ሀገር እና ግጥም
""""""""""""""""
እኔ ያለ ሀገሬ ቅኔ ብደረድር
በህብረ ቃል አስውቤ
ሰም ከወርቅ አድርጌ ፤ግጥሜን ብሰድር
ብቀምር......ባሳምር
የሚያምርብኝ በሀገር!
(ግና)
አንድ እግሬን ባነሳ
ልጥፋ ብል ከሀገሬ
የሰው ሀገር ብመኝ በተስፋ ሰክሬ
ቅኔዬም መከነ ጠፋ ቁም ነገሬ
ጦቢያዊ ነው 'ሚያውቀው
የሆድ ሆዴን ብሶት የቃላቴን ፍሬ።
አብርሃም
@getem
@getem
@gebriel_19
""""""""""""""""
እኔ ያለ ሀገሬ ቅኔ ብደረድር
በህብረ ቃል አስውቤ
ሰም ከወርቅ አድርጌ ፤ግጥሜን ብሰድር
ብቀምር......ባሳምር
የሚያምርብኝ በሀገር!
(ግና)
አንድ እግሬን ባነሳ
ልጥፋ ብል ከሀገሬ
የሰው ሀገር ብመኝ በተስፋ ሰክሬ
ቅኔዬም መከነ ጠፋ ቁም ነገሬ
ጦቢያዊ ነው 'ሚያውቀው
የሆድ ሆዴን ብሶት የቃላቴን ፍሬ።
አብርሃም
@getem
@getem
@gebriel_19
...የበስ ያጡ ነብሶች…
...ስምህን አላውቀው ስቃይህ ነው የጠራኝ
የሞት ሽረት ትግልህ ልቤን ሰብሮ ያስከፋኝ፤
ምስኪኑ ወንድሜ… እናስ ምን ልበልህ…
ያንተን ቦታ ይስጠኝ - እኔ ተስፋ ልጣ - ልንከራተትልህ፣
አየሩ ይጠረኝ - ምድርም ትካደኝ - ባህር ልውደቅልህ፡፡
---
ጋዝ ጋዝ ለሚል ኑሮ - ጨው ለሞላው ውሀ፣
የከበበው ፅልመት - የፈሳሽ በረሀ፣
ከጥልቁ ውቅያኖስ - ከማጣት ሸለቆ - ከሻርክ ሽርከታ፣
መድረሻ አልባዋ - ከርካሳዋ ጀልባ ፣
አጭቃ ያዘለች - የተስፋ ጭላጮች - የመለወጥ ዳባ፣
የብስ ያጡ ነብሶችን - ከኦና ላይ ጥላ፤
እሷም እንደኑሮ - ክዳቸው ስትሰምጥ - ወደስር ስትገባ
እንጀራ ፍለጋ - ቀሩ እንደወጡ - ለማይጨበጥ ተስፋ!
አበቦች ረገፉ - ልክ እንደገለባ ፥
...ምስኪን ወገኖቼን - ስደት አ’ረጋቸው የውሀ ሰለባ::
---
(ግጥሙ በቀይ ባህር ሰጥመው ህይወታቸውን ላጡ ከርታታ ወንድሞቼ በሙሉ ይሁን፤... የሐገሬ ሰው እባክህን ከዚህ የእርስ በርስ ሽኩቻና ፀብ ውጣ። ሩቅ ካለው የሐገርህ ዜጋ ጋር ከምትነቋቆር ከጎንህ ያለውን ወንድምህን እርዳ! ስሜታዊነታችንን እንተወውና ይህቺን ምስኪን ሐገር ከዚህ አንገት አስደፊ ድህነታችን እናውጣት!!)
-------(ገጣሚ ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)
@getem
@getem
@getem
...ስምህን አላውቀው ስቃይህ ነው የጠራኝ
የሞት ሽረት ትግልህ ልቤን ሰብሮ ያስከፋኝ፤
ምስኪኑ ወንድሜ… እናስ ምን ልበልህ…
ያንተን ቦታ ይስጠኝ - እኔ ተስፋ ልጣ - ልንከራተትልህ፣
አየሩ ይጠረኝ - ምድርም ትካደኝ - ባህር ልውደቅልህ፡፡
---
ጋዝ ጋዝ ለሚል ኑሮ - ጨው ለሞላው ውሀ፣
የከበበው ፅልመት - የፈሳሽ በረሀ፣
ከጥልቁ ውቅያኖስ - ከማጣት ሸለቆ - ከሻርክ ሽርከታ፣
መድረሻ አልባዋ - ከርካሳዋ ጀልባ ፣
አጭቃ ያዘለች - የተስፋ ጭላጮች - የመለወጥ ዳባ፣
የብስ ያጡ ነብሶችን - ከኦና ላይ ጥላ፤
እሷም እንደኑሮ - ክዳቸው ስትሰምጥ - ወደስር ስትገባ
እንጀራ ፍለጋ - ቀሩ እንደወጡ - ለማይጨበጥ ተስፋ!
አበቦች ረገፉ - ልክ እንደገለባ ፥
...ምስኪን ወገኖቼን - ስደት አ’ረጋቸው የውሀ ሰለባ::
---
(ግጥሙ በቀይ ባህር ሰጥመው ህይወታቸውን ላጡ ከርታታ ወንድሞቼ በሙሉ ይሁን፤... የሐገሬ ሰው እባክህን ከዚህ የእርስ በርስ ሽኩቻና ፀብ ውጣ። ሩቅ ካለው የሐገርህ ዜጋ ጋር ከምትነቋቆር ከጎንህ ያለውን ወንድምህን እርዳ! ስሜታዊነታችንን እንተወውና ይህቺን ምስኪን ሐገር ከዚህ አንገት አስደፊ ድህነታችን እናውጣት!!)
-------(ገጣሚ ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)
@getem
@getem
@getem
ለአንዳንድ ሰማዮች
((እዮብ ሰብስቤ))
ደመናማ ሰማይ!
ከንፋስ ተማክሮ እምቡጦች ሊያስደንስ፤
በውሀ መልክ ሲረጨው ሀብቱን ሲነሰንስ፤
ፅጌሬዳነትሽን ሊቀጥፍ ፈልጎ፤
በረዶውን ሲልክ፣ ውሽንፍሩን ሲልክ፣
አማላጅ አድርጎ፤
ቢራቢሮው እኔ!
ሰማዩ በቅናት!
ሲጠቁር ሲፈካ አሻቅቤ እያየሁ፤
ባበቦች ግዛት ላይ፣ እምነሸነሻለሁ፡፡
እስቅበታለሁ !
እ…..ስ……ቅ…..በ…..ታ…..ለ…..ሁ፡፡
በ…………..ቃአ!
እርሱ! በገፍ ይዞ
የኮከብን ውበት የጨረቃን ድምቀት
የፀሀይን ሙቀት በወጉ ካልረካ፤
ላጓጉል ነው እንጂ ቅስምን ለሚነካ፤
ምን ያደርግለታል ያበቦች መዓዛ፣ የእምቡጦቹ ቀለም፤
የሚያስጎመዥ ሁሉ የሚበላ አይደለም፡፡
ይልቅስ ንገሩት!
ተፈጥሮን አዛብቶ
ከቢራቢሮው ጋር ከንብ አይፋለም
በጨረቃ እቅፍ ነው የፈካው የእርሱ ዓለም፡፡
በወሰኑ ይንገስ በድንበሩ ይግዛ፤
ከፀሀይ ይጠጋ በኮከቦች ይውዛ፡፡
ከፍታውን ያስብ ለክብሩ ይጠንቀቅ፤
የራስን ያሳጣል የሌላውን መንጥቅ፤
ብላችሁ ንገሩት፡፡
አዎ ! ሂዱ ንገሩት፣ ጠፈር አምላኪዎች፤
ለረገፈ ገላ አበባ ላኪዎች፡፡
@getem
@getem
((እዮብ ሰብስቤ))
ደመናማ ሰማይ!
ከንፋስ ተማክሮ እምቡጦች ሊያስደንስ፤
በውሀ መልክ ሲረጨው ሀብቱን ሲነሰንስ፤
ፅጌሬዳነትሽን ሊቀጥፍ ፈልጎ፤
በረዶውን ሲልክ፣ ውሽንፍሩን ሲልክ፣
አማላጅ አድርጎ፤
ቢራቢሮው እኔ!
ሰማዩ በቅናት!
ሲጠቁር ሲፈካ አሻቅቤ እያየሁ፤
ባበቦች ግዛት ላይ፣ እምነሸነሻለሁ፡፡
እስቅበታለሁ !
እ…..ስ……ቅ…..በ…..ታ…..ለ…..ሁ፡፡
በ…………..ቃአ!
እርሱ! በገፍ ይዞ
የኮከብን ውበት የጨረቃን ድምቀት
የፀሀይን ሙቀት በወጉ ካልረካ፤
ላጓጉል ነው እንጂ ቅስምን ለሚነካ፤
ምን ያደርግለታል ያበቦች መዓዛ፣ የእምቡጦቹ ቀለም፤
የሚያስጎመዥ ሁሉ የሚበላ አይደለም፡፡
ይልቅስ ንገሩት!
ተፈጥሮን አዛብቶ
ከቢራቢሮው ጋር ከንብ አይፋለም
በጨረቃ እቅፍ ነው የፈካው የእርሱ ዓለም፡፡
በወሰኑ ይንገስ በድንበሩ ይግዛ፤
ከፀሀይ ይጠጋ በኮከቦች ይውዛ፡፡
ከፍታውን ያስብ ለክብሩ ይጠንቀቅ፤
የራስን ያሳጣል የሌላውን መንጥቅ፤
ብላችሁ ንገሩት፡፡
አዎ ! ሂዱ ንገሩት፣ ጠፈር አምላኪዎች፤
ለረገፈ ገላ አበባ ላኪዎች፡፡
@getem
@getem
እንደምነህ እግዜር?
(አሌክስ አብርሃም)
.
እንደምን ነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው ?
እኛማ .....
ለእልፍ አላፍ አለቃ
ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን
ፆለት ቤታችንን
እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ
ህግጋቱን አልፈን ደብዳቤ ላክንልህ፤
አይንህን ካየነው
ሁለት ሽ ዘመን
እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ
መቅረትህ ገዘፈ ...
እንደውም እንደውም ...
‹‹በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ሽ ዘመን
ቀጥሮን ከጠፋ
በቀጠሮው ሰአት
መምጣት ከተሳነው
እግዜር አበሻ ነው›› እያሉ ያሙሃል
እኔ ምን አውቃለሁ ...
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ
እግዚኦ በሉ ሲባል ...እንባየን የማፈስ
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ ...በሳቅ ልቤ እሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ ምን አውቃለሁ ...
ግን አንተ ደህና ነህ ?
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ !
ከሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው
አብረሃም ሰላም ነው ...
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው ?
እኛማ ይሄውልህ ...
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
‹‹ኤሎሄ›› እንላለን ጎጆ እንድጥልልን ....
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን
እንደጉድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን !!
አባታችን ሙሴ እነዴት ነው ለክብሩ
ውቂያኖስ መክፈያው ደህናናት ብትሩ ?
እኛማ ይሄውልህ ....
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ን ገ ር ል ን ና ብትሩን ያውሰን ....
እናልህ እግዜር ሆይ ....
ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን
...!
ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን ...
‹‹የመሄድ ዘመን ነው
ባህር የመሻገር
‹‹ዱላህን ላክልን›› ብሎሃል በልልኝ ...
ሰማይ ቤት እንዴት ነው ? ....ዳዊትስ ደህና ነው ?
ዛሬም ይዘምራል ...ዛሬም ይፎክራል ?
ሰላም ነው ጠጠሩ .... ሰላም ናት ወንጭፉ ?
እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ ?
እልፍ አላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ ?
ብሎሃል በልልኝ !!
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ
‹‹ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ››
ብለህ እዘዝልን !!
እንዴት ነህ ጌታ ሆይ ... ሰማይ ቤት እንዴት ነው ?
የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው ....
ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው ...
ያው እንደምታውቀው
አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው ...
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ ፀሃይ እያዘለ
የተሸመው ሁሉ ‹ፀሃይ ነኝ› እያለ
የአስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ
የአስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሃይ ሁኖ እንደመፈጠር ....
ኧረ እግዜር በናትህ ....
ኧረ እግዜር በናትህ ...በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና !
እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል ...
ጳውሎስ ሲሉን ...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ...ወይየ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን
ስማችንን ሸጠን ...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን
ተወው የኛን ነገር ...ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
ሂዋንስ ደህና ናት ?
ያው የልጅ ልጆቿ
በእግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ
ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም
ባይኑ ያገምጡታል
ሰይጣንም ደህና ነው
ኑሮ ተስማምቶታል
@getem
@getem
@getem
(አሌክስ አብርሃም)
.
እንደምን ነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው ?
እኛማ .....
ለእልፍ አላፍ አለቃ
ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን
ፆለት ቤታችንን
እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ
ህግጋቱን አልፈን ደብዳቤ ላክንልህ፤
አይንህን ካየነው
ሁለት ሽ ዘመን
እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ
መቅረትህ ገዘፈ ...
እንደውም እንደውም ...
‹‹በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ሽ ዘመን
ቀጥሮን ከጠፋ
በቀጠሮው ሰአት
መምጣት ከተሳነው
እግዜር አበሻ ነው›› እያሉ ያሙሃል
እኔ ምን አውቃለሁ ...
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ
እግዚኦ በሉ ሲባል ...እንባየን የማፈስ
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ ...በሳቅ ልቤ እሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ ምን አውቃለሁ ...
ግን አንተ ደህና ነህ ?
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ !
ከሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው
አብረሃም ሰላም ነው ...
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው ?
እኛማ ይሄውልህ ...
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
‹‹ኤሎሄ›› እንላለን ጎጆ እንድጥልልን ....
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን
እንደጉድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን !!
አባታችን ሙሴ እነዴት ነው ለክብሩ
ውቂያኖስ መክፈያው ደህናናት ብትሩ ?
እኛማ ይሄውልህ ....
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ን ገ ር ል ን ና ብትሩን ያውሰን ....
እናልህ እግዜር ሆይ ....
ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን
...!
ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን ...
‹‹የመሄድ ዘመን ነው
ባህር የመሻገር
‹‹ዱላህን ላክልን›› ብሎሃል በልልኝ ...
ሰማይ ቤት እንዴት ነው ? ....ዳዊትስ ደህና ነው ?
ዛሬም ይዘምራል ...ዛሬም ይፎክራል ?
ሰላም ነው ጠጠሩ .... ሰላም ናት ወንጭፉ ?
እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ ?
እልፍ አላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ ?
ብሎሃል በልልኝ !!
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ
‹‹ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ››
ብለህ እዘዝልን !!
እንዴት ነህ ጌታ ሆይ ... ሰማይ ቤት እንዴት ነው ?
የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው ....
ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው ...
ያው እንደምታውቀው
አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው ...
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ ፀሃይ እያዘለ
የተሸመው ሁሉ ‹ፀሃይ ነኝ› እያለ
የአስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ
የአስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሃይ ሁኖ እንደመፈጠር ....
ኧረ እግዜር በናትህ ....
ኧረ እግዜር በናትህ ...በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና !
እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል ...
ጳውሎስ ሲሉን ...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ...ወይየ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን
ስማችንን ሸጠን ...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን
ተወው የኛን ነገር ...ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
ሂዋንስ ደህና ናት ?
ያው የልጅ ልጆቿ
በእግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ
ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም
ባይኑ ያገምጡታል
ሰይጣንም ደህና ነው
ኑሮ ተስማምቶታል
@getem
@getem
@getem
👍1
////የባልእንጀሬ ወግ///
የተፈጥሮ ውበት እውነት ነው ክስተቱ
አብቦ እንዳፈራ ከስሞ መተኛቱ
ይህን እያወጋኝ ከጎኑ ወሽቆ
እራሴን አስናፈቀኝ ከራሱ ደብቆ
ብላ የምትለኝ አለች ባል እንጀሬ
ላለመስማት እክል በህመም ታስሬ
ብዙውን በቃሏ ታወጋኝ ነበረ
ፍቅር ከጥላቻ እርቅ እንደ ጀመረ
ለማለት ፈልጌ ምን ነበር ቃላቱ
ሰብከት መጀመርያው መውረጃ ድርጊቱ
ልልህ የፈለኩት ከሰመ ሀሳቡ
ለምንም ምላሽ ነው የመጥፊያው ሰበቡ
ባዶነት ሲገዝፍ የማንነት ልኩ
መጥፋቱ ካልቀረ የመሰከርከው ቃል
አበው እንደሚሉት ከልጅ ቃል ይበልጣል
ዕዳ ነው አይጠፋም ውስጥን ያናውጣል
በዚህ አንድ ሀሳቤን ለማለት ፈልጌ ምን ነበር ቃላቱ
ስብከት መጀመርያው መውረጃው ድርጊቱ
መሄጃ እንዳጣ እንዳመለኛ ወንዝ
ቤቴን እንደሞላህ የውሸትህን መዘዝ
እንደ ደራሽ ውሃ ባከላቴ ፈሰህ
እርግማን አልወድም መነሻ ያሳጣህ ...!!!!
ተከተበ
በ ሮዚ የያቡ
@getem
@getem
@gebriel_19
የተፈጥሮ ውበት እውነት ነው ክስተቱ
አብቦ እንዳፈራ ከስሞ መተኛቱ
ይህን እያወጋኝ ከጎኑ ወሽቆ
እራሴን አስናፈቀኝ ከራሱ ደብቆ
ብላ የምትለኝ አለች ባል እንጀሬ
ላለመስማት እክል በህመም ታስሬ
ብዙውን በቃሏ ታወጋኝ ነበረ
ፍቅር ከጥላቻ እርቅ እንደ ጀመረ
ለማለት ፈልጌ ምን ነበር ቃላቱ
ሰብከት መጀመርያው መውረጃ ድርጊቱ
ልልህ የፈለኩት ከሰመ ሀሳቡ
ለምንም ምላሽ ነው የመጥፊያው ሰበቡ
ባዶነት ሲገዝፍ የማንነት ልኩ
መጥፋቱ ካልቀረ የመሰከርከው ቃል
አበው እንደሚሉት ከልጅ ቃል ይበልጣል
ዕዳ ነው አይጠፋም ውስጥን ያናውጣል
በዚህ አንድ ሀሳቤን ለማለት ፈልጌ ምን ነበር ቃላቱ
ስብከት መጀመርያው መውረጃው ድርጊቱ
መሄጃ እንዳጣ እንዳመለኛ ወንዝ
ቤቴን እንደሞላህ የውሸትህን መዘዝ
እንደ ደራሽ ውሃ ባከላቴ ፈሰህ
እርግማን አልወድም መነሻ ያሳጣህ ...!!!!
ተከተበ
በ ሮዚ የያቡ
@getem
@getem
@gebriel_19
"አንድ ግጥም አንድ ወግ" በልዑል ሀይሌ እና አዱኛ አስራት
አይጠራጠሩ ይወዱታል!!
https://m.youtube.com/watch?v=uQeOUPsKI2k&itct=CBgQpDAYACITCJ343--S2uECFdHywQodEskBPlIk4Yqg4YqV4Yu1IOGMjeGMpeGInSDhiqDhipXhi7Ug4YuI4YyN&hl=en&gl=US&client=mv-google
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
አይጠራጠሩ ይወዱታል!!
https://m.youtube.com/watch?v=uQeOUPsKI2k&itct=CBgQpDAYACITCJ343--S2uECFdHywQodEskBPlIk4Yqg4YqV4Yu1IOGMjeGMpeGInSDhiqDhipXhi7Ug4YuI4YyN&hl=en&gl=US&client=mv-google
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ሂወትና ፎቶ
_
በዚህ ታዳጊ ልጅ ለ‘ይን በሚያሳሳ
ውብ ፈገግታው ሲረጭ አቅልን በሚያስረሳ
ታየችኝ ሂወቴ ሻሿን ተከናንባ
በተነሳው ፎቶ ከካሜራው ጀርባ
በልጁ በስተቀኝ አያለሁ ግድግዳ
አናጣቢ እንዳላይ የነብሴን መከዳ
ተላብሶ ቲሸርቱን ሸሚዙን ደርቦ
ታየኝ ማንነቴ በኩራት ተከቦ
በሱ ቤት መስሎታል እጁን ኪሱ ከቶ
ካፈር ወዳፈር ቤት መሆኑን ዘንገቶ
ከ‘ርሱ በላይ ጀግና ከቶ ኬት ተገኝቶ
ወይ በደንብ አልሳቀ ወይ አላለቀሰ
ወይ ሰላም አልሰጠኝ ወይም አልቦከሰ
ትምህረት ይሉት ነገር ተጥሎብኝ እዳ
እመረቅ ስል ሺቼ አያለሁኝ ፍዳ
ከጀርባው ባየኋት የጮራ ፈገግታ
እንስት አልማለሁ ጥላዋን ዘርግታ
ድንገት ቀን ሞልቶልኝ ዘወር ያልኩኝ ጊዜ
ስናጥጥ አያለሁ ሆናልኝ ምርኩዜ
ደጅ በተከማቸው በነጠላው ጫማ
አያለሁ ሞገሴን በላጤነት ደክማ
ሳር ድንጋይ ሰብስቦ ካላጠናከረ
በቻውን እንጨቱ ቤት መቼ ፈጠረ
ፀጉሩን ባልነቀሰው ካናቱ ላይ ዘልቃ
ተወርውራ መልዕክት አያሰማች ሲቃ
እንዲህ ትለኛለች,,,,,,,
አንተም ልክ እንደዚህ የንባብ ዉሃ አጥተህ
እንዳታድግ ነብስህ ታሳጥራታለህ
ምንም እንኳ ብታድግ ውስብስብ ብላ
ስላመሳቀልካት አያያትም ሌላ
እነም,,,,,,,
ይሄ ፎቶ ፎቶ ብቻ አይደለም
ከመልኩ ባሻገር ይታያል ሂወትም።
በሀሰን ኢድሪስ(የዘይነብ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
_
በዚህ ታዳጊ ልጅ ለ‘ይን በሚያሳሳ
ውብ ፈገግታው ሲረጭ አቅልን በሚያስረሳ
ታየችኝ ሂወቴ ሻሿን ተከናንባ
በተነሳው ፎቶ ከካሜራው ጀርባ
በልጁ በስተቀኝ አያለሁ ግድግዳ
አናጣቢ እንዳላይ የነብሴን መከዳ
ተላብሶ ቲሸርቱን ሸሚዙን ደርቦ
ታየኝ ማንነቴ በኩራት ተከቦ
በሱ ቤት መስሎታል እጁን ኪሱ ከቶ
ካፈር ወዳፈር ቤት መሆኑን ዘንገቶ
ከ‘ርሱ በላይ ጀግና ከቶ ኬት ተገኝቶ
ወይ በደንብ አልሳቀ ወይ አላለቀሰ
ወይ ሰላም አልሰጠኝ ወይም አልቦከሰ
ትምህረት ይሉት ነገር ተጥሎብኝ እዳ
እመረቅ ስል ሺቼ አያለሁኝ ፍዳ
ከጀርባው ባየኋት የጮራ ፈገግታ
እንስት አልማለሁ ጥላዋን ዘርግታ
ድንገት ቀን ሞልቶልኝ ዘወር ያልኩኝ ጊዜ
ስናጥጥ አያለሁ ሆናልኝ ምርኩዜ
ደጅ በተከማቸው በነጠላው ጫማ
አያለሁ ሞገሴን በላጤነት ደክማ
ሳር ድንጋይ ሰብስቦ ካላጠናከረ
በቻውን እንጨቱ ቤት መቼ ፈጠረ
ፀጉሩን ባልነቀሰው ካናቱ ላይ ዘልቃ
ተወርውራ መልዕክት አያሰማች ሲቃ
እንዲህ ትለኛለች,,,,,,,
አንተም ልክ እንደዚህ የንባብ ዉሃ አጥተህ
እንዳታድግ ነብስህ ታሳጥራታለህ
ምንም እንኳ ብታድግ ውስብስብ ብላ
ስላመሳቀልካት አያያትም ሌላ
እነም,,,,,,,
ይሄ ፎቶ ፎቶ ብቻ አይደለም
ከመልኩ ባሻገር ይታያል ሂወትም።
በሀሰን ኢድሪስ(የዘይነብ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
🏳️ “ጥቁሩ ብርሀን” 🏴
(በ👨🏾 መፅሀፈ)
የሰው ማንነቱ የውስጡ ትርታ፣
ደብቆት የሚኖር እማይገለጥ ላፍታ፤
በስጋው ከልሎት በምሽጉ መንደር፣
ብርሀንን ለብሶ በጭለማ ሚኖር::
መልካምነት ወስዶ ተቀብሎ አደራ፣
መታመኑን ሲያውቀ በደል የሚዘራ፤ እንዴት ያለች ውስጠት ሌሎች የማያውቀት፣
በግልፅነት ባህር ድብቀት ሚዘራባት፤
በመውደድ አንደበት ፍቅርን ሲሸነግል፣
ጦርነትን ገዝቶ ሰላም የሚደልል፤
አስቀድሞ ገሎ ላንተ ሟች ነኝ ይላል፣
ለሰጠከው መውደድ በቀል ያበቅላል፤
አይቻልም እንጂ ቢቻልስ ብችለው፣
የያንዳዱን ሰው ውስጣቸውን ባውቀው፣
እኔስ እርቅ ነበር ሰው ካልሆነው ሰው::
@getem
@getem
@getem
(በ👨🏾 መፅሀፈ)
የሰው ማንነቱ የውስጡ ትርታ፣
ደብቆት የሚኖር እማይገለጥ ላፍታ፤
በስጋው ከልሎት በምሽጉ መንደር፣
ብርሀንን ለብሶ በጭለማ ሚኖር::
መልካምነት ወስዶ ተቀብሎ አደራ፣
መታመኑን ሲያውቀ በደል የሚዘራ፤ እንዴት ያለች ውስጠት ሌሎች የማያውቀት፣
በግልፅነት ባህር ድብቀት ሚዘራባት፤
በመውደድ አንደበት ፍቅርን ሲሸነግል፣
ጦርነትን ገዝቶ ሰላም የሚደልል፤
አስቀድሞ ገሎ ላንተ ሟች ነኝ ይላል፣
ለሰጠከው መውደድ በቀል ያበቅላል፤
አይቻልም እንጂ ቢቻልስ ብችለው፣
የያንዳዱን ሰው ውስጣቸውን ባውቀው፣
እኔስ እርቅ ነበር ሰው ካልሆነው ሰው::
@getem
@getem
@getem
👍1
ትርጉም !
(በረከት በላይነህ)
..
"አስቀያሚ፣
አሰጠሊታ ፣
መልከ ጥፉ፤
እንደ ደሀ ቀዬ መስቦችህ የረገፉ!
የማትባል እዚህ ግባ ፣
የሰው ፍራሽ ፣ ማማር አልባ!
ፊተ መአት ፣ ያመድ ክምር!
የጭራቅ ሳቅ ያይጥ ፞ ድምር
ባትታይም የማታምር! !!"
እረ ! ሌላም፣ ሌላም፣
ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ ፤
አቤት ሀሴት ፣ አቤት ደስታ!
ለምን ብትይ?
መልኬ ከሸለመሽ የማይሽር ጥላቻ ፤
ደስታ አሰከረኝ 'ስላየሺኝ' ብቻ
@getem
@getem
@poemempire
(በረከት በላይነህ)
..
"አስቀያሚ፣
አሰጠሊታ ፣
መልከ ጥፉ፤
እንደ ደሀ ቀዬ መስቦችህ የረገፉ!
የማትባል እዚህ ግባ ፣
የሰው ፍራሽ ፣ ማማር አልባ!
ፊተ መአት ፣ ያመድ ክምር!
የጭራቅ ሳቅ ያይጥ ፞ ድምር
ባትታይም የማታምር! !!"
እረ ! ሌላም፣ ሌላም፣
ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ ፤
አቤት ሀሴት ፣ አቤት ደስታ!
ለምን ብትይ?
መልኬ ከሸለመሽ የማይሽር ጥላቻ ፤
ደስታ አሰከረኝ 'ስላየሺኝ' ብቻ
@getem
@getem
@poemempire
ከ፦አምባ፦ጔሮ
#ፀሀፈ_ብሩህ
በተለቀመ ጥጥ፣
በሸማኔ ድውር
የሰው እራቁቱ፣
ገላ እንደሚከለል
እኩይ ስብእና፣
የታጨቀ በነውር
የበግ ለምድ ለብሶ፣
ተሰው እንደሚኖር
ማየት ማመን ብለህ፣
አይንህን አትመን
እዪዪን አታብዛ፣
ፊትህ ለሚከወን
ባየኽው አትኮንን፣
አይንህን አስዳኝተህ
የውስጥህን ግለት፣
ማየቱ ተስኖህ
ከእሳቤህ በላይ፣
የሰው ልጅ አናት ላይ
ላንተ ተሰውሮ ፣
ለግዜሩ ከሚታይ
አምባጔሮ አለ፣
ከ–እንባ–እጔሮው ውስጥ
ሰላም የሚነሳ፣
ሰውሮ የከተመ
የማንነቶች ነውጥ።
@getem
@getem
@Birukam
#ፀሀፈ_ብሩህ
በተለቀመ ጥጥ፣
በሸማኔ ድውር
የሰው እራቁቱ፣
ገላ እንደሚከለል
እኩይ ስብእና፣
የታጨቀ በነውር
የበግ ለምድ ለብሶ፣
ተሰው እንደሚኖር
ማየት ማመን ብለህ፣
አይንህን አትመን
እዪዪን አታብዛ፣
ፊትህ ለሚከወን
ባየኽው አትኮንን፣
አይንህን አስዳኝተህ
የውስጥህን ግለት፣
ማየቱ ተስኖህ
ከእሳቤህ በላይ፣
የሰው ልጅ አናት ላይ
ላንተ ተሰውሮ ፣
ለግዜሩ ከሚታይ
አምባጔሮ አለ፣
ከ–እንባ–እጔሮው ውስጥ
ሰላም የሚነሳ፣
ሰውሮ የከተመ
የማንነቶች ነውጥ።
@getem
@getem
@Birukam
" ዝናብና መብራት "
( በአምባዬ ጌታነህ )
እየውልሽ ውዴ...
በዚህ በእኛ ሰፈር
የዝናብ ጓጓታ፣
የመብረቅ ብልጭታ፣
የተሰማ እንደሆን
መብራቱ ይጠፋል፣
እኔ አንቺን ላወራ ስልኬን ያነሳሁ ለት
ባትሪዬ ይዘጋል ።
ውዴ
የእኔና አንቺ ፍቅር
የበዜና ሰብለን ለምኔ ሚያስብለው፣
አለምን ሚያስቀናው፣
ከታይታኒክ በልጦ ሁሌ የሚወራው፣
አንቺ ስትደውይ እኔ ከፍራሼ ስልኬን ቻርጅ እንዳረኩ ሳወራሽ ብቻ ነው።
ታዲያ ይሄን አውቆ ያ ድንጋይ መብራት ሀይል፣ ከፈመ ፍቅራችን፣
መብራት እያጠፋ ውሀ ቸለሰብን።
እናም የኔ ቆንጆ.....
የዝናቡን መምጣት ሰበብ እያረገ፣
በፍቅራችን ጎጆ ጠብ እየመረገ፣
ሆም ብሎ እየገባ የሚፈተፍተው በእኔና አንቺ መሀል፣
የፍቅራችን መቀስ ከመብራት ሀይል ውጪ ሌላ ማንም አይደል።
እናም ከዚህ ኋላ አንቺ ወደ እኔ ስልክ ደውልሽ ከዘጋ፣
ብልሽ ተረጅልኝ መብራት የለም እሱ ጋ።
ወይም
መብራት ሀይል የሚሉት
በእኔ አንቺ መንገድ ስላለ እንቅፋት፣
ልታወሪኝ ካሰብሽ...
መብራቱን ቸክ አርጊ ከመደወልሽ ፊት።
@getem
@getem
@getem
( በአምባዬ ጌታነህ )
እየውልሽ ውዴ...
በዚህ በእኛ ሰፈር
የዝናብ ጓጓታ፣
የመብረቅ ብልጭታ፣
የተሰማ እንደሆን
መብራቱ ይጠፋል፣
እኔ አንቺን ላወራ ስልኬን ያነሳሁ ለት
ባትሪዬ ይዘጋል ።
ውዴ
የእኔና አንቺ ፍቅር
የበዜና ሰብለን ለምኔ ሚያስብለው፣
አለምን ሚያስቀናው፣
ከታይታኒክ በልጦ ሁሌ የሚወራው፣
አንቺ ስትደውይ እኔ ከፍራሼ ስልኬን ቻርጅ እንዳረኩ ሳወራሽ ብቻ ነው።
ታዲያ ይሄን አውቆ ያ ድንጋይ መብራት ሀይል፣ ከፈመ ፍቅራችን፣
መብራት እያጠፋ ውሀ ቸለሰብን።
እናም የኔ ቆንጆ.....
የዝናቡን መምጣት ሰበብ እያረገ፣
በፍቅራችን ጎጆ ጠብ እየመረገ፣
ሆም ብሎ እየገባ የሚፈተፍተው በእኔና አንቺ መሀል፣
የፍቅራችን መቀስ ከመብራት ሀይል ውጪ ሌላ ማንም አይደል።
እናም ከዚህ ኋላ አንቺ ወደ እኔ ስልክ ደውልሽ ከዘጋ፣
ብልሽ ተረጅልኝ መብራት የለም እሱ ጋ።
ወይም
መብራት ሀይል የሚሉት
በእኔ አንቺ መንገድ ስላለ እንቅፋት፣
ልታወሪኝ ካሰብሽ...
መብራቱን ቸክ አርጊ ከመደወልሽ ፊት።
@getem
@getem
@getem