ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የወፈፌው ቃላት!!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
ደግሞ ተነሳብኝ!
የአምና ካቻምናው ፥ የፊቱ እብደቴ
አንቺን ባየው ቁጥር.. .
ወፈፈ ሚያስብለኝ ፥ ህመም ምልክቴ።
ይኸው ፌስታል ሸረብሁ !
ቡልኮዬን ቀደድሁ
ገረባዬን ሸከፍሁ
ካላፊ ካግዳሚው ...
ቅጥሬን ለይቼ ፥ በፅኑ ተኳረፍሁ።
ብልሀት በራቀው ፥ መላ በሌለበት
ህመምን የሚያብስ...
ከንፈር መጣጭ ሀኪም ፥ ደጁን በሞላበት
ከተማ ሸሽቼ ...
ብቻዬን ወጥቼ...
ለሚሰግር ፍቅር ፥ መንገድ ላበጅለት
አበድሁ ስላንቺ ...
ያለ አንዳች ከልካይ ፥ ተመላለሺበት ።
ይኸው እንኪ ሰበዙን
የልምዱ እብደቴን...
በወስፌ ለይተሽ ፥ መሶቡን አበጂ
ተቀበይ ህመሜን!
አንጀትሽ እንዲርስ...
ከዳሩ ላይ ጨልፈሽ ፥ ወይንሽን ቅጂ ።
እንኪ ንሽማሽን!
ዘርጊው መዳፍሽን ...
ጠያቂው በተርታ ፥ በሰልፍ ተሰድሮ
ምን ክፉ አጊንቶህ
ከጤናህ ተሽረህ ፥ ሆንህ እንደ ድሮ ?
ብለው ሳይጠይቁኝ ....
#እኔም በተራዬ
"አዎን እንደዚህ ነው !
ሰው ፍቅርን ሊያነግስ ፥
ልቡን ተሸክሞ ፥ ሲወርድ ከገበያ
አቅልን የመሳት ፥ የእብደት መጀመርያ
ደግሞም የእውነት ህመም ...
መላወሻ አልባው ፥ ሀቀኛው በሽታ
ሰው ልቡን አቅርቦ ፥ ዘርግቶ በፎጣ
ሸማች ሲርቀው ነው ፥ የሚገዛው ሲያጣ "
ብዬ ሳልመልስ ፥ ሳይገለጥ ምክንያቴ
ፈጥነሽ ድረሽልኝ ፥ ተሿሚ ልዕልቴ ።

@getem
@getem
@getem
#የወፈፌው ቃላት!!

(ሚካኤል አስጨናቂ) 

።።።።።።።።።።።።።።።

ደግሞ ተነሳብኝ!

የአምና ካቻምናው ፥ የፊቱ እብደቴ

አንቺን ባየው ቁጥር.. .

ወፈፈ ሚያስብለኝ ፥ ህመም ምልክቴ።

ይኸው ፌስታል ሸረብሁ !

ቡልኮዬን ቀደድሁ 

ገረባዬን ሸከፍሁ 

ካላፊ ካግዳሚው ...

ቅጥሬን ለይቼ ፥  በፅኑ ተኳረፍሁ።

ብልሀት በራቀው ፥ መላ በሌለበት 

ህመምን የሚያብስ...

ከንፈር መጣጭ ሀኪም ፥ ደጁን በሞላበት

ከተማ ሸሽቼ ...

ብቻዬን ወጥቼ...

ለሚሰግር ፍቅር ፥ መንገድ ላበጅለት 

አበድሁ ስላንቺ ... 

ያለ አንዳች ከልካይ ፥ ተመላለሺበት ።

ይኸው እንኪ ሰበዙን

የልምዱ እብደቴን...

በወስፌ ለይተሽ ፥ መሶቡን አበጂ 

ተቀበይ ህመሜን!

አንጀትሽ እንዲርስ...

ከዳሩ ላይ ጨልፈሽ ፥ ወይንሽን ቅጂ ።

እንኪ ንሽማሽን!

ዘርጊው መዳፍሽን ...

ጠያቂው በተርታ ፥ በሰልፍ ተሰድሮ 

ምን ክፉ አጊንቶህ

ከጤናህ ተሽረህ ፥ ሆንህ እንደ ድሮ ?

ብለው ሳይጠይቁኝ ....

#እኔም በተራዬ

"አዎን እንደዚህ ነው !

ሰው ፍቅርን ሊያነግስ  ፥ 

ልቡን ተሸክሞ ፥ ሲወርድ ከገበያ

አቅልን የመሳት ፥ የእብደት መጀመርያ 

ደግሞም የእውነት ህመም ...

መላወሻ አልባው ፥ ሀቀኛው በሽታ

ሰው ልቡን አቅርቦ ፥  ዘርግቶ በፎጣ 

ሸማች ሲርቀው ነው  ፥ የሚገዛው ሲያጣ "

ብዬ ሳልመልስ ፥ ሳይገለጥ ምክንያቴ

ፈጥነሽ ድረሽልኝ ፥ ተሿሚ ልዕልቴ ።

@getem
@getem
@getem
👍1
​​፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨

(((እኔም #ገጣሚ_ነኝ)))

ስሙኝ.......
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!
በሶሻል ሚዲያ
ስሜ ያልተጠራ
ብዙም ያልታወኩኝ....
በደሳሳ ጎጆ
ህልሜን ያጠበብኩኝ
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!
*
*
*
ከምሁራን ተርታ
ፈፅሞ ያልተሰለፍኩ
ከእውቅ ፀሀፊያን
መሀል ያልተካተትኩ
እኔም #ደራሲ_ነኝ!
በሰላች ብእሬ
ስሜቴን የገለፅኩ
*
*
ነገር ግን......
እንደነ እንትና
እስካርፕ አልጠመጠምኩ
እንደ ሀያሲያን
ሸሚዝ በከረባት
ታጥቄ አለበስኩ
በአምስቱ ጣቶቼ
የእከሌን መፅሀፍ
ይዤ አልተሽከረከርኩ....
በሄድኩበት ሁሉ
#ደራሲ_ነኝ እኔ
እውቅ ነው ሀሳቤ
ብዬም አልተናዘዝኩ.....
*
*
.........ግናም እፅፋለሁ........
ብእር ከወረቀት
እያዋደድኳቸው
ለሰው የማይገባ
ዝብርቅርቅ ሀሳባት
እኔም አፈሳለሁ ...
በሀሳቤ አርግዤው
ለአእላፉ ቀናት
እያብሰለሰልኩት
ይዤው እከርማለሁ...
የቁርጥ ቀን መቶ
እስክገላገለው
ወረቀት ከብእር
እስከማጋጥመው
ብዙ አምጣለሁ...
ያማጥኩት ተባርኮ
በመድብል ሲወለድ
ማየትን እሻለሁ..
*
*
እና እንደሌሎቹ.....
#እኔም_ገጣሚ ነኝ!
ብዬ አልዘባርቅም...
የገጠምኩት #ግጥም
የደረስኩት ድርሰት
የከሌ ነው ታሪክ ነው
ብዬ አልናገርም...
*
*
እውነቱ ገብቷቸው
አንተ #ደራሲ_ነክ
የሰዎችን እውነት
በብእር የገለፅክ
ብለው እስኪረዱኝ
በቤቴ የምኖር
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!

ተፃፈ በ @Mak_bale
ግንቦት 1,2012

@getem
@getem
@getem