ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የመንታ~ጡጦች~ህልም
ቅዳሜ ምሽት 1

አንቺ'ኮ ቅኔ ነሽ
ሲፈጥርሽ ጀምሮ
ጠቢብ ሰው ካልሆነ ማንም የማይፈታሽ
ለዚህ ነው እምዬ
ህመምሽ ሳይገባን የሚፈሰው እንባሽ፡፡

ጡቶችሽም ቢሆን
ላንዱ ደም አፍልቀው
ለሌላኛው ልጅሽ ወተት እየሰጡ
ላታዳይ ወልደሽ
እኛ ስንባላ
ለማሳደጉ እንኳ ጠፋሽ መላ ቅጡ፡፡

አልቅሺ ግዴለም
ከመንታ ጡቶችሽ
ደምና ወተቱም በተቃርኖ ይፍሰስ
በዘመን ተረግመን
አልታደልንም እና እንባሽን ለማበስ፡፡

ግን በለቅሶሽ መሀል
ስሚኝ እናታለም ልንገርሽ የልቤን
ቀን ጥሎሻል ብዬ
ክታቤን በጥሼ አልጥልም ማተቤን
ከወተትሽ እንጂ
ከደምሽ አልጠባም ላስታግስ እራቤን፡

ለክፉ ሌጆችሽ
እንባሽን እያዩ
ማዘን ተስኗቸው ደምሽን ለሚጠቡ
አውቃለሁ ደግ ነሽ
ህመምሽ ቢጠናም
ጡቶችሽ አይነጥፉም እነሱ እስኪጠግቡ፡፡

እኔ ግን እኔ ነኝ
እንባሽን አንብቼ
የቁስልሽ ስቃይ የሚያመኝ መርቅዞ
ታዲያ እንዴት ብዬ?
ለሀዘንሽ ልድረስ
የቆሰለ ልቤ ከጤነኞች ጋራ ባብሮነት ተጉዞ
ቃልሽ ነው ተስፋዬ
ያመነ አይወድቅም
በልቡ ማድጋ ፈጣሪውን ይዞ፡፡

ሰአሊው ድንቅ ነህ ተመስግነሀል፡፡


(ልብ አልባው ገጣሚ)
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1