ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ኡስታዙ_እና_ቄሱ
ከውሰር[ጋዜጠኛው ዶክተር]
.
በዚህች ጠባብ ሀገር፣በዚህች በአንድ ምድር፤
ቄሱ እና ኡስታዙ አይተናኮስም፣በወል ነው የሚያድር።
.
ይሄ ጀግና ኡስታዝ አማማውን ታጥቆ፣ሙደወሩን ለብሶ፤
ፂሙን አስረዝሞ ሱሪውን አሳጥሮ፤ከቁርአን አጣቅሶ፤
ከመስጂዱ ቅጥር፣ሲያሰግድ ይውላል ኻምሴ ተመላልሶ።
ከሰላት ቡሀላም ዲስኩር ይጀምራል፣ወደ ኡማው ዞሮ፤
የአንድዬን እዝነት፣የአምላክን ቀጪነት፣ይነግራል ዘርዝሮ።

ይሄም ጀግና ፓፓስ፣መስቀሉን ጨብጦ፣ካባውን ደርቦ፤
ውቡን አክሊል ለብሶ፣ይገባል ቤተስቲያን፣ከምእመናን ቀርቦ።
መርጌታው ሲያስተምር፣የያሬድን ዜማ፤
ዲያቆኑ ይቀድሳል፣የእግዜርን ቃላት፣ለህዝቡ ሊያሰማ።
መምህሩም ለህዝቡ፣ሠላም ይሰብካሉ፤
ቄሱም ፀበል ረጭተው፣በስም አብ ይላሉ።

እንዲህ ናት ሀገሬ፣ይህች ጠባብ ምድር፤
ቄሱ እና ኡስታዙ፣አይተናኮልም፣በወል ነው የሚያድር።

አሀዱ አምላክ ብለው፣ቤተስቲያን ገብተው፣ሲቀድሱ ቄሱ፤
ከመስጂዱ ቅጥር፣አላሁ አክበር አሉ፣ጌታን ሲያወድሱ፤
በስም አብ ብለው፣ስብከት ሲጀምሩ፣ቄሱ ለምእመናን፤
ቢስሚላህ ብለው ነው፣ኡስታዝ የሚያሰሙት፣ሚጀምሩት ዳእዋን።

እንዲህ ናት ሀገሬ፣ይህች ጠባብ ምድር፤
ሙስሊም ክርስቲያኑ አይተናኮስም፣በወል ነው የሚያድር።

#Kewser

@getem
@getem
@getem