ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
"ሰው" ሆሆሆሆ..ይይይይ !!!...."

ሰው" በመሆን ብቻ የምንግባትን ኩዳይ ስለሆነ እንብበህ "ሽር" !!!.....በማድርግ ግደታህን ትወጣ ዘንድ እንደእምነትህ እንደ አስተሳሰብህ በፈጣሪህ ስም
እንጠይቅሀለ!!!!................

በምስሉ ላይ የምትመለከቱዋት ወጣት ብሩህ ተስፋ ትባላለች። እንደማንኛውም ሰው ብሩህ ተስፋ ነበራት !!!አሁን ግን በደረሰባት ህመም የሆርሞን መጨመር የትነሳ ከ90 ኪሎ በላይ ጨምራለች የሰውነት ውፍረቶም እየጨመር በመሄድ ለተጎዳኝ በሽታውች ተጋልጣለች ይህንንም ህመም ለመታከም በሀገር ውስጥ ህክምና መዳን ስላልቻለች ከባህር ማዶ በሚገኙ ሀገራት ሂዳ ብትታከም እንደምትድን ከሀኪሞች ተነግሮታል። ብሩህን ለማሳገም የከቢ ማሰባሰቢያ በእንድቅትዮን የኪነ-ጥበብ ቤተሰብ፣ በአለን የጋዜጦች ማህበር ፣በኑሀሚን የፊልም ብሮዳክሽን እንድሁም ከቅን አጎሮች ጋር በመሆን ሚያዝያ 7 ሰኞ የኪነ-ጥበብ ምሽት እዘጋጂተናል። እረሶም በገቢ ማሳባስቢያው ምሽት በመታደም፣ሰውችን በመጋበዝ፣ሽር በማድረግ፣በምትችሉት ሁሉ በማድርግ ብሩህን እንታደጋት ዘንድ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን............





ሼር!!!
ሼር!!!
ሼር!!!.......

@getem
@getem
@getem
👍1
Ethiopia: ፈጣሪ ብሔሩ ምንድን ነዉ...?? 16k
Andafta
🎬 Ethiopia: ፈጣሪ ብሔሩ ምንድን ነዉ...?? በልዑል ሀይሌ

👤 Andafta
🕛 10:13
💾 1.2MB

@getem
@getem
@gebriel_19
ጣዕም
(( እዮብ ሰብስቤ ))

የውስጡን ጥፍጥና በሙሉ እያስላሰው
የማንነቱን ጣዕም ጨርሶ ቀነሰው፡፡
እረ ባክህ ንቃ!
በፍጹም አትሁን ግንድ አልባ ቅርንጫፍ
መሰልቸት እኮ ነው የመደጋገም ጫፍ፡፡

@getem
@getem
(ለአባቴ)
ደህና ነኝ፡፡
መንታላ ገላዬን ችጋር ቢደቁሰው
ፍቅር ስጠቀለል ክፋትን ብጎርሰው
ህልሜ ቢጨናገፍ መንገዴ ቢያደክመኝ
እንዳለኸኝ ሳስብ ተስፋ አለኝ ደና ነኝ፡፡

ማግኘትና ማጣት ቢፈራረቁብኝ
ዋዛ ሆኜ ብታይ ቁምነገር ቢያጡብኝ
ፈርሷል ብለው ሲያልፉ ሰባብረውት ውስጤን
አንተ የኔ ጋሻ ነገዬን በማጤን
በርታ 'እንጂ ስትለኝ
ተዛ እለት ጀምሮ ተስፋ አለኝ ደህና ነኝ፡፡
---
ምን አፍራሽ ቢበዛ ከየጎዳናው ጫፍ
ያዘን እንጉርጉሮ በአካላቴ ቢያልፍ
ብጎብጥ ባቀረቅር 'መላም የለህ' ብሰኝ
አባቴ ፊቴ ቁም
ስትኖረኝ ተስፋ አለኝ፡፡ ስትኖረኝ ደህና ነኝ፡፡

#ELU @Username_under_construction

@GETEM
@GETEM
#ኪርያላይሶ#

ታጥፎ፥ እንደ ድግ፥ወገቧን ዞሮ
እንደ ተረኛ ቄስ፥ሳይዘ'ጋ ያይኑ ጭራሮ
ሙሉ ሌሊት ከድሟት፥በፅናፅል በክበሮ
ተፈስሒ ዘምሮ
ለክብሯ፥ አጎንብሶ
ኪዳን፥ በስሟ አድርሶ
አልተሰረዬም ንስሃዉ፥ተመልሶ ኪርያላይሶ።

የጉም ፈትል ፈትሎ፥ቀጭን ክንዱ
አልቅሶ ወደ መሬት፥የሆዱን ይዞ በሆዱ...
ሆኖ ብኩን ፥እፉዬ ገላ
የዕብድ አሞራ፥ተከታይ፥ሲላ...
እንደ ሰንበሌጥ ጣሪያ፥የልብ ቋቱ አፍሶ
በቃኝ ብሎ፥ወይ ላይችለዉ፥ ጨርሶ
ነጋ መሸ ፥እሷን ብቻ ኪርያላይሶ።

#መሪጌታ
@getem
@getem
@gebriel_19
*አስማት *
ፀሀፈ ብሩህ

በትእዛዝ ወልዶት፣
መሪ አብዝቶበት፣
ቀኑን አርቆበት፣
ምስጋና ሸልሞት፣
እሺን መርቆለት፣
ጥሮ ግሮን ወርሶ፣
ህሊናን ሰውቶ
ለአንዲት ቀን አዳር፣
ሺ’ ቀናትን ገሎ
ካልቻለ ማሳደር፣
ነፍሱን ሳያሳርር
ሰው በእህል አይኖርም፣
እውነት ነች ክታቧ
አስማተኛ ይኖራል፣
የሆዱን ስልቻ በቃል የሚሞላ።

@getem
@getem
@Birukam
#Giday Kindaya
::ብርዱም ተነሳበት - ያው ዝናቡ መጣ '
ትውስ አለኝ ፍቅርሽ - አንቺን አለኝ አምጣ
#እርሷ_በንዴት :
የሄን ሁላ ጊዜ አንዴም - ትዝ ያላልኩህ !
ክረምቱ ሲገባ አሁን - የታወስኩህ '
ዘርተህ ያበቀልከኝ - በቆሎ መሰልኩህ !!😜😂
@getem
@getem
@kaleab_1888
Ethiopia: “የዘር ሀረግሽ ሲመዘዝ አፈር መሆኑን አትርሺ“በላይ በቀለ ወያ 16k
Andafta
“የዘር ሀረግሽ ሲመዘዝ አፈር መሆኑን አትርሺ“ በላይ በቀለ ወያ

👤 ግጥም ብቻ
🕡 10:04
💾 1.2 MB

@getem
@getem
@gebriel_19
እኔ ለሀገሬ.3gpp
3.5 MB
ግጥም ፡ በላይ በቀለ ወያ
ንባብ( አቅራቢ) ፡ መብረቁ ጥቁር ሰው(መባ)

@getem
@getem
@Bookfor
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (👋ገብረዬ)
ሠላም ለሁላችሁ
#የሥዕል_ዉድድር ሰሞኑን እምንጀምር ስለሆነ ለመወዳደርያችሁ የሚሆነውን ምርጥ የምትሉት ሥዕላችሁን ላኩልን!!!
ለውድድር ሚበቃውን እኛ መርጠን በመልቀቅ #vote_እናስደርጋለን

#ከፍተኛውን like ያገኙ 3 አሸናፊዎች
የ ሥዕል መሳያ እቃዎችና ፣ የኢንተርኔት pakage እና የካርድ ተሸላሚ ይሆናሉ።

#የራሳችሁ_ያለሆነ ሥዕል ማቅረብ ከቻናሉ ያስባርራል!!!

ሥዕላችሁን ምትልኩበትን አድራሻ
@gebriel_19 ነው

ሠአሊያን ተዘጋጁ መለካም እድል!!!

@seiloch
@seiloch
በሰላም መቃወም
እዮብ ሰብስቤ
:
ማርቲን ሉተር ኪንግ ሆይ
ማመፅ እንዴት ይሆን?
ኔልሰን ማንዴላ ሆይ
ማመፅ እንዴት ይሆን?
ባ'ካችሁ ስለ ሀገር፤
ስለ እናቶች ክብር፤
ማመፅ እንዴት ይሆን?
እኛ እንደው ስንሻ ለማግኘት ነፃነት
ጠብመንጃ አንግተን
ምርጫችን ነው መዝመት።
ውሀውን ተክቶ ደም በቦዩ ሳይፈስ
ጋሻ ጦሩን ሰብቆ ሰው ሳይጨራረስ
ተገምብቶ የቆመው ወድሞ ሳይፈራርስ
ክብሯ ሳይደፋ፤
ሀገር ሳትጠፋ፤
እንደ ጅረት ሆኖ ሳይንቆረቆር ደም
እንዴት ይሆን ማመፅ በሰላም መቃወም?

@getem
@getem
@gebriel_19
ፀሀፈ ብሩክ

ብረ–አብሔር
አባታችን ሆይ ሰማይ እርቆህ
በምድር የምትኖር
ስምህን የምንቀድስ
አንተም እኛን የምታድስ
መንግስትህ በኛ የከተመ
መሄድ መምጣት ያልቃረመ
ለፈቃድህ የማንፀልይ
የምንኖር አንዴ ፈቅደህ
የለት እንጀራ የማንጠይቅ
ባንተ ፍቅር የምንጠርቅ
የማንለምን ይቅርታህን
የለት በደል የሌለብን
አንተ ካለህ ከኪሳችን
የምን ፀሎት
የምን ምልጃ በደል ፅድቀት
እስክትጎል ካለህበት
እስኪያቅትህ ሰውን መግዛት።


@getem
@getem
@Birukam
"የኔታ መርቀኝ"
==
አኮፋዳ ባልይዝ የቅኔ ድብተሬን
ሃሁን ባላጠና የአድማስ ፍሬ ስንቄን
በለብቅህ ገርፈህ
በጣጦችህ አሽተህ
ባንደበትህ ቀልጽህ
ግዴለም ግረፈኝ መርቀኝ የኔታ
ያላዋቂ ልቤን አሳውቅው ቀርጸህ የፊደል ገበታ

እሷን ለኔ ይዤ መርቀኝ እስከሷ
በሻገተ ቆሎ በሻገተ ድርቆሽ ፍቅር ይሁን ምሷ
የልጀነት ወዜን በልጀነት ወዟ እንዳስታረቀችው
ጎዶሎ ግራዬን እንደሞላ ቀኜ ሞልታ ባሳየችው
መርቅልኝ እሷን መርቅልኝ እኔን
ቤታችን ግባልን ባርክልኝ ጎኔን

Mezin worku

@getem
@getem
@getem
Ethiopia: ዜጋ በሌለበት ምን ይሉት ፈሊጥ ነዉ የዜግነት ክብር!!” 16k
Andafta
ዜጋ በሌለበት ምን ይሉት ፈሊጥ ነዉ የዜግነት ክብር!!”

👤 አንዳፍታ
ግጥም ብቻ

🕢 10:20
💾 1።2 MB

@getem
@getem
@gebriel_19
መርጋት ምን ድረስ ነው?


ታገስ ተረጋጋ፣
ታግሶ የረጋ ወተት፣ቅቤ ይወጣዋል
ብላቹ ብትመክሩት፣
መታገሱ ብቻ፣ምንስ ይበጀዋል፥
ለቅቤው ቢረጋ፣
ቅቤውን የሚሻ፣አፍኖ ይንጠዋል።

ስለዚህ-
ምክራቸውን ትፋና፣
የኔን ምክር ዋጠው፥
ቅቤህ እንዲወጣ፣
እስኪንጡህ አትጠብቅ፣
ራስህን ናጠው።


ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
(@San2w)
08/08/2011 WOLDIA UNIVERSITY

@getem
@getem
@getem
#ኢዮሪካ
( አሚር የ ሸምስ )

የለሊት ጭንቀቴ ምናቤን አይቶልኝ
ፀሎቴን በመስማት አምላክ ፈረደልኝ
ከአንድ መሸታ ቤት ዳግም ተፈጠርኩ
እውነተኛ ፍቅርን ኢዮሪካ አልኩኝ::

ማንቆርቆሪያ ይዛ ብርሌ ምታድል
የቀሉ ጉንጮቿ ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል
በስርቅርቅ ድምፇ ቀልቤን ተነጠኩ
አግድም ላይ ቁጭ ብዬ ኮማሪት አፈቀርኩ::
አይን አይኗን እያየው በድንገት ፈዘዝኩኝ
ታሪክ ተለውጦ በገሀዱ አለም ሴት ልጅ አፈቀርኩኝ

.........መንገዴን ዘንግቼ በጠጅ ድንፋታ
.........በኮማሪት ፍቅር ነብሴ ተንገላታ
ጠጥቼ ጨርሼ ወደ ቤት ሄድኩ ስል
መንገዴን ተጉዤ ብዙ ርቀት ሄጄ
ኩርባዎችን ዞሬ ቤቴ ደረስኩ ስል
.....የፍቅሯ መአበል
አዙሮ ይጥለኛል እዛው ጠጅ ቤት ስር::

.......ደግሞም ከምግብ ቤት
ምግብ ለመመገብ ካፌ ጎራ ካልኩኝ
አስተናጋጅ ሁሉ እሷ እየመሰሉኝ
ከአስተናጋጆች ጋ እነታረካለው እዘባርቃለው
ምግብ በብርሌ ቅዱልኝ እላለው::
ያለመደብኝን ብርሌ ታቅፌ
ወደኔ ስትመጣ አንገቷን አቅፌ
ስትቀዳ አጎንብሳ ጡቶቿን አያለው
ሰከንድ ሳይሞላት ትንሽ ስትርቀኝ
የቀዳችው ሳያልቅ ድገሚኝ እላለው
ጡቶቿ ናፍቀውኝ መልሼ እጣራለው
ሰረቅ እያረኩኝ ደረቷን አያለው
ፍቅርን በማለት ኪሴን እያጎደልኩ ብርሌ አስሞላለው::

@getem
@getem
@getem
** ሄዱ በ1 ጊዜ! **
"""""""""፠"""""""""
@Johny_Debx
ነበር ቀርቶ መሆን በርትቶ
.... አይ~
መቼ እንዳምናው አቤት' ካልሠጠኸኝ "መቶ"!
"ወዴት" ሲቀይር ደርሶ "በእንዴት"?
መፃፍ ትዝ ቢለኝ~ ከድሮ ቢተወኝ፣
.....እኔም አልኩኝ ታዲያ~
ገንዘብ ተከምሮ ካልሆነ ተራራ!
ሠው አየው ይሉኛል ሄደው በየተራ?

@getem
@getem
@getem
''ክደት ያከባብረን''
~~~~~
እንኳን አንድ ገነት 'ሺ ገነት ይቅር
እንኳን አንድ በለስ 'ሺ በለስ ይረር
.....ብቻ አብረሽኝ ነይ
የኤዶምን ውሃ ይቅር ለፈጣሪ ካጠገቤ አትለይ
.....
በሰውነት ተርታ የጉልበቴ ክፋይ ከእንብርትሻ ባይወጣ
የአለምን ጣእም በምላስ ባልቀምሰው ማሩ ቢኮ'መጣ
የተጋረደው የፈጣሪን ሸማ
ቀምሰን ልንፋ'ትተው በ'ፀ-በለስ ጣዝማ
ደግሞ በዚህ ዘመን ዝሙትና ሴራ በበዛበት ጊዜ
እንዴት ይፈሩታል ያምላክን እርግማን የሰውን ኑዛዜ
ነይልኝ ዘበ'ናይ......!
ቆፍረን ሞንጭረን የጠፋውን ፍቅር በገሀዳ እናሳይ
አንቺ ግን ተከተይ
......
በቅጠሉ ክልል በሀፍረተ ገ'ላ
የተገለጠውን የ'ውነት አለም ሚስጥር በሀሰት ከለላ
በሚቀደድ እራፊ
ማንነት ክብራችን ከለበስነው ሸማ ቀድሞ እረጋፊ
ያውም ላንዲት ፍሬ ተቆርጣ ለምትወድቅ
እየሰሩ ማፍረስ አጣብቀው ማላቀቅ
እውነቴን ነው ምልሽ 'ክደት ያከባብረን'
እኔም ሀገር የለኝ አንቺም ጌታ የለሽ ፍቅር ያሳድረን
====
አንቺዬ......
አብሮ ለመኖር ግን አንድ ህግ እንስራ
አብረን የምንጾመው ቀለም ያልገለጸው ከብ'ራና ሼራ
የጋራ 'ፀ-በለስ የሞት አሪማሞ በሁለታችን ይብራ
እሱ ይሁን ቃሌ.....
አይንሽ ካይኔ ሌላ የሚያይ እንደሆ'ን
ይሄ ይሆን ቃልሽ....
አይኔ ካይንሽ ሌላ የሚያይ እንደሆ'ን
ግዴለም ነይልኝ ''ክደት ያከባብረ'ን''

mezin worku

@getem
@getem
@getem
👍1
እነርሱ!!!!

((እዮብ ሰብስቤ))

ሌባ ነበር አሉ!
ያጣ የገረጣ
የከሳ የነጣ
ቁራጭ ዳቦ ሰርቆ
አመት የተቀጣ፡፡
ዛሬ ግን ጀግና ነው
ሲሉ ያደንቁታል
ሀገር ሲመዘብር
መቼ ይነኩታል
ጭራሽ ይባስ ብለው
ድርሻዬን ይሉታል፡፡

@getem
@getem