* ልዑል ሀይሌ*
በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ
ባለታሪኩ በስም ባይገለፅም በምግባሩ ግን የእውነት መገለፁን ሳስብ
ደስ ይለኛል።
ዕድሜ ለክፉው ሰው(ልዑል ሀይሌ)
ንቅሳቴን ሽረህ በሌላ ንቅሳት፤
ሰውነቴን ጣልካት ዳግም ላላነሳት፤
ዕድሜህ ይርዘምልህ
የኔ አጥሯልና፤
እንገናኛለን የዕድሜ መዘዙን
አታውቀውምና፤
.
ዕድሜ መዘዘኛው
መዓት በመዓት ላይ እየደራረበ፤
ሞትን ያስበልጣል
እየተገበረ እውነት የተራበ፤
.
ዕድሜህ ይርዘም ወንድም!
ኑረው ይህን ዓለም፤
ራሴን ቀጭቻለሁ
የስቃይ ልኬቱን ይህ ጎኔ አልቻለም፤
ኑረው በክፋትህ
ተውነው አስመስል፤
በአንተ ዓይነት ልኬት ነው
በዚህች ውሸት ዓለም የተሰራው ምስል፤
.
ተውነው ተውነው
ተውነው ይ'ን ኑሮ፤
ዕድሜ አቡጀዲ ነው
በረዘመ ቁጥር መግነዝ ይሆንሃል
በአፈር በእውነት ቀብሮ፤
.
ክፉ ሐሳብህን
መርዝህን ሳትረጨው አይውሰድበኝ ሞት፤
ፈጣሪም ይለመን
መቸሩን አይርሳ ያንተ ክፋት ደክሞት፤
.
ኑርበት ዕድሜዬን ዝገነው ቀንሰው፤
በቁም ሞቷልና እንዳንተ ያለ ሠው፤
ስንት'ዜ ሞት አለ?..
አንዴ እንጂ ሚ:ሞተው፤
ተዝካርም ባይኖርህ
አትሙት እንደ ሠው
አትሙት እንደሞተው፤
ብቻህን እንደኖርክ
የብቻህን ሞት ሙት፤
ኑርልኝ ወንድሜ
ክፋትህን ዝራ
ጥባው የመርዙን ጡት፤
.
ዕድሜ መዘዘኛው ይርዘምልህ ላንተ፤
እንዳንተ ክፉ ሰው
የኖረ ይመስለዋል በዕድሜው እየሞተ፤
የዕድሜ መጋረጃ ሲገለጥ እውነቱ፤
ልክ ያንገት ገመድ ነው
ጌጥ እየመሠለ
አይታወቅህም እስከ ስቅላቱ፤
.
መረቅኩህ ወዳጄ!
አቅም የለኝምና አልፎካከርም ከክፋትህ ጋራ፤
ዕድሜ ይስጥህ ብቻ
በኑረት ውስጥ ነው ገሃድ የሚወጣው
ያንተ እኩይ ስራ፤
.
ኑርበት ምድሩን
አታቆሽሽ ሰማይ፤
ክፋትህ ተሻግሮ
ከአፈር አልፎ እንዳላይ፤
ጨርሰው ዕድፍህን
አራግፈው በኑረት፤
ታጥቦ አይጠራምና
ያቆሸሽከው እውነት፤
.
19-09-11
@getem
@getem
@lula_al_greeko
በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ
ባለታሪኩ በስም ባይገለፅም በምግባሩ ግን የእውነት መገለፁን ሳስብ
ደስ ይለኛል።
ዕድሜ ለክፉው ሰው(ልዑል ሀይሌ)
ንቅሳቴን ሽረህ በሌላ ንቅሳት፤
ሰውነቴን ጣልካት ዳግም ላላነሳት፤
ዕድሜህ ይርዘምልህ
የኔ አጥሯልና፤
እንገናኛለን የዕድሜ መዘዙን
አታውቀውምና፤
.
ዕድሜ መዘዘኛው
መዓት በመዓት ላይ እየደራረበ፤
ሞትን ያስበልጣል
እየተገበረ እውነት የተራበ፤
.
ዕድሜህ ይርዘም ወንድም!
ኑረው ይህን ዓለም፤
ራሴን ቀጭቻለሁ
የስቃይ ልኬቱን ይህ ጎኔ አልቻለም፤
ኑረው በክፋትህ
ተውነው አስመስል፤
በአንተ ዓይነት ልኬት ነው
በዚህች ውሸት ዓለም የተሰራው ምስል፤
.
ተውነው ተውነው
ተውነው ይ'ን ኑሮ፤
ዕድሜ አቡጀዲ ነው
በረዘመ ቁጥር መግነዝ ይሆንሃል
በአፈር በእውነት ቀብሮ፤
.
ክፉ ሐሳብህን
መርዝህን ሳትረጨው አይውሰድበኝ ሞት፤
ፈጣሪም ይለመን
መቸሩን አይርሳ ያንተ ክፋት ደክሞት፤
.
ኑርበት ዕድሜዬን ዝገነው ቀንሰው፤
በቁም ሞቷልና እንዳንተ ያለ ሠው፤
ስንት'ዜ ሞት አለ?..
አንዴ እንጂ ሚ:ሞተው፤
ተዝካርም ባይኖርህ
አትሙት እንደ ሠው
አትሙት እንደሞተው፤
ብቻህን እንደኖርክ
የብቻህን ሞት ሙት፤
ኑርልኝ ወንድሜ
ክፋትህን ዝራ
ጥባው የመርዙን ጡት፤
.
ዕድሜ መዘዘኛው ይርዘምልህ ላንተ፤
እንዳንተ ክፉ ሰው
የኖረ ይመስለዋል በዕድሜው እየሞተ፤
የዕድሜ መጋረጃ ሲገለጥ እውነቱ፤
ልክ ያንገት ገመድ ነው
ጌጥ እየመሠለ
አይታወቅህም እስከ ስቅላቱ፤
.
መረቅኩህ ወዳጄ!
አቅም የለኝምና አልፎካከርም ከክፋትህ ጋራ፤
ዕድሜ ይስጥህ ብቻ
በኑረት ውስጥ ነው ገሃድ የሚወጣው
ያንተ እኩይ ስራ፤
.
ኑርበት ምድሩን
አታቆሽሽ ሰማይ፤
ክፋትህ ተሻግሮ
ከአፈር አልፎ እንዳላይ፤
ጨርሰው ዕድፍህን
አራግፈው በኑረት፤
ታጥቦ አይጠራምና
ያቆሸሽከው እውነት፤
.
19-09-11
@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew (Mykey))
🔴AFF 2020 🔵
The sixth edition of the Addis Foto Fest open call is now accepting submissions!
We invite photographers, curators, and photography collectives to submit projects that could be exhibited during the next edition of the Addis Foto fest, which will take place in Addis Ababa, Ethiopia on December 3-7, 2020. Submit your work to our online application by visiting the festival website; www.addisfotofest.com
Addis Foto Fest is a biennial international photography festival, which has previously featured exhibitions, portfolio reviews, workshops, conference and an award ceremony. It is also the first and only international photography festival in East Africa. The Addis Foto Fest has been recognized as one of the biggest and leading photography festival in Africa.
For more information contact us
Email: addisfotofest@gmail.com
Phone: +251118681351
Pass on this information for photographers you know and admire.
GOOD LUCK!
#Addisfotofest #Destaforafrica #aff #AFF2020 #dfaplc #Photography #Ethiopia
The sixth edition of the Addis Foto Fest open call is now accepting submissions!
We invite photographers, curators, and photography collectives to submit projects that could be exhibited during the next edition of the Addis Foto fest, which will take place in Addis Ababa, Ethiopia on December 3-7, 2020. Submit your work to our online application by visiting the festival website; www.addisfotofest.com
Addis Foto Fest is a biennial international photography festival, which has previously featured exhibitions, portfolio reviews, workshops, conference and an award ceremony. It is also the first and only international photography festival in East Africa. The Addis Foto Fest has been recognized as one of the biggest and leading photography festival in Africa.
For more information contact us
Email: addisfotofest@gmail.com
Phone: +251118681351
Pass on this information for photographers you know and admire.
GOOD LUCK!
#Addisfotofest #Destaforafrica #aff #AFF2020 #dfaplc #Photography #Ethiopia
ተስፋ የግጥም መፅሀፍ ለ አንባቢ በመሰራጨት ላይ ይገኛል ተሰፋን ይሸምቱ !! ምርጥ ምርጡን ለናንተ ።
#ተስፋ
ገጣሚ አስታውሰኝ ረጋሳ
@getem
@getem
@gebriel_19
#ተስፋ
ገጣሚ አስታውሰኝ ረጋሳ
@getem
@getem
@gebriel_19
****የባላባቶች ወግ****
አንዲት ምስኪን ሃገር -ዘወትር ጠዋት ማታ
ቁራሽ እንዲሰጣት - አምላኳን ስትለምን - እጆቿን ዘርግታ
መስጠት ማይሰለቸው - ቸር የሆነው አምላክ
ዘወትር ይሰጣታል የለት እንጀራዋን - እጆቿን በመላክ
መቼም!
"ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል" በሚባለው ተረት
ተቀባይ ባይኖርም የሚል የመሰረት
ጥቂት ባላባቶች "ሆድ ካገር ይሰፋል" እየተባባሉ
ከሃገር እጅ ላይ እንጀራ እየበሉ
እንጀራ ሰጪውን አምላክ ይከሳሉ አምላክ ይወቅሳሉ
እንዲህ ይላሉ!
ዘወትር ተቀብሎ ዘወትር መዘርጋት ነው የዚች ሃገር እጣ
ታዲያ እንዴት ተብሎ ሁሌ ከመቀበል ከልመና ትውጣ
ምነካው ፈጣሪ!
በገዛ ሃገራችን ሁልግዜ እየሰጠ ክንዱን የሚያለፋው
ድህነት ለማጥፋት ቆርጠን ስንነሳ ልመና ሚያስፋፋው
እረ አሰዳቢ ሃገር ነች ሁልግዜም አልቃሻ
ስራ የማትወድ ጉልበትዋን ቆጥባ ልመና ምትሻ
ይህው በኛ ጥረት ስንት ዲጂት አደጋ
እስከመቼ ድረስ እጆቿን ትዘርጋ!?
እግዜር አይናገር እግዜር አይጋገር
ዝም ነው ጭጭ ነው
ደሞ እንዲህ ይላሉ
እግዚሐሩስ ቢሆን እንባ ፈልጎ እንጂ ሁልግዜም ሮሮ
የለት እንጀራዋን ሚስጣት ቆንጥሮ
ካዘነላትማ የእውነት ከወደዳት
ቁጭ ብላ እንድትባል ነዳጅ ለምን ከዳት!
አየህ አደል እግዜር
እንዲህ ነው ቋንቋቸው በዘመን ድፍረት ጡርን የማይፈሩ
ኬት ይመጣል ነዳጅ አለ ባሉት ስፍራ ተግተው ካልቆፈሩ
እግዜር አይናገር እግዜር አይጋገር
ዝም ነው ጭጭ ነው
እረባክህ እግዜር ይህን ሁሉ ነገር
አንድ ቃል አውጣና ቼ ብለህ ተናገር
እረባክህ እግዜር
እኛ ፈረሶች ነን ንጉስ ሚጋልበን ንጉስ የሚነዳን
ክንድ ባይኖረንም አንተን እንድንለምን እባክህን እርዳን
እረባክህ እግዜር
ከጥያቄው በፊት ታውቃዋለህ መልሱን
ማሮጥ ብቻ ሳይሆን መሮጥ ያስተማረን "ቼ” በለው ንጉሱን
እረባክህ እግዜር እረባክህ አምላክ
ከመከራ ቋጥኝ ከሣት የሚያወጣን ገብርኤልህን ላክ
እረባክህ አላህ
እኛ ቢላሎች ነን መሳቅ የናፈቀን ደስታን የተቀማን
መሀመድ የታለ አንተን የሚያሳየን ወዳንተ የሚያሰማን
እኛ ቢላሎች ነን ደስታን የተቀማን
እኛ በሬዎች ነን
የገረፈን ጅራፍ ከሁዋላ እየፈራን
በስንዴ መስክ ላይ እንክርዳድ ያፈራን
እኛ በሬዎች ነን
ግን በዚህ ሁሉ መሀል
አንዲት ምስኪን ሀገር ዘወትር ጠዋት ማታ
ቁራሽ እንዲሰጣት አምላኳን ስትለምን እጆቿን ዘርግታ
መስጠት ማይሰለቸው ቸር የሆነው አምላክ
ዘወትር ይሰጣታል የለት እንጀራዋን እጆቿን በመላክ
ኢትዮጵያን
እግዚአብሔር
ይባርክ
#አስታዎሰኝ_እረጋሳ
@getem
@getem
@getem
አንዲት ምስኪን ሃገር -ዘወትር ጠዋት ማታ
ቁራሽ እንዲሰጣት - አምላኳን ስትለምን - እጆቿን ዘርግታ
መስጠት ማይሰለቸው - ቸር የሆነው አምላክ
ዘወትር ይሰጣታል የለት እንጀራዋን - እጆቿን በመላክ
መቼም!
"ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል" በሚባለው ተረት
ተቀባይ ባይኖርም የሚል የመሰረት
ጥቂት ባላባቶች "ሆድ ካገር ይሰፋል" እየተባባሉ
ከሃገር እጅ ላይ እንጀራ እየበሉ
እንጀራ ሰጪውን አምላክ ይከሳሉ አምላክ ይወቅሳሉ
እንዲህ ይላሉ!
ዘወትር ተቀብሎ ዘወትር መዘርጋት ነው የዚች ሃገር እጣ
ታዲያ እንዴት ተብሎ ሁሌ ከመቀበል ከልመና ትውጣ
ምነካው ፈጣሪ!
በገዛ ሃገራችን ሁልግዜ እየሰጠ ክንዱን የሚያለፋው
ድህነት ለማጥፋት ቆርጠን ስንነሳ ልመና ሚያስፋፋው
እረ አሰዳቢ ሃገር ነች ሁልግዜም አልቃሻ
ስራ የማትወድ ጉልበትዋን ቆጥባ ልመና ምትሻ
ይህው በኛ ጥረት ስንት ዲጂት አደጋ
እስከመቼ ድረስ እጆቿን ትዘርጋ!?
እግዜር አይናገር እግዜር አይጋገር
ዝም ነው ጭጭ ነው
ደሞ እንዲህ ይላሉ
እግዚሐሩስ ቢሆን እንባ ፈልጎ እንጂ ሁልግዜም ሮሮ
የለት እንጀራዋን ሚስጣት ቆንጥሮ
ካዘነላትማ የእውነት ከወደዳት
ቁጭ ብላ እንድትባል ነዳጅ ለምን ከዳት!
አየህ አደል እግዜር
እንዲህ ነው ቋንቋቸው በዘመን ድፍረት ጡርን የማይፈሩ
ኬት ይመጣል ነዳጅ አለ ባሉት ስፍራ ተግተው ካልቆፈሩ
እግዜር አይናገር እግዜር አይጋገር
ዝም ነው ጭጭ ነው
እረባክህ እግዜር ይህን ሁሉ ነገር
አንድ ቃል አውጣና ቼ ብለህ ተናገር
እረባክህ እግዜር
እኛ ፈረሶች ነን ንጉስ ሚጋልበን ንጉስ የሚነዳን
ክንድ ባይኖረንም አንተን እንድንለምን እባክህን እርዳን
እረባክህ እግዜር
ከጥያቄው በፊት ታውቃዋለህ መልሱን
ማሮጥ ብቻ ሳይሆን መሮጥ ያስተማረን "ቼ” በለው ንጉሱን
እረባክህ እግዜር እረባክህ አምላክ
ከመከራ ቋጥኝ ከሣት የሚያወጣን ገብርኤልህን ላክ
እረባክህ አላህ
እኛ ቢላሎች ነን መሳቅ የናፈቀን ደስታን የተቀማን
መሀመድ የታለ አንተን የሚያሳየን ወዳንተ የሚያሰማን
እኛ ቢላሎች ነን ደስታን የተቀማን
እኛ በሬዎች ነን
የገረፈን ጅራፍ ከሁዋላ እየፈራን
በስንዴ መስክ ላይ እንክርዳድ ያፈራን
እኛ በሬዎች ነን
ግን በዚህ ሁሉ መሀል
አንዲት ምስኪን ሀገር ዘወትር ጠዋት ማታ
ቁራሽ እንዲሰጣት አምላኳን ስትለምን እጆቿን ዘርግታ
መስጠት ማይሰለቸው ቸር የሆነው አምላክ
ዘወትር ይሰጣታል የለት እንጀራዋን እጆቿን በመላክ
ኢትዮጵያን
እግዚአብሔር
ይባርክ
#አስታዎሰኝ_እረጋሳ
@getem
@getem
@getem
ያንድ ሳንቲም ገፆች!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ተገርሜ መስሎት
ደንቆኝ የማደምጠው
"ያኔ በእኛ ጊዜ ፥ ድንጋይ ዳቦ ነበር
ማንም መንገደኛ ፥ አንስቶ 'ሚገምጠው
ዳቦ ነበር የሰው ፥ ግምባር የሚገምሰው
ቅጠሉ እንጀራ
ጤፍ ነበር አፈሩ
መራብ አይታሰብም ፥ ጥጋብ ነው ሀገሩ
እንዲህ እንደዛሬው!
እንዲህ እንዳሁኑ
ዳቦ ድንጋይ ሳይሆን
አፈር ሳይሆን ጤፉ
ባንድ ጠርሙስ ውስኪ
በየግሮሰሪው ፥ በሺዎች ሳይጠሩ
ጠኔ ሳያዝለው ፥ ኸተማ መንደሩ
በውሀ ነበረ ፥ ሁሉም የሚሰክሩ"
ብሎ ይተርታል
እንዲህ ይናገራል
አያቴ ሞኝ ነው!
ጊዜውን ሳይዋጅ ፥ ከዘመን ተኳርፏል።
ይኸው ዛሬም እኮ!
ዘር ማስላት ድንጋዩ
መወገን አፈሩ
አሁንም ዳቦ ነው ፥ብሄር ለሚቆጥሩ።
አዎን አይገርመኝም!
አያቴ ሲናገር ፥ አያቴ ሲተርት
ሰው ዛሬም በደም ነው...
ብርችስችስ እያለ ፥ አቅሉን የሚስት።
አዎን አይገርመኝም!
ዘመንህ ዘመኔ
ዘመኔ ዘመንህ
ያንድ ሣንታም ገፆች ፥ ሰውና አንበሳ
ለውጥ ስለሌለ
ያስደነቅኸኝ መስሎህ ፥ ታሪክን አታውሳ!
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ተገርሜ መስሎት
ደንቆኝ የማደምጠው
"ያኔ በእኛ ጊዜ ፥ ድንጋይ ዳቦ ነበር
ማንም መንገደኛ ፥ አንስቶ 'ሚገምጠው
ዳቦ ነበር የሰው ፥ ግምባር የሚገምሰው
ቅጠሉ እንጀራ
ጤፍ ነበር አፈሩ
መራብ አይታሰብም ፥ ጥጋብ ነው ሀገሩ
እንዲህ እንደዛሬው!
እንዲህ እንዳሁኑ
ዳቦ ድንጋይ ሳይሆን
አፈር ሳይሆን ጤፉ
ባንድ ጠርሙስ ውስኪ
በየግሮሰሪው ፥ በሺዎች ሳይጠሩ
ጠኔ ሳያዝለው ፥ ኸተማ መንደሩ
በውሀ ነበረ ፥ ሁሉም የሚሰክሩ"
ብሎ ይተርታል
እንዲህ ይናገራል
አያቴ ሞኝ ነው!
ጊዜውን ሳይዋጅ ፥ ከዘመን ተኳርፏል።
ይኸው ዛሬም እኮ!
ዘር ማስላት ድንጋዩ
መወገን አፈሩ
አሁንም ዳቦ ነው ፥ብሄር ለሚቆጥሩ።
አዎን አይገርመኝም!
አያቴ ሲናገር ፥ አያቴ ሲተርት
ሰው ዛሬም በደም ነው...
ብርችስችስ እያለ ፥ አቅሉን የሚስት።
አዎን አይገርመኝም!
ዘመንህ ዘመኔ
ዘመኔ ዘመንህ
ያንድ ሣንታም ገፆች ፥ ሰውና አንበሳ
ለውጥ ስለሌለ
ያስደነቅኸኝ መስሎህ ፥ ታሪክን አታውሳ!
@getem
@getem
@getem
👍1
ካልዶረየው አትበይ
-- @Johny_Debx -- ✍ገጣሚ --
እንደ ድሮ ሁኚ ያኔው ተመልሶ ፤
እንደ ተዋወቅነው ሚኒስትሪ ደርሶ ፤
የኔ ልጅ እያለን እኔም ሦስተኛ አመት ፤
ደብሮሽ ያቅ የለ ቤትሽ የቀረው ለት ፤
የመጣው ቀንማ' አንድ ቀን ዘልዬ ፤
ስመሽኝ አትጠግቢ ከፊት-ከሇላዬ ፤
ታዲያስ የቀረውት አደለም ደልቶኝ ፤
ፍቅርሽ እንኳን አደል' ስቅታ ገድሎኝ ፤
አንቺ ምታነሺኝ' እኔ ተቀምጬ ፤
መቼስ እራት በላው ከናፍቆት አምልጬ ፤
የኔ ፍቅር በልጦ አቤት' አታቂማ ፤
መርዝስ አልጠጣልሽ ዳገት ወጥቶ ማማ' ፤
መድሀኒቱ ብዙ ተናጋሪ' ነበርሽ ፤
ዘንድሮ አትጠሪኝ ታማሚዬ ብለሽ ፤
ግና ምን ያረጋል አልፎ አይቀር ሊበቃ ፤
እርሾስ በዛ መሠል የፍቅርሽ ቡሀቃ ፤
ጤፉ ያንቺ ነበር አቡኳክቼሽ እኔ ፤
እንጎቻ ጋግሪልኝ በወደድሽው ገሌ' ፤
እናም አሁን ምልሽ መፍትሄ ንገሪኝ ፤
የፃፍሺውን ድሮ ተረስቶሽ ላኪልኝ ፤
መልዕክትና ፍቅርን ጠርዘሽ አንድ ላይ ፤
የቤት-ልጅ አይሻል' ካልዶረየው አትበይ ፤
********************
@getem
@getem
@getem
-- @Johny_Debx -- ✍ገጣሚ --
እንደ ድሮ ሁኚ ያኔው ተመልሶ ፤
እንደ ተዋወቅነው ሚኒስትሪ ደርሶ ፤
የኔ ልጅ እያለን እኔም ሦስተኛ አመት ፤
ደብሮሽ ያቅ የለ ቤትሽ የቀረው ለት ፤
የመጣው ቀንማ' አንድ ቀን ዘልዬ ፤
ስመሽኝ አትጠግቢ ከፊት-ከሇላዬ ፤
ታዲያስ የቀረውት አደለም ደልቶኝ ፤
ፍቅርሽ እንኳን አደል' ስቅታ ገድሎኝ ፤
አንቺ ምታነሺኝ' እኔ ተቀምጬ ፤
መቼስ እራት በላው ከናፍቆት አምልጬ ፤
የኔ ፍቅር በልጦ አቤት' አታቂማ ፤
መርዝስ አልጠጣልሽ ዳገት ወጥቶ ማማ' ፤
መድሀኒቱ ብዙ ተናጋሪ' ነበርሽ ፤
ዘንድሮ አትጠሪኝ ታማሚዬ ብለሽ ፤
ግና ምን ያረጋል አልፎ አይቀር ሊበቃ ፤
እርሾስ በዛ መሠል የፍቅርሽ ቡሀቃ ፤
ጤፉ ያንቺ ነበር አቡኳክቼሽ እኔ ፤
እንጎቻ ጋግሪልኝ በወደድሽው ገሌ' ፤
እናም አሁን ምልሽ መፍትሄ ንገሪኝ ፤
የፃፍሺውን ድሮ ተረስቶሽ ላኪልኝ ፤
መልዕክትና ፍቅርን ጠርዘሽ አንድ ላይ ፤
የቤት-ልጅ አይሻል' ካልዶረየው አትበይ ፤
********************
@getem
@getem
@getem
ጭፍን አማኝ !!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።።
እኔማ...
የሕይወት ስሌቴ ፥ መተንፈሻ በሯ
የጎጆዬ ደጀን ፥ ምሰሶ ማገሯ
የግቢዬ ፍካት ፥ አበባና ስሯ
እሷ ናት እያልሁኝ
እንዲህ እያሰብሁኝ
ስንት ዘመን ቀርጥፌ
ዓመታትን ኖርሁኝ።
ይብላኝ እንጂ ለኔ!
መገን የሷ ፍጥረት
የውበት ሰገነት
ዓይኗ ጠሀይ ሆኖ ፥ በዓለም የሚያበራ
ሽንጧ የሺህ ግምት ፥ ዳሌዋ ተራራ
ተረከዘ ሎሚ ፥ ጣቶቿ አለንጋ
ጡቷ የንጉስ ጦር ፥ ደረት የሚወጋ
እያልሁ ለምፎክር
መንደር ለማሸብር
በመልክሽ ምጥማጥ ውስጥ
እግሬን ቀብድ አሲዤ
እዛዉ ለምዳክር ።
ልቤን ኸሌማቱ ፥ ከበላይ አኑሬ
ቁረሺ ለምልሽ ፥ ሥጋዬን ደርድሬ
ይብላኝ እንጂ ለኔ!
ሀገሬዉ በስላቅ ፥ እሳት ለገረፈኝ
በከንፈሩ ምፀት
አልሰማም እያለ ፥ ሀዘኑን ለቸረኝ
ይብላኝ እንጂ ለኔ!
ጣዖቴ ነሽ ብዬ ፥ ሰግጄ ሳልጨርስ
መልክዐ ስምሽን ፥ ቀድሼ ሳልጨርስ
ንፁህ ናት እያልሁኝ ፥ ለማድር ፎክሬ
ጆሮዬን ላሸሸሁ ፥ ከመንደሩ ወሬ።
ይብላኝ እንጂ ለኔ!
በዘመናት ማምሻ ፥ ሀቅ አገኘሁ ብዬ ፥ ስለት ለገበርሁኝ
ከፀሎቴ ማግስት ...
ከሰው ጋር ተኝተሽ ፥ የቀኑ ቅዠቴን ፥ በቁም ለተጋትሁኝ።
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።።
እኔማ...
የሕይወት ስሌቴ ፥ መተንፈሻ በሯ
የጎጆዬ ደጀን ፥ ምሰሶ ማገሯ
የግቢዬ ፍካት ፥ አበባና ስሯ
እሷ ናት እያልሁኝ
እንዲህ እያሰብሁኝ
ስንት ዘመን ቀርጥፌ
ዓመታትን ኖርሁኝ።
ይብላኝ እንጂ ለኔ!
መገን የሷ ፍጥረት
የውበት ሰገነት
ዓይኗ ጠሀይ ሆኖ ፥ በዓለም የሚያበራ
ሽንጧ የሺህ ግምት ፥ ዳሌዋ ተራራ
ተረከዘ ሎሚ ፥ ጣቶቿ አለንጋ
ጡቷ የንጉስ ጦር ፥ ደረት የሚወጋ
እያልሁ ለምፎክር
መንደር ለማሸብር
በመልክሽ ምጥማጥ ውስጥ
እግሬን ቀብድ አሲዤ
እዛዉ ለምዳክር ።
ልቤን ኸሌማቱ ፥ ከበላይ አኑሬ
ቁረሺ ለምልሽ ፥ ሥጋዬን ደርድሬ
ይብላኝ እንጂ ለኔ!
ሀገሬዉ በስላቅ ፥ እሳት ለገረፈኝ
በከንፈሩ ምፀት
አልሰማም እያለ ፥ ሀዘኑን ለቸረኝ
ይብላኝ እንጂ ለኔ!
ጣዖቴ ነሽ ብዬ ፥ ሰግጄ ሳልጨርስ
መልክዐ ስምሽን ፥ ቀድሼ ሳልጨርስ
ንፁህ ናት እያልሁኝ ፥ ለማድር ፎክሬ
ጆሮዬን ላሸሸሁ ፥ ከመንደሩ ወሬ።
ይብላኝ እንጂ ለኔ!
በዘመናት ማምሻ ፥ ሀቅ አገኘሁ ብዬ ፥ ስለት ለገበርሁኝ
ከፀሎቴ ማግስት ...
ከሰው ጋር ተኝተሽ ፥ የቀኑ ቅዠቴን ፥ በቁም ለተጋትሁኝ።
@getem
@getem
@getem
ለበእውቀቱ “ተመለስ ዜናዊ”
===================
ታዘዘልህ አሉ ተ'ላይ ለታች ጌታ
የማታ እንጀራ የጨለማ ውርስ
ለለፋህበቱ ለብዙ ድካምህ ለላብህ መፍሰስ
ደስ ብሎኛልና ንሳ ልመርቅህ
በቸረህ ፀጋ ላይ #በረከት ያድልህ
እንዳገዳ #ጥንቅሽ ጨምሮ ያጣፍጥልህ
#የጽዮን_ደብር ጸጋ ይጨማመርልህ
አደራህን ታድያ
ሁሉን ስለቸረህ የሁሉንም አባት
የጌታን #ስብሃት በነጋ በጠባ
ምንም ሳታስታጉል ሁሌ እንድታደርስ
እኛ አናፍቅህም እዛው ባለህበት
በሄድክበት ይቅናህ
ስለ መድኃኔዓለም እንዳት...መ ለ ስ
✍🏾✍🏾✍🏾 ናቲ
@getem
@getem
@getem
===================
ታዘዘልህ አሉ ተ'ላይ ለታች ጌታ
የማታ እንጀራ የጨለማ ውርስ
ለለፋህበቱ ለብዙ ድካምህ ለላብህ መፍሰስ
ደስ ብሎኛልና ንሳ ልመርቅህ
በቸረህ ፀጋ ላይ #በረከት ያድልህ
እንዳገዳ #ጥንቅሽ ጨምሮ ያጣፍጥልህ
#የጽዮን_ደብር ጸጋ ይጨማመርልህ
አደራህን ታድያ
ሁሉን ስለቸረህ የሁሉንም አባት
የጌታን #ስብሃት በነጋ በጠባ
ምንም ሳታስታጉል ሁሌ እንድታደርስ
እኛ አናፍቅህም እዛው ባለህበት
በሄድክበት ይቅናህ
ስለ መድኃኔዓለም እንዳት...መ ለ ስ
✍🏾✍🏾✍🏾 ናቲ
@getem
@getem
@getem
አዎ ካንቺ በቀር
እኔ አለም የለኝም ከቶ መዳረሻ
በምክንያት ሚዛን
ጥልቅ ነው ትርጉሙ መባሌ ሀበሻ፡፡
፡
አላዋቂ በዝቶ
ከክብሩ ሊረክስ ደርሶ ቢክድሽም
እመኚኝ ሀገሬ
በሰንደቅሽ ስምል በስምሽ አልዋሽም፡፡
፡
ስለዚህ ምላለሁ
ባወራሁኝ ቁጥር ሰንደቅሽን ብዬ
ከ'ግዜር የተቸርሽኝ
ማተቤ ነሽና መቅደስ ኢትዮጲያዬ፡፡
(ልብ አልባው ገጣሚ)
@getem
@getem
@gebriel_19
እኔ አለም የለኝም ከቶ መዳረሻ
በምክንያት ሚዛን
ጥልቅ ነው ትርጉሙ መባሌ ሀበሻ፡፡
፡
አላዋቂ በዝቶ
ከክብሩ ሊረክስ ደርሶ ቢክድሽም
እመኚኝ ሀገሬ
በሰንደቅሽ ስምል በስምሽ አልዋሽም፡፡
፡
ስለዚህ ምላለሁ
ባወራሁኝ ቁጥር ሰንደቅሽን ብዬ
ከ'ግዜር የተቸርሽኝ
ማተቤ ነሽና መቅደስ ኢትዮጲያዬ፡፡
(ልብ አልባው ገጣሚ)
@getem
@getem
@gebriel_19
** ተስፋ *
ለፋሁ ሞከርኩ ጨበጥኩኝ ስል አሟለጨኝ
ያባዘነኝ ያባከነኝ ሙከራዬ ሁሉ ቆጨኝ
ተስፋ አልቆርጥም ከሚል በቀር ተስፋ እራሱ ተስፋ አሳጣኝ
ቃል ብቻውን ተስፋ አይሆንም ተስፋዬ ነው እንዲ የቀጣኝ
በተስፋ ነው የምኖረው ያለውጤት ያለ አንዲት ድል
ምን ሆኜ ነው እኔ እራሴን በይሆናል የምበድል
በቃ ይብቃኝ ልቁረጥ ልሳልመጥረቢያዬን ሞረድ ሞረድ
ይህን ተስፋ ግንድስ ድስ ድስ ይህን ተስፋ ከስር ጎረድ
አረኩና
ያለተስፋ ስኖር ስኖር ያለተስፋ ስጓዝ ስጓዝ
ምስቅልቅል ነው መቼም አለም ዘብትልትል ነው የጊዜ ጓዝ!
እንደው ድንገት
አንዲት ፍሬ
ያልወለደች የሌላት ባል
ተስፋዬነሽ የምትባል
ልክ እንደኔ ተስፋ ቆርጣ
ነገን ትታ ህልም አርጣ
በመንገዴ መንገድ ዘጋች በመንገዷመንገድ ዘጋሁ
ባርምሞዋ ከኔ አደረች በዝምታ ከሷ አነጋሁ
ሳናወራ ተረዳዳን ሳንናገር ተዋሀድን
መኖር ደጉ ህልም ሰጠን "ተስፋ ” እሚባል ልጅ ወለድን
ይዞ መጣ አዲስ ህይወት ይዞ መጣ አዲስ እድል
ከዛ ወዲህ ሙሉ ሆንኩኝ ከተስፋዬ የማልጎድል ።
ተስፋን በመግዛት ያንብቡ።
ገጣሚ አስታዎሰኝ እረጋሳ
@getem
@getem
@gebriel_19
ለፋሁ ሞከርኩ ጨበጥኩኝ ስል አሟለጨኝ
ያባዘነኝ ያባከነኝ ሙከራዬ ሁሉ ቆጨኝ
ተስፋ አልቆርጥም ከሚል በቀር ተስፋ እራሱ ተስፋ አሳጣኝ
ቃል ብቻውን ተስፋ አይሆንም ተስፋዬ ነው እንዲ የቀጣኝ
በተስፋ ነው የምኖረው ያለውጤት ያለ አንዲት ድል
ምን ሆኜ ነው እኔ እራሴን በይሆናል የምበድል
በቃ ይብቃኝ ልቁረጥ ልሳልመጥረቢያዬን ሞረድ ሞረድ
ይህን ተስፋ ግንድስ ድስ ድስ ይህን ተስፋ ከስር ጎረድ
አረኩና
ያለተስፋ ስኖር ስኖር ያለተስፋ ስጓዝ ስጓዝ
ምስቅልቅል ነው መቼም አለም ዘብትልትል ነው የጊዜ ጓዝ!
እንደው ድንገት
አንዲት ፍሬ
ያልወለደች የሌላት ባል
ተስፋዬነሽ የምትባል
ልክ እንደኔ ተስፋ ቆርጣ
ነገን ትታ ህልም አርጣ
በመንገዴ መንገድ ዘጋች በመንገዷመንገድ ዘጋሁ
ባርምሞዋ ከኔ አደረች በዝምታ ከሷ አነጋሁ
ሳናወራ ተረዳዳን ሳንናገር ተዋሀድን
መኖር ደጉ ህልም ሰጠን "ተስፋ ” እሚባል ልጅ ወለድን
ይዞ መጣ አዲስ ህይወት ይዞ መጣ አዲስ እድል
ከዛ ወዲህ ሙሉ ሆንኩኝ ከተስፋዬ የማልጎድል ።
ተስፋን በመግዛት ያንብቡ።
ገጣሚ አስታዎሰኝ እረጋሳ
@getem
@getem
@gebriel_19
*ለምን አልሽኝ ልበል*
ለምን ላልሽኝ መልሴ ይህ ነው በቃ አድምጪኝ
ከሴትነትሽ ላይ ውበትሽን ፈልጌ ፈልጌ አጣትሁትኝ
እናም ምን አሰብኩኝ
አይኔን በምርቃና በጫት አስፈጥጬ
ውበትሽን ፍለጋ ተጋው ተለጥጬ
ታድያ የምቅመው (*2)
በእውነተኛው ዓለም ያጣውትን ውበት ፍለጋ ብዬ ነው
የሆነው ሆኖ ግን ይህስ መች ተሳካ
እንኳን ሳልመረቅን ሳልፈጥ ይቅርና
መርቅኜስ ውበትሽን መች አየሁትና
።።
ላጨሰኝ በሀሪሽ
እንደ ኩሽ ሸብልሎ ጭሮ ላነደደኝ
አጣብቂኝ ውስጥ ከቶ ስቦ ለወደደኝ
ምላሼ ማጨስ ነው
ለውስጤ መቃጠል ተምሳሌት ቢሆንሽ ቢገባሽ ብዬ ነው
።።
ሺሻውን ብነፋ ከሴሽ ተዋድጄ
በመድሀኒት ብጦስ ካለሽበት ሄጄ
ለራስሽ ብዬ ነው
Paf ሳልል አይቼሽ በምጠላሽ ፈንታ
paf ብዬ ልውደድሽ ጆሮሽ ከአፍንጫሽ እያየው ሲምታታ
ይልቁን ልምከርሽ ስሚኝ በእርጋታ
አንቺም ጦዝ ብለሽ መስታውት ፊት ቁሚ
ያልሆንሽውን ሁነሽ ሳተኚ አልሚ
ገለምሶም ግዢና ምርቅን በይ ልይሽ
ለኔ የጨለመ ላንቺ ከበራልሽ
ፈልገሽ ጠቁሚኝ ውበትሽን ልይልሽ
ታድያ የሱስ ዓለም እንዳልሆነ ከንቱ
የተረዳሽ ለታ ሲገባሽ ስሜቱ
ለምን ለምን አልኩት በይና ጠይቂ
እኔም መልስ ልስጥሽ ዝም ብለሽ አትሳቂ።
✍አኒታ
@getem
@getem
@gebriel_19
ለምን ላልሽኝ መልሴ ይህ ነው በቃ አድምጪኝ
ከሴትነትሽ ላይ ውበትሽን ፈልጌ ፈልጌ አጣትሁትኝ
እናም ምን አሰብኩኝ
አይኔን በምርቃና በጫት አስፈጥጬ
ውበትሽን ፍለጋ ተጋው ተለጥጬ
ታድያ የምቅመው (*2)
በእውነተኛው ዓለም ያጣውትን ውበት ፍለጋ ብዬ ነው
የሆነው ሆኖ ግን ይህስ መች ተሳካ
እንኳን ሳልመረቅን ሳልፈጥ ይቅርና
መርቅኜስ ውበትሽን መች አየሁትና
።።
ላጨሰኝ በሀሪሽ
እንደ ኩሽ ሸብልሎ ጭሮ ላነደደኝ
አጣብቂኝ ውስጥ ከቶ ስቦ ለወደደኝ
ምላሼ ማጨስ ነው
ለውስጤ መቃጠል ተምሳሌት ቢሆንሽ ቢገባሽ ብዬ ነው
።።
ሺሻውን ብነፋ ከሴሽ ተዋድጄ
በመድሀኒት ብጦስ ካለሽበት ሄጄ
ለራስሽ ብዬ ነው
Paf ሳልል አይቼሽ በምጠላሽ ፈንታ
paf ብዬ ልውደድሽ ጆሮሽ ከአፍንጫሽ እያየው ሲምታታ
ይልቁን ልምከርሽ ስሚኝ በእርጋታ
አንቺም ጦዝ ብለሽ መስታውት ፊት ቁሚ
ያልሆንሽውን ሁነሽ ሳተኚ አልሚ
ገለምሶም ግዢና ምርቅን በይ ልይሽ
ለኔ የጨለመ ላንቺ ከበራልሽ
ፈልገሽ ጠቁሚኝ ውበትሽን ልይልሽ
ታድያ የሱስ ዓለም እንዳልሆነ ከንቱ
የተረዳሽ ለታ ሲገባሽ ስሜቱ
ለምን ለምን አልኩት በይና ጠይቂ
እኔም መልስ ልስጥሽ ዝም ብለሽ አትሳቂ።
✍አኒታ
@getem
@getem
@gebriel_19
የኔ ቃየል
፨፨፨
ጥንት በሰው ልጆች ክፋት ሲጠነሰስ
ባንዱ ጥፋት ሌላው ባንድነት ሲወቀስ
ቅናትና ተንኮል ውስጡ ሰፍረውበት
በሸንጋይ ቃላቶች ስሜት በማይሰጡት
ያሰበለት መስሎ ለገዛ ወንድሙ
ደም አፍሶ ነበር ቃየል የአዳሙ
የሰው ልጅ መግደልን በሰው መነሳትን
በጭካኔ ጣርያ ራሥን መሳትን
ከሰው ልጅ ተማረ ከዛም ተገበረ
ክፋት ነው በሚለው ዝም ብሎ መች ቀረ
ዛሬም ላይ ብዙ አሉ
ያሰቡልን መሥለው እኛን የሚገሉ
ነብስ ባያጠፉ ደምም ባያፈሱ
በተንኮል በክፋት ከሱ ያላነሱ
የቅናት ዛር ለብሰው ውስጣቸው ያቄመ
በሰው ስኬት ታሞ ቀኑ የጨለመ
በሱሶች ተከቦ
ቅሌት ተከናንቦ
መስመር የለቀቅን መረን የወጣን ለት
በርቱ የሚለን በዝቶ ተግሳፅ አልቀውበት
እኛም እያወቅን እሱም እያወቀ
ለጥፋት ያጨን ሰው ቀድሞን የወደቀ
የኛ ቃየላችን
አለ አጠገባችን
አብሮን የሚኖር ነው የሚውል ከኛው ጋር
በስመ ጓደኛ ያጠፋን በምግባር
በስመ ወንድም ያረከሰን
ወዳጅ መስሎ ተኮንኖ ያሥኮነን
ያልተለየን ከኛ መሃል
ብዙ ነው እጅግ ብዙ....የኛ ቃየል
፨፨፨
✍ ኪነ ዳን @Nirvana134
@getem
@getem
፨፨፨
ጥንት በሰው ልጆች ክፋት ሲጠነሰስ
ባንዱ ጥፋት ሌላው ባንድነት ሲወቀስ
ቅናትና ተንኮል ውስጡ ሰፍረውበት
በሸንጋይ ቃላቶች ስሜት በማይሰጡት
ያሰበለት መስሎ ለገዛ ወንድሙ
ደም አፍሶ ነበር ቃየል የአዳሙ
የሰው ልጅ መግደልን በሰው መነሳትን
በጭካኔ ጣርያ ራሥን መሳትን
ከሰው ልጅ ተማረ ከዛም ተገበረ
ክፋት ነው በሚለው ዝም ብሎ መች ቀረ
ዛሬም ላይ ብዙ አሉ
ያሰቡልን መሥለው እኛን የሚገሉ
ነብስ ባያጠፉ ደምም ባያፈሱ
በተንኮል በክፋት ከሱ ያላነሱ
የቅናት ዛር ለብሰው ውስጣቸው ያቄመ
በሰው ስኬት ታሞ ቀኑ የጨለመ
በሱሶች ተከቦ
ቅሌት ተከናንቦ
መስመር የለቀቅን መረን የወጣን ለት
በርቱ የሚለን በዝቶ ተግሳፅ አልቀውበት
እኛም እያወቅን እሱም እያወቀ
ለጥፋት ያጨን ሰው ቀድሞን የወደቀ
የኛ ቃየላችን
አለ አጠገባችን
አብሮን የሚኖር ነው የሚውል ከኛው ጋር
በስመ ጓደኛ ያጠፋን በምግባር
በስመ ወንድም ያረከሰን
ወዳጅ መስሎ ተኮንኖ ያሥኮነን
ያልተለየን ከኛ መሃል
ብዙ ነው እጅግ ብዙ....የኛ ቃየል
፨፨፨
✍ ኪነ ዳን @Nirvana134
@getem
@getem
እግዜር ጨክኖ
ልቡ ከማለ በቶ መስቀሉ
እንዲህ እንዳበጠ
በቀን ይርዳል ጎጠኛው ሁሉ፡፡
፡
አይዞሽ ሃገሬ
ድሮም ክፉ ቀን እስኪያልፍ ያለፋል
ትንሳኤሽ ደርሶ
ያለፈው ክብርሽ ዳግም ይገዝፋል፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@gebriel_19
ልቡ ከማለ በቶ መስቀሉ
እንዲህ እንዳበጠ
በቀን ይርዳል ጎጠኛው ሁሉ፡፡
፡
አይዞሽ ሃገሬ
ድሮም ክፉ ቀን እስኪያልፍ ያለፋል
ትንሳኤሽ ደርሶ
ያለፈው ክብርሽ ዳግም ይገዝፋል፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@gebriel_19
#የመንታ~ጡጦች~ህልም
ቅዳሜ ምሽት 1
፡
አንቺ'ኮ ቅኔ ነሽ
ሲፈጥርሽ ጀምሮ
ጠቢብ ሰው ካልሆነ ማንም የማይፈታሽ
ለዚህ ነው እምዬ
ህመምሽ ሳይገባን የሚፈሰው እንባሽ፡፡
፡
ጡቶችሽም ቢሆን
ላንዱ ደም አፍልቀው
ለሌላኛው ልጅሽ ወተት እየሰጡ
ላታዳይ ወልደሽ
እኛ ስንባላ
ለማሳደጉ እንኳ ጠፋሽ መላ ቅጡ፡፡
፡
አልቅሺ ግዴለም
ከመንታ ጡቶችሽ
ደምና ወተቱም በተቃርኖ ይፍሰስ
በዘመን ተረግመን
አልታደልንም እና እንባሽን ለማበስ፡፡
፡
ግን በለቅሶሽ መሀል
ስሚኝ እናታለም ልንገርሽ የልቤን
ቀን ጥሎሻል ብዬ
ክታቤን በጥሼ አልጥልም ማተቤን
ከወተትሽ እንጂ
ከደምሽ አልጠባም ላስታግስ እራቤን፡
፡
ለክፉ ሌጆችሽ
እንባሽን እያዩ
ማዘን ተስኗቸው ደምሽን ለሚጠቡ
አውቃለሁ ደግ ነሽ
ህመምሽ ቢጠናም
ጡቶችሽ አይነጥፉም እነሱ እስኪጠግቡ፡፡
፡
እኔ ግን እኔ ነኝ
እንባሽን አንብቼ
የቁስልሽ ስቃይ የሚያመኝ መርቅዞ
ታዲያ እንዴት ብዬ?
ለሀዘንሽ ልድረስ
የቆሰለ ልቤ ከጤነኞች ጋራ ባብሮነት ተጉዞ
ቃልሽ ነው ተስፋዬ
ያመነ አይወድቅም
በልቡ ማድጋ ፈጣሪውን ይዞ፡፡
፡
ሰአሊው ድንቅ ነህ ተመስግነሀል፡፡
(ልብ አልባው ገጣሚ)
@getem
@getem
@gebriel_19
ቅዳሜ ምሽት 1
፡
አንቺ'ኮ ቅኔ ነሽ
ሲፈጥርሽ ጀምሮ
ጠቢብ ሰው ካልሆነ ማንም የማይፈታሽ
ለዚህ ነው እምዬ
ህመምሽ ሳይገባን የሚፈሰው እንባሽ፡፡
፡
ጡቶችሽም ቢሆን
ላንዱ ደም አፍልቀው
ለሌላኛው ልጅሽ ወተት እየሰጡ
ላታዳይ ወልደሽ
እኛ ስንባላ
ለማሳደጉ እንኳ ጠፋሽ መላ ቅጡ፡፡
፡
አልቅሺ ግዴለም
ከመንታ ጡቶችሽ
ደምና ወተቱም በተቃርኖ ይፍሰስ
በዘመን ተረግመን
አልታደልንም እና እንባሽን ለማበስ፡፡
፡
ግን በለቅሶሽ መሀል
ስሚኝ እናታለም ልንገርሽ የልቤን
ቀን ጥሎሻል ብዬ
ክታቤን በጥሼ አልጥልም ማተቤን
ከወተትሽ እንጂ
ከደምሽ አልጠባም ላስታግስ እራቤን፡
፡
ለክፉ ሌጆችሽ
እንባሽን እያዩ
ማዘን ተስኗቸው ደምሽን ለሚጠቡ
አውቃለሁ ደግ ነሽ
ህመምሽ ቢጠናም
ጡቶችሽ አይነጥፉም እነሱ እስኪጠግቡ፡፡
፡
እኔ ግን እኔ ነኝ
እንባሽን አንብቼ
የቁስልሽ ስቃይ የሚያመኝ መርቅዞ
ታዲያ እንዴት ብዬ?
ለሀዘንሽ ልድረስ
የቆሰለ ልቤ ከጤነኞች ጋራ ባብሮነት ተጉዞ
ቃልሽ ነው ተስፋዬ
ያመነ አይወድቅም
በልቡ ማድጋ ፈጣሪውን ይዞ፡፡
፡
ሰአሊው ድንቅ ነህ ተመስግነሀል፡፡
(ልብ አልባው ገጣሚ)
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ቅዳሜ ምሽት 2
፡
አልዋሽሽም ውዴ
ደስታዬ ነበረ
ከሌሎቹ በላይ አንቺን ሲያስበልጡ
ዛሬ ግን ከበደኝ
ከሁሉ በላቀች ባ'ገሬ ሲመጡ፡፡
፡
እና እትታዘቢኝ
ከኔ ማንነት ላይ ማንንም ቢለኩ
አልችልም ያመኛል
በጫወታ መሀል አገሬን ሲነኩ፡፡
፡
እናም ተበሳጨሁ
አንቺን አወድሰው ሀገሬን ሲሰድቡ
በቃ ገደል ግቢ
በሷ አይምጡብኝ ልክ አለው ገደቡ
ለኔ ፍቅሩን ካ'ገር
ያስበለጠ ሰው ነው በምድር ደደቡ፡፡
(ልብ አልባው ገጣሚ)
@getem
@getem
@gebriel_19
፡
አልዋሽሽም ውዴ
ደስታዬ ነበረ
ከሌሎቹ በላይ አንቺን ሲያስበልጡ
ዛሬ ግን ከበደኝ
ከሁሉ በላቀች ባ'ገሬ ሲመጡ፡፡
፡
እና እትታዘቢኝ
ከኔ ማንነት ላይ ማንንም ቢለኩ
አልችልም ያመኛል
በጫወታ መሀል አገሬን ሲነኩ፡፡
፡
እናም ተበሳጨሁ
አንቺን አወድሰው ሀገሬን ሲሰድቡ
በቃ ገደል ግቢ
በሷ አይምጡብኝ ልክ አለው ገደቡ
ለኔ ፍቅሩን ካ'ገር
ያስበለጠ ሰው ነው በምድር ደደቡ፡፡
(ልብ አልባው ገጣሚ)
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
#የፍቅር ጥግ#
ፍቅሯ ገደብ አጥቶ ጥግ ቢደርስባት
ልጆቿን ከእቅፏ ካይኗ እንዳይወሰሰዱባት
ከጥፋት መከራ ልትታደጋቸው
ድመት ግልገሎቿን ወልዳ በላቻቸው።
((የሳራ ልጅ))
@getem
@getem
@gebriel_19
ፍቅሯ ገደብ አጥቶ ጥግ ቢደርስባት
ልጆቿን ከእቅፏ ካይኗ እንዳይወሰሰዱባት
ከጥፋት መከራ ልትታደጋቸው
ድመት ግልገሎቿን ወልዳ በላቻቸው።
((የሳራ ልጅ))
@getem
@getem
@gebriel_19