🙏ትውልድ የመታደግ ጥሪ🙏
ይህ የምትመለከቱት ህፃን ማቴዎስ ይባላል እንደማንኛውም ህፃን ልጅ ሲወለድ እልል ተብሎለት ሀገር ያኮራል አድጎ ቤተሰብ ይጠቅማል ተሎ ነበር። ግን እንዳለመታደል ሆኖ ከፍተኛና የተወሳሰበ የልብ ህመም የዚን ቆንጅዬ አፍላ ህይወት አስቸጋሪ አደረገበት የበሽታው ከባድ መሆን ደግሞ እንደእኩዮቹ እንዳይራመድ እንዳያወራ እንዲሁም እንዳይጫወት እክል ሆኖበታል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ይሄ የእርዳታ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት፣የሰብዐዊነትና እኔም ያገባኛል የሚል ስሜት የሚሰማው ሁሉ ሊረባረብበት የሚገባ የአንድነት ጥሪ ነው ።ስለዚህ ወላጆችም የኔ ልጅ ነው ወጣቶችም ታናሽ ወንድሜ ነው ህፃናትም ጓደኛዬ ነው በማለት የቻላቹትን በገንዘብም፣በምግብም፣በቁሳቁስም፣በሀሳብም በተቻላቹ አቅም ይህን የነገይቱን የኢትዮጵያ ተስፋ እንታደግ ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም እንለምናለን።
እኛው ለኛው ከተባበርን
እንኳን ለራስ ለአለም እንተርፋለን
ንግድ ባንክ፦1000289124458
ስልክ፦ 0932275457
ስልክ፦ 0937678839
Share share share share share share share share share share
share
share
share
share
ይህ የምትመለከቱት ህፃን ማቴዎስ ይባላል እንደማንኛውም ህፃን ልጅ ሲወለድ እልል ተብሎለት ሀገር ያኮራል አድጎ ቤተሰብ ይጠቅማል ተሎ ነበር። ግን እንዳለመታደል ሆኖ ከፍተኛና የተወሳሰበ የልብ ህመም የዚን ቆንጅዬ አፍላ ህይወት አስቸጋሪ አደረገበት የበሽታው ከባድ መሆን ደግሞ እንደእኩዮቹ እንዳይራመድ እንዳያወራ እንዲሁም እንዳይጫወት እክል ሆኖበታል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ይሄ የእርዳታ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት፣የሰብዐዊነትና እኔም ያገባኛል የሚል ስሜት የሚሰማው ሁሉ ሊረባረብበት የሚገባ የአንድነት ጥሪ ነው ።ስለዚህ ወላጆችም የኔ ልጅ ነው ወጣቶችም ታናሽ ወንድሜ ነው ህፃናትም ጓደኛዬ ነው በማለት የቻላቹትን በገንዘብም፣በምግብም፣በቁሳቁስም፣በሀሳብም በተቻላቹ አቅም ይህን የነገይቱን የኢትዮጵያ ተስፋ እንታደግ ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም እንለምናለን።
እኛው ለኛው ከተባበርን
እንኳን ለራስ ለአለም እንተርፋለን
ንግድ ባንክ፦1000289124458
ስልክ፦ 0932275457
ስልክ፦ 0937678839
Share share share share share share share share share share
share
share
share
share
"ከዛፍ የተቀመረ ዜማ"
ካ'ለም እቅፍ ወጥቶ
ካ'ለም እቅፍ ሸሽቶ
ወደ ገዳም ሲሄድ
ደክሞት ተዝለፍልፎ
ብላቴናዉ ያሬድ ካ'ንድ ዛፍ ስር አርፎ
ከዛፉ ግንድ ሥር ትል ሲሸልል ሰማ
እንዲህ በሚል ዜማ
"ዛፍ ነዉ ህይወቴ
ቅጠልዋ እራቴ
ሰባት ጊዜ ልውደቅ
ሰባቴ እንድወጣ
የኀላ ኀላ 'ራቴን አላጣ"
ይህን ስትሰማ ቅጠሊቱ ራደች
መሸሽ ባይሆንላት ሙሾን አወረደች
"ዛፉ ህይወቴ ነው
ግን ኀያል ቢመስልም
ተራራ ቢመስልም
ተራራ ቢያክልም
የማታ የማታ
ከትል አያስጥልም"
ያሬድ ይሄን ሰምቶ
ትሉ በጥረቱ ራት ሲበላ አይቶ
ተስፋውን አጸናዉ
በቅጠሏ ዕጣ ግን ተነካ ልቡናው
ከዚያም ተመልሶ
የትሉን ፉከራ
የቅጠሏን ለቅሶ
ባ'ንድ ላይ ለውሶ
ዜማውን ቀመረ
ዜማው ተዘመረ
ከሰው ነፍስ ተስማማ
በሰው ድምፅ አማረ ።
@getem
@getem
@getem
ካ'ለም እቅፍ ወጥቶ
ካ'ለም እቅፍ ሸሽቶ
ወደ ገዳም ሲሄድ
ደክሞት ተዝለፍልፎ
ብላቴናዉ ያሬድ ካ'ንድ ዛፍ ስር አርፎ
ከዛፉ ግንድ ሥር ትል ሲሸልል ሰማ
እንዲህ በሚል ዜማ
"ዛፍ ነዉ ህይወቴ
ቅጠልዋ እራቴ
ሰባት ጊዜ ልውደቅ
ሰባቴ እንድወጣ
የኀላ ኀላ 'ራቴን አላጣ"
ይህን ስትሰማ ቅጠሊቱ ራደች
መሸሽ ባይሆንላት ሙሾን አወረደች
"ዛፉ ህይወቴ ነው
ግን ኀያል ቢመስልም
ተራራ ቢመስልም
ተራራ ቢያክልም
የማታ የማታ
ከትል አያስጥልም"
ያሬድ ይሄን ሰምቶ
ትሉ በጥረቱ ራት ሲበላ አይቶ
ተስፋውን አጸናዉ
በቅጠሏ ዕጣ ግን ተነካ ልቡናው
ከዚያም ተመልሶ
የትሉን ፉከራ
የቅጠሏን ለቅሶ
ባ'ንድ ላይ ለውሶ
ዜማውን ቀመረ
ዜማው ተዘመረ
ከሰው ነፍስ ተስማማ
በሰው ድምፅ አማረ ።
@getem
@getem
@getem
♡ ስሞት አትቅበረኝ ♡♡♡
በሂወት እያለሁ እንባዬን ካልጠረግህ ፣
በእኔ እንባ ማንባት ካላዘነ ልብህ ፣
ሰታመም ዝም ካልህ ፣
እራቤ ካልገባህ ፣
ጭንቀቴም ብሶቴም ከመሰለህ ተራ ፣
ድፍርሱ ሂወቴ በፍቅርህ ካልጠራ ፣
ደብዛዛዉ ሂወቴ በፍቅርህ ካልበራ ፣
ተልካሻዉ ኑሮዬን
ካላሰናዳከዉ ፣
የተደላደለ ቦታ ካላሲያዝከዉ ፣
ማየት የተሳነዉ
ፍቅሬን ካልመራሀዉ ፣
እዉነት እልሃለሁ ዉዴ...
ስሞት አትቅበረኝ ፣
እንባም አታንባልኝ ፣
ፀፀትም አትግባ
ይልቁንስ ፍቅሬ...
እንደ ሻማ ቀልጦ ፍቅሬ ሳያልቅብህ ፣
እጂጉን አምሮ ልቤ ሳይቆርጥብህ ፣
ስታመም አስታመኝ ፣
ሰከፋ አፅናናኝ ፣
ስወድቅ ደግፈኝ ፣
የጭንቀቴን ብሶት
የዉስጤን ተረዳኝ ፣
ድፍርሱን ሂወቴን
በፍቅርህ አጥራልኝ ፣
ደብዛዛዉ ሂወቴን
በፍቅርህ አብራልኝ ፣
ተልካሻዉ ኑሮዬ
ፈጥነህ አሰናዳዉ ፣
የተደላደለ ቦታዉን አሲዘዉ ፣
ማየት የተሳነዉ
ልቤን ይዘሀ ምራዉ ፣
ደስታና ፍቅርን ከልብ አስተምረኝ ፣
ሁል ጊዜ ሳቅልኝ ፣
ይሄ ካልሆነ ግን
ስሞት አትቅበረኝ ::
ምንጭ፦ ወንጌላዊት እሙ
=======================
ለ "ስሞት አትቅበረኝ" ግጥም ምላሽ
ከአያልቅበት ሰለሞን
እሙ በህይወት እስካለሽ እንባሽን አብሼ
ስታለቅሺ ሳይሽ ተንሰቅስቄ አልቅሼ
ስትዝኚ ዕያየሁ እጥፍ ካላዘንኩኝ
ምኑን ሰው ተባልኩኝ
ሢያምሽ ካላመመኝ
እራብሽ ካልራበኝ
ምኑን አፈቀርኩሽ ምኑን ወዳጅ ሆንኩኝ
ጭንቀትሽ ብሶትሽ ከመሰለኝ ተራ
ድፍርሱ ህይወትሽ በፍቅሬ ካልጠራ
ተልካሻው ኑሮሽን ካላሰናዳሁት
የተደላደለ ቦታ ካላሲያዝኩት
ምናል ባልተዋወቅን እላለሁኝ ዕኔ
ለፍቅርሽ መከታ ስላለመሆኔ
ይልቅስ አታስቢ ፍቅሬ
ቃል ልግባልሽ ዛሬ
ስታለቅሺ አልቅሼ ስታዝኝም አዝናለው
ባስለቀሰሽ ጉዳይ ዳኛም እሆናለው
እፋረደዋለው።
ፍቅርሽን ቀንበቀን በፍቅሬ አድሳለው
ምስቅልቅል ህይወትሽን ዘውትር አድሳለው
እታመንሻለው
አይንሽ አያለቅስም
ልብሽ አይቆዝምም
ፈገግታሽ አይፈዝም
የፊትሽም ፀዳል ከቶ አይደብዝዝም
ይኸውልሽ ፍቅሬ ቃል ልግባ ደግሜ
ፍቅርሽ ተሰራጭቷል ባካልና ደሜ
ሲያምሽ ያምመኛል ሥታዝኚም አዝናለው
ስታለቅሺ አልቅሼ ስትስቂም ስቃለው
በፊትሽ ብርሐን እኔም እደምቃለው
ነገርግን ፍቅሬ ሆይ ስሚኝ በጽሞና
ምናልባት ሚሆነውን አላውቀውምና
አድምጭ እንደገና
ምናልባት ይህ ቃሌን መጠበቅ ቢያቅተኝ
ለፍቅርሽ መከታ መሖን ቢያታክተኝ
ህይወትሽን ማቃናት ባልችል በስንፍና
ይሄ ወዳጅነት ከቶ አይሆንምና
አድምጭ እንደገና
በፍቅሬ ፍቅርሽን መፈውስ ቢሳነኝ
ሀዘንሽን ማዘን ከቶ ባይቻለኝ
ዕንባሽን አብሼ
ባንቺ ፈንታ አልቅሼ
ሀዘንሽን አዝኜ
ሥታባክኝ ባክኜ
ካልተገኝኁ እኔ
ስትሞች አላለቅስም
ለቅሶ አልቀመጥም
በሞትሽ አላዝንም
ይልቅስ አድምጭ ነግርሻለው
ስትሞቺ ሞታለው
እከተልሻለው
እዚሕ በበደልኩሽ ላይ ቤት እክስሻለው
እመኝኝ ቃሌ ነው።
ምንጭ፦ አያልቅበት ሰለሞን
@getem
@getem
@gebriel_19
በሂወት እያለሁ እንባዬን ካልጠረግህ ፣
በእኔ እንባ ማንባት ካላዘነ ልብህ ፣
ሰታመም ዝም ካልህ ፣
እራቤ ካልገባህ ፣
ጭንቀቴም ብሶቴም ከመሰለህ ተራ ፣
ድፍርሱ ሂወቴ በፍቅርህ ካልጠራ ፣
ደብዛዛዉ ሂወቴ በፍቅርህ ካልበራ ፣
ተልካሻዉ ኑሮዬን
ካላሰናዳከዉ ፣
የተደላደለ ቦታ ካላሲያዝከዉ ፣
ማየት የተሳነዉ
ፍቅሬን ካልመራሀዉ ፣
እዉነት እልሃለሁ ዉዴ...
ስሞት አትቅበረኝ ፣
እንባም አታንባልኝ ፣
ፀፀትም አትግባ
ይልቁንስ ፍቅሬ...
እንደ ሻማ ቀልጦ ፍቅሬ ሳያልቅብህ ፣
እጂጉን አምሮ ልቤ ሳይቆርጥብህ ፣
ስታመም አስታመኝ ፣
ሰከፋ አፅናናኝ ፣
ስወድቅ ደግፈኝ ፣
የጭንቀቴን ብሶት
የዉስጤን ተረዳኝ ፣
ድፍርሱን ሂወቴን
በፍቅርህ አጥራልኝ ፣
ደብዛዛዉ ሂወቴን
በፍቅርህ አብራልኝ ፣
ተልካሻዉ ኑሮዬ
ፈጥነህ አሰናዳዉ ፣
የተደላደለ ቦታዉን አሲዘዉ ፣
ማየት የተሳነዉ
ልቤን ይዘሀ ምራዉ ፣
ደስታና ፍቅርን ከልብ አስተምረኝ ፣
ሁል ጊዜ ሳቅልኝ ፣
ይሄ ካልሆነ ግን
ስሞት አትቅበረኝ ::
ምንጭ፦ ወንጌላዊት እሙ
=======================
ለ "ስሞት አትቅበረኝ" ግጥም ምላሽ
ከአያልቅበት ሰለሞን
እሙ በህይወት እስካለሽ እንባሽን አብሼ
ስታለቅሺ ሳይሽ ተንሰቅስቄ አልቅሼ
ስትዝኚ ዕያየሁ እጥፍ ካላዘንኩኝ
ምኑን ሰው ተባልኩኝ
ሢያምሽ ካላመመኝ
እራብሽ ካልራበኝ
ምኑን አፈቀርኩሽ ምኑን ወዳጅ ሆንኩኝ
ጭንቀትሽ ብሶትሽ ከመሰለኝ ተራ
ድፍርሱ ህይወትሽ በፍቅሬ ካልጠራ
ተልካሻው ኑሮሽን ካላሰናዳሁት
የተደላደለ ቦታ ካላሲያዝኩት
ምናል ባልተዋወቅን እላለሁኝ ዕኔ
ለፍቅርሽ መከታ ስላለመሆኔ
ይልቅስ አታስቢ ፍቅሬ
ቃል ልግባልሽ ዛሬ
ስታለቅሺ አልቅሼ ስታዝኝም አዝናለው
ባስለቀሰሽ ጉዳይ ዳኛም እሆናለው
እፋረደዋለው።
ፍቅርሽን ቀንበቀን በፍቅሬ አድሳለው
ምስቅልቅል ህይወትሽን ዘውትር አድሳለው
እታመንሻለው
አይንሽ አያለቅስም
ልብሽ አይቆዝምም
ፈገግታሽ አይፈዝም
የፊትሽም ፀዳል ከቶ አይደብዝዝም
ይኸውልሽ ፍቅሬ ቃል ልግባ ደግሜ
ፍቅርሽ ተሰራጭቷል ባካልና ደሜ
ሲያምሽ ያምመኛል ሥታዝኚም አዝናለው
ስታለቅሺ አልቅሼ ስትስቂም ስቃለው
በፊትሽ ብርሐን እኔም እደምቃለው
ነገርግን ፍቅሬ ሆይ ስሚኝ በጽሞና
ምናልባት ሚሆነውን አላውቀውምና
አድምጭ እንደገና
ምናልባት ይህ ቃሌን መጠበቅ ቢያቅተኝ
ለፍቅርሽ መከታ መሖን ቢያታክተኝ
ህይወትሽን ማቃናት ባልችል በስንፍና
ይሄ ወዳጅነት ከቶ አይሆንምና
አድምጭ እንደገና
በፍቅሬ ፍቅርሽን መፈውስ ቢሳነኝ
ሀዘንሽን ማዘን ከቶ ባይቻለኝ
ዕንባሽን አብሼ
ባንቺ ፈንታ አልቅሼ
ሀዘንሽን አዝኜ
ሥታባክኝ ባክኜ
ካልተገኝኁ እኔ
ስትሞች አላለቅስም
ለቅሶ አልቀመጥም
በሞትሽ አላዝንም
ይልቅስ አድምጭ ነግርሻለው
ስትሞቺ ሞታለው
እከተልሻለው
እዚሕ በበደልኩሽ ላይ ቤት እክስሻለው
እመኝኝ ቃሌ ነው።
ምንጭ፦ አያልቅበት ሰለሞን
@getem
@getem
@gebriel_19
* ላንች ይሁን **
ሀቅሽ ገዝፎ
አንችን ከቶ እገፋበት አቅም ነሳኝ፣
ድኩም ልቤ
ነፍሱ ጠ'ባ አስብበት ቀልቤ ጠፋኝ፣
ደግ መንፈስሽ
ከአንች መቅደስ ወደ ውስጤ ሲንቆረቆር፣
ፍቅር የራቃት
ገዳዳዋ ችኩል ልቤ ትርታዋን ስትደረድር፣
ባዶ ቀፎ ገላ
ምናብ አልባው እኔ ቅያስ አሠመረ፣
የነፍሴ ቅኝቷ
እልፍ ደስታን አቅፎ መንገዱን ጀመረ፣
የመኖሬ ምክንያት
ድጋሚ ላይታሠር ሚስጥሩ ተፈታ፣
በፀና መሠረት
የህይወቴ ምህዋር ተሞላ በፌሽታ፣
ላንች ይሁን.........Abrsh
ግንቦት 24/2011 ዓ.ም
@getem
@getem
@getem
ሀቅሽ ገዝፎ
አንችን ከቶ እገፋበት አቅም ነሳኝ፣
ድኩም ልቤ
ነፍሱ ጠ'ባ አስብበት ቀልቤ ጠፋኝ፣
ደግ መንፈስሽ
ከአንች መቅደስ ወደ ውስጤ ሲንቆረቆር፣
ፍቅር የራቃት
ገዳዳዋ ችኩል ልቤ ትርታዋን ስትደረድር፣
ባዶ ቀፎ ገላ
ምናብ አልባው እኔ ቅያስ አሠመረ፣
የነፍሴ ቅኝቷ
እልፍ ደስታን አቅፎ መንገዱን ጀመረ፣
የመኖሬ ምክንያት
ድጋሚ ላይታሠር ሚስጥሩ ተፈታ፣
በፀና መሠረት
የህይወቴ ምህዋር ተሞላ በፌሽታ፣
ላንች ይሁን.........Abrsh
ግንቦት 24/2011 ዓ.ም
@getem
@getem
@getem
በዘርዓሰብ ሣጌጥ የተደረሰው የወጎች፣ መጣጥፎች እና አጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ የሆነው "ሰቆቃወ ዘዪግ" ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ከ11ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ በድምቀት ይመረቃል።
ደራሲው ከዚህ በፊት እግዜር እንቆቅልህ (ግጥሞች)እና ጌርሳም (ረጅም ልብ ወለድ) ማስነበቡ ይታወቃል።
@getem
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ደራሲው ከዚህ በፊት እግዜር እንቆቅልህ (ግጥሞች)እና ጌርሳም (ረጅም ልብ ወለድ) ማስነበቡ ይታወቃል።
@getem
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ለጁምኣችን
እንደ እናንተ መብዛት እንደኔ አንድ መሆን
ምን ይውጠኝ ነበር አላህ ከኔ ባይሆን ።
ይልሃል የወሎ ደረሳ ።
ፈረንጅ ደግሞ ከወሎ ደረሳ ኮርጆ
"God and me are always a majority!!!! ሲል ተልባ ቢንጫጫ ፈጣሪ ካንተ ጋር
ነውና ተልባው በአንድ ሙቀጫ ይደቃል ብሎ ያስደመምሃል ።
--------------------------------------------
ጁመኣን መንዙማ
ያመመው ነው እንጂ መድሀኒት የሚሻው
ያለከፈውማ ይሄዳል እንዳሻው
አሽረው ባሪያህን ሀሳብ
ለመሼከም አይችልም ትካሻው
ሁሉም ተውሶ ነው አንተ ነህ ወጌሻው
ሸጋ ጁምኣ!!💚
@balmbaras
@getem
@getem
እንደ እናንተ መብዛት እንደኔ አንድ መሆን
ምን ይውጠኝ ነበር አላህ ከኔ ባይሆን ።
ይልሃል የወሎ ደረሳ ።
ፈረንጅ ደግሞ ከወሎ ደረሳ ኮርጆ
"God and me are always a majority!!!! ሲል ተልባ ቢንጫጫ ፈጣሪ ካንተ ጋር
ነውና ተልባው በአንድ ሙቀጫ ይደቃል ብሎ ያስደመምሃል ።
--------------------------------------------
ጁመኣን መንዙማ
ያመመው ነው እንጂ መድሀኒት የሚሻው
ያለከፈውማ ይሄዳል እንዳሻው
አሽረው ባሪያህን ሀሳብ
ለመሼከም አይችልም ትካሻው
ሁሉም ተውሶ ነው አንተ ነህ ወጌሻው
ሸጋ ጁምኣ!!💚
@balmbaras
@getem
@getem
*ባዶ ገፅ*
Mr. Trump(የመጨረሻ ግጥም)
(4:13)
ክምር የቃል ናዳ በላክሽው ወረቀት ተፅፎ ይታየኛል
ከደብዳቤሽ በላይ ላንቺ እንዲ መሆኔ ይከነክነኛል
ህመም ይሆነኛል።
የፍቅር ግትልትል የማይሄድ ትዝታ
በትላንቱ ፍቅር በዛሬው እህታ
ስዋልል ስዋልል እንደ ጠፋ ሎሌ ጌታው እንደረሳው
ምን አስዋሸኝ ውዴ በላክሽው መስመር ነው ከተኛበት አለም ያ ልቤ የተነሳው
ቦታ ሳደላድል ቃልሽን ለማንበብ የሚመጥን ሳጣ
ከወንበሬ ስወርድ ካልጋዬ ስወጣ
አልጋውንም ትቼ ወንበር ሳደላድል ቦታ ስመረምር
ምቹ ቦታ አገኘው ከጨረቃ እግር ስር።
ክምር የቃል ናዳ በላክሽው ወረቀት ተፅፎ ይታየኛል
ከደብዳቤሽ በላይ ላንቺ እንዲ መሆኔ ይከነክነኛል
ህመም ይሆነኛል።
ጨረቃ..!
ቋንቋን ያልጀመረው ኮልታፋው ፍቅራችን
ድክ ድክ እያለ እየተራመደ ሲልቅ በላያችን
ከጅማሬ አንስቶ እስከዚ ፍጣሜ
ከጨረቃ በላይ ማን ያውቃል አለሜ!
ከዚች ከጨረቃ ተፋቀሩ ብላ በፍቅር የሚያሞቅ ፍቅር ከሰጠችን
ሙሉነትን ልካ ላልሞላው ፍቅራችን ሙላት ከሆነችን
ከዚች ከጨረቃ በፀዳል ብርሃኗ መልክሽን ከልቤ ከቀረፀችብኝ
በሚሞቅ ብርሃኗ ተዋደዱ ብላ ቃል ካኖረችብኝ
ከእግሯ የተሻለ ቃልሽን ማንበብያ እቴ እንደምን ላገኝ?
ደብዳቤሽ ይዤ አንድ ግዜ አየሗት እንባ ባቀረሩት የደከሙ አይኖቼ
ከነጭ አካሏ ላይ በርታና ግለጠው የሚል ቃል ለማየት አለሜ ጓጉቼ
ሙሉ ናት ታምራለች ልክ እንደምትወጃት
ኮከብ ግን የላትም ዛሬ ብቸኛ ናት።
ሙሉነቷን ሳየው እስከነ ሙላትሽ አንቺን መሰለችኝ
በብቸኝነቷ መንጋው ያገለላት አስታዋሽ ያጣውን ልቤን አሳየችኝ።
በጎዶሎው አለም ሙሉነትን ሰቶ ብርሐን እንደመሆን
ለሰንካላው ተጓዥ መንገድ እንደመሆን
የሚያስደስት የለም
ቀናው በጨረቃ በሐሪዋን መሆን ናፈኩኝ የኔ አለም።
ኮከብ ግን የላትም በድቅድቁ መሀል ብቻዋን ቆማለች
በብቸኝነቷ እኔን ትመስላለች።
በዚ ማጣቴ ላይ ሙሉነት ቢሰጠኝ
ልክ እንደ ጨረቃ አለሙን ላበራ ከሰማይ ነው 'ምገኝ
ምናምን እያልኩኝ የማይረባ ሐሳብ አቀባጥራለው
አወይ ሲጀማምር ከጨረቃ ጋራ ሙግት እገጥማለው
እናልሽ አለሜ
ክምር የቃል ናዳ በላክሽው ወረቀት ተፅፎ ይታየኛል
ከደብዳቤሽ በላይ ላንቺ እንዲ መሆኔ ይከነክነኛል
ህመም ይሆነኛል።
ቃልሽን ገለጥኩት...!
ግዜው እንዳለፈ አውቃለው ካልሽበት ከደብዳቤው አናት
እስከ ቋጨሽበት የመራራቅ ቅኔ የመሄድ ስንብት
ቃላት እየደገምኩ ቃላት እየቆጠርኩ
ካኖርሽው ስሜት ላይ ሃቅ እየሰበስብኩ
ጨረስኩት ቃልሽን አየዋት ጨረቃን ደብዳቤሽን አብራኝ ስላነበበችው ኩስምን ብላለች
ብርሃኗን አታለች ፅልመትን ለብሳለች
ወይ ደሞ ለኔ አይን ያንን የመሰለ አካሏን ልካለች
በቦዘዘው አይኔ ብርሀን አልባ ፋኖስ ወይ መስላ ታይታለች።
ምንድነው ይህ ቃሏ ምንድነው ትርጉሜ
እኔስ የቱ ጋነኝ የቱ ነው ቀለሜ
እውነት እንደ ቃሏ ልቧን የምኮንን ልቧን የምደቃ
ፍቅሯን የምገፋ ከንቱ ነኝ ወይ እኔ ንገሪኝ ጨረቃ
ንገሪኝ በማርያም የፍቅር ልኬቱ ቢገባኝ እኮ ነው
ልቧን ላለመስበር ልቤን የምሰብረው
የሆነውን ቀርቶ ለሚሆነው ገና ይቅርታዋን እንኳ ሳልስማ 'ምተወው
እሷ እንደ ፃፈችው ጠልቻት መች ሆነ ቃላት የማይፈልግ ፍቅር ቢይዘኝ ነው።
ንገሪኝ በማርያም..
እስትንፋስ አጥቼ ምተነፍስበት
ስልኳ ላይ ደውዬ ናፍቅሽኝ 'ምልበት
ትንፋሼን ከልቤ የሚሰውርብኝ እንዳልናገረው
ፍቅሯ አይደለም እንዴ ወይስ እናደለችው ኮከብ ጨረቃዬኔ እኔ ጠልቻት ነው?
ንገሪኝ በማርያም..
አጊንቼ ስለያት ነገ አገኝሽ ይሆን ብዬ መጠየቁ ሀሳቤን ቢከብደው
ከሸኘዋት ወዲ ነገም እመጣለው ብዬ በለሆሳስ ለራሴ የምነግረው
ብወዳት እኮ ነው።
በቃኝ አትንገሪኝ
ለኔም የምትወጪው ለሷም የምትጪው
አንቺው ከሆንሽማ
ባክሽ ተለመኚኝ በዛሬው ጨለማ
የፃፈችው ሁሉ ስለት እንደ ሆነ አይኔን እንደወጋ
እባክሽ ንገርያት ይህ ለሊት ሳይነጋ።
......
ክምር የቃል ናዳ በላክሽው ወረቀት ተፅፎ ይታየኛል
ከደብዳቤሽ በላይ ላንቺ እንዲ መሆኔ ይከነክነኛል
ህመም ይሆነኛል።
ወረቀት አወጣው ብዕሬን አነሳው
ፊትና ሗላውን በገፁ ለያየው
ገፅ አንድ
አየሽ የኔ አበባ ካሰፈርሽው ሁሉ ይኸኛው ይከብዳል
ነብስያውን ሰቶ ዋሸክ እንደ መባል መሞት አቅም ያጣል
ብዙ ቃል የለኝም...
ከሚል ቃላ አንስቶ እስከ ገፁ ማብቂያ ባዶ ገፅ ይታያል
ገፅ ሁለት
የፊቱን ስትገልጪው ቃላት አተሽበት
ሃቄን ያኖርኩበት ነበረው አንድ እውነት
ያልታየሽን እውነት ባልታየኝ ገፅ ላይ ስላሰፈርኩልሽ
ይኸው ስንብቴ
ባዶነቴን ይዤ ልሰነባት እኔ ይኸው ባዶ ገፅሽ።
************
@getem
@getem
@getem
Mr. Trump(የመጨረሻ ግጥም)
(4:13)
ክምር የቃል ናዳ በላክሽው ወረቀት ተፅፎ ይታየኛል
ከደብዳቤሽ በላይ ላንቺ እንዲ መሆኔ ይከነክነኛል
ህመም ይሆነኛል።
የፍቅር ግትልትል የማይሄድ ትዝታ
በትላንቱ ፍቅር በዛሬው እህታ
ስዋልል ስዋልል እንደ ጠፋ ሎሌ ጌታው እንደረሳው
ምን አስዋሸኝ ውዴ በላክሽው መስመር ነው ከተኛበት አለም ያ ልቤ የተነሳው
ቦታ ሳደላድል ቃልሽን ለማንበብ የሚመጥን ሳጣ
ከወንበሬ ስወርድ ካልጋዬ ስወጣ
አልጋውንም ትቼ ወንበር ሳደላድል ቦታ ስመረምር
ምቹ ቦታ አገኘው ከጨረቃ እግር ስር።
ክምር የቃል ናዳ በላክሽው ወረቀት ተፅፎ ይታየኛል
ከደብዳቤሽ በላይ ላንቺ እንዲ መሆኔ ይከነክነኛል
ህመም ይሆነኛል።
ጨረቃ..!
ቋንቋን ያልጀመረው ኮልታፋው ፍቅራችን
ድክ ድክ እያለ እየተራመደ ሲልቅ በላያችን
ከጅማሬ አንስቶ እስከዚ ፍጣሜ
ከጨረቃ በላይ ማን ያውቃል አለሜ!
ከዚች ከጨረቃ ተፋቀሩ ብላ በፍቅር የሚያሞቅ ፍቅር ከሰጠችን
ሙሉነትን ልካ ላልሞላው ፍቅራችን ሙላት ከሆነችን
ከዚች ከጨረቃ በፀዳል ብርሃኗ መልክሽን ከልቤ ከቀረፀችብኝ
በሚሞቅ ብርሃኗ ተዋደዱ ብላ ቃል ካኖረችብኝ
ከእግሯ የተሻለ ቃልሽን ማንበብያ እቴ እንደምን ላገኝ?
ደብዳቤሽ ይዤ አንድ ግዜ አየሗት እንባ ባቀረሩት የደከሙ አይኖቼ
ከነጭ አካሏ ላይ በርታና ግለጠው የሚል ቃል ለማየት አለሜ ጓጉቼ
ሙሉ ናት ታምራለች ልክ እንደምትወጃት
ኮከብ ግን የላትም ዛሬ ብቸኛ ናት።
ሙሉነቷን ሳየው እስከነ ሙላትሽ አንቺን መሰለችኝ
በብቸኝነቷ መንጋው ያገለላት አስታዋሽ ያጣውን ልቤን አሳየችኝ።
በጎዶሎው አለም ሙሉነትን ሰቶ ብርሐን እንደመሆን
ለሰንካላው ተጓዥ መንገድ እንደመሆን
የሚያስደስት የለም
ቀናው በጨረቃ በሐሪዋን መሆን ናፈኩኝ የኔ አለም።
ኮከብ ግን የላትም በድቅድቁ መሀል ብቻዋን ቆማለች
በብቸኝነቷ እኔን ትመስላለች።
በዚ ማጣቴ ላይ ሙሉነት ቢሰጠኝ
ልክ እንደ ጨረቃ አለሙን ላበራ ከሰማይ ነው 'ምገኝ
ምናምን እያልኩኝ የማይረባ ሐሳብ አቀባጥራለው
አወይ ሲጀማምር ከጨረቃ ጋራ ሙግት እገጥማለው
እናልሽ አለሜ
ክምር የቃል ናዳ በላክሽው ወረቀት ተፅፎ ይታየኛል
ከደብዳቤሽ በላይ ላንቺ እንዲ መሆኔ ይከነክነኛል
ህመም ይሆነኛል።
ቃልሽን ገለጥኩት...!
ግዜው እንዳለፈ አውቃለው ካልሽበት ከደብዳቤው አናት
እስከ ቋጨሽበት የመራራቅ ቅኔ የመሄድ ስንብት
ቃላት እየደገምኩ ቃላት እየቆጠርኩ
ካኖርሽው ስሜት ላይ ሃቅ እየሰበስብኩ
ጨረስኩት ቃልሽን አየዋት ጨረቃን ደብዳቤሽን አብራኝ ስላነበበችው ኩስምን ብላለች
ብርሃኗን አታለች ፅልመትን ለብሳለች
ወይ ደሞ ለኔ አይን ያንን የመሰለ አካሏን ልካለች
በቦዘዘው አይኔ ብርሀን አልባ ፋኖስ ወይ መስላ ታይታለች።
ምንድነው ይህ ቃሏ ምንድነው ትርጉሜ
እኔስ የቱ ጋነኝ የቱ ነው ቀለሜ
እውነት እንደ ቃሏ ልቧን የምኮንን ልቧን የምደቃ
ፍቅሯን የምገፋ ከንቱ ነኝ ወይ እኔ ንገሪኝ ጨረቃ
ንገሪኝ በማርያም የፍቅር ልኬቱ ቢገባኝ እኮ ነው
ልቧን ላለመስበር ልቤን የምሰብረው
የሆነውን ቀርቶ ለሚሆነው ገና ይቅርታዋን እንኳ ሳልስማ 'ምተወው
እሷ እንደ ፃፈችው ጠልቻት መች ሆነ ቃላት የማይፈልግ ፍቅር ቢይዘኝ ነው።
ንገሪኝ በማርያም..
እስትንፋስ አጥቼ ምተነፍስበት
ስልኳ ላይ ደውዬ ናፍቅሽኝ 'ምልበት
ትንፋሼን ከልቤ የሚሰውርብኝ እንዳልናገረው
ፍቅሯ አይደለም እንዴ ወይስ እናደለችው ኮከብ ጨረቃዬኔ እኔ ጠልቻት ነው?
ንገሪኝ በማርያም..
አጊንቼ ስለያት ነገ አገኝሽ ይሆን ብዬ መጠየቁ ሀሳቤን ቢከብደው
ከሸኘዋት ወዲ ነገም እመጣለው ብዬ በለሆሳስ ለራሴ የምነግረው
ብወዳት እኮ ነው።
በቃኝ አትንገሪኝ
ለኔም የምትወጪው ለሷም የምትጪው
አንቺው ከሆንሽማ
ባክሽ ተለመኚኝ በዛሬው ጨለማ
የፃፈችው ሁሉ ስለት እንደ ሆነ አይኔን እንደወጋ
እባክሽ ንገርያት ይህ ለሊት ሳይነጋ።
......
ክምር የቃል ናዳ በላክሽው ወረቀት ተፅፎ ይታየኛል
ከደብዳቤሽ በላይ ላንቺ እንዲ መሆኔ ይከነክነኛል
ህመም ይሆነኛል።
ወረቀት አወጣው ብዕሬን አነሳው
ፊትና ሗላውን በገፁ ለያየው
ገፅ አንድ
አየሽ የኔ አበባ ካሰፈርሽው ሁሉ ይኸኛው ይከብዳል
ነብስያውን ሰቶ ዋሸክ እንደ መባል መሞት አቅም ያጣል
ብዙ ቃል የለኝም...
ከሚል ቃላ አንስቶ እስከ ገፁ ማብቂያ ባዶ ገፅ ይታያል
ገፅ ሁለት
የፊቱን ስትገልጪው ቃላት አተሽበት
ሃቄን ያኖርኩበት ነበረው አንድ እውነት
ያልታየሽን እውነት ባልታየኝ ገፅ ላይ ስላሰፈርኩልሽ
ይኸው ስንብቴ
ባዶነቴን ይዤ ልሰነባት እኔ ይኸው ባዶ ገፅሽ።
************
@getem
@getem
@getem
በዘርዓሰብ ሣጌጥ የተደረሰው የወጎች፣ መጣጥፎች እና አጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ የሆነው "ሰቆቃወ ዘዪግ" ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ከ11ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ በድምቀት ይመረቃል።
ደራሲው ከዚህ በፊት እግዜር እንቆቅልህ (ግጥሞች)እና ጌርሳም (ረጅም ልብ ወለድ) ማስነበቡ ይታወቃል።
መግቢያ በነፃ
@getem
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ደራሲው ከዚህ በፊት እግዜር እንቆቅልህ (ግጥሞች)እና ጌርሳም (ረጅም ልብ ወለድ) ማስነበቡ ይታወቃል።
መግቢያ በነፃ
@getem
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
......አንች?....
የጭካኔ አቁማዳ የክህደት አቢይ በርኖስ፣
የይሁዳ የበኩር ልጅ ታናሽ እህቱ ለዲያብሎስ፣
አንች የሸንበቆ መቋሚያ በትረ ሳጥናኤል ለአርዮስ፣
የዝሙት ማህደሩ የሰቆቃ መፅሐፍ አትሮኑስ፣
....አንች?..
የመንገድ አሽክትጥቁር ሽንጉግ የጓሮ ታኮ ዘመድ፣
ቀላዋጭ ቀበዝባዛ የሲኦል አቢይ መንገድ።
........ህ......
እንዲህ እያልሁ ልመርቅሽ ፈጣሪ እድሜውን ይስጥሽ፣
በጆረፌ ገላሽ ነዶ ማከኪያ ጥፍሩን ያሳጣሽ፤
በላየ ላይ እንደ ነገድሽ በላይሽ ላይ ይነግዱ፣
የፍቅርሽን ማህፀን ንደው በገላሽ ሸርተቴ ይውረዱ።
....ተባረኪ የኔ ሌባ¡¡...
አይኖችሽ የብርሃን ግርዶሽ እግሮችሽ እሾህ ያጥልቁ፣
የተኩራራሽባቸው ክንዶች
በሲኖ ትራክ ይድቀቁ።
....ተባረኪ...
ለአይኖችሽ ስለታም ጉጥ ለጥርሶችሽ ጥቁር ድንጋይ፣
ለፀጉርሽ የእሳት ሰደድ ለአንገትሽ የሰይፍ እንኮይ፤
ለወገብሽ ብረት መጋዝ ለጭኖችሽ የእሳት ላንቃ፣
ለቂጥሽ አጋም እሾህ ለደረትሽ ብረት ሰደቃ፣
አብዝቶ ስቃዩን ይስጥሽ ኪስሽ እንደ ቾክ ይንጣ፣
አፅመ ህሊናሽ ተቀጥቅጦ ከሃዲ ገላሽ ይገርጣ፤
.......ህ......
ገላሽ በንፍርውሃ ይቀቀል ልቦናሽ በክህደት እሳት ይብሰል፣
ጡቶችሽ በሰይፍ ይታሹ ምላስሽ ለጅብ ይጠልጠል፤
...ተባረኪ እድሜ ይስጥሽ....
የስሜት ጭኖችሽ ሢሞቁ የስሜት ጭኑ ይሙትብሽ፣
ውስጤን በቅናት እንዳ ቀለጥሽው እንደቅቤ ይቅለጥ ልብሽ፣
ክንድሽ በአመድ ይታቀፍ ጣትሽ በክር ይታበት፣
ልሳንሽ በሀፍረት ይመረግ የአፍሽ እጢ ያምንጭ እበት።
...ብሩክ ያርግሽ..
ፈጣሪ ጤናውን ነስቶ እንደ ማቱሳላ እድሜ ይስጥሽ፤
እንደ እዮብ ስጋሽ ይንፈር እንደ መፃጉ ያጉብጥሽ።
......ተበረኪ የኔ ሌባ¡..
ለምን መረቅኸኝ ካልሽኝ ? ምስጢሩ እንዲህ ነው አልሁሽ፣
በፍቅርሽ ህማም ታምሜ ለአመታት ብጠይቅሽ፣
በዝምታ በተደሞ በአይኖችሽ ሽፋል ደልለሽ፣
ገደል ግባ አልሽኝ ሳታፍሪ በእኔ ላይ ፍቅር አጫርተሽ።
.....እናም ተበረኪ...
የተኩራራሽበት ገላሽ ፈርሶ ይሁን የዝንብ መዋያ፣
ለሚወዱሽ ግም ጠረንሽ መሣሪያ ይሁን ማባረሪያ።
.....ቡሩክ ያርግሽ...
እንደ ቶማስ ቆዳሽ ተገፎ ገላሽን ውሻ ይላሰው፣
ሸንጋይ ጥርሶችሽ ሣር ይጋጡ እንደ ናቡከደነፆር አጎንብሰው፣(2)
(ሶሎሞን ያይንዋጋ)
@getem
@getem
@getem
የጭካኔ አቁማዳ የክህደት አቢይ በርኖስ፣
የይሁዳ የበኩር ልጅ ታናሽ እህቱ ለዲያብሎስ፣
አንች የሸንበቆ መቋሚያ በትረ ሳጥናኤል ለአርዮስ፣
የዝሙት ማህደሩ የሰቆቃ መፅሐፍ አትሮኑስ፣
....አንች?..
የመንገድ አሽክትጥቁር ሽንጉግ የጓሮ ታኮ ዘመድ፣
ቀላዋጭ ቀበዝባዛ የሲኦል አቢይ መንገድ።
........ህ......
እንዲህ እያልሁ ልመርቅሽ ፈጣሪ እድሜውን ይስጥሽ፣
በጆረፌ ገላሽ ነዶ ማከኪያ ጥፍሩን ያሳጣሽ፤
በላየ ላይ እንደ ነገድሽ በላይሽ ላይ ይነግዱ፣
የፍቅርሽን ማህፀን ንደው በገላሽ ሸርተቴ ይውረዱ።
....ተባረኪ የኔ ሌባ¡¡...
አይኖችሽ የብርሃን ግርዶሽ እግሮችሽ እሾህ ያጥልቁ፣
የተኩራራሽባቸው ክንዶች
በሲኖ ትራክ ይድቀቁ።
....ተባረኪ...
ለአይኖችሽ ስለታም ጉጥ ለጥርሶችሽ ጥቁር ድንጋይ፣
ለፀጉርሽ የእሳት ሰደድ ለአንገትሽ የሰይፍ እንኮይ፤
ለወገብሽ ብረት መጋዝ ለጭኖችሽ የእሳት ላንቃ፣
ለቂጥሽ አጋም እሾህ ለደረትሽ ብረት ሰደቃ፣
አብዝቶ ስቃዩን ይስጥሽ ኪስሽ እንደ ቾክ ይንጣ፣
አፅመ ህሊናሽ ተቀጥቅጦ ከሃዲ ገላሽ ይገርጣ፤
.......ህ......
ገላሽ በንፍርውሃ ይቀቀል ልቦናሽ በክህደት እሳት ይብሰል፣
ጡቶችሽ በሰይፍ ይታሹ ምላስሽ ለጅብ ይጠልጠል፤
...ተባረኪ እድሜ ይስጥሽ....
የስሜት ጭኖችሽ ሢሞቁ የስሜት ጭኑ ይሙትብሽ፣
ውስጤን በቅናት እንዳ ቀለጥሽው እንደቅቤ ይቅለጥ ልብሽ፣
ክንድሽ በአመድ ይታቀፍ ጣትሽ በክር ይታበት፣
ልሳንሽ በሀፍረት ይመረግ የአፍሽ እጢ ያምንጭ እበት።
...ብሩክ ያርግሽ..
ፈጣሪ ጤናውን ነስቶ እንደ ማቱሳላ እድሜ ይስጥሽ፤
እንደ እዮብ ስጋሽ ይንፈር እንደ መፃጉ ያጉብጥሽ።
......ተበረኪ የኔ ሌባ¡..
ለምን መረቅኸኝ ካልሽኝ ? ምስጢሩ እንዲህ ነው አልሁሽ፣
በፍቅርሽ ህማም ታምሜ ለአመታት ብጠይቅሽ፣
በዝምታ በተደሞ በአይኖችሽ ሽፋል ደልለሽ፣
ገደል ግባ አልሽኝ ሳታፍሪ በእኔ ላይ ፍቅር አጫርተሽ።
.....እናም ተበረኪ...
የተኩራራሽበት ገላሽ ፈርሶ ይሁን የዝንብ መዋያ፣
ለሚወዱሽ ግም ጠረንሽ መሣሪያ ይሁን ማባረሪያ።
.....ቡሩክ ያርግሽ...
እንደ ቶማስ ቆዳሽ ተገፎ ገላሽን ውሻ ይላሰው፣
ሸንጋይ ጥርሶችሽ ሣር ይጋጡ እንደ ናቡከደነፆር አጎንብሰው፣(2)
(ሶሎሞን ያይንዋጋ)
@getem
@getem
@getem
መቼም ታውቂዋልሽ
።።።።።።።።።።።።።
ድንጉጥ ነው መንፈሴ
ፈሪ ነው ልቤ እንደው፣
ታዲያ እንዴት አድርጌ
ቁጣሽን ልልመደው።
ኩርፊያሽን ላብርደው።
ምናለኝ ከኩርፊያሽ፣
ምን አለኝ ከቁጣሽ።
ጠልቼስ አይደለም፣
እንድትስቂልኝ ነው፣
አስክትሰክኚ ልጣሽ።
@getem
@getem
@paappii
#astawseng regasa
።።።።።።።።።።።።።
ድንጉጥ ነው መንፈሴ
ፈሪ ነው ልቤ እንደው፣
ታዲያ እንዴት አድርጌ
ቁጣሽን ልልመደው።
ኩርፊያሽን ላብርደው።
ምናለኝ ከኩርፊያሽ፣
ምን አለኝ ከቁጣሽ።
ጠልቼስ አይደለም፣
እንድትስቂልኝ ነው፣
አስክትሰክኚ ልጣሽ።
@getem
@getem
@paappii
#astawseng regasa
❤1
የዘመነኛው ኑዛዜ!!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።
እንኳን አንተ አባቴ!
ጨለማው ምናብ ላይ ~ ፋኖስን ለኩሰህ
ከመሀል እስከ ጫፍ ~ የዞርከው ጀግነህ
ሀገርን በሌማት.. .
ለመቋደሻችን ~ ዘርግተህ የሰጠህ
ስንቱ ታሪክ አባሽ
ስንቱ አዳም አስለቃሽ
ገሀዱ እውነታው ~ ሀቅታው ታብሎ
ሀውልቱ ይቆማል.. .
ኧኸተማ መሀል ~ ዠግና ነው ተብሎ።
።።።።
እምዬ ሚኒልክ
የፅናታችን ልክ
ሀላፊ አግዳሚው ~ ታሪክህን ቢሰማ
አረሙን መንግሎ...
የባርነትን ጥግ ~ የሀሳቡን ጥሻ ~ መንጥሮ ቢያለማ
ለባንዳ ህመም ሆነህ ~ መቅደሱ ፊትለፊት ~ ቁምልን በግርማ።
።።።።
ቁምልን አባቴ!
በአክሊል አጊጥህ ~ ተውበህ በካባ
ልጓምህን አንቀህ ~ ኸፈረስህ ጀርባ
ማነው? ብለው ሲሉን ~ ንጉስ ነው እንድንል
ሸማችን ሲሳሳ...
ሀገር እንዳይበርዳት ~ ታሪክ እንድንፈትል
ወኔያችን ሲላላ...
ዳግም ዘራፍ ብለን ~ በስምህ እንድንምል
በዓለም ጎዳና ላይ...
ግዞተኛ ሆነን ~ እንዳንቆርጥ ተስፋ
ለምልክት ቆመህ...
የአርነት መለከት ~ በኩራት ይነፋ ።
መልካም ልደት ሚኒሊክ
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።
እንኳን አንተ አባቴ!
ጨለማው ምናብ ላይ ~ ፋኖስን ለኩሰህ
ከመሀል እስከ ጫፍ ~ የዞርከው ጀግነህ
ሀገርን በሌማት.. .
ለመቋደሻችን ~ ዘርግተህ የሰጠህ
ስንቱ ታሪክ አባሽ
ስንቱ አዳም አስለቃሽ
ገሀዱ እውነታው ~ ሀቅታው ታብሎ
ሀውልቱ ይቆማል.. .
ኧኸተማ መሀል ~ ዠግና ነው ተብሎ።
።።።።
እምዬ ሚኒልክ
የፅናታችን ልክ
ሀላፊ አግዳሚው ~ ታሪክህን ቢሰማ
አረሙን መንግሎ...
የባርነትን ጥግ ~ የሀሳቡን ጥሻ ~ መንጥሮ ቢያለማ
ለባንዳ ህመም ሆነህ ~ መቅደሱ ፊትለፊት ~ ቁምልን በግርማ።
።።።።
ቁምልን አባቴ!
በአክሊል አጊጥህ ~ ተውበህ በካባ
ልጓምህን አንቀህ ~ ኸፈረስህ ጀርባ
ማነው? ብለው ሲሉን ~ ንጉስ ነው እንድንል
ሸማችን ሲሳሳ...
ሀገር እንዳይበርዳት ~ ታሪክ እንድንፈትል
ወኔያችን ሲላላ...
ዳግም ዘራፍ ብለን ~ በስምህ እንድንምል
በዓለም ጎዳና ላይ...
ግዞተኛ ሆነን ~ እንዳንቆርጥ ተስፋ
ለምልክት ቆመህ...
የአርነት መለከት ~ በኩራት ይነፋ ።
መልካም ልደት ሚኒሊክ
@getem
@getem
@getem
ለቅዳሚታችን
❤️❤️❤️❤️❤️
.....
ካድሚልኝ እስቲ
ከቡናው ገበታ
# ጨስ_ጨስ አድርጊልኝ
ልቤም አያመንታ
ዷ ለአድርግ ለአንቺ
ቢደርስ ፀሎቴ
አንቺን ቢያስገኝልኝ
ከራማው ታቦቴ
ቁጭ ካልሽ ከቡናው
ቁጭ ካልሽ ከቡናው
መገን ልመርቅሽ
.
.
ተስፋሁን ከበደ
@getem
@getem
@balmbaras
❤️❤️❤️❤️❤️
.....
ካድሚልኝ እስቲ
ከቡናው ገበታ
# ጨስ_ጨስ አድርጊልኝ
ልቤም አያመንታ
ዷ ለአድርግ ለአንቺ
ቢደርስ ፀሎቴ
አንቺን ቢያስገኝልኝ
ከራማው ታቦቴ
ቁጭ ካልሽ ከቡናው
ቁጭ ካልሽ ከቡናው
መገን ልመርቅሽ
.
.
ተስፋሁን ከበደ
@getem
@getem
@balmbaras
👍1
//የይሁዳ ገመድ//
ገርበብ ባለ ሰማይ፣ በሩ ያልተዘጋ፤
ደጅ የተበተኑ ፣የከዋክብት መንጋ፤
ሳቅ ሳቅ የሚላት፣ ሸራፋ ጨረቃ፤
ቁልቁል ታፈጣለች፣ በእኛ እጅግ ተደንቃ፡፡
እኛ
በፀለመ ፅለመት ፣አብርሆት ለኮስን፤
በመጣጣም ጥላ፣ ከሰው ተጠለልን፤
ጣቶችሽ በጣቴ፣ መሃል ተጣመሩ፤
በስሜት ጌሾ፣ ጠጥተው ሰክሩ፤
ግለትን ሊፈጠሩ፡፡
አይኖችሽ ውስጥ ፣ያለ የፍቅር ነበልባል፤
አይኖቼን ገረፈው፤
ትኩሱ ትንፋሽሽ፣ እኔነቴን ሳበው፤
በገላሽ ፍኖት፣ አይኔን ጨፍናለው፤
መንታ ከንፈርሽ ፣ከንፈሬን ሲስመው፤
ልትክጂው እንደሆን፣ ለቤ ያኔ ታወቀው፡፡
አንቺ ይሁዳ ሴት፣ እስኪ ልጠይቅሽ፤
መሳሳም ምንድ ነው(
የመሳም አባትሽ፤
የመሳምን ክደት ፣መላ ሲያስተምርሽ፤
ራሱን ማጥፋቱ፣ ለምን አልነገረሽ፤
እስኪ ልጠይቅሽ(
አንቺ ማለት ይሁዳ!
ወደሽ የጠላሽኝ፤
ስቀርብሽ የራቅሽኝ፤
አንቺ እኮ ይሁዳ ፤
እኔ ደግሞ ጌታ!
ላንቺ ሲል የባዘንኩ፤
ላንቺ ሲል የዋለልኩ፤
ላንቺ ሲል የኖርኩ፤
ላንቺ ሲል የሞትኩ፤
እኔ ማለት ጌታ፡ አንቺ ደግሞ ይሁዳ፡፡
እንድት ረሳሽው!
አምላኬ ባረግሽ ፣ጣኦቴ ሆነሽ፤
በምን ቀለም ይሁን ፣ስምሽን የፃፍሽ፤
ካንቺ ሌላ ካህን ፣እንዳይቀድስ አርገሽ፤
ቅዱሱ ልቤ ውስጥ፣ ለብቻሽ ለመነንሽ፤
ልብ ማጥፊያ ፍቅር፣ ማን ይሆን የካነሽ(
እስኪ ልጠይቅሽ(
ገርበብ ያለ ሰማይ፣ በሩ ተጠርቅሞ፤
ጨረቃ አነባች፣ የኔ ፍቅር ታሞ፤
ባንቺ ክህደት ፍቅር፣ ተሰቅዬ ሳለው፤
ተጠማው ተጠማው፤
ደቀመዝሙሬ ሆይ፣ እኔ አንቺን ተጠማው፤
እባክሽ አለሜ ፣ክደትሽን ችዬ፡ መሳምሽን
ልሳም፤
ከነ ጲላጦስ ፊት ፣ምርኮዬን ባላጣም፤
ዝምታን ቢመርጥም
ያለበዚያ!
እኔም እንደ አምላኬ ፣ፅዋሽን ከጠጣው፤
ተፈፀመ በቃ ፣እኔ እሱን አይደለው፤
ሞቼ የምነሳው
በ በዛብህ ብርሃኑ
@getem
@getem
@gebriel_19
ገርበብ ባለ ሰማይ፣ በሩ ያልተዘጋ፤
ደጅ የተበተኑ ፣የከዋክብት መንጋ፤
ሳቅ ሳቅ የሚላት፣ ሸራፋ ጨረቃ፤
ቁልቁል ታፈጣለች፣ በእኛ እጅግ ተደንቃ፡፡
እኛ
በፀለመ ፅለመት ፣አብርሆት ለኮስን፤
በመጣጣም ጥላ፣ ከሰው ተጠለልን፤
ጣቶችሽ በጣቴ፣ መሃል ተጣመሩ፤
በስሜት ጌሾ፣ ጠጥተው ሰክሩ፤
ግለትን ሊፈጠሩ፡፡
አይኖችሽ ውስጥ ፣ያለ የፍቅር ነበልባል፤
አይኖቼን ገረፈው፤
ትኩሱ ትንፋሽሽ፣ እኔነቴን ሳበው፤
በገላሽ ፍኖት፣ አይኔን ጨፍናለው፤
መንታ ከንፈርሽ ፣ከንፈሬን ሲስመው፤
ልትክጂው እንደሆን፣ ለቤ ያኔ ታወቀው፡፡
አንቺ ይሁዳ ሴት፣ እስኪ ልጠይቅሽ፤
መሳሳም ምንድ ነው(
የመሳም አባትሽ፤
የመሳምን ክደት ፣መላ ሲያስተምርሽ፤
ራሱን ማጥፋቱ፣ ለምን አልነገረሽ፤
እስኪ ልጠይቅሽ(
አንቺ ማለት ይሁዳ!
ወደሽ የጠላሽኝ፤
ስቀርብሽ የራቅሽኝ፤
አንቺ እኮ ይሁዳ ፤
እኔ ደግሞ ጌታ!
ላንቺ ሲል የባዘንኩ፤
ላንቺ ሲል የዋለልኩ፤
ላንቺ ሲል የኖርኩ፤
ላንቺ ሲል የሞትኩ፤
እኔ ማለት ጌታ፡ አንቺ ደግሞ ይሁዳ፡፡
እንድት ረሳሽው!
አምላኬ ባረግሽ ፣ጣኦቴ ሆነሽ፤
በምን ቀለም ይሁን ፣ስምሽን የፃፍሽ፤
ካንቺ ሌላ ካህን ፣እንዳይቀድስ አርገሽ፤
ቅዱሱ ልቤ ውስጥ፣ ለብቻሽ ለመነንሽ፤
ልብ ማጥፊያ ፍቅር፣ ማን ይሆን የካነሽ(
እስኪ ልጠይቅሽ(
ገርበብ ያለ ሰማይ፣ በሩ ተጠርቅሞ፤
ጨረቃ አነባች፣ የኔ ፍቅር ታሞ፤
ባንቺ ክህደት ፍቅር፣ ተሰቅዬ ሳለው፤
ተጠማው ተጠማው፤
ደቀመዝሙሬ ሆይ፣ እኔ አንቺን ተጠማው፤
እባክሽ አለሜ ፣ክደትሽን ችዬ፡ መሳምሽን
ልሳም፤
ከነ ጲላጦስ ፊት ፣ምርኮዬን ባላጣም፤
ዝምታን ቢመርጥም
ያለበዚያ!
እኔም እንደ አምላኬ ፣ፅዋሽን ከጠጣው፤
ተፈፀመ በቃ ፣እኔ እሱን አይደለው፤
ሞቼ የምነሳው
በ በዛብህ ብርሃኑ
@getem
@getem
@gebriel_19
ምኒሊክ !!!!!!!!!!!!!!!!!!
ምኒሊክ ተወልዶ ፤
ባይተኩስ ናስማሰር ፤ ባያነሳ ሞይዘር ፤
ባንዳና ሰላቶ ፤
ፓስታ እያስቀቀለ፤ ተጫውቶብን ነበር ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባይባል ነፍጠኛ ፤
ተሸከም እያለ ፤
ተጫውቶብን ነበር ባንዳና ጎጠኛ ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባይባል እምዬ ፤
መይሳው ጃሎ ሲል ባይመጣ ገብርዬ ፤
አገር ሞታ ነበር ኧረ እናንተ ሆዬ ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ዘገር ፤
ሹምባሻና ባንዳ፤
እንደዝክር ቂጣ፤
ቁርስርስ አድርጎ በጨረሰን ነበር ።
ምኒሊክ ተወልዶ ፤
ባድዋ ሰማይ ላይ ፤
ደመቅመቅ ብላ ፤ ባትወጣ ጠሃይ ፤
ጦቢያን ያህል ሃገር ፤ ይገኝ ነበር ወይ? ???
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
መልካም ልደት 👑👑👑👑👑👑
@getem
@getem
@balmbaras
ምኒሊክ ተወልዶ ፤
ባይተኩስ ናስማሰር ፤ ባያነሳ ሞይዘር ፤
ባንዳና ሰላቶ ፤
ፓስታ እያስቀቀለ፤ ተጫውቶብን ነበር ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባይባል ነፍጠኛ ፤
ተሸከም እያለ ፤
ተጫውቶብን ነበር ባንዳና ጎጠኛ ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባይባል እምዬ ፤
መይሳው ጃሎ ሲል ባይመጣ ገብርዬ ፤
አገር ሞታ ነበር ኧረ እናንተ ሆዬ ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ዘገር ፤
ሹምባሻና ባንዳ፤
እንደዝክር ቂጣ፤
ቁርስርስ አድርጎ በጨረሰን ነበር ።
ምኒሊክ ተወልዶ ፤
ባድዋ ሰማይ ላይ ፤
ደመቅመቅ ብላ ፤ ባትወጣ ጠሃይ ፤
ጦቢያን ያህል ሃገር ፤ ይገኝ ነበር ወይ? ???
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
መልካም ልደት 👑👑👑👑👑👑
@getem
@getem
@balmbaras