ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
[ "የባይተዋሮች ወግ]
።።።።።።።።።።።።።።
ጨረቃዋን ሰብሮ፥ነጎድጓደ ወረደ ፥
መሬት ተርበድብዳ ፥መሰረቷ ራደ።
እንኳን ዝናብ ያህል ፥ ነጎድጓድ ታክሎ
ከብዶኛል ውድቅቱ፥
በላይ ተጭኖ ፥ ልክ እንዳክንባሎ።
ልክ እንዳክንባሎ ፥
ምጣድ እኔነት ላይ ፥ ክንዱን ያበረታል
ሸክም የከበደው፥
የኔ አይነት ድኩም ሰው ፥ መች ታግሎ ይረታል።
መች ታግሎ ይረታል፥
ሕይወት ምድጃ ላይ ፥ ተጥዶ መንቀልቀል
ላልተቦካ ቡኮ፥
ለማይሰፋ ሊጥ ፥ በ'እሳት መቀቀል።
በእሳት መቀቀል ፥
በሀሳብ ወላፈን ፥ በሰው እቅፍ ናፍቆት
ሌት ተቀን መበረድ ፥
ልብስ መሀል ሁኖ ፥ መገፈፍ መራቆት።
መገፈፍ መራቆት ፥
ነጠላነት ውሉ ፥ ብቻነት መቅኑ
የትራሱ ላይ ውርጭ፥ ያንሶላው ቅንቅኑ።
ያንሶላው መቀንቀን፥
እንቅልፌን ሰርቆኛል ፥
ጅራታም ሌሊት ስር ፥ ሀሳብ እየፈተልኩ
በምኞቴን ዳና ፥
እየተቅዘመዘምኩ ፥ እየተክተለተልኩ
እየተክተለተልኩ ፥
በማይመልስ መንገድ ፥
ስነጉድ ስነጉድ ፥ ማጣቴን እያማሁ
በግርግዳዬ ስር፥
ሰርስሮ የገባ ፥ አንድ ድምጽ ሰማሁ።
አንድ ድምጽ ሰማሁ፥ ትኩረቴን የሚሰብ
ጆሮዬ የሚያስጥል ፥ ቀልቤን ሚሰበስብ።
ከኔ ኩታ ገጠም ፥ ግርግዳ ሚጋራኝ
በአስፈሪው ሌሊት ፥ በክራሩ አወራኝ።
በክራሩ አወራኝ፥
የማያውቀኝን ሰው ፥ በቅኔው ነካካኝ
አላወቀም እሱ፥
ሕመሙን ሲያስታምም ፥ ቁስሌን እንደነካኝ።
(ቁስሌን እንደነካኝ፥
የጋራ ግርግዳ ፥ ብቻ እንዳልተጋራን
አልገባውም እሱ፥
እኔንም እሱንም ፥ ሌሊቱ እንዳስፈራን።
ሌሊቱ እንዳስፈራን፥
መንታ 'መም እንዳለን ፥
ቢረዳማ ኖሮ ፥ እንዲህ ባልተቀኝ…
"አልጋው አያስተኛ ፥ ናፍቆትሽ በቅሎበት
ሰማዩ አያባራ ፥ ብሶት ገንፎሎበት
እኔ ያንቺ ነዳይ ፥ የፍቅርሽ ምንዱባን
ልክ እንደሰማዩ ፥ አነባሁ ዕንባን"
ሳላስበው ድንገት፥ ግርግዳ ደቅቼ
የምኞት መንገዴን ፥ ለአፍታ ገትቼ
ስንኝ አቀበልኩት፥
አነባለሁ እንባ፥
ውድቅቱ አስፈርቶኝ ፥ የሰው እቅፍ 'ርቦኝ
አያሳዝንም ወይ፥
ሚዘረጋ ሳጣ ፥ እልፍ ክንድ ከቦኝ።
ክራሩን ገረፈ፥
ከትዝታ መንደር ፥
ተስፈንጦሮ ወጣ ፥ አግባባን ቅኝቱ
ብቻነትን ገሶ፥
ቅኔ አቀባበለን ፥ ስሜት ቁርኝቱ።
እንዲህ ሲል ቀጠለ……
እልፍ ክንድ ከቦኝ፥
ደመና ለብሼ
ቆፈንን ታጥቄ ፥ ውርጭ ሳገለድም
ህመምሽ ቢገባኝ፥
የሄደ አልናፍቅም ፥ ከነጎደ አልነጉድም።
ይለኛል ወዳጄ፥
ምስኪን ጎረቤቴ ፥ ትራስ አቅፎ አዳሪው
የማይመጣ ቀጥሮ፥
ሚጠብቅ እንደኔ ፥ ከምኞት ጋር ኗሪው።
እንዲህ አቀበልኩት።
ከነጎደ አልነጉድም ፥
ብለህ ራስህን ፥ በከንቱ አትውቀሰው
በፍቅር የከበረ ፥ በፍቅር ነው ሚያንሰው።
ሰገር ጦር ሰብቄ፥
ባልፎክርም እንኳን ፥ እንደባለ ገድል
ስንቱን በፍቅር ቀስት፥ ኑሪያለሁ ስገድል።
ዛሬ ተራ ደርሶኝ፥
መውደድ መቀናጆ ፥ ከሩቅ ሰው አጠምዶኝ
ሲያስለቅሰኝ ያድራል ፥ ናፍቆት አቆራምዶኝ።
ይልቅ ባለክራር ፥ ምስኪን ጎረቤቴ
እንካ አንዲት ቅኔ ፥ለቤትህ ለቤቴ።
ናፍቆት አቆራምዶት፥
ህመም አቅፎ ሚያድር ፥ ከብርዳም ማክዳው
ማፍረስ ስላቃተው፥
እየከለለው ነው፥ "ሕይወትን" ግርግዳው።
ይገባሃል መቼም!!
#Dagim_Hiwet

@getem
@getem
@gebriel_19
እያዩ እስታይል

ተው!
ከንፁሑ ልቤ አታኑር አንካካ
ኪስህን ልታደልብ አስራቴን አትንካ።
እረፍ!
ላታስታግስልኝ
ቁስሌን አታራግበው
ከዝንቦቹ ብሰህ ፥ ልታንገበግበው
አድብ
በንባዬ ጠብታ ኩሬህን አትገድብ።

ይቅርብሽ
ከኔ ለማትረጊ ህይወቴን አትረብሽ።
ተኚ በትራስሽ
እንኳንስ ልተርፊኝ አትበቂም ለራስሽ።
አትምጪ
ከኔ ጩኸት ርቀሽ የራስሽን አድምጪ።
አንቀላፊ ባልጋሽ
በራስሽ ህልም ነው የሚተመን ዋጋሽ
አይደለም ባጃቢሽ ስምሽ የሚጻፈው
በየራስ እግር ነው ፥ ዳና ሚነደፈው።
ደግሞም አትኩራሪ
ድህረ ጠላነት ነውና ቅራሪ
እኔና አንቺንማ፥
መጨረሻችን ነው ፥ የሚዳኘን እኩል
መቃብር ስንገባ ፥ በሞት በር በኩል።

እረፉ!
ንፁሕ ነን ለማለት ሰፈር አታከርፉ!
አትንኩን
ልክ ሳይኖራችሁ ፥ እኛን አትለኩን።
ኧረ ትርፍ የለውም፥ነገር አትፈልፍሉ
አዋቂ ለመባል ፥ እውቅና አትቀፍሉ!!
አድምጡን!
አትራፊ ለመባል ፥ በጫረታ አትሽጡን።
ለጋራችን ማጀት ፥ ምሰሶና ማገር
ስላገር ካነሳን፥
ምነው ብቻችሁን¡ ፥ እኛም እንናገር¡¡
ተዉ እረፉ!
እቤት ልታንጹ ሀገር አትዝረፉ።
ተው ግን አይበጅም ፥
ዲስኩር ለመኳኳል ፥ አትንገሩን ውሸት
ሀገርን ያፈርሳል ፥ ታሪክ ማበላሸት
ውርስም አታውርሱን፥ ያለንን አትቀሙን
በመወደድ ናፍቆት ፥ሙታን አታሰሙን።
ዛሬ በቁማችሁ ፥ ደግደጉን ስሩ
ክፋት ስትነግዱ ፥ለነገ እንዳትከስሩ።

#Dagim Hiwet


@getem
@getem
@getem
የኗሪ ታዛቢ!
።።።።።።።።።
ተይ በሏት ይችን ሰው፥ ምከሯት ትታረም
አጀብ አያሰኝም ፥ጅብ ካህያ መክረም!¡
ታግሼው ነው እንጂ!
እስስት አመልሽን ፥ ስታግለበልቢኝ
ፈርቼሽ አይደለም ፥ እንዳሻሽ ስትገልቢኝ።
ተቻችሎ መክረም!
አንቺ ትብሺ አንተ ፥
በሚል የጋራ ሀሳብ ፥ ፍቅር ካላሰረን
ቤታችን ፈረሰ፥ አውላላ ላይ ቀረን።
እወቂበት በቃ!
ማን የገነባውን ፥ ማን አፍርሶ ያልፋል
በመቻቻል ሲሆን ፥ የኔም ልብ ይሰፋል።
መቼስ ምን ይደረግ!
ጊዜ ላይቀይርሽ !
ታጥቦ ጭቃ አመልሽ ፥ ቀኔን እያስረጀው
(ትኖሪያለሽ እንጂ)
ባኗኗሪነት ነው ፥ እድሜዬን ምፈጀው።

@getem
@getem
#Dagim_Hiwet
"መሸ ደግሞ ………!!"
።።።።።።።።።።።።።።።

የክንድህን ብርታት ልርታው
ያብራክህን ቅኔ ልፍታው።
ያዘኝና ገነት ግባ ፥ ከኤደን ጠበል ንከረኝ
ልመጽውትህ ተመጽወተኝ፥ልዘከርህ ተዘከረኝ።
ባርኮትህን አትሰስት ፥ ቡራኬዬን አልሰስትም
ሀጥያትን ብሰራ 'ኳን ፥ ባንተ ከሆን ከቶ አልስትም።
ዝምም ብለን እንመንን ፥ ያለስንቅ ያለቀለብ
በፍቅር እሳት በፍቅር እቶን እንለብለብ።
አትተንፍስ ወደ ውጪ ፥ ንፋስ እንኳን እንዳይሰማን
ከባህሩ ከንፈር አርፎ ፥ ለማዕበል እንዳያማን።
አይገለጥ ቡሉኳችን ፥ ይጠቅጠቅ የጣራው ሽንቁር
አይሹለክ የሌሊቱ ውርጭ ፥ አይንካን የማለዳ ቁር።
ቢነጋም አትውጣ ከጄ ፥ ትቅናብን ፀሐይ ትቅደመን
አይንጋ ሌሊቱ ይርዘም ፥ ሳንድን በፍቅር ታመን
መቅኔን ቆሌህ ያውግዘው ፥ በጠሉ እያረጠበ
ዓለሜ በፍቅርህ ቁመት ፥ ይከርከም እየጠበበ።
ምክንያቱም!"
መንጋት መመሸቱን ማስታውስ ፥ የቀናት እድሜን ምለካ
በምትዘርፍልኝ ቅኔና ፥ በውብ ጣቶችህ ነው ለካ።
#ዝናቡ_ግን_ዛሬ_ምን_አስቦ_ነው_ ¿¿

#Dagim_Hiwet

@getem
@getem
@getem
" ምላሽ!"
።።።።።።
.
ለቅያሜህ፥ ሽረት፥ ይቅርታን ፥ ሸርቤ
ለፀብህ፥ ማርከሻ ፥ ፍቅርን ፥ ደርቤ
ለሀጥያትህ ፥ ስርየት፥ ሱባዔ ፥ ገብቼ
ክፍተትህን፥ በጡብ ፥በመቻል ፥ ገንብቼ
እ ታ ረ ቅ ሃ ለ ሁ ተመለስ ይበቃል
ይቅርታ፥ እንኳን ፥ከሰው፥ ከግዜር ፥ ያስታርቃል።
.
#Dagim_Hiwet
@getem
@getem