ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
...ተይ ግን እንታረቅB...
#የበእውቀቱ_ስዩም_ልጅ😉

እኔ ስለማመጥ፤ አንቺ ስትይ እንቢ
ማር እየላስሽልኝ፤ እየበላኝ ቢንቢ
መልኬ መስሎ ቡግር፤
ልቤን ይዞት ፍቅር...
አይተሽ አትለፊ፤ ውዴ ሆይ ተረጂ
እኔ ላግባሽና፤ ከሌላ ውለጂ😂
(ብዬ ባልልሽም)

እና ያንቺ መቅበጥ፤
የኔ መለማመጥ
የልቤ መልጥመጥ፤
የልብሽ መቁረጥ-ቀጥ
ትንፋሽ እያሳጣኝ-እየካደኝ ልቤ
ሀኪም ላያድነኝ-ቀይ ደሜን ታልቤ
በላመ ምርመራ-በተረጋገጠ
የህመሜን ሚዛን-ፍቅርሽ እረገጠ፡፡

መድሀኒት ስለሆንሽ፤ ፈዋሽ ለህመሜ
በአካል ካልሆነ፤ አትምጪ በህልሜ
እንቢ ካልሺም እሺ
እሺ ካልሺም እሺ
ብቻ ልለምንሽ፤ ልብስ ግን ልበሺ

በቅዠት እርቃንሽ- ሲያወልቅብኝ ሱሪ
በእውን ውበትሽ- እያስባለኝ እሪ..
እንዴት እኔ ልበድ-አንቺ ተናገሪ።

አሁን ስለገባኝ፤ ለማበድም ምቾት
ለማልቀስም ብሶት፤
ስለ-ማስፈለጉ
ቅርብ ስለማይሆን፤ ለመሀልም ጥጉ
ቀረብ በይኝና፤ ሁነሽ አጠገቤ
የተንቀዠቀዠው፤ ይረጋጋ ልቤ፡፡ቀልቤ።

[አብርሃም ሙሉ]

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1