#ያየልኝ
ትዝ ካለህ ያን ጊዜ እጣችን ተሳስቦ፣
በወቅቱ እማይታይ ሌላ አላማ አንግቦ፣
አላየሁም ነበር ማስተዋያ ቅሌ በሀሳብ ተከቦ፡፡
የህይወት ዉጣዉረድ ፤የልብ ምት መጥፋት፣
ያሳለፍኩት ታሪክ የሄደው ሞገዴ ሆኖብኝ እንቅፋት፣
ነገሩስ ጭንቀት ነው የሰው ስህተት ላርም ቀን ሌት እንቅልፍ ማጣት፡፡
ዉስጤ ሀር ሳለ ነስር አደፍርሶት፣
ከሀሳብ እንባየ ከቃል ዝምታየ እየቀደመብኝ ሲያመጣብኝ ብሶት፣
ተው አትፍረድ ውዴ ይሄ ሁሉ ሲሆን አላሰብኩም ክፋት፡፡
እውነቱ ይሄ ነው
በወደዱት መካድ ይሰብራል ይቆርሳል፣
እንኳንስ ከሀሳብ ከቀዬ ያሰድዳል፣
አምኖ ለታመኑት ምላሹ ሲከፋ እጂጉን ያስከፋል፡፡
የተሰበረ ልብ የዋለለ አዕምሮ፣
ቁስሉ ደርቆ እስኪድን ያበዛል ሮሮ፣
የፊቱን አይሻም ይመሽጋል ጓሮ፡፡
አንተም እንግዳየ ዝምታህ ጨምሮ ቤተሰብም ሆንከኝ፣
የውስጥ ውስጤን ጩኸት አንደበት አርገኸው ሳልነግርህ ሰማኸኝ፣
ምሽጌ ሳይርቅህ ጓዳየም ሳይቀፍህ መድሀኒት ሆንክልኝ፡፡
እርግጥ አጥፍቻለሁ ልኬትን ጥሻለሁ፣
የጎሳ ጭፈጨፋ አዳም ላይ ጥያለሁ፣
የአዳምም አዳም እንዳለዉ ስቻለሁ፡፡
ግና በመሀሉ ቁስሌ እየደረቀ ቀልቤ እያንዣበበ፣
በመልካሙ ሽቶ በፍቅርህ መዐዛ ከውስጡ ታጀበ፣
ውሃን ካልጨበጥኩኝ ነፋስ ካላፈስኩኝ ከሚሉ እብደቶች ሊታቀብ አሰበ፡፡
በአይኔ ሳላስተዉል ማዳመጫየንም ከዉል ሳላዉለው፣
ሚያቆመኝ ምሰሶ አንድ ብቻ መስሎኝ ወደቀብኝ ብየ ሂያጁን ስጠብቀው፣
እኔ ሳልችልበት ከኔ በላይ አሱ በእኔ እምነት የጣለው ፣
ትልቁ ምሰሶ ከመሰረቱ ጋር አብሮ የተከለኝ የልቤ ንጉሦ ነው፣
ደስታውን አብዝቶ ጤና እንዲሰጥልኝ ፀሎት አቅራቢ ነኝ ሁሌም ለላይኛው፡፡
#SElamawit
@getem
@getem
@gebreil_19
ትዝ ካለህ ያን ጊዜ እጣችን ተሳስቦ፣
በወቅቱ እማይታይ ሌላ አላማ አንግቦ፣
አላየሁም ነበር ማስተዋያ ቅሌ በሀሳብ ተከቦ፡፡
የህይወት ዉጣዉረድ ፤የልብ ምት መጥፋት፣
ያሳለፍኩት ታሪክ የሄደው ሞገዴ ሆኖብኝ እንቅፋት፣
ነገሩስ ጭንቀት ነው የሰው ስህተት ላርም ቀን ሌት እንቅልፍ ማጣት፡፡
ዉስጤ ሀር ሳለ ነስር አደፍርሶት፣
ከሀሳብ እንባየ ከቃል ዝምታየ እየቀደመብኝ ሲያመጣብኝ ብሶት፣
ተው አትፍረድ ውዴ ይሄ ሁሉ ሲሆን አላሰብኩም ክፋት፡፡
እውነቱ ይሄ ነው
በወደዱት መካድ ይሰብራል ይቆርሳል፣
እንኳንስ ከሀሳብ ከቀዬ ያሰድዳል፣
አምኖ ለታመኑት ምላሹ ሲከፋ እጂጉን ያስከፋል፡፡
የተሰበረ ልብ የዋለለ አዕምሮ፣
ቁስሉ ደርቆ እስኪድን ያበዛል ሮሮ፣
የፊቱን አይሻም ይመሽጋል ጓሮ፡፡
አንተም እንግዳየ ዝምታህ ጨምሮ ቤተሰብም ሆንከኝ፣
የውስጥ ውስጤን ጩኸት አንደበት አርገኸው ሳልነግርህ ሰማኸኝ፣
ምሽጌ ሳይርቅህ ጓዳየም ሳይቀፍህ መድሀኒት ሆንክልኝ፡፡
እርግጥ አጥፍቻለሁ ልኬትን ጥሻለሁ፣
የጎሳ ጭፈጨፋ አዳም ላይ ጥያለሁ፣
የአዳምም አዳም እንዳለዉ ስቻለሁ፡፡
ግና በመሀሉ ቁስሌ እየደረቀ ቀልቤ እያንዣበበ፣
በመልካሙ ሽቶ በፍቅርህ መዐዛ ከውስጡ ታጀበ፣
ውሃን ካልጨበጥኩኝ ነፋስ ካላፈስኩኝ ከሚሉ እብደቶች ሊታቀብ አሰበ፡፡
በአይኔ ሳላስተዉል ማዳመጫየንም ከዉል ሳላዉለው፣
ሚያቆመኝ ምሰሶ አንድ ብቻ መስሎኝ ወደቀብኝ ብየ ሂያጁን ስጠብቀው፣
እኔ ሳልችልበት ከኔ በላይ አሱ በእኔ እምነት የጣለው ፣
ትልቁ ምሰሶ ከመሰረቱ ጋር አብሮ የተከለኝ የልቤ ንጉሦ ነው፣
ደስታውን አብዝቶ ጤና እንዲሰጥልኝ ፀሎት አቅራቢ ነኝ ሁሌም ለላይኛው፡፡
#SElamawit
@getem
@getem
@gebreil_19