰኖሩ
እንደተዋደዱ እንደተፋቀሩ
እንደተጋገዙ እንደተባበሩ
መሰረት እንድናይ...
አንዋር ከራጉኤል ፣ ተጎራብተው ቀሩ
"እሺ"
"እሺ" ማለት ጥሩ
መሰረት ሳይዙ ...
የመሰረት ብሎ ፣ መኖር ነው ችግሩ!!!
።።።።።
።።።።።
በኮልፌ ጠሮ የሚገኝ የኡስማን በስጅድ እና የስላሴ ቤተ ክርስቲያን ጉርብትና።
#ሼር ለሁሉም!!!
@getem
@getem
@getem
=== ጓደኛዬ እምለው ====
ወረትን አርቆ ከእኔ ተጎዳኝቶ፣
የጀርባ ሹክሹክታን እርግፍ እድርጎ ትቶ፤
ብከፋ ጠይቆ ብሳሳት አርሞ፣
እንደ እናት እንደ አባት ገስጾ ኮርኩሞ፤
የሚያቃናኝን ነው፣
ጓደኛዬ እምለው።
አስተዋይ አሳቢ ክፋት የሌለበት፣
ዝብርቅርቅ ባህሪ የማይታይበት፤
ዛሬም ነገም ፍፁም የማይቀያየር፣
ቁልፉን ያልደበቀ የልቦናውን በር፤
መንፈሰ ጠንካራ የፀና አቋም ያለው፣
ይህ ነው ጓደኛዬ ምርጫዬ ማደርገው፤
ርኅሩኅ አዛኝ ተፈጥሮን አፍቃሪ፣
በእውነት ተመርኩዞ እውነት ተናጋሪ፤
ደስታም ሆነ ሀዘን ቢፈራረቅብኝ፣
አለሁህ የሚለኝ በጣም የማይርቀኝ፤
እምነቱና እምነቴ ልዩነትን ፍቀው፣
የሚሄድ ከሆነ በአንድነት ተሳስረው፣
እስከ እለቴ ሞቴ ጓደኛዬ እሱ ነው።
@getem
@getem
@getem
ወረትን አርቆ ከእኔ ተጎዳኝቶ፣
የጀርባ ሹክሹክታን እርግፍ እድርጎ ትቶ፤
ብከፋ ጠይቆ ብሳሳት አርሞ፣
እንደ እናት እንደ አባት ገስጾ ኮርኩሞ፤
የሚያቃናኝን ነው፣
ጓደኛዬ እምለው።
አስተዋይ አሳቢ ክፋት የሌለበት፣
ዝብርቅርቅ ባህሪ የማይታይበት፤
ዛሬም ነገም ፍፁም የማይቀያየር፣
ቁልፉን ያልደበቀ የልቦናውን በር፤
መንፈሰ ጠንካራ የፀና አቋም ያለው፣
ይህ ነው ጓደኛዬ ምርጫዬ ማደርገው፤
ርኅሩኅ አዛኝ ተፈጥሮን አፍቃሪ፣
በእውነት ተመርኩዞ እውነት ተናጋሪ፤
ደስታም ሆነ ሀዘን ቢፈራረቅብኝ፣
አለሁህ የሚለኝ በጣም የማይርቀኝ፤
እምነቱና እምነቴ ልዩነትን ፍቀው፣
የሚሄድ ከሆነ በአንድነት ተሳስረው፣
እስከ እለቴ ሞቴ ጓደኛዬ እሱ ነው።
@getem
@getem
@getem
አገር ዕንቁጣጣሽ!
(በዕውቀቱ ሥዩም)
..
የ’ዳ ክንድሽ አቅፎኝ
ያሳር ክንፍሽ አቅፎኝ
እንቁሽን ስመኘው
ጣጣሽ ብቻ ተርፎኝ
መኖርን ስፈራ - መሞትም ስፈራ
ካየር ንብረት በቀር - ንብረት ሳላፈራ
ወሩ ተጠራቅሞ - አንድ ደርዘን ሞልቶ
እንደባለጌ ልጅ - በሩን በግሩ ከፍቶ
አዲስ ዘመን ገባ
አዲስ አመት ገባ
ያለ መስቀል ወፎች... ያለ አደይ አበባ።
በግዜር ሰራሽ ማማ፣
ቁራ ብቻ ሰፍሯል
የመስቀል ወፍማ፣
ወይ አገር ለውጧል
ወይ ልብሱን ቀይሯል።
.
አዲስ አመት ገባ...
በቄጤማ ምትክ - ቡልኬት ጎዝጉዞ
በቅፍ አደይ ምትክ -ጉንጉን ሽቦ ይዞ
በሉባንጃ ምትክ- አቡዋራ እያጤሰ
በፈንድሻ ምትክ - ጠጠር እያፈሰ።
.
አዲስ አመት ገባ...
አዲስ እንዲህ ዋዛ
ተፈጥሮ በውበት - መንፈሴን ሳይገዛ
በመአዛው ሳይዋጅ፣
መስከረም መግባቱን - በሬድዮ ልስማው?
እንደ መንግስት አዋጅ።
@getem
@getem
@getem
(በዕውቀቱ ሥዩም)
..
የ’ዳ ክንድሽ አቅፎኝ
ያሳር ክንፍሽ አቅፎኝ
እንቁሽን ስመኘው
ጣጣሽ ብቻ ተርፎኝ
መኖርን ስፈራ - መሞትም ስፈራ
ካየር ንብረት በቀር - ንብረት ሳላፈራ
ወሩ ተጠራቅሞ - አንድ ደርዘን ሞልቶ
እንደባለጌ ልጅ - በሩን በግሩ ከፍቶ
አዲስ ዘመን ገባ
አዲስ አመት ገባ
ያለ መስቀል ወፎች... ያለ አደይ አበባ።
በግዜር ሰራሽ ማማ፣
ቁራ ብቻ ሰፍሯል
የመስቀል ወፍማ፣
ወይ አገር ለውጧል
ወይ ልብሱን ቀይሯል።
.
አዲስ አመት ገባ...
በቄጤማ ምትክ - ቡልኬት ጎዝጉዞ
በቅፍ አደይ ምትክ -ጉንጉን ሽቦ ይዞ
በሉባንጃ ምትክ- አቡዋራ እያጤሰ
በፈንድሻ ምትክ - ጠጠር እያፈሰ።
.
አዲስ አመት ገባ...
አዲስ እንዲህ ዋዛ
ተፈጥሮ በውበት - መንፈሴን ሳይገዛ
በመአዛው ሳይዋጅ፣
መስከረም መግባቱን - በሬድዮ ልስማው?
እንደ መንግስት አዋጅ።
@getem
@getem
@getem
አበባና ዘመን!!!!! ዘመንና አበባ! !!!!
አበባ ለዘመን፣ ቀለም እያዋሰ፣
ዘመን ለመስኩ ዳር፣የእንቁጣጣሽ ጥሎሽ ፣ ጃኖ እያለበሰ፣
የመስከረም አደይ፤ በመልካው ከንፈር ላይ ሳቅ እየደገሰ፤
ታዲያ በዚህ መሃል ፥
እቴ ለምን ይሆን??
"ጠብቅ እመጣለሁ!!!!"
የሚለው ያ ቃልሽ፣
መልሶ መላልሶ መልሶ ፈረሰ???
ደማቃው መስከረም፣
ሸብራቃው መስከረም፤
ይዘልቀው ይሆን ወይ????
ይቻለው ይሆን ወይ????
የከረመን ፍቅር ፣
የሻገተን መውደድ፣
አዚሙን ገላልጦ፣በብርሃን ፀዳል ማንቃት እንደገና፣
ይሆንለት ይሆን፣
ገጥሞ መቀጣጥል፣የፈረሰውን ቃል፣ የእምነቱን ቁመና????
ይህ አበባ ማለት፣
የመስክ ላይ ቆሎ፣
ፍክትክት ፣ፍንድቅድቅ ፣ ፍልቅልቅ አለሳ???
አዝመራና እሸቱ፤
ሜዳው ላይ ሲያሽቃርር ፣
እንደ እምቦሳ ጥጃ፣ እንደ ደንገላሳ፣
ደግሞ በእርሻየ ላይ፤
የከረመ መውደድ፣
የከሰረ ናፍቆት፣
እንደ እንግጫ በዝቶ አለሁኝ እያለ፣ ሆ ብሎ ይነሳ???
በከረመው ሰማይ፣ በሃምሌ ደመና፣
አደይ አበባየ ልምጣ አልምጣ እያለች በጉም ተሸፍና ፤
ነይልኝ እያልኳት፣
ጳጉሜ ዝናብ ጥሏል ፤ጎርፍ ነው አለችኝ መንገዷም አልቀና፤
ብየ አልቅሼ ነበር፤
ምነው በኔ መንደር፤
ዝናብ አልሆን አለ ፤ አይኔ ላይ ያበጠው የናፍቆት ደመና??
በናፍቆት ሲጠሩት፤
ወይ!!!!! ያላለ መውደድ፣
እሽ እማይል መንገድ፣ያላከመው ናፍቆት፣ ያላደለው ገላ፣
ቢስሙት አይድንም፣
ቢጠሩት አይሰማም፣ ጳጉሜ ከበረረ ከተሸኘ ዃላ።
ሃኒ የኔ ቆንጆ !!!!
የሚለውን ተረት፣ ተይው ገደል ይግባ፣
ምን በወጣኝ ዛሬ፣
በእንቁጣጣሽ ማጀት፣በሃኒ ቁልምጫ፣ ሆዴ የሚባባ??
ይልቅ፣
ያ ደማሙ ፍቅርሽ፣
ያ ጌጠኛው ሳቅሽ፣አይኔን የሚያሽረው፣ ካንጀቴ እሚገባ፣
ይህ ከርታታው ልቤ፣አልመጣችም ብሎ፣ ቂም የማይጋባ፣
ስትልኪልኝ ነው፣
የመስኩን ላይ እሸት፣
አደይ እንጉዳዩን፣ የአድባሩን ቀዘባ፣
ውብ አንች ሳቅሽን ፣ ውብ አደይ አበባ።
አበባና ዘመን፣ዘመንና ተስፋ፣ ከተሸባረቁ፣
በመስኩ ገላ ላይ፤ እቅፍቅፍ ብለው ፍቅር ከወደቁ፣
ናፍቆት ላሰከረው፣
መውደድ ላተኮሰው፣ በእንቁጣጣሽ ሰሞን፣
ለካስ መድሃኒት ነው፣እንቁጣጣሽ ብሎ፣ በአበባ ማሽሞንሞን።
ይኸውልሽ ማሬ፣
ጳጉሜ ተፋሰሰ፣ እንቁጣጣሽ ገባ፣
ቀንሽና ቀኔ፣
አለ እንደተራበ፣ አለ እንደተዛባ፣
ወይ መውደዴ አልሻረ፣ ወይ እግርሽ አልገባ፣
አይዞህ ይለኛል፣
የማዶ አገር ፍቅርሽ፣
በጄ እያስታቀፈኝ፣በስእል ያማረ ፤ ናፍቆትና አበባ።
እናም፣
ከምናምን ከንፈር፣ ከተደሟሞሰ፣
ከሽፍንፍን ገላ፣ ቂም ከተለወሰ፣
ከእመጣለሁ ተስፋ፣ ከተልፈሰፈሰ፣
ከጠብቀኝ ምኞት፣ ከተልከሰከሰ፣
ይቅርብሽ እቴ ሆይ፣
ምኞት ምን ሊፈይድ፣ ቅዠት ምን ሊረባ፣
ያን የለመድኩትን፣
ችፍርግ አበባሽን፣
እንቁጣጣሽ ብለሽ ላኪው ቤቴ ይግባ።
አየሽ፣
አገኝሽ ይሆናል፣
ትመጭ ይሆናል፣
በመስከረም ሰማይ፣
ምድር እንዳማረች፣ቄጤማ ነስንሳ፣ እንግጫ ደርባ፣
ግን እስከዚያው ድረስ፣
መጣሁኝ እያለ፣ጳጉሜ ሲያረገርግ፣ መስከረም ሲገባ፣
ትልኪው አታጭም፣ሳቅና ሆይ ላሌ፣ ሆየና ወሸባ፣
መላክ አይሰለችሽ፣
ያንኑ ፖስት ካርድ ፤
ከላዮ ያለበት ፤እንግጫና ናፍቆት፣ አደይና አበባ።
((( ጃ ኖ ))💚🌼💛🌼❤️🌼
@getem
@getem
@balmbaras
አበባ ለዘመን፣ ቀለም እያዋሰ፣
ዘመን ለመስኩ ዳር፣የእንቁጣጣሽ ጥሎሽ ፣ ጃኖ እያለበሰ፣
የመስከረም አደይ፤ በመልካው ከንፈር ላይ ሳቅ እየደገሰ፤
ታዲያ በዚህ መሃል ፥
እቴ ለምን ይሆን??
"ጠብቅ እመጣለሁ!!!!"
የሚለው ያ ቃልሽ፣
መልሶ መላልሶ መልሶ ፈረሰ???
ደማቃው መስከረም፣
ሸብራቃው መስከረም፤
ይዘልቀው ይሆን ወይ????
ይቻለው ይሆን ወይ????
የከረመን ፍቅር ፣
የሻገተን መውደድ፣
አዚሙን ገላልጦ፣በብርሃን ፀዳል ማንቃት እንደገና፣
ይሆንለት ይሆን፣
ገጥሞ መቀጣጥል፣የፈረሰውን ቃል፣ የእምነቱን ቁመና????
ይህ አበባ ማለት፣
የመስክ ላይ ቆሎ፣
ፍክትክት ፣ፍንድቅድቅ ፣ ፍልቅልቅ አለሳ???
አዝመራና እሸቱ፤
ሜዳው ላይ ሲያሽቃርር ፣
እንደ እምቦሳ ጥጃ፣ እንደ ደንገላሳ፣
ደግሞ በእርሻየ ላይ፤
የከረመ መውደድ፣
የከሰረ ናፍቆት፣
እንደ እንግጫ በዝቶ አለሁኝ እያለ፣ ሆ ብሎ ይነሳ???
በከረመው ሰማይ፣ በሃምሌ ደመና፣
አደይ አበባየ ልምጣ አልምጣ እያለች በጉም ተሸፍና ፤
ነይልኝ እያልኳት፣
ጳጉሜ ዝናብ ጥሏል ፤ጎርፍ ነው አለችኝ መንገዷም አልቀና፤
ብየ አልቅሼ ነበር፤
ምነው በኔ መንደር፤
ዝናብ አልሆን አለ ፤ አይኔ ላይ ያበጠው የናፍቆት ደመና??
በናፍቆት ሲጠሩት፤
ወይ!!!!! ያላለ መውደድ፣
እሽ እማይል መንገድ፣ያላከመው ናፍቆት፣ ያላደለው ገላ፣
ቢስሙት አይድንም፣
ቢጠሩት አይሰማም፣ ጳጉሜ ከበረረ ከተሸኘ ዃላ።
ሃኒ የኔ ቆንጆ !!!!
የሚለውን ተረት፣ ተይው ገደል ይግባ፣
ምን በወጣኝ ዛሬ፣
በእንቁጣጣሽ ማጀት፣በሃኒ ቁልምጫ፣ ሆዴ የሚባባ??
ይልቅ፣
ያ ደማሙ ፍቅርሽ፣
ያ ጌጠኛው ሳቅሽ፣አይኔን የሚያሽረው፣ ካንጀቴ እሚገባ፣
ይህ ከርታታው ልቤ፣አልመጣችም ብሎ፣ ቂም የማይጋባ፣
ስትልኪልኝ ነው፣
የመስኩን ላይ እሸት፣
አደይ እንጉዳዩን፣ የአድባሩን ቀዘባ፣
ውብ አንች ሳቅሽን ፣ ውብ አደይ አበባ።
አበባና ዘመን፣ዘመንና ተስፋ፣ ከተሸባረቁ፣
በመስኩ ገላ ላይ፤ እቅፍቅፍ ብለው ፍቅር ከወደቁ፣
ናፍቆት ላሰከረው፣
መውደድ ላተኮሰው፣ በእንቁጣጣሽ ሰሞን፣
ለካስ መድሃኒት ነው፣እንቁጣጣሽ ብሎ፣ በአበባ ማሽሞንሞን።
ይኸውልሽ ማሬ፣
ጳጉሜ ተፋሰሰ፣ እንቁጣጣሽ ገባ፣
ቀንሽና ቀኔ፣
አለ እንደተራበ፣ አለ እንደተዛባ፣
ወይ መውደዴ አልሻረ፣ ወይ እግርሽ አልገባ፣
አይዞህ ይለኛል፣
የማዶ አገር ፍቅርሽ፣
በጄ እያስታቀፈኝ፣በስእል ያማረ ፤ ናፍቆትና አበባ።
እናም፣
ከምናምን ከንፈር፣ ከተደሟሞሰ፣
ከሽፍንፍን ገላ፣ ቂም ከተለወሰ፣
ከእመጣለሁ ተስፋ፣ ከተልፈሰፈሰ፣
ከጠብቀኝ ምኞት፣ ከተልከሰከሰ፣
ይቅርብሽ እቴ ሆይ፣
ምኞት ምን ሊፈይድ፣ ቅዠት ምን ሊረባ፣
ያን የለመድኩትን፣
ችፍርግ አበባሽን፣
እንቁጣጣሽ ብለሽ ላኪው ቤቴ ይግባ።
አየሽ፣
አገኝሽ ይሆናል፣
ትመጭ ይሆናል፣
በመስከረም ሰማይ፣
ምድር እንዳማረች፣ቄጤማ ነስንሳ፣ እንግጫ ደርባ፣
ግን እስከዚያው ድረስ፣
መጣሁኝ እያለ፣ጳጉሜ ሲያረገርግ፣ መስከረም ሲገባ፣
ትልኪው አታጭም፣ሳቅና ሆይ ላሌ፣ ሆየና ወሸባ፣
መላክ አይሰለችሽ፣
ያንኑ ፖስት ካርድ ፤
ከላዮ ያለበት ፤እንግጫና ናፍቆት፣ አደይና አበባ።
((( ጃ ኖ ))💚🌼💛🌼❤️🌼
@getem
@getem
@balmbaras
ግጥም ብቻ 📘
Photo
በአንድነት እንዘምን
______
🌼🌼🌼🌼🌼
አሮጌዋን አመት
ቆፈኑን ተሻግረን
ክረምቷን አጀብናት፣
በውርጩ ዘለቅናት
የሰማይ ዶፍ አልፈን፣
ውሃው ላይ ተንሳፈን፣
የሀምሌን ነጎድጓድ
ምጡን ተቋቁመን፣
ይኸው ተገናኘን፣
ዳግም በአዲስ ዘመን።🌼
አደይ ሽሙንሙኗ፣
ሲነጉድ ዘመኗ፣
በመስከረም ነፍሷ፣
ከተፍ ትላለች
ከተራሮች አናት፣
በቢጫ ቀሚሷ።
ጀምበር ሳቅ ስትል፣🌼
በአዲሷ መስከረም፣
ተነቅሎ ይወገድ፣
የጥላቻው አረም።
መስከረም ስታጌጥ፣
የዘር ፍቅር እሳት፣
ውሃ ይደፋበት፣
አስክሮ የሚጥል፣🌼
የብሔር አረቄ፣
ሀይሉ ይድከምበት።
በአንድነት ሰማይ ላይ፣
ከ ሰላም ደመና ፣
ጠማማ የነበረው፣
ዳግም እንዲቃና፣
የጥላቻው በርኖስ፣
ይውደቅ ከገሀነብ፣
ለስኬቱ ጣሪያ፣
የሰላም ዶፍ ይዝነብ።
አሮጌው አመት አልፎ፣🌼
አዲሱ ሲገባ፣
ለምልማ ያጌጠች፣
አዲሲቷ ኢትዮጵያ፣
እንድትገነባ፣
የደረቀው ሰላም፣🌼
በፍቅር እንዲርስ፣
አንቆ የሚያስቀረውን ፣
የጥሉን ግድግዳ፣
በአንድነት እናፍርስ።🌼
በአደይ አበቦች፣
መሐል ላይ ተከበን፣
ያቺ የመስቀል ወፍ፣
እንዳትታዘበን፣🌼
ለእድገት ከፍታ፣
ተስፋን እያለምን፣
ከአዲሱ ዘመን ጋር፣
በአንድነት እንዘምን።
መልካም አዲስ አመት!!!
✍
ዮሐንስ ገርማሜ
@getem
@getem
@getem
______
🌼🌼🌼🌼🌼
አሮጌዋን አመት
ቆፈኑን ተሻግረን
ክረምቷን አጀብናት፣
በውርጩ ዘለቅናት
የሰማይ ዶፍ አልፈን፣
ውሃው ላይ ተንሳፈን፣
የሀምሌን ነጎድጓድ
ምጡን ተቋቁመን፣
ይኸው ተገናኘን፣
ዳግም በአዲስ ዘመን።🌼
አደይ ሽሙንሙኗ፣
ሲነጉድ ዘመኗ፣
በመስከረም ነፍሷ፣
ከተፍ ትላለች
ከተራሮች አናት፣
በቢጫ ቀሚሷ።
ጀምበር ሳቅ ስትል፣🌼
በአዲሷ መስከረም፣
ተነቅሎ ይወገድ፣
የጥላቻው አረም።
መስከረም ስታጌጥ፣
የዘር ፍቅር እሳት፣
ውሃ ይደፋበት፣
አስክሮ የሚጥል፣🌼
የብሔር አረቄ፣
ሀይሉ ይድከምበት።
በአንድነት ሰማይ ላይ፣
ከ ሰላም ደመና ፣
ጠማማ የነበረው፣
ዳግም እንዲቃና፣
የጥላቻው በርኖስ፣
ይውደቅ ከገሀነብ፣
ለስኬቱ ጣሪያ፣
የሰላም ዶፍ ይዝነብ።
አሮጌው አመት አልፎ፣🌼
አዲሱ ሲገባ፣
ለምልማ ያጌጠች፣
አዲሲቷ ኢትዮጵያ፣
እንድትገነባ፣
የደረቀው ሰላም፣🌼
በፍቅር እንዲርስ፣
አንቆ የሚያስቀረውን ፣
የጥሉን ግድግዳ፣
በአንድነት እናፍርስ።🌼
በአደይ አበቦች፣
መሐል ላይ ተከበን፣
ያቺ የመስቀል ወፍ፣
እንዳትታዘበን፣🌼
ለእድገት ከፍታ፣
ተስፋን እያለምን፣
ከአዲሱ ዘመን ጋር፣
በአንድነት እንዘምን።
መልካም አዲስ አመት!!!
✍
ዮሐንስ ገርማሜ
@getem
@getem
@getem
👍2
ደስ ይላል መስከረም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በግርሻ'ጣይ ሰርዶ ነቅሎ በሚያዚያንሽ ተርበጥብጦ ...
በግንቦት ሐሩር ተቀቅሎ ... በፀሐይ አብስሎ በዝናብ አብቅሎ
ከወዳጅ ከዘመድ ተቀላቅሎ ...
ባዝራን ከአህያ አዳቅሎ ...
በባለበርሸት ሽልም በቅሎ ...
ተፈናጦ አብሮ ገስግሶ ...
ጅራፍ ግርፊያ ሆያ ሆዬ ...ቡሄ በሉ ተጫውቶ ...
ኪዳነ ምሕረትን አንግሶ ... ደግሞ በወሩ ለአስተሮዬው..
ግሼን ማሪያም እማአርያም ... ደጀሰላም ደርሶ ለመሳለም..
" እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ ..
ዐደይ ለምለም ለኔ እንዳንቺ የለም..."
እያሉ ንጥቂያ ...
ከጀንበር መፍለቂያ እሥከ ጀንበር መጥለቂያ
አለላ ነቅሎ ባሕር እንጉዳይ ...
ጀግና ሰውገዳይ...
አካል እንጉዳይ...
እያሉ ሲያንጎራጉሩ
ደስ ይላል መስከረም !
.
ቡቃያው ጣል ከንበል ሲስ ...
ሽሩባዋ ወርዶ እንዲያ ሲዘናፈል ...
ልቤ እንደበቆሎ ያድራል ሲፈለፈል...
በቀጭን ተሰርታ ሥትል ዘንከት ዘንከት ...
ጃሎ ሲል ሊያነጋ አገር በመለከት ...
ለመስቀል ጠንስሶ ... በማድጋ ገንቦ ለእንግዳ ቀንሶ ...
በሞቴ አፈር ስሆን እያለ ሲያጋፍር ...
ጥርስ እንጎቻ አስፍቶ አሞጭ በመሰለው እርጎ ፍርፍር ...
እንኳን ሳቅ ጨዋታው ድብድቡ ልፊያው ...
ድገሙኝ ያሰኛል ሰፈፍ የለሽ ሞገድ መደዶ ዘር ዜማ ሲቆረቆር ክትፊያው..
ደስ ይላል መስከረም !
.
የሽንብራ ሸት እየጠረጠሩ ...
የልጅነት ሚዜ 'ኧረ አይዋ ክንዴ' እያሉ እየጠሩ ..
አብሮ ወፍ ጥበቃ ማማ ላይ ተሰቅሎ ...
ካፊያውን በገሳ በአንድ ተጠልሎ...
እሳት አቀጣጥሎ በቆሎ ጠባብሶ ...
አየሁ አላየሁም...ሰማሁ አልሰማሁም ...
በላልቶ አፍ አብሶ ...
ለስለሶ አስፈትሎ የ'ናት ኩታ ለብሶ ...
ላዋቂ ተልኮ ለልጅ ተጎናብሶ ...
ደስ ይላል መስከረም !
.
እንደቢራ ቢሮ አበባ ለአበባ ዐደይ እንቡር እንቡር ...
በፍቅር ለመክረም ... !
ደስ ይላል መስከረም !
ወፉ ከነ ጎጆው እሥከ መናጆው ...
ንቡ ከነ ቀፎው መረባ ከነ እርፎው ...
በዐደይ ለምለም ክብር ለመስከረም ክብር ...
ቅዱስ ! ቅዱስ ! ቅዱስ !
የዓመት አሥራት ሊያፈስ ...
ሊያስገባለት ግብር ...
በዝማሬ ሲያብር ...
አንጄት ሲበረብር ... !
ደስ ይላል መስከረም !
ተዋዶ ወዶ ተወሕዶ ... ያንጀት ተፈቃቅዶ ...
ባንድ አብሮ ለመክረም ...
ደስ ይላል መስከረም !
ለቅኔ ዘረፋው ጠፈፍ ሲል ፈፋው ...
የቆሎ ተማሪ ያ ተመራማሪ ...
የወላዲት አምላክ የድንግል አዝማሪ ...
ያ ደበሎ ለባሽ .... !
በእግዚትነ ማሪያም ...እባካቹህ እባሽ እባካቹህ ቁራሽ..
እያለ ሲለምን ...
ከጥንቅሹ ቅንጥሽ ማሩቴ ባይሰጠው ...
አይቀር መደንገጡ አራሽ አባ ወራሽ ማብላት ያሰለጠው..!
የማይለወጠው..!
በዐይኑ እየመዘነ በልቡ እማይመርጠው ...
ገሩ ባላገሩ...!
ያ ባለሞፈሩ ያ ባለዘገሩ ...,!
በሞቴ ነው ቋንቋው ስሞት ነው ነገሩ...!
ደስ ይላል መስከረም !
.
ወዶ ተወሕዶ ያንጀት ተፈቃቅዶ ...!
አንድ ልብ አቅዶ...!
አንድ ላይ ለመክረም...!
ደስ ይላል መስከረም !
...
ጥቅምትና ኅዳር ቢያዋውል ምንጭ ዳር ...
ታኅሳስና ጥር ዐውድማ አስለቅልቆ ጥሪት እሚያስቋጥር..
የካቲት መጋቢት መኸር አስከትቶ ቢያበስል እንደ ዐቃቢት..
ሚያዚያና ግንቦቱ ተርቲበኛው ቀርቦ ወርዶ ራከቦቱ...
የላም ልጅ በዋንጫ ቢቀርብ ሥልባቦቱ...
ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ እንደ ቄስ ምናሴ...
እያረበረበ ደግሞ እየወረበ...
ሰማይ በበረቀ ታርሶርሶ ሲስረቀረቅ...
ከራሱ እስኪታረቅ...!
ሁሉም እንደ ግብሩ..
ሁሉም እንደ ሙያው...!
አሥራ ሁለቱም ወር ...
እዮሃ አበባዬ መስከረም ሲጠባ..
ያኔ ነው ገቢያ..
ያኔ ነው መታያው ...
ያኔ ነው ማባያው ...
ደስ ይላል መስከረም ! ! !
.
( ሙሉ ጌታ ተስፋዬ )💚🌼💛🌼❤️🌼
… እንቁጣጣሽ ነበር መስከረም ሲጠባ
አውቆ የበቀለ ወፍ ዘራሽ አበባ፡፡
ለምለም አረንጓዴ…
ያልተጠበቀ መስክ ከብት የሚግጥበት
የደመና ግላጭ የሚጫወትበት፡፡
ሌላም ብዙ ነበር
ሌላም… ደግሞ ሌላ
አለብኝ ትዝታ!
ዘመዶቼ ሳሙኝ
ጓደኞቼም ጋብዙኝ
ሊስትሮ ጨብጠኝ
ባለጋሪ ንዳ መንገዴን አሳየኝ
ያገሬ ልጅ ቆንጆ ‹‹ቤት ለእንግዳ›› በይኝ
አለብኝ ትዝታ…
ገ/ክርስቶስ ደስታ
(እንደገና)🌼🌼🌼
…በይ ብር በይ ቢራ ቢሮ፣ ክረምት ላንቺ
ብቻ አለፈ
ሌላው በጎርፍ ጎረፈ
ሞተ፣ በተኛበት ረጋ…
ፀደይ ላንቺ ብቻ ነጋ
ሽር ብለሽ መንቆጥቆጥ ነው፤ ከዚያም፤
ከዚያም፤ ከዚያም ሰምሮ
አወቅሁብሽ፤ ነቃሁብሽ፤ አንቺ ሕይወት
ቢራ ቢሮ…
ቀናሁ መሰል አንች ወላዋይ?
ነይ ብር በይ እንወያይ
አንቺ የዕፅዋት አዋዋይ
ከፀደይ ጋር ፀደይ መሳይ
ከአበባም አበባ መሳይ…
ምን አለበት ላንዲት ሰሞን
ቢራ ቢሮ እኔ አንቺን ብሆን?
ፀጋዬ ገ/መድህን
(ሕይወት ቢራቢሮ)🌼🌼🌼
… ወፎች ሲዘምሩ ሰማይ ደማስ መስሎ፣
ሐሴት ገባ ልቤ በውበት ተኩሎ፡፡
ዮሐንስ አድማሱ
(ወፎች በተጥለግለግ - 1955 ዓ.ም)
* * *
…ነበረች አበባ፣
በሾህ ተቀንብባ፣
መዓዛዋ ዘምቶ፣
ተወርዋሪን ኮከብ አቀረበው ጠርቶ፡፡
በውበት ብትልቅ ይህች የዋህ አበባ፣
ረብ የሰው ዘየ በሾህ ተቀንብባ፣
እሾህ አያስደርስ፣ ቆንጥሩ አያስጠጋ፣ የዘመን
ጋሬጣ አድርጓት ሰለባ፣
በእጦት መቃጠል ነው መዓዛዋ ሲያውድ
ከልብ እየገባ፡፡
ዮሐንስ አድማሱ
(ተወርዋሪ ኮከብ)🌼🌼🌼
የተስፋዬ ዛፉ
ሊከረከም ቅርንጫፉ፣
ሥሩ ሲነቃቀል
ሲበጠስ ሲፈነገል፤
ጭላንጭል ስትዳፈን
ብርሀን ዐይኑ ሲከደን፣
አንጥፌ ደርቤ ማቄን
ዘንግቻት እንቁጣጣሽን
ፀደይ አበባ ዐደዬን፣
በድቅድቅ ተቀመጥሁኝ
ላለማሰብ እያሰብሁኝ፣
የልቤን ልበ ባሻነት ገሰጽኩኝ
ተስፋ መቁረጥን ተስፋ አረኩኝ፡፡
ደበበ ሰይፉ
(የተስፋዬ ዛፉ)🌼🌼🌼
@getem
@getem
@balmbaras
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በግርሻ'ጣይ ሰርዶ ነቅሎ በሚያዚያንሽ ተርበጥብጦ ...
በግንቦት ሐሩር ተቀቅሎ ... በፀሐይ አብስሎ በዝናብ አብቅሎ
ከወዳጅ ከዘመድ ተቀላቅሎ ...
ባዝራን ከአህያ አዳቅሎ ...
በባለበርሸት ሽልም በቅሎ ...
ተፈናጦ አብሮ ገስግሶ ...
ጅራፍ ግርፊያ ሆያ ሆዬ ...ቡሄ በሉ ተጫውቶ ...
ኪዳነ ምሕረትን አንግሶ ... ደግሞ በወሩ ለአስተሮዬው..
ግሼን ማሪያም እማአርያም ... ደጀሰላም ደርሶ ለመሳለም..
" እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ ..
ዐደይ ለምለም ለኔ እንዳንቺ የለም..."
እያሉ ንጥቂያ ...
ከጀንበር መፍለቂያ እሥከ ጀንበር መጥለቂያ
አለላ ነቅሎ ባሕር እንጉዳይ ...
ጀግና ሰውገዳይ...
አካል እንጉዳይ...
እያሉ ሲያንጎራጉሩ
ደስ ይላል መስከረም !
.
ቡቃያው ጣል ከንበል ሲስ ...
ሽሩባዋ ወርዶ እንዲያ ሲዘናፈል ...
ልቤ እንደበቆሎ ያድራል ሲፈለፈል...
በቀጭን ተሰርታ ሥትል ዘንከት ዘንከት ...
ጃሎ ሲል ሊያነጋ አገር በመለከት ...
ለመስቀል ጠንስሶ ... በማድጋ ገንቦ ለእንግዳ ቀንሶ ...
በሞቴ አፈር ስሆን እያለ ሲያጋፍር ...
ጥርስ እንጎቻ አስፍቶ አሞጭ በመሰለው እርጎ ፍርፍር ...
እንኳን ሳቅ ጨዋታው ድብድቡ ልፊያው ...
ድገሙኝ ያሰኛል ሰፈፍ የለሽ ሞገድ መደዶ ዘር ዜማ ሲቆረቆር ክትፊያው..
ደስ ይላል መስከረም !
.
የሽንብራ ሸት እየጠረጠሩ ...
የልጅነት ሚዜ 'ኧረ አይዋ ክንዴ' እያሉ እየጠሩ ..
አብሮ ወፍ ጥበቃ ማማ ላይ ተሰቅሎ ...
ካፊያውን በገሳ በአንድ ተጠልሎ...
እሳት አቀጣጥሎ በቆሎ ጠባብሶ ...
አየሁ አላየሁም...ሰማሁ አልሰማሁም ...
በላልቶ አፍ አብሶ ...
ለስለሶ አስፈትሎ የ'ናት ኩታ ለብሶ ...
ላዋቂ ተልኮ ለልጅ ተጎናብሶ ...
ደስ ይላል መስከረም !
.
እንደቢራ ቢሮ አበባ ለአበባ ዐደይ እንቡር እንቡር ...
በፍቅር ለመክረም ... !
ደስ ይላል መስከረም !
ወፉ ከነ ጎጆው እሥከ መናጆው ...
ንቡ ከነ ቀፎው መረባ ከነ እርፎው ...
በዐደይ ለምለም ክብር ለመስከረም ክብር ...
ቅዱስ ! ቅዱስ ! ቅዱስ !
የዓመት አሥራት ሊያፈስ ...
ሊያስገባለት ግብር ...
በዝማሬ ሲያብር ...
አንጄት ሲበረብር ... !
ደስ ይላል መስከረም !
ተዋዶ ወዶ ተወሕዶ ... ያንጀት ተፈቃቅዶ ...
ባንድ አብሮ ለመክረም ...
ደስ ይላል መስከረም !
ለቅኔ ዘረፋው ጠፈፍ ሲል ፈፋው ...
የቆሎ ተማሪ ያ ተመራማሪ ...
የወላዲት አምላክ የድንግል አዝማሪ ...
ያ ደበሎ ለባሽ .... !
በእግዚትነ ማሪያም ...እባካቹህ እባሽ እባካቹህ ቁራሽ..
እያለ ሲለምን ...
ከጥንቅሹ ቅንጥሽ ማሩቴ ባይሰጠው ...
አይቀር መደንገጡ አራሽ አባ ወራሽ ማብላት ያሰለጠው..!
የማይለወጠው..!
በዐይኑ እየመዘነ በልቡ እማይመርጠው ...
ገሩ ባላገሩ...!
ያ ባለሞፈሩ ያ ባለዘገሩ ...,!
በሞቴ ነው ቋንቋው ስሞት ነው ነገሩ...!
ደስ ይላል መስከረም !
.
ወዶ ተወሕዶ ያንጀት ተፈቃቅዶ ...!
አንድ ልብ አቅዶ...!
አንድ ላይ ለመክረም...!
ደስ ይላል መስከረም !
...
ጥቅምትና ኅዳር ቢያዋውል ምንጭ ዳር ...
ታኅሳስና ጥር ዐውድማ አስለቅልቆ ጥሪት እሚያስቋጥር..
የካቲት መጋቢት መኸር አስከትቶ ቢያበስል እንደ ዐቃቢት..
ሚያዚያና ግንቦቱ ተርቲበኛው ቀርቦ ወርዶ ራከቦቱ...
የላም ልጅ በዋንጫ ቢቀርብ ሥልባቦቱ...
ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ እንደ ቄስ ምናሴ...
እያረበረበ ደግሞ እየወረበ...
ሰማይ በበረቀ ታርሶርሶ ሲስረቀረቅ...
ከራሱ እስኪታረቅ...!
ሁሉም እንደ ግብሩ..
ሁሉም እንደ ሙያው...!
አሥራ ሁለቱም ወር ...
እዮሃ አበባዬ መስከረም ሲጠባ..
ያኔ ነው ገቢያ..
ያኔ ነው መታያው ...
ያኔ ነው ማባያው ...
ደስ ይላል መስከረም ! ! !
.
( ሙሉ ጌታ ተስፋዬ )💚🌼💛🌼❤️🌼
… እንቁጣጣሽ ነበር መስከረም ሲጠባ
አውቆ የበቀለ ወፍ ዘራሽ አበባ፡፡
ለምለም አረንጓዴ…
ያልተጠበቀ መስክ ከብት የሚግጥበት
የደመና ግላጭ የሚጫወትበት፡፡
ሌላም ብዙ ነበር
ሌላም… ደግሞ ሌላ
አለብኝ ትዝታ!
ዘመዶቼ ሳሙኝ
ጓደኞቼም ጋብዙኝ
ሊስትሮ ጨብጠኝ
ባለጋሪ ንዳ መንገዴን አሳየኝ
ያገሬ ልጅ ቆንጆ ‹‹ቤት ለእንግዳ›› በይኝ
አለብኝ ትዝታ…
ገ/ክርስቶስ ደስታ
(እንደገና)🌼🌼🌼
…በይ ብር በይ ቢራ ቢሮ፣ ክረምት ላንቺ
ብቻ አለፈ
ሌላው በጎርፍ ጎረፈ
ሞተ፣ በተኛበት ረጋ…
ፀደይ ላንቺ ብቻ ነጋ
ሽር ብለሽ መንቆጥቆጥ ነው፤ ከዚያም፤
ከዚያም፤ ከዚያም ሰምሮ
አወቅሁብሽ፤ ነቃሁብሽ፤ አንቺ ሕይወት
ቢራ ቢሮ…
ቀናሁ መሰል አንች ወላዋይ?
ነይ ብር በይ እንወያይ
አንቺ የዕፅዋት አዋዋይ
ከፀደይ ጋር ፀደይ መሳይ
ከአበባም አበባ መሳይ…
ምን አለበት ላንዲት ሰሞን
ቢራ ቢሮ እኔ አንቺን ብሆን?
ፀጋዬ ገ/መድህን
(ሕይወት ቢራቢሮ)🌼🌼🌼
… ወፎች ሲዘምሩ ሰማይ ደማስ መስሎ፣
ሐሴት ገባ ልቤ በውበት ተኩሎ፡፡
ዮሐንስ አድማሱ
(ወፎች በተጥለግለግ - 1955 ዓ.ም)
* * *
…ነበረች አበባ፣
በሾህ ተቀንብባ፣
መዓዛዋ ዘምቶ፣
ተወርዋሪን ኮከብ አቀረበው ጠርቶ፡፡
በውበት ብትልቅ ይህች የዋህ አበባ፣
ረብ የሰው ዘየ በሾህ ተቀንብባ፣
እሾህ አያስደርስ፣ ቆንጥሩ አያስጠጋ፣ የዘመን
ጋሬጣ አድርጓት ሰለባ፣
በእጦት መቃጠል ነው መዓዛዋ ሲያውድ
ከልብ እየገባ፡፡
ዮሐንስ አድማሱ
(ተወርዋሪ ኮከብ)🌼🌼🌼
የተስፋዬ ዛፉ
ሊከረከም ቅርንጫፉ፣
ሥሩ ሲነቃቀል
ሲበጠስ ሲፈነገል፤
ጭላንጭል ስትዳፈን
ብርሀን ዐይኑ ሲከደን፣
አንጥፌ ደርቤ ማቄን
ዘንግቻት እንቁጣጣሽን
ፀደይ አበባ ዐደዬን፣
በድቅድቅ ተቀመጥሁኝ
ላለማሰብ እያሰብሁኝ፣
የልቤን ልበ ባሻነት ገሰጽኩኝ
ተስፋ መቁረጥን ተስፋ አረኩኝ፡፡
ደበበ ሰይፉ
(የተስፋዬ ዛፉ)🌼🌼🌼
@getem
@getem
@balmbaras
👍1
ወቅታዊ አበባየሁሽ
(በላይ በቀለ ወያ)ፈገግ ብላችሁ ዋሉ
.
.
ዋ ብለን መጣን ዋ ብለን
እስከመቼ "እህ " ሆ እንላን
ዋ ብለን መጣን ዋ ብለን
አበባየሁሽ
/ለምለም/
ገንቡ በተራ
/ለምለም/
እንጨት ሰባብረን
/ለምለም/
ቤት እስክንሰራ
/ለምለም/
እንኳን ቤትና
/ለምለም/
የለንም አጥር
/ለምለም/
ደጅ እናድራለን
/ለምለም/
ዘር ስንቆጥር
/ለምለም/
ዘርማንዘር ቆጥረን
/ለምለም/
ሥንሰራ ቤት
/ለምለም/
ለውጡን ሚመራው
/ለምለም/
ደጉ መንግስት
/ለምለም/
ያፈርስብናል
/ለምለም/
መዝናኛ ቦታ ለመገንባት ፡፡
........................... ......
አደይ
ያገር ጉዳይ
ውይ ስቃይ፡፡
አደይ
የጋራ ታሪክ ፣ የለንም ባይ
የጋራ ድንጋይ አይደለም ወይ
።።።
እቴ አበሳ አቴ አበሳዬ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
አቴ አበሳ ስትለኝ ከርማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
ባንክ ዘርፋ ነፃ አውጪዬማ
ጥላኝ ጠፋሽ ፣ ድምጿን ሳልሰማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
መብራት ሀይል ሁሌ ጨለማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
ውሃ ልማት ውሃ ሚያስጠማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
መንገድ ሞልቶ መጎዝ ነው አድማ
"አዬ አቴ አበሳዬ"
ይሁን ኑሮ ከተባለማ
"አዬ አቴ አበሳዬ"
አዬ
"እቴ አበሳዬ"
አዬ
"እቴ አበሳዬ"
...................
እዬዬ
እህ ሁሌ እዬዬ
ገዦች አሉ ብዬ
በገዛ ሀገሬ ላይ በዛብኝ ስቃዬ፡፡
........... ......................
ይሸታል ሽንኩርት ሽንኩርት
የአባብዬ ምኩት
አይሸትም ዶሮ ዶሮ
የእማምዬ ጓሮ
ዶሮ አልሰሩም መሠል ፣ ሽንኩርት ዋጋው ንሮ
።።
ከብረው ይቆዩን ከብረው
ተረኝነትን ጥለው ፣ዘረኝነትን ቀብረው
ሺህ አክቲቪስቶች አስረው
ቅድሚያ ለሰው ልጅ ሰጥተው
ህዝቦችን አቀራርበው
ሜንጫና ዱላ ጥለው
አንዲት ኢትዮጵያን ይዘው
ከብረው ይቆዩን ከብረው።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለመላው የአንዲት ኢትዮጵያ እምነት ተከታዮች መልካም አዲስ አመት
@getem
@getem
@GEBRIEL_19
(በላይ በቀለ ወያ)ፈገግ ብላችሁ ዋሉ
.
.
ዋ ብለን መጣን ዋ ብለን
እስከመቼ "እህ " ሆ እንላን
ዋ ብለን መጣን ዋ ብለን
አበባየሁሽ
/ለምለም/
ገንቡ በተራ
/ለምለም/
እንጨት ሰባብረን
/ለምለም/
ቤት እስክንሰራ
/ለምለም/
እንኳን ቤትና
/ለምለም/
የለንም አጥር
/ለምለም/
ደጅ እናድራለን
/ለምለም/
ዘር ስንቆጥር
/ለምለም/
ዘርማንዘር ቆጥረን
/ለምለም/
ሥንሰራ ቤት
/ለምለም/
ለውጡን ሚመራው
/ለምለም/
ደጉ መንግስት
/ለምለም/
ያፈርስብናል
/ለምለም/
መዝናኛ ቦታ ለመገንባት ፡፡
........................... ......
አደይ
ያገር ጉዳይ
ውይ ስቃይ፡፡
አደይ
የጋራ ታሪክ ፣ የለንም ባይ
የጋራ ድንጋይ አይደለም ወይ
።።።
እቴ አበሳ አቴ አበሳዬ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
አቴ አበሳ ስትለኝ ከርማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
ባንክ ዘርፋ ነፃ አውጪዬማ
ጥላኝ ጠፋሽ ፣ ድምጿን ሳልሰማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
መብራት ሀይል ሁሌ ጨለማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
ውሃ ልማት ውሃ ሚያስጠማ
"አዬ እቴ አበሳዬ"
መንገድ ሞልቶ መጎዝ ነው አድማ
"አዬ አቴ አበሳዬ"
ይሁን ኑሮ ከተባለማ
"አዬ አቴ አበሳዬ"
አዬ
"እቴ አበሳዬ"
አዬ
"እቴ አበሳዬ"
...................
እዬዬ
እህ ሁሌ እዬዬ
ገዦች አሉ ብዬ
በገዛ ሀገሬ ላይ በዛብኝ ስቃዬ፡፡
........... ......................
ይሸታል ሽንኩርት ሽንኩርት
የአባብዬ ምኩት
አይሸትም ዶሮ ዶሮ
የእማምዬ ጓሮ
ዶሮ አልሰሩም መሠል ፣ ሽንኩርት ዋጋው ንሮ
።።
ከብረው ይቆዩን ከብረው
ተረኝነትን ጥለው ፣ዘረኝነትን ቀብረው
ሺህ አክቲቪስቶች አስረው
ቅድሚያ ለሰው ልጅ ሰጥተው
ህዝቦችን አቀራርበው
ሜንጫና ዱላ ጥለው
አንዲት ኢትዮጵያን ይዘው
ከብረው ይቆዩን ከብረው።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለመላው የአንዲት ኢትዮጵያ እምነት ተከታዮች መልካም አዲስ አመት
@getem
@getem
@GEBRIEL_19
👍1
እነሆ መስከረም መጣ
ኑ!
አዲስ እቅድ እናውጣ።
ቃል-ኪዳናችንን..
ራስ-ለራስ የገባነውን...
ከኻቻምና ያሳደርነውን...
አምናም አስበን ያልፈፀምነውን ...
ኑ!
አሮጌው ውጥናችንን እንኳል
ዘንድሮስ አይቀርም ይሳካል...!!!
(በርናባስ ከበደ)
@getem
@getem
@gebriel_19
ኑ!
አዲስ እቅድ እናውጣ።
ቃል-ኪዳናችንን..
ራስ-ለራስ የገባነውን...
ከኻቻምና ያሳደርነውን...
አምናም አስበን ያልፈፀምነውን ...
ኑ!
አሮጌው ውጥናችንን እንኳል
ዘንድሮስ አይቀርም ይሳካል...!!!
(በርናባስ ከበደ)
@getem
@getem
@gebriel_19
እይታ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እዮሀ አበባዬ
መስከረም ጠባዬ
መስከረም ሲጠባ
ወደ ሀገሬ ልግባ
ሐሜት ባይሆንብኝ ስር የሌለው ወሬ
መኖርን እሻለው እኔስ በሀገሬ
እኔን የገረመኝ
በዚህች ሀገር ውስጥ ሰርክ የሚለፈለፍ
መስከረም በጠባ በወራቱ ግዜ ሁሌ የሚለፈፍ
ይህ መዝሙር መልክቱ በሌላ ስናየው
ብዙ ያልተመለሰ ግዙፍ ጥያቄ አለው
ለምሳሌ
አንድ ሀገር ላይ
ሆኖ ወደ ሀገሬ ልግባ ምን አይነት ፈሊጥ ነው
አንድ ሀገር ውስጥ
ሆኖ ወደ ሀገሬ ልሂድ ማለትስ ምንድነው
አንዳች ነገር ባይኖር ድብቅ ሴራ ነገር
ባለ ሀገሩ ህዝቤ እንዲህ አይልም ነበር
በዛኛው ጫፍ ሆነን ነገሩን ስናየው
ግጥሙ ሲገጠም
ስንኝ ሲደረደር ክልል እና ብሄር አለ እንደማለት ነው
አለበለዚያ ግን
ገጣሚው ሰውዬ
ወይ ይጠነቁላል ወይ ነብይ ነበር ብሎ መመስከር ነው
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መልካም አዲስ ዓመት
✍✍ ናብሊስ
@nablis12
@getem
@getem
@getem
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እዮሀ አበባዬ
መስከረም ጠባዬ
መስከረም ሲጠባ
ወደ ሀገሬ ልግባ
ሐሜት ባይሆንብኝ ስር የሌለው ወሬ
መኖርን እሻለው እኔስ በሀገሬ
እኔን የገረመኝ
በዚህች ሀገር ውስጥ ሰርክ የሚለፈለፍ
መስከረም በጠባ በወራቱ ግዜ ሁሌ የሚለፈፍ
ይህ መዝሙር መልክቱ በሌላ ስናየው
ብዙ ያልተመለሰ ግዙፍ ጥያቄ አለው
ለምሳሌ
አንድ ሀገር ላይ
ሆኖ ወደ ሀገሬ ልግባ ምን አይነት ፈሊጥ ነው
አንድ ሀገር ውስጥ
ሆኖ ወደ ሀገሬ ልሂድ ማለትስ ምንድነው
አንዳች ነገር ባይኖር ድብቅ ሴራ ነገር
ባለ ሀገሩ ህዝቤ እንዲህ አይልም ነበር
በዛኛው ጫፍ ሆነን ነገሩን ስናየው
ግጥሙ ሲገጠም
ስንኝ ሲደረደር ክልል እና ብሄር አለ እንደማለት ነው
አለበለዚያ ግን
ገጣሚው ሰውዬ
ወይ ይጠነቁላል ወይ ነብይ ነበር ብሎ መመስከር ነው
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መልካም አዲስ ዓመት
✍✍ ናብሊስ
@nablis12
@getem
@getem
@getem